አዲስ ሪፖርተር - NEWS
35.8K subscribers
16.9K photos
414 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
አንድ የፓሪስ ሴንት ጀርመን ደጋፊ በአዉሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ጋብሬል ማጋሌሽ የሳታትን የፍጹም ቅጣት ምት በግራ እግሩ ላይ ተነቅሶታል።

የማይታመን ነዉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁41🙉54👍3🤪1
መረጃ‼️

ከጦርነቱ በፊት ተቃቁሞ የነበረውና በቅርቡ ወደ ሥራ የተመለሠው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ሕወሃት ያቀረባቸውን የአዲስ የካቢኔ አባላት፣ የዞን አስተዳዳሪዎችና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሹመት ዛሬ ማምሻውን አጸደቀ።

የሕወሃት ምክትል ሊቀመንበር አማኑኤል አሠፋ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንትና የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ ኾነው እንደተሾሙ የክልሉ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

70 በመቶ ያህሉ የካቢኔ አባላት ከሕወሃት የተውጣጡ ሲሆኑ፣ 30 በመቶዎቹ ከተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና ከምሁራን የተውጣጡ እንደሆኑ ተገልጧል።

በተመሳሳይ፣ ወልደአብርሃ ገብረጻዲቅ የሰሜን ምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ሺሻይ ግርማይ የማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ዝናቡ ገብረመድኅን የደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ግዴይ አዘናው የምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ፍስሃ ኃይላይ የምሥራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንዲሁም ከለሊ ሐጋዚ የደቡብ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኾነው እንደተሾሙ ዘገባዎቹ ጠቅሠዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
22😁10👍2🤯2👏1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የኢራኑ ፕሬዚዳንት የስራ
መልቀቂያ ማቅረባቸው ተሰማ


የኢራኑ ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ለሀገሪቱ የበላይ መሪ ጽህፈት ቤት ይፋዊ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ለጉዳዩ ቅርብ የሆነ ምንጭ ለኢራን ኢንተርናሽናል ገልጧል። እሁድ ዕለት በተላከው በዚህ ደብዳቤ ላይ ፕሬዝዳንቱና መንግስታቸው በሀገሪቱ ዋና ዋና እና ወሳኝ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ውስጥ ሙሉ በሙሉ መገለላቸውን ፔዜሽኪያን አጽንኦት ሰጥተውበታል። በዚህም ምክንያት በተፈጠረው ክፍተት የኢስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ጦር ውስጥ ያሉ ጽንፈኛ አንጃዎች የሀገሪቱን ጉዳዮች እንዲቆጣጠሩ ዕድል እንደሰጣቸው ምንጩ ጠቁሟል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ በእንዲህ ያለ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መንግስትን መምራትም ሆነ ህጋዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደማይችሉ በመግለጽ፣ በአስቸኳይ ከስልጣናቸው ለመልቀቅ መጠየቃቸውን አስታውቀዋል።
የበላይ መሪው ሞጅታባ ኻሜኒ የፕሬዝዳንቱን መልቀቂያ ይቀበሉት አይቀበሉት እስካሁን ግልጽ ባይሆንም፣ የደብዳቤው ይዘት ግን በከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ ታይቶ የማይታወቅና ጥልቅ የሆነ የስልጣን ክፍፍል  መኖሩን በግልጽ ያሳያል። ይህ ክስተት የመጣው በመንግስትና በኢስላማዊቷ ሪፐብሊክ ወታደራዊ-ደህንነት ተቋማት መካከል ለወራት የዘለቀው ውጥረት ከተቀሰቀሰ በኋላ ነው።

ኢራን ኢንተርናሽናል ቀደም ሲል እንደዘገበው፣  የኢስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ጦር የፕሬዝዳንቱን በርካታ ስልጣኖች ደረጃ በደረጃ በመገደብ ቁልፍ የመንግስት አካላትን በቁጥጥሩ ስር አውሏል። የውስጥ ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ፣ ይህ ሁኔታ የፔዜሽኪያን አስተዳደር በፖለቲካዊና አስፈፃሚ የውሳኔ ማጣት አዙሪት ውስጥ እንዲገባ ያደረገው ሲሆን፣ ይህም ዲፕሎማሲያዊ ድርድሮች ወደፊት እንዳይራመዱና በካቢኔ መዋቅር ላይ የሚፈለጉ ለውጦች እንዳይተገበሩ እንቅፋት ሆኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍6😢5😁2🤪1
"ምርጫ ጣቢያው ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ተወስኗል"

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቡርጂ የምርጫ ጣቢያ ተፈጽሟል በተባለ ሕገ-ወጥ ድርጊት ምክንያት፣ ጣቢያው ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ መወሰኑን የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ አስታወቁ።

የቦርዱ ሰብሳቢ እንደገለጹት "በቡርጂ ምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች እራሳቸው በምርጫ ጣቢያ በድምጽ መስጫ ወረቀት ላይ ምልክት እያደረጉ ድምጽ ሲሰጡ ስለተገኙ ያ ምርጫ ጣቢያ ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ቦርዱ ወስኖ ዘግቷል። ይሄን ድርጊት የፈጸሙ አስፈጻሚዎች ላይ በቀጣይ የሚወሰደውን እርምጃ በቀጣይ ያሳውቃል" ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁2416😢3👍2🤪2🥰1👏1👌1
አሳዛኝ መረጃ‼️

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ከ10 በላይ ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉ

የ101 ዓመት እድሜ ያለው የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል።

የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይም ዘረፋ የተካሄደ ሲሆን ምእመናን ጽላቱን ይዘው ተሰደዋል፤ መኖሪያ ቤታቸውም ተቃጥሏል።

ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት፣ አሰኮ ወረዳ፣ ጠላታ ጨፋ ቀበሌ እና ካራ ኩፍቴና በሚባሉ አካባቢዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ ያነጣጠረ አሰቃቂ ግድያ ተፈጽሟል።

በአሰኮ ወረዳ ጠላታ ጨፋ ቀበሌ ብቻ በታጣቂ  ኃይሎች  በተፈጸመ ሰብአዊነት በጎደለው ጥቃት ከ10 በላይ ንጹሃን ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል።

በአካባቢው 101 ዓመታትን ዕድሜ ያስቆጠረው፣ የጠላታ ጨፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወውደሙ ተገልጿል።

በተመሳሳይ ጥቃት በካራ ኩፍቴና መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት የተሰነዘረ ሲሆን፣ የቤተክርስቲያኑ ንብረት የሆኑ ቤቶች በመቃጠላቸው ምእመናን የመድኃኔዓለምን ቅዱስ ጽላት ይዘው በእግራቸው ወደሌላ አካባቢ መሸሻቸው ታውቋል።

በዚሁ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት  በሺርካ ወረዳ በሁለት ወጣት ኦርቶዶክሳውያን ላይ ዘግናኝ ግድያ መፈጸሙ ተሰምቷል።

ድርጊቱ የተፈጸመው ሚታና ዋጂ ቀበሌ ሲሆን፣ ታጣቂዎች ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ወጣቶቹ መኖሪያ ቤት በመግባት በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸውና በመቀጠልም ወጣቶቹን ወደ ሚታና ጋዶ ቀበሌ በመውሰድ፣ አንደኛውን በስለት አር ደው፣ ሁለተኛውን ደግሞ በጥይት በመምታት በጭካኔ ሕይወታቸውን እንዳጠፉት ተገልጿል።

ሕይወታቸውን ያጡት የእነዚህ ወጣቶች ሥርዓተ ቀብር ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በጋዶ ማሕደረ ስብሐት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን፣ ምዕመናንና በቤተሰብ በተገኘበት በአንድ መቃብር  ተፈጽሟል።

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በአገልጋዮችና ምእመናን ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት እንደሚፈጸምበት ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ለዓመታት መረጃ እያደረሰ ቢሆንም  ዛሬም ድረስ ዘላቂ መፍትሔ አልተገኘም።

መረጃው የማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢4818💔9😡8👍2😁1🤯1🙏1
በጎንደር የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ ውጤት መለጠፍ ተጀምሯል

በጎንደር ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ ቆጠራ ተጠናቅቆ ጊዜያዊ ውጤት መለጠፍ ተጀምሯል፡፡

በትናንትናው ዕለት በተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በጎንደር ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምጽ መስጠቱ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረት በከተማዋ በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ ቆጠራ ሂደት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ ጊዜያዊ ውጤቶችም በምርጫ ጣቢያዎቹ እየተለጠፉ ይገኛሉ፡፡

በግዛቸው ግርማዬ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁2511👍2🤔21👏1🤯1🤪1
ጸሎት በጤናችን ላይ የሚያመጣው አስገራሚ ለውጥ

በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርት ቤት ተመራማሪዎች አማካኝነት የተካሄደ አዲስ ሳይንሳዊ ጥናት እንደሚያሳየው፣ በቀን ለአምስት ደቂቃ ብቻ የሚደረግ የጸሎት ሥነ-ሥርዓት በሰዎች ላይ የሚከሰትን ከፍተኛ የሕመም ስሜትና ጭንቀትን በከፍተኛ ሁኔታ የመቀነስ አቅም አለው።

ይህ "ፕሮክሲማል ኢንተርሴሰሪ ፕሬየር (PIP)" ወይም በአካል ተገኝቶ ለሌላ ሰው ደኅንነት የሚደረግ የፊት ለፊት ጸሎት በመባል የሚታወቀው ልምምድ፣ በሙከራው ወቅት ከተሳተፉት መካከል ከሙዚቃ ማዳመጥ ይልቅ የላቀና ዘላቂ እፎይታን መስጠት መቻሉ ተረጋግጧል።

በጥናቱ ላይ የተሳተፉት ዶክተር ካትሪን ጃኮብሰን እንደገለጹት፣ ይህ የጸሎት አገልግሎት በሕክምና ተቋማት ውስጥ እንዲካተት 97% የሚሆኑት ታካሚዎች ሙሉ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
45👍3🙏2👏1
የምርጫ ውጤት‼️
በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የተረጋገጠ የመጨረሻ ውጤት ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ይፋ ይደረጋል።

ይሁን እንጂ አጠቃላይ ውጤቱ ከመታወቁ በፊት፣ ከዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በየምርጫ ጣቢያዎቹ ላይ ጊዜያዊ ውጤቶች መለጠፍ ይጀምራሉ።

በተመሳሳይ ከግንቦት 25 እስከ ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በምርጫ ክልሎች ደረጃ ጊዜያዊ ውጤቶች ይፋ እንደሚደረጉ ተገልጿል።

ምርጫ ቦርድ ከየምርጫ ክልሎቹ ውጤቶችን የመረከብ ሒደቱን ከግንቦት 26 እስከ ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ የሚያከናውን ሲሆን፣ ከምርጫው ዕለት (ግንቦት 24) ጀምሮ እስከ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት ቅሬታዎችን የመቀበልና የማስተናገድ ሥራ እንደሚሠራ አመልክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪2219👍2🤯1
በቅርቡ ወደ ሥራ የተመለሠው የትግራይ ክልል ምክር ቤት አዳዲስ ሹመቶች አፀደቀ

ከጦርነቱ በፊት ተቃቁሞ የነበረውና በቅርቡ ወደ ሥራ የተመለሠው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ሕወሃት ያቀረባቸውን የአዲስ የካቢኔ አባላት፣ የዞን አስተዳዳሪዎችና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሹመት ዛሬ ማምሻውን አጸደቀ።

የሕወሃት ምክትል ሊቀመንበር አማኑኤል አሠፋ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንትና የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ ኾነው እንደተሾሙ የክልሉ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

70 በመቶ ያህሉ የካቢኔ አባላት ከሕወሃት የተውጣጡ ሲሆኑ፣ 30 በመቶዎቹ ከተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና ከምሁራን የተውጣጡ እንደሆኑ ተገልጧል።

በተመሳሳይ፣ ወልደአብርሃ ገብረጻዲቅ የሰሜን ምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ሺሻይ ግርማይ የማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ዝናቡ ገብረመድኅን የደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ግዴይ አዘናው የምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ፍስሃ ኃይላይ የምሥራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንዲሁም ከለሊ ሐጋዚ የደቡብ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኾነው እንደተሾሙ ዘገባዎቹ ጠቅሠዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17🤪5👍2🤯1
"የጽምዶ ጥምረት" በርካታ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ቡድኖችን እያካተተ መሆኑ ተገለጠ

​በኤርትራ እና ህወሃት መካከል የተጀመረውና "ጽምዶ" (Ximdo) በመባል የሚታወቀው አዲሱ የፖለቲካ ትስስር፣ አሁን ላይ በርካታ የኢትዮጵያ የታጠቁና የፖለቲካ ተቃዋሚ ቡድኖችን ወደማካተት እየሰፋ መሄዱን አፍሪካ ኢንተለጀንስ  ዘግቧል።

📌 የአዲስ አበባውን ማዕከላዊ መንግስት የሚቃወሙት የህወሃት/ትግራይ መከላከያ ኃይል አመራሮች፣ በቅርቡ በሱዳን የወደብ ከተማ ፖርት ሱዳን ከተደረጉ የኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ከሱዳን ጦር ኃይል ተወካዮች ጋር ስብሰባ ማድረጋቸው ተረጋግጧል።

​ይህ በኤርትራ መንግስት  አስተባባሪነት እየተመራ ያለው ጥምረት የህወሃትን "የአሮጌው ጎራ ጨምሮ፣ እንደ ፋኖ  ያሉ፣ የኦብነግ የተገነጠሉ ክንፎችን እና ሌሎች ታዋቂ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን በአንድ ጥላ ስር ለማሰባሰብ እየሰራ እንደሆነ የደህንነት ምንጮች ጠቁመዋል።

​የሰሜኑ ጦርነት ወቅት ኤርትራ እና ህወሃት እርስ በእርስ የገጠሙ ደመኛ ጠላቶች የነበሩ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን "የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው" በሚለው መርህ የአዲስ አበባውን መንግስት ለመጫንና የራሳቸውን የፖለቲካ ህልውና ለማስጠበቅ ስልታዊ ህብረት ፈጥረዋል።ይህ አዲስ የሀይሎች መሸጋሸግ በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ እና በሱዳን መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ እያሻከረው ሲሆን፣ ቀጠናዊ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
39🤔4🏆4👍2👀1
የሟቾቹ ቁጥር 13 ደርሷል‼️

ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የአርሲና ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት 13 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን፣ ከ280 በላይ ምእመናን መፈናቀላቸውንና የ101 ዓመት ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉን አሳወቁ።

ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ:ም ጀምሮ በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ ወረዳ; በሺርካ ወረዳና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ 13  ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉ የ101 ዓመት እድሜ ያለው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል።

የካራ ኩፍተና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይም ዘረፋ የተካሄደ ሲሆን ምእመናን ጽላቱን ይዘው ተሰደዋል፤ መኖሪያ ቤታቸውም ተቃጥሏል።

የተገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝርም

1. አቶ ደምረው አበራ የ70 ዓመት
2. ከፈለኝ ልክየለው የ56ዓመት
3. ሐይሉ ንጉሴ የ70 ዓመት
4. እሸቴ ዳመና የ42 ዓመት
5. አበባየሁ ዳኜ የ42 ዓመት
6. ሰሙ አባይነህ የ70 ዓመት
7. 1 ሚሊሻ
8.  አማረ በላይነህ የ80 ዓመት
9.  ተሬ ደሴ የ25 ዓመት

10. ወጣት ገነነ ጥላሁን  በሽርካ ወረዳ
11. ሙርቴሳ ጥላሁን በሽርካ ወረዳ

12. አቶ ንጉሱ ማንደፍሮ በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ
13. አቶ በቀለ ኃ/ሚካኤል በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ

በአጠቃላይ የ13 ሰዎች ህይወት አልፈዋል።

በተጨማሪ በአሰኮ ወረዳ ከ280 ሰው በላይ ተፈናቅለዋል:: 
በመሆኑም ኦርቶዶክሳውያኑ ተወልደው ካደጉበት፣ ወልደው ከሳሙበት ቀያቸው በሃይማኖታቸው ብቻ ቤታቸው እየተለየ ተቃጥሏል፤ ንብረታቸውና ከብቶቻቸው ተዘርፈዋል።

ከጥቃቱ የተረፉት ነዋሪዎችም ይዘውት የሸሹት እምነታቸውንና ማንነታቸውን ብቻ በመሆኑ አሁን ላይ ሜዳ ላይ ወድቀው ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
💔38😢3115👍2🤯2🙏2🕊2🤔1
በበሻሻ የምርጫ ጣቢያ የድምፅ ቆጠራ ውጤት

በኢትዮጵያ የተካሄደው የሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ የድምፅ ቆጠራ ውጤት፣ ዛሬ ማክሰኞ ከማለዳው ጀምሮ በአብዛኞቹ የምርጫ ጣቢያዎች እየተለጠፈ ይገኛል።  በጅማ ከተማም ሆነ በዞኑ ስር በሚገኙ የምርጫ ክልሎች የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ በሰላም መጠናቀቁን የዞኑ የምርጫ አስተባባሪ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤔27🙉1511🤪10🤣6🥰3👍2👀1
ደሴ‼️
በደሴ ከተማ  የአይጥ መርዝ ለበርካታ ሰዎች  ህልፈት ምክኒያት ሆኗል ተባለ።
 
በ2018 በጀት አመት ዘጠኝ ወራት የኬሚካል መመረዝ ጉዳት ለደረሰባቸው በርካታ ሰዎች ህክምና መስጠቱን የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታውቋል።የሆስፒታሉ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሙያ አቶ ብርሃኑ አዱኛ ለብስራት ሬድዮ እንደገለፁት ሆስፒታሉ በዘጠኝ ወራት ውስጥ  የኬሚካል መመረዝ አደጋ ለደረሰባቸው 1መቶ 72 ሰዎች የህክምና አገልግሎት ሰጥቷል።
 
ከእነዚህ መካከል 6.8 በመቶ የሞት ምጣኔ መመዝገቡን ገልፀው በሆስፒታሉ በተሰራው የተቀናጀ ስራ ከመመረዝ ጋር የተያያዘ የሞት ምጣኔ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ 27.3 በመቶ ቀንሷል ብለዋል።የጉዳቱን የስርጭት መጠን አስመልክቶ 67 በመቶ የሚሆነው ከደሴ እንዲሁም 29 በመቶ የሚሆነው ደግሞ  ከደቡብ ወሎ የተከሰተ መሆኑ ተገልጿል።
 
እነዚህ አካባቢዎች በኬሚካል መመረዝ በከፍተኛ ሁኔታ የተጠቁ የማህበረሰብ ክፍሎች መገኛ  መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ ብርሀኑ በሆስፒታሉ አስፈላጊውን ህክምና እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል።86.5 በመቶ የሚሆኑት ራሳቸውን ለማጥፋት በሚል ህብረተሰቡ አይጥን ለመግደል የሚጠቀምባቸውን መርዞች  የተጠቀሙ  ናቸው።
 
የመርዝ ዓይነቶች ትንታኔ እንደሚያሳየው የአይጥ መመረዝ 35.9 በመቶ ፣ የመድኃኒት መመረዝ 17.6 በመቶ እንዲሁም የበረኪና መመረዝ ደግሞ 15.3 በመቶ ድርሻን ይይዛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21😢6👍3🤯2🙏1👀1
የኢትዮጵያ መርከብ የሆርሙዝ ሰርጥን በሰላም መሻገሯ ተሰማ

በመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ምክንያት ከፍተኛ ስጋት በነበረበት የሆርሙዝ ሰርጥ አካባቢ፣ የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ንብረት የሆነችው “አሶሳ” መርከብ ከሆርሙዝ ሰርጥ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ኮርፋካን ወደብ በመድረስ ወሳኝ የሕክምና እና የንግድ ጭነቶችን በተሳካ ሁኔታ ጭና ወደ ሀገሯ ተመልሳለች።

ይህ ስኬት የኢትዮጵያን ባሕረኞች ቁርጠኝነት እና የኢትዮጵያን የባሕር ሎጅስቲክስ ብቃት በተግባር ያሳየ ነው ተብሎለታለ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁4138👍5👏2🤯2🤩2🙏2👌1💋1🤝1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የአሜሪካ መንግስት በአፍሪካ የቪዛ አገልግሎት መስጫ ቦታዎችን ወደ 20 ብቻ ሊቀንስ ነው‼️

👉 አዲስ አበባ አገልግሎቷን እንደምትቀጥል ተረጋግጧል

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአፍሪካ አህጉር የሚገኙ የቪዛ ማስተናገጃ ማዕከላቱን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ መወሰኑን ይፋ አደረገ።

ይህ አዲስ መመሪያ የትራምፕ አስተዳደር በስደት ላይ የጀመረውን ጠንካራ የቁጥጥር ፖሊሲ ይበልጥ ለማጥበቅ ከሚያደርገው ጥረት ጋር የተያያዘ ነው።

እስካሁን ድረስ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ወደ 50 የሚጠጉ የአሜሪካ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች የቪዛ ማመልከቻዎችን ሲቀበሉ የነበረ ቢሆንም፣ አዲሱ እቅድ ይህንን ቁጥር ወደ 20 "ማዕከላት" ብቻ ዝቅ የሚያደርግ ይሆናል።

እንደ አሶሺየትድ ፕሬስ ዘገባ እና ከውስጥ ባለስልጣናት በተገኘ መረጃ መሠረት፣ ይሄው አሰራር በሚቀጥሉት ሳምንታት (በሰኔ ወር ውስጥ) ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ በፀደቀው በዚህ መመሪያ መሠረት፣ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ሙሉ የቪዛ አገልግሎት መስጠቷን እንድትቀጥል ከተመረጡት 20 ጥቂት ማዕከላት መካከል አንዷ ሆናለች።

ይህም ማለት በኢትዮጵያ የሚገኙ አመልካቾች ያለምንም እንግልት መደበኛ የቪዛ አገልግሎታቸውን ከአዲስ አበባ ማግኘት ይችላሉ።

ይሁን እንጂ ይህ ውሳኔ ማዕከል ባልሆኑ ሀገራት ዜጎች ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚና የጉዞ ጫና ያሳድራል።

በእነዚህ ሀገራት የሚገኙ የአሜሪካ ቆንስላዎች መደበኛ የቪዛ አገልግሎት መስጠታቸውን የሚያቆሙ በመሆኑ፣ ዜጎቹ ቪዛ ለማግኘት ድንበር አቋርጠው አዲስ አበባን ወደመሳሰሉ የቪዛ ማዕከላት ለመጓዝ ይገደዳሉ። ይህም ተጨማሪ የጉዞ ወጪን እና የጊዜ መዘግየትን ያስከትላል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አገልግሎታቸው በሚቀነስባቸው ሀገራት የሚገኙ ኤምባሲዎች ሙሉ በሙሉ የማይዘጉ ሲሆን፣ ለአሜሪካ ዜጎች የሚሰጡ ድንገተኛ ድጋፎችን እና ልዩ የዲፕሎማቲክ ጉዳዮችን ማስተናገዳቸውን ይቀጥላሉ ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍5🙈1
የቻይናው መከላከያ ተቋም “የአሜሪካን ድብቅ ተዋጊ አውሮፕላኖች በኤአይ (AI) መከታተል ችያለሁ” ማለቱ መነጋገሪያ ሆኗል
 
አንድ ጂንጋን (Jingan) የተሰኘ የቻይና የግል መከላከያ ቴክኖሎጂ ተቋም፣ በቅርቡ በኢራን ግጭት ወቅት “ጂንግቺ” በተሰኘው የሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI) የጦርነት ክትትል ስርዓቱ አማካኝነት አራት የአሜሪካ “ቢ-2 ስፒሪት” (B-2 Spirit) ድብቅ ስውር ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖችን መከታተል መቻሉን ገለጸ።
 
የቴክኖሎጂ ተቋሙ አውሮፕላኖቹ “ፔትሮ 41 እስከ 44” (Petro 41 to 44) በሚሉ የመገናኛ ኮዶች ሲንቀሳቀሱ እንደነበር የጠቀሰ ሲሆን፣ ከአውሮፕላኖቹ የወጡ የሬዲዮ ሞገዶችን በመጥለፍ እና በኤአይ (AI) አማካኝነት የበረራ መስመራቸውን መልሶ መገንባት መቻሉን ተናግሯል። ይሁን እንጂ ተቋሙ ይህንን አስገራሚ ክስ የሚያረጋግጥ እስካሁን ያቀረበው ምንም ዓይነት ተጨባጭ ማስረጃ የለም።
 
እንደ ጂንጋን ገለጻ ከሆነ፣ ስርአቱ ግጭቱ ከመቀስቀሱ ሳምንታት በፊት የሳተላይት ምስሎችን፣ የበረራ መረጃዎችን እና ግልጽ የሆኑ የመረጃ ምንጮችን (open-source intelligence) በማቀናጀት በኢራን አቅራቢያ እያደገ የመጣውን የአሜሪካ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ቀድሞ መለየት ችሎ ነበር። ተቋሙ አራቱ የቢ-2 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች የተከታተላቸው አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ኢላማዎች ላይ ጥቃት ከሰነዘሩ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ መሆኑን አስታውቋል።
 
ይሁን እንጂ ይህ የቻይናው ተቋም ይፋ ያደረገው መረጃ በተናጠል በገለልተኛ ወገን ያልተረጋገጠ ሲሆን፣ እጅግ ዘመናዊ እና በራዳር እንዳይታዩ ተደርገው የተሰሩት ስውር አውሮፕላኖች ተለይተው ስለመገኘታቸው የሚገልጸው ዘገባ እስካሁን ድረስ በማስረጃ አልተደገፈም።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19👍10🤣3🤔2