🔴 ቻይና ግዙፍ የዳታ ማዕከላትን በባህር ወለል ስር ማሰማራት ጀመረች፤ ባህሩ እንደ ተፈጥሯዊ ማቀዝቀዣ ያገለግላል!
የቴክኖሎጂው ልዕለ-ኃያል ቻይና የዓለማችንን የዲጂታል መሠረተ-ልማት አወቃቀር ሙሉ በሙሉ ሊቀይር የሚችል እጅግ አስደናቂ የፈጠራ ስራ በተግባር ማከናወን መጀመሯ ይፋ ሆኗል። ሀገሪቱ እጅግ ግዙፍ የሆኑ የዳታ ማዕከላትን (Data Centers) በቀጥታ በውቅያኖስ ወለል ላይ የማስቀመጥ እና ለንግድ አገልግሎት የማዋል ስራን በተሳካ ሁኔታ ጀምራለች።
ይህ ታይቶ የማይታወቅ አዲስ አሰራር የዳታ ማዕከላቱ ሰርቨሮች መረጃዎችን በከፍተኛ ፍጥነት በሚያሰሉበት ጊዜ የሚፈጥሩትን እጅግ ኃይለኛ ሙቀት ለማስወገድ ቀዝቃዛውን የባህር ውሃ እንደ ተፈጥሯዊ ማቀዝቀዣ የሚጠቀም ነው። ይህም በየብስ ላይ እንደሚደረገው ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ማቀዝቀዣ ማሽኖችን (Chillers) የመጠቀም አስፈላጊነትን ሙሉ በሙሉ ያስቀራል።
ይህ የቴክኖሎጂ ስኬት ባህላዊ የዳታ ማዕከላት የሚጠይቁትን የኤሌክትሪክ ፍጆታ በ22.8 በመቶ የሚቀንስ ሲሆን፣ ለባህላዊ ማቀዝቀዣ የሚባክነውን በሚሊዮን የሚቆጠር ሊትር ንጹህ የውሃ ፍጆታን ሙሉ በሙሉ ያስቀራል። በተጨማሪም በየብስ ላይ ሊያዝ የሚችለውን ውድ የቦታ ስፋት በ90 በመቶ መታደግ ያስቻለ ሲሆን፣ ማዕከላቱ በቀጥታ በባህር ላይ ከተተከሉ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች ጋር የተገናኙ በመሆኑ ሙሉ በሙሉ በአረንጓዴ እና ታዳሽ ኃይል የሚሰሩ ናቸው።
@Addis_Reporter

❤23👍5🏆2👏1
የአዲስ አበባ ከተማ የቀድሞ ከንቲባ አምባሳደር ዓሊ አብዶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን በ27ኛ ከንቲባነት ከ1990 እስከ 1995 ዓ.ል. የመሩት አምባሳደር ዓሊ አብዶ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰማ።
አምባሳደር ዓሊ አብዶ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው፣ ዛሬ ሌሊት ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል። በአርሲ ድሬ ከተማ ከአባታቸው ከአቶ ዓሊ ሱለይማን እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አፀደ ወልደማሪያም የተወለዱት አምባሳደር ዓሊ፣ ከትዳር አጋራቸው ጋር በጋራ ያፈሯቸው ሁለት ሴት እና አንድ ወንድ ልጆች አሏቸው።
አምባሳደር ዓሊ አብዶ በቆዩባቸው የሥራ ዘመናት ሀገራቸውንና ሕዝባቸውን በቅንነት፣ በታማኝነትና በታታሪነት ሲያገለግሉ የነበሩ መሪ እንደነበሩ ተገልጿል።
የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸው በዛሬው ዕለት ከጁምዓ ሶላት በኋላ፣ በዳለቲ አካባቢ በሚገኘው የሙስሊሞች መቃብር ስፍራ፤ ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውና የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ይፈጸማል።
የኔቲዩብ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን እየተመኘ፤ አላህ (ሱ.ወ) ጀነተል ፊርዶስ ይወፍቃቸው ዘንድ ዱዓ ያደርጋል።

😢12❤11👏5🎉2💔2👍1🕊1
በነገው እለት የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን ኃይል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦
✅4:30 – 9:00
👉መስቀል ፋላዎር፣ ወንግላዊት፣ ወሎ ሰፈር ጀርባ፣ ጎርጎርዮስ፣ ጎተራ እና አካባቢው፣
✅ከጠዋቱ 2፡00 – 9፡30
👉ሰበታ ከተማ ፣ አለርት ሆስፒታል፣ ቻይና ቱቦ አካባቢ፣ ኢንዱስቲሪ መንደር እና አካባቢያቸው፣
✅ከጠዋቱ 12፡00 – 7፡00
👉መቀለ ከተማ 03፣ አይደር ሪፌራል ሆስፒታል፣ አድሽምን፣ አዲሃ አክረም እና ደኤሮ አካባቢ፣
✅ከጠዋቱ 2፡00 – 12፡00
👉መቀለ ከተማ 05፣ ኮንዶሚኒየም ሰፈር፣ ግብርና ብሮና ማይዱባ እና አካባቢያቸው፣
✅ከጠዋቱ 2፡00 – 10፡00
👉አዳማ ፖስታ ቤት፣ አዳማ ሆስፒታል፣ ፍራንኮ፣ ፒኮክ፣ 105 አካባቢ፣ አኪሊስያ ሆስፕታል እና አካባቢያቸው፣
✅ከጠዋቱ 2፡00 – 6፡30
👉በወልድያ መቻሬ፣ አዳጎ፣ አሸዋ ሜዳ፣ አመያመጫ፣ ሁርጌሳ፣ ኡድመን፣ ልብሶ፣ ጊረና፣ መሀለምብ እና አካባቢያቸው፣
✅ከጠዋቱ 12፡00 - 11፡00
👉የአዳሚ ቱሉ ገንዳ አርባ 132 ኪ.ቮ አግሮ ኢንዱትሪ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ለመዘርጋት በታወር ቁጥር 11 እና በታወር ቁጥር 12 መካከል በሚገኙ ኩርማ 33 ኪ.ቮ ኢንዱስትሪ ፓርክ 33 ኪ.ቮ እና ቡልቡላ 15 ኪ.ቮ የኤሌክትሪክ መስመሮች ይቋረጣሉ፡፡
ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ የተከበራችሁ ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን እንጠይቃለን፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

❤12👍7
ኦብነግ ከፋኖ ጋር መነጋገሩን ይፋ አደረገ
ከአንድ ወር በፊት በአስመራ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የተገናኙት የኦብነግ አንጃ መሪ የሆኑት አብዱራህማን መህዲ ከኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ንግግር እያደረጉ መሆናቸውን አሳውቀዋል፡፡ አፍሪካን ኢንተለጀንስ ትናንት ባወጣው ዘገባ፣ ከሰላማዊ ትግል ራሱን ያገለለው የኦብነግ አንጃ ከኢትዮጵያ ተቃዋሚ እና አማጺ ኃይሎች ጋር ጥምረት እንዲፈጥሩ ከግብጽ እና ኤርትራ መንግስታት ጫና እየተደረገባቸው መሆኑን ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች በጋራ እየተሰባሰቡ መሆኑን የጠቀሰው ዘገባው፤ ከሚሰባሰቡት ኃይሎች መካከል ኦብነግ አንዱ ነው ብሏል፡፡ እንደ ፋኖ፣ ህውሃት እና ኦነግ ሸኔ ካሉ ሀይሎች ጋር ጥምረት መፍጠራቸውን በአፍሪካ ኢንተለጀንስ የተጠየቁት የቡድኑ መሪ አብዱራህማን መህዲ፤ ‹‹ጥምረት የመፍጠር ደረጃ ላይ ባንደርስም፤ ከፋኖም ሆነ ሌሎች ሀይሎች ጋር ተነጋግረናል፤ ለመስራትም ዝግጁ ነን፤ ነገር ግን ውይጥቱ የመጨረሻ ደረጃ ላይ አልደረሰም›› በማለት መልሰዋል፡፡
አፍሪካን ኢንተለጀንስ እንደዘገባው፣ የኦብነግ አንጃ ከሌሎች ሀይሎች ጋር ትብብር እንዲፈጥር፣ በሱዳን፣ ኤርትራ እና ግብጽ መንግስታት ጫና እየተደረገበት ሲሆን፤ በቅርቡም በአስመራ እና በፖርት ሱዳን ስብሰባዎችን ማደረረጋቸውን ጠቅሷል፡፡via:- andafta

❤27🤔11👍5🏆3🤯1
የባንኩ መግለጫ‼️
በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ደንበኞች የባንክ ሒሳብን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ማጣመርን በተመለከተ ከንግድ ባንክ የተሰጠ መግለጫ‼️
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሠረት በዋና ዋና ከተሞች በሚገኙ የባንካችን ቅርንጫፎች የተከፈቱ የባንክ ሒሳቦች ባለቤቶች የሆኑ እና እስከ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ሳያጣምሩ የቀሩ ደንበኞች በቀጣይ እስኪያጣምሩ ሒሳባቸው በጊዜያዊነት እንዳይንቀሳቀስ መደረጉ ይታወቃል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መኖሪያቸውን ከኢትዮጵያ ውጭ ያደረጉ ደንበኞች የባንክ ሒሳባቸውን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ማጣመር ሳያስፈልጋቸው በጊዜያዊነት በልዩ ሁኔታ መስተናገድ የሚችሉበትን አሠራር ዘርግቷል።
በዚህ መሠረት ከዚህ በፊት ሒሳብ በሚከፍቱበት ወቅት የመኖሪያ አድራሻቸው ከኢትዮጵያ ውጭ እንደሆነ በባንካችን የመረጃ ቋት የተመዘገበ ማስረጃ ያቀረቡ ደንበኞች ሒሳብ ያልታገደ መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታውቋል።
በተለያየ ምክንያት ውጭ ሀገር እንደሚኖሩ በባንኩ የመረጃ ቋት ላይ ያላስመዘገቡ እና የባንክ ሒሳባቸው የታገደባቸው ደንበኞች ከዚህ በታች በተገለፀው አግባብ መስተናገድ የሚችሉ መሆኑን ገልጿል፦
1. ከኢትዮጵያ ውጭ መኖራቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ለምሳሌ - የትምህርት ማስረጃ፣ የሕክምና ማስረጃ፣ የውጭ ሀገር መንጃ ፈቃድ፣ ከውጭ ሀገር የተሰጠ ውክልና፣ የመኖሪያ ፈቃድ (የሎው ካርድ)፣ የሥራ ፈቃድ ወይም ሀገር ውስጥ እያሉ የተሰጠ ውክልና ሆኖ ነገር ግን ውክልናው ላይ ውጭ ሀገር መኖራቸውን የሚገልጽ ሐሳብ ካለ በሕጋዊ መኪሎቻቸው አማካኝነት በማቅረብ እግዱን ማስለቀቅ ይችላሉ፤
2. ዲፕሎማቶች የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ መታወቂያቸውን በማሳየት ወይም ሒሳቡ የተከፈተው በዲፕሎማት መታወቂያ ከሆነ እግዱ ተነስቶላቸው ሒሳባቸውን ማንቀሳቀስ ይችላሉ፤
3. ደንበኛው በውጭ ሀገር እንደሚኖር የሚያረጋግጥ የኢሜይል መልእክት በኢምባሲ/ቆንስላ በኩል ከመጣ እግዱ በጊዜያዊነት ተነስቶላቸው መሰተናገድ ይችላሉ፤
4. በተጨማሪም ደንበኞች በውጭ ሀገር መኖራቸውን ሊያስረዱ የሚችሉ ማስረጃዎችን በቀጥታ የባንክ ሒሳቡ በተከፈተበት ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ የኢ-ሜል አድራሻ ወይም በዲያስፖራ ባንኪንግ ክፍል የኢ-ሜል አድራሻ DiasporaBanking@cbe.com.et በመላክ እግዱን በጊዜያዊነት ማስነሳት ይችላሉ ብሏል።

❤12😢3👍2
⁉️ የምስራቁ ጦርነት የኑሮአችንን ዋጋ እንዴት እያናጋው ነው? 💥
🚨የኃያላን መንግስታት ፍጥጫ እና የድንበር ጦርነቶች ከሩቅ የሚታዩ የዜና አርዕስቶች ብቻ አይደሉም፤ የኢትዮጵያን ገበያ እና የኪሳችንን አቅም በቀጥታ የሚፈትኑ ማዕበሎች እንጂ።
የሀገር ውስጥ ወቅታዊ ፈተናዎችን እና አጠቃላይ የአህጉራችንን እና የዓለምን ዜናዎች አቀናጅቶ የሚያቀርብላችሁን ስፑትኒክን አሁኑኑ ይከተሉ 👇
🔗 https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy
📣 @sputnik_ethiopia

👍5❤2
"አዝኛለው" ጠቅላይ ሚኒስትሩ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአርሲው የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞችና ቤተ እምነት ጥቃት፣ "ጥልቅ ኅዘን" እንደተሰማቸው በጽ/ቤታቸው በኩል ባወጡት መገለጫ አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ምርጫ እና ልማት ላይ ባደረገው መግለጫው፣ የአርሲውን ሃይማኖታዊ ጥቃት ከታጣቂዎች እና ከውጭ ኃይሎች ጋር አያይዞታል።
የጥቃቱ ፈጻሚ ኦነግ-ሸኔ መሆኑን የገለጸ መግለጫው፤ በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሱ አማጺያን እና ለኢትዮጵያ ጥላቻ አላቸው ከተባሉ የውጭ ኃይሎች ጋር በቅንጅት የተፈጸመ ነውም ብሏል።
በአርሲው ጥቃት የተወነጀሉት የውስጥና የውጭ ኃይሎች፣ 'ጽምዶ' የተሸኘ ቅንጅት እንደፈጠረበትም መንግሥት ገልጿል።
በዚሁ ቅንጅት ባለፈው ሰኞ'ለት የተካሄደውን 7ኛ ዙር ጠቅላላ ምርጫ ለማኮላሸት መከራ የተደረገ ቢሆንም፣ የደህነንት ኃይሉ አምክኖታልም ብሏል።
የመግለጫውን ሙሉ ይዘት ከላይ ተያይዟል

🤪52😡17❤16🤔6🥱3🙉3👍2😁2🕊1
የጦርነቱ አድማስ ይሰፋል-ኢራን‼️
የኢራን ጠቅላይ መሪ ከፍተኛ ወታደራዊ አማካሪ ለ CNN፡-
'ጦርነቱ ከቀጠለ እና አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችውን የባህር ላይ እገዳ ካልተነሳ ጦርነቱን ወደ ህንድ ውቅያኖስ ፣ቀይባህር (ባብ አል ማንዳብ ሰርጥ) እና ሜዲትራኒያን ባህር እናስፋፋለን። እስካሁን ጥቃት ስንፈጽምባቸው ከነበሩት የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች በተጨማሪ ሌሎች ቀጠናዎች ላይ በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ቤዞች ላይ ጥቃት በመፈፀም ለጦርነቱ ሌላ ገጽታ እንሰጣለን'ብለዋል።

👍22❤8👀2👏1🕊1🤣1
መረጃ‼️
ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች – ኢትዮጵያ፣ የትግራይ ጸጥታ ኃይሎች በክልሉ መጠነ ሠፊ "አፈሳ" እና "የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ" እየተካሄደ መኾኑን በምርመራ ማረጋገጡን ገለጠ።
ድርጊቶቹ ከሚፈጸሙቧቸው አካባቢዎች መካከል፣ ሰሜን ምስራቅ ዞን፣ ማዕከላዊ ዞንና ምሥራቃዊ ዞን እንደሚገኙበት ተቋሙ ጠቅሷል።
ኾኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከመቀሌና ሌሎይ ጥቂት አካባቢዎች በስተቀር አፈሳው በመላዋ ትግራይ መስፋፋቱን ተቋሙ አስታውቋል።
አፈሳው ባብዛኛው ዒላማ ያደረገው የቀድሞ ተዋጊዎችንና ወጣቶችን እንደኾነ መረዳቱን የጠቀሠው ተቋሙ፣ በጦርነቱ ተዋጊ ያላዋጡ ቤተሰቦች አንድ ምልምል እንዲያዋጡ እየተገደዱ ይገኛሉ ብሏል።
ተቋሙ የትግራይ ባለሥልጣናት አፈሳውን ባስቸኳይ እንዲያስቆሙ፣ በጊዜያዊ ማቆያ የያዟቸውን ግለሰቦች እንዲለቁና ጊዜያዊ መጠለያዎችን ለሰብዓዊ መብት ተቋማት ክፍት እንዲያደርጉ የጠየቀ ሲኾን፣ አፍሪካ ኅብረት፣ አውሮፓ ኅብረትና አሜሪካም አፈሳው እንዲቆም ግፊት እንዲፈጥሩ ጥሪ አድርጓል።

❤13👍7💊6👏1😁1👀1
ኤርትራ የንጹህ መጠጥ ውሃ እጥረት ገጠማት።
የውሃ ማጓጓዣ ታንከሮች ስራ ማቆማቸው ለዋሃ እጥረት መከሰት ምክንያት ሆኗል።
የአሜሪካ እና የኢራን ጦርነት ባስከተለው የሀይል እጥረት ኤርትራ ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩ ተገልጿል።
በዚሁ የሀይል እጥረት ሳቢያ ነዳጅ የሚጠቀሙ የውሃ ታንከሮች ስራ አቁመዋል ተብሏል።
የመጠጥ፣ የንፅህና እና ሌሎች አገልግሎት የሚውል በቂ የውሃ አቅርቦት አለመኖሩ ተመልክቷል። የውሃ እጥረት በከተማ እና በገጠር ዋነኛ ችግር ሆኗል ተብሏል። #awate

😢10❤9🎉4👍3🙏2🕊1💔1🙊1
#ሰበር❗የድሮን ጥቃት ተፈፀመ‼️
ከኤርትራ ድንበር ስድስት ኪሎሜትር ርቀት በምትገኘው #ገምሃሎ (ሽራሮ አካባቢ) ዛሬ አዳሩን ከለሊቱ 6:30 ጀምሮ የድሮን ጥቃት መፈፀሙን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ አረጋግጠዋል።
የድሮን ጥቃት ከተፈፀመ በኋላ ለረጅም ግዜ ፍንዳታ እና ቃጠሎ ተፈጥሮ እንደነበር ገልፀውልናል። በገምሃሎ አካባቢ የህወሓት አርሚ 13 በስፋት የሚንቀሳቀስበት ቀጠና ሲሆን ጥቃቱ የተፈፀመው ግን በጦር መሳሪያ መጋዘን ላይ ሳይሆን እንዳልቀረ ጠቁመዋል።
ድሮኗ ወደ

አዲሀገራይ፣አዲነብሪድ እና አዲ ዳዕሮ አሰሳ በማድረግ ላይ መሆኑን ገልፀዋል።(አዩ)@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍23❤8😡8😢3👏2🤯1👀1🤪1
Update❗የፖሊስ አዛዡ ተይዟል‼️
በአርሲ አሰኮ ወረዳ በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ አሳዛኝ ጭፍጨፋ መፈፀሙን ተከትሎ ከጥቃቱ ጀርባ የተጠረጠሩት የወረዳው ፖሊስ አዛዥ አቶ አባቡ አብደላ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን የሰላምና ፀጥታ ሀላፊው ደግሞ ለግዜው ተሰውረዋል፣ ያሉበት አልታወቀም። አነዚህ አመራሮች ከጥቃቱ ቀደም ብሎ ከመንግሥት የመጣ ጥይት በ118 ብር ግዙ በሚል ከገበሬው ብር በመሰብሰብ ጥይቱን ለገበሬው ሳይሰጡ ብሩን በመዝረፍ ዋነኛ ተዋናይ እንደሆኑ ትናንት መዘገባችን ይታወሳል።(ayu)

❤28🥱11👍4😢4🤔2🌚2👏1😁1💯1
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና በአርሲ ዞን በተፈጸሙ ጥቃቶች የሰው ህይወት ጠፋ
በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ምርጫውን ለማደናቀፍና በህዝቡ ላይ ሽብር ለመፍጠር የታለሙ ጥቃቶች መፈጸማቸውን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች የስፖርት ውድድር (Champions League) በመመልከት ላይ እያሉ በተሰነዘረ ጥቃት አንድ ተማሪ ሲሞት 26 የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በተመሳሳይ ሁኔታ በአርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ "ሸኔ" ተብሎ በሚጠራው ቡድን በተሰነዘረ ጥቃት አምስት የሚሊሻ አባላት፣ ሶስት የፖሊስ አባላት እና አራት ሲቪሎች መገደላቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በጥቃቱ አንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፣ የመንግስት ጤና ጣቢያ እና የቀበሌ ጽህፈት ቤት መቃጠላቸው እንዲሁም 65 የግለሰብ ቤቶች መውደማቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም በሸርካ እና በእንቆሌ ዋቤ ወረዳዎች ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውና ታግተው የነበሩ ግለሰቦች ህይወት ማለፉ በመግለጫው ተጠቅሷል።

😡21❤18🤪4👍2
“ኢትዮጽያ ደሀ ሀገር ነች” ኤለን መስክ!
ኤለን መስክ ስለ ኢትዮጵያ ያጋራው ነገር በዚህ ሰአት ላይ በጣም መነጋገሪያ ሆኗል። 1 ፖስት ላይ ሼር ያደረገው ኤለን መስክ ኢትዮጵያም ድሃ ሀገር ነች። ኮሎናይዜሽን ሀገራትን ድሃ የሚያደርግ ቢሆን ኢትዮጵያ ሀብታም መሆን ነበረባት፤ ነገር ግን በጣም ድሃ ሀገር ነች። እንደዚሁም ደግሞ ቬትናም በፈረንሳይ ተገዝታለች፤ ነገር ግን አሁን ላይ ሀብታም ሀገር ነች። ስለዚህ ኮሎናይዜሽን ሀገራትን ድሃም ሀብታምም አያደርግም። እንደዚህ አይነት ነንሴንስ ነገር መቆም አለበት የሚለውን ፖስት ያጋራው ኤለን መስክ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ መነጋገሪያ ሆኗል።

👍45💯20❤10😱7😢3👏1🤯1👌1🙊1
የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ የሁሉንም አሽከርካሪዎች ብቃት ዳግም ለመመዘን እየተሰናዳሁ ነው ብሏል፡፡
ይህም ሀሳብ በብዙዎች ጥያቄ እንዲነሳ አድርጓል፡፡
ለረጅም ዓመታት በአሽከርካሪነት ያሳለፉ የከባድ መኪና ሾፌሮች ከዚህ ሁሉ ዘመን በኋላ ዳግም ለፈተና የምንቀመጠው እንዴት ነው የሚል ጥያቄን ያነሳሉ፡፡
ከዓመታት የማሽከርከር ልምድ በኋላ እንደ አዲስ ብቃትን ለመመዘን ስራ የሚሰራውስ ምን ውጤትን ለማምጣት ነው ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡

❤11🤣8👍3🙉2😢1🤪1😡1
የማስታወቂያ ግብዣ
የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል‼
✔Youtube ቻናል …
✔የትምህርት ተቋማት…...
✔የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
✔የትራንስፖርት አገልግሎት…....
✔ኤጀንሲዎች……
✔ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
✔ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot

❤3👍3