አዲስ ሪፖርተር - NEWS
35.8K subscribers
16.9K photos
414 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
#ሰበር_መረጃ‼️
በዩናይትድ ስቴትስ ሰማይ ላይ የፈነዳው ተወርዋሪ ኮከብ በበርካታ ግዛቶች የሚገኙ መኖሪያ ቤቶችን አናወጠ!

ከ300 ቶን ቲኤንቲ (TNT) ፈንጂ ጋር እኩል የሆነ ኃይል ያመነጨ ተወርዋሪ ኮከብ (Meteor) በሰሜን ምስራቅ አሜሪካ ሰማይ ላይ መፈንዳቱን የሀገሪቱ የህዋ ምርምር ተቋም (NASA) አስታወቀ። ክስተቱን ተከትሎ በተፈጠረው ከፍተኛ የድንጋጤ ማዕበል (shockwave) በበርካታ ግዛቶች የሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ተንቀጥቅጠዋል።

ናሳ ባወጣው መግለጫ መነሻነቱ ከህዋ የሆነው ይኸው አካል በሰዓት በአማካይ 120,000 ኪሎ ሜትር በሆነ እጅግ ከፍተኛ ፍጥነት ወደ ምድር ከባቢ አየር ከገባ በኋላ፣ በማሳቹሴትስ እና በኒው ሃምፕሻየር ግዛቶች ከፍተኛ የአየር ክልል ላይ ፈንድቷል።

በአየር ላይ የተከሰተው የዚህ ፍንዳታ እምቅ ኃይል ከፍተኛ የድምፅ ቦምብ እና የምድር ንዝረት ያስከተለ ሲሆን፣ በአካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎች የድንጋጤ ማዕበሉ በተለያዩ ማህበረሰቦች ውስጥ በግልጽ እንደተሰማቸው ገልጸዋል።

የዓይን እማኞች ድንገተኛና አስፈሪ የፍንዳታ ድምፅ መስማታቸውን ሲያረጋግጡ፣ ሌሎች ደግሞ ፍንዳታው ባስከተለው ንዝረት የመስኮት መስታወቶች መርገብገባታቸውንና ህንጻዎች መናወጣቸውን ተናግረዋል።

የአደጋ ጊዜ ኃላፊዎች እንደገለጹት፣ የህዋ አካሉ መሬት ሳይነካ በአየር ላይ በመበታተኑ ምክንያት ሊደርስ የሚችለውን የቀጥታ ግጭት አደጋ ማስቀረት ተችሏል። በክስተቱ ሳቢያ እስካሁን የደረሰ የሰው አካል ጉዳትም ሆነ ከፍተኛ የንብረት ውድመት አለመኖሩን ባለስልጣናቱ አክለው ገልጸዋል።

ይህ በሰሜን ምስራቅ ዩናይትድ ስቴትስ ሰማይ ላይ ለአጭር ጊዜ የተከሰተው ያልተለመደ ክስተት፣ ጥቃቅን የህዋ አካላት እንኳ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ምድር ከባቢ አየር በሚገቡበት ወቅት ሊያስከትሉ የሚችሉትን ግዙፍ የኃይል መጠን የሚያሳይ መሆኑን ተመራማሪዎች ጠቁመዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
34😱4👍2👏1👀1
ጅቡቲ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዴፖ ለመገንባት የኢትዮጵያን የፋይናንስ ድጋፍ እየጠበቀች መሆኑን አስታወቀች

የጅቡቲ ወደቦችና ነፃ ቀጣናዎች ባለሥልጣን በዳመርጆግ ፈሳሽ ጭነት ወደብ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዴፖ ለመገንባት በመጪው የበጀት ዓመት የኢትዮጵያን ተሳትፎና ድጋፍ እየጠበቀ መሆኑን ይፋ አድርጓል።

የባለሥልጣኑ ሰብሳቢ አቡበከር ሀዲ ኡመር፤ ተቋማቸው ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ጋር ድርድር እያደረገ እንደሚገኝ ለሀገር ውስጥ የግል ሚዲያ ገልፀዋል።
 
የነዳጅ ማከማቻው ከኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር 13 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገነባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል።
 
👉 ኢትዮጵያ እየተጠቀመችበት ያለው የ "ሆራይዘን ተርሚናል" አቅሙ መሙላቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ጅቡቲ ውስጥ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ለመገንባት 10 ሄክታር መሬት መጠየቁ የሚታወስ ነው።
 
ጅቡቲ በአፍሪካ ቀንድ እና በምስራቅ አፍሪካ ቁልፍ የኢነርጂ ማከፋፈያ መናኃሪያ ያደርጋታል የተባለ የ160 ሚሊዮን ዶላር ሁለገብ የነዳጅ ማከማቻ ማዕከል በስልታዊው የዳመርጆግ ኮሪደር ልትገነባ እንደሆነ ከዚህ በፊት ተዘግቧል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣9👍74😱2😢1
#ምርጫ2018

በምርጫው ድምፅ የተሰጠባቸውን ወረቀቶች ዋጋ አልባ የሚያደርጓችው ምክንያቶች የትኞቹ ናቸው ?

1. የመራጩ ማንነት በስም የተገለጸ ከሆነ፣
2. ለምክር ቤቱ ሊመረጥ ከሚቻለው ተመራጮች ቁጥር በላይ ላላቸው ዕጩዎች ምልክት የተደረገበት ከሆነ፣
3. ምንም ምልክት ያልተደረገበት ከሆነ፣
4. መራጩ ማንን አንደመረጠ መለየት የሚያስቸግር ከሆነ፣
5. ሕጋዊ የድምፅ መስጫ ወረቀት ያልሆነ ወይም በምርጫ ጣቢያው ያልተሠራጨ የድምፅ መስጫ ወረቀት ከሆነ ዋጋ አልባ ይሆናል፡፡

Via : tikvah

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍2
ኋይት ሃውስ (የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ቤተ-መንግስት) "Alien" (ባዕዳን/የውጭ ዜጎች) የተባሉትን ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞች የሚያሳይ ካርታ የያዘ ድረ-ገጽ ይፋ አድርጓል።

​"ዘ ኤክስ-ፋይልስ"  ከተሰኘው የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ ሙዚቃ ጋር የተቀናበረው ይህ ገጽ፣ የአሜሪካ ባለስልጣናት "በመካከላችን ስለኖሩትና አብረውን ስለተግባቡት" 'ባዕዳን' እውነቱን ለብዙ አሥርት ዓመታት ደብቀዋል ሲል ይሞግታል።

​ድረ-ገጹ “እነዚህ ትናንሽ አረንጓዴ ፍጥረታት አይደሉም፤ እነዚህ በጨለማ ተገን በማድረግ አገራችንን የወረሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕገ-ወጥ ስደተኞች ናቸው” ይላል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👀7👍1😱1🤣1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የእንግሊዝ የጉዞ ማሳሰቢያ‼️
ብሪታንያ ወደ ኢትዮጵያ ለሚጓዙ ዜጎቿ የጉዞ ማሳሰቢያ ሰጠች‼️

የብሪታንያ መንግስት ዛሬ ባወጣው የጉዞ ማሳሰቢያ ነገ የሚካሄደውን የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ተከትሎ ዜጎቿ ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል።

ማስጠንቀቂያው አብዛኛውን የኢትዮጵያ ክፍል ለጉዞ አደገኛ አድርጎ በመጥቀስ ዜጎቹ ወደ ትግራይ፣ አማራ፣በአፋር እና ጋምቤላ ክልሎች ሙሉ በሙሉ እና ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት በምትዋሰንባቸው የድንበር አካባቢዎች ከአሥር እስከ አንድ መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ ማንኛውም ዜጋ እንዳይንቀሳቀስ አሳስቧል።

በኦሮሚያ ክልል ከዋና ዋና መንገዶች እና ከተሞች በስተቀር ከኬንያ ጋር በሚያዋስነው ድንበር በ10 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምዕራብ ሸዋ ፣በሰሜን ሸዋ ዞን ምዕራብ ዋናውን የአዲስ አበባ ወደ ጋምቤላ የሚወስደውን መንገድ ጨምሮ ምዕራብ ወለጋ እና ምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ቄለምም ወለጋ እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ እንዳይጓዙ አሳስቧል።

ከአዲስ አበባ እስከ አዳማ ካለው የፍጥነት መንገድ በስተቀር  የምስራቅ ሸዋ ዞንም ማስጠንቀቂያ ከወጣባቸው ቦታዎች መካከል አንዱ ነው።

በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን፤ በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል ደግሞ ከሱዳን ጋር ባለው ድንበር በ20 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሜተከል ዞን የማኦኮሞ ልዩ ዞን አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ሁሉንም ጉዞዎች እንዳይደረግ ይመክራል።

ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 በሚካሄደው ምርጫ ምክንያት የህዝብ   እንደ ባንኮች ያሉ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ስለሚዘጉ ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

በምርጫ ጣቢያዎች ዙሪያ ከፍተኛ ጥበቃ ይደረግላቸዋል፣ እንዲሁም የተሽከርካሪና የመታወቂያ ፍተሻዎች ይኖራሉ ብሏል።

አላስፈላጊ ጉዞዎችን ከማድረግ እንዲቆጠቡ ፣ከአካባቢው ባለስልጣናት የተሰጡ መመሪያዎችን እንዲከተሉ እና  እና መታወቂያ እንዲይዙ ዜጎቹን አሳስቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24👍4🥰1👏1😁1
#የህፃናት ማጅራት ገትር #በሽታ (#Meningitis) ምንድነው❓️

📝 የማጅራት ገትር ህመም ወይንም በህክምናው አጠራር ሜኔንጃይትስ(Meningitis) የምንለው አንጎልን እና ህብረሰረሰርን ሸፍኖ የሚገኝ የሰውነታችን ክፍል በኢንፌክሽን ሲጠቃ ነው።

📝 የማጅራት ገትር በሽታ በቫይረስ፣በባክቴሪያ ወይንም በፈንገስ ምክንያት ሊከሰት ይችላል።

✏️ ይህ ህመም በአፋጣኝ ህክምና ካልተደረገለት ለከፍተኛ ጉዳት ከዚያም ባለፈ ለህልፈተ ህይወት ሊዳርግ የሚችል ነው።

👉 #ለማጅራት ገትር #ህመም ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?

✔️ የጆሮ እና የሳይነስ ኢንፌክሽን
✔️ የጭንቅላት በአደጋ መጎዳት
✔️ የእናት ጡት ወተት ጠብቶ አለማደግ
✔️ ክትባት አለመከትብ
✔️ ዝቅተኛ የበሽታ የመከላከል አቅም
✔️ ተጠጋግቶ መኖር
✔️ ኤች አይ ቪ ቫይረስ
✔️ የስኳር ህመም

👉 የማጅራት ገትር ህመም ምልክቶች ምንድንናቸው?

✏️ ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት
✏️ የአንገት ህመም
✏️  ከፍተኛ የሆነ የራስምታት
✏️ ማቅለሽለሽና ትውከት (ማስመለስ)
✏️ እራስን መሳት
✏️ ማንቀጥቀጥ
✏️ግራ መጋባት እና ትኩረት ማጣት
✏️ ብርሃን መፍራት
✏️ የምግብ ፍላጎት መቀነስ

📝 አንድ ህፃን ልጅ ሳይታከም ከበሽታው ጋር የሚቆይ ከሆነ  ዉሎ አድሮ ብዙ አይነት የጤና መዘዞች ችግሮች ሊኖሩት ይቺላል ለምሳሌ

✏️የሚጥል በሽታ
✏️ የመስማት ችሎታን ማጣት
✏️የማስታዎስ ችግር
✏️ የመማር ብቃትን ማጣት
✏️ ሚዛን ጠብቆ የመቆም እና የመራመድ ችግር
✏️የኩላሊት ህመም እና የመሳሰሉት ናቸው።
✔️ ተገቢውን ህክምና በአፋጣኝ የሚያገኝ ከሆነ ግን ከህመሙ በሚገባ ሊያግግም ይችላል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍4👏1🙏1👌1
የትናንቷን ኢትዮጵያ የዛሬ 5 ዓመት አናያትም-አብይ አህመድ

“እኔን ዛሬ የሚያሳስበኝ መራጩ ሳይሆን ተመራጩ ነው” ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፃቸውን ለመስጠት በበሻሻ ጎማ ሁለት ሀሮ ምርጫ ጣቢያ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) አሁን ላይ እሳቸውን የሚያሳስባቸው ጉዳይ መራጩ ህዝብ ሳይሆን የተመራጩ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ድምፃቸውን ከሰጡ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ማህበረሰቡ እጩዎችን ከመረጠ በኋላ የተመረጡ ሰዎች ህዝቡ በጠበቃቸው ልክ በመታመን “እጃቸው ልባቸው ንፁህ ሁነው ደከመን ታከተን ሳይሉ ይሄን አገር ታሪክ የሚቀይሩ እና እና የህዝቡን ውለታ ለመክፈል ዝጁነታቸው ምን ያህል ነው ?” ሲሉ የጠየቁ ሲሆን እልህ ቁጣ ክርክር አሸንፋለሁ እና እሸነፋለሁ ሳይሆን ያመነን ህዝብ እንደት አገለግላለሁ፣ ህይወቱን እቀይራለሁ የሚለው ነው ሲሉ ጠቅላዩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የትናንቷን ኢትዮጵያ የዛሬ አምስት ዓመት አናያትም፤ የተለየች የበለጸገች ሀገር ማየት ደግሞ የሁሉም ኃላፊነት ነው” ብለዋል።

ይህ ምርጫ በሰላም እንዳይጠናቀቅ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የሚዘውሯቸው ኃይሎች በስፋት ሲሠሩ ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ “ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማድረግ አይቻልም” እያሉ ብዙ ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁2721👍3😢2🤪2😡2💔1
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ድምጽ ሰጥተዋል

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ጄነራል ጃጋማ ኬሎ ምርጫ ጣቢያ ድምጽ ሰጥተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣32👍10🤪83😡2👏1🤔1🌭1
ከትግራይ ክልል በስተቀር በመላ አገሪቱ በሚካሄደው ሰባተኛው አገራዊ ምርጫ ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ድምጽ መስጠት ተጀምሯል‼️

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ እና በአማራ ክልል ደግሞ በተወሰኑ አካባቢዎች ምርጫው በዛሬው ዕለት እንደማይካሄድ ቀደም ብሎ አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😡15🤷‍♂149👍2😁2👏1🙏1🤪1
በቦንብ ጥቃት ሁለት ሰዎች ተጎዱ‼️
በትናንትናው ዕለት ግንቦት 23/2018 ዓ.ም በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ ራስ አሊ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 06 ጎንደር በር ኖክ ማደያ ፊት ለፊት ከቀኑ 6:00 አካባቢ በአንድ ባጃጅ ላይ የተጠመደ ቦንብ ፈንድቶ ሁለት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
💔108😢6😡4👍2😱1👀1
143 የምርጫ ጣቢያዎች አልተከፈቱም‼️
በጸጥታ ችግር ምክንያት 143 የምርጫ ጣቢያዎች በዛሬው ዕለት አለመከፈታቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል “በተወሰኑ ቦታዎች” የድምጽ መስጠት ሂደቱ ከተጀመረ በኋላ የተቋረጠባቸው የምርጫ ጣቢያዎች እንዳሉም ቦርዱ ገልጿል።

ቦርዱ ይህን ያስታወቀው ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24፤ 2018 ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ያለውን ሰባተኛ ጠቅላላ ምርጫ በተመለከተ በሰጠው መግለጫ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁30👍98🙏2🙈2🤪2👀1
ታዛቢዎቼ ተደብድበዋል-ጎጎት‼️
#የምርጫ ታዛቢዎች ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ጎጎት ፓርቲ ከሰሰ!!!

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ወልቂጤ ምርጫ ጣቢያ የምርጫ ታዛቢዎች ተደብድበው ከምርጫ እንዲወጡ ተደርገዋል ሲል ጎጎት ፓረቲ ገለጸ። ፓረቲው በኦፊሸል የፌስ ቡክ ገጹ እንዳብራራው “ፓርቲዉ ይንቀሳቀስበት የነበረዉ ሞተር ተነጥቋል።

የምርጫ ወረቀት በፌስታል ይዘዉ ሲበትኑ ተመልክተናል። ለምርጫ ቦርድ ምርጫው እንዲቆም አሳዉቀናል” ብሎ፣ከምርጫ ቦርድ አፍጣኝ ምላሽ እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡
በስፍራው የምትገኘው የሪፖርተር ዘጋቢ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ምርጫ አስተባባሪ አቶ ነጋሽን አነጋግራቸው በሰጡት ምላሽ፣ ጎጎት ፓርቲ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ወልቂጤ ከተማ ምርጫ ጣቢያ የምርጫ  ታዛቢዎች ተደብድበው ከምርጫ እንዲወጡ ተደርገዋል ማለቱን ተከትሎ ወደ ቦታው አስተባባሪዎች ልከው  እንዳጣሩና ምንም ነገር እንዳልተደረገ ማረጋገጣቸውንተናግረዋል፡፡

ፓርቲው ይህ ሆኗል ባለበት የምርጫ ጣቢያ ሁለት ታዛቢዎቹ እንደነበሩ የገለጹት ዋና አስተባባሪው፣ ፓርቲው የተናገረው  ከእውነት የራቀ መሆኑን አክለዋል። ሌላው ሱልካ በተባለ ጣቢያ አካባቢ የፓርቲው ታዛቢ ባጅ ስለተጠየቀ አኩርፎ ከመውጣቱ ውጭ ሌላ  የተፈጠረ ነገር እንደሌለም አስረድተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🙊147👍4😁3😢1👀1
ቀይ ባህርን እዘጋለሁ-ኢራን‼️
ኢራን ከአሜሪካ ተደራዳሪዎች ጋር በተዘዋዋሪ (indirectly) የምታደርገውን ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ ማቋረጧን አስታወቀች።

ኢራን ይህንን እርምጃ የወሰደችው እስራኤል በሊባኖስ እና ጋዛ የምታደርገው ጥቃት ባለመቆሙ ምክንያት መሆኑን የሀገሪቱ የዜና ወኪል የሆነው ታስኒም ኒውስ ዘግቧል።

እስራኤል በሊባኖስ እና በጋዛ የምታደርገውን ጥቃት ካልቆመች ኢራን የሆርሙዝ ባህርን እና የቀይ ባህር ዋነኛ መተላለፊያ የሆነውን የባብ አል ማንዳብ ሰርጥን ሙሉ በሙሉ እንደምትዘጋ ዝታለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍247😁7🤣4👀1