አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በነዳጅ የተበሳጨው ቻይናዊ‼️👆
ምስራቅ ጉራጌ ዞን ያሉ ለልማት የገቡ ቻይናወች በነዳጅ ምሬት ምክንያት ብዙ ኢንቨስተር እየተማረረ ነው፣ባወጣችሁት ህግ መሰረት ስሩ ይላል።
እኔ የያዝኩት ኩፖን እውነተኛ ነው የውሸት አይደለም ለምንድነው ለሌላ እየቀዳችሁ ለእኔ እምቢ የምትሉኝ ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
39😢26🤣12👍10😁4🙊4💔1👀1
⁉️ የምስራቁ ጦርነት የኑሮአችንን ዋጋ እንዴት እያናጋው ነው? 💥

🚨የኃያላን መንግስታት ፍጥጫ እና የድንበር ጦርነቶች ከሩቅ የሚታዩ የዜና አርዕስቶች ብቻ አይደሉም፤ የኢትዮጵያን ገበያ እና የኪሳችንን አቅም በቀጥታ የሚፈትኑ ማዕበሎች እንጂ።

የሀገር ውስጥ ወቅታዊ ፈተናዎችን እና አጠቃላይ የአህጉራችንን እና የዓለምን ዜናዎች አቀናጅቶ የሚያቀርብላችሁን ስፑትኒክን አሁኑኑ ይከተሉ 👇
🔗 https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy
📣 @sputnik_ethiopia
10👍3🤯1
"ከአሁን በኋላ መንገድ ላይ ጉድጓድ
ካየሁ ኮንትራክተሩ ያልቅለታል!"

የኡጋንዳው ታዋቂ ጄኔራል ሙሆዚ ካይነሩጋባ በሙስና በተዘፈቁ የመንገድ ተቋራጮች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስዱ ዝተዋል። "የመንገድ ግንባታ ክፍያ ከፍለን ካበቃን በኋላ በመንገዱ ላይ አንድም ጉድጓድ ካየሁ፣ ያ ኮንትራክተር በህይወቱ ይከፍላል" ሲሉ ባለሙሉ ስልጣኑ ጄኔራል በይፋ አስታውቀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍4314🤣11👏5
የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ኢቶሪካ የተሰኘ የሙዚቃ አልበም መውጣቱን ተከትሎ የቅርብ ጓደኛው አቶ ዩሱፍ ያሲንን ጨምሮ የታሰሩት ስምንት ሰዎች ፍርድ ቤት ቀርበው በዋስትና እንዲለቀቁ እንደተወሰነላቸው ተሰማ።

ከአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን ጋር ቅርብ የሥራ ግንኙነት ያላቸው ምንጭ ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ታሳሪዎቹ እንዲለቀቁ የወሰነዉ ትናንት ነዉ። እነዚህ ታሳሪዎች በየግል አንድ፤ ሁለት እንዲሁም ሦስት ክሶች እንደቀረቡባቸው ነው የመረጃ ምንጩ የተናገሩት።

አዲስ የሙዚቃ ሥራዎቹ በዩትዩብ መድረክ ማስታወቂያ እንዲታጀቡ አስፈላጊ ሂደቶችን ለማመቻቸት ጀምራ ከነበረው ወይዘሮ ማኅሌት ሰለሞን(በትክክለኛ ስሟ ሃና ሰለሞን) እና አቶ ዩሱፍ ያሲን እያንዳንዳቸው የመቶ ሺህ ብር ዋስትና እንዲከፍሉ ታዝዘው በትናንትናው ዕለት ከፍለው ማጠናቀቃቸውንም አስረድተዋል።

በተለምዶ ሲኤምሲ በሚባለው አካባቢ የሚገኘው የአርቲስት ቴዎድሮስ ስቱዲዮ ሁለት ጠባቂዎች ደግሞ እያንዳንዳቸው 50 ሺህ ዋስትና እንዲያስይዙ ትዕዛዝ ተሰጥቷል ብለዋል።

ጠባቂዎቹ ዋስትና ለመክፈል በሂደት ላይ መሆኑንም ገልጸዋል። የዋስትና ከፍለው ያጠናቀቁት ሁለቱ ታሳሪዎች እስካሁን ከእስር እንዳልወጡ ሆኖም ግን እስከ ሰኞ ይወጣሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

[ዶይቸ ቬለ]

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
26👍5😢3😁1
በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ዮናታን ከድር፣ ደረሰ ኃይሉና አብደላ በድር የተባሉት ተጠርጣሪዎች የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት ሚያዝያ 16 ቀን 2018 ዓ/ም በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታው አዲስ አበባ ፉሪ ኮንዶሚኒየም አካባቢ ነው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ሟች ኪሩቤል ከበደ የተባለውን ስራ አለ በሚል በስልክ በመጥራት አንገቱን አንቀው ህይወቱ እንዲያልፍ አድርገዋል፡፡

አስከሬኑንም በፕላስተርና በላስቲክ በጠቅለል በልብስ መያዣ ሻንጣ ውስጥ በመክተት የሟችን የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አ/አ 50945 D4D ፒካፕ ተሽከርካሪ በመያዝ ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 3፡00 ሠዓት አካባቢ ለዕይታ ተጋላጭ በማይሆኑበት ቆጣሪ ኮንዶሚኒየም አካባቢ አስከሬኑን ጥለው ከአካባቢው ተሰውረዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከሟች ላይ የወሰዱትን ሳምሰንግ አልትራ 21 ተንቀሳቃሽ ስልክና ተሽከርካሪውን ይዘው ወደ ሳሪስ በመጓዝ ብሔረ ፅጌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተሽከርካሪው ሞተር በመጥፋቱና በማስቸገሩ በአካባቢው በሚገኝ የመኪና ማሳደሪያ ቦታ በማቆም የሟችን ስልክ በመሸጥ ራሳቸውን ደብቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ የምርመራና የክትትል ቡድኑ ከሟች ጋር ተያያዥነት ሊኖራቸው ይችላል ባላቸው መረጃዎች ላይ ሰፊ ጥናትና ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪዎቹን የመለየት እንዲሁም ከአድካሚ ክትትል በኋላ በቁጥጥር ስር የማዋል ተግሩንም በድንቅ ብቃት ፈጽሟል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20💔12👍6
መረጃ‼️

በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር 2027 የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔን የምታስተናግደው ኢትዮጵያ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በከፍተኛ ድምጽ ያጸደቀውን በአየር ንብረት ዙሪያ የአገራትን ግዴታ በሚደነግገው ውሳኔ ላይ ድምጸ ተዓቅቦ አደረገች።

ውሳኔውን 141 አገራት የደገፉትና ስምንት አገራት የተቃወሙት ሲሆን፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ደቡብ አፍሪካና ኩዌይትን ጨምሮ 28 አገራት ድምጸ ተዓቅቦ አስመዝግበዋል።

ጠቅላላ ጉባኤው ድምጽ የሠጠው፣ ዓለማቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት አገራት ካባቢን እና አየር ንብረትን ከበካይ ጋዝ ልቀት የመጠበቅ ግዴታ እንዳለባቸውና ይህን ካላደረጉ ለሚያደርሱት ጉዳት እንደ ሁኔታው ካሳ እንዲከፍሉ ሊገደዱ እንደሚችሉ በሠጠው የሕግ አስተያየት ላይ ነው።

የፍርድ ቤቱ ውሳኔ፣ የአገራት የከባቢና የአየር ንብረት ፖሊሲዎች፣ የሕዝባቸውን በሕይወት የመኖር መብት፣ የጤና እና ደረጃውን የጠበቀ ኑሮ የመኖር መብት ማስጠበቅ መቻሉን ማረጋገጥ አለባቸው ይላል።

አሜሪካ እና ሩሲያ የጠቅላላ ጉባኤውን ውሳኔ ከተቃወሙት አገራት መካከል ናቸው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍2
ልደት እና ሞት በወቅቱ በማያስመዘግቡ ነዋሪዎች ላይ 5 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት ሊጣል ነው

የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከሚቀጥለው በጀት ዓመት (ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም.) ጀምሮ እንደ ልደት እና ሞት ያሉ የወሳኝ ኩነት ምዝገባዎችን በወቅቱ በማያስመዘግቡ ነዋሪዎች ላይ የ5 ሺሕ ብር ቅጣት ሊጥል እንደሚችል አስታውቋል።

​የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ሹመይ የማኅበረሰቡን የግንዛቤ ማነስ ከግምት ውስጥ በማስገባት እስካሁን አስገዳጅ የቅጣት ውሳኔዎች ሳይተላለፉ መቆየታቸውን ገልጸው፣ አሁን ግን ደንቡን ተግባራዊ ለማድረግ መታቀዱን  ተናግረዋል።

​እንደ አቶ ጥጋቡ ማብራሪያ፤ ማንኛውም ነዋሪ፦

👉ልደትን ፦ በ90 ቀናት ውስጥ

👉ጋብቻ፣ ፍቺ፣ ሞት እና ጉድፈቻ ኩነቶችን ፦ በ30 ቀናት ውስጥ ማስመዝገብ ግዴታ አለበት።

​ነዋሪዎች የተቀመጠውን የጊዜ ቀነ-ገደብ በአግባቡ በመጠቀም ራሳቸውን ካልተፈለገ የገንዘብ ቅጣት እንዲጠብቁም ኤጀንሲው አሳስቧል።

ምንጭ: አሐዱ ራዲዮ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11🙊7👍4😁3🤪3🥰1👏1
"የኢቦላ ቫይረስ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው" - WHO

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የኢቦላ ቫይረስ አደጋ "አደገኛ ነው" አለ። ድርጅቱ ወረርሽኙ በዲሞክራቲክ ኮንጎ በፍጥነት እየተስፋፋ እንደሚገኝ ገልጿል።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም "በሀገር አቀፍ፣ ቀጠናዊና ዓለማቀፍ ደረጃ ሊኖረው የሚችለውን ተፅዕኖ እየገመገምን ነው" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ፣ "ኮንጎ ውስጥ እስካሁን  177 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፣ 750 በሻይረሱ ተይዘዋል" ብለዋል።

አክለው፣ "በኡጋንዳ የተመዘገበ ሞትም ሆነ ተጠርጣሪ የለም" ሲሉ ተናግረዋል።

እንዲሁም፣ በዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ ጤና ስጋት ምላሽ ዳይሬክተር አብዱረህማን መሐመድ፣ "የኢቦላ ቫይረስ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው" ብለዋል።

"ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያገለግል እውቅና የተሰጠው ክትባት የለም" ሲሉም ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሜሪካዊውን መሪ የሚመስለውና «ዶናልድ ትራምፕ» የተባለው ጎሽ ሊታረድ ነው

​በባንግላዴሽ የሚገኝና የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንትን ዶናልድ ትራምፕን በሚል ስያሜ የተሰጠው አንድ ጎሽ፣ ከሰዎች ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ ለጭንቀት መዳረጉ ተሰማ።

የ38 ዓመቱ ገበሬ ዚያ ኡዲን ምሪዳ እንደሚለው፣ የጎሹ ልዩ ነጭ ቀለምና የረዥም ጸጉሩ አቀማመጥ ከአሜሪካዊው መሪ ጋር ስለሚመሳሰል የቅርብ ዘመዱ ይህንን ስም ሰጥቶታል።

​ይህ 700 ኪሎ ግራም የሚመዝነው እንስሳ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ታዋቂነትን ካገኘ በኋላ፣ በርካታ ጎብኝዎችና ህጻናት እሱን ለማየት በዕለታዊ መልኩ ይተማማሉ።

በዚህም ምክንያት እንስሳው በከፍተኛ ውጥረት  ውስጥ በመውደቁ ክብደት እየቀነሰ መጥቷል።

ባለቤቱ ምንም እንኳን ለእንስሳው ጥልቅ ፍቅር ቢኖረውም፣ እየደረሰበት ካለው ጭንቀት ለመገላገልና የባህሉን ሥርዓት ለመፈጸም በቅርቡ በሚከበረው የዒድ አል-አድሃ በዓል ላይ ለሰዋዕትነት (እርድ) ለማቅረብ መወሰኑን አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁4022🤣11👍3👀1
ኢትዮጵያ የግብፅን "የመክበብ ስልት" እና "እግር የመጥለፍ" ሙከራ ነቀፈች

ኢትዮጵያ፣ ግብፅ በቀጠናው የምታደርገው እንቅስቃሴ የሀገሪቱን "እግር የመጥለፍ ሙከራ" ነው ስትል በጽኑ ወቀሰች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ካይሮ እና አስመራ በቀይ ባህር ላይ ያተኮረ ስምምነት ከተፈራረሙ ከቀናት በኋላ እንዲሁም ደቡብ ሱዳን በግዛቷ የሚገኝ የግብፅ ጦር እንዲወጣ ማዘዟ በተሰማበት ሳምንት በሰጡት በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ነው ይሄን ያሉት።
አምባሳደሩ እንደገለጹት፣ ግብፅ እያሳየችው ያለው "የመክበብ ስነ-ልቦና" (siege mentality) እና ግልጽ ትንኮሳ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስከበር በቆረጠች ቁጥር የሚበረታ "የታወቀ የታሪክ ቅሪት" ነው። ኢትዮጵያ ማንኛውንም ዓይነት ተጽዕኖ በዲፕሎማሲያዊ ወኔ እንደምትመክተው የገለጹት ቃል አቀባዩ፣ ግብፅ በጎረቤት ሀገራት ጦሯን ለማስፈር የምታደርገው ጥረትም የዚሁ ስልት አካል መሆኑን ጠቁመዋል።

በተያያዘም፣ ግብፅ "የባህር ጠረፍ የሌላቸው አገራት በቀይ ባህር ጉዳይ መሳተፍ አይገባቸውም" በማለት የያዘችውን አግላይ አቋም አዲስ አበባ እንደማትቀበለው ታውቋል። ምንም እንኳ ግብፅ ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመክበብ ብትሞክርም፣ የባህር በር ጥያቄ ግን የሀገር ህልውና ጉዳይ በመሆኑ በማንኛውም ዓይነት ጫና የማይገታ እና የማይተው አጀንዳ መሆኑን ሚኒስቴሩ በድጋሚ አረጋግጧል።

ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር ለመድረስ የምታደርገው ጥረት "ሰላማዊ እና ዘላቂ" መሆኑን የጠቀሱት አምባሳደር ነቢያት፣ አሁን እየታየ ያለው ቀጠናዊ ፍጥጫ ሀገሪቱ የወደብ አማራጮቿን ለማስፋፋት የያዘችው አቋም ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጫ ነው ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍6😢1
አሜሪካ ለአዲስ ጥቃት እየተዘጋጀች ነው-ሲቢኤስ‼️
ትራምፕ ለጎልፍ ጨዋታ ያሰቡትን ጉዞ ሰርዘው በፍጥነት ወደ ኋይት ሀውስ ተመለሱ።
📌ትራምፕ በኢራን የድርድር አቋም ተበሳጭተዋል።
📌በዚህ ሳምንት መጨረሻ ሊጫወቱ ያሰቡትን የጎልፍ ዕቅዶች ተሰርዘዋል።
📌ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት የመታሰቢያ በዓል ዕቅዶችን ሰርዘዋል።
📌አሜሪካ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃቶችን ለመፈፀም እያዘጋጀች ነው'
📌የኢራን ጦር ለማንኛውም ጥቃት ዝግጁ ነው - ታስኒም ኒውስ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍7🤯2😡2🤔1
አዲስአበባን ክልል እናደርጋለን ሲል ኢዜማ አስታወቀ

ኢዜማ ቀጣዩን ሃገራዊ ምርጫ  የሚያሸንፍ ከሆነ አዲስአበባን ክልል ሊያደርግ እንደሚችል በተወካዩ በኩል አስታወቀ ::

የኢዜማዉ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ከፋና ሚዲያ ጋር ቆይታ ባደረጉበት ወቅት ኢዜማ  ቀጣይ መንግስት ቢሆን የሃገሪቱን የክልል አወቃቀር በምን መልኩ ያዋቅራል የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል ፡፡

ለዚህም ምላሺ ሲሰጡ አዲስአበባን በማንሳት ከተማዋን ከአቅራቢያዋ ከሚገኙ ከተሞች ጋር በማጣመር ክልል እናደርጋለን ብለዋል ፡፡

አዲስአበባ ክልል የምትሆን ከሆነ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ማን ይሆናል ተብሎ ከጋዜጠኞች ጥያቄ የተነሳላቸዉ የኢዜማዉ ተወካይ በፓርቲዉ የክልል አወቃቀር ኦሮሚያ የሚባል ክልል እንዳማይኖር ጠቅሰዋል ፡፡

Via : Ankuar merja

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁65👍5114🙊14🤪6🥱5💊4🤣3👏21🏆1
በዳውሮ ዞን፦ የአርሰናል ደጋፊዎች የ120 ሺህ ብር ሰንጋ ሲያዘጋጁ፣ የማንችስተር ደጋፊዎች አቤቱታ አቀረቡ!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ በዳውሮ ዞን ገሳ ጫሬ ከተማ የሚገኙ የአርሰናል ደጋፊዎች ቡድናቸው ከ22 ዓመታት በኋላ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ስላነሳ የ120 ሺህ ብር ዋጋ ያለው የዳውሮ ቅልብ ሰንጋ በሬ መግዛታቸው ተሰማ።

ደጋፊዎቹ የእሁዱን ጨዋታ እና የዋንጫ ዝግጅት በታላቅ ድግስ ለማክበር ሰንጋቸውን አዘጋጅተው ቀኑን በጉጉት እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

ይሁን እንጂ ይህ ዝግጅት በከተማዋ በሚገኙ የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ዘንድ ስጋትንና ቅሬታን ፈጥሯል።

ከስፍራው ለአዘጋጅ ክፍላችን አቤቱታቸውን ያቀረቡ የማንችስተር ደጋፊ እንደገለጹት፦” በአንድነት፣ ተከባብረን እና አብረን በልተን ባደግንባት ማህበረሰብ ውስጥ፣ የአርሰናል ደጋፊዎች ይህንን ዝግጅት ለብቻቸው ማድረጋቸው ተገቢ አይደለም፤ ስግብግብነት ነው»* ሲሉ ቅሬታቸውን ሰንዝረዋል።

አክለውም “ በገዛ ሰፈራችን ሰላም አጥተናል፣ እባካችሁ በስፖርታዊ ጨዋነት ገስጹልን» ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

የእሁዱ የፕሪሚየር ሊግ ማጠቃለያ ጨዋታ በአውሮፓ መድረክ ብቻ ሳይሆን በገሳ ጫሬ ከተማም በጉጉት የሚጠበቅ ትልቅ የስፖርታዊ ፉክክር ድባብ መፍጠሩ የታወቀ ሲሆን፣ ደጋፊዎች ጨዋታውን በሰላማዊ እና በስፖርታዊ ጨዋነት መንፈስ እንዲከታተሉ መልዕክታችን ነው።

እናንተስ ምን ትላላችሁ? አርሰናሎች ሰንጋውን ይበሉታል ወይስ ማንችስተሮች ይጋበዛሉ?#gursha

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁4016🤪13👍4👏3😎2😢1🎉1👌1🥱1🍾1
የታጣቂዎች ጥቃት‼️
"በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ ታጣቂዎች ሰሞኑን በፈጸሙት አዲስ ጥቃት አባት እና ልጅን ጨምሮ ስድስት ሰዎች ሲገደሉ የስድስት ቀበሌ ቤቶች መቃጠላቸውን፣ በርካታ ከብቶች መዘረፋቸው ታውቋል።

አንድ ነዋሪ በሰጡን ቃል፣ "በወረዳው ሸንኮራ ቀበሌ በሸኔ ታጣቂዎች ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ/ም አራት ሰዎች ሲገደሉ፣ አንዲት እናት ቆስላ በህክም ትገኛለች። 100 ኩንታል እህል ወድሟል። 150 የቀንድ ከብት ተዘርፏል። 150 የንብ ቀፎ ተቃጥሏል" ብለዋል።

"ሰዎች ታፍነው ተወስደዋል። በቁጥር አልታወቁም። አንድ፣ አንድ ሚሊዮን ብር ከፍለው የተለቀቁም አሉ። በዚህ ሳምንት ብቻ ከስድስት ቀበሌ በላይ ንብረት ወድሟል፣ ከብት ተዘርፏል" ሲሉም ተናግረዋል።
#tikvah

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢279😡6👍4💔3😱1🕊1
ሰበር
አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ለመድረስ ተቃርበዋል ሲል አክሲዎስ ዘግቧል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ስምምነት ለፈፀም የቃላት ልዩነቶች ብቻ እንደቀሩ ገልጿል።
ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን ሙሉ ለሙሉ ክፍት ታደርጋለች ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍18🕊106🙏5🤷‍♂3👏1😁1
መረጃ‼️

መከላከያ ሠራዊት፣ ሕወሃት እና የኤርትራ መንግሥት በጥምረት በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ስጋት የሚፈጥር እንቅስቃሴ ካደረጉ ስለሚወስደው ርምጃ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ማሳወቁን የሠራዊቱ የውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዳይሬክተር ሜ/ጀነራል ተሾመ ገመቹ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

መከላከያ ሠራዊት ይህን ያደረገው፣ "ጽምዶ" የተባለውን የሕወሃትና ኤርትራ "የጸረ-ሉዓላዊነት" ጥምረት ወደ ተግባር ለመቀየር የሚፈልጉ አካላት ካሉ ርምጃው ምን እንደሚኾን የኢትዮጵያ ወዳጆች ማወቅ ስላለባቸው መኾኑን ጀነራሉ ገልጸዋል።

ያም ኾኖ መከላከያ ሠራዊቱ የ"ጽምዶ" እንቅስቃሴን አሁን ባለበት ደረጃ ለኢትዮጵያ "ሰላም" እና "ደኅንነት" አስጊ አድርጎ እንደማይወስደው ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
31🤪27👍5😎3👏1😢1🕊1🫡1
በአርሴናል ደጋፊዎች ምክንያት ሞተር ተከለከለ‼️
#በአርሰናል_ጨዋታ_ምክንያት_በወላይታ_ሶዶ_ባለሁለት_እግር_ሞተር_እንቅስቃሴ_ታገደ

‎ዛሬ ግንቦት 16/2018 በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የዋንጫ ርክብክብ ስነ-ስርዓት መኖሩን ተከትሎ አንድአንድ ዲስፕልን የሌላቸው ደጋፍዎች በአንድንድ ግለሰቦች ላይ ዛቻና ማስፈራርያ እያደረሱ እንዳለ ለፖሊስ መረጃዎች እየደረሰ በመሆኑ ደጋፊ ደስታውን ስገልጽ በጨዋነትና በልክ መሆን እንዳለበትና የሶዶ ከተማ ፖሊስ ያሳስባል።

‎በዕለቱም ከምሽቱ 12:30 ሰዓት እስከ ጠዋት ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክል በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ ፈጽመው የተከለከለ መሆኑንም እየገለፀ በተጨማር የትኛውም ተሽከርካር በከተማ ውስጥ ማጮህና የመኪና ሰልፍ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪2718👍11👏5😢2🥰1🏆1🙈1🫡1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ አቡሰራ እያስገነባ የሚገኘውን ታላቅ የአየር መንገድ ፕሮጀክት ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል 40 ሚሊዮን ዶላር በማውጣት አዲስ መንደርደሪያ ለመገንባት መገደዱ ታውቋል።

በግንባታ ላይ የሚገኘው ታላቁ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እና የኢትዮጵያ አየር ኃይል በአንድ ከተማ ላይ መገኘታቸው፣ ፕሮጀክቱ ከተጠነሰሰበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ጥያቄዎችን ሲያስነሳ መቆየቱ ይታወቃል። በተለይም ግዙፍ አውሮፕላን ማረፊያ እና ተዋጊ ጄቶች የሚበሩበት ወታደራዊ ይዞታ በአንድ የአየር ክልል ውስጥ እንዴት ሊዘወሩ ይችላሉ? የሚለው ጥያቄ የብዙዎች ስጋት ነበር።

ይህንን ሊከሰት የሚችለውን ቴክኒካዊ ተግዳሮት አስቀድሞ በመለየት፣ መንግስት እና አማካሪ ድርጅቶቹ የአየር ኃይሉን ስራ ሳይገታ አዲሱን አውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት የሚያስችል የ40 ሚሊዮን ዶላር መፍትሄ በቅድመ ጥናቱ አካትተዋል። ይህ 40 ሚሊዮን ዶላር በዋነኝነት ለአዲሱ ወታደራዊ መንደርደሪያ ግንባታ፣ ለበረራ መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂዎች ዝርጋታ እና የአየር ኃይሉን ይዞታ ከአዲሱ አየር መንገድ ጋር ለማጣጣም ለሚከናወኑ የመሠረተ ልማት ማሻሻያዎች የሚውል ነው።

ይህ ሲሆን ሁለቱም ተቋማት አውሮፕላኖቻቸውን በተመሳሳይ አቅጣጫ ማስነሳትና ማሳረፍ ስለሚችሉ፣ በአውሮፕላኖች መካከል ሊፈጠር የሚችለውን የመጋጨት ስጋት ይቀንሳል። በተጨማሪም የአየር ትራፊክ ቁጥጥሩን ቀላል፣ ግልጽ እና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ያደርገዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14🤔9👍4
በዋይት ሀውስ አቅራቢያ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ተጠርጣሪው በጥይት ተመትቶ ተገደለ

🟠 ቅዳሜ አመሻሽ በዋሽንግተን በሚገኘው የዋይት ሀውስ የደህንነት ፍተሻ ኬላ አቅራቢያ አንድ የታጠቀ ግለሰብ ተኩስ ከፍቷል፡፡

🟠 የሕግ አስከባሪ አካላት በወሰዱት የአጸፋ እርምጃ ተኳሹ የቆሰለ ሲሆን፣ ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ በደረሰበት ጉዳት ሕይወቱ አልፏል፡፡

🟠 በተኩስ ልውውጡ ወቅት አንድ መንገደኛ ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡

🟠 ዶናልድ ትራምፕ በማኅበራዊ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ተኳሹ ቀደም ሲል የጥቃት ታሪክ የነበረውና በአገራችን ውስጥ እጅግ ውድ በሆነው ሕንፃ (በዋይት ሀውስ) ላይ ከፍተኛ አባዜ የተጠናወተው ሰው ይመስላል ሲሉ ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13🥱5👍2😡2