ሰበር :-
የአርሰናል እና የፔዤን ጨዋታ እያዩ የነበሩ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የቦምብ ተፈፀመባቸው
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ትላንት ምሽት በተከሰተ የቦምብ ፍንዳታ የተማሪዎች ህይወት ማለፉና በርካቶች መቁሰላቸው ተሰምቷል፡፡
አደጋው የተከሰተው ተማሪዎች በካምፓሱ አዳራሽ ውስጥ ተጨናንቀው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የእግር ኳስ ጨዋታን በፕሮጀክተር እየተከታተሉ በነበረበት ወቅት እንደሆነ ተገልጿል።
ከተማሪዎችና ከአካባቢው ነዋሪዎች በተገኘ መረጃ መሠረት፣ በፍንዳታው ሳቢያ በትንሹ የሁለት ተማሪዎች ህይወት ማለፉ የተረጋገጠ ሲሆን፤ የሟቾች ቁጥር እስከ 3 ሊደርስ እንደሚችል ተጠቁሟል።
ህይወታቸው ያለፈው ተማሪዎች አስክሬን ዛሬ ጠዋት ወደ ቤተሰቦቻቸው ተሸኝቷል።
በተጨማሪም ከ30 በላይ ተማሪዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን፤ ተጎጂዎቹ በካምፓሱ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።
ፍንዳታው በተከሰተበት ወቅት በአዳራሹ ውስጥ ከፍተኛ የሰው ቁጥር በመኖሩና በመግቢያና መውጫዎች ላይ በተፈጠረው መረጋገጥ ሳቢያ የጉዳቱ መጠን ሊጨምር እንደቻለ የዓይን እማኞች ገልጸዋል።
@Addis_Reporter

❤19😢16💔6👍5😱4🤯1👀1
ደቡብ ሱዳን በድንበሯ ላይ የተገነባውን
የግብፅ ጦር ሠፈር እንዲዘጋ አዘዘች
የደቡብ ሱዳን መንግሥት፣ ግብፅ በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው የላይኛው ናይል ግዛት ፓጋክ አካባቢ ያቋቋመችውን ወታደራዊ ጦር ሠፈር በአስቸኳይ እንድትዘጋ ማዘዙን የዓረብኛ የዜና ምንጮች በሰፊው ዘግበዋል።
ይህ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አቅራቢያ የተገነባውና ወታደራዊ ሥልጠና የመስጠት እንዲሁም የናይል ወንዝ ፍሰትን የመቆጣጠር ስውር ዓላማ የነበረው ጦር ሠፈር፣ የሥልጠና ባለሙያዎችን ጨምሮ 260 የሚያህል የሰው ኃይል አሰማርቶ የነበረ መሆኑ ታውቋል።

❤13👍5🤪4😢3👏2
ነገ ኢትዮጵያ ትመርጣለች
በፓርቲዎች ስም 10 ሺህ 437 ዕጩዎች እንዲሁም 80 የግል ተወዳዳሪዎች ለመመረጥ ተዘጋጅተዋል
42 የፖለቲካ ፓርቲዎች በሰኞው ሀገራዊ ምርጫ እንደሚወዳደሩ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቋል
ቦርዱ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በአጠቃላይ 54 ሚሊዮን 057 ሺህ 871 መራጮች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፤ በፓርቲዎች ስም 10 ሺህ 437 ዕጩዎች እንዲሁም 80 የግል ተወዳዳሪዎች ለምርጫ መቅረባቸውን ይፋ አድርገዋል።
ቦርዱ የምርጫ ቁሳቁሶችን ሙሉ በሙሉ ማድረሱን፣ የዜጎችን ግንዛቤ ለማሳደግ በ5 ቋንቋዎች 19 የሕዝብ ክርክሮችን ማደራጀቱንና ከ250 ሺህ በላይ የታዛቢዎች ባጅ ማሰራጨቱን ሰብሳቢዋ ገልፀዋል።
ምርጫውን የአፍሪካ ኅብረት፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት እና የሀገር ውስጥ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ይታዘባሉ።
በምርጫ ቦርድ የግዜ ሠለዳ መሠረት የድምጽ ውጤት ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

🤣24❤10👍5😢3🤪3
የዓሳ ቆዳ ለቃጠሎ ህክምና፤ በብራዚል ሐኪሞች የተገኘው አስደናቂና አነስተኛ ወጪ የሚጠይቅ ፈውስ
በብራዚል የሚገኙ ተመራማሪዎችና የሕክምና ባለሙያዎች በከባድ የእሳት ቃጠሎ የተጎዱ ሰዎችን ለማከም ልዩ በሆነ ዘዴ የተዘጋጀ የዓሳ ቆዳን በመጠቀም አስደናቂ ስኬት እያስመዘገቡ ይገኛሉ። ይህ አዲስ የሕክምና ፈጠራ የተጎጂዎችን ስቃይ በከፍተኛ ሁኔታ ከመቀነሱም በላይ የሕክምና ወጪን በግማሽ ያህል ያቀለለ መሆኑ ተገልጿል።
የሴአራ ፌደራል ዩኒቨርሲቲ (Federal University of Ceará) ተመራማሪዎች እንዳረጋገጡት፣ የቲላፒያ ዓሳ ቆዳ ለሰው ልጅ ቆዳ መፈወስ እጅግ አስፈላጊ የሆኑትን ‘ታይፕ 1’ ኮላጅን (Collagen) የተሰኙ ፕሮቲኖችን እና ከፍተኛ እርጥበትን በውስጡ ይዟል። ይህም የቆሰለው አካል በፍጥነት እንዲያገግም እና ከበሽታ አምጪ ተህዋስያን እንዲጠበቅ ያደርገዋል ብለዋል።
ቀደም ሲል በብራዚል የቆዳ ባንኮች እጥረት በመኖሩ ምክንያት ለቃጠሎ ተጎጂዎች የሚደረገው መደበኛ ሕክምና በየቀኑ የሚቀያይር ፋሻ እና የቃጠሎ ክሬም በመጠቀም የሚከናወን ሲሆን፣ ይህም ለታካሚዎቹ ከፍተኛ ስቃይ የሚፈጥር ነበር።
አዲሱ የቲላፒያ ቆዳ ሕክምና ግን አንዴ ከቆሰለው አካል ላይ ከተለጠፈ በኋላ በተፈጥሮ እስኪላጥ ድረስ ለቀናት የሚቆይ በመሆኑ፣ ፋሻ በየቀኑ የመቀየርን ስቃይ ሙሉ በሙሉ ያስቀረና ፈውስን የሚያፋጥን ሆኗል። የወጪው መቶኛም ከመደበኛው ሕክምና ጋር ሲነጻጸር እስከ 50 በመቶ ቅናሽ አለው።

❤11👍8🤔2👏1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
#ሰበር_መረጃ‼️
በዩናይትድ ስቴትስ ሰማይ ላይ የፈነዳው ተወርዋሪ ኮከብ በበርካታ ግዛቶች የሚገኙ መኖሪያ ቤቶችን አናወጠ!
ከ300 ቶን ቲኤንቲ (TNT) ፈንጂ ጋር እኩል የሆነ ኃይል ያመነጨ ተወርዋሪ ኮከብ (Meteor) በሰሜን ምስራቅ አሜሪካ ሰማይ ላይ መፈንዳቱን የሀገሪቱ የህዋ ምርምር ተቋም (NASA) አስታወቀ። ክስተቱን ተከትሎ በተፈጠረው ከፍተኛ የድንጋጤ ማዕበል (shockwave) በበርካታ ግዛቶች የሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ተንቀጥቅጠዋል።
ናሳ ባወጣው መግለጫ መነሻነቱ ከህዋ የሆነው ይኸው አካል በሰዓት በአማካይ 120,000 ኪሎ ሜትር በሆነ እጅግ ከፍተኛ ፍጥነት ወደ ምድር ከባቢ አየር ከገባ በኋላ፣ በማሳቹሴትስ እና በኒው ሃምፕሻየር ግዛቶች ከፍተኛ የአየር ክልል ላይ ፈንድቷል።
በአየር ላይ የተከሰተው የዚህ ፍንዳታ እምቅ ኃይል ከፍተኛ የድምፅ ቦምብ እና የምድር ንዝረት ያስከተለ ሲሆን፣ በአካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎች የድንጋጤ ማዕበሉ በተለያዩ ማህበረሰቦች ውስጥ በግልጽ እንደተሰማቸው ገልጸዋል።
የዓይን እማኞች ድንገተኛና አስፈሪ የፍንዳታ ድምፅ መስማታቸውን ሲያረጋግጡ፣ ሌሎች ደግሞ ፍንዳታው ባስከተለው ንዝረት የመስኮት መስታወቶች መርገብገባታቸውንና ህንጻዎች መናወጣቸውን ተናግረዋል።
የአደጋ ጊዜ ኃላፊዎች እንደገለጹት፣ የህዋ አካሉ መሬት ሳይነካ በአየር ላይ በመበታተኑ ምክንያት ሊደርስ የሚችለውን የቀጥታ ግጭት አደጋ ማስቀረት ተችሏል። በክስተቱ ሳቢያ እስካሁን የደረሰ የሰው አካል ጉዳትም ሆነ ከፍተኛ የንብረት ውድመት አለመኖሩን ባለስልጣናቱ አክለው ገልጸዋል።
ይህ በሰሜን ምስራቅ ዩናይትድ ስቴትስ ሰማይ ላይ ለአጭር ጊዜ የተከሰተው ያልተለመደ ክስተት፣ ጥቃቅን የህዋ አካላት እንኳ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ምድር ከባቢ አየር በሚገቡበት ወቅት ሊያስከትሉ የሚችሉትን ግዙፍ የኃይል መጠን የሚያሳይ መሆኑን ተመራማሪዎች ጠቁመዋል።

❤34😱4👍2👏1👀1
ጅቡቲ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዴፖ ለመገንባት የኢትዮጵያን የፋይናንስ ድጋፍ እየጠበቀች መሆኑን አስታወቀች
የጅቡቲ ወደቦችና ነፃ ቀጣናዎች ባለሥልጣን በዳመርጆግ ፈሳሽ ጭነት ወደብ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዴፖ ለመገንባት በመጪው የበጀት ዓመት የኢትዮጵያን ተሳትፎና ድጋፍ እየጠበቀ መሆኑን ይፋ አድርጓል።
የባለሥልጣኑ ሰብሳቢ አቡበከር ሀዲ ኡመር፤ ተቋማቸው ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ጋር ድርድር እያደረገ እንደሚገኝ ለሀገር ውስጥ የግል ሚዲያ ገልፀዋል።
የነዳጅ ማከማቻው ከኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር 13 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገነባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል።
👉 ኢትዮጵያ እየተጠቀመችበት ያለው የ "ሆራይዘን ተርሚናል" አቅሙ መሙላቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ጅቡቲ ውስጥ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ለመገንባት 10 ሄክታር መሬት መጠየቁ የሚታወስ ነው።
ጅቡቲ በአፍሪካ ቀንድ እና በምስራቅ አፍሪካ ቁልፍ የኢነርጂ ማከፋፈያ መናኃሪያ ያደርጋታል የተባለ የ160 ሚሊዮን ዶላር ሁለገብ የነዳጅ ማከማቻ ማዕከል በስልታዊው የዳመርጆግ ኮሪደር ልትገነባ እንደሆነ ከዚህ በፊት ተዘግቧል፡፡

🤣9👍7❤4😱2😢1
#ምርጫ2018
በምርጫው ድምፅ የተሰጠባቸውን ወረቀቶች ዋጋ አልባ የሚያደርጓችው ምክንያቶች የትኞቹ ናቸው ?
1. የመራጩ ማንነት በስም የተገለጸ ከሆነ፣
2. ለምክር ቤቱ ሊመረጥ ከሚቻለው ተመራጮች ቁጥር በላይ ላላቸው ዕጩዎች ምልክት የተደረገበት ከሆነ፣
3. ምንም ምልክት ያልተደረገበት ከሆነ፣
4. መራጩ ማንን አንደመረጠ መለየት የሚያስቸግር ከሆነ፣
5. ሕጋዊ የድምፅ መስጫ ወረቀት ያልሆነ ወይም በምርጫ ጣቢያው ያልተሠራጨ የድምፅ መስጫ ወረቀት ከሆነ ዋጋ አልባ ይሆናል፡፡
Via : tikvah

❤14👍2
ኋይት ሃውስ (የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ቤተ-መንግስት) "Alien" (ባዕዳን/የውጭ ዜጎች) የተባሉትን ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞች የሚያሳይ ካርታ የያዘ ድረ-ገጽ ይፋ አድርጓል።
"ዘ ኤክስ-ፋይልስ" ከተሰኘው የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ ሙዚቃ ጋር የተቀናበረው ይህ ገጽ፣ የአሜሪካ ባለስልጣናት "በመካከላችን ስለኖሩትና አብረውን ስለተግባቡት" 'ባዕዳን' እውነቱን ለብዙ አሥርት ዓመታት ደብቀዋል ሲል ይሞግታል።
ድረ-ገጹ “እነዚህ ትናንሽ አረንጓዴ ፍጥረታት አይደሉም፤ እነዚህ በጨለማ ተገን በማድረግ አገራችንን የወረሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕገ-ወጥ ስደተኞች ናቸው” ይላል።

❤15👀7👍1😱1🤣1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የእንግሊዝ የጉዞ ማሳሰቢያ‼️
ብሪታንያ ወደ ኢትዮጵያ ለሚጓዙ ዜጎቿ የጉዞ ማሳሰቢያ ሰጠች‼️
የብሪታንያ መንግስት ዛሬ ባወጣው የጉዞ ማሳሰቢያ ነገ የሚካሄደውን የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ተከትሎ ዜጎቿ ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል።
ማስጠንቀቂያው አብዛኛውን የኢትዮጵያ ክፍል ለጉዞ አደገኛ አድርጎ በመጥቀስ ዜጎቹ ወደ ትግራይ፣ አማራ፣በአፋር እና ጋምቤላ ክልሎች ሙሉ በሙሉ እና ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት በምትዋሰንባቸው የድንበር አካባቢዎች ከአሥር እስከ አንድ መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ ማንኛውም ዜጋ እንዳይንቀሳቀስ አሳስቧል።
በኦሮሚያ ክልል ከዋና ዋና መንገዶች እና ከተሞች በስተቀር ከኬንያ ጋር በሚያዋስነው ድንበር በ10 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምዕራብ ሸዋ ፣በሰሜን ሸዋ ዞን ምዕራብ ዋናውን የአዲስ አበባ ወደ ጋምቤላ የሚወስደውን መንገድ ጨምሮ ምዕራብ ወለጋ እና ምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ቄለምም ወለጋ እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ እንዳይጓዙ አሳስቧል።
ከአዲስ አበባ እስከ አዳማ ካለው የፍጥነት መንገድ በስተቀር የምስራቅ ሸዋ ዞንም ማስጠንቀቂያ ከወጣባቸው ቦታዎች መካከል አንዱ ነው።
በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን፤ በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል ደግሞ ከሱዳን ጋር ባለው ድንበር በ20 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሜተከል ዞን የማኦኮሞ ልዩ ዞን አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ሁሉንም ጉዞዎች እንዳይደረግ ይመክራል።
ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 በሚካሄደው ምርጫ ምክንያት የህዝብ እንደ ባንኮች ያሉ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ስለሚዘጉ ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
በምርጫ ጣቢያዎች ዙሪያ ከፍተኛ ጥበቃ ይደረግላቸዋል፣ እንዲሁም የተሽከርካሪና የመታወቂያ ፍተሻዎች ይኖራሉ ብሏል።
አላስፈላጊ ጉዞዎችን ከማድረግ እንዲቆጠቡ ፣ከአካባቢው ባለስልጣናት የተሰጡ መመሪያዎችን እንዲከተሉ እና እና መታወቂያ እንዲይዙ ዜጎቹን አሳስቧል።

❤24👍4🥰1👏1😁1
#የህፃናት ማጅራት ገትር #በሽታ (#Meningitis) ምንድነው❓️
📝 የማጅራት ገትር ህመም ወይንም በህክምናው አጠራር ሜኔንጃይትስ(Meningitis) የምንለው አንጎልን እና ህብረሰረሰርን ሸፍኖ የሚገኝ የሰውነታችን ክፍል በኢንፌክሽን ሲጠቃ ነው።
📝 የማጅራት ገትር በሽታ በቫይረስ፣በባክቴሪያ ወይንም በፈንገስ ምክንያት ሊከሰት ይችላል።
✏️ ይህ ህመም በአፋጣኝ ህክምና ካልተደረገለት ለከፍተኛ ጉዳት ከዚያም ባለፈ ለህልፈተ ህይወት ሊዳርግ የሚችል ነው።
👉 #ለማጅራት ገትር #ህመም ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
✔️ የጆሮ እና የሳይነስ ኢንፌክሽን
✔️ የጭንቅላት በአደጋ መጎዳት
✔️ የእናት ጡት ወተት ጠብቶ አለማደግ
✔️ ክትባት አለመከትብ
✔️ ዝቅተኛ የበሽታ የመከላከል አቅም
✔️ ተጠጋግቶ መኖር
✔️ ኤች አይ ቪ ቫይረስ
✔️ የስኳር ህመም
👉 የማጅራት ገትር ህመም ምልክቶች ምንድንናቸው?
✏️ ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት
✏️ የአንገት ህመም
✏️ ከፍተኛ የሆነ የራስምታት
✏️ ማቅለሽለሽና ትውከት (ማስመለስ)
✏️ እራስን መሳት
✏️ ማንቀጥቀጥ
✏️ግራ መጋባት እና ትኩረት ማጣት
✏️ ብርሃን መፍራት
✏️ የምግብ ፍላጎት መቀነስ
📝 አንድ ህፃን ልጅ ሳይታከም ከበሽታው ጋር የሚቆይ ከሆነ ዉሎ አድሮ ብዙ አይነት የጤና መዘዞች ችግሮች ሊኖሩት ይቺላል ለምሳሌ
✏️የሚጥል በሽታ
✏️ የመስማት ችሎታን ማጣት
✏️የማስታዎስ ችግር
✏️ የመማር ብቃትን ማጣት
✏️ ሚዛን ጠብቆ የመቆም እና የመራመድ ችግር
✏️የኩላሊት ህመም እና የመሳሰሉት ናቸው።
✔️ ተገቢውን ህክምና በአፋጣኝ የሚያገኝ ከሆነ ግን ከህመሙ በሚገባ ሊያግግም ይችላል።

❤14👍4👏1🙏1👌1