⚡ "የጽምዶ ጥምረት" በርካታ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ቡድኖችን እያካተተ መሆኑ ተገለጠ
በኤርትራ እና ህወሃት መካከል የተጀመረውና "ጽምዶ" (Ximdo) በመባል የሚታወቀው አዲሱ የፖለቲካ ትስስር፣ አሁን ላይ በርካታ የኢትዮጵያ የታጠቁና የፖለቲካ ተቃዋሚ ቡድኖችን ወደማካተት እየሰፋ መሄዱን አፍሪካ ኢንተለጀንስ ዘግቧል።
📌 የአዲስ አበባውን ማዕከላዊ መንግስት የሚቃወሙት የህወሃት/ትግራይ መከላከያ ኃይል አመራሮች፣ በቅርቡ በሱዳን የወደብ ከተማ ፖርት ሱዳን ከተደረጉ የኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ከሱዳን ጦር ኃይል ተወካዮች ጋር ስብሰባ ማድረጋቸው ተረጋግጧል።
ይህ በኤርትራ መንግስት አስተባባሪነት እየተመራ ያለው ጥምረት የህወሃትን "የአሮጌው ጎራ ጨምሮ፣ እንደ ፋኖ ያሉ፣ የኦብነግ የተገነጠሉ ክንፎችን እና ሌሎች ታዋቂ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን በአንድ ጥላ ስር ለማሰባሰብ እየሰራ እንደሆነ የደህንነት ምንጮች ጠቁመዋል።
የሰሜኑ ጦርነት ወቅት ኤርትራ እና ህወሃት እርስ በእርስ የገጠሙ ደመኛ ጠላቶች የነበሩ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን "የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው" በሚለው መርህ የአዲስ አበባውን መንግስት ለመጫንና የራሳቸውን የፖለቲካ ህልውና ለማስጠበቅ ስልታዊ ህብረት ፈጥረዋል።ይህ አዲስ የሀይሎች መሸጋሸግ በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ እና በሱዳን መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ እያሻከረው ሲሆን፣ ቀጠናዊ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።
@Addis_Reporter

❤39🤔4🏆4👍2👀1
የሟቾቹ ቁጥር 13 ደርሷል‼️
ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የአርሲና ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት 13 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን፣ ከ280 በላይ ምእመናን መፈናቀላቸውንና የ101 ዓመት ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉን አሳወቁ።
ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ:ም ጀምሮ በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ ወረዳ; በሺርካ ወረዳና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ 13 ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉ የ101 ዓመት እድሜ ያለው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል።
የካራ ኩፍተና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይም ዘረፋ የተካሄደ ሲሆን ምእመናን ጽላቱን ይዘው ተሰደዋል፤ መኖሪያ ቤታቸውም ተቃጥሏል።
የተገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝርም
1. አቶ ደምረው አበራ የ70 ዓመት
2. ከፈለኝ ልክየለው የ56ዓመት
3. ሐይሉ ንጉሴ የ70 ዓመት
4. እሸቴ ዳመና የ42 ዓመት
5. አበባየሁ ዳኜ የ42 ዓመት
6. ሰሙ አባይነህ የ70 ዓመት
7. 1 ሚሊሻ
8. አማረ በላይነህ የ80 ዓመት
9. ተሬ ደሴ የ25 ዓመት
10. ወጣት ገነነ ጥላሁን በሽርካ ወረዳ
11. ሙርቴሳ ጥላሁን በሽርካ ወረዳ
12. አቶ ንጉሱ ማንደፍሮ በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ
13. አቶ በቀለ ኃ/ሚካኤል በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ
በአጠቃላይ የ13 ሰዎች ህይወት አልፈዋል።
በተጨማሪ በአሰኮ ወረዳ ከ280 ሰው በላይ ተፈናቅለዋል::
በመሆኑም ኦርቶዶክሳውያኑ ተወልደው ካደጉበት፣ ወልደው ከሳሙበት ቀያቸው በሃይማኖታቸው ብቻ ቤታቸው እየተለየ ተቃጥሏል፤ ንብረታቸውና ከብቶቻቸው ተዘርፈዋል።
ከጥቃቱ የተረፉት ነዋሪዎችም ይዘውት የሸሹት እምነታቸውንና ማንነታቸውን ብቻ በመሆኑ አሁን ላይ ሜዳ ላይ ወድቀው ይገኛሉ።

💔38😢31❤15👍2🤯2🙏2🕊2🤔1
በበሻሻ የምርጫ ጣቢያ የድምፅ ቆጠራ ውጤት
በኢትዮጵያ የተካሄደው የሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ የድምፅ ቆጠራ ውጤት፣ ዛሬ ማክሰኞ ከማለዳው ጀምሮ በአብዛኞቹ የምርጫ ጣቢያዎች እየተለጠፈ ይገኛል። በጅማ ከተማም ሆነ በዞኑ ስር በሚገኙ የምርጫ ክልሎች የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ በሰላም መጠናቀቁን የዞኑ የምርጫ አስተባባሪ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።

🤔27🙉15❤11🤪10🤣6🥰3👍2👀1
ደሴ‼️
በደሴ ከተማ የአይጥ መርዝ ለበርካታ ሰዎች ህልፈት ምክኒያት ሆኗል ተባለ።
በ2018 በጀት አመት ዘጠኝ ወራት የኬሚካል መመረዝ ጉዳት ለደረሰባቸው በርካታ ሰዎች ህክምና መስጠቱን የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታውቋል።የሆስፒታሉ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሙያ አቶ ብርሃኑ አዱኛ ለብስራት ሬድዮ እንደገለፁት ሆስፒታሉ በዘጠኝ ወራት ውስጥ የኬሚካል መመረዝ አደጋ ለደረሰባቸው 1መቶ 72 ሰዎች የህክምና አገልግሎት ሰጥቷል።
ከእነዚህ መካከል 6.8 በመቶ የሞት ምጣኔ መመዝገቡን ገልፀው በሆስፒታሉ በተሰራው የተቀናጀ ስራ ከመመረዝ ጋር የተያያዘ የሞት ምጣኔ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ 27.3 በመቶ ቀንሷል ብለዋል።የጉዳቱን የስርጭት መጠን አስመልክቶ 67 በመቶ የሚሆነው ከደሴ እንዲሁም 29 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ከደቡብ ወሎ የተከሰተ መሆኑ ተገልጿል።
እነዚህ አካባቢዎች በኬሚካል መመረዝ በከፍተኛ ሁኔታ የተጠቁ የማህበረሰብ ክፍሎች መገኛ መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ ብርሀኑ በሆስፒታሉ አስፈላጊውን ህክምና እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል።86.5 በመቶ የሚሆኑት ራሳቸውን ለማጥፋት በሚል ህብረተሰቡ አይጥን ለመግደል የሚጠቀምባቸውን መርዞች የተጠቀሙ ናቸው።
የመርዝ ዓይነቶች ትንታኔ እንደሚያሳየው የአይጥ መመረዝ 35.9 በመቶ ፣ የመድኃኒት መመረዝ 17.6 በመቶ እንዲሁም የበረኪና መመረዝ ደግሞ 15.3 በመቶ ድርሻን ይይዛሉ።

❤21😢6👍3🤯2🙏1👀1
የኢትዮጵያ መርከብ የሆርሙዝ ሰርጥን በሰላም መሻገሯ ተሰማ
በመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ምክንያት ከፍተኛ ስጋት በነበረበት የሆርሙዝ ሰርጥ አካባቢ፣ የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ንብረት የሆነችው “አሶሳ” መርከብ ከሆርሙዝ ሰርጥ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ኮርፋካን ወደብ በመድረስ ወሳኝ የሕክምና እና የንግድ ጭነቶችን በተሳካ ሁኔታ ጭና ወደ ሀገሯ ተመልሳለች።
ይህ ስኬት የኢትዮጵያን ባሕረኞች ቁርጠኝነት እና የኢትዮጵያን የባሕር ሎጅስቲክስ ብቃት በተግባር ያሳየ ነው ተብሎለታለ።

😁41❤38👍5👏2🤯2🤩2🙏2👌1💋1🤝1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የአሜሪካ መንግስት በአፍሪካ የቪዛ አገልግሎት መስጫ ቦታዎችን ወደ 20 ብቻ ሊቀንስ ነው‼️
👉 አዲስ አበባ አገልግሎቷን እንደምትቀጥል ተረጋግጧል
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአፍሪካ አህጉር የሚገኙ የቪዛ ማስተናገጃ ማዕከላቱን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ መወሰኑን ይፋ አደረገ።
ይህ አዲስ መመሪያ የትራምፕ አስተዳደር በስደት ላይ የጀመረውን ጠንካራ የቁጥጥር ፖሊሲ ይበልጥ ለማጥበቅ ከሚያደርገው ጥረት ጋር የተያያዘ ነው።
እስካሁን ድረስ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ወደ 50 የሚጠጉ የአሜሪካ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች የቪዛ ማመልከቻዎችን ሲቀበሉ የነበረ ቢሆንም፣ አዲሱ እቅድ ይህንን ቁጥር ወደ 20 "ማዕከላት" ብቻ ዝቅ የሚያደርግ ይሆናል።
እንደ አሶሺየትድ ፕሬስ ዘገባ እና ከውስጥ ባለስልጣናት በተገኘ መረጃ መሠረት፣ ይሄው አሰራር በሚቀጥሉት ሳምንታት (በሰኔ ወር ውስጥ) ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ በፀደቀው በዚህ መመሪያ መሠረት፣ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ሙሉ የቪዛ አገልግሎት መስጠቷን እንድትቀጥል ከተመረጡት 20 ጥቂት ማዕከላት መካከል አንዷ ሆናለች።
ይህም ማለት በኢትዮጵያ የሚገኙ አመልካቾች ያለምንም እንግልት መደበኛ የቪዛ አገልግሎታቸውን ከአዲስ አበባ ማግኘት ይችላሉ።
ይሁን እንጂ ይህ ውሳኔ ማዕከል ባልሆኑ ሀገራት ዜጎች ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚና የጉዞ ጫና ያሳድራል።
በእነዚህ ሀገራት የሚገኙ የአሜሪካ ቆንስላዎች መደበኛ የቪዛ አገልግሎት መስጠታቸውን የሚያቆሙ በመሆኑ፣ ዜጎቹ ቪዛ ለማግኘት ድንበር አቋርጠው አዲስ አበባን ወደመሳሰሉ የቪዛ ማዕከላት ለመጓዝ ይገደዳሉ። ይህም ተጨማሪ የጉዞ ወጪን እና የጊዜ መዘግየትን ያስከትላል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አገልግሎታቸው በሚቀነስባቸው ሀገራት የሚገኙ ኤምባሲዎች ሙሉ በሙሉ የማይዘጉ ሲሆን፣ ለአሜሪካ ዜጎች የሚሰጡ ድንገተኛ ድጋፎችን እና ልዩ የዲፕሎማቲክ ጉዳዮችን ማስተናገዳቸውን ይቀጥላሉ ተብሏል።

❤16👍5🙈1
የቻይናው መከላከያ ተቋም “የአሜሪካን ድብቅ ተዋጊ አውሮፕላኖች በኤአይ (AI) መከታተል ችያለሁ” ማለቱ መነጋገሪያ ሆኗል
አንድ ጂንጋን (Jingan) የተሰኘ የቻይና የግል መከላከያ ቴክኖሎጂ ተቋም፣ በቅርቡ በኢራን ግጭት ወቅት “ጂንግቺ” በተሰኘው የሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI) የጦርነት ክትትል ስርዓቱ አማካኝነት አራት የአሜሪካ “ቢ-2 ስፒሪት” (B-2 Spirit) ድብቅ ስውር ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖችን መከታተል መቻሉን ገለጸ።
የቴክኖሎጂ ተቋሙ አውሮፕላኖቹ “ፔትሮ 41 እስከ 44” (Petro 41 to 44) በሚሉ የመገናኛ ኮዶች ሲንቀሳቀሱ እንደነበር የጠቀሰ ሲሆን፣ ከአውሮፕላኖቹ የወጡ የሬዲዮ ሞገዶችን በመጥለፍ እና በኤአይ (AI) አማካኝነት የበረራ መስመራቸውን መልሶ መገንባት መቻሉን ተናግሯል። ይሁን እንጂ ተቋሙ ይህንን አስገራሚ ክስ የሚያረጋግጥ እስካሁን ያቀረበው ምንም ዓይነት ተጨባጭ ማስረጃ የለም።
እንደ ጂንጋን ገለጻ ከሆነ፣ ስርአቱ ግጭቱ ከመቀስቀሱ ሳምንታት በፊት የሳተላይት ምስሎችን፣ የበረራ መረጃዎችን እና ግልጽ የሆኑ የመረጃ ምንጮችን (open-source intelligence) በማቀናጀት በኢራን አቅራቢያ እያደገ የመጣውን የአሜሪካ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ቀድሞ መለየት ችሎ ነበር። ተቋሙ አራቱ የቢ-2 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች የተከታተላቸው አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ኢላማዎች ላይ ጥቃት ከሰነዘሩ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ መሆኑን አስታውቋል።
ይሁን እንጂ ይህ የቻይናው ተቋም ይፋ ያደረገው መረጃ በተናጠል በገለልተኛ ወገን ያልተረጋገጠ ሲሆን፣ እጅግ ዘመናዊ እና በራዳር እንዳይታዩ ተደርገው የተሰሩት ስውር አውሮፕላኖች ተለይተው ስለመገኘታቸው የሚገልጸው ዘገባ እስካሁን ድረስ በማስረጃ አልተደገፈም።

❤19👍10🤣3🤔2
ጅቡቲ በዳመርጆግ የነዳጅ ማከማቻ ግንባታ ላይ የኢትዮጵያን ድጋፍና ተሳትፎ እየጠበቀች መሆኑን ገለጸች
የጅቡቲ ወደቦች እና ነፃ ቀጠናዎች ባለስልጣን በሀገሪቱ ደቡብ ምስራቅ በኩል በሚገኘው አዲሱ የዳመርጆግ ፈሳሽ ጭነት ወደብ ላይ የነዳጅ ማከማቻ ዴፖ ግንባታ ለመጀመር በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ላይ የኢትዮጵያን ተሳትፎና የገንዘብ ድጋፍ እየጠበቀ መሆኑን አስታውቋል።
የባለስልጣኑ ሰብሳቢ አቡበከር ኦማር ሀዲ ለካፒታል እንደገለፁት ፣ ዘመናዊው የነዳጅ ወደብ ወደ ስራ እንዲገባ የነዳጅ ማራገፊያ ዴፖ ግንባታ ይቀረዋል።
ለዚህም ባለስልጣኑ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጋር ድርድር እያደረገ ሲሆን፣ ተቋሙ ሐምሌ 1 ቀን በሚጀምረው አዲስ የበጀት አመት በጀት አፀድቆ ለስራው እንደሚመጣ ይጠበቃል ሲሉ ነው የገለፁት።

❤17🤣3👍2
⚡️ "የኢራን ድሮኖች በኩዌት ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ከባድ ጥቃት ሰነዘሩ"
በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣውን ቀጠናዊ ጦርነት ተከትሎ፣ የኢራን ድሮኖች በኩዌት ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዋናው የመንገደኞች ተርሚናል (T1) ላይ ከባድ ጥቃት ማድረሳቸውን የኩዌት ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እና የመከላከያ ሚኒስቴር በይፋ አስታውቀዋል። ጥቃቱ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱንና በርካታ ሰዎችን ማቁሰሉ ተገልጿል።
📌 ጥቃቱን ተከትሎ የኩዌት ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የአደጋ ጊዜ እቅድን ያነቀሳቀሰ ሲሆን፣ ሁሉንም የንግድ በረራዎች በማቋረጥ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ የነበሩ አውሮፕላኖችን ወደ ጎረቤት ሀገራት አማራጭ አውሮፕላን ማረፊያዎች እንዲቀየሩ አድርጓል።

❤7👍3🙏3👏2
የምርጫ ቦርድ ይፋዊ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ ማንኛውም አካል ራሱን አሸናፊ አድርጎ ከመግለጽ ይቆጠብ":-ኢሰመጉ‼️
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ባወጣው የምርጫ መታዘብ ቅድመ መግለጫ ላይ ያነሳቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
ጥብቅ ማሳሰቢያ፦የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (NEBE) ይፋዊ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ ማንኛውም ግለሰብ፣ የፖለቲካ ድርጅት ወይም የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ጊዜያዊ ውጤት በማጋራት ማኅበረሰቡን ከማደናገር እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
የምልከታ ስፋት፦ኢሰመጉ ባሰማራቸው 433 ታዛቢዎች አማካኝነት ከ800 በላይ የምርጫ ጣቢያዎችን ተከታትሏል።
⚠️ የተስተዋሉ ዋና ዋና ተግዳሮቶች፦
* የአዲሱ ዲጂታል የመራጮች ምዝገባ ሥልት መጀመሩ የሚበረታታ ቢሆንም፣ የአስፈጻሚዎች ሥልጠና ማነስ ለመራጮች መጨናነቅና ለሰዓት መራዘም ምክንያት ሆኗል።
* በበርካታ አካባቢዎች የትራንስፖርት መቋረጥ፣ በአዲስ አበባ የሰልፍ አስተባባሪዎች ማነስ እና በመራጮች ላይ የደረሰ የእንግልት ሰዓት።
* በሐዋሳና አካባቢው በሚገኙ ውስን ጣቢያዎች የምርጫ አስፈጻሚዎች በሚስጥራዊ ድምፅ መስጫ ቦታ በመግባት የሥነ-ልቦና ጫና ማድረጋቸው እና ያልተመረጡ ወረቀቶችን ወደ ሳጥን ማስገባት የመሳሰሉ የነፃነት መብትን የገደቡ ክስተቶች መታየታቸው።
✅ በበጎ ጎን የተነሱ ነጥቦች፦
* የመራጮች ከፍተኛ ተነሳሽነት፣ በቂ የቁሳቁስ አቅርቦት እና በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች የጎላ የጸጥታ መደፍረስ ሳይኖር ሂደቱ መጠናቀቁ።
"ኢሰመጉ ምርጫ ቦርድ በአንጻራዊነት ስኬታማና ሰላማዊ ምርጫ ማከናወኑን በመግለጽ ዕውቅና የሰጠ ሲሆን፣ በቀጣይ ግን የተስተዋሉ ችግሮችን በዝርዝር ለይቶ እንዲያርም ጥሪ አቅርቧል።"

😁23❤16👍5🤪4🤔1
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት በማስመልከት መልእክት አስተላለፉ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በአርሲ ሀገረ ስብከት በቤተ ክርስቲያን እና በኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ ::
"በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሽርካ፣ በሆንቆሎ፣ በዋቤ እና በሙኔሳ ወረዳዎች በመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ስለደረሰው አሰቃቂ ጥቃት የሰማነው በተሰበረ ልብ ነው።
ይህ መከራ እያበቃ ሳይሆን እየሰፋ በመምጣቱ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅና ሰላምን የማስፈን አደራ የተጣለባችሁ የጸጥታ አካላትና በየመዋቅሩ ያላችሁ ሓላፊዎች ከምንም በላይ ታሪክ የሚጠይቃችሁ በሥልጣን ዘመናችሁ ለዜጎች ደኅንነት በምትከፍሉት ዋጋ ነውና ይህንን የጥቃት ሰንሰለት በማስቆምና ወንጀለኞችን ለሕግ በማቅረብ ከታሪክ ባለዕዳነት ትድኑ ዘንድ በቤተ ክርስቲያናችን ስም አበክረን እናሳስባለን።
በየአካባቢው የምትገኙ ምእመናንና መላው ኢትዮጵያውያንም በወንድማማችነት መንፈስ ተጋግዛችሁ፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍና በጸሎት ከቤተክርስቲያናችን ጎን እንድትሆኑ ጥሪያችንን::"

❤37🙏10👍3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢራን የኩዌት አየር መንገድን በዚ መልኩ ነው ያወደመችው በዚህ ጥቃት 63 ሰዎች ቀላል እና ከባድ ጉዳት የደርሰባቸው ሲሆን የሞቾች ቁጥርም ከአንድ ሊበልጥ እንደሚችል እየተናገሩ ይገኛል"
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤16💔7🤯3👍2👏1😢1
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን ኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች ፦
⏰ ከጠዋቱ 2:00-12:00
👉 በአዳማ ሪጅን አዳማ ቆርቆሮ፣
⏰ ከጠዋቱ 2:00-11:00
አዳማ ፈትል ፋብሪካ፣ ሬድሬስ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ፣ አህዋን ፋብሪካ
⏰ ከጠዋቱ 2:30-9:00
👉 በአዳማ ሪጅን ከአዋሽ መልካሳ ወደ አዱላላና አሮሪቲ፣
⏰ ከጠዋቱ 2:30-7:00
👉 በሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን አስኮ ገብርኤል፣ ሳንሱሲ፣ እያሱ ምንጭ፣ ብርጭቆ ኮንዶሚኒየም፣ ከታ አፍያ ዴቄት፣
⏰ ከጠዋቱ 3:00 እስከ ምሽቱ 4:00 ድረስ
👉 በደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ኬኬ ብርድ ልብስ ፋብሪካ፣ ቂሊንጦ ኮንዶሚኒየም፣ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት፣ አስቱ ዩኒቨርስቲ እና ኢንዱስትሪ መንደር፣ ዋልያ ቢራ
⏰ ከጠዋቱ 6:00-9:00
👉 በምዕረብ አደስ አበባ ሪጅን ስልጤ ሰፈር፣ አጃምባ ኮንዶሚኒየም
⏰ ከቀኑ 7፡00- 11፡00
👉 በሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ሸጎሌ አንበሳ ጋራዥ፣ ሸጎሌ መንደር-7፣ ፊናንስ፣ አበበ ቢቂላ፣ ኳስ ሜዳ፣ መሳለሚያ
⏰ ከቀኑ 7:30-10:30
👉 በሽረ ረጅን እደጋ አርቢ፣ ማይ ቐንታል
ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻች የጥገና ሥራው ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትእግስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

👍11❤9⚡2
በ130 ምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች መዝገብ ላይ ያልተገኙ እና ካርድ ያልያዙ መራጮች እንዲመርጡ መደረጋቸውን ኅብረት ለምርጫ ገለጸ
የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ (CECOE / ኅብረት ለምርጫ) ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የተከናወነውን 7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ አስመልክቶ ዛሬ ረቡዕ ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ የትዝብት ሪፖርቱ፣ በ130 ምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች መዝገብ ላይ ያልተገኙ እና ካርድ ያልያዙ፣ በእያንዳንዱ ጣቢያ ከአንድ እስከ 10 የሚሆኑ መራጮች እንዲመርጡ መደረጋቸውን ገለጸ።
እንዲሁም በስምንት የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ደግሞ ከ10 በላይ ሰዎች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ ሳይገኝ እና የመራጭነት ካርድ ሳይዙ እንዲመርጡ መፈቀዱንም ኅብረቱ በምርጫ ትዝብት ጊዜያዊ ሪፖርቱ ላይ አስታውቋል።
ኅብረቱ ከታዘባቸው 2,506 የምርጫ ጣቢያዎች መካከል በ2,458 ጣቢያዎች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ ሰፍሮ ድምጽ መስጠት የተከለከለ ሰው እንዳልነበር መታዘቡን ጠቅሷል፤ ይሁንና በ46 የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ከ1 እስከ 10 ግለሰቦች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ ሰፍሮ ድምጽ መስጠት መከልከላቸው ተገልጿል።
በሁለት ድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ደግሞ ከ10 በላይ ሰዎች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ ሰፍሮ ድምጽ መስጠት መከልከላቸውን የኅብረቱ ሰብሳቢ ተናግረዋል።
Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

❤16😁11👍5