የ26 ኪሎ ግራም እጢ በተሳካ ኦፕሬሽን ተወገደ‼
በመቀሌ ዓይደር ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ14 ዓመታት በማህፀን እጢ ሲሰቃዩ የነበሩ የ56 ዓመት እናት፣ ከሦስት ሰዓታት በላይ በፈጀ አስቸጋሪ ቀዶ ጥገና የ26 ኪሎ ግራም እጢ ተወግዶላቸው እፎይታ አግኝተዋል።
📌እነዚህ እናት ቀደም ሲል በርካታ የሕክምና ሙከራዎችን ቢያደርጉም ሳይሳካላቸው የቀረ ሲሆን፣ አልፎ ተርፎም የተሳሳተ ምርመራ ተደርጎላቸው የቲቢ መድኃኒት እስከመውሰድ ደርሰው ነበር። በአሁኑ ወቅት ከቀዶ ጥገናው በኋላ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።
📌የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ዶ/ር ተወልደብርሃን አብርሃ የተመራውና ዶ/ር ገብረኪሮስ ፀጋዛአብ፣ ዶ/ር ተኽላይ ዘርአይ፣ ዶ/ር ማርየ አለሜ እንዲሁም ማደንዘዣ ባለሙያዎችና ነርሶችን ያካተተው የሕክምና ቡድን ከፍተኛ ምስጋና ተችቶታል።
Via : Wasu Mohammed
@Addis_Reporter

❤32🙏8👍7😱2👏1
ግጭት ተቀስቅሷል‼️
ከትናንት በስተያ ግንቦት 10/2018 ዓ.ም በኦሮሚያ እና በሲዳማ ድንበር በምስራቅ ሲዳማ ዞን በጭሬ ወረዳ ጉበ ሔማ ቀበሌ በገበያ ቦታ ላይ በተነሳ አለመግባባት ምክንያት በሲዳማ እና በኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት መካከል ግጭት ተቀስቅሷል።
በዚህም ምክንያት የሰው ሕይወት የጠፋ ሲሆን፣ በርካታ ወገኖቻች ጉዳት እንደደረሰባቸው የአካባቢው ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
እስካሁን ባለው መረጃ የአንድ ሰው አስከሬን እና 7 የቆሰሉ ሰዎች ወደ ጤና ጣቢያ የገቡ ሲሆን፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሌሎች ሰዎችም መጎዳታቸው ታውቋል።
ግጭቱ አድማሱን አስፍቶ በሰብሎች ላይ ጭፍጨፋ ተፈፅሟል፣ ቤቶች ተቃጥለዋል።
Via : አዩዘሀበሻ

😢20❤4🌚3👍2🕊2
ድምፃዊ ሳሚ ዳን ለፕሪሚየር ሊግ አሸናፊው አርሰናል አዲስ የደስታ መግለጫ ሙዚቃ ሊለቅ ነዉ
ድምፃዊ ሳሚ ዳን ለፕሪሚየር ሊግ ዋንጫው ባለቤት አርሰናል አዲስ የደስታ መግለጫ ሙዚቃ ሊለቅ መሆኑን አስታወቀ።
ድምፃዊ ሳሚ ዳን መድፈኞቹ ከ22 ዓመታት ረጅም የጥበቃ ጊዜ በኋላ የኢንግሊሽ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ማንሳታቸውን ተከትሎ፣ ዛሬ ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ አዲስ ልዩ የደስታ መግለጫ ሙዚቃ ለአድማጮች እንደሚያደርስ ይፋ አድርጓል።
ታዋቂው ድምፃዊ ለአርሰናል ክለብ ያለውን ጥልቅ ፍቅርና አጋርነት በገለጸበት ማስታወቂያው፥ My አርሴ እማ አንድ ሙዚቃማ ይገባታል!!! 12 ሰዓት 🙌”በማለት የስሜቱን መጋፈል የገለጸ ሲሆን፣ ሙዚቃው ክለቡና ደጋፊዎቹ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ያሳለፉትን ውጣ ውረድና አሁን የተቀዳጁትን ታላቅ ድል የሚያጣጥም እንደሚሆን ይጠበቃል።
የአርሰናልን የዋንጫ ድል ተከትሎ በርካታ ታዋቂ ሰዎችና ከያንያን ደስታቸውን እየገለጹ በሚገኙበት በዚህ ወቅት፣ በሳሚ ዳን የሚለቀቀው አዲስ ዜማ በማህበራዊ ሚዲያ እና በስፖርት አፍቃሪው ዘንድ ከፍተኛ ጉጉትን ፈጥሯል።
Via ጉርሻ page

🤣55❤33👍10🤪6🙊1
ሻዕቢያ በመቀሌ ቢሮ
በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው የባይቶና ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ ክብሮም በፋና ቴሌቪዥን በሰጡት ማብራሪያ፣ በክልሉ ወቅታዊ የፖለቲካ እና የፀጥታ ሁኔታዎች ላይ እጅግ ጠንከር ያሉና አነጋጋሪ ትችቶችን ሰንዝረዋል።
አመራሩ በትነተናቸው እንዳብራሩት፣ የኤርትራ መንግስት (ሻዕቢያ) በመቀለ ከተማ ውስጥ ምንም ዓይነት ታፔላ ወይም መለያ ምልክት የሌለበት ድብቅ ቢሮ በመክፈት፣ "ፅምዶ" ከተባለው ስብስብ ጋር በፈጠረው ውህደት አማካኝነት በትግራይ ምድር ላይ እንደልቡና ያለ ምንም ከልካይ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ይህ ዓይነቱ አሰራር በክልሉ ውስጥ ያለውን የህግ የበላይነትና የፀጥታ ቁጥጥር ጥያቄ ውስጥ የሚከት ከመሆኑም በላይ፣ በትግራይ ህዝብ የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ ከፍተኛ ስጋትና ምስቅልቅል የሚፈጥር መሆኑን በአፅንኦት ገልጸዋል።
በተጨማሪም አቶ ክብሮም በዚሁ የፋና ቲቪ ቆይታቸው፣ በትግራይ ክልል ለረጅም ዓመታት በስልጣን ላይ የቆየውን የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሃት) ፓርቲን ክፉኛ ተችተዋል።
ህወሃት ባለፉት ዓመታት የተከተላቸው የተሳሳቱ የፖለቲካ መስመሮችና የወሰዳቸው ውሳኔዎች የትግራይን ህዝብ ለከፍተኛ መከራ፣ ስደትና ውድመት የዳረጉ መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ድርጅቱ በተግባር የትግራይ ህዝብ ዋነኛ አጥፊ ነው ሲሉ በደፍረት ተናግረዋል።

❤10👍2
ጥቆማ🚨🚨🚨
በእርግጠኝነት የሚታመን ዜና ጠፍቶ ተቸግራችኋል‼️
እነሆ ትኩስና ወቅታዊ ተጨባጭ ዜናዎችን እና ታማኝ መረጃዎችን ይከታተሉ:-
ተቀላቀሉ👇👇👇
https://t.me/seledadotio

👍4❤3🥰1
የአፍሪካ አህጉር ከታሰበው በላይ በከፍተኛ ፍጥነት ለሁለት እየተሰነጠቀች መሆኑ ተገለጠ‼️
የምስራቅ አፍሪካ ታላቁ ስምጥ ሸለቆን ተከትሎ የአፍሪካ አህጉር ለሁለት የመከፈል ሂደቷ ከዚህ ቀደም ከሚገመተው በላይ እየፈጠነ መምጣቱን ይፋዊ መረጃዎች አመላከቱ።
ታዋቂው የሳይንስና የዕውቀት መድረክ ብራይት ሳይድ (BRIGHT SIDE) ይፋ ባደረገው ወቅታዊ ዘገባ መሠረት፣ ይህ የምድር ንጣፍ የመሰነጣጠቅ ሂደት (Continental Rifting) በንድፈ-ሐሳብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በተግባር "ቀድሞውኑ መጀመሩን" (Already Started) አረጋግጧል።
አህጉሪቱ በሁለት ታላላቅ የምድር ንጣፎች (በኑቢያን እና በሶማሊያን ፕሌቶች) እየተከፈለች ሲሆን፣ ሂደቱ በቢሊዮን እና በሚሊዮን በሚቆጠሩ ዓመታት ውስጥ አዲስ ውቅያኖስ በመፍጠር የምስራቅ አፍሪካን ክፍል (ኢትዮጵያን፣ ኬንያን፣ ሶማሊያንና ማዳጋስካርን ጨምሮ) ከቀሪው የአፍሪካ ምድር ሙሉ በሙሉ ይገነጥላል ተብሎ ይጠበቃል። አሁን ላይ የታዩት ፈጣን የጂኦሎጂካል ለውጦች ግን ክስተቱ ሳይንቲስቶች ካሰቡት በላይ እየተፋጠነ መሆኑን የሚያሳይ ሆኗል።

❤22🤣9👍6👏4😢2🥱2👀2🤔1😱1
ገንዘብ ሚንስትር አሕመድ ሽዴ፣ ዓለማቀፍ አጋሮችና የፋይናንስ ተቋማት ለታዳጊ አገራት የነዳጅና ማዳበሪያ መግዣና ለአነስተኛ አርሶ አደሮች መደጎሚያ አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠየቁ።
አሕመድ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ሳቢያ የተፈጠረው የማዳበሪያ አቅርቦት ማሽቆልቆልና የምርት ወጪዎች መጨመር የግብርና ምርታማነትን እንደሚቀንስና የምግብ ዋስትናን እንደሚሸረሽር ትናንት ለንደን ላይ በተካሄደው ግሎባል ፓርትነርሺፕ ኮንፈረንስ ላይ ስጋታቸውን መግለጣቸውን በለንደን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጠቅሷል።
የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት ያስከተለው የነዳጅ ዋጋ መናር፣ የትራንስፖርት፣ የመስኖ፣ የግብርና ማቀነባበርና የምግብ ሥርጭት ወጪዎችን እንዳናረ አሕመድ መናገራቸውንም ኢምባሲው ጠቅሷል።
አሕመድ፣ በቀጠናዊ የአቅርቦት ሠንሠለቶች፣ መጋዘኖችና ሎጅስቲክ ላይ የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት ሊፈስባቸው የሚገቡ ዘርፎች መኾናቸውን አጽንዖት ሠጥተዋል ተብሏል።
ሰብዓዊ ዕርዳታ ጥገኝነትን ከመፍጠር ወጥቶ ከአገራዊ ሥርዓቶችና አገራት ቅድሚያ ከሚሠጧቸው ጉዳዮች ጋር መጣጣም እንዳለበትም አሕመድ ማሳሰባቸው ተገልጧል።

❤9👍3🤩2👏1😢1
መረጃ‼️
አዲሱ የታክስ አስተዳደር ሕግ፣ በግብይት ወቅት ደረሠኝ የማይቆርጡ ነጋዴዎች እስከ 100 ሺሕ ብር የሚደርስ ቅጣት እንዲጣልባቸው የሚያዝ ኾኖ ተዘጋጀ።
ሸቀጦች የተሸጡበትን ዋጋ ኾነ ብሎ በመቀነስ ደረሠኝ መቁረጥም ተመሳሳይ ቅጣት ይጣልበታል።
አሁን በሥራ ላይ ባለው ሕግ፣ ነጋዴዎች ያለ ደረሠኝ በሚያካሂዱት እያንዳንዱ ግብይት የሚከፍሉት ቅጣት 50 ሺሕ ብር ነው።
አዲሱ ረቂቅ ሕግ፣ ደረሠኝ ባለመቁረጥ ባንድ ዓመት ውስጥ ሁለት ጊዜ የገንዘብ ቅጣት የተጣለባቸው ነጋዴዎች ድርጊቱን በድጋሚ ከፈጸሙ ከአምስት እስከ ሰባት ዓመት በሚደርስ እስር እንደሚቀጡም አስፍሯል።
በረቂቅ ሕጉ ላይ ትናንት ምክክር ያደረጉ ባለድርሻ አካላት፣ የገንዘብ ቅጣቱ የተጋነነ መኾኑን በመጥቀስ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

❤11🥱10👍4😁1🌚1
የባንኩ መግለጫ‼️
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት በሀገሪቱ በሚገኙ በተመረጡ ከተሞች ላይ የተከፈቱ የባንክ ሂሳቦች እስከ ግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ከደንበኞች የፋይዳ መታወቂያ ጋር እንዲተሳሰር የተቀመጠው ቀነ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ በትዕዛዙ መሰረት ደንበኞች እነዚህን ሂሳቦች ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ ተደርጓል፡፡
ይህንን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ የማስተሳሰር ጥያቄ ወደ ባንካችን እየቀረበ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ባንካችን ይህንን ጫና በመቋቋም ለደንበኞቻችን በሚፈለገው ፍጥነት ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተለያዩ አሰራሮችን ተግባራዊ አድርጓል፡፡
ለአብነት ከግንቦት 7 እስከ ግንቦት 12 በተለየ ምክንያት እንዳይንቀሳቀሱ ከተደረጉት ሂሳቦች ውጪ የተሳሰሩ ሂሳቦችን ደንበኞች ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ተደርጓል፡፡ እንዲሁም ከ ከግንቦት 12 ጀምሮ ደንበኞች ሂሳባቸውን እንዳስተሳሰሩ የመረጃ ስርዓታችን (system) በራሱ ጊዜ ገደቡን እንዲያነሳ ተደርጓል፡፡
መሰል ፈጣን ምላሾን እየሰጠን የደንበኞቻችንን እርካታ እውን ለማድረግ የምንሰራ መሆኑን እያረጋገጥን በዚህ ሂደት ላሳያችሁት ትዕግስት ከልብ እያመሰገንን በደንበኞቻችን ላይ ለተፈጠረው መጉሏሏት ይቅርታ ለመጠየቅ እንወዳለን፡፡
በተጨማሪም እንዳይንቀሳቀስ ከተደረጉ ሂሳቦች እና ከነዚህ ውጭ በተቀሩት የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ የባንክ ቅርንጫፍ ደንበኞች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ አስቀድማችሁ የማስተሳሰር ሂደቱን በባንካችን ቅርንጫፎች በመገኘት ወይም በበይነ መረብ (Online) ማስተሳሰሪያ አማራጭ (https://cbefayda.cbe.com.et) ሂሳባችሁን ለማንቀሳቀስ እንድትችሉ በአክብሮት እንጠይቃለን፡

❤16👍9😡3🥰2😢1
የቲክቶክ መረጃ አቅራቢ የሆነው Dylan Page ወደ ኢትዮጵያ እየመጣ እንደሆነ ተነገረ። ከ19 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያለው Dylan በኢትዮጵያ በሚኖረው ቆይታ የተለያዩ ቦታዎችን ይጎበኛል ተብሎ ይጠበቃል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤27🤷♂11👍3😁1
ትራምፕ የነዳጅ ዋጋ አንደሚቀንስ ቃል ገብተዋል‼️
በሆርሙዝ ሰርጥ 1,600 መርከቦች 'ነዳጅ የጫኑ 1,600 መርከቦች በቅርብ ጊዜ ውስጥ ነፃ ይወጣሉ ብለዋል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
በሆርሙዝ ሰርጥ 1,600 መርከቦች 'ነዳጅ የጫኑ 1,600 መርከቦች በቅርብ ጊዜ ውስጥ ነፃ ይወጣሉ ብለዋል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤18🥱5🤷4👍2🤪1
በኢራን እና አሜሪካ መካከል አዲስ የሰላም ንግግር ማድረጋቸው ተሰማ
የኢራኑ ታስኒም የዜና ወኪል እንደዘገበው፤ ኢራን ከሶስት ቀናት በፊት በፓኪስታን አምባሳደር በኩል 14 ነጥቦችን የያዘ አዲስ የተሻሻለ የሰላም ረቂቅ ሰነድ ለአሜሪካ ካስገባች በኋላ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በበኩሏ የራሷን ማሻሻያ እና የውይይት ነጥቦች ዛሬ በፓኪስታን በኩል ለቴህራን ልካለች።
በአሁኑ ወቅት የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣናት የአሜሪካን ሰነድ በጥልቅ እየገመገሙት ሲሆን፣ እስካሁን ይፋዊ ምላሽ አልሰጡ፡ የፓኪስታን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሞህሲን ናቅቪ በቴህራን የሚገኙ ሲሆን፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያሉትን ሰፊ የሃሳብ ልዩነቶች ለማጥበብ እና ስምምነቱ እንዳይከሽፍ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጥረት እያደረጉ ነው።
አሜሪካ በድርድሩ ወቅት የኢራን የዘይት ማዕቀብ እንዲነሳ ልትስማማ እንደምትችል ፍንጭ የሰጠች ቢሆንም፣ ኢራን ግን ሁሉንም ማዕቀቦች ሙሉ በሙሉ በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚያስገድድ ስምምነት እንዲሆን እየወተወተች ነው።
የቴህራን 14 ነጥብ እቅድ በዋናነት የሚያተኩረው ጦርነቱን ሙሉ በሙሉ ለማቆም እና በአሜሪካ በኩል “የእምነት ግንባታ እርምጃዎች እንዲወሰዱ በሚሉ ነጥቦች ላይ ነው።

❤18👍2😢2
በጣና ሐይቅ ላይ በደረሰ ድንገተኛ የጀልባ መስመጥ አደጋ የብዙዎች ሕይወት አለፈ
ግንቦት 13፤ ባሕር ዳር የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ዓመታዊ የዋዜማ በዓል ለማክበር በጣና ሐይቅ ላይ በጉዞ ላይ የነበሩ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮችን የጫነች ጀልባ ድንገተኛ የመስመጥ አደጋ ደርሶባታል።
በደረሰው አሳዛኝ አደጋ ምክንያት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የብዙ ወገኖቻችን ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል።
Via የባሕር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት

💔32😢20❤7👏4👍2😁2🤔2
የምርጫ ጸሎት እና ዱአ ሊደረግ ነው!
የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ መጪውን ምርጫ አስመልክቶ፣ ሰባት የሃይማኖት ተቋማት የሚሳተፉበት የጸሎት መርሀ ግብር ማዘገጀቱን መሆኑን አስታውቋል፡፡
ግንቦት 16/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ፓርክ በሚካሄው የምርጫ ጸሎት መርሀግብር ላይ ሰባት የሃይማኖት ተቋማት የሃይማኖት አባቶች ባሉበት እንደሚከናወን ተገልጿል። በተመሳሳይ ሰዓት በሁሉም ክልሎች የጸሎት ሥነ ሥርዓት እንደሚከናወንም የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ቀሲስ ታጋይ ገልጸዋል።
የአደባባይ ጸሎቱ በዋናነት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ በማሰብ የሚካሄድ መሆኑም የጉባኤው ጸሐፊ ገልጸዋል። ጉባኤው ያዘጋጀው መርሀግብር ከ1 ሺሕ በላይ ዜጎች የሚሳተፉበት የጸሎት እና የዱአ መርሃግብር መሆኑን ተናግረዋል፡፡(አንድ አፍታ)

🤣82❤20😁15💔3👍2
የፈተና ፕሮግራም ተቀይሯል‼️
የሪሜዲያል ፈተና እና የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) የሚሰጥበት ቀን ተቀይሯል።
በዚህም የ ሪሚዲያል ፈተና ከግንቦት 27- እስከ ሰኔ 3 የሚሰጥ ሲሆን የድህረ ምረቃ መውጫ ፈተና ከሰኔ 4-12 የሚሰጥ ይሆናል።

👍6❤4🤯1
ነዳጅና ጋዝ ለአለም ገበያ
ኢትዮጵያ የነዳጅ እና የጋዝ ምርቶቿን በጅቡቲ በኩል ለአለም ገበያ ለማቅረብ እቅድ አውጥታለች
ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዝ እና ድፍድፍ ነዳጅን በጅቡቲ በኩል ለአለም ገበያ የመላክ እቅዷን ከጅቡቲ ጋር የተጋራች ሲሆን የተጣራ የነዳጅ ምርቶችንም ከጅቡቲ በቧንቧ ታስገባለች።
ሃሳቡን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ ለጅቡቲ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ አቅርበዋል።
የጅቡቲ የዜና ወኪል (ADI) እንደዘገበው ፕሬዚዳንቱ እቅዱን ተቀብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበው ሃሳብ ሁለት ምዕራፎችን ያካተተ ነው።
የመጀመሪያው ምዕራፍ 113 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተጣራ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ ሲሆን ከጅቡቲ ወደብ ተነስቶ መጨረሻው በኢትዮጵያ ጅቡቲ ድንበር ላይ በሚገኘው ደወሌ ላይ ነው።
ሁለተኛው ምዕራፍ 760 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የጋዝ እና ድፍድፍ ነዳጅ መስመር ዝርጋታ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ውስጥ ካለው የኦጋዴን ክልል ጀምሮ እስከ ጅቡቲ ወደብ ድረስ ይዘልቃል። ለሁለቱም የቧንቧ መስመር ዝርጋታ እና የነዳጅ ማጣሪያዎች አጠቃላይ ወጪ ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው።
የፕሮጀክቶቹ ስኬት በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እና በዳንጎቴ ኢንቨስትመንት ግሩፕ መካከል ያለውን ትብብር ወደ ላቀ እና ስትራቴጂካዊ ደረጃ
እንደሚያሳድገው ይጠበቃል።
ከ7 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተገኘውን ድፍድፍ ነዳጅ ወደ ውጭ ለመላክ ቱቦ እየተቀበረ መሆኑን መዘገቡ የሚታወስ ነው።

😁22❤17🤔8👍7🤪6👏2🎉1😎1