አዲስ ሪፖርተር - NEWS
35.8K subscribers
16.9K photos
414 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ከትግራይ ክልል በስተቀር በመላ አገሪቱ በሚካሄደው ሰባተኛው አገራዊ ምርጫ ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ድምጽ መስጠት ተጀምሯል‼️

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ እና በአማራ ክልል ደግሞ በተወሰኑ አካባቢዎች ምርጫው በዛሬው ዕለት እንደማይካሄድ ቀደም ብሎ አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😡15🤷‍♂149👍2😁2👏1🙏1🤪1
በቦንብ ጥቃት ሁለት ሰዎች ተጎዱ‼️
በትናንትናው ዕለት ግንቦት 23/2018 ዓ.ም በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ ራስ አሊ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 06 ጎንደር በር ኖክ ማደያ ፊት ለፊት ከቀኑ 6:00 አካባቢ በአንድ ባጃጅ ላይ የተጠመደ ቦንብ ፈንድቶ ሁለት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
💔108😢6😡4👍2😱1👀1
143 የምርጫ ጣቢያዎች አልተከፈቱም‼️
በጸጥታ ችግር ምክንያት 143 የምርጫ ጣቢያዎች በዛሬው ዕለት አለመከፈታቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል “በተወሰኑ ቦታዎች” የድምጽ መስጠት ሂደቱ ከተጀመረ በኋላ የተቋረጠባቸው የምርጫ ጣቢያዎች እንዳሉም ቦርዱ ገልጿል።

ቦርዱ ይህን ያስታወቀው ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24፤ 2018 ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ያለውን ሰባተኛ ጠቅላላ ምርጫ በተመለከተ በሰጠው መግለጫ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁30👍98🙏2🙈2🤪2👀1
ታዛቢዎቼ ተደብድበዋል-ጎጎት‼️
#የምርጫ ታዛቢዎች ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ጎጎት ፓርቲ ከሰሰ!!!

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ወልቂጤ ምርጫ ጣቢያ የምርጫ ታዛቢዎች ተደብድበው ከምርጫ እንዲወጡ ተደርገዋል ሲል ጎጎት ፓረቲ ገለጸ። ፓረቲው በኦፊሸል የፌስ ቡክ ገጹ እንዳብራራው “ፓርቲዉ ይንቀሳቀስበት የነበረዉ ሞተር ተነጥቋል።

የምርጫ ወረቀት በፌስታል ይዘዉ ሲበትኑ ተመልክተናል። ለምርጫ ቦርድ ምርጫው እንዲቆም አሳዉቀናል” ብሎ፣ከምርጫ ቦርድ አፍጣኝ ምላሽ እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡
በስፍራው የምትገኘው የሪፖርተር ዘጋቢ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ምርጫ አስተባባሪ አቶ ነጋሽን አነጋግራቸው በሰጡት ምላሽ፣ ጎጎት ፓርቲ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ወልቂጤ ከተማ ምርጫ ጣቢያ የምርጫ  ታዛቢዎች ተደብድበው ከምርጫ እንዲወጡ ተደርገዋል ማለቱን ተከትሎ ወደ ቦታው አስተባባሪዎች ልከው  እንዳጣሩና ምንም ነገር እንዳልተደረገ ማረጋገጣቸውንተናግረዋል፡፡

ፓርቲው ይህ ሆኗል ባለበት የምርጫ ጣቢያ ሁለት ታዛቢዎቹ እንደነበሩ የገለጹት ዋና አስተባባሪው፣ ፓርቲው የተናገረው  ከእውነት የራቀ መሆኑን አክለዋል። ሌላው ሱልካ በተባለ ጣቢያ አካባቢ የፓርቲው ታዛቢ ባጅ ስለተጠየቀ አኩርፎ ከመውጣቱ ውጭ ሌላ  የተፈጠረ ነገር እንደሌለም አስረድተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🙊147👍4😁3😢1👀1
ቀይ ባህርን እዘጋለሁ-ኢራን‼️
ኢራን ከአሜሪካ ተደራዳሪዎች ጋር በተዘዋዋሪ (indirectly) የምታደርገውን ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ ማቋረጧን አስታወቀች።

ኢራን ይህንን እርምጃ የወሰደችው እስራኤል በሊባኖስ እና ጋዛ የምታደርገው ጥቃት ባለመቆሙ ምክንያት መሆኑን የሀገሪቱ የዜና ወኪል የሆነው ታስኒም ኒውስ ዘግቧል።

እስራኤል በሊባኖስ እና በጋዛ የምታደርገውን ጥቃት ካልቆመች ኢራን የሆርሙዝ ባህርን እና የቀይ ባህር ዋነኛ መተላለፊያ የሆነውን የባብ አል ማንዳብ ሰርጥን ሙሉ በሙሉ እንደምትዘጋ ዝታለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍247😁7🤣4👀1
⁉️ የምስራቁ ጦርነት የኑሮአችንን ዋጋ እንዴት እያናጋው ነው? 💥

🚨የኃያላን መንግስታት ፍጥጫ እና የድንበር ጦርነቶች ከሩቅ የሚታዩ የዜና አርዕስቶች ብቻ አይደሉም፤ የኢትዮጵያን ገበያ እና የኪሳችንን አቅም በቀጥታ የሚፈትኑ ማዕበሎች እንጂ።

የሀገር ውስጥ ወቅታዊ ፈተናዎችን እና አጠቃላይ የአህጉራችንን እና የዓለምን ዜናዎች አቀናጅቶ የሚያቀርብላችሁን ስፑትኒክን አሁኑኑ ይከተሉ 👇
🔗 https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy
📣 @sputnik_ethiopia
6
<<የምርጫ አስፈጻሚዎች መራጮቾችን ቶሎ ቶሎ ማስተናገድ እንዳለባቸው ተናግሪያለሁ>> ካሙዙ ካሳ

ብልጽግናን የወከለውና በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ምርጫ ክልል 11/4 ቤተሰብ ሆቴል ምርጫ ጣቢያ የሚወዳደረው ካሙዙ ካሳ፣ የምርጫውን ሒደት አስመልክቶ ለሪፖርተር አስተያይቱን ሰጥቷል።

<<የምርጫ አስፈጻሚዎች መራጮቾችን ቶሎ ቶሎ ማስተናገድ እንዳለባቸው ተናግሪያለሁ>> ሲል ሙዚቃ አቀናባሪው ካሙዙ ካሳ ተናግሯል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣49🤪2612👍2😁2
ጦርነቱ ሊያገረሽ ይችላል‼️
ኢራን የሰሜን እስራኤል ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ አስጠነቀቀች - Mehr news‼️
'መጎዳት ካልፈለጉ በአስቸኳይ ለቀው ይውጡ ብላለች።

' ኔታንያሁ በደቡባዊ ቤሩት ሰፈሮች ላይ የቦምብ ጥቃት ለመፈፀም የአካባቢው ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ ከላይ በምስል እንደሚታየው የደቡባዊ ሊባኖስ ዜጎች አካባቢውን ለቀው እየወጡ ነው።

ይህንን ተከትሎ ኢራን በእስራኤል ላይ አደገኛ ጥቃት እከፍታለሁ ብላለች።

ትራምፕ እና ኔታንያሁ ከደቂቃዎች በፊት በስልክ መወያየታቸውን የእስራኤል ሚዲያዎች ዘግበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍6😁5🥰1👏1😢1💯1👀1
የማስታወቂያ ግብዣ

የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል
Youtube ቻናል …
የትምህርት ተቋማት…...
የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
የትራንስፖርት አገልግሎት…....
ኤጀንሲዎች……
ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot
7👍2
ትምህርት ቤቶች አይዘጉም‼️
"ትምህርት ቤቶች እስከ ረቡዕ ዝግ ይሆናሉ" በሚል በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ ተገለጸ።

"ከነገ ጀምሮ ሁሉም መደበኛ ስራዎች ይቀጥላሉ" ምርጫ ቦርድ
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዛሬ ግንቦት 24/2018 ከማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል።

በዚህም መሠረት በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ሁሉ ድምፃቸውን ለመስጠት ይችሉ ዘንድ እና የደምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር ይከናወን ዘንድ ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ እንዲጠቀሙ የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት ከሚሰጡ ተቋማት በስተቀር በፌዴራል እና በክልሎች የሚገኙ ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑ እና የግል ተቋማት ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ብቻ ዝግ እንዲያደርጉ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ይታወቃል::

በዚህም መሰረት ከነገ ማክሰኞ ዕለት ጀምሮ መደበኛ የመንግስትና የግል ተቋማት ስራ እንደሚቀጥል ቦርዱ አመልክቷል።

በአንዳድ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች "ትምህርት ቤቶች እስከ ረቡዕ ዝግ ይሆናሉ" ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍5👀3🙉3🥰1
አንድ የፓሪስ ሴንት ጀርመን ደጋፊ በአዉሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ጋብሬል ማጋሌሽ የሳታትን የፍጹም ቅጣት ምት በግራ እግሩ ላይ ተነቅሶታል።

የማይታመን ነዉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁41🙉54👍3🤪1
መረጃ‼️

ከጦርነቱ በፊት ተቃቁሞ የነበረውና በቅርቡ ወደ ሥራ የተመለሠው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ሕወሃት ያቀረባቸውን የአዲስ የካቢኔ አባላት፣ የዞን አስተዳዳሪዎችና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሹመት ዛሬ ማምሻውን አጸደቀ።

የሕወሃት ምክትል ሊቀመንበር አማኑኤል አሠፋ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንትና የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ ኾነው እንደተሾሙ የክልሉ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

70 በመቶ ያህሉ የካቢኔ አባላት ከሕወሃት የተውጣጡ ሲሆኑ፣ 30 በመቶዎቹ ከተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና ከምሁራን የተውጣጡ እንደሆኑ ተገልጧል።

በተመሳሳይ፣ ወልደአብርሃ ገብረጻዲቅ የሰሜን ምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ሺሻይ ግርማይ የማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ዝናቡ ገብረመድኅን የደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ግዴይ አዘናው የምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ፍስሃ ኃይላይ የምሥራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንዲሁም ከለሊ ሐጋዚ የደቡብ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኾነው እንደተሾሙ ዘገባዎቹ ጠቅሠዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
22😁10👍2🤯2👏1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የኢራኑ ፕሬዚዳንት የስራ
መልቀቂያ ማቅረባቸው ተሰማ


የኢራኑ ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ለሀገሪቱ የበላይ መሪ ጽህፈት ቤት ይፋዊ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ለጉዳዩ ቅርብ የሆነ ምንጭ ለኢራን ኢንተርናሽናል ገልጧል። እሁድ ዕለት በተላከው በዚህ ደብዳቤ ላይ ፕሬዝዳንቱና መንግስታቸው በሀገሪቱ ዋና ዋና እና ወሳኝ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ውስጥ ሙሉ በሙሉ መገለላቸውን ፔዜሽኪያን አጽንኦት ሰጥተውበታል። በዚህም ምክንያት በተፈጠረው ክፍተት የኢስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ጦር ውስጥ ያሉ ጽንፈኛ አንጃዎች የሀገሪቱን ጉዳዮች እንዲቆጣጠሩ ዕድል እንደሰጣቸው ምንጩ ጠቁሟል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ በእንዲህ ያለ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መንግስትን መምራትም ሆነ ህጋዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደማይችሉ በመግለጽ፣ በአስቸኳይ ከስልጣናቸው ለመልቀቅ መጠየቃቸውን አስታውቀዋል።
የበላይ መሪው ሞጅታባ ኻሜኒ የፕሬዝዳንቱን መልቀቂያ ይቀበሉት አይቀበሉት እስካሁን ግልጽ ባይሆንም፣ የደብዳቤው ይዘት ግን በከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ ታይቶ የማይታወቅና ጥልቅ የሆነ የስልጣን ክፍፍል  መኖሩን በግልጽ ያሳያል። ይህ ክስተት የመጣው በመንግስትና በኢስላማዊቷ ሪፐብሊክ ወታደራዊ-ደህንነት ተቋማት መካከል ለወራት የዘለቀው ውጥረት ከተቀሰቀሰ በኋላ ነው።

ኢራን ኢንተርናሽናል ቀደም ሲል እንደዘገበው፣  የኢስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ጦር የፕሬዝዳንቱን በርካታ ስልጣኖች ደረጃ በደረጃ በመገደብ ቁልፍ የመንግስት አካላትን በቁጥጥሩ ስር አውሏል። የውስጥ ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ፣ ይህ ሁኔታ የፔዜሽኪያን አስተዳደር በፖለቲካዊና አስፈፃሚ የውሳኔ ማጣት አዙሪት ውስጥ እንዲገባ ያደረገው ሲሆን፣ ይህም ዲፕሎማሲያዊ ድርድሮች ወደፊት እንዳይራመዱና በካቢኔ መዋቅር ላይ የሚፈለጉ ለውጦች እንዳይተገበሩ እንቅፋት ሆኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍6😢5😁2🤪1
"ምርጫ ጣቢያው ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ተወስኗል"

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቡርጂ የምርጫ ጣቢያ ተፈጽሟል በተባለ ሕገ-ወጥ ድርጊት ምክንያት፣ ጣቢያው ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ መወሰኑን የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ አስታወቁ።

የቦርዱ ሰብሳቢ እንደገለጹት "በቡርጂ ምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች እራሳቸው በምርጫ ጣቢያ በድምጽ መስጫ ወረቀት ላይ ምልክት እያደረጉ ድምጽ ሲሰጡ ስለተገኙ ያ ምርጫ ጣቢያ ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ቦርዱ ወስኖ ዘግቷል። ይሄን ድርጊት የፈጸሙ አስፈጻሚዎች ላይ በቀጣይ የሚወሰደውን እርምጃ በቀጣይ ያሳውቃል" ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁2416😢3👍2🤪2🥰1👏1👌1
አሳዛኝ መረጃ‼️

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ከ10 በላይ ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉ

የ101 ዓመት እድሜ ያለው የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል።

የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይም ዘረፋ የተካሄደ ሲሆን ምእመናን ጽላቱን ይዘው ተሰደዋል፤ መኖሪያ ቤታቸውም ተቃጥሏል።

ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት፣ አሰኮ ወረዳ፣ ጠላታ ጨፋ ቀበሌ እና ካራ ኩፍቴና በሚባሉ አካባቢዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ ያነጣጠረ አሰቃቂ ግድያ ተፈጽሟል።

በአሰኮ ወረዳ ጠላታ ጨፋ ቀበሌ ብቻ በታጣቂ  ኃይሎች  በተፈጸመ ሰብአዊነት በጎደለው ጥቃት ከ10 በላይ ንጹሃን ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል።

በአካባቢው 101 ዓመታትን ዕድሜ ያስቆጠረው፣ የጠላታ ጨፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወውደሙ ተገልጿል።

በተመሳሳይ ጥቃት በካራ ኩፍቴና መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት የተሰነዘረ ሲሆን፣ የቤተክርስቲያኑ ንብረት የሆኑ ቤቶች በመቃጠላቸው ምእመናን የመድኃኔዓለምን ቅዱስ ጽላት ይዘው በእግራቸው ወደሌላ አካባቢ መሸሻቸው ታውቋል።

በዚሁ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት  በሺርካ ወረዳ በሁለት ወጣት ኦርቶዶክሳውያን ላይ ዘግናኝ ግድያ መፈጸሙ ተሰምቷል።

ድርጊቱ የተፈጸመው ሚታና ዋጂ ቀበሌ ሲሆን፣ ታጣቂዎች ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ወጣቶቹ መኖሪያ ቤት በመግባት በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸውና በመቀጠልም ወጣቶቹን ወደ ሚታና ጋዶ ቀበሌ በመውሰድ፣ አንደኛውን በስለት አር ደው፣ ሁለተኛውን ደግሞ በጥይት በመምታት በጭካኔ ሕይወታቸውን እንዳጠፉት ተገልጿል።

ሕይወታቸውን ያጡት የእነዚህ ወጣቶች ሥርዓተ ቀብር ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በጋዶ ማሕደረ ስብሐት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን፣ ምዕመናንና በቤተሰብ በተገኘበት በአንድ መቃብር  ተፈጽሟል።

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በአገልጋዮችና ምእመናን ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት እንደሚፈጸምበት ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ለዓመታት መረጃ እያደረሰ ቢሆንም  ዛሬም ድረስ ዘላቂ መፍትሔ አልተገኘም።

መረጃው የማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢4818💔9😡8👍2😁1🤯1🙏1
በጎንደር የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ ውጤት መለጠፍ ተጀምሯል

በጎንደር ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ ቆጠራ ተጠናቅቆ ጊዜያዊ ውጤት መለጠፍ ተጀምሯል፡፡

በትናንትናው ዕለት በተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በጎንደር ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምጽ መስጠቱ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረት በከተማዋ በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ ቆጠራ ሂደት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ ጊዜያዊ ውጤቶችም በምርጫ ጣቢያዎቹ እየተለጠፉ ይገኛሉ፡፡

በግዛቸው ግርማዬ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁2511👍2🤔21👏1🤯1🤪1
ጸሎት በጤናችን ላይ የሚያመጣው አስገራሚ ለውጥ

በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርት ቤት ተመራማሪዎች አማካኝነት የተካሄደ አዲስ ሳይንሳዊ ጥናት እንደሚያሳየው፣ በቀን ለአምስት ደቂቃ ብቻ የሚደረግ የጸሎት ሥነ-ሥርዓት በሰዎች ላይ የሚከሰትን ከፍተኛ የሕመም ስሜትና ጭንቀትን በከፍተኛ ሁኔታ የመቀነስ አቅም አለው።

ይህ "ፕሮክሲማል ኢንተርሴሰሪ ፕሬየር (PIP)" ወይም በአካል ተገኝቶ ለሌላ ሰው ደኅንነት የሚደረግ የፊት ለፊት ጸሎት በመባል የሚታወቀው ልምምድ፣ በሙከራው ወቅት ከተሳተፉት መካከል ከሙዚቃ ማዳመጥ ይልቅ የላቀና ዘላቂ እፎይታን መስጠት መቻሉ ተረጋግጧል።

በጥናቱ ላይ የተሳተፉት ዶክተር ካትሪን ጃኮብሰን እንደገለጹት፣ ይህ የጸሎት አገልግሎት በሕክምና ተቋማት ውስጥ እንዲካተት 97% የሚሆኑት ታካሚዎች ሙሉ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
45👍3🙏2👏1
የምርጫ ውጤት‼️
በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የተረጋገጠ የመጨረሻ ውጤት ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ይፋ ይደረጋል።

ይሁን እንጂ አጠቃላይ ውጤቱ ከመታወቁ በፊት፣ ከዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በየምርጫ ጣቢያዎቹ ላይ ጊዜያዊ ውጤቶች መለጠፍ ይጀምራሉ።

በተመሳሳይ ከግንቦት 25 እስከ ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በምርጫ ክልሎች ደረጃ ጊዜያዊ ውጤቶች ይፋ እንደሚደረጉ ተገልጿል።

ምርጫ ቦርድ ከየምርጫ ክልሎቹ ውጤቶችን የመረከብ ሒደቱን ከግንቦት 26 እስከ ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ የሚያከናውን ሲሆን፣ ከምርጫው ዕለት (ግንቦት 24) ጀምሮ እስከ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት ቅሬታዎችን የመቀበልና የማስተናገድ ሥራ እንደሚሠራ አመልክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪2219👍2🤯1
በቅርቡ ወደ ሥራ የተመለሠው የትግራይ ክልል ምክር ቤት አዳዲስ ሹመቶች አፀደቀ

ከጦርነቱ በፊት ተቃቁሞ የነበረውና በቅርቡ ወደ ሥራ የተመለሠው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ሕወሃት ያቀረባቸውን የአዲስ የካቢኔ አባላት፣ የዞን አስተዳዳሪዎችና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሹመት ዛሬ ማምሻውን አጸደቀ።

የሕወሃት ምክትል ሊቀመንበር አማኑኤል አሠፋ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንትና የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ ኾነው እንደተሾሙ የክልሉ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

70 በመቶ ያህሉ የካቢኔ አባላት ከሕወሃት የተውጣጡ ሲሆኑ፣ 30 በመቶዎቹ ከተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና ከምሁራን የተውጣጡ እንደሆኑ ተገልጧል።

በተመሳሳይ፣ ወልደአብርሃ ገብረጻዲቅ የሰሜን ምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ሺሻይ ግርማይ የማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ዝናቡ ገብረመድኅን የደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ግዴይ አዘናው የምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ፍስሃ ኃይላይ የምሥራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንዲሁም ከለሊ ሐጋዚ የደቡብ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኾነው እንደተሾሙ ዘገባዎቹ ጠቅሠዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17🤪5👍2🤯1