አዲስ ሪፖርተር - NEWS
35.8K subscribers
16.9K photos
414 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የትናንቷን ኢትዮጵያ የዛሬ 5 ዓመት አናያትም-አብይ አህመድ

“እኔን ዛሬ የሚያሳስበኝ መራጩ ሳይሆን ተመራጩ ነው” ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፃቸውን ለመስጠት በበሻሻ ጎማ ሁለት ሀሮ ምርጫ ጣቢያ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) አሁን ላይ እሳቸውን የሚያሳስባቸው ጉዳይ መራጩ ህዝብ ሳይሆን የተመራጩ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ድምፃቸውን ከሰጡ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ማህበረሰቡ እጩዎችን ከመረጠ በኋላ የተመረጡ ሰዎች ህዝቡ በጠበቃቸው ልክ በመታመን “እጃቸው ልባቸው ንፁህ ሁነው ደከመን ታከተን ሳይሉ ይሄን አገር ታሪክ የሚቀይሩ እና እና የህዝቡን ውለታ ለመክፈል ዝጁነታቸው ምን ያህል ነው ?” ሲሉ የጠየቁ ሲሆን እልህ ቁጣ ክርክር አሸንፋለሁ እና እሸነፋለሁ ሳይሆን ያመነን ህዝብ እንደት አገለግላለሁ፣ ህይወቱን እቀይራለሁ የሚለው ነው ሲሉ ጠቅላዩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የትናንቷን ኢትዮጵያ የዛሬ አምስት ዓመት አናያትም፤ የተለየች የበለጸገች ሀገር ማየት ደግሞ የሁሉም ኃላፊነት ነው” ብለዋል።

ይህ ምርጫ በሰላም እንዳይጠናቀቅ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የሚዘውሯቸው ኃይሎች በስፋት ሲሠሩ ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ “ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማድረግ አይቻልም” እያሉ ብዙ ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁2721👍3😢2🤪2😡2💔1
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ድምጽ ሰጥተዋል

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ጄነራል ጃጋማ ኬሎ ምርጫ ጣቢያ ድምጽ ሰጥተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣32👍10🤪83😡2👏1🤔1🌭1
ከትግራይ ክልል በስተቀር በመላ አገሪቱ በሚካሄደው ሰባተኛው አገራዊ ምርጫ ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ድምጽ መስጠት ተጀምሯል‼️

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ እና በአማራ ክልል ደግሞ በተወሰኑ አካባቢዎች ምርጫው በዛሬው ዕለት እንደማይካሄድ ቀደም ብሎ አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😡15🤷‍♂149👍2😁2👏1🙏1🤪1
በቦንብ ጥቃት ሁለት ሰዎች ተጎዱ‼️
በትናንትናው ዕለት ግንቦት 23/2018 ዓ.ም በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ ራስ አሊ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 06 ጎንደር በር ኖክ ማደያ ፊት ለፊት ከቀኑ 6:00 አካባቢ በአንድ ባጃጅ ላይ የተጠመደ ቦንብ ፈንድቶ ሁለት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
💔108😢6😡4👍2😱1👀1
143 የምርጫ ጣቢያዎች አልተከፈቱም‼️
በጸጥታ ችግር ምክንያት 143 የምርጫ ጣቢያዎች በዛሬው ዕለት አለመከፈታቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል “በተወሰኑ ቦታዎች” የድምጽ መስጠት ሂደቱ ከተጀመረ በኋላ የተቋረጠባቸው የምርጫ ጣቢያዎች እንዳሉም ቦርዱ ገልጿል።

ቦርዱ ይህን ያስታወቀው ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24፤ 2018 ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ያለውን ሰባተኛ ጠቅላላ ምርጫ በተመለከተ በሰጠው መግለጫ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁30👍98🙏2🙈2🤪2👀1
ታዛቢዎቼ ተደብድበዋል-ጎጎት‼️
#የምርጫ ታዛቢዎች ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ጎጎት ፓርቲ ከሰሰ!!!

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ወልቂጤ ምርጫ ጣቢያ የምርጫ ታዛቢዎች ተደብድበው ከምርጫ እንዲወጡ ተደርገዋል ሲል ጎጎት ፓረቲ ገለጸ። ፓረቲው በኦፊሸል የፌስ ቡክ ገጹ እንዳብራራው “ፓርቲዉ ይንቀሳቀስበት የነበረዉ ሞተር ተነጥቋል።

የምርጫ ወረቀት በፌስታል ይዘዉ ሲበትኑ ተመልክተናል። ለምርጫ ቦርድ ምርጫው እንዲቆም አሳዉቀናል” ብሎ፣ከምርጫ ቦርድ አፍጣኝ ምላሽ እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡
በስፍራው የምትገኘው የሪፖርተር ዘጋቢ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ምርጫ አስተባባሪ አቶ ነጋሽን አነጋግራቸው በሰጡት ምላሽ፣ ጎጎት ፓርቲ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ወልቂጤ ከተማ ምርጫ ጣቢያ የምርጫ  ታዛቢዎች ተደብድበው ከምርጫ እንዲወጡ ተደርገዋል ማለቱን ተከትሎ ወደ ቦታው አስተባባሪዎች ልከው  እንዳጣሩና ምንም ነገር እንዳልተደረገ ማረጋገጣቸውንተናግረዋል፡፡

ፓርቲው ይህ ሆኗል ባለበት የምርጫ ጣቢያ ሁለት ታዛቢዎቹ እንደነበሩ የገለጹት ዋና አስተባባሪው፣ ፓርቲው የተናገረው  ከእውነት የራቀ መሆኑን አክለዋል። ሌላው ሱልካ በተባለ ጣቢያ አካባቢ የፓርቲው ታዛቢ ባጅ ስለተጠየቀ አኩርፎ ከመውጣቱ ውጭ ሌላ  የተፈጠረ ነገር እንደሌለም አስረድተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🙊147👍4😁3😢1👀1
ቀይ ባህርን እዘጋለሁ-ኢራን‼️
ኢራን ከአሜሪካ ተደራዳሪዎች ጋር በተዘዋዋሪ (indirectly) የምታደርገውን ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ ማቋረጧን አስታወቀች።

ኢራን ይህንን እርምጃ የወሰደችው እስራኤል በሊባኖስ እና ጋዛ የምታደርገው ጥቃት ባለመቆሙ ምክንያት መሆኑን የሀገሪቱ የዜና ወኪል የሆነው ታስኒም ኒውስ ዘግቧል።

እስራኤል በሊባኖስ እና በጋዛ የምታደርገውን ጥቃት ካልቆመች ኢራን የሆርሙዝ ባህርን እና የቀይ ባህር ዋነኛ መተላለፊያ የሆነውን የባብ አል ማንዳብ ሰርጥን ሙሉ በሙሉ እንደምትዘጋ ዝታለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍247😁7🤣4👀1
⁉️ የምስራቁ ጦርነት የኑሮአችንን ዋጋ እንዴት እያናጋው ነው? 💥

🚨የኃያላን መንግስታት ፍጥጫ እና የድንበር ጦርነቶች ከሩቅ የሚታዩ የዜና አርዕስቶች ብቻ አይደሉም፤ የኢትዮጵያን ገበያ እና የኪሳችንን አቅም በቀጥታ የሚፈትኑ ማዕበሎች እንጂ።

የሀገር ውስጥ ወቅታዊ ፈተናዎችን እና አጠቃላይ የአህጉራችንን እና የዓለምን ዜናዎች አቀናጅቶ የሚያቀርብላችሁን ስፑትኒክን አሁኑኑ ይከተሉ 👇
🔗 https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy
📣 @sputnik_ethiopia
6
<<የምርጫ አስፈጻሚዎች መራጮቾችን ቶሎ ቶሎ ማስተናገድ እንዳለባቸው ተናግሪያለሁ>> ካሙዙ ካሳ

ብልጽግናን የወከለውና በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ምርጫ ክልል 11/4 ቤተሰብ ሆቴል ምርጫ ጣቢያ የሚወዳደረው ካሙዙ ካሳ፣ የምርጫውን ሒደት አስመልክቶ ለሪፖርተር አስተያይቱን ሰጥቷል።

<<የምርጫ አስፈጻሚዎች መራጮቾችን ቶሎ ቶሎ ማስተናገድ እንዳለባቸው ተናግሪያለሁ>> ሲል ሙዚቃ አቀናባሪው ካሙዙ ካሳ ተናግሯል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣49🤪2612👍2😁2
ጦርነቱ ሊያገረሽ ይችላል‼️
ኢራን የሰሜን እስራኤል ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ አስጠነቀቀች - Mehr news‼️
'መጎዳት ካልፈለጉ በአስቸኳይ ለቀው ይውጡ ብላለች።

' ኔታንያሁ በደቡባዊ ቤሩት ሰፈሮች ላይ የቦምብ ጥቃት ለመፈፀም የአካባቢው ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ ከላይ በምስል እንደሚታየው የደቡባዊ ሊባኖስ ዜጎች አካባቢውን ለቀው እየወጡ ነው።

ይህንን ተከትሎ ኢራን በእስራኤል ላይ አደገኛ ጥቃት እከፍታለሁ ብላለች።

ትራምፕ እና ኔታንያሁ ከደቂቃዎች በፊት በስልክ መወያየታቸውን የእስራኤል ሚዲያዎች ዘግበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍6😁5🥰1👏1😢1💯1👀1
የማስታወቂያ ግብዣ

የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል
Youtube ቻናል …
የትምህርት ተቋማት…...
የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
የትራንስፖርት አገልግሎት…....
ኤጀንሲዎች……
ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot
7👍2
ትምህርት ቤቶች አይዘጉም‼️
"ትምህርት ቤቶች እስከ ረቡዕ ዝግ ይሆናሉ" በሚል በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ ተገለጸ።

"ከነገ ጀምሮ ሁሉም መደበኛ ስራዎች ይቀጥላሉ" ምርጫ ቦርድ
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዛሬ ግንቦት 24/2018 ከማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል።

በዚህም መሠረት በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ሁሉ ድምፃቸውን ለመስጠት ይችሉ ዘንድ እና የደምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር ይከናወን ዘንድ ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ እንዲጠቀሙ የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት ከሚሰጡ ተቋማት በስተቀር በፌዴራል እና በክልሎች የሚገኙ ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑ እና የግል ተቋማት ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ብቻ ዝግ እንዲያደርጉ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ይታወቃል::

በዚህም መሰረት ከነገ ማክሰኞ ዕለት ጀምሮ መደበኛ የመንግስትና የግል ተቋማት ስራ እንደሚቀጥል ቦርዱ አመልክቷል።

በአንዳድ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች "ትምህርት ቤቶች እስከ ረቡዕ ዝግ ይሆናሉ" ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍5👀3🙉3🥰1
አንድ የፓሪስ ሴንት ጀርመን ደጋፊ በአዉሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ጋብሬል ማጋሌሽ የሳታትን የፍጹም ቅጣት ምት በግራ እግሩ ላይ ተነቅሶታል።

የማይታመን ነዉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁41🙉54👍3🤪1
መረጃ‼️

ከጦርነቱ በፊት ተቃቁሞ የነበረውና በቅርቡ ወደ ሥራ የተመለሠው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ሕወሃት ያቀረባቸውን የአዲስ የካቢኔ አባላት፣ የዞን አስተዳዳሪዎችና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሹመት ዛሬ ማምሻውን አጸደቀ።

የሕወሃት ምክትል ሊቀመንበር አማኑኤል አሠፋ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንትና የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ ኾነው እንደተሾሙ የክልሉ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

70 በመቶ ያህሉ የካቢኔ አባላት ከሕወሃት የተውጣጡ ሲሆኑ፣ 30 በመቶዎቹ ከተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና ከምሁራን የተውጣጡ እንደሆኑ ተገልጧል።

በተመሳሳይ፣ ወልደአብርሃ ገብረጻዲቅ የሰሜን ምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ሺሻይ ግርማይ የማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ዝናቡ ገብረመድኅን የደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ግዴይ አዘናው የምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ፍስሃ ኃይላይ የምሥራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንዲሁም ከለሊ ሐጋዚ የደቡብ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኾነው እንደተሾሙ ዘገባዎቹ ጠቅሠዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
22😁10👍2🤯2👏1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የኢራኑ ፕሬዚዳንት የስራ
መልቀቂያ ማቅረባቸው ተሰማ


የኢራኑ ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ለሀገሪቱ የበላይ መሪ ጽህፈት ቤት ይፋዊ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ለጉዳዩ ቅርብ የሆነ ምንጭ ለኢራን ኢንተርናሽናል ገልጧል። እሁድ ዕለት በተላከው በዚህ ደብዳቤ ላይ ፕሬዝዳንቱና መንግስታቸው በሀገሪቱ ዋና ዋና እና ወሳኝ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ውስጥ ሙሉ በሙሉ መገለላቸውን ፔዜሽኪያን አጽንኦት ሰጥተውበታል። በዚህም ምክንያት በተፈጠረው ክፍተት የኢስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ጦር ውስጥ ያሉ ጽንፈኛ አንጃዎች የሀገሪቱን ጉዳዮች እንዲቆጣጠሩ ዕድል እንደሰጣቸው ምንጩ ጠቁሟል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ በእንዲህ ያለ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መንግስትን መምራትም ሆነ ህጋዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደማይችሉ በመግለጽ፣ በአስቸኳይ ከስልጣናቸው ለመልቀቅ መጠየቃቸውን አስታውቀዋል።
የበላይ መሪው ሞጅታባ ኻሜኒ የፕሬዝዳንቱን መልቀቂያ ይቀበሉት አይቀበሉት እስካሁን ግልጽ ባይሆንም፣ የደብዳቤው ይዘት ግን በከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ ታይቶ የማይታወቅና ጥልቅ የሆነ የስልጣን ክፍፍል  መኖሩን በግልጽ ያሳያል። ይህ ክስተት የመጣው በመንግስትና በኢስላማዊቷ ሪፐብሊክ ወታደራዊ-ደህንነት ተቋማት መካከል ለወራት የዘለቀው ውጥረት ከተቀሰቀሰ በኋላ ነው።

ኢራን ኢንተርናሽናል ቀደም ሲል እንደዘገበው፣  የኢስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ጦር የፕሬዝዳንቱን በርካታ ስልጣኖች ደረጃ በደረጃ በመገደብ ቁልፍ የመንግስት አካላትን በቁጥጥሩ ስር አውሏል። የውስጥ ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ፣ ይህ ሁኔታ የፔዜሽኪያን አስተዳደር በፖለቲካዊና አስፈፃሚ የውሳኔ ማጣት አዙሪት ውስጥ እንዲገባ ያደረገው ሲሆን፣ ይህም ዲፕሎማሲያዊ ድርድሮች ወደፊት እንዳይራመዱና በካቢኔ መዋቅር ላይ የሚፈለጉ ለውጦች እንዳይተገበሩ እንቅፋት ሆኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍6😢5😁2🤪1