አዲስ ሪፖርተር - NEWS
35.8K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
በሰባተኛው አገራዊ ምርጫ ከአፍሪካ ተቋማት በስተቀር ሌሎች የውጭ ታዛቢዎች እንደማይሳተፉ ተነገረ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሚቀጥለው ሳምንት በሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከአፍሪካ ተቋማት በስተቀር የውጭ ታዛቢዎች ፈቃድ አለማግኘታቸውን ገለጸ፡፡

ምርጫ ቦርድ የሰባተኛውን አገራዊ ምርጫ አጠቃላይ የቅድመ ምርጫ ሥራዎችንና የድምፅ መስጫ ቀን አስመልክቶ፣ ማክሰኞ ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ ይህ የተገለጸው፡፡

መግለጫውን የሰጡት የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ፣ የአፍሪካ ኅብረትና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) በሰባተኛው አገራዊ ምርጫ ለመታዘብ እንደሚመጡ የሚገልጽ ዝርዝርና ሙሉ ሪፖርት ቦርዱ ደርሶታል ብለዋል፡፡

ዓለም አቀፍ ታዛቢዎችን በሚመለከት ፈቃድ የሚጠየቀውም ሆነ የሚሰጠው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሆኑንና ሁለቱ የአፍሪካ ተቋማት ለመታዘብ እንደሚመጡ የተነገራቸውና ሪፖርታቸው የተላከላቸውም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል እንደሆነ፣ ቦርዱም ለተቋማቱ የታዛቢነት ባጅ ለመስጠት ዝግጅት ላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

‹‹እነዚህ ትልልቅ ተቋማት ከሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በኋላ ወደ አገር ውስጥ ይገባሉ፤›› ብለዋል፡፡

ሪፖርተር ከሁለቱ ተቋማት ውጪ ሌሎች ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ፈቃድ ስለመጠየቃቸውም ሆነ ስለመፈቀዱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

ሆኖም የአውሮፓ ኅብረት በታዛቢነት እንደማይሳተፍ መረጃዎች ያሳያሉ ሲል ዘግቧል፡፡

Via ሪፖርተር

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁2810🤪3👍2🤔2🤯2🤣1
በኢትዮጵያ በቴሌግራም የሚደረግ የክሪፕቶ ግብይት (P2P Trading) ሊቆም ነው።

በቴሌግራም ላይ ክሪፕቶ ግብይት መድረክ የሆነው ዋሌቴ (Wallet) ከግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ብር የሚደረጉ የክሪፕቶ ግብይቶችን (P2P Trading) እንደሚያቆም አስታውቋል።

ይህ ውሳኔ የተወሰደው የሀገሪቱን የፋይናንስ ህግ መሰረት አድርጎ እንደሆነ ነው የገለጸው።

ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ሁሉም በኢትዮጵያ ብር የሚደረጉ የP2P ማስታወቂያዎች በሙሉ ይጠፋሉ ፤ አዲስ ማስታወቂያዎችንም መለጠፍም አይቻልም ተብሏል።

ከቀነ ገደቡ በፊት የተጀመሩ ግብይቶች በተለመደው አሰራር መሠረት መፈጸም እንደሚቻል ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም ፦
- ቢትጌት
- ባይናንስ
- ኦኬኤክስ
- ባይቢት ... የመሳሳሉ መድረኮች በኢትዮጵያን ብር የሚደረጉ የክሪፕቶ ግብይቶች (P2P) ማቆማቸው ይታወሳል።

አሁን ደግሞ በP2P ግብይት በስፋት የሚታወቀው የቴሌግራም ዋሌት ከግንቦት 25 በኋላ ያቆማል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍2💔1
የመቀሌ ነዋሪዎች ስጋት‼️
በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ አፈሳ እና እስር ህዝቡን ሌላ ስጋት ውስጥ ከቶታል።
ባለፈው አንድ ወር ውስጥ ከ 30000 በላይ ወጣቶች ታፍሰው ወደ ክልሉ ልዩ ሀይል መግባታቸው ታውቋል።
የሰሞኑ አፈሳ እና እስር በርካታ ሰዎችን ያሳሰበ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከወትሮው በተለየ መልኩ የትግራይ ተወላጆች በአውቶብስ ወደ አዲስ አበባ ለመሳፈር ከፍተኛ ሰልፍ እንደታየ የመቀሌ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
ምስል:- ዛሬ መቀሌ መነን ሆቴል አካባቢ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9🤔6😢4👍3💔3🥰2🕊1
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLA) ከምርጫ ጋር የተያያዛ ያወጀው የትራንስፖርት እግድ

OLA ባስተላለፈው እግድ ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የምቆይ በመላው ኦሮሚያ ውስጥ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንደተከለከለ አሳወቀ።

ከጤና አምቡላንስ በስተቀር ማንኛውም ተሽከርካሪ ኦሮሚያ ውስጥ ማለፍ እንደማይቻል በጥብቅ አሳወቀ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁2116👍6🤔2🤣2🤪2🙊1
ዜና እረፍት
ተወዳጇ ተዋናይት ሰላማዊት ደስታ ከእዚህ ዓለም በሞት ተለየች


በፊልም ቲያትር እና በሌሎችም ተወዳጅ ጥበባዊ ሥራዎቿ ዝናን ያተረፈችው አርቲስት ሰላማዊት ደስታ ከእዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

አርቲስት ሰላማዊት ደስታ ባደረባት ህመም ሳቢያ በህክምና ስትረዳ ቆይታ ዛሬ ዓርብ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ማረፏን የቅርብ ወዳጇና አብሮ አደጓ ጋዜጠኛ ግርማ ፍስሃ አስታውቋል።

የሽኝት ፕሮግራሙ ነገ ቅዳሜ  ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም 3:00 በሀገር ፍቅር ቲያትር የሚከናወን ሲሆን፣ የቀብር ሥነ-ሥርዓቷም በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ ይፈፀማል።" ሲል አስታውቋል።

የዝግጅት ክፍላችን በአርቲስት ሰላማዊት ደስታ ዜና እረፍት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቿ፣ ለሙያ አጋሮቿና አድናቂዎቿ መፅናናትን ይመኛል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢298👍2🤔2💔2🙉2
ከ54 ሚሊየን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ54 ሚሊየን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ።

ቦርዱ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ዙሪያ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ እንዳሉት፤ ለምርጫው 54 ሚሊየን 571 ሺህ 871 መራጮች ተመዝግበዋል።

የምርጫውን ሂደት የአፍሪካ ህብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ልዑካን እንደሚታዘቡ ገልጸዋል።

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዜጎች የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁166🤪4👍2😢2
በአራት አመት ውስጥ 7,400 ግጭቶች‼️
የአልጀዚራ የግጭት መቆጣጠሪያ እንደሚያሳየው ከ Janurary 2022 እስከ may 15/2026 ድረስ በኢትዮጵያ በመላ አገሪቱ ከ7,400 በላይ ግጭቶች ተመዝግበዋል።

ከግጭቶቹ ከግማሽ በላይ (3,719)
በአማራ ክልል በፋኖ እና በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ጭምር የተመዘገቡ ናቸው።

በኦሮሚያ ክልል 2,735 ግጭቶች የተመዘገቡት በ OLA በሚመራው የትጥቅ አመጽ እና ከተለያዩ የጋራ ግጭቶች ጎን ለጎን ነው። ሌሎች ክልሎችም አለመረጋጋት አጋጥሟቸዋል፣ በትግራይ ክልል 262 ግጭቶች ሲመዘገቡ፣ በምዕራብ ጋምቤላ ክልል ደግሞ 144 ግጭቶች ተመዝግበዋል።

ከላይ ያለው ካርታ ባለፉት አራት አመታት ውስጥ በመላ ሀገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች የተፈፀሙ አጠቃላይ ግጭቶች መሆኑን አልጀዚራ ይፋ አድርጓል። (ayu)

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14😢7👍2
መረጃ‼️

የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ ከአውሮፓውያኑ 2010 እስከ 2024 ባለው ጊዜ ውስጥ ለኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ ልማት ከአፍሪካ 54 አገራት መካከል 31ኛ ደረጃ ሠጣት።

በተጠቀሠው የ15 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ባንኩ ለኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት የሠጠው ነጥብ፣ ከ0 ነጥብ 47 ወደ 0 ነጥብ 52 አድጓል።

አገሪቱ በመካከለኛ የኢንዱስትሪ ልማት ደረጃ ላይ እንድትወሠን አስተዋጽኦ ካደረጉት ምክንያቶች መካከል፣ ዋነኛው የማኑፋክቸሪንግ ዘርፏ ደካማ አፈጻጸም እንደኾነ ሪፖርቱ ጠቅሷል።

ባንጻሩ፣ አገሪቱ በኢንቨስትመንት፣ መሠረተ ልማት እና የሰው ሀብት ልማት መካከለኛ ውጤት አስመዝግባለች።

ሞሮኮ፣ ደቡብ አፍሪካን በመቅደም በአፍሪካ ግንባር ቀደም በኢንዱስትሪ ልማት በከፍተኛ ደረጃ ያደገች አገር መኾኗን ሪፖርቱ አመልክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7😢7👍2🙊2
የፋይዳ መታወቂያ የተመዘገበን ስልክ ቁጥር በአካል እና በኢንተርኔት መቀየር የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱ ተገለጸ

የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የፋይዳ መታወቂያ ያወጡበት ስልክ ቁጥር በተለያየ ምክንያት እጃቸው ላይ የሌለ ዜጎች በሌላ ስልክ ቁጥር እንዲቀይሩ እድል የሚሰጥ አሰራር መኖሩን አስታውቋል።

አሰራሩ የተዘረጋው ፋይዳ መታወቂያ የወሰዱበትን ስልክ ቁጥር ማግኘት ባለመቻላቸው የባንክ ሂሳብ ማንቀሳቀስን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ማግኘት ለተቸገሩ ዜጎች ምላሽ ለመስጠት ነው ተብሏል።

የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የባለድርሻ አካላት እና የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳሚናስ ሰይፉ ለአሐዱ ሬድዮ እንደገለጹት፤ መረጃውን የምዝገባ ማሽኖች ባሉባቸው ጣቢያዎች በመገኘት ስልክ ቁጥር መቀየር እንደሚቻል ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።

በአሁኑ ወቅት የበርካታ ሰዎች ስልክ ቁጥር፣ የስም እና የልደት ዘመን መረጃዎች በመሳሳታቸው ይስተካከልልን የሚል ጥያቄ በመቅረቡ የማስተካከል ስራ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።


መታወቂያቸው ላይ ያስመዘገቡትን ስልክ ቁጥር ማግኘት ለሚቸገሩ ዜጎች ሁለት አማራጮች መዘጋጀታቸውን ዳይሬክተሩ ለአሐዱ ገልጸዋል።

የመጀመሪያው አማራጭ ነዋሪዎች የቀድሞውን ስልክ ቁጥራቸውን ማግኘት የሚችሉ ከሆነ በራሳቸው የተቋሙ ድረ-ገጽ ውስጥ በመግባት መቀየር የሚችሉበት ነው ተብሏል።

ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ የተመዘገቡበትን ስልክ ቁጥር ሙሉ በሙሉ ማግኘት ለማይችሉ ዜጎች የተዘጋጀ እንደሆነ ተገልጿል።

እነዚህ ወገኖች የፋይዳ ምዝገባ ማሽኖች ወደሚገኙባቸው ጣቢያዎች በአካል በመገኘት ማስተካከል እንደሚችሉ አቶ ሳሚናስ ሰይፉ አስታውቀዋል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
29👍4👏1👌1
የእንግሊዝ መንግሥት የስደተኞችን ዕድሜ ለመለየት የኤአይ ቴክኖሎጂ ሊጠቀም ነው።

የእንግሊዝ መንግሥት በድንበር ላይ ያሉ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ዕድሜ በኤአይ (AI) ለመለየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ አስጀምራለሁ ብሏል።

ቴክኖሎጂው በድንበር ላይ የተነሱ ፎቶግራፎችን በመተንተን የሰውን ዕድሜ የሚመረምር ሲሆን ከዚህ ቀደም ለዚሁ አገልግሎት ሥራ ላይ ከዋሉ የሰነድ ምርመራ እና የህክምና ምርመራዎች (ኤክስ-ሬይ እና ኤም.አር.አይ) የሚያግዝ ተጨማሪ አማራጭ ነው ተብሏል።

መረጃዎች እንደሚያሳዩት እ.ኤ.አ እስከ መጋቢት 2026 ባለው መረጃ መሠረት  ከ6,400 በላይ ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ እንግሊዝ ህጻን ነን ብለው በማቅረባቸው ዕድሜያቸው ተጣርቷል። ከእነዚህ ውስጥ 43 በመቶ የሚሆኑት አዋቂዎች መሆናቸው ተረጋግጧል።

የቴክኖሎጂው ዝግጅት እና የሶስት ዓመት የሙከራ ጊዜ በድምሩ 322,000 ፓውንድ ወጪ እንደሚጠይቅ ሲሆን የሙከራ ሂደቱ በሚቀጥለው ዓመት ይጀምራል ተብሏል።

የአገሪቱ የድንበር ደኅንነት እና ጥገኝነት ሚኒስትር አሌክስ ኖሪስ፣ አዋቂዎች የሐሰት ዕድሜ በመጥቀስ ሥርዓቱን መበዝበዛቸው ለህጻናት መድረስ የነበረበትን ድጋፍ እያስተጓጎለ መሆኑን በመጥቀስ፣ ቴክኖሎጂውን መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል።

Source : BBC

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍4
ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ኮንጎ ገቡ

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ቴዎድሮስ በኢቦላ ወረርሽኝ በተጠቃችው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አቅንተዋል።

ሀገሪቱ የተከሰተውን ወረርሽኝ ለመከላከል እየወሰደች ያለውን እርምጃ ይገመግማሉ ተብሏል።

በኢቦላ ሳቢያ 238 ሰዎች ሲሞቱ 1,077 ደግሞ መጠቃታቸው ተገልጿል። #npr

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17🥰3👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ነዳጅ በባቡር ኤክስፖርት‼️
አሜሪካ በኢራን ላይ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ምክንያት ኢራን ነዳጇን ወደ ቻይና እና ፓኪስታን በባቡር መስመር መላክ ጀመረች።
አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው እገዳ 50 ቀናትን አስቆጥሯል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23👍10
#RemedialExamSchedule

የ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል (አቅም ማሻሻያ) ፕሮግራም ፈተና ከግንቦት 27/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም ለአምስት ቀናት እንደሚሰጥ ይታወቃል።

በተጠቀሱት ቀናት በሁለት ፈረቃ በጠዋት እና በከሰዓት መርሐግብር የሚሰጠው የሪሚዲያል ፕሮግራም (የተፈጥሮ ሳይንስ እና ማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች) የፈተና መርሐግብር ከላይ ተያይዟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
8👍2
ለችግሩ ባንኩ ምላሽ ሰጥቷል‼️

የተሻሻለውን የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ሲያዘምኑ 'Passphrase'  ጠይቆዎት ከነበረ ወደ አቅራቢያዎ በሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ አገልግሎቱን እንደገና በቀላሉ አስጀምረው መጠቀም የሚችሉ መሆኑን አስታውቋል።

መተግበሪያውን እስኪያስተካከሉ ድረስ አገልግሎቱን በ USSD *889# በኩል እንዲጠቀሙ በአክብሮት ገልጿል።

ከሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ጋር በተያያዘ በስልክ ተደውሎ የሚሰጥ ምንም አይነት የአሰራር ሂደት የሌለ መሆኑን በመረዳት እራስዎን ከአጭበርባሪዎች ይጠብቁ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17👍2🤣1
በደሴ ከተማ የውሻ እብደት በሽታ አሳሳቢ የማህበረሰብ ችግር እየሆነ መምጣቱ ተገለፀ

ባለፋት ዘጠኝ ወራት ውስጥ የውሻ ንክሻ ላጋጠማቸው ከ3መቶ በላይ ለሆኑ ሰዎች ህክምና መስጠቱን የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታውቋል፡፡

የሆስፒታሉ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሙያ አቶ ብርሃኑ አዱኛ ከብስራት ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት አሁን ላይ የውሻ እብደት በሽታ አሳሳቢ የማኅበረሰብ ችግር እየሆነ ይገኛል።

ባለፋት ዘጠኝ ወራት በሆስፒታሉ ለ3 መቶ 3 የእብድ ውሻ ንክሻ ተጠርጣሪዎች እና ለ172 የኬሚካል መመረዝ ላጋጠማቸው ሰዎች ህክምና መሰጠቱን አስረድተዋል።

በደሴ ከተማ 34.3 በመቶ፣ በደቡብ ወሎ 29.4 በመቶ እንዲሁም በሰሜን ወሎ 21.5 በመቶ የሆነ ከፍተኛ የእብድ ውሻ ንክሻ ስርጭት ተመዝግቧል።

ግኝቱ በአካባቢው በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች የእብድ ውሻ ንክሻ በሽታ ስርጭት መስፋፋቱን የሚያሳይ መሆኑን አቶ ብርሀኑ ጠቅሰው ይህም በክልሉ እየጨመረ ያለውን የህብረተሰብ ጤና ስጋት አጉልቶ እንደሚሳይ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል ።Via_dagu

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍2
ኢራን ሚሳይል ተኮሰች‼️
ኢራን ኩዌት ወደ ሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ባሊስቲክ ሚሳኤል አስወነጨፈች።

በጥቃቱ ቢያንስ 5 አሜሪካውያን እንደቆሰሉ ብሉምበርግ ዘግቧል።
ሁለት ሪፐር ሰው አልባ አውሮፕላኖች ክፉኛ ተጎድተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
25👍3🤔3😱1
ካናዳዊዉ ራፐር ድሬክ አርሰናል ፒኤስጂን ያሸንፋል ብሎ 1.5 ሚሊዮን ዶላር አስይዟል

ከአለማችን እዉቅ ራፐሮች አንዱ የሆነዉ ካናዳዊዉ ድምጻዊ ድሬክ አርሰናል የምሽቱን የአዉሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ፒኤስጂን ረትቶ ሻምፒዮን ይሆናል ሲል 1.5 ሚሊዮን ዶላር ማስያዙ ተዘግቧል።

ድሬክ 1 ሚሊዮን ዶላሩን በቀጥታ አርሰናል የምሽቱን ፍጻሜ ያሸንፋል ፣ እንዲሁም ቡካዮ ሳካ አሲስት ወይም ግብ ያስቆጥራል ብሎ ያስያዘዉ ሲሆን ቀሪዉን 500 ሺህ ዶላር ደግሞ አርሰናል ጨዋታዉን 1 ለ 0 ያሸንፋል ሲል መድቦበታል።

ድሬክ ከዚህ ቀደም በስፖርታዊ ዉርርዶቹ ቀንቶት አያዉቅም ይባላል። እርሱ በተደጋጋሚ ያሸንፋሉ ብሎ ገንዘቡን ያስያዘባቸዉ ክለቦች ድል ሲቀናቸዉ አልታየም።

በ 2022 አርሰናል ሊድስን ያሸንፋል ብሎ አስይዞ ድል ቀንቶት የነበረ ቢሆንም በተመሳሳይ ትኬት ግን ባርሴሎና ሪያልማድሪድን ያሸንፋል ብሎ አስይዞ ባርሳ ተረትቶ ነበር። በተለያዩ የቦክስ ጨዋታዎችም ድሬክ በመቶሺዎች ያስያዘበት ተጨዋች በተደጋጋሚ ሲረታ እንጂ ሲያሸንፍ አልታየም።

ብዙሃኑ የስፖርት አፍቃሪያኖችም "የድሬክ እርግማን" ሲሉ ሽንፈቱን ይጠሩታል። ድሬክ ገንዘብ ያስያዘበት ቡድን ይረታል እንደማለት ነዉ። ዛሬስ ድሬክ አርሰናል አሸንፎለት ይህንን እርግማኑን ያስነሳ ይሆን የሚለዉ ጥያቄ በቡዳፔስት ምሽት 1 ሰዓት ላይ የሚጀምረው ጨዋታ ሲጠናቀቅ ምላሽ ያገኛል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
28🤣14💔7👍2
ፒኤስጂ 1-1 አርሰናል

ጨዋታው ወደ ተጨማሪ ደቂቃ አምርቷል !

የአርሰናል እና ፒኤስጂ ጨዋታ በመደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።

ይህንንም ተከትሎ ጨዋታው ወደ ተጨማሪ ሰላሳ ደቂቃ አምርቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍128🤪5🤯3👏1😁1😢1🙏1👌1🏆1