ኬቭ ስትነድ አመሸች‼️
የዩክሬን ዋና መዲና ኬቬ በራሺያ ኦርሸኒክ ሚሳይል እና ካሚካዚ ድሮን ስትነድ አመሸች።
ዩክሬን በራሺያ ላይ ከሰሞኑ ጥቃት መፈፀሟን ተከትሎ ራሺያ በትናንትናው ዕለት ምሽት 90 ሚሳይል እና ከ600 በላይ ድሮን በመጠቀም በዩክሬን ላይ ጥቃት የፈፀመች ሲሆን ከ90 በላይ ሰዎች እንደተጎዱ ተዘግቧል። አንድ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያን ሙሉ ለሙሉ ተቃጥሏል።
@Addis_Reporter

👍14❤5⚡4💔1
ሀገሬ ቴሌቪዥን የዓለም ዋንጫና ኦሊምፒክን በነፃ ለማስተላለፍ ታሪካዊ ስምምነት ተፈራረመ
ሀገሬ ቴሌቪዥን ታላላቅ ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ሁነቶችን የማቅረብ ሙሉ መብት ካለው የማርኬቲንግ እና ሚዲያ ሶሉሽን (MMS) ጋር ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት የሚቆይ ታሪካዊ የስርጭት ስምምነት ተፈራረመ።
ይህ በሀገሪቱ የግል ሚዲያ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነው ውል፥ ጣቢያው የ2026 የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫን በነፃ ስርጭት ለሕዝብ እንዲያደርስ ያስችለዋል።
በተጨማሪም ጣቢያው የኦሊምፒክና የዓለም አትሌቲክስ ውድድሮችን በብቸኝነት የማስተላለፍ ልዩ መብት ተረክቧል።

❤40👍6
የታክስ ተመላሽ ክፍያ በጊዜ ገደቡ ካልተፈጸመ ባለሥልጣኑ ለከፋዩ ወለዱን ጨምሮ እንዲከፍል የሚያስገድድ መመሪያ ወጥቷል።
የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ተመላሽ አሰጣጥ ሥርዓትን ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ ለመምራት ያስችላል ያለውን "የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ የሚደረግበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 1132/2018" አውጥቷል።
ይህ አዲስ መመሪያ የወጣው ቀደም ሲል የነበረው የታክስ አዋጅ ተሽሮ በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 መተካቱን ተከትሎ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም የታክስ ተመላሽ አገልግሎትን የታክስ ከፋዮችን የስጋት ደረጃ መሠረት ባደረገ መልኩ ዘመናዊ ለማድረግ ነው።
መመሪያው የታክስ ተመላሽ ጥያቄ የሚያቀርቡ ከፋዮችን በሦስት ዋና ዋና የስጋት ደረጃዎች የሚከፍል ሲሆን፣ ይህም የኦዲትና የማጣራት ሥራው በታማኝ ከፋዮች ላይ የሚፈጥረውን እንግልት ለመቀነስ ያለመ ነው ይላል።
በዚህም መሠረት ዝቅተኛ የስጋት ደረጃ ያላቸው ከፋዮች ሰፊ ኦዲት ሳይደረግባቸው በተፋጠነ ሁኔታ ተመላሽ የሚያገኙበት ሥርዓት ሲዘረጋ፣ መካከለኛና ከፍተኛ የስጋት ደረጃ ላይ የሚገኙ ከፋዮች ደግሞ እንደሁኔታው ዝርዝርና ጥብቅ የሰነድ ማጣራት እንዲሁም የኦዲት ምርመራ ይደረግባቸዋል።
ይህም በመንግሥት ገቢ ላይ ሊፈጠር የሚችለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመከላከልና ተገቢው የታክስ ተመላሽ ለትክክለኛው ከፋይ መድረሱን ለማረጋገጥ ይረዳል ይላል።
በመመሪያው ዝርዝር አፈጻጸም መሠረት፣ በዜሮ የማስከፈያ ልክ ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ ለሚልኩ አምራቾች፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወርቅ ለሚያቀርቡና ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ የካፒታል ዕቃ ግዥ ለፈጸሙ ከፋዮች ልዩ ትኩረት ሰጥቷል።
በተለይም በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተመርጠው ወደ ውጭ ላኪነት የተሰማሩ አምራቾች ምርታቸውን ወደ ውጭ ከመላካቸው በፊት በሀገር ውስጥ ለገዟቸው ግብዓቶች የከፈሉት ታክስ በሰባት ቀናት ውስጥ የሚመለስበት "የተፋጠነ የተመላሽ ሥርዓት" ተዘርግቷል።
ሌሎች መደበኛ የተመላሽ ጥያቄዎች ደግሞ አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎባቸው በአርባ አምስት ቀናት ውስጥ ውሳኔ እንዲያገኙ በመመሪያው ተደንግጓል።
የታክስ ተመላሽ ጥያቄ የሚያቀርቡ አካላት ሊያሟሏቸው የሚገቡ ጥብቅ ቅድመ ሁኔታዎችም በመመሪያው የተካተቱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ግብይቱ የተፈጸመባቸው ሕጋዊ ኦርጅናል ደረሰኞች፣ የባንክ ክፍያ ማረጋገጫዎችና ሌሎች ተያያዥ ሰነዶች ይገኙበታል።
መመሪያው በተለየ ሁኔታ ካስቀመጣቸው ነጥቦች መካከል፣ ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከ50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር በላይ የሆኑ ማናቸውም ግብይቶች በባንክ በኩል ካልተፈጸሙና የጥሬ ገንዘብ ግብይት ገደብን ካላለፉ ለታክስ ተመላሽ ጥያቄ ተቀባይነት እንደማይኖራቸው በግልጽ አስፍሯል።
የታክስ ባለሥልጣኑ (ገቢዎች ሚኒስቴር) ተመላሽ ሊደረግ የሚገባውን ገንዘብ በሕጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሳይከፍል ከዘገየ፣ ለከፋዩ የወለድ ክፍያ የመክፈል ግዴታ የሚኖርበት መሆኑን መመሪያው ያዛል።
ወለዱ የተመላሸ ሒሣብ መከፈል ከነበረበት አግባብነት ካለው ጊዜ መጨረሻ ጀምሮ ተመላሹ ሒሣብ እስከተከፈለ ድረስ ላለው ጊዜ የሚሰላ ሲሆን የወለድ ምጣኔውም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ባንኮች የንግድ ብድር የሚሰጡበት ከፍተኛው የወለድ ምጣኔ መሰረት ይሆናል፡፡
ወለዱን ለመክፈል አግባብ ላለው ፍ/ቤት ቀርቦ የተሰጠ ውሳኔ ማስረጃ በማያያዝ ውሳኔው በተሰጠበት በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ መቅረብ አለበት፤በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ያልቀረበ ጥያቄ መብቱ እንደተወ እንደሚቆጠር መመሪያው ደንግጓል፡፡
ይህ መመሪያ በፍትህ ሚኒስቴር ተመዝግቦ የጸደቀ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከገቢዎች ሚኒስቴር አረጋግጧል።
Via : tikvah

❤13👍2🤷1
በፓኪስታን በባቡር ላይ ባነጣጠረ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ቢያንስ የ24 ሰዎች ህይወት አለፈ
👉 መንገደኞች ለኢድ በዓል እየተጓዙ ነበር
በፓኪስታን ወታደራዊ ሰራተኞችን በሚያጓጉዝ ባቡር ላይ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ የ20 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 70 ሰዎች ቆስለዋል። ፍንዳታው የተከሰተው ባቡሩ እሁድ ጧት በምእራብ ባሎቺስታን ክልል ዋና ከተማ በሆነችው በኬታ በሚገኘው በቻማን ፋታክ ጣቢያ ሲጓዝ ነው።
የባቡር ሀዲድ ባለስልጣናት እንደተናገሩት ሞተሩ ከሀዲዱ ስቶ የተገለበጠ ሲሆን ባቡሩ ለኢድ ወደ ቤታቸው የሚመለሱትን የአገልግሎት ሰራተኞችን እና ቤተሰቦቻቸውን ሲያጓጉዝ ነበር። የክልሉ መንግስት ለጥቃቱ ተጠያቂ የሆነው የባሎቺስታን ነፃ አውጪ ጦር ተገንጣይ ቡድን መሆኑን ገልጾ ድርጊቱ የአጥፍቶ ጠፊ ፍንዳታ ነው ብሏል። ቡድኑ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ወስዷል።
ከስፍራው የተገኙ ምስሎች የተቃጠሉ የባቡሩ ክፍሎች፣ በአቅራቢያው ያሉ መኪኖች እና ህንፃ ላይ የቦምብ ጉዳት መድረሱን ያሳያሉ። "ባቡሩ እየተንቀሳቀሰ ነበር ፍንዳታው ሲደርስ ተሳፋሪዎችም ነበሩ" ሲሉ የአደጋው የዓይን እማኝ ናሲር አህመድ ተናግረዋል። እሑድ ፍንዳታው ሲደርስ ቤተሰቦቼ ተኝተው ነበር የቤቱ መስኮቶች ሲሰቡሩ በድንጋጤ መንቃታቸውን አክለዋል።

❤7👍4💔2😢1
ፓይለቱ በበራራ ላይ እያለ የልብ ህመም አጋጠመው
ባለፈው አርብ ከቴነሪፍ ወደ በርሚንግሃም 220 ተጓዦችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረው የጄት2 (Jet2 LS1266) በረራ፣ ዋናው አብራሪ በድንገት በደረሰባቸው የልብ ህመም ምክንያት በፖርቶ፣ ፖርቱጋል አስቸኳይ ማረፊያ ለማድረግ ተገዷል ሲል ሜትሮ ዘግቧል።
በበረራው ወቅት የረዳት አብራሪው አይሮፕላኑን ለመቆጣጠር ከፍታ በፍጥነት በቀነሰበት ወቅት ተጓዦች ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ወድቀው ነበር።
የበረራ አስተናጋጆች እያለቀሱ በህክምና የሰለጠነ ሰው ይፈልጉ እንደነበር ተገልጿል።
አይሮፕላኑ በፖርቶ አውሮፕላን ማረፊያ በሰላም ያረፈ ሲሆን፣ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ለአብራሪው አስቸኳይ ህክምና አድርገውላቸዋል።
ተሳፋሪዎች ግን ያለምንም ማረፊያ ለአውሮፕላን ሰራተኞቹ ያላቸውን አጋርነት እየገለጹ፣ ለአስራ ሶስት ሰዓታት በአውሮፕላን ማረፊያው ለመቆየት መገደዳቸውን ተናግረዋል።

❤11👍3
መከላከያ “ሰም በእሳት እንደሚቀልጥ ይቀልጣሉ” ሲል ባስጠነቀቀ ማግስት ህወሓት ለኤርትራ ይፋዊ መልዕክት አስተላለፈ፤
ህወሓት ለኤርትራ ሕዝብ 35ኛ የነፃነት በዓልን ምክንያት በማድረግ ይፋዊ የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላለፈ። በመግለጫው፤ የኤርትራ ሕዝብ ለራሱ ዕድል በራሱ የመወሰን መብት ላደረገው ትግል ያለውን ድጋፍ አረጋግጦ፣ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን ወንድማማችነትና ሰላማዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚፈልግ አስታውቋል።
ይህ የህወሓት መልዕክት የተላለፈው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት “ጽምዶ” በሚባለው እንቅስቃሴ በኩል በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ የሚቃጣን ስጋት ለመመከት እርምጃ እንደሚወስድ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ካሳወቀ ማግስት ነው ሜ/ጄነራል ተሾመ ገመቹ ለዲፕሎማቶች በሰጡት መግለጫ ይህን እንቅስቃሴ “ወደ መሬት እናወርዳለን” ብለው ስንዝር እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላት “ሰም በእሳት እንደሚቀልጥ ይቀልጣሉ” ሲሉ ከትናንት በስቲያ ነበር ያስጠነቀቁት።

❤19🤪4👍2🤩2🤷2😁1🙊1
የታሸጉ ምርቶች ተጠቃሚነት በመጨመሩ ታዳጊዎችን ለደምግፊት እየተጋለጡ ይገኛል
እንደ ግፊት ያሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ከዕድሜ ጋር ቁርኝት ያላቸዉ ሲሆን ዕድሜ በጨመረ ቁጥር የመከሰት ዕድላቸዉ ሰፊ ነዉ። ነገር ግን ታዳጊዎች ለዚህ ችግር ተጋላጭ እየሆኑ መምጣታቸዉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል ።
በሚኒስቴሩ የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ህይወት ሰለሞን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ከ50 በመቶ በላይ የማህበረሰብ የሞት ምክንያት እየሆኑ መምጣታቸውን ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል ።
የአኗኗር ስርዓት እየተቀየረ መምጣት በተለይ በፋብሪካ ዉስጥ ተቀነባብረዉ የሚያልፉ ምግቦችን አዘዉትሮ መጠቀም የታዳጊዎችን ለግፊት ተጋላጭነት እየጨመረ ይገኛል ። በፋብሪካ ተቀነባብረዉ የሚያልፋ ምግቦች ለጤና ጠቃሚ ያልሆኑ ይዘት ያላቸዉ በመሆኑ ለበሽታው አጋላጭ ናቸዉ።
ከእነዚህም መካከል ከፍተኛ የጨዉ መጠን ያላቸዉ የታሸጉ ምግቦች በስፋት በህፃናትም ይሁን በአዋቂዎች ዘንድ ተመራጭ እየሆኑ መምጣታቸዉን ያነሱት ዶክተር ህይወት በተመሳሳይ መልኩ የቅባት አይነታቸዉ ለጤና ጠንቅ የሆኑ ምግቦች በስፋት ጥቅም ላይ ሲዉሉ ይስተዋሏል።
በተጨማሪም በመጠጥ ይሁን በደረቅ ምግብ ላይ የስኳር መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦች ተመራጭ እየሆኑ መጥተዋል ። ሌሎች አጋላጭ ምክንያቶች እንዳሉ ሆነዉ ታዳጊዎች ላይ የሚከሰት የደም ግፊትን ለመከላከል የታሸጉ ምርቶች አጠቃቀምን ማስተካከል ይገባል። ልጆቻቸዉን የለስላሳ መጠጦችንና የታሸጉ ምርቶችን አሲዘዉ ትምህርት ቤት የሚልኩ ወላጆች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ ተላልፋል።
1.4 ቢሊዮን የሚሆነዉ የዓለም ህዝብ ከፍተኛ ከሆነ የደም ግፊት ጋር እንደሚኖር የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

❤14🤯3👍2
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለውጭ ንግድ ተዋንያን አዲስ ፈቃድና የዋጋ ማስተካከያ ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ቢሮክራሲን ለማቅለልና የንግድ ከባቢውን ለማሻሻል በሚል በውጭ ምንዛሬ መመሪያው ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ።
በአዲሱ መመሪያ መሠረት፣ የውጭ ምንዛሬ እና የቁጠባ (Retention) አካውንት ያላቸው ተቋማት ያለ ብሔራዊ ባንክ ቅድመ ፈቃድ የሥራ ማረጋገጫ ሰነድ (LC) እና በሰነድ ማረጋገጫ ክፍያ (CAD) በባንኮች በኩል ማጽደቅ ይችላሉ።
በተጨማሪም፣ እነዚህ ተቋማት ያለ ባንኮች ቅድመ ፈቃድ የዕቃ ጭነት ትዕዛዝ ማስተላለፍ የሚችሉ ሲሆን፣ ክፍያው ግን ሰነዶችን በማረጋገጥ ላይ የተመሠረተ ይሆናል።
በሌላ በኩል፣ ብሔራዊ ባንኩ በኤልሲ (LC) ግብይቶች ላይ የሚጣሉ ክፍያዎችን ከዓለም አቀፍ አሠራር ጋር ለማስማማት የዋጋ ማስተካከያ አድርጓል።
በዚህም መሠረት የኤልሲ አገልግሎት ክፍያዎች በዓመታዊ ተመን ተሰልተው፣ እንደ ኤልሲው የአገልግሎት ዘመን (tenor) በቪሶ (pro-rata) የሚታሰቡ ይሆናል።
ይህም የአስመጪና ላኪዎችን የግብይት ወጪ በመቀነስ የውጭ ንግድ ተወዳዳሪነትን ያሳድጋል ተብሏል።

❤10👍4
ዶክተር ደብረፅዮን የኤሌክትሪክ የህዝብ ትራንስፖርት ለማቅረብ ወሰኑ፡፡
በዛሬው እለት ደግሞ ይህ ካቢኔ በኤሌክትሪክ የሚሰራ የህዝብ ትራንስፖርት ለማቅረብ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ደብረጽዮን እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የፌዴራል መንግስቱ በነዳጅ ላይ የጣለው እገዳ በትራንስፖርት ላይ ችግሮችን በመፍጠሩ ነው፡፡ እነዚህን ችግሮች ለማቃለል ለህዝብ ትራንስፖርት የሚውሉ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውቶቡሶችን እንደሚያስገባ የገለፀው ፅህፈት ቤቱ ጨምሮም ለመንግስት ሰራተኞች ደግሞ ማእከላዊ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡

🤣41❤24👍16🤪6🤯3🤷♂2👏1😢1👀1🙈1🫡1
የአሜሪካ እና ኢራን ስምምነት‼️
የአሜሪካ-ኢራን የስምምነት ረቂቅ (draft) እንደሚከተለው ቀርቧል።
📌የተኩስ አቁሙ ለ60 ቀን እንዲራዘም
📌ኢራን ነዳጇን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በነፃነት መሸጥና መላክ ትችላለች።
📌ሆርሙዝ ያለ ክፍያ ይከፈታል, በሰርጡ የተቀበሩ ፈንጂዎች ይወገዳሉ።
📌በኢራን ነዳጅ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ይቃለላል።
📌 አሜሪካ በኢራን ወደቦች ላይ የጣለችው እገዳ ይቃለላል።'
📌በኑክሌር ዙሪያ በ 60-ቀን ጊዜ ውስጥ ድርድር እንዲደረግ' የሚሉ ናቸው።
እስካሁን ሁለቱ ሀገራት በይፋ አልተፈራረሙም።
ምንጫችን አልአረቢያ ነው።

👍10❤6👏4🤪2
ነገ መስቀል አደባባይ በሚደረገው ፕሮግራም ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
በመሆኑም ፕሮግሙ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ፦
ከመገናኛ በባንቢስ ሱፐር ማርኬት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ
ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ጥላሁን አደባባይ ወይም መሾለኪያ ለከባድ ተሽከርካረዎች አጎና ሲኒማ
ከሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለገሃር መብራት
ከንግድ ባንክ ወደ አዲስ አበባ ስቴዲዩም ቴሌ መ/ቤት
ከፒያሳ በአምባሳደር ቴአትር ወደ መስቀል አደባባይ ሀራምቤ ሆቴል
ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግስት
ከሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ለገሃር መብራት
በቦሌ መንገድ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎፒምያ ወይም ደንበል አደባባ ጋር ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
መረጃ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ በተጠቀሱ አካባቢ ለአጭርም ሆነ ለእረጅም ጊዜ ተሽከርከካሪ አቆሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ዋና መምሪያው ገልጾ መሰል ፕሮግሞች በሚዘጋጁበት ወቅት ሆነ በሌሎች የፀጥታ ስራዎች ህዝቡ እያደረገ ላለው ቀና ትብብር የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምስጋናውን እያቀረበ አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እዳያጋጥማቸው አመራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

❤6😁5👍2🫡2