አዲስ ሪፖርተር - NEWS
35.9K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
70 ሚሊዮን ብር ካልተከፈለኝ አልመለስም»— የማርሻል አርት ተወዳዳሪው ሴዶ ማርሻል ከቱርክ ቅድመ-ሁኔታዎችን አስቀመጠ

አዲስ አበባ — በቅርቡ ሙያዊ የውድድር ስምምነት (Professional Fight Contract) መፈረሙ የሚነገርለት የማርሻል አርት ተወዳዳሪ ሴዶ ማርሻል (Sedo Martial)፣ በአሁኑ ወቅት ከሀገር ውጪ መሆኑን ገልጾ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ለመወዳደር ከፍተኛ የገንዘብና የንብረት ጥያቄዎችን የያዘ ቅድመ-ሁኔታ አቀረበ።

ተወዳዳሪው በቱርክ አውሮፕላን ማረፊያ ሆኖ ባሰራጨው የቪዲዮ መልዕክት፣ ያለምንም በቂ ክፍያ
«በነጻ» እንዲወዳደር ለቀረበለት ጥሪ ምላሽ እንደማይሰጥና በአደራዳሪዎች ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳለው በይፋ ተናግሯል።

ሴዶ ማርሻል ወደ ሀገሩ ተመልሶ ወደ መጋጠሚያው መድረክ (Ring) ለመግባት በአጠቃላይ የ70 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸውን የሚከተሉትን ሦስት ዋና ዋና መስፈርቶች አስቀምጧል፡-

* የ20 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ዋጋ ያለው ተሽከርካሪ፤
* የ30 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የመኖሪያ ቤት፤
* በቀጥታ ወደ ግል አካውንቱ ገቢ የሚደረግ 20 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር።

እነዚህ መስፈርቶች ተሟልተው አካውንቴ ላይ ከተገቡ ብቻ መጥቼ እደባደብላችኋለሁ፤ ካልሆነ ግን በነጻ የሚሆን ምንም ነገር የለም።

በስፖርቱ ዓለም እራሱን እንደ «ፕሮፌሽናል» ተወዳዳሪ የሚቆጥረው ሴዶ፣ ስሙን ጠቅሶ «ጌች» ካለው አካልና ከሌሎች አዘጋጆች ጋር ባለው አለመግባባት ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቷል።

እሱን በነጻ በማወዳደር ሌሎች አካላት የገንዘብ ጥቅም (ቢዝነስ) ለማግኘት ማቀዳቸውን የገለጸው ስፖርተኛው፣ ይህንን አካሄድ እንደማይቀበለውና በአሁኑ ወቅት በአውሮፓ ምድር ምቹ ዝግጅት ላይ እንደሚገኝ በኩራት ተናግሯል።

ይህ የተወዳዳሪው ያልተጠበቀ መግለጫና ያስቀመጠው ከፍተኛ የገንዘብ ጥያቄ፣ በቀጣይ ሊደረጉ በታቀዱት ውድድሮች እና በአዘጋጅ ኮሚቴው ዘንድ ምን ዓይነት ምላሽ ሊያስከትል እንደሚችል የታወቀ ነገር የለም። ጉዳዩን በቅርበት መከታተላችንን እንቀጥላለን።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣8517👍5👏1🎉1👀1🙊1
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በኢቦላ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 220 መድረሱን አስታወቁ
 
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር በአሁኑ ወቅት በኢቦላ ወረርሽኝ 220 ተጠርጣሪዎች መሞታቸውን እና የበሽታዉን ተጠርጣሪዎች የመለየት ጉዳይ መዘግየት ቢኖርም ባለሙያዎች “በመቆጣጠር ላይ ናቸው” ብለዋል ።“በአሁኑ ወቅት ወረርሽኙ ከአቅማችን በላይ እየሆነ ነው” ሲሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በማንሳት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ  አዋሳኝ ሀገራት አፋጣኝ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል ብለዋል።
 
ሰኞ እለት ኡጋንዳ ሁለት ተጨማሪ የኢቦላ ተጠቂዎችን ሪፖርት አድርጋለች ፣ አጠቃላይ የተረጋገጡ የበሽታዉ ተጠቂዎች ቁጥር ወደ ሰባት ከፍ ብሏል፡፡የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ምላሽ ላይ የክትትል ጥረቱ እየጨመረ በመምጣቱ እስካሁን ከ 900 በላይ የተጠረጠሩ ሰዎች ተለይተዋል ብለዋል። ኢቦላ በቀጥታ ከሰውነት ፈሳሽ ጋር በመገናኘት የሚተላለፍ የቫይረስ በሽታ ነው። ከባድ የደም መፍሰስ እና የአካል ክፍሎች ጉዳት በማስከተል ለሞት ይዳርጋል፡፡
 
የቅርቡ ወረርሽኝ የተከሰተዉ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ሰሜን ምስራቅ ኢቱሪ ግዛት ውስጥ ሲሆን ወደ አጎራባች ክልሎችም ተሰራጭቷል፡፡ ወረርሽኙ እስከ 200 ኪ.ሜ ርቀት እንዲሁም ጀሀገሪቱ ድንበሮች ባሻገር ተስፋፍቷል፡፡ለአዲሱ የኢቦላ ዝርያ ምንም አይነት ክትባት ወይም ህክምና የለም።ባለፈው ሳምንት የአለም ጤና ድርጅት ያልተለመደዉና ቡንዲቡጊዮ የተሰኘዉ የኢቦላ ወረርሽኝ የአለም አቀፍ ስጋት የህዝብ ጤና ድንገተኛ አደጋ መሆኑን የገለጸ ሲሆን በዲሞክራቲክ ኮንጎ እና በኡጋንዳ ከተሞች ፍርሃትን አንግሷል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14😢7👍3
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለኢድ አል-አድሃ በዓል የበዓሉን አከባበር መመሪያዎች አስተላለፈ።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እና የኢድ አከባበር አስተባባሪ አቢይ ኮሚቴ፣ ነገ ረቡዕ ለሚከበረው 1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል የጸጥታ፣ የሎጂስቲክስ እና የሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶችን የተመለከቱ መመሪያዎችን ዛሬ በሰጡት መግለጫ ይፋ አድርገዋል።

በዓሉ በአዲስ አበባ ስታዲየም እና በዙሪያው የሚከበር ሲሆን፣ መጨናነቅን ለመቀነስ ምእመናን በክፍለ ከተሞች በአወሊያ፣ በኢማም አህመድ መስጂድ፣
በገርመንት አደባባይ፣ በኡመር ኢብኑል ኸጣብ መስጂድ፣ ከከነማ ፋርማሲ (ከተባበሩት) እስከ ፔፕሲ አደባባይ ያሉ ስፍራዎች  ላይ መሰገድ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

የኢድ ሰላት በጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ላይ የሚጀመር በመሆኑ ምእመናን ቀደም ብለው እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል።

ምክር ቤቱ፣ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ምእመናን ከጸጥታ አካላት ጋር እንዲተባበሩ አጥብቆ ጠይቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍4😁3
የአይኤምኤፍ (IMF) የብር ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ በገበያ እንዲወሰንና ድጎማዎች እንዲነሱ ጠየቀ

​የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ልዑክ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያደረገውን አምስተኛ ግምገማ በአዲስ አበባ አጠናቋል።

ድርጅቱ የኢትዮጵያ መንግስት የብርን የውጭ ምንዛሬ ተመን ሙሉ በሙሉ ለገበያ ፍላጎትና አቅርቦት እንዲተው፣ የመንግስት ቀጥተኛ ድጎማዎችን በሂደት እንዲያስወግድ እና የሀገር ውስጥ ታክስ ስብሰባን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያሳድግ ጠይቋል።

​ይህ የአይኤምኤፍ ጥያቄ ተግባራዊ መሆን መጀመሩን ተከትሎ፣ ውሳኔው በተራው ህዝብ እና በንግዱ ማህበረሰብ ላይ ፈጣንና ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ይገኛል።

የብር የመግዛት አቅም መውረድ፣ የዋጋ ንረት መናር እና የኑሮ ውድነት መባባስ ዋነኛ ማሳያዎች ናቸው።

በተጨማሪም መንግስት የታክስ ገቢውን ለማሳደግ የጀመረው ጥብቅ ቁጥጥር፣ መደበኛውን የታክስ ህግ የማስከበር ሂደት ወደ አስገዳጅ የቀየረው ይመስላል ሲሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ስጋታቸውን ገልጸዋል።

​ምንም እንኳን ማሻሻያው የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ መረጋጋትን ያመጣል ተብሎ በዓለም አቀፍ ተቋማት ቢታመንም፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግን ማህበረሰቡን እና የግሉን ዘርፍ ክፉኛ እየፈተነ ይገኛል።

መንግስት በበኩሉ የድሆችን ጫና ለመቀነስ የማህበራዊ ደህንነት መረቦችን እንደሚዘረጋ ቀደም ሲል መግለጹ ይታወሳል።

ዘገባው የአዲስ ፎርቹን ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢179🥱4👍3🤪3
መረጃ‼️

መንግሥታዊው ኢትዮ ቴሌኮም ወደ አክሲዮን ማኅበርነት መቀየሩንና የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያን መቀላቀሉን ዛሬ ይፋ አደረገ።

ተቋሙ በጠቅላላው አክሲዮን የገዙት 47 ሺሕ 377 ሰዎች መሆናቸውን ዛሬ አስታውቋል።

በስህተት ኢትዮጵያዊ ዜግነት ለሌላቸው 248 ሰዎች የአክሲዮን ድርሻዎችን መሸጡን የጠቀሠው ተቋሙ፣ ገንዘቡ ለገዥዎቹ ተመላሽ እንደሚያደርግ ገልጿል።

መንግሥት የኩባንያውን 10 በመቶ አክሲዮን ማለትም 100 ሚሊዮን አክሲዮኖችን በ2017 ዓ፣ም ለሽያጭ ማቅረቡ የሚታወስ ሲኾን፣ ከሽያጩም 30 ቢሊዮን ብር ይገኛል ተብሎ ተጠብቆ ነበር።

ኩባንያው በእስካሁኑ መስፈርቱን ያሟሉ 10 ነጥብ 7 ሚሊዮን አክሲዮኖች የተገኘው ገንዘብ ግን 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ብቻ እንደኾነ ተገልጧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍4👏3
" ሁሉም አሽከርካሪዎች እንደገና እንዲሰለጥኑና እንዲመዘኑ ይደረጋል " - ሚኒስቴሩ

"የመንገድ  የትራፊክ አደጋን ለመግታት" አሽከርካሪዎች በዘመናዊ አሰራር ብቃታቸው እንደገና ሊመዘን እንደሆነ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አሳወቀ።

ሚኒስቴሩ፤ " አሁን በስራ ላይ ያሉ ሁሉም አሽከርካሪዎች እንደገና እንዲሰለጥኑና እንዲመዘኑ በማድረግ ብቃታቸውን እንዲያረጋግጡ የሚያስችል አጠቃላይ የሰነድ ዝግጅት ተጠናቋል " ብሏል።

" ይህ አዲስ አሰራር ከተለመደው አሰራር በተለየ መልኩ ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንደሆነና የምዘና ሂደቱ ከእጅ ንክኪ (የሰው ጣልቃገብነት) የጸዳ እንደሆነ " አመልክቷል።

አሽከርካሪዎች ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ቅድሚያ ስልጠና እንደሚወስዱና ከመጀመሪያው ምዝገባ ጀምሮ እስከ ስልጠናው ብሎም ምዘናና ሰርተፊኬሽን ድረስ ያለው አጠቃላይ ሂደት በዘመናዊ ሲስተም እንደሚመራ ነው ሚኒስቴሩ ያመልከተው።

ይህን ስራ ለመስራት ሚኒስቴሩ SDS Safety & Driving Skills ከተባለ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጋር የስራ ውል ስምምነት መፈረሙን አሳውቋል።

ሁሉም አሽከርካሪዎች አዲሱን የብቃት ምዘና በመውሰድ እና በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ብቃታቸውን በተጨባጭ በማረጋገጥ ብቻ እንዲያሽከረክሩ የሚያስገድድ ዘመናዊ የቁጥጥር ሥርዓት እንደሚዘረጋም ተነግሯል።

ሚኒስቴሩ " ሁሉም አሽከርካሪ በዚህ ሂደት የሚያልፍ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በተለይ ለዚህ ዙር በቅድሚያ ማንኛውም የንግድ ተሽከርካሪ የሚያሽከረክር አሽከርካሪ የምዝገባና የስልጠና እንዲሁም የምዘና ሂደቱ በቅርቡ ስለሚጀመር ዝግጁ እንዲሆን " ሲል አሳስቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
28😁7🤔7👍5🤣2👏1🤯1💯1👀1
እንኳን ለኢድ-አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ 

መልካም በዓል 🙏🙏

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍86
በወሊድ ምጣኔ መቀነስ ምክንያት ትምህርት ቤቶች ባዶ ሆኑ‼️
የደቡብ ኮሪያ የወሊድ ምጣኔ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሶ በርካታ የገጠር ትምህርት ቤቶች በተማሪዎች እጥረት ምክንያት የመዘጋት ስጋት ተጋርጦባቸዋል ተባለ። እነዚህን የመማሪያ ክፍሎች ክፍት ላለማድረግ ሲባል በወጣትነታቸው መሰረታዊ የማንበብ ክህሎት ትምህርት ያላገኙ እና የተነፈጉ አዛውንቶችን መመዝገብ ጀምረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍4👏4
የኢትዮጲያ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ አርሰናልን ጨምሮ የአውሮፓ ክለቦችን ለምርጫ ቅስቀሳነት ተጠቀሙ!

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ተመስገን ጥሩነህ ትላንት በባህርዳር ስቴዲየም በምርጫ ቅስቀሳ መረሀግብር ላይ በዚህ የባህርዳር ስቴዲየም እነ አርሰናል ማንቺስተር ቼልሲ ሊቨርፑ ባርሳ ቫሌንሺያአምጥተን ማጫወት እንፈልጋለን ሲሉ የአውሮፓ ክለቦችን ለምራጫ ቅስቀሳ መጠቀማቸው ተነግሯል።

ፖለቲከኞች የወጣቱን ሙቀት እየለኩ በወጣቱ ስሜት የበሬ ወለደ ንግግር ትርፍ ለማግኘት ሲሞክሩ በጣም አስቂኝ ነው። ወጣቱ ከሰሞኑ በኳስ እንዲህ ሲደሰት ያያችሁት በሀገሪቷ ያለውን ምስቅልቅል ረስቶ አይደለም  ስራ ማጣቱንም ዘንግቶ አይደለም ፤
በጥቅሉ በሀገሪቱ ያለውን ችግር ረስቶ ሳይሆን እግርኳስ ከችግሮቹ ርቆ የሚደሰትበት አንዱ አማራጩ ስለሆነ ነው። ስለዚህ የበሬ ወለደ ወሬ ትታችሁ ለወጣቱ የሚሆን መፍትሄ ፈልጉ። ወጣቱ ዝምታን መምረጡ የናንተ ማላገጫ እንዲሆን ፈቅዶላችሀኋል ግን ተረጋጉ!

የፓርቲያችሁ ርዕዮተ አለም የሀገሪቷ ችግር ላይ ያተኩር እንጂ ወጣቱን ላሞኘው የሚል አይሁን እኛ ጅል አይደለንም።

የሕዝብ ሕልውና ማስጠበቅ ፣ የአገር ሉዓላዊነትን ማስከበር፣ በጋራ ዕሴቶች ላይ የተመሰረተ ብሄራዊ አንድነትን ማጽናት እና ለሁሉም ዜጋ እኩል እድል የሚሰጥ የፍትሕ ስርዓትን መገንባት የሚሉ ርዕዮተ አለማዊ መርሆዎች ሊኖራችሁ ሲገባ በንደዚህ ተራ ነገር የወጣቱን ቀልብ ልሳብ ተብሎ አይሞከርም። ስንት የቤት ስራ ተከምሮባችሁ ጨረቃ ላይ ስለማውጣት አትንገሩን ወጣቱ ስለሀገሩ የማይጨነቅ አይመሰላችሁ!
የሕዝብ ንቃተ - ሕሊና ላይ የሚረማመዱበት መጠን በቃል አይገለፅም። በነገራችን ላይ ይሄ ፖለቲካ አይደለም ወጣቱ ሲናገር ምክር ስሙ የኛን ክለብ የወጣቱ ልብ ውስጥ ለመግቢያ በውሸት እና በህልም እንጀራ አትጠቀሙት!

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
32🤣24👏8👍4🥰2🤯1😡1
ሰበር‼️ የኢራን አብዮታዊ ዘብ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ ላይ የአሜሪካን MQ-9 ድሮን መትተው መጣላቸውን፣ እንዲሁም የአየር መከላከያ ክፍሎቻቸው ተኩስ በመክፈታቸው አንድ የአሜሪካ RQ-4 ድሮን እና አንድ ኤፍ-35 ተዋጊ ጄት ከኢራን የአየር ክልል እንዲወጡ መገደዳቸውን አስታውቀዋል። ዘቡ የአሜሪካ ጦር የተኩስ አቁም ስምምነቱን እንዳይጥስ አስጠንቅቀው፣ የአጸፋ እርምጃ የመውሰድ መብታቸው "ህጋዊ እና ወሳኝ" መሆኑን ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍1813🤔1
ለልጆች በወር 160 ዶላር ክፍያ‼️
የታይዋን የወሊድ መጠን በዓለም ዝቅተኛው ደረጃ ላይ በመውደቁ ወሊድን ለማበረታታት ወርሃዊ የልጅ ድጎማዎችን ልትከፍል ነው። በዚህም ታይዋን ከ17 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት በወር 160 ዶላር ልትከፍል መሆኑን አስታውቃለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍135🤔4👏2
በነገሌ ቦረና የተገነባው የገዳ አውሮፕላን ማረፊያ  ተመረቀ

ይህ አውሮፕላን ማረፊያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ መዳረሻ ሲሆን፣ እንደ ቦይንግ 737 ማክስ ያሉ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን የማስተናገድ ሙሉ አቅም እንዳለው ተገልጿል።

​በምረቃው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ  እንደተናገሩት፣ አውሮፕላን ማረፊያው የአካባቢውንና ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ልውውጥን እንዲሁም ቱሪዝምን ለማሳደግ አልሞ በሳምንት ሦስት በረራዎችን ያስተናግዳል።

​"የምንገነባው እያንዳንዱ አውሮፕላን ማረፊያ ርቀትን በማጥበብ ትስስር ይፈጥራል፣ የክልሎችን ኢኮኖሚ ያነቃቃል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በፈረንጆቹ 2026 80ኛ ዓመቱን የያዘውና የአፍሪካ ኩራት የሆነው አየር መንገድ በእርግጥም “የአፍሪካ አዲሱ መንፈስ” መሆኑን በተግባር እያረጋገጠ ነው ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11🤪7👍3
የጀነራሉ እገታ እና ያሉበት መታወቅ!

ጀነራሉ መታገታቸው ተረጋገጠ፡፡ አንድ ወር ለሚሆን ጊዜ ከአደባባይ የጠፉት ጀነራሉ፤ መታገታቸውን የፈረንሳዩ ጋዜጣ ይፋ አድርጓል፡፡ ጀነራሉ ወደ አዲስአበባ እንዳይጓዙ እና ለፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ጋር እንዳይገናኙ በሚል ነው የታገቱት ተብሏል፡፡

ጀነራሉ ታግተዋል፡፡ የተረጋገጠ መረጃ ነው፡፡ ህውሃት ከአንድር ወር በፊት ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን ፕሬዝዳንት አድርጎ ጀነራል ታደሰ ላይ መፈንቅለ መንግስት ካከናወነ በኋላ፤ ጀነራሉ ጠፍተው ከርመዋል፡፡ ከዚህ የመፈንቅለ አስተዳደር በኋላ በአደባባይ ያልታዩት ጀነራል ታደሰ፤ የት ጠፉ በሚልም ብዙ ሲጠየቅ ነበር፡፡ ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚሆን መረጃ ዛሬ ይፋ ሆኗል፡፡

ታማኙ የፈረንሳይ ጋዜጣ አፍሪካን ኢንተለጀንስ ስለ ጉዳዩ ሰማሁት ያለውን መረጃ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡ ጀነራል ታደሰ ወረደ ከመቀሌ እንዳይወጡ እና እንዳይንቀሳቀሱ ታግተው እንደሚገኙ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ ‹‹ጀነራሉ ወደ አዲስአበባ እንዳይጓዙ በዚያም ከፌዴራል ባለስልጣናት ጋር እንዳይገናኙ በሚል በህውሃት ቁጥጥር ስር ናቸው›› በማለት ዘግቧል፡፡

የአፍሪካን ኢንተለጀንስ ዘገባ እንደሚያመላክተው፣ ይህ እገዳ የተጣለው በጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ እና ጌታቸው ረዳ አሰባሳቢነት ባለፈው ሳምንት በአዲስአበባ ምክርቤት መመስረቱን ተከትሎ ነው፡፡ የእነ ጀነራል ፃድቃን የአዲስአበባው ምክርቤት ሕውሓትን ባጭር ጊዜ አስወግዶ ክልሉን ለመቆጣጠር አቅዷል፡፡ ህውሓት ጀነራል ታደሰ ወደ አዲስአበባ ኮብልለው ከአዲሱ ምክርቤት ጋር እዳይቀላቀሉ በሚል ነው ጀነራል ታደሰን የቁም እስረኛ ያደረጋቸው ብሏል ዘገባው፡፡ ጀነራሉ ብዙ ሚስጥር የሚያውቁ እና ህውሃት አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ሰው በመሆናቸው እንደሆነ ጋዜጣው አብራርቷል፡፡

ከአፍሪካን ኢንተለጀንስ መረጃ መረዳት እንደተቻለው ህውሓት ጀነራሉን ለማገት የወሰነው በሁለት አበይት ምክንያቶች ናቸው፡፡ አንደኛው ጀነራሉ የእነፃድቃንን ምክርቤት እንዳይቀላቀሉ በሚል ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጀነራሉ እጅ ላይ በርካታ የሕውሓት ሚስጥሮች በመኖራቸው ነው፡፡

Via : Yene tube

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
22👍3😈1
ከ6ሺ በላይ ለሚሆኑ የአዕምሮ ህሙማን ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ የሚያግዝ ህክምና ተሰጠ
 
ይህ የህክምና ዓይነት በአእምሮ ጤና አውድ ውስጥ የተሃድሶ ህክምና የሚባል ሲሆን የአእምሮ ህመም ያለባቸው ሰዎች በህብረተሰቡ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተሳታፊ እንዲሆኑና ጥራት ያለው ሕይወት እንዲመሩ የሚረዳ የህክምና እና ድጋፍ ሂደት ነው።
 
በዚህም የአማኑኤል አዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ6ሺህ334 ዜጎች የተሀድሶ የህክምና አገልግሎት መስጠቱን የሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አብዩ የኔአለም ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።
 
ህክምናው  ​ታካሚው የዕለት ከዕለት ተግባራቱን በራሱ እንዲያከናውን የሚረዳ ራስን መንከባከብ ፣ ንፅህናን መጠበቅ እና  ከሰዎች ጋር እንዴት መግባባትና ጤናማ ግንኙነት መፍጠር እንደሚቻል የሚሰጥ ነው።
 
በተጨማሪም የስነልቦና እና ማህበራዊ ድጋፍ  የሙያ እና ስራ ስልጠና እንዲሁም ​ከሆስፒታል የወጡ ታካሚዎች በቀጥታ ወደ ማህበረሰቡ ከመቀላቀላቸው በፊት የቅርብ ክትትል የሚደረግባቸው ጊዜያዊ ማቆያዎችን ማመቻቸትን ይጨምራል።
 
ታካሚው በተቻለ መጠን በሌሎች ላይ ጥገኝነቱ እንዲቀንስ ፣ያለ አድልዎና ማግለል በቤተሰብና በሰፈር ውስጥ እንዲይኖር የሚያስችል ሲሆን ህመሙ ተመልሶ እንዳይቀሰቀስ  ራሱን እንዲጠብቅ ይረዳል ሲሉ አቶ  አብዩ የኔአለም ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍2🤯1🤩1
#ሰበር-መረጃ‼️
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከስልጣን ተነሱ‼️
የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ እና የቅርብ ሰው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከስልጣን መነሳታቸውን መሰረት ሚዲያ ዘግቧል።

ዲያቆን ዳንኤል የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩ ሲሆን፤ ከተቋሙ ሰራተኞች በተነሳባቸው ቅሬታ ምክንያት ከቦርድ ሰብሳቢነታቸው ተነስተዋል ሲል የዜና ጣብያው ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።

በምትካቸውም የኮሙኒኬሽን ሚኒስትሯ ወይዘሯ እናትአለም መለስ ተተክተዋል።

ይህን የስልጣን ሽግሽግ በተመለከተ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንም ሆነ ከመንግሥት በኩል የተባለ ነገር የለም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣3819👍8👏3🤪2🙊2🥰1🤔1🎉1🏆1
ግንቦት 24 ሥራ ዝግ ነው‼️
ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም በፌዴራል እና ክልል መንግሥታዊ ተቋማት እንዲሁም የግል ተቋማት ሥራ ዝግ ሆኖ ይውላል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚካሄደውን የ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷል።

ቦርዱ፦

- ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ሥራ ዝግ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

- ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ በፌዴራል እና በክልሎች የሚገኙ ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑ እና የግል ተቋማት በተመሳሳይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ዝግ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

- የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪዎችም (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ እንዲያከነውኑ ፤ የመተባበር ግዴታው እነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት እንደማያስገድድ አሳውቋል።

- የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም፤ ዜጎች ድምፅ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችን እና ዕቅዶችን እንዳይይዙ እና እንቅስቃሴያቸውን ድምፅ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ አረበታቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17👍6👏2🤪1