በኢራን እና አሜሪካ መካከል አዲስ የሰላም ንግግር ማድረጋቸው ተሰማ
የኢራኑ ታስኒም የዜና ወኪል እንደዘገበው፤ ኢራን ከሶስት ቀናት በፊት በፓኪስታን አምባሳደር በኩል 14 ነጥቦችን የያዘ አዲስ የተሻሻለ የሰላም ረቂቅ ሰነድ ለአሜሪካ ካስገባች በኋላ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በበኩሏ የራሷን ማሻሻያ እና የውይይት ነጥቦች ዛሬ በፓኪስታን በኩል ለቴህራን ልካለች።
በአሁኑ ወቅት የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣናት የአሜሪካን ሰነድ በጥልቅ እየገመገሙት ሲሆን፣ እስካሁን ይፋዊ ምላሽ አልሰጡ፡ የፓኪስታን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሞህሲን ናቅቪ በቴህራን የሚገኙ ሲሆን፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያሉትን ሰፊ የሃሳብ ልዩነቶች ለማጥበብ እና ስምምነቱ እንዳይከሽፍ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጥረት እያደረጉ ነው።
አሜሪካ በድርድሩ ወቅት የኢራን የዘይት ማዕቀብ እንዲነሳ ልትስማማ እንደምትችል ፍንጭ የሰጠች ቢሆንም፣ ኢራን ግን ሁሉንም ማዕቀቦች ሙሉ በሙሉ በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚያስገድድ ስምምነት እንዲሆን እየወተወተች ነው።
የቴህራን 14 ነጥብ እቅድ በዋናነት የሚያተኩረው ጦርነቱን ሙሉ በሙሉ ለማቆም እና በአሜሪካ በኩል “የእምነት ግንባታ እርምጃዎች እንዲወሰዱ በሚሉ ነጥቦች ላይ ነው።
@Addis_Reporter

❤18👍2😢2
በጣና ሐይቅ ላይ በደረሰ ድንገተኛ የጀልባ መስመጥ አደጋ የብዙዎች ሕይወት አለፈ
ግንቦት 13፤ ባሕር ዳር የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ዓመታዊ የዋዜማ በዓል ለማክበር በጣና ሐይቅ ላይ በጉዞ ላይ የነበሩ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮችን የጫነች ጀልባ ድንገተኛ የመስመጥ አደጋ ደርሶባታል።
በደረሰው አሳዛኝ አደጋ ምክንያት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የብዙ ወገኖቻችን ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል።
Via የባሕር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት

💔32😢20❤7👏4👍2😁2🤔2
የምርጫ ጸሎት እና ዱአ ሊደረግ ነው!
የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ መጪውን ምርጫ አስመልክቶ፣ ሰባት የሃይማኖት ተቋማት የሚሳተፉበት የጸሎት መርሀ ግብር ማዘገጀቱን መሆኑን አስታውቋል፡፡
ግንቦት 16/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ፓርክ በሚካሄው የምርጫ ጸሎት መርሀግብር ላይ ሰባት የሃይማኖት ተቋማት የሃይማኖት አባቶች ባሉበት እንደሚከናወን ተገልጿል። በተመሳሳይ ሰዓት በሁሉም ክልሎች የጸሎት ሥነ ሥርዓት እንደሚከናወንም የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ቀሲስ ታጋይ ገልጸዋል።
የአደባባይ ጸሎቱ በዋናነት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ በማሰብ የሚካሄድ መሆኑም የጉባኤው ጸሐፊ ገልጸዋል። ጉባኤው ያዘጋጀው መርሀግብር ከ1 ሺሕ በላይ ዜጎች የሚሳተፉበት የጸሎት እና የዱአ መርሃግብር መሆኑን ተናግረዋል፡፡(አንድ አፍታ)

🤣82❤20😁15💔3👍2
የፈተና ፕሮግራም ተቀይሯል‼️
የሪሜዲያል ፈተና እና የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) የሚሰጥበት ቀን ተቀይሯል።
በዚህም የ ሪሚዲያል ፈተና ከግንቦት 27- እስከ ሰኔ 3 የሚሰጥ ሲሆን የድህረ ምረቃ መውጫ ፈተና ከሰኔ 4-12 የሚሰጥ ይሆናል።

👍6❤4🤯1
ነዳጅና ጋዝ ለአለም ገበያ
ኢትዮጵያ የነዳጅ እና የጋዝ ምርቶቿን በጅቡቲ በኩል ለአለም ገበያ ለማቅረብ እቅድ አውጥታለች
ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዝ እና ድፍድፍ ነዳጅን በጅቡቲ በኩል ለአለም ገበያ የመላክ እቅዷን ከጅቡቲ ጋር የተጋራች ሲሆን የተጣራ የነዳጅ ምርቶችንም ከጅቡቲ በቧንቧ ታስገባለች።
ሃሳቡን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ ለጅቡቲ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ አቅርበዋል።
የጅቡቲ የዜና ወኪል (ADI) እንደዘገበው ፕሬዚዳንቱ እቅዱን ተቀብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበው ሃሳብ ሁለት ምዕራፎችን ያካተተ ነው።
የመጀመሪያው ምዕራፍ 113 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተጣራ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ ሲሆን ከጅቡቲ ወደብ ተነስቶ መጨረሻው በኢትዮጵያ ጅቡቲ ድንበር ላይ በሚገኘው ደወሌ ላይ ነው።
ሁለተኛው ምዕራፍ 760 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የጋዝ እና ድፍድፍ ነዳጅ መስመር ዝርጋታ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ውስጥ ካለው የኦጋዴን ክልል ጀምሮ እስከ ጅቡቲ ወደብ ድረስ ይዘልቃል። ለሁለቱም የቧንቧ መስመር ዝርጋታ እና የነዳጅ ማጣሪያዎች አጠቃላይ ወጪ ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው።
የፕሮጀክቶቹ ስኬት በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እና በዳንጎቴ ኢንቨስትመንት ግሩፕ መካከል ያለውን ትብብር ወደ ላቀ እና ስትራቴጂካዊ ደረጃ
እንደሚያሳድገው ይጠበቃል።
ከ7 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተገኘውን ድፍድፍ ነዳጅ ወደ ውጭ ለመላክ ቱቦ እየተቀበረ መሆኑን መዘገቡ የሚታወስ ነው።

😁22❤17🤔8👍7🤪6👏2🎉1😎1
የኢራን ሰማይ በረራ አቆመ‼️
አውሮፕላኖች በኢራን ሰማይ ላይ መብረር አቆሙ፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ግጭት መልሶ ይቀሰቀሳል በሚል ስጋት በዛሬው እለት የኢራን ሰማይ ላይ የሚበሩ አውሮፕላኖች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል፡፡
በተጨማሪም በአረብ ባህረ ሰላጤ ሰማይ ላይ ከተፈጠረው የኤሌክትሮኒክስ ግንኙነት መቋረጥ ጋር ተያይዞ የኢራን ሰማይ ጭር ብሏል፡፡ ወታደራዊ ተንታኞችና ታዛቢዎች ለገልፍ ኒውስ እንደገለፁት በተለይ የኤሌክትሮኒክስ ግንኙነት መቋረጡ ከወታደራዊ ዝግጅት ጋር ሊያያዝ ይችላል፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች የተፈጠሩት ፕሬዝደንት ትራምፕ በቴሄራን የኒውክሌይር ፕሮግራም ጉዳይ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ድርድሩ የማይሳካ ከሆነም ወደጥቃት እንደሚመለሱ መግለፃቸው ይታወቃል፡፡ የአውሮፕላን በረራዎችን የሚከታተሉ መረጃ ሰጪዎች እንደሚገልፁት ዛሬ በኢራን ሰማይ ላይ አውሮፕላኖች የጠፉበት ሁኔታ ፌብሩዋሪ 28 በኢራን ላይ ጥቃት በተጀመረበት ወቅት ከነበረው ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡

❤7👍4🙏2🥰1😁1
መረጃ‼️
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ ኮንትሮባንድ የጫኑ ተሽከርካሪዎችን ከመውረስ ይልቅ ቅጣቱን ከፍ ማድረግ ይሻላል አለ።
ቋሚ ኮሚቴው ይህን ያለው፣ በጉሙሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ዛሬ በመወያየበት ወቅት ነው።
የጉምሩክ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ፣ ኮንትሮባንድ ጭነው የሚገኙ ተሽከርካሪዎችን እንዲወርስ ሥልጣን ይሠጣል።
የኮንትሮባንድ እቃዎች አወራረስ በመመሪያ ሳይሆን፣ በተቋሙ ደንብ ውስጥ መደንገግ እንዳለበትና ኮሚሽኑ የሚጥላቸው አሥተዳደራዊ ቅጣቶችም በአዋጁ ሊካተቱ እንደሚገባ ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል።
በኮንትሮባንድ ንግድ የተያዙ ንብረቶች ጠቃሚ እቃዎች ስለመሆናቸው በቴክኒክ ባለሙያዎች ተረጋግጠው በገንዘብ ሚንስቴር ውሳኔ አግባብ ላለው የመንግሥት ተቋም እንዲተላለፉ መደረጉ፣ ለተለያዩ እቃዎች ግዢ አገሪቱ የምታወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንደሚያስቀር ኮሚቴው ገልጧል።

❤15👍8👏4😁1🤪1
ሌተና ጄኔራል አልብሩሀን ከዩናይትድ አረብ ኤመሬትስ ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ መሆናቸውን አስታወቁ፡፡
የሱዳን ወታደራዊ መንግስት መሪ የሆኑት ሌተና ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልብሩሀን ከዩናይትድ አረብ ኤመሬትስ ጋር ለመነጋገር ፈቃደኝነታቸውን ገልፀው ቅድመ ሁኔታዎችን ግን አስቀምጠዋል፡፡
ጄኔራሉ ከሚድል ኢስት አይ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ሲናገሩ ‹‹እኛ ከዩናይትድ አረብ ኤመሬትስ ጋር የሰላም ንግግር ለመጀመር ፈቃደኛ ነን፡፡
ይሁንና ይህንን ንግግር ለመጀመር ሱዳን የሱዳን ፍላጎቶች መሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
ዩናይትድ አረብ ኤመሬትስ የሱዳንን አንድነት ማክበር ይጠበቅባታል፣ለሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር የምታደርገውን ወታደራዊ ድጋፍ ታቁም ብለዋል፡፡
የጋዜጣው ምንጮች እንደገለፁት ባለፈው ሳምንት አልብሩሀን ወደባህሬን የተጓዙት ባህሬን በሱዳንና በኤመሬትስ መካከል ንግግር እንዲጀመር እያደረገችው ያለው ጥረት አካል ነበር፡፡
በኤመሬትስና በሱዳን መካከል ቀጥተኛ ዲፕሎማሲያዊ መስመር እንዲከፈት የተደረገው ሙከራ እስካሁን ሊሳካ አለመቻሉንም አስታውቋል፡፡
የሱዳን መንግስት ኤመሬትስ ለፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ የምትሰጠውን ጦር መሳሪያ ድጋፍ እንድታቋርጥ አቋም መያዙን የገለፀው ዘገባው ቀጥተኛ ንግግር ለማድረግ ይህንን እንደ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡንም አስረድቷል፡፡

❤15👍3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንድ ሮቦት በፖላንድ የዱር አሳማዎችን ከከተማ በማባረር መነጋገሪያ ሆኗል
ኤድዋርድ ዋርቾኪ የተባለ አንድ ሰው መሰል ሮቦት፣ በፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሳው በሚገኙ የመኖሪያ መንደሮች ውስጥ የዱር አሳማዎችን ሲያባርር የተቀረጸና በሮቦቱ ማሕበራዊ ትስስር ገጽ የተለቀቀ ቪዲዮ በበይነመረብ ላይ አነጋጋሪ ሆኗል።
በዋርሳው ከተማ የዱር አሳማዎች በብዛት መታየታቸው አሳሳቢ ችግር እየሆነ በመምጣቱ እንስሳቱን ያለምንም ጉዳት ወደ ጫካው መልሶ ለማባረር ይህ ያልተለመደ የሮቦት ዘዴ ስራ ላይ ውሏል።
በዋርሳው ከተማ የዱር አሳማዎች በተደጋጋሚ ምግብ ፍለጋ ወደ ከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች እና ተሽከርካሪ ማቆሚያዎች የሚገቡ ሲሆን በሰፊው በተሰራጨው ቪዲዮ ላይ ኤድዋርድ አሳማዎቹን በተጫዋችነት ስሜት ግን ደግሞ በቁርጠኝነት ሲያሳድዳቸው ይታያል።
ሮቦቱ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን የሚጠቀም ሲሆን፥ እንስሳቱ ፈርተው ወደጫካ እንዲሸሹ ለማድረግ እግሩን መሬት ላይ እየመታ “ከዚህ ሂዱ!” እያለ በፖላንድኛ ሲጮህ ተሰምቷል።
የቻይናው የቲክኖሎጂ ድርጅት ዩኒትሪ ምርት የሆነ G1 ሞዴል ሮቦት የሆነው ኤድዋርድ፥ በአሁኑ ጊዜ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ተከታይ ያለው ተጸዕኖ ፈጣሪ መሆን የቻለ ሲሆን፣ አብዛኛውን ጊዜ የስፖርት ቦርሳ አግቶ እና የአልማዝ ፈርጦች ያሉት ሮሌክስ የእጅ ሰዓት አድርጎ ከተማ ውስጥ ሲንቀሳቀስና ከሰዎች ጋር ሲያወራ ብዙ ጊዜ ይታያል።
ኤድዋርድ የዱር እንስሳትን የመቆጣጠር ስራውን ከማከናወኑ ባሻገር፣ በፖላንድ የጠዋት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች እና የዳንስ ውድድር ላይ በመቅረብ ትልቅ ዝናን አትርፏል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው
በ- ዳንኤል መኮንን

❤14👍6🤪3
1.2 ቢሊዮን ህዝብ በአእምሮ ህመም‼️
በዓለም ላይ 1.2 ቢሊዮን ሰዎች በአእምሮ መቃወስ ሕመም (mental disorder) እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ጥናት አመላከተ።
ይህ እ.ኤ.አ ከ 1990 ወዲህ በ 95.5% ጭማሪ አሳይቷል።
Via:- CNN

👍12😢4😱3❤2
ኬንያ የነዳጅ ዋጋ ልትቀንስ ነው‼️
ኬንያ የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረጓን ተከትሎ በሀገሪቱ የተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች መካሄዳቸውን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ላይ መጠነኛ የዋጋ ቅናሽ ልታደርግ መሆኑን አስታውቃለች።

👍30❤12🫡2
ማንቼስተር ሲቲ ከፔፕ ጋርዲዮላ ጋር እንደሚለያይ ይፋ አደረገ
ማንቼስተር ሲቲ ከአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ጋር በውድድር ዓመቱ መጨረሻ እንደሚለያይ ይፋ አድርጓል፡፡
ስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በኢትሃድ የአስር ዓመታት ቆይታቸው 20 ዋንጫዎችን አሳክተዋል፡፡
አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በማንቼስተር ሲቲ ታሪክ በርካታ ዋንጫዎችን ያሳኩ ቀዳሚው አሰልጣኝ ናቸው፡፡
የ55 ዓመቱ አሰልጣኝ የፊታችን እሑድ ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ኢትሃድ ከአስቶን ቪላ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ክለቡን የሚሰናበቱ ይሆናል።

❤24👍9😢4🤝2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በነዳጅ የተበሳጨው ቻይናዊ‼️👆
ምስራቅ ጉራጌ ዞን ያሉ ለልማት የገቡ ቻይናወች በነዳጅ ምሬት ምክንያት ብዙ ኢንቨስተር እየተማረረ ነው፣ባወጣችሁት ህግ መሰረት ስሩ ይላል።
እኔ የያዝኩት ኩፖን እውነተኛ ነው የውሸት አይደለም ለምንድነው ለሌላ እየቀዳችሁ ለእኔ እምቢ የምትሉኝ ብሏል።

❤39😢26🤣12👍10😁4🙊4💔1👀1
⁉️ የምስራቁ ጦርነት የኑሮአችንን ዋጋ እንዴት እያናጋው ነው? 💥
🚨የኃያላን መንግስታት ፍጥጫ እና የድንበር ጦርነቶች ከሩቅ የሚታዩ የዜና አርዕስቶች ብቻ አይደሉም፤ የኢትዮጵያን ገበያ እና የኪሳችንን አቅም በቀጥታ የሚፈትኑ ማዕበሎች እንጂ።
የሀገር ውስጥ ወቅታዊ ፈተናዎችን እና አጠቃላይ የአህጉራችንን እና የዓለምን ዜናዎች አቀናጅቶ የሚያቀርብላችሁን ስፑትኒክን አሁኑኑ ይከተሉ 👇
🔗 https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy
📣 @sputnik_ethiopia

❤10👍3🤯1
"ከአሁን በኋላ መንገድ ላይ ጉድጓድ
ካየሁ ኮንትራክተሩ ያልቅለታል!"
የኡጋንዳው ታዋቂ ጄኔራል ሙሆዚ ካይነሩጋባ በሙስና በተዘፈቁ የመንገድ ተቋራጮች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስዱ ዝተዋል። "የመንገድ ግንባታ ክፍያ ከፍለን ካበቃን በኋላ በመንገዱ ላይ አንድም ጉድጓድ ካየሁ፣ ያ ኮንትራክተር በህይወቱ ይከፍላል" ሲሉ ባለሙሉ ስልጣኑ ጄኔራል በይፋ አስታውቀዋል።

👍43❤14🤣11👏5
የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ኢቶሪካ የተሰኘ የሙዚቃ አልበም መውጣቱን ተከትሎ የቅርብ ጓደኛው አቶ ዩሱፍ ያሲንን ጨምሮ የታሰሩት ስምንት ሰዎች ፍርድ ቤት ቀርበው በዋስትና እንዲለቀቁ እንደተወሰነላቸው ተሰማ።
ከአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን ጋር ቅርብ የሥራ ግንኙነት ያላቸው ምንጭ ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ታሳሪዎቹ እንዲለቀቁ የወሰነዉ ትናንት ነዉ። እነዚህ ታሳሪዎች በየግል አንድ፤ ሁለት እንዲሁም ሦስት ክሶች እንደቀረቡባቸው ነው የመረጃ ምንጩ የተናገሩት።
አዲስ የሙዚቃ ሥራዎቹ በዩትዩብ መድረክ ማስታወቂያ እንዲታጀቡ አስፈላጊ ሂደቶችን ለማመቻቸት ጀምራ ከነበረው ወይዘሮ ማኅሌት ሰለሞን(በትክክለኛ ስሟ ሃና ሰለሞን) እና አቶ ዩሱፍ ያሲን እያንዳንዳቸው የመቶ ሺህ ብር ዋስትና እንዲከፍሉ ታዝዘው በትናንትናው ዕለት ከፍለው ማጠናቀቃቸውንም አስረድተዋል።
በተለምዶ ሲኤምሲ በሚባለው አካባቢ የሚገኘው የአርቲስት ቴዎድሮስ ስቱዲዮ ሁለት ጠባቂዎች ደግሞ እያንዳንዳቸው 50 ሺህ ዋስትና እንዲያስይዙ ትዕዛዝ ተሰጥቷል ብለዋል።
ጠባቂዎቹ ዋስትና ለመክፈል በሂደት ላይ መሆኑንም ገልጸዋል። የዋስትና ከፍለው ያጠናቀቁት ሁለቱ ታሳሪዎች እስካሁን ከእስር እንዳልወጡ ሆኖም ግን እስከ ሰኞ ይወጣሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።
[ዶይቸ ቬለ]

❤26👍5😢3😁1
በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ዮናታን ከድር፣ ደረሰ ኃይሉና አብደላ በድር የተባሉት ተጠርጣሪዎች የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት ሚያዝያ 16 ቀን 2018 ዓ/ም በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታው አዲስ አበባ ፉሪ ኮንዶሚኒየም አካባቢ ነው፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ሟች ኪሩቤል ከበደ የተባለውን ስራ አለ በሚል በስልክ በመጥራት አንገቱን አንቀው ህይወቱ እንዲያልፍ አድርገዋል፡፡
አስከሬኑንም በፕላስተርና በላስቲክ በጠቅለል በልብስ መያዣ ሻንጣ ውስጥ በመክተት የሟችን የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አ/አ 50945 D4D ፒካፕ ተሽከርካሪ በመያዝ ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 3፡00 ሠዓት አካባቢ ለዕይታ ተጋላጭ በማይሆኑበት ቆጣሪ ኮንዶሚኒየም አካባቢ አስከሬኑን ጥለው ከአካባቢው ተሰውረዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ከሟች ላይ የወሰዱትን ሳምሰንግ አልትራ 21 ተንቀሳቃሽ ስልክና ተሽከርካሪውን ይዘው ወደ ሳሪስ በመጓዝ ብሔረ ፅጌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተሽከርካሪው ሞተር በመጥፋቱና በማስቸገሩ በአካባቢው በሚገኝ የመኪና ማሳደሪያ ቦታ በማቆም የሟችን ስልክ በመሸጥ ራሳቸውን ደብቀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ የምርመራና የክትትል ቡድኑ ከሟች ጋር ተያያዥነት ሊኖራቸው ይችላል ባላቸው መረጃዎች ላይ ሰፊ ጥናትና ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪዎቹን የመለየት እንዲሁም ከአድካሚ ክትትል በኋላ በቁጥጥር ስር የማዋል ተግሩንም በድንቅ ብቃት ፈጽሟል፡፡

❤20💔12👍6
መረጃ‼️
በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር 2027 የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔን የምታስተናግደው ኢትዮጵያ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በከፍተኛ ድምጽ ያጸደቀውን በአየር ንብረት ዙሪያ የአገራትን ግዴታ በሚደነግገው ውሳኔ ላይ ድምጸ ተዓቅቦ አደረገች።
ውሳኔውን 141 አገራት የደገፉትና ስምንት አገራት የተቃወሙት ሲሆን፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ደቡብ አፍሪካና ኩዌይትን ጨምሮ 28 አገራት ድምጸ ተዓቅቦ አስመዝግበዋል።
ጠቅላላ ጉባኤው ድምጽ የሠጠው፣ ዓለማቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት አገራት ካባቢን እና አየር ንብረትን ከበካይ ጋዝ ልቀት የመጠበቅ ግዴታ እንዳለባቸውና ይህን ካላደረጉ ለሚያደርሱት ጉዳት እንደ ሁኔታው ካሳ እንዲከፍሉ ሊገደዱ እንደሚችሉ በሠጠው የሕግ አስተያየት ላይ ነው።
የፍርድ ቤቱ ውሳኔ፣ የአገራት የከባቢና የአየር ንብረት ፖሊሲዎች፣ የሕዝባቸውን በሕይወት የመኖር መብት፣ የጤና እና ደረጃውን የጠበቀ ኑሮ የመኖር መብት ማስጠበቅ መቻሉን ማረጋገጥ አለባቸው ይላል።
አሜሪካ እና ሩሲያ የጠቅላላ ጉባኤውን ውሳኔ ከተቃወሙት አገራት መካከል ናቸው።

❤12👍2
ልደት እና ሞት በወቅቱ በማያስመዘግቡ ነዋሪዎች ላይ 5 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት ሊጣል ነው
የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከሚቀጥለው በጀት ዓመት (ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም.) ጀምሮ እንደ ልደት እና ሞት ያሉ የወሳኝ ኩነት ምዝገባዎችን በወቅቱ በማያስመዘግቡ ነዋሪዎች ላይ የ5 ሺሕ ብር ቅጣት ሊጥል እንደሚችል አስታውቋል።
የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ሹመይ የማኅበረሰቡን የግንዛቤ ማነስ ከግምት ውስጥ በማስገባት እስካሁን አስገዳጅ የቅጣት ውሳኔዎች ሳይተላለፉ መቆየታቸውን ገልጸው፣ አሁን ግን ደንቡን ተግባራዊ ለማድረግ መታቀዱን ተናግረዋል።
እንደ አቶ ጥጋቡ ማብራሪያ፤ ማንኛውም ነዋሪ፦
👉ልደትን ፦ በ90 ቀናት ውስጥ
👉ጋብቻ፣ ፍቺ፣ ሞት እና ጉድፈቻ ኩነቶችን ፦ በ30 ቀናት ውስጥ ማስመዝገብ ግዴታ አለበት።
ነዋሪዎች የተቀመጠውን የጊዜ ቀነ-ገደብ በአግባቡ በመጠቀም ራሳቸውን ካልተፈለገ የገንዘብ ቅጣት እንዲጠብቁም ኤጀንሲው አሳስቧል።
ምንጭ: አሐዱ ራዲዮ

❤11🙊7👍4😁3🤪3🥰1👏1
"የኢቦላ ቫይረስ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው" - WHO
የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የኢቦላ ቫይረስ አደጋ "አደገኛ ነው" አለ። ድርጅቱ ወረርሽኙ በዲሞክራቲክ ኮንጎ በፍጥነት እየተስፋፋ እንደሚገኝ ገልጿል።
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም "በሀገር አቀፍ፣ ቀጠናዊና ዓለማቀፍ ደረጃ ሊኖረው የሚችለውን ተፅዕኖ እየገመገምን ነው" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ፣ "ኮንጎ ውስጥ እስካሁን 177 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፣ 750 በሻይረሱ ተይዘዋል" ብለዋል።
አክለው፣ "በኡጋንዳ የተመዘገበ ሞትም ሆነ ተጠርጣሪ የለም" ሲሉ ተናግረዋል።
እንዲሁም፣ በዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ ጤና ስጋት ምላሽ ዳይሬክተር አብዱረህማን መሐመድ፣ "የኢቦላ ቫይረስ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው" ብለዋል።
"ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያገለግል እውቅና የተሰጠው ክትባት የለም" ሲሉም ገልጸዋል።

❤4👍4