ፓይለቱ በበራራ ላይ እያለ የልብ ህመም አጋጠመው
ባለፈው አርብ ከቴነሪፍ ወደ በርሚንግሃም 220 ተጓዦችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረው የጄት2 (Jet2 LS1266) በረራ፣ ዋናው አብራሪ በድንገት በደረሰባቸው የልብ ህመም ምክንያት በፖርቶ፣ ፖርቱጋል አስቸኳይ ማረፊያ ለማድረግ ተገዷል ሲል ሜትሮ ዘግቧል።
በበረራው ወቅት የረዳት አብራሪው አይሮፕላኑን ለመቆጣጠር ከፍታ በፍጥነት በቀነሰበት ወቅት ተጓዦች ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ወድቀው ነበር።
የበረራ አስተናጋጆች እያለቀሱ በህክምና የሰለጠነ ሰው ይፈልጉ እንደነበር ተገልጿል።
አይሮፕላኑ በፖርቶ አውሮፕላን ማረፊያ በሰላም ያረፈ ሲሆን፣ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ለአብራሪው አስቸኳይ ህክምና አድርገውላቸዋል።
ተሳፋሪዎች ግን ያለምንም ማረፊያ ለአውሮፕላን ሰራተኞቹ ያላቸውን አጋርነት እየገለጹ፣ ለአስራ ሶስት ሰዓታት በአውሮፕላን ማረፊያው ለመቆየት መገደዳቸውን ተናግረዋል።
@Addis_Reporter

❤11👍3
መከላከያ “ሰም በእሳት እንደሚቀልጥ ይቀልጣሉ” ሲል ባስጠነቀቀ ማግስት ህወሓት ለኤርትራ ይፋዊ መልዕክት አስተላለፈ፤
ህወሓት ለኤርትራ ሕዝብ 35ኛ የነፃነት በዓልን ምክንያት በማድረግ ይፋዊ የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላለፈ። በመግለጫው፤ የኤርትራ ሕዝብ ለራሱ ዕድል በራሱ የመወሰን መብት ላደረገው ትግል ያለውን ድጋፍ አረጋግጦ፣ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን ወንድማማችነትና ሰላማዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚፈልግ አስታውቋል።
ይህ የህወሓት መልዕክት የተላለፈው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት “ጽምዶ” በሚባለው እንቅስቃሴ በኩል በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ የሚቃጣን ስጋት ለመመከት እርምጃ እንደሚወስድ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ካሳወቀ ማግስት ነው ሜ/ጄነራል ተሾመ ገመቹ ለዲፕሎማቶች በሰጡት መግለጫ ይህን እንቅስቃሴ “ወደ መሬት እናወርዳለን” ብለው ስንዝር እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላት “ሰም በእሳት እንደሚቀልጥ ይቀልጣሉ” ሲሉ ከትናንት በስቲያ ነበር ያስጠነቀቁት።

❤19🤪4👍2🤩2🤷2😁1🙊1
የታሸጉ ምርቶች ተጠቃሚነት በመጨመሩ ታዳጊዎችን ለደምግፊት እየተጋለጡ ይገኛል
እንደ ግፊት ያሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ከዕድሜ ጋር ቁርኝት ያላቸዉ ሲሆን ዕድሜ በጨመረ ቁጥር የመከሰት ዕድላቸዉ ሰፊ ነዉ። ነገር ግን ታዳጊዎች ለዚህ ችግር ተጋላጭ እየሆኑ መምጣታቸዉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል ።
በሚኒስቴሩ የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ህይወት ሰለሞን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ከ50 በመቶ በላይ የማህበረሰብ የሞት ምክንያት እየሆኑ መምጣታቸውን ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል ።
የአኗኗር ስርዓት እየተቀየረ መምጣት በተለይ በፋብሪካ ዉስጥ ተቀነባብረዉ የሚያልፉ ምግቦችን አዘዉትሮ መጠቀም የታዳጊዎችን ለግፊት ተጋላጭነት እየጨመረ ይገኛል ። በፋብሪካ ተቀነባብረዉ የሚያልፋ ምግቦች ለጤና ጠቃሚ ያልሆኑ ይዘት ያላቸዉ በመሆኑ ለበሽታው አጋላጭ ናቸዉ።
ከእነዚህም መካከል ከፍተኛ የጨዉ መጠን ያላቸዉ የታሸጉ ምግቦች በስፋት በህፃናትም ይሁን በአዋቂዎች ዘንድ ተመራጭ እየሆኑ መምጣታቸዉን ያነሱት ዶክተር ህይወት በተመሳሳይ መልኩ የቅባት አይነታቸዉ ለጤና ጠንቅ የሆኑ ምግቦች በስፋት ጥቅም ላይ ሲዉሉ ይስተዋሏል።
በተጨማሪም በመጠጥ ይሁን በደረቅ ምግብ ላይ የስኳር መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦች ተመራጭ እየሆኑ መጥተዋል ። ሌሎች አጋላጭ ምክንያቶች እንዳሉ ሆነዉ ታዳጊዎች ላይ የሚከሰት የደም ግፊትን ለመከላከል የታሸጉ ምርቶች አጠቃቀምን ማስተካከል ይገባል። ልጆቻቸዉን የለስላሳ መጠጦችንና የታሸጉ ምርቶችን አሲዘዉ ትምህርት ቤት የሚልኩ ወላጆች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ ተላልፋል።
1.4 ቢሊዮን የሚሆነዉ የዓለም ህዝብ ከፍተኛ ከሆነ የደም ግፊት ጋር እንደሚኖር የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

❤14🤯3👍2
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለውጭ ንግድ ተዋንያን አዲስ ፈቃድና የዋጋ ማስተካከያ ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ቢሮክራሲን ለማቅለልና የንግድ ከባቢውን ለማሻሻል በሚል በውጭ ምንዛሬ መመሪያው ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ።
በአዲሱ መመሪያ መሠረት፣ የውጭ ምንዛሬ እና የቁጠባ (Retention) አካውንት ያላቸው ተቋማት ያለ ብሔራዊ ባንክ ቅድመ ፈቃድ የሥራ ማረጋገጫ ሰነድ (LC) እና በሰነድ ማረጋገጫ ክፍያ (CAD) በባንኮች በኩል ማጽደቅ ይችላሉ።
በተጨማሪም፣ እነዚህ ተቋማት ያለ ባንኮች ቅድመ ፈቃድ የዕቃ ጭነት ትዕዛዝ ማስተላለፍ የሚችሉ ሲሆን፣ ክፍያው ግን ሰነዶችን በማረጋገጥ ላይ የተመሠረተ ይሆናል።
በሌላ በኩል፣ ብሔራዊ ባንኩ በኤልሲ (LC) ግብይቶች ላይ የሚጣሉ ክፍያዎችን ከዓለም አቀፍ አሠራር ጋር ለማስማማት የዋጋ ማስተካከያ አድርጓል።
በዚህም መሠረት የኤልሲ አገልግሎት ክፍያዎች በዓመታዊ ተመን ተሰልተው፣ እንደ ኤልሲው የአገልግሎት ዘመን (tenor) በቪሶ (pro-rata) የሚታሰቡ ይሆናል።
ይህም የአስመጪና ላኪዎችን የግብይት ወጪ በመቀነስ የውጭ ንግድ ተወዳዳሪነትን ያሳድጋል ተብሏል።

❤10👍4
ዶክተር ደብረፅዮን የኤሌክትሪክ የህዝብ ትራንስፖርት ለማቅረብ ወሰኑ፡፡
በዛሬው እለት ደግሞ ይህ ካቢኔ በኤሌክትሪክ የሚሰራ የህዝብ ትራንስፖርት ለማቅረብ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ደብረጽዮን እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የፌዴራል መንግስቱ በነዳጅ ላይ የጣለው እገዳ በትራንስፖርት ላይ ችግሮችን በመፍጠሩ ነው፡፡ እነዚህን ችግሮች ለማቃለል ለህዝብ ትራንስፖርት የሚውሉ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውቶቡሶችን እንደሚያስገባ የገለፀው ፅህፈት ቤቱ ጨምሮም ለመንግስት ሰራተኞች ደግሞ ማእከላዊ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡

🤣41❤24👍16🤪6🤯3🤷♂2👏1😢1👀1🙈1🫡1
የአሜሪካ እና ኢራን ስምምነት‼️
የአሜሪካ-ኢራን የስምምነት ረቂቅ (draft) እንደሚከተለው ቀርቧል።
📌የተኩስ አቁሙ ለ60 ቀን እንዲራዘም
📌ኢራን ነዳጇን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በነፃነት መሸጥና መላክ ትችላለች።
📌ሆርሙዝ ያለ ክፍያ ይከፈታል, በሰርጡ የተቀበሩ ፈንጂዎች ይወገዳሉ።
📌በኢራን ነዳጅ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ይቃለላል።
📌 አሜሪካ በኢራን ወደቦች ላይ የጣለችው እገዳ ይቃለላል።'
📌በኑክሌር ዙሪያ በ 60-ቀን ጊዜ ውስጥ ድርድር እንዲደረግ' የሚሉ ናቸው።
እስካሁን ሁለቱ ሀገራት በይፋ አልተፈራረሙም።
ምንጫችን አልአረቢያ ነው።

👍10❤6👏4🤪2
ነገ መስቀል አደባባይ በሚደረገው ፕሮግራም ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
በመሆኑም ፕሮግሙ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ፦
ከመገናኛ በባንቢስ ሱፐር ማርኬት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ
ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ጥላሁን አደባባይ ወይም መሾለኪያ ለከባድ ተሽከርካረዎች አጎና ሲኒማ
ከሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለገሃር መብራት
ከንግድ ባንክ ወደ አዲስ አበባ ስቴዲዩም ቴሌ መ/ቤት
ከፒያሳ በአምባሳደር ቴአትር ወደ መስቀል አደባባይ ሀራምቤ ሆቴል
ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግስት
ከሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ለገሃር መብራት
በቦሌ መንገድ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎፒምያ ወይም ደንበል አደባባ ጋር ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
መረጃ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ በተጠቀሱ አካባቢ ለአጭርም ሆነ ለእረጅም ጊዜ ተሽከርከካሪ አቆሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ዋና መምሪያው ገልጾ መሰል ፕሮግሞች በሚዘጋጁበት ወቅት ሆነ በሌሎች የፀጥታ ስራዎች ህዝቡ እያደረገ ላለው ቀና ትብብር የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምስጋናውን እያቀረበ አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እዳያጋጥማቸው አመራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

❤6😁5👍2🫡2
ኢትዮጵያውያንን ያገቱ ኢትዮጵያውያን በደቡብ አፍሪካ‼
በደቡብ አፍሪካ አምስት ኢትዮጵያውያንን አግተው የያዙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ደቡብ አፍሪካ ፖሊስ በሊምፖፖ ግዛት በአንድ አነስተኛ የገበያ ሱቅ ውስጥ ታግተው የነበሩ አምስት ኢትዮጵያውያን ማስለቀቁንና ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉ ሁለት ኢትዮጵያውያን ተጠርጣሪዎን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ዘ ሲቲዘን ዘግቧል።
ከዚህ የወንጀል ድርጊት ጋር በተያያዘ ሚስጋኑ ጌታቸው እና ተሻለ ጡሜቦ የተባሉ ሁለት የኢትዮጵያ ዜጎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፤ ከዚህ የወንጀል ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች ግን አምልጠው በመሰወራቸው ፖሊስ ከፍተኛ ክትትል እያደረገ ይገኛል።

😢19❤12🤔3👍2👏1
በኢትዮጵያ የእቃ አስተላላፊነት ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ሆነ‼️
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ የእቃ አስተላላፊነት ዘርፍን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ለማድረግ ውሳኔ አስተላለፈ።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ ዛሬ ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ የእቃ አስተላላፊነት ዘርፍን ለውጭ ባለሃብቶች ተሳትፎ ክፍት ለማድረግ ውሳኔ አሳልፏል።
ቀደም ሲል በደንብ ቁጥር 474/2012 የውጭ ባለሀብቶች የዕቃ አስተላላፊነት የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ለአገር ውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች የቅንጅት ኢንቨስትመንት የተከለለ ሲሆን የውጭ ባለሃብቶች የካፒታል የሽርክና ተሳትፎም በ49% ተገድቦ ቆይቷል።
ከዚህም የተነሳ በዘርፉ የሚፈለገውን አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፍሰት ላይ ክፍተት ፈጥሮ የቆየ ሲሆን የቦርዱ ውሳኔም ይህን እና መሰል ችግሮችን የሚቀርፍ እንደሚሆን ይጠበቃል።
በዘርፉ የተሰማሩ ነባር ባለሃብቶችንም ሆነ አዲስ ወደ ዘርፉ ለሚገቡት ባለሃብቶች በሎጂስትክስ ዘርፉ ላይ ተጨማሪ እምነት እንዲያሳድሩም የሚያግዝ ነው ተብሏል።
በውሳኔው መሰረት ዘርፉን ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት ማድረግ ፈጣን ቀልጣፋ እና ዘመናዊ የሎጂስቲክስ አገልግሎት ለመስጠት፣ አገራዊ የሎጂስቲክስ ወጪን ለመቀነስ፣ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማምጣት እንዲሁም የአገር ውስጥ ተዋናዮች አቅማቸውን አሳድገው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።

❤13👍2🤯1
#ሰበር_መረጃ‼️
የአሜሪካ ጦር በደቡባዊ ኢራን ፈንጂዎችን ለማጥመድ በሚሞክሩ ጀልባዎች እና በሚሳኤል ማስወንጨፊያ ጣቢያዎች ላይ "ራስን የመከላከል እርምጃ" ሲል በገለጸው ወታደራዊ ዘመቻ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ።
የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ የዚህ ጥቃት ዋና ዓላማ "ከኢራን ኃይሎች የሚሰነዘሩ ስጋቶችን በመቀልበስ የጦር ሰራዊታችንን ደህንነት ለመጠበቅ ታስቦ የተወሰደ እርምጃ ነው" ብሏል። አሜሪካ ይህንን ጥቃት የፈፀመችው ሁለቱ ሀገራት ድርድር እያደረጉ ባለበት ሰዓት ነው።

❤10👍2👏1🤯1😡1
ወደ ቻይና የሚላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ (EXPORT) ፈቃድ በሁሉም ባንኮች እንዲሰጥ ተወሰነ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ወደ ቻይና የሚላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ (EXPORT) ፈቃድ በሁሉም ባንኮች እንዲሰጥ ወስኗል።
ብሔራዊ ባንክ መንግሥት ከቻይና ጋር በነበረው አጠቃላይ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ትብብር ስምምነት መሠረት ወደ ቻይና የሚላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ ፈቃድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ብቻ እንዲሰጥ ቀደም ሲል በቁጥር ባውምዳ/097/99 በጻፈው ደብዳቤ መወሰኑ አስታውሶ ነገር ግን የሀገሪቱን የወጪ ንግድ ዘርፍ ይበልጥ ለማቀላጠፍ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ እና ለላኪዎች ምቹና ተደራሽ የባንክ አገልግሎት ለመፍጠር ሲባል ይህ ቀደም ሲል ተጥሎ የነበረው ገደብ ሙሉ በሙሉ መነሳቱን አስታውቋል።
ከዛሬ ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ቻይና የሚላኩ ማናቸውም የወጪ ንግድ (EXPORT) ምርቶች የፈቃድ አሰጣጥ ሰነድ ማደራጀትና ተያያዥ የባንክ አገልግሎቶች በሀገሪቱ ውስጥ ፈቃድ ባላቸው በሁሉም ባንኮች በኩል መስተናገድ የሚችሉ እንደሆነ ተገልጿል።
ሁሉም የንግድ ባንኮች ከተለመዱት የወጪ ንግድ እና የውጭምንዛሪ መመሪያዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ ለደንበኞቻቸው አገልግሎቱን እንዲሰጡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማሳሰቡን ቅዳሜ ገበያ ከመግለጫው ተመልክቷል፡፡

❤7👍6🤯2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለአንድ ድሮን 10 ህንፃ‼️
ለእያንዳንዱ የሂዝቦላህ የድሮን ጥቃት በቤሩት ውስጥ 10 የመኖሪያ ሕንፃዎች ማውደም አለብን ሲሉ የእስራኤል ፋይናንስ ሚኒስትር ቤዛሊል ስሞትሪች አስታወቁ።

❤9😡6👍3👏1🤯1
በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ የሚገኙ ከ ከ432 ሺህ በላይ ዜጎችን ወደ ሀገር ተመልሰዋል
ከተመላሽ ዜጎች መካከል 308 ሺህ 155 ወንድ እና 101 ሺህ 636 ሴቶች እንዲሁም 22 ሺህ 900 እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዲጊ ህጻናት ይገኙበታል።
መንግስት መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ከመከላከል ጎን ለጎን ዜጎች ሰብዓዊ ክብራቸው በተጠበቀበት አግባብ በህጋዊ መንገድ ሰርተው የሚጠቀሙበት አሰራር በመዘርጋት በስራ ላይ እንዲውል አድርጓል።
ከስደት ተመላሽ ዜጎችን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማድረግ የሚያስችሉ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።
በዚህም እስካሁን 432 ሺህ 691 ዜጎችን በጊዜያዊ መጠለያና በማቆያ ማዕከላት በመቀበል የስነልቦና፣ የማህበራዊ፣ የኢኮኖሚ አገልግሎት በመስጠት ወደ ማህበረሰቡ የማቀላቀል ስራ በትኩረት ተሰርቷል።
በሌላ በኩል መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት ከሀገር ሊወጡ ሲሞክሩ በድንበር አካባቢ በተለይም በሞያሌ፣ ጋላፊ፣ መተማና ቶጎጫሌ ኬላዎች የተያዙትን ጨምሮ መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት ወደ ተለያዩ ሀገራት ሄደው በዋናነት ከሳዑዲ ዓረቢያ፣ ከየመን፣ ከኦማን፣ ከኳታር፣ ከቤሩት እንዲሁም ከማይናማር የተመለሱ የፍልሰት ተጎጂዎች አስፈላጊውን የሥነ-ልቦናና የማህበራዊ አገልግሎቶች እንዲያገኙ በማስቻል ከቤተሰቦቻቸውና ከማህበረሰቡ ጋር እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡

👍11❤5😱1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
70 ሚሊዮን ብር ካልተከፈለኝ አልመለስም»— የማርሻል አርት ተወዳዳሪው ሴዶ ማርሻል ከቱርክ ቅድመ-ሁኔታዎችን አስቀመጠ
አዲስ አበባ — በቅርቡ ሙያዊ የውድድር ስምምነት (Professional Fight Contract) መፈረሙ የሚነገርለት የማርሻል አርት ተወዳዳሪ ሴዶ ማርሻል (Sedo Martial)፣ በአሁኑ ወቅት ከሀገር ውጪ መሆኑን ገልጾ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ለመወዳደር ከፍተኛ የገንዘብና የንብረት ጥያቄዎችን የያዘ ቅድመ-ሁኔታ አቀረበ።
ተወዳዳሪው በቱርክ አውሮፕላን ማረፊያ ሆኖ ባሰራጨው የቪዲዮ መልዕክት፣ ያለምንም በቂ ክፍያ
«በነጻ» እንዲወዳደር ለቀረበለት ጥሪ ምላሽ እንደማይሰጥና በአደራዳሪዎች ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳለው በይፋ ተናግሯል።
ሴዶ ማርሻል ወደ ሀገሩ ተመልሶ ወደ መጋጠሚያው መድረክ (Ring) ለመግባት በአጠቃላይ የ70 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸውን የሚከተሉትን ሦስት ዋና ዋና መስፈርቶች አስቀምጧል፡-
* የ20 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ዋጋ ያለው ተሽከርካሪ፤
* የ30 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የመኖሪያ ቤት፤
* በቀጥታ ወደ ግል አካውንቱ ገቢ የሚደረግ 20 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር።
እነዚህ መስፈርቶች ተሟልተው አካውንቴ ላይ ከተገቡ ብቻ መጥቼ እደባደብላችኋለሁ፤ ካልሆነ ግን በነጻ የሚሆን ምንም ነገር የለም።
በስፖርቱ ዓለም እራሱን እንደ «ፕሮፌሽናል» ተወዳዳሪ የሚቆጥረው ሴዶ፣ ስሙን ጠቅሶ «ጌች» ካለው አካልና ከሌሎች አዘጋጆች ጋር ባለው አለመግባባት ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቷል።
እሱን በነጻ በማወዳደር ሌሎች አካላት የገንዘብ ጥቅም (ቢዝነስ) ለማግኘት ማቀዳቸውን የገለጸው ስፖርተኛው፣ ይህንን አካሄድ እንደማይቀበለውና በአሁኑ ወቅት በአውሮፓ ምድር ምቹ ዝግጅት ላይ እንደሚገኝ በኩራት ተናግሯል።
ይህ የተወዳዳሪው ያልተጠበቀ መግለጫና ያስቀመጠው ከፍተኛ የገንዘብ ጥያቄ፣ በቀጣይ ሊደረጉ በታቀዱት ውድድሮች እና በአዘጋጅ ኮሚቴው ዘንድ ምን ዓይነት ምላሽ ሊያስከትል እንደሚችል የታወቀ ነገር የለም። ጉዳዩን በቅርበት መከታተላችንን እንቀጥላለን።

🤣85❤17👍5👏1🎉1👀1🙊1
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በኢቦላ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 220 መድረሱን አስታወቁ
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር በአሁኑ ወቅት በኢቦላ ወረርሽኝ 220 ተጠርጣሪዎች መሞታቸውን እና የበሽታዉን ተጠርጣሪዎች የመለየት ጉዳይ መዘግየት ቢኖርም ባለሙያዎች “በመቆጣጠር ላይ ናቸው” ብለዋል ።“በአሁኑ ወቅት ወረርሽኙ ከአቅማችን በላይ እየሆነ ነው” ሲሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በማንሳት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አዋሳኝ ሀገራት አፋጣኝ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል ብለዋል።
ሰኞ እለት ኡጋንዳ ሁለት ተጨማሪ የኢቦላ ተጠቂዎችን ሪፖርት አድርጋለች ፣ አጠቃላይ የተረጋገጡ የበሽታዉ ተጠቂዎች ቁጥር ወደ ሰባት ከፍ ብሏል፡፡የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ምላሽ ላይ የክትትል ጥረቱ እየጨመረ በመምጣቱ እስካሁን ከ 900 በላይ የተጠረጠሩ ሰዎች ተለይተዋል ብለዋል። ኢቦላ በቀጥታ ከሰውነት ፈሳሽ ጋር በመገናኘት የሚተላለፍ የቫይረስ በሽታ ነው። ከባድ የደም መፍሰስ እና የአካል ክፍሎች ጉዳት በማስከተል ለሞት ይዳርጋል፡፡
የቅርቡ ወረርሽኝ የተከሰተዉ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ሰሜን ምስራቅ ኢቱሪ ግዛት ውስጥ ሲሆን ወደ አጎራባች ክልሎችም ተሰራጭቷል፡፡ ወረርሽኙ እስከ 200 ኪ.ሜ ርቀት እንዲሁም ጀሀገሪቱ ድንበሮች ባሻገር ተስፋፍቷል፡፡ለአዲሱ የኢቦላ ዝርያ ምንም አይነት ክትባት ወይም ህክምና የለም።ባለፈው ሳምንት የአለም ጤና ድርጅት ያልተለመደዉና ቡንዲቡጊዮ የተሰኘዉ የኢቦላ ወረርሽኝ የአለም አቀፍ ስጋት የህዝብ ጤና ድንገተኛ አደጋ መሆኑን የገለጸ ሲሆን በዲሞክራቲክ ኮንጎ እና በኡጋንዳ ከተሞች ፍርሃትን አንግሷል፡፡

❤14😢7👍3
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለኢድ አል-አድሃ በዓል የበዓሉን አከባበር መመሪያዎች አስተላለፈ።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እና የኢድ አከባበር አስተባባሪ አቢይ ኮሚቴ፣ ነገ ረቡዕ ለሚከበረው 1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል የጸጥታ፣ የሎጂስቲክስ እና የሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶችን የተመለከቱ መመሪያዎችን ዛሬ በሰጡት መግለጫ ይፋ አድርገዋል።
በዓሉ በአዲስ አበባ ስታዲየም እና በዙሪያው የሚከበር ሲሆን፣ መጨናነቅን ለመቀነስ ምእመናን በክፍለ ከተሞች በአወሊያ፣ በኢማም አህመድ መስጂድ፣
በገርመንት አደባባይ፣ በኡመር ኢብኑል ኸጣብ መስጂድ፣ ከከነማ ፋርማሲ (ከተባበሩት) እስከ ፔፕሲ አደባባይ ያሉ ስፍራዎች ላይ መሰገድ እንደሚችሉ ገልጸዋል።
የኢድ ሰላት በጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ላይ የሚጀመር በመሆኑ ምእመናን ቀደም ብለው እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል።
ምክር ቤቱ፣ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ምእመናን ከጸጥታ አካላት ጋር እንዲተባበሩ አጥብቆ ጠይቋል።

❤7👍4😁3
የአይኤምኤፍ (IMF) የብር ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ በገበያ እንዲወሰንና ድጎማዎች እንዲነሱ ጠየቀ
የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ልዑክ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያደረገውን አምስተኛ ግምገማ በአዲስ አበባ አጠናቋል።
ድርጅቱ የኢትዮጵያ መንግስት የብርን የውጭ ምንዛሬ ተመን ሙሉ በሙሉ ለገበያ ፍላጎትና አቅርቦት እንዲተው፣ የመንግስት ቀጥተኛ ድጎማዎችን በሂደት እንዲያስወግድ እና የሀገር ውስጥ ታክስ ስብሰባን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያሳድግ ጠይቋል።
ይህ የአይኤምኤፍ ጥያቄ ተግባራዊ መሆን መጀመሩን ተከትሎ፣ ውሳኔው በተራው ህዝብ እና በንግዱ ማህበረሰብ ላይ ፈጣንና ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ይገኛል።
የብር የመግዛት አቅም መውረድ፣ የዋጋ ንረት መናር እና የኑሮ ውድነት መባባስ ዋነኛ ማሳያዎች ናቸው።
በተጨማሪም መንግስት የታክስ ገቢውን ለማሳደግ የጀመረው ጥብቅ ቁጥጥር፣ መደበኛውን የታክስ ህግ የማስከበር ሂደት ወደ አስገዳጅ የቀየረው ይመስላል ሲሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ስጋታቸውን ገልጸዋል።
ምንም እንኳን ማሻሻያው የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ መረጋጋትን ያመጣል ተብሎ በዓለም አቀፍ ተቋማት ቢታመንም፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግን ማህበረሰቡን እና የግሉን ዘርፍ ክፉኛ እየፈተነ ይገኛል።
መንግስት በበኩሉ የድሆችን ጫና ለመቀነስ የማህበራዊ ደህንነት መረቦችን እንደሚዘረጋ ቀደም ሲል መግለጹ ይታወሳል።
ዘገባው የአዲስ ፎርቹን ነው።

😢17❤9🥱4👍3🤪3
መረጃ‼️
መንግሥታዊው ኢትዮ ቴሌኮም ወደ አክሲዮን ማኅበርነት መቀየሩንና የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያን መቀላቀሉን ዛሬ ይፋ አደረገ።
ተቋሙ በጠቅላላው አክሲዮን የገዙት 47 ሺሕ 377 ሰዎች መሆናቸውን ዛሬ አስታውቋል።
በስህተት ኢትዮጵያዊ ዜግነት ለሌላቸው 248 ሰዎች የአክሲዮን ድርሻዎችን መሸጡን የጠቀሠው ተቋሙ፣ ገንዘቡ ለገዥዎቹ ተመላሽ እንደሚያደርግ ገልጿል።
መንግሥት የኩባንያውን 10 በመቶ አክሲዮን ማለትም 100 ሚሊዮን አክሲዮኖችን በ2017 ዓ፣ም ለሽያጭ ማቅረቡ የሚታወስ ሲኾን፣ ከሽያጩም 30 ቢሊዮን ብር ይገኛል ተብሎ ተጠብቆ ነበር።
ኩባንያው በእስካሁኑ መስፈርቱን ያሟሉ 10 ነጥብ 7 ሚሊዮን አክሲዮኖች የተገኘው ገንዘብ ግን 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ብቻ እንደኾነ ተገልጧል።

❤10👍4👏3