ሂውማን ራይትስ ዎች፣ የኮሎምቢያ ተዋጊ ቅጥረኞች ለሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ለመዋጋት የተሠለፉት በተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች ተቀጥረው መኾኑን አዲስ ባወጣው የምርመራ ሪፖርት አስታወቀ።
ድርጅቱ፣ ኮሎምቢያዊያን ቅጥረኞቹ ሱዳን ከመግባታቸው በፊት በኢምሬቶች ወታደራዊ ጦር ሠፈሮች በኩል እንዳለፉና ሥልጠና እንደወሠዱ ማረጋገጡን ገልጧል።
ቅጥረኞቹን በመቅጠር የተሳተፈው፣ 'ግሎባል ሴኩሪቲ ሠርቪስስ ግሩፕ' የተባለ ከኢምሬቶች መንግሥት ጋር ግንኙነት ያለው የግል የጸጥታ ኩባንያ ነው ተብሏል።
ሂውማን ራይትስ ዎች፣ ሌሎች አገራት የኢምሬቶች ባለሥልጣናትን ጨምሮ በጉዳዩ ተሳታፊዎች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የሚያስችል ምርመራ እንዲደረግ ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቋል።
አገራት ከኢምሬቶች ጋር ያላቸውን ወታደራዊ ትብብርና ለአገሪቱ የጦር መሳሪያ መሸጥ እንዲያቆሙ የጠየቀው ድርጅቱ፣ የአውሮፓ ኅብረት አገራት ደሞ ኢምሬቶች ለፈጥኖ ደራሹ ኃይል ድጋፍ መስጠት እንድታቆም በባለሥልጣናቷ ላይ ግፊት እንዲያደርጉ ጥሪ አድርጓል።
@Addis_Reporter

❤12👍2
‘ዶናልድ ትራምፕ’ የተባለው ጎሽ ከእርድ ተረፈ
በባንግላዲሽ ወርቃማ ፀጉር ስላለው ‘ዶናልድ ትራምፕ’ ተብሎ የተሰየመውና በሰፊው የተነገረለት አልቢኖ ጎሽ ለዒድ አል-አድሃ በዓል ላይ ሊታረድ የነበረ ቢሆንም በመንግሥት ጣልቃ ገብነት ሕይወቱ ተርፏል።
700 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ይህ እንስሳ፣ በባንግላዲሽ እጅግ አልፎ አልፎ የሚገኝ ዝርያ በመሆኑና በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባሳየው ዝና ምክንያት የሕዝብ ትኩረት መሳብ ችሏል።
ገዢዎች እንስሳውን ለመግዛት ከፍተኛ ፍላጎት ባሳዩበት ወቅት፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት ባደረጉት አስቸኳይ ጣልቃ ገብነት ለገዢው ገንዘብ ተመላሽ ተደርጓል።
ይህ ልዩ ጎሽ ለደኅንነቱ ሲባል ከእርድ ተርፎ በዳካ ወደሚገኘው ብሔራዊ መካነ አራዊት እንዲዛወር መደረጉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

🤣24❤18👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔴 ሰበር መረጃ‼️
በስትራቴጂካዊቷ የኢራን የወደብ ከተማ ባንደር አባስ ሦስት ከባድ ፍንዳታዎች ተሰሙ፤ አሜሪካ በኢራን የድሮን ጣቢያ ላይ "ራስን የመከላከል" ጥቃት መፈጸሟን አረጋገጠች‼️
ትናንት ማታ ግንቦት 19/2018 ዓ.ም በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ አቅራቢያ በምትገኘው ስልታዊዋ የኢራን የወደብ እና የባህር ኃይል መሠረት ከተማ ባንደር አባስ (Bandar Abbas) ምሥራቃዊ ክፍል ሦስት እጅግ ከባድ የሆኑ የፍንዳታ ድምፆች ተሰምተዋል። ፍንዳታውን ተከትሎም የኢራን የአየር መከላከያ ሥርዓቶች (Air defenses) ለአጭር ደቂቃዎች ተንቀሳቅሰው እንደነበር የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
የአሜሪካ መከላከያ ባለሥልጣናት ለዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እንደገለጹት፤ የአሜሪካ ጦር ኃይል በባንደር አባስ የሚገኝን የኢራን የድሮን መቆጣጠሪያ ጣቢያ (Ground control station) በአየር ጥቃት መቷል። ይህ እርምጃ የተወሰደው ኢራን በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ ላይ ስጋት የሆኑ 4 የጥቃት ድሮኖችን ካስወነጨፈች እና በአሜሪካ ከተመቱ በኋላ፥ አምስተኛውን ድሮን ለመከላከል የተሰነዘረ ስልታዊ እርምጃ መሆኑን ዋሽንግተን አስታውቃለች።
ይህንን ተከትሎ ኢራን አሜሪካ ይህንን ጥቃት የፈፀመችው ከኩዮት የጦር ሰፈር በመነሳት ነው ያለች ሲሆን ኢራን በኩዬት በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ቤዝ ላይ ጥቃት ፈፅማለች።
ኩዬት አብዛኞቹን የኢራን ሚሳኤሎች እና ድሮን ማክሸፏን ገልፃለች።

❤19👍3🥱3👏1🤔1
ብሔራዊ ባንክ በቁጠባና ብድር ማኅበራት ላይ ቀጥተኛ ቁጥጥር ሊጀምር ነው ተባለ‼️
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቁጠባና ብድር ማኅበራትን በቀጥታ ለመቆጣጠር የወሰነው እርምጃ፣ ዘርፉ ለሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር መሸሸጊያ እንዳይሆን ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር የፋይናንስ ባለሙያ ገልፀዋል።
ባለሙያው አቶ ገመቹ ብርሃኑ፤ ማኅበራቱ ከብሔራዊ ባንክ ቁጥጥር ውጪ መቆየታቸው በፋይናንስ ገበያው ላይ ከፍተኛ መዛባትና የደህንነት ስጋት ደቅነው መቆየታቸውን ጠቁመዋል።
የፋይናንስ ባለሙያው አቶ ገመቹ ብርሃኑ እንደገለጹት፤ እስካሁን ማኅበራቱ የብሔራዊ ባንክ የቁጥጥር ማዕቀፍ ውስጥ አለመኖራቸው ለሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ወይም "መኒ ላውንድሪንግ"ሰፊ በር ከፍቶ ቆይቷል።
ሕገ-ወጥ ገንዘብ ያላቸው አካላት የገንዘቡን ምንጭ ለመደበቅ በአባላት ቁጠባ ስም በትናንሹ እየከፋፈሉ ወደ ማኅበራቱ በማስገባት፣ ወደ ሕጋዊ የባንክ ሥርዓት እንዲቀላቀል ሲያደርጉት መቆየታቸውን ባለሙያው ጠቁመዋል።
አዲሱ አሰራር ግን ይህንን የገንዘብ ማጠብ ሥራ ለመቆጣጠር ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ አብራርተዋል።

❤7👍7
የ ዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዋና ዳሪክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም
ወደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC) ማቅናታቸውን ገልፅው አያይዘው እንዲ ብለዋል.
የኢቦላ ወረርሽኝ በድጋሚ አገርሽቷል። የኢቱሪ ግዛት ደግሞ የችግሩ ዋነኛ ሰለባ ሆኗል። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት መሪነት፣ ከዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ቡድኖቻችን፣ ከአጋሮቻችን እና የጤና ባለሙያዎች ጋር በመሆን በቦታው እገኛለሁ።
ይህች አገር የኢቦላ ወረርሽኝን 16 ጊዜ ድል አድርጋለች። 17ኛው ጊዜም ከዚህ የተለየ አይሆንም። ነገር ግን አሁን፣ በጋራ መነሳት አለብን።

❤17👍9
አሜሪካ ኩባን ለመምታት‼️
የአሜሪካ ወታደሮች እና የጦር መሳሪያዎች ኩባን ለማጥቃት ዝግጅታቸውን ጨርሰው የትራምፕን የመጨረሻ ትእዛዝ ብቻ እየጠበቁ መሆኑን ፖለቲኮ ዘግቧል።

❤11😡11😱3👍2😁1🥱1
ወታደራዊ አፈሳ‼️
ህወሓት ከቅርብ ቀናት ወዲህ አስገዳጅ የወጣቶች ወታደራዊ አፈሳ እያካሄደ መሆኑንና ይህም ህዝብን በጭንቅ ውስጥ የከተተ ሆኗል።
ህወሃት ላለፉት ሁለት ሳምንት በለሊት ጭምር ቤት ለቤት ወታደራዊ አፈሳ ጀምሯል።
ይህ ሁኔታ ነዋሪው ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።
የህወሓት ተቃዋሚ ናቸው የተባሉ የመንግስትም የግልም ታጣቂዎች መሳሪያቸው እየተወሰደባቸው ይገኛል።ህወሓት " እያካሄደ ያለውን አስገዳጅ አፈሳ ለማስቆም ፓለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ሥራዎች እንዲሰሩ ስምረት ፓርቲ እንዲሁም ሳልሳዊ ወያኔ ፓርቲ ጠይቀዋል።
ምስል:- በAI የተቀናበረ

❤13🤔11😢8🥰2👍1👀1🙊1
የኢትዮጵያ የሰው ሀብት ልማት መገታቱን እና የትምህርት ጥራት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አንድ አዲስ የዓለም ባንክ ሪፖርት ጠቆመ
በሪፖርቱ የቀረቡት መረጃዎች እንደሚያሳዩት ሀገሪቱ ጥራት ያለው ትውልድ ከመገንባት አኳያ የከፋ ቀውስ ውስጥ የምትገኝ ሲሆን ይህም የወደፊት የኢኮኖሚ ዕድገቷንና የዜጎቿን የነፍስ ወከፍ ገቢ በእጅጉ የሚገድብ ሆኖ ተገኝቷል።
Via : መሠረት ሚድያ

❤12👍5🤔2😢2😁1
ውድ የአዲስ ሪፖርተር ተከታታዮቻችን ማስታወቂያ ማሰራት የምትፈልጉ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል👇
@Addis_reporter_bot
@Addis_reporter_bot
❤4👍3
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ከቀናት በፊት የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ማሻሻያ (Update) አድርጓል።
ይህን ማሻሻያ ተከትሎ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆነ ደንበኞች ከፍተኛ የአገልግሎት መስተጓጎል እየገጠማቸው መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ደንበኞች ቅሬታ ከሆነ መተግበሪያው አፕዴት ከተደረገ በኋላ፦
- አንዳንዴ ሙሉ በሙሉ ስታክ የማድረግ፣
- Passphrase አስገቡ የማለት፣
- "Unexpected error occurred!" የሚል የቴክኒክ ስህተት መልዕክት የማሳየት፣
- የመዘግየት እና ምንም አለማሳየት ችግር እየገጠማቸው መሆኑን ጠቁመዋል።
ቃላቸውን የሰጡን የባንኩ ደንበኞች ችግሩን ለመፍታት በአካል ወደ ባንክ ቅርንጫፍ ቢያመሩም ከቅርንጫፎቹ የተሰጣቸው ምላሽ " ችግሩ ከአቅማቸው በላይ " መሆኑን እንደነገሯቸው ገልጸዋል።
በዚህ ችግር ምክንያት ስራ ለመስራት፣ እንቅስቃሴ ለማድረግ ማቸገራቸውንና ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸውን ጠቁመዋል።
ወደ 951 ቢደውሉም ረጅም ደቂቃ የሚያስተናግዳቸውን እያገኙ እንዳልሆነ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምሽቱን ይፋዊ ማብራሪያ ሰጥቷል።
አዲስ መተግበሪያ በማስተዋወቁ ምክንያት በተወሰኑ ደንበኞች ላይ የአገልግሎት መስተጓጎል ማጋጠሙን አምኖ ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን፣ ችግሩን በአፋጣኝ ለመፍታት ርብርብ እያደረገ መሆኑን እና ደንበኞች በ951 የጥሪ ማዕከል ወይም ባዘጋጀው የዋትስአፕ ማህበራዊ ገጽ (https://chat.whatsapp.com/BFR1h7SrAti091qznFEP4u) በኩል ድጋፍ ማግኘት እንደሚችሉ አስታውቋል።

❤18👍6
መረጃ‼️
የኢትዮጵያ መንግሥት እና የ1 ቢሊዮን ዶላር የዩሮ ቦንድ አበዳሪ ዓለማቀፍ ባለሃብቶች በእዳ አከፋፈል ዙሪያ ሲያደርጉት የቆዩት ሌላ ዙር ድርድር ሳይሳካ ቀረ።
ድርድሩ ያልተሳካው፣ የዓለማቀፍ ቦንድ ያዥዎች መንግሥት በእዳ አከፋፈሉ ዙሪያ አሻሽሎ ያቀረበውን ሀሳብ ውድቅ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።
መንግሥት ሁሉም የውጭ አበዳሪዎች በቡድን 20 የአበዳሪዎች ማዕቀፍ ሥር የእዳ ሽግሽግ ሊያደርጉ ይገባል በሚለው አቋሙ የጸና ሲሆን፣ ኢትዮጵያ አኹንም የአበዳሪዎችን እኩልነት መርህ የሚያረጋግጥ “በገበያ ላይ የተመሠረተ መፍትሄ” ለመተግበር ቁርጠኛ መኾኗን ገልጧል።
ድርድሩ ሲካሄድ የቆየው፣ መንግሥትና የዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች ባለፈው ጥር ወር በመርህ ደረጃ የደረሱበትን ስምምነት የሁለትዮሽ አበዳሪ አገራት ኮሚቴ ሳይቀበለው ከቀረ በኋላ ነበር።(ዋዜማ)

❤12👍7😁3🤪3👏2🤔1😎1
#አሳዛኝ_ዜና‼️
ትናንት ሐሙስ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ወረጃርሶ ወረዳ፣ ከጎሐጽዮን 6 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ቀሬቡሐ ቀበሌ ከጠዋቱ 4:30 አካባቢ ከአማራ ክልል ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ ታታ የሚባለው የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ሙሉ ተጓዦች ታፍነው የተወሰዱ ሲኾን እስከአኹን ባለን መረጃ 6 ሰዎች ተገድለዋል፣አስር ቆስለዋል።
እነዚኽ ብቻ ሳይኾን ወደጫካ ሲወስዱ መሮጥ ያልቻሉትንም በርካቶችን ሳይገድሏቸው እንዳልቀረ ምንጮች ለአዩዘሀበሻ የገለፁ ሲሆን በአቅራቢያ ከሚገኘው መከላከያ ሰራዊት በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 30 ተሳፋሪዎች ከእገታ ማስለቀቁን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
ከሳምንት በፊት በገብረ ጉራቻ አካባቢ በተደጋጋሚ ጥቃት በሚደርስበት "አሊደሮ" በተባለው ቦታ ታጣቂዎች ከ60 በላይ ተሳፋሪዎችን ያያዘ "ኤፍኤም ባስ" በማስቆም በርካቶችን አግተው መውሰዳቸው፣ አብሮ የነበረ ሌላኛው 63 ሰዎች ያሳፈረ ባስም በጥይት እየተደበደበ በሹፌሩ ጥረት ማምለጡ አይዘነጋም።(አዩ)

😢35❤8😡6👍3💔3😱2🤯1🙉1
ትራምፕ በ250 ዶላር የኖት ገንዘብ ላይ እንዲታተሙ ግፊት መደረጉ ተገለጠ
የትራምፕ አስተዳደር ባለስልጣናት እና የገንዘብ ሚኒስቴር ተሿሚዎች የትራምፕ ምስል ያረፈበት አዲስ የ250 ዶላር የኖት ገንዘብ ለማዘጋጀት የዲዛይን ፕሮቶታይፕ (ናሙና) እንዲሰራ በመንግስት የገንዘብ ማተሚያ ተቋም ላይ ግፊት እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ሃሳብ የቀረበው አሜሪካ በ2026 ዓ.ም የምታከብረውን 250ኛ ዓመት የነፃነት በዓል ለማሰብ ነው። ሆኖም በህይወት ያሉ ሰዎች ምስል በአሜሪካ ገንዘብ ላይ እንዳያርፍ የሚከለክል የፌዴራል ህግ በመኖሩ እና ጉዳዩ የኮንግረስ ማፅደቅ የሚፈልግ በመሆኑ ውዝግብ መፍጠሩን ዋሽንግተን ፖስት አስነብቧል።

❤12🤡11🤪3👍2👏1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
ነፃ የትምህርት ዕድል‼️
#የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን የነጻ ትምህርት ዕድል ጥሪ አቅርቧል!!!
የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ጠንካራ ሀገራዊ የኒውክሊየር መሰረተ ልማት ለመገንባት የሚያስችሉ ከፍተኛ ባለሙያዎችን ለማፍራት ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎችና ሰልጣኞች በሩሲያ የነጻ ትምህርት ዕድል ማመቻቸቱን አስታውቋል።
@ኮሚሽኑ ለ2026/27 የትምህርት ዘመን በሩሲያ በሚገኙ ስመጥር የሳይንስና የምህንድስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ መማር የሚፈልጉ ብቁ አመልካቾች እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል።
@የሚሰጡ የትምህርት ዘርፎች በኒውክሊየር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ሲሆን እነዚህን ዘርፎችንም ያካትታል ፡-
- Nuclear Power Engineering and Heat Physics (BSc & MSc)
- Nuclear Physics and Technology (BSc)
- Nuclear Power Plants Design, Operation and Engineering (BSc)
- Heat Power Engineering (BSc)
- Management in Technological Systems (MA)
@የመወዳደሪያ መስፈርቶች ?
• ለመጀመሪያ ዲግሪ (BSc) ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት ያልበለጠ እና የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ አማካኝ ውጤታቸው 500 እና ከዚያ በላይ የሆነ።
.ለሁለተኛ ዲግሪ (MSc/MA) ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት ያልበለጠ እና በሳይንስና ምህንድስና ዘርፍ በከፍተኛ ውጤት የተመረቁ።
ሴት አመልካቾች ለዘርፉ እንዲበረታቱ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።
መስፈርቱን ምታሟሉ አመልካቾች ከዛሬ ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በPDF በማዘጋጀት በኮሚሽኑ የኢሜል አድራሻ enecinfo@enec.gov.et መላክ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።
የትምህርት ዕድል‼️

መስፈርቱን ምታሟሉ አመልካቾች ከትናንት ግንቦት 20/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በPDF በማዘጋጀት በኮሚሽኑ የኢሜል አድራሻ enecinfo@enec.gov.et መላክ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

❤20😡3👍2🤪1
"የአለም ዋንጫን በሀገሬ ቴሌቪዥን እንዳናይ እገዳ ሊጣል ነው ተብሏል
"ጋዜጠኛ ነዋይ ይመር ኢቲቪን ጥሎ ሀገሬን ከተቀላቀለ በኋላ፣ ጣቢያው የአለም ዋንጫን ለማስተላለፍ ስምምነት ተፈራርሞ ነበር።
አሁን ግን ኢቲቪ 'የጥቅም ግጭት አለ' በሚል ለሚዲያ ባለስልጣን እግድ እንዲጣል ደብዳቤ ጽፏል!"
"ከዚህም በላይ... የመንግስት ድርጅቶች በሀገሬ ቴሌቪዥን ላይ ማስታወቂያ እንዳያስነግሩ መመሪያ ወርዷል።
ሀገሬ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞችን እያስተዋወቀ ባለበት ሰዓት ይሄ መደረጉ ትክክል ነው?"
"

😡41❤15👍1😁1🤔1🍾1🤪1
በሰባተኛው አገራዊ ምርጫ ከአፍሪካ ተቋማት በስተቀር ሌሎች የውጭ ታዛቢዎች እንደማይሳተፉ ተነገረ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሚቀጥለው ሳምንት በሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከአፍሪካ ተቋማት በስተቀር የውጭ ታዛቢዎች ፈቃድ አለማግኘታቸውን ገለጸ፡፡
ምርጫ ቦርድ የሰባተኛውን አገራዊ ምርጫ አጠቃላይ የቅድመ ምርጫ ሥራዎችንና የድምፅ መስጫ ቀን አስመልክቶ፣ ማክሰኞ ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ ይህ የተገለጸው፡፡
መግለጫውን የሰጡት የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ፣ የአፍሪካ ኅብረትና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) በሰባተኛው አገራዊ ምርጫ ለመታዘብ እንደሚመጡ የሚገልጽ ዝርዝርና ሙሉ ሪፖርት ቦርዱ ደርሶታል ብለዋል፡፡
ዓለም አቀፍ ታዛቢዎችን በሚመለከት ፈቃድ የሚጠየቀውም ሆነ የሚሰጠው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሆኑንና ሁለቱ የአፍሪካ ተቋማት ለመታዘብ እንደሚመጡ የተነገራቸውና ሪፖርታቸው የተላከላቸውም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል እንደሆነ፣ ቦርዱም ለተቋማቱ የታዛቢነት ባጅ ለመስጠት ዝግጅት ላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
‹‹እነዚህ ትልልቅ ተቋማት ከሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በኋላ ወደ አገር ውስጥ ይገባሉ፤›› ብለዋል፡፡
ሪፖርተር ከሁለቱ ተቋማት ውጪ ሌሎች ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ፈቃድ ስለመጠየቃቸውም ሆነ ስለመፈቀዱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡
ሆኖም የአውሮፓ ኅብረት በታዛቢነት እንደማይሳተፍ መረጃዎች ያሳያሉ ሲል ዘግቧል፡፡
Via ሪፖርተር

😁28❤10🤪3👍2🤔2🤯2🤣1