አዲስ ሪፖርተር - NEWS
35.8K subscribers
16.9K photos
412 videos
21 files
3K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት በማስመልከት መልእክት አስተላለፉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በአርሲ ሀገረ ስብከት በቤተ ክርስቲያን እና በኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ ::

"በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሽርካ፣ በሆንቆሎ፣ በዋቤ እና በሙኔሳ ወረዳዎች በመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ስለደረሰው አሰቃቂ ጥቃት የሰማነው በተሰበረ ልብ ነው።

ይህ መከራ እያበቃ ሳይሆን እየሰፋ በመምጣቱ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅና ሰላምን የማስፈን አደራ የተጣለባችሁ የጸጥታ አካላትና በየመዋቅሩ ያላችሁ ሓላፊዎች ከምንም በላይ ታሪክ የሚጠይቃችሁ በሥልጣን ዘመናችሁ ለዜጎች ደኅንነት በምትከፍሉት ዋጋ ነውና ይህንን የጥቃት ሰንሰለት በማስቆምና ወንጀለኞችን ለሕግ በማቅረብ ከታሪክ ባለዕዳነት ትድኑ ዘንድ በቤተ ክርስቲያናችን ስም አበክረን እናሳስባለን።

በየአካባቢው የምትገኙ ምእመናንና መላው ኢትዮጵያውያንም በወንድማማችነት መንፈስ ተጋግዛችሁ፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍና በጸሎት ከቤተክርስቲያናችን ጎን እንድትሆኑ ጥሪያችንን::"

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
37🙏10👍3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢራን የኩዌት አየር መንገድን በዚ መልኩ ነው ያወደመችው በዚህ ጥቃት 63 ሰዎች ቀላል እና ከባድ ጉዳት የደርሰባቸው ሲሆን የሞቾች ቁጥርም ከአንድ ሊበልጥ እንደሚችል እየተናገሩ ይገኛል"

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16💔7🤯3👍2👏1😢1
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት


ነገ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን ኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች ፦

ከጠዋቱ 2:00-12:00

👉 በአዳማ ሪጅን አዳማ ቆርቆሮ፣
ከጠዋቱ 2:00-11:00
አዳማ ፈትል ፋብሪካ፣ ሬድሬስ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ፣ አህዋን ፋብሪካ

ከጠዋቱ 2:30-9:00

👉 በአዳማ ሪጅን ከአዋሽ መልካሳ ወደ አዱላላና አሮሪቲ፣

  ከጠዋቱ 2:30-7:00

👉 በሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን አስኮ ገብርኤል፣ ሳንሱሲ፣ እያሱ ምንጭ፣ ብርጭቆ ኮንዶሚኒየም፣ ከታ አፍያ ዴቄት፣

ከጠዋቱ 3:00 እስከ ምሽቱ 4:00 ድረስ

👉 በደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ኬኬ ብርድ ልብስ ፋብሪካ፣ ቂሊንጦ ኮንዶሚኒየም፣ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት፣ አስቱ ዩኒቨርስቲ እና ኢንዱስትሪ መንደር፣ ዋልያ ቢራ

ከጠዋቱ 6:00-9:00

👉 በምዕረብ አደስ አበባ ሪጅን ስልጤ ሰፈር፣ አጃምባ ኮንዶሚኒየም

ከቀኑ 7፡00- 11፡00

👉 በሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ሸጎሌ አንበሳ ጋራዥ፣ ሸጎሌ መንደር-7፣ ፊናንስ፣ አበበ ቢቂላ፣ ኳስ ሜዳ፣ መሳለሚያ

ከቀኑ 7:30-10:30

👉 በሽረ ረጅን እደጋ አርቢ፣ ማይ ቐንታል


ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻች የጥገና ሥራው ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትእግስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍1192
በ130 ምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች መዝገብ ላይ ያልተገኙ እና ካርድ ያልያዙ መራጮች እንዲመርጡ መደረጋቸውን ኅብረት ለምርጫ ገለጸ

የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ (CECOE / ኅብረት ለምርጫ) ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የተከናወነውን 7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ አስመልክቶ ዛሬ ረቡዕ ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ የትዝብት ሪፖርቱ፣ በ130 ምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች መዝገብ ላይ ያልተገኙ እና ካርድ ያልያዙ፣ በእያንዳንዱ ጣቢያ ከአንድ እስከ 10 የሚሆኑ መራጮች እንዲመርጡ መደረጋቸውን ገለጸ።

እንዲሁም በስምንት የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ደግሞ ከ10 በላይ ሰዎች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ ሳይገኝ እና የመራጭነት ካርድ ሳይዙ እንዲመርጡ መፈቀዱንም ኅብረቱ በምርጫ ትዝብት ጊዜያዊ ሪፖርቱ ላይ አስታውቋል።

ኅብረቱ ከታዘባቸው 2,506 የምርጫ ጣቢያዎች መካከል በ2,458 ጣቢያዎች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ ሰፍሮ ድምጽ መስጠት የተከለከለ ሰው እንዳልነበር መታዘቡን ጠቅሷል፤ ይሁንና በ46 የድምጽ መስጫ  ጣቢያዎች  ከ1 እስከ 10 ግለሰቦች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ ሰፍሮ ድምጽ መስጠት መከልከላቸው ተገልጿል።

በሁለት ድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ደግሞ ከ10 በላይ ሰዎች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ ሰፍሮ ድምጽ መስጠት መከልከላቸውን የኅብረቱ ሰብሳቢ ተናግረዋል።

Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16😁11👍5
ይህንን ያውቃሉ
የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ በወረዳ ጽሕፈት ቤቶቹ የሚሰጣቸውን የኩነት (የልደት፣ ጋብቻ፣ ፍቺ፣ ሞትና ጉዲፈቻ) ማስረጃዎችን የማረጋገጥ አገልግሎት ለማግኘት ተገልጋዮች ይዘው መቅረብ የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችንና ደጋፊ ሰነዶችን እንደሚከተለው ያሳውቃል።
ለእያንዳንዱ አገልግሎት የሚያስፈልጉ ልዩ ቅድመ ሁኔታዎች
1. የልደት ሰርተፍኬት ለማረጋገጥ
ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ፦ በወረዳ ደረጃ የተመዘገበ የልደት ማስረጃ
 አገልግሎቱ የሚሰጠው ከሁለቱ አንዱ ወላጅ በአካል ሲገኝ ነው (የወላጆች የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ያስፈልጋል)።
 ምዝገባው በሞግዚትነት ከሆነ የፍርድ ቤት የሞግዚትነት ውሳኔ ሰነድ መቅረብ አለበት።
ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ፦ ባለጉዳዩ በአካል መቅረብ አለበት። በአካል መቅረብ ካልቻለ፣ ጉዳዩን የሚገልጽ ልዩ ውክልና ከወካይና ተወካይ የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
2.  የጋብቻ ማስረጃ ለማረጋገጥ
 በክፍለ ከተማ ወይም በወረዳ ደረጃ የተመዘገበ የጋብቻ ማስረጃ መያዝ።
 ለግልባጭ ወይም ለእርማት አገልግሎት፦ የተጋቢዎች ሁለት ሁለት (2) ጉርድ ፎቶግራፍ።
 በውክልና የሚጠየቅ ከሆነ (ለእርማት፣ ዕድሳትና ግልባጭ)፦ ባልና ሚስት ጉዳዩን በግልጽ የሚያሳይ ውክልና፣ የወካዮች እና የተወካይ የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት ወይም የታደሰ የመኖሪያ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።
3.  የፍቺ ማስረጃ ለማረጋገጥ
 በክፍለ ከተማ ወይም በወረዳ ደረጃ የተመዘገበ የፍቺ ማስረጃ
 የህግ አስገዳጅነቱ የተረጋገጠ የፍርድ ቤት የፍቺ ውሳኔ ሰነድ መቅረብ አለበት።
4.  የጉዲፈቻ ሰርተፍኬት ለማረጋገጥ
 በወረዳ የተመዘገበ የጉዲፈቻ ሰርተፍኬት እና የፍርድ ቤት ውሳኔ ሰነድ
 ጉዲፈቻ አድራጊዎች የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት በመያዝ በአካል መቅረብ አለባቸው።
 ጉዳዩ በውክልና ከሆነ፣ይህንኑ የሚያስረዳ ልዩ ውክልና መቅረብ አለበት።

5.  የሞት ማስረጃ ለማረጋገጥ
በወረዳ ደረጃ የተመዘገበ የሞት ማስረጃ የማረጋገጥ አገልግሎት ለማግኘት
 ከሟች ጋር አብሮ ይኖር የነበረ ሰው፣ እርሱ ከሌለ የሟች የስጋ ወይም የጋብቻ ዘመዶች፣ እነዚህም ከሌሉ የቅርብ ጎረቤት ወይም ስለሟቹ መሞት የሚያውቅ ማንኛውም ሰው የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት በማቅረብ ማስመዝገብና ማረጋገጥ ይችላል።
 ሟች የውጭ ሀገር ዜጋ ከሆነ ከሆስፒታል የተሰጠ የማሳወቂያ ወረቀት መቅረብ አለበት።
ማሳሰቢያ፡- ለሁሉም ከላይ ለተዘረዘሩት የኩነት አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስፈልግ ደጋፊ ሰነድ
• የታደሰ ብሔራዊ መታወቂያ / የታደሰ ፓስፖርት / የትውልደ ኢትዮጵያ የውጭ ዜግነት መታወቂያ (የቢጫ ካርድ)።
• ከዝቅተኛው አስተዳደር ጽ/ቤት መደበኛ ነዋሪነቱን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ / የስደተኛነት ማስረጃ / የመኖሪያ ፈቃድ።
• ከሚሰራበት መስሪያ ቤት ባልደረባነቱንና ዜግነቱን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ከመስሪያ ቤቱ መታወቂያ ጋር / የመከላከያ ሰራዊት ከሆነ የመከላከያ ሰራዊት መታወቂያ መያዝ
• የጠፋ ሰርተፍኬት ግልባጭ ለመውሰድ፦ ከፖሊስ የተሰጠ የጠፋ ሰነድ ማረጋገጫ ማቅረብ ግዴታ ነው።
• ከወረዳ የመጡ ማስረጃዎች፦ ከወረዳው ስለመውጣታቸው የሚገልጽ ማረጋገጫ ደብዳቤ ያስፈልጋቸዋል።
• ከክፍለ ከተማ የመጡ ማስረጃዎች፦ ከሰነዱ በስተጀርባ የማረጋገጫ ማህተም ማረፍ ይኖርበታል።
• ከውጭ ሀገር የሚመጣ ውክልና፦ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በፌደራል ሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ መረጋገጥ አለበት።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍5
ኢትዮጵያና አይ ኤም ኤፍ (አይኤምኤፍ) የ468 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ላይ ደረሱ

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በተራዘመው የብድር አቅርቦት ፕሮግራም አምስተኛ ግምገማ ላይ በባለሙያዎች ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል።

ይህ ስምምነት በሚቀጥሉት ሳምንታት በድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሙሉ በሙሉ ሲጸድቅ፣ ኢትዮጵያ የ468 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ተጨማሪ የፋይናንስ ድጋፍ እንድታገኝ ያደርጋታል።

ይህም ሀገሪቱ በ4 ዓመታት ውስጥ ከምታገኘው የ3.4 ቢሊዮን ዶላር አጠቃላይ ድጋፍ ውስጥ እስካሁን የተለቀቀላትን የገንዘብ መጠን ወደ 2.65 ቢሊዮን ዶላር ከፍ የሚያደርገው ሲሆን፣ ስምምነቱ ሊደረስ የተቻለው ከአልቫሮ ፒሪስ የተመራው የድርጅቱ ልዑክ ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ባደረገው የሁለት ሳምንታት ጉብኝትና ተከታታይ የሥራ ውይይቶች ማጠናቀቂያ ላይ ነው።

በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት መግለጫ ላይ እንደተመለከተው ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከቀጠናዊ ቀውሶች ጋር ተያይዞ የመጣውን ትልቅ ውጫዊ ጫና በመቋቋም ረገድ ከፍተኛ ጥንካሬ አሳይቷል።

ይሁን እንጂ፣ ዓለም አቀፋዊ አለመረጋጋትና የሸቀጦች ዋጋ መዋዠቅ አሁንም እያደገ በመምጣቱ በኢኮኖሚው የወደፊት ጉዞ ላይ የሚታዩት ስጋቶች መጨመራቸውን አይ ኤም ኤፍ አስጠንቅቋል።

የሀገሪቱን የኢኮኖሚ መረጋጋት በዘላቂነት ለማስቀጠልም ድርጅቱ ለኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ቁልፍ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን የጠቆመ ሲሆን፣ ይህም የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲን አጠናክሮ መቀጠልን፣ የውጭ ምንዛሬ ገበያውን ግልጽነትና አሠራር ይበልጥ ማሻሻልን እንዲሁም የአገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብን በማጠናከር የወጪ አያያዝን በጥንቃቄ መምራት አስፈላጊ መሆኑን አሳስቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
💔104🤪4👍3🤯1👀1
"በሚሊተሪ ካምፓች እና በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ምርጫ ሰኔ 2 ይካሄዳል" - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በሚሊተሪ ካምፓች እና በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በተመዘገቡባቸው ልዩ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የመራጮች ምዝገባ ሰኔ 1 ቀን እንደሚያካሂድ የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን በዛሬው ዕለት በሪፖርቱ ጠቅሶት ነበር።

ይህንን አስመልክቶ ማብራሪያ እንዲሰጡበት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ በሚሊተሪ ካምፓች እና በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በተመዘገቡባቸው ልዩ የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫው በተለየ ቀን እንደሚካሄድ አረጋግጠዋል።

ሆኖም ህብረቱ "June-8 / ሰኔ 1" ቀን እንደሚካሄድ ሪፖርቱ ቢጠቅስም፥ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ግን ምርጫው በእነዚህ ልዩ ጣቢያዎች የሚካሄደው #ሰኔ_2 መሆኑን ነው የገለጹት።

ይህ የተፈጠረበትን ምክንያትም ቦርዱ ያለበትን የተጨናነቀ ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ውጤቶቹም "በፍጥነት ተጠቃለው መቅረብ የሚችሉ ውጤቶች በመሆናቸው " ነው ሲሉ ቦርዱ ከሌሎች ውጤቶች ጋር አብሮ የሚያቀርባቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ካምፖች 28,632 እንዲሁም በሚሊተሪ ካምፖች 126,498 ሺ መራጮች መመዝገባቸው መገለጹ ይታወሳል።

በተጨማሪም ህብረቱ የተጠናቀቀ ውጤት የሚገለጽበትን ቀን በተመለከተ ህብረቱ ሰኔ 4 መሆኑን በሪፖርቱ ጠቅሷል።

የቦርዱ ሰብሳቢ በበኩላቸው ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ቦርዱ ከገጠመው የድምጽ በይፋ የማሳወቅ ሥራ እስከ 20 ቀን የመግፋት መብት እንዳለውም ጠቁመዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪86👍3
ኢዜማ፣ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን በንጹሃን ላይ ለተፈጸመው ጥቃት መንግሥት አስፈላጊውን ማጣራት አድርጎ ኃላፊነት የሚወስዱ አካላትን በመለየት "ሕጋዊ የእርምት እርምጃ" እንዲወስድ ጠየቀ።

ፓርቲው፣ "ማንነትን" ወይም "ኃይማኖትን" መሠረት ባደረገ ጥቃት በርካታ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የኾኑ ዜጎች ለጊዜው "ማንነቱ ባልታወቀ" አካል እንደተገደሉ፣ ቤተክርስቲያን እንደተቃጠለና ከጥቃቱ የሸሹ ነዋሪዎች ከቀያቸው እንደተሠደዱ መረዳቱን ገልጧል።

ለዚህ ዐይነቱ "ማንነትን መሠረት" ያደረገ ጥቃት ምንጬ የአገሪቱ ፖለቲካ "በማንነት ላይ የተመሠረተ" መኾኑ ነው ያለው ፓርቲው፣ በማንነት ላይ የተመሠረተው ፖለቲካ መፍትሔ እንዲበጀለት የኹሉም ባለድርሻ አካላት የቤት ሥራ መኾኑን አጽንዖት ሠጥቷል።

ኢዜማ፣ በምስራቅ አርሲ ዞን ውስጥ በንጹሃን ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን በመከላከል ረገድ የአካባቢው አስተዳደርና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በተደጋጋሚ ተፈትነው ወድቀዋል በማለት ተችቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
32👍9🤪9😡5🙏2👏1💯1
ሕወሃት አዲስ አውዳሚ ጦርነት ሊቀሰቀስ እንደሚችል በማስጠንቀቅ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አስቸኳይ ጥሪ አቀረበ።

ህውሃት ከፊታችን አውዳሚ ጦርነት እየመጣ ይገኛል አስወግዱ ሲል ለአለማቀፍ ማህብረሰብ ባሰራጨው ደብዳቤ፣ በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ሲል ገልጿል።

በምርጫ ቦርድ እውቅናው የተሰረዘው ድርጅቱ ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም "ሊቀረፍ የማይችልና አውዳሚ ጦርነትን ለመከላከል የቀረበ አስቸኳይ ጥሪ" በሚል ርዕስ ለዲፕሎማሲያዊ ሚሲዮኖች እና ለዓለም አቀፍ አጋሮች ባሰራጨው የዲፕሎማሲያዊ ማስታወሻ ሀገሪቱ ወደ አዲስ የትጥቅ ግጭት እያመራች መሆኑን አስጠንቅቋል።

እንደ ሕወሃት መግለጫ ከሆነ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ የውይይት እና የስምምነት መንፈስ እየጠፋ በመምጣቱ በእርሱ ፋንታ "የአንድ ወገን ውሳኔ፣ ማስገደድ እና ወታደራዊ የኃይል እርምጃ" ፖሊሲዎች እየነገሱ መጥተዋል ብሏል። ይህ አካሄድ መቀጠሉ ደግሞ ዳግም የትጥቅ ግጭት መከሰቱ የማይቀሬ እንዲሆን እያደረገው ነው ብሏል።

ይህ ሊቀሰቀስ የሚችለው ጦርነት በኢትዮጵያ ድንበር ብቻ ተወስኖ እንደማይቀር የጠቆመው መግለጫው በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ቀጣናዊ ውጥረት እና ለጎረቤት ሀገራት የሚታየውን የጠብ አጫሪነት ዝንባሌ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ግጭቱ አጠቃላይ ቀጣናውን ሊያናጋና ሰብዓዊ ቀውሱን ሊያባብስ እንደሚችል አመልክቷል።

የፌዴራል መንግሥቱ "ግትር አቋም" ይዟል ሲል የወቀሰው ሕወሃት፣ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ግን አሁንም ለሰላማዊ መፍትሔ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጿል።

ከሰሞኑ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የትግራይ ወጣቶች ወደ ወታደራዊ የስልጠና ካምፖች መግባታቸውን ሪፖርቶች በተሰሙበት በዚህ ወቅት የወጣው መግለጫ ጨምሮም "ማንኛውም ማህበረሰብ ሊሸከመው የሚችለው የጽናት ገደብ አለው" በሚል በትግራይ ላይ ያለው ጫና መጥበቁን የገለጸው ድርጅቱ፣ ቢሆንም ግን ብቸኛው አማራጭ መንገድ የፖለቲካ ውይይት መሆኑን በጽኑ እንደሚያምን አስታውቋል።

በመጨረሻም ሕወሃት የችግሩን ስር የሰደዱ መንስኤዎች ለመፍታት እንዲቻል፣ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚመራና የሚደገፍ ታማኝ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመርና ለዚህም ዝግጁ መሆኑን በመግለጫው ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20🤪11😡9👍4😁2🥰1👏1🕊1
በሚቀጥሉት ቀናት የክረምት ዝናብ ስርጭት

በሚቀጥሉት ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ የሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ የሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዮት ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በሚቀጥሉት ቀናት ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይጠበቃል።

እርጥበታማው የአየር ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ያመላክታል።

የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች እና የደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎችን የሚሸፍን ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙም አስታውቋል።

በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከ30 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖርም አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩ ገልጿል።

በሌላ በኩል በተለይም የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በአፋር ክልል፣ በሰሜንና ደቡብ ምዕራብ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከ32 እስከ 40 ዲግሪ ሴሊሺየስ በላይ ይሆናል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍3
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
ኤርትራ ተመረጠች‼️
ኤርትራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆና ተመረጠች።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በ85ኛው መደበኛ ስብሰባው ላይ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ዙሪያ ያተኮሩ ቁልፍ አጀንዳዎችን የተወያየ ሲሆን፣ በስብሰባውም ለድርጅቱ 81ኛ ጠቅላላ ጉባኤ መሪ የሚሆኑትን አካላት መርጧል።

በዚህም መሰረት የምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ኤርትራ የከፍተኛ አባል ሀገራትን ድምጽ በማግኘት ከጠቅላላ ጉባኤው ምክትል ፕሬዝዳንቶች አንዷ ሆናለች።

ኤርትራ ከተመረጡ ሌሎች 16 አገራት ጋር በመሆን የጸጥታው ምክር ቤት አምስት ቋሚ አባላትን (ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ሩሲያ፣ ብሪታንያ እና አሜሪካ) በመቀላቀል የጠቅላላ ጉባኤውን ቢሮ በጋራ ትመራለች።

በተጨማሪም ከእሷ ጋር እንደ አፍጋኒስታን፣ ፊንላንድ፣ ግብፅ፣ ሊባኖስ፣ ፓራጓይ እና ዚምባብዌ ያሉ ሀገራትም በምክትል ፕሬዝዳንትነት መመረጣቸውን ለመረዳት ተችሏል።

በተመሳሳይ ዕለት በምስጢር በተካሄደው የድምፅ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት፣ የወቅቱ የባንግላዲሽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካሊሉር ራህማን የ81ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል

ሚስተር ራህማን 99 ድምጽ በማግኘት የተመረጡ ሲሆን፣ ተፎካካሪያቸውን የቆጵሮሱን አንድሪያስ ካኩሪስን በ91 ድምጽ አሸንፈዋል። በነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ሥራቸውን በይፋ የሚረከቡት ተመራጩ ፕሬዝዳንት ካሊሉር ራህማን ከአሸናፊነታቸው በኋላ ባደረጉት ንግግር፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአሁኑ ወቅት ከባድ የፋይናንስ ቀውስ እና ዓለም አቀፍ የእምነት ማጣት ጉድለት እየገጠመው መሆኑን ጠቅሰው፣ አባል ሀገራቱ ድርጅቱ መለወጥና የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚችል በተግባር ማሳየት እንዳለባቸውና በየብስ የሚደረገውን እያንዳንዱን አስተዋጽኦ ውጤታማ በማድረግ የጠፋውን እምነት መመለስ እንደሚገባ አሳስበዋል።
Via capital

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤔2516👍5
"የአርሲው ጥቃት በሸኔ ታጣቂዎች የተፈጸመ ነው"፦ አቶ ሀይሉ አዱኛ

"የአርሲው ጥቃት ምርጫውን ለማደናቀፍ በሸኔ ታጣቂዎች የተፈጸመ ነው" የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ።

በጥቃቱ ከዚህም በላይ ጉዳት እንዳይደርስ ህዝቡና የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ሀይል መስዋዕትነት ከፍሏል ብለዋል። አሸባሪው ሸኔ ይህንን ጥቃት ያደረሰው ከታሪካዊ ጠላቶች ተልዕኮ ተቀብሎ የሀይማኖት ግጭት ለማስነሳት የነበረ ቢሆንም በህዝቡ አስተዋይነት ከሽፏል ብለዋል።

መከላከያ ሰራዊት፣የፌዴራል ፖሊስ የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ሀይል የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ እና አካባቢውን ለማረጋጋት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪5114💔11😡7😢4👍2🙏2🤣2😁1🤯1
ነዳጅ በሁለት ዶላር ቀነሰ።

የነዳጅ ዋጋ በአለማቀፍ ደረጃ መጠነኛ ቅናሽ አሳየ።

የዋጋ ቅናሽ የተስተዋለው እስራኤል እና ሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።

አንድ ብሬንት ነዳጅ በርሚል 67 ሳንቲም ወይም 0.69 % ቅናሽ አሳይቷል ተብሏል።

በ97.14 ዶላር ሲሸጥ የነበረው አንድ በርሚል ነዳጅ ወደ 95.40 ዝቅ ማለቱ ተመላክቷል። 

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍3
የቻይናው ኩባንያ የአዲስአበባ አውቶቡሶችን ወደ ተፈጥሮ ጋዝ ተሽከርካሪዎች የመቀየር ሥራ ጀመረ

ኢትዮጵያ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችን ከናፍጣ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ ለመቀየር የሚያስችል መጠነ ሰፊ ፕሮግራም የጀመረች ሲሆን፥ በቻይናው ኩባንያ የመጀመሪያው ማሻሻያ የተደረገለት አውቶቡስ በአዲስ አበባ የጎዳና ላይ ፍተሻውን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን ቻይና ዴይሊ ዘግቧል።

በቻይናው ጂሲኤል አፍሪካ ኢንዱስትሪያል ግሩፕ የሚመራው ይህ መርሃ ግብር፥ ኢትዮጵያ ከውጭ በሚገባ ነዳጅ ላይ ያላትን ጥገኝነት ለመቀነስ እና ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ የሆነ የሕዝብ ትራንስፖርትን ለማስፋፋት የምታደርገው ሰፊ ጥረት አካል ነው ተብሏል።

ቻይና ዴይሊ እንደዘገበው፤ ፕሮጀክቱ፤ በአዲስ አበባ አገልግሎት የሚሰጡ ከ2,000 በላይ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችን በስምንት ወራት ውስጥ ለመቀየር ያለመ ነው።

በተጨማሪም የመንግሥት ንብረት የሆኑ የመርሴዲስ ቤንዝ አውቶቡሶችን ለመቀየር ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23👍10
እዳ ባለመከፈሉ ኢትዮጵያ ልትከሰስ‼️
#የኢትዮጵያ #ዩሮቦንድ አበዳሪዎች ያልተከፈለ ዕዳን በተመለከተ መንግሥትን ለመክሰስ የሕግ ሂደት መጀመራቸው ተዘገበ‼️

የኢትዮጵያ የዩሮቦንድ አበዳሪዎች ቡድን፣ መንግሥት ያልከፈለውን የ1 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ በተመለከተ ክስ ለመመሥረት የሚያስችላቸውን የሕግ ሂደት በይፋ መጀመራቸው ተዘገበ።

ብሉምበርግ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ምንጮች ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፤ የኢትዮጵያ ‘አድ ሆክ’ የቦንድ ባለቤቶች ኮሚቴ (Ethiopia Ad Hoc Bondholder Committee) አባላት፣ በእንግሊዝ ፍርድ ቤቶች ክስ ለመመሥረት ማቀዳቸውን የሚገልጽ የቅድመ-ክስ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ባለፈው ሳምንት ለኢትዮጵያ መንግሥት ልከዋል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉት የመረጃው ምንጮች እንዳሉት፣ መንግሥት ደብዳቤው እንደደረሰው ለማሳወቅ 14 ቀናት አሉት ያሉ ሲሆን፣ ሆኖም የጊዜ ገደቡ መቼ እንደሚጀምር በዝርዝር አላብራሩም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣149👍7😢4🎉1
ችሎት ውስጥ የተፈፀመ አሰቃቂ ግድያ

ዛሬ ረፋድ ላይ በሆለታ ወልመራ ወረዳ ፍርድ ቤት ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት፣ የዕለቱን የችሎት ውሳኔ በማንበብ ላይ የነበሩ ዳኛ እና አንዲት ተከራካሪ ህይወታቸው ማለፉን አክሰስ ቱ ጃስቲስ ኢኒሼቲቭ - ኢትዮጵያ አስታውቋል።

እንደ ምንጩ መረጃ፣ የቤተሰብ ክርክር ጉዳይን በመመልከት ላይ የነበሩት ዳኛ ወርቄ ፈካንሳ የፍርድ ውሳኔውን እያነበቡ ባሉበት ወቅት፣ ተከሳሹ በድንገት ባወጣው ሽጉጥ ዳኛዋን በጥይት በመምታት ህይወታቸውን ቀጥፏል።

በዚሁ አጋጣሚ በችሎቱ ላይ በጉዳዩ ላይ ይከራከሩ የነበሩት (ተከራካሪዋ) በተመሳሳይ ሁኔታ በተከሳሹ በተተኮሰ ጥይት ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል።

የሕግ ባለሙያዎችና ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ድርጊቱን በጽኑ ያኮነኑ ሲሆን፤ ዳኞችና የሕግ ባለሙያዎች በሥራ ገበታቸው ላይ አስተማማኝ የደህንነት ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ በርካቶች በመጻፍ ላይ ይገኛሉ።

“አንድ ግለሰብ ታጥቆ ወደ ፍርድ ቤት አዳራሽ መግባት መቻሉ፣ የፍርድ ቤቶችን የጸጥታና የፍተሻ አሰራር ምን ያህል ደካማ እንደሆነ በአሳዛኝ ሁኔታ አሳይቷል” በማለት አክሰስ ቱ ጃስቲስ ኢኒሼቲቭ የድርጊቱን አሳሳቢነት ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢3018👍4😡2
ወደኋላ አስር አመት‼️
ማንኛውም ደረሰኝ ሳይቆርጥ የተገበያየ አካል በወንጀል እስከመጠየቅ የሚያደርሰው የተሻሻለው የታክስ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀረበ፡፡

ረቂቁ የታክስ ማጭበርበርን ለመከላከል ለ10 ዓመታት ወደኋላ በመሄድ ሂሳቡን በመመርመር ወይም ሂሳብ ኦዲት በማድረግ ተጨማሪ ግብር ማስከፈልን ለገቢ ሰብሳቢው የሚፈቅድ ነው፡፡

ዛሬ ለምክር ቤቱ የቀረበው ረቂቅ የግብር አስተዳደር አዋጅ በተለይ ደረሰኝ ባለመቁረጥ የሚደረግ ግብይት ላይ ከፍ ያለ ቅጣትን የሚያስከትሉ አንቀፆችን የያዘ ነው፡፡

ማንኛውም ሰው ህጋዊ ደረሰኝ ያልሰጠ እንደሆነ በእያንዳንዱ ባልሰጠው ደረሰኝ ልክ 100 ሺህ ብር አስተዳደራዊ ቅጣት በገንዘብ ይቀጣል ይላል የማሻሽያ አዋጁ ማብራሪያ፡፡

በተጨማሪ ይሄንኑ አስተዳደራዊ ቅጣት በዓመት ሁለት ጊዜ የተቀጣ እንደሆነ እና ሆን ብሎ ድርጊቱን መፈፀሙን ከቀጠለ ድርጊቱ እንደ ወንጀል ጥፋት ተቀጥሮ በወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑም ተብራርቷል፡፡

በተጠቀሰው ድርጊት የድርጅት ስራ አስኪያጅ በግል በወንጀል ተጠያቂ የሚሆነው በወንጀሉ ተግባር ተባባሪ ከሆነ ወይንም ደረሰኝ ያለመስጠትን መከላከል የሚያስችል የቁጥጥር ሥርዓት ያልዘረጋ ከሆነ እንዲሆንም ተደንግጓል፡፡

በሌላ በኩል አንድ ግብር ከፋይ ግብር ከከፈለ በኋላ በ10 አመት ጊዜ ውስጥ በማንኛው ጊዜ እንደገና ሂሳቡ ተመርምሮ ወይም በኦዲት ተጨማሪ ግብር ሊጠየቅ ይችላል ይላል የረቂቅ አዋጁ ማብራሪያ፡፡

ይህም በ10 ዓመት የተገደበው በኢትዮጵያ የንግድ ህግና የሂሳብ አያያዝ ህጎች መሰረት የሂሳብ ሰነዶች ተጠብቀው መቆየት ያለባቸው ለ10 ዓመታት ብቻ በመሆኑ ነው ተብሏል፡፡

ሌላው የታክስ አስተዳደር አዋጁ ማሻሻያ የያዘው አዲስ ነገር በታክስ ባለስልጣኑ እና በታክስ ከፋዩ መካከል የሚፈጠርን አለመግባባት መፍቻ ዘዴን ይመለከታል፡፡

ከዚህ ቀደም በነበረው ህግ ግብር ከፋዮች የተጣለባቸውን ግብር ተገቢ አይደለም ብለው ባመኑ ጊዜ መፍትሄ ፍለጋ በታክስ አስተዳደሩ ስር ለተቋቋመ የቅሬታ ሰሚ ፣ ለግብር ይግባኝ ኮሚሽን እና የህግ ትርጉምን በተመለከተ በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች እንዲመለከቱት የሚያስችል ስርዓት ነበር፡፡

ይህን ለማድረግ ግን ግብር ከፋዮች ቅድሚያ የተወሰነባቸውን ግብር ከ50 እስከ 75 በመቶ መክፈልም ይጠበቅባቸው ነበር፡፡

ያም ሆኖ መፍትሄ ለማግኘት ረዥም ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል በማብራሪያው ተጠቅሷል፡፡

በተሻሻለውና በረቂቅ ደረጃ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በቀረበው የታክስ አስተዳደር አዋጅ የተጠቀሰው አሰራር እንዳለ ሆኖ በአጭር ጊዜ አለመግባባቶችን ለመፍታት ያግዛል የተባለ የገለልተኛ አስማሚን አሰራር ስራ ላይ ያውላል ተብለዋል፡፡

ይህም አዲስ “የመስማማት ሥርዓት” በሚል አዋጁ እንዲዘረጋ በሚፈቅደው ገለልተኛ አስማሚ ግብር ከፋዩን እና ግብር ሰብሳቢውን በሚስጥራዊነት መርህዎች ጭምር የሚያስማማበት ሥርዓት ነው ተብሏል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15😢15🤷‍♂4👍3👀2😁1🤯1
#ስዕላዊመረጃ በአርሲ፣ አሰኮ ወረዳ ከሰሞኑ በደረሰው ጥቃት ዙርያ መሠረት ሚድያ ከመንግስት ምንጮች እና ከአካባቢው ነዋሪዎች ያሰባሰበው አዲስ መረጃ!

ህይወታቸው እንዳለፈ የተረጋገጠ= 53

ያሉበት ያልታወቀ ሰዎች= 190

የቆሰሉ= 47

የታገቱና ገንዘብ የተጠየቀባቸው= 6

የተቃጠለ ቤት= 308

የተቃጠለ ቤተክርስቲያን= 2

ተፈናቅለው እሬቻ ማካኤል የተጠለሉ= 789

ተፈናቅለው ሱንቴ ማርያም የተጠለሉ= 691

ተፈናቅለው አሰኮ ከተማ የተቀመጡ= 262

ተፈናቅለው ሌንጫ ኦዳ፣ ወራንቡስ፣ ቦግዶ፣ ኮበሬ የተጠለሉ= 133

ጠቅላላ የተፈናቀሉ= 1,875

*የአካባቢው ነዋሪዎች ዛሬ ለሚድያችን እንደተናገሩት ተኩሱ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ቆሟል፣ ነገር ግን የተፈናቀለው ህዝብ ወደ ቀዬው መመለስ አልቻለም።

ምንጭ :- | መሠረት ሚድያ |

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢41💔1712👍3🕊2🤯1😱1🎉1🙉1