ደረሰኝ ሳይሰጡ ሽያጭ የፈፀሙ ግብር ከፋዩች ቅጣትን ከ50 ሺህ ብር ወደ 100 ሺህ ብር ከፍ እንዲል የሚያደርግ የታክስ አስተዳደር የማሻሻያ አዋጅ ተዘጋጀ
በዛሬዉ እለት ለ10 አመት ሲሰራበት የቆየዉን የታክስ አስተዳደር አዋጅ ማሻሻያ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት እና ባለሙያዎች ጋር የግብአት መሰባሰብ ዉይይት አድርጓል።
በዚህ የማሻሻያ ረቂቅ ዉስጥ ተሻሽለው ከቀረቡ ነጥቦች መካከል ደረሰኝ ሳይሰጡ ሽያጭ የሚፈፅሙ ግብር ከፋዩች ላይ ከዚህ ቀደም ቅጣት ተብሎ ተቀምጦ የነበረዉን የገንዘብ ቅጣት ከፍ ያደረገ ህግ ተቀምጦበታል።
በዚህም 50 ሺህ ብር ቅጣትን ያስቀምጥ የነበረዉን በማሻሻል የ100 ሺህ ብር ቅጣት የሚጥል አዲስ ህግ በረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ላይ ተቀምጧል።
ይህም በእያንዳንዱ ደረሰኝ የደረሰኙ ዋጋ ከግምት ዉስጥም የማይገባ ነዉ ተብሏል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ የህግ አማካሪዉ አቶ ዋሲሁን አባተ እንደገለፁት "የተቀመጠዉ ገንዘቡ መጠን በግብር ከፋዩ ዘንድ እንደ አንድ ወጪ ታሳቢ እየተደረገ መጥቷል፤ ይህ ደግሞ ህገወጥነቱን እየጨመረ እንዲመጣ እያደረገ መጥቷል ብለዋል"።
ለዚህም ማሻሻያ እንዲደረግበት ሆኖ መቀመጡን ለዉይይቱ ተሳታፊዎች አስረድተዋል ።
በዚህ ሽያጭ ደረሰኝ ሳይሰጡ ሽያጭ በሚፈፅሙ ግብር ከፋይ በዚህ ድርጊት ከሁለት ጊዜ በላይ ከተገኙ ግን ወደ እስር የሚወስድ አስተዳደራዊ ቅጣት እንደሚኖር አያይዘዉ ገልፀዋል።
ቁምነገር አየለ
@Addis_Reporter

❤10😡7👍3
የዶላር ዋጋ ወደ 159.98 ብር ከፍ አለ፤ ብሔራዊ ባንክ ካቀረበው የውጭ ምንዛሬ ከእጥፍ በላይ ፍላጎት ቀረበበት
አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ፣ የዶላር አማካይ የማሸነፊያ ዋጋ 159.98 ብር መድረሱን ይፋ አደረገ።
ባንኩ ይፋ ባደረገው መግለጫ መሠረት፣ በገበያው ውስጥ አሁንም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት መኖሩን የሚያሳዩ ውጤቶች ተመዝግበዋል።
ብሔራዊ ባንኩ ለዚህ ልዩ ጨረታ 500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያቀረበ ቢሆንም፣ ከንግድ ባንኮች በኩል የቀረበው አጠቃላይ የፍላጎት መጠን ግን ከቀረበው አቅርቦት በእጥፍ በመጨመር 1.06 ቢሊዮን (አንድ ቢሊዮን ከስድሳ ሚሊዮን) ዶላር ሆኖ ተመዝግቧል።
በጨረታው ላይ በአጠቃላይ 30 የንግድ ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 14ቱ ባንኮች ብቻ ጨረታውን አሸንፈው የውጭ ምንዛሬውን ማግኘት ችለዋል።
የዕለቱ የምንዛሬ ተመን ዝርዝር፦
1. የማሸነፊያ አማካይ ክብደት ዋጋ (Weighted Average Rate): 159.9865 ብር
2. የመቁረጫ ዋጋ (Marginal/Cut-off Rate): 159.6299 ብር
3. ከፍተኛው የቀረበ የማሸነፊያ ዋጋ:160.9064 ብር
4. ዝቅተኛው የቀረበ የማሸነፊያ ዋጋ:157.3005 ብር
ብሔራዊ ባንክ ከሁለት ወራት በፊት ባካሄደው ተመሳሳይ ጨረታ 70 ሚሊዮን ዶላር አቅርቦ የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱ የአንድ ዶላር አማካይ ዋጋ 157 ብር ከ46 ሳንቲም ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል።

❤20😢5😱4👍3
ትራምፕ ሌላ ጦርነት ሊጀምሩ ነው‼️
ትራምፕ በኩባ ላይ ጦርነት ለመጀመር እያሰቡ መሆኑን ፖለቲኮ ዘግቧል።
"ትራምፕ እና አማካሪዎቹ በኩባ ላይ እየተደረገ ያለው ጫና ባለመስራቱ እንደተበሳጩ እና ወታደራዊ አማራጭን ለመጠቀም እያጤኑ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል። አሜሪካ ጦርነት ከጀመረች ኩባ እፋለማለሁ ብላለች።

❤17😢5🙉3👍2🤷♂1😈1👀1
በኦሮሚያ ክልል ታጣቂዎች በሕዝብ አውቶብስ ላይ ተኩስ በመክፈት ተሳፋሪዎችን አገቱ
በኦሮሚያ ክልል ከገብረ ጉራቻ ወደ ፍቼ በሚወስደው መንገድ አሊደሮ በተባለ አካባቢ ታጣቂዎች ሕዝብ ጭኖ እየተጓዘ በነበረ ልዩ የሕዝብ አውቶብስ ላይ ተኩስ በመክፈትና ተሽከርካሪውን አስገድደው በማስቆም ከሦስት ሰዎች በቀር ሁሉንም ተሳፋሪዎች አፍነው መውሰዳቸውን የካቢኔ ሹፌሮች ገለጹ።
የአውቶብሱን መስታወትና ጎማዎች በመምታት የተፈጸመውን ይህንን ጥቃት ተከትሎ፣ አካባቢው ለዓመታት የታጠቁ ወንበዴዎች እገታ፣ ዘረፋና ግድያ የሚፈጽሙበት ቢሆንም በጉዳቱ ግዝፈት ልክ ትኩረት እንዳልተሰጠው የተጠቆመ ሲሆን፤ የሕግ አስከባሪዎች ተሳፋሪዎችን ለማዳን ሕይወታቸውን ጭምር እየከፈሉ መሆኑ ቢመሰገንም፣ የአፈና ወንጀሉን ከስር መሰረት ለመንቀልና ሾፌሮችን፣ ረዳቶችንና ተሳፋሪዎችን ከአደጋ ለመጠበቅ የአሠራር ግምገማ በማድረግ አዳዲስ ስልቶችን መከተልና በቂ ጥበቃ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

😢16❤14💔12👍4
መረጃ‼️
የኦሮሚያ ክልል የጸጥታና አሥተዳድር ቢሮ፣ የመንግሥትን የሠላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ማኅበረሰቡ የተቀላቀሉ የቀድሞ የ"ሸኔ" ታጣቂዎችንና ቤተሰቦቻቸውን ቡድኑ እየገደለ፣ አፍኖ እየወሠደና ቤታቸውን እያቃጠለ ይገኛል ሲል ከሠሠ።
በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች አርሶ አደሮችን የመዝረፍ፣ ሰዎችን አግቶ የማስለቀቂያ ገንዘብ የመጠየቅና ባለሀብቶችን በማስፈራራት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ የመቀበል ወንጀሎችን የሚፈጽሙት የ"ሸኔ" ታጣቂዎች ናቸው ሲል የከሠሠው ቢሮው፣ ታጣቂዎቹ ከሻዕቢያ፣ ከሕወሃትና ሌሎች ጠላቶች ተልእኮ የሚቀበሉ ናቸው በማለት ጭምር ወንጅሏል።
ጥቂቶቹ ታጣቂዎች "ከተራ ዝርፊያ" ያለፈ ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ዓላማ እንደሌላቸው የቢሮው ኃላፊ ኮሚሽነር ጄነራል አራርሳ መርዳሳ መናገራቸውን ቢሮው በይፋዊ ማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሠራጨው መረጃ ገልጿል።
ኮሚሽነር ጄነራል አራርሳ፣ የመንግሥትን የሠላም ጥሪ በማይቀበሉ ታጣቂዎች ላይ የጸጥታ ኃይሎች አስፈላጊውን ርምጃ ይወስዳሉ ማለታቸውንም ከቢሮው መረጃ ላይ ተመልክተናል።

🤪10❤7👍4✍2🙉2👏1😁1😢1
አርሰናል የዋንጫ ባለቤት መሆኑን ተከትሎ ከአቶ ጌታቸው ረዳ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ተላለፈ
የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዋንጫ ባለቤት መሆኑን ተከትሎ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ "Bravo Arsenal" በማለት ለክለቡና ለደጋፊዎቹ ያላቸውን አድናቆትና ደስታ ገልጸዋል።

❤43😁41👍16🤪6👏3🥱2🥰1🎉1👌1😎1
ጥንቃቄ‼️
በፋይዳ ማጣመር ስም እንዳይጭበረበሩ‼️
ደንበኞች የባንክ ሂሳባቸውን ከፋይዳ መታወቂያቸው ጋር እንዲያጣምሩ የተጀመረውን ሥራ አንዳንድ አጭበርባሪዎች እንደአጋጣሚ ለመጠቀም እየሞከሩ መሆኑ ተደርሶበታል።
በመሆኑም ደንበኞች የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች በማድረግ ራሳቸውን ከአጭበርባሪዎች እንዲከላከሉ ባንኩ አሳውቋል፡
• በባንኩ ቅርንጫፎች በመገኘት ወይም ባንካችን ያዘጋጀውን የበይነ መረብ (Online) ማስተሳሰሪያ አማራጭ (https://cbefayda.cbe.com.et) በመጠቀም ብቻ የሂሳብ ቁጥርዎን ከፋይዳ መታወቂያዎ ጋር ያስተሳስሩ፤
• የማስተሳሰሩ ሥራ በስልክ ተደውሎ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ በሚላኩ መልእክቶች የማይሠራ መሆኑን ተገንዝበው መሰል ጥያቄዎችን አያስተናግዱ፤
• ባሉበት በበይነ መረብ ለማስተሳሰር ሲሞክሩ እርዳታ ከፈለጉ ከማያውቁት ወይም በሚገባ ከማያምኑት ሰው እገዛ አይጠይቁ።

❤14👍5
#EU : የአውሮፓ ኅብረት ከሁለት ዓመት በፊት በኢትዮጵያውያን ላይ የጣለውን የቪዛ ገደብ ማንሳቱን አስታውቋል።
" የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ ወጥ መንገድ በአውሮፓ የሚኖሩ ዜጎቹን ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ ነው " በሚል በኢትዮጵያውያን ላይ የቪዛ ገደብ ተጥሎ ቆይቷል።
የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት አሁን ባወጣው መግለጫ፤ በኅብረቱ አባል አገራት ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በመለየት እና ወደ አገራቸው በመመለስ ረገድ መሻሻሎች ስለታዩ ገደቡ እንዲነሳ ተወስኗል።
ተጠሎ የነበረው እግዳ ምን ነበር ?
- አባል ሀገራት ኢትዮጵያውያን በሚያቀርቧቸው ማስረጃዎች መሠረት ቪዛ ሲጠይቁ የሚያስፈልጓቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማንሳት (waiving requirements) እንዳይችሉ፤
- የኅብረቱ አባል ሀገራት ከሁለት ጊዜ በላይ ወደ ህብረቱ አባል ሀገራት ለመግባት የሚያስችለውን ቪዛ ለኢትዮጵያውያን መስጠት እንደማይችሉ ፤
- የዲፕሎማቲክ ወይም የሰርቪስ ፓስፖርት የያዙ ኢትዮጵያውያን ቪዛ ሲፈልጉ መደበኛ የቪዛ ክፍያ ለመክፈል እንደሚገደዱ፤
- መደበኛ ቪዛ ለማግኘት የሚጠበቀው የ15 ቀን ጊዜ ወደ 45 ቀን ከፍ እንዲል ... ተወስኖ ነበር።
አሁን ግን ይህ የቪዛ እገዳ ተነስቷል።
በሌላ በኩል፣ ከዚህ ቀደም በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ መስጠት አቋርጦት የነበረውን የበጀት ድጋፍ መልሶ አስጀምሯል።

❤9👍2
የሁለት ወራት ደመወዝ የለም-ህወሓት‼️
በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የህወሃት ቡድን፣ በትግራይ ክልል ለሚገኝ ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ የግንቦት እና የሰኔ ወራት ደመወዝ እንዳይከፈል የሚል ጥብቅ መመሪያ አስተላለፈ።
ዶ/ር ደብረጽዮን ለክልሉ ዞኖች፣ ወረዳዎች እና ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ጭምር ባስተላለፉት የጽሁፍ ትዕዛዝ «ለሁለት ወራት ደሞዝ የለም፤ ይህንን ከወዲሁ እወቁት» ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ለውሳኔው እንደ ምክንያት የቀረበው የሀብት ውስንነት መኖሩ እና ፍትሃዊ የደመወዝ ማስተካከያ ለማድረግ መታሰቡ ቢሆንም፣ ቡድኑ «ፌደራሉ በጀት ከልክሎናል» በማለት አስቸኳይ የሀብት ማሰባሰብ ስራ እንዲጀምርም አዟል።
ይህ ይፋዊ መግለጫ «የበጀት እጥረት» ቢለውም፣ ታዛቢዎችና የፖለቲካ ተንታኞች ግን ውሳኔው ህወሃት ለሌላ አዲስ ጦርነትና ወታደራዊ ግጭት እያደረገው ያለውን ስውር ዝግጅት የሚያሳይ ግልጽ ማሳያ ነው ይላሉ።
ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ ክልል ትምህርት ግንቦት 30 እንዲያበቃ ወስኗል።

😁7👍6❤5🤔1🤪1
የ26 ኪሎ ግራም እጢ በተሳካ ኦፕሬሽን ተወገደ‼
በመቀሌ ዓይደር ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ14 ዓመታት በማህፀን እጢ ሲሰቃዩ የነበሩ የ56 ዓመት እናት፣ ከሦስት ሰዓታት በላይ በፈጀ አስቸጋሪ ቀዶ ጥገና የ26 ኪሎ ግራም እጢ ተወግዶላቸው እፎይታ አግኝተዋል።
📌እነዚህ እናት ቀደም ሲል በርካታ የሕክምና ሙከራዎችን ቢያደርጉም ሳይሳካላቸው የቀረ ሲሆን፣ አልፎ ተርፎም የተሳሳተ ምርመራ ተደርጎላቸው የቲቢ መድኃኒት እስከመውሰድ ደርሰው ነበር። በአሁኑ ወቅት ከቀዶ ጥገናው በኋላ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።
📌የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ዶ/ር ተወልደብርሃን አብርሃ የተመራውና ዶ/ር ገብረኪሮስ ፀጋዛአብ፣ ዶ/ር ተኽላይ ዘርአይ፣ ዶ/ር ማርየ አለሜ እንዲሁም ማደንዘዣ ባለሙያዎችና ነርሶችን ያካተተው የሕክምና ቡድን ከፍተኛ ምስጋና ተችቶታል።
Via : Wasu Mohammed

❤32🙏8👍7😱2👏1
ግጭት ተቀስቅሷል‼️
ከትናንት በስተያ ግንቦት 10/2018 ዓ.ም በኦሮሚያ እና በሲዳማ ድንበር በምስራቅ ሲዳማ ዞን በጭሬ ወረዳ ጉበ ሔማ ቀበሌ በገበያ ቦታ ላይ በተነሳ አለመግባባት ምክንያት በሲዳማ እና በኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት መካከል ግጭት ተቀስቅሷል።
በዚህም ምክንያት የሰው ሕይወት የጠፋ ሲሆን፣ በርካታ ወገኖቻች ጉዳት እንደደረሰባቸው የአካባቢው ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
እስካሁን ባለው መረጃ የአንድ ሰው አስከሬን እና 7 የቆሰሉ ሰዎች ወደ ጤና ጣቢያ የገቡ ሲሆን፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሌሎች ሰዎችም መጎዳታቸው ታውቋል።
ግጭቱ አድማሱን አስፍቶ በሰብሎች ላይ ጭፍጨፋ ተፈፅሟል፣ ቤቶች ተቃጥለዋል።
Via : አዩዘሀበሻ

😢20❤4🌚3👍2🕊2
ድምፃዊ ሳሚ ዳን ለፕሪሚየር ሊግ አሸናፊው አርሰናል አዲስ የደስታ መግለጫ ሙዚቃ ሊለቅ ነዉ
ድምፃዊ ሳሚ ዳን ለፕሪሚየር ሊግ ዋንጫው ባለቤት አርሰናል አዲስ የደስታ መግለጫ ሙዚቃ ሊለቅ መሆኑን አስታወቀ።
ድምፃዊ ሳሚ ዳን መድፈኞቹ ከ22 ዓመታት ረጅም የጥበቃ ጊዜ በኋላ የኢንግሊሽ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ማንሳታቸውን ተከትሎ፣ ዛሬ ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ አዲስ ልዩ የደስታ መግለጫ ሙዚቃ ለአድማጮች እንደሚያደርስ ይፋ አድርጓል።
ታዋቂው ድምፃዊ ለአርሰናል ክለብ ያለውን ጥልቅ ፍቅርና አጋርነት በገለጸበት ማስታወቂያው፥ My አርሴ እማ አንድ ሙዚቃማ ይገባታል!!! 12 ሰዓት 🙌”በማለት የስሜቱን መጋፈል የገለጸ ሲሆን፣ ሙዚቃው ክለቡና ደጋፊዎቹ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ያሳለፉትን ውጣ ውረድና አሁን የተቀዳጁትን ታላቅ ድል የሚያጣጥም እንደሚሆን ይጠበቃል።
የአርሰናልን የዋንጫ ድል ተከትሎ በርካታ ታዋቂ ሰዎችና ከያንያን ደስታቸውን እየገለጹ በሚገኙበት በዚህ ወቅት፣ በሳሚ ዳን የሚለቀቀው አዲስ ዜማ በማህበራዊ ሚዲያ እና በስፖርት አፍቃሪው ዘንድ ከፍተኛ ጉጉትን ፈጥሯል።
Via ጉርሻ page

🤣55❤33👍10🤪6🙊1
ሻዕቢያ በመቀሌ ቢሮ
በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው የባይቶና ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ ክብሮም በፋና ቴሌቪዥን በሰጡት ማብራሪያ፣ በክልሉ ወቅታዊ የፖለቲካ እና የፀጥታ ሁኔታዎች ላይ እጅግ ጠንከር ያሉና አነጋጋሪ ትችቶችን ሰንዝረዋል።
አመራሩ በትነተናቸው እንዳብራሩት፣ የኤርትራ መንግስት (ሻዕቢያ) በመቀለ ከተማ ውስጥ ምንም ዓይነት ታፔላ ወይም መለያ ምልክት የሌለበት ድብቅ ቢሮ በመክፈት፣ "ፅምዶ" ከተባለው ስብስብ ጋር በፈጠረው ውህደት አማካኝነት በትግራይ ምድር ላይ እንደልቡና ያለ ምንም ከልካይ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ይህ ዓይነቱ አሰራር በክልሉ ውስጥ ያለውን የህግ የበላይነትና የፀጥታ ቁጥጥር ጥያቄ ውስጥ የሚከት ከመሆኑም በላይ፣ በትግራይ ህዝብ የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ ከፍተኛ ስጋትና ምስቅልቅል የሚፈጥር መሆኑን በአፅንኦት ገልጸዋል።
በተጨማሪም አቶ ክብሮም በዚሁ የፋና ቲቪ ቆይታቸው፣ በትግራይ ክልል ለረጅም ዓመታት በስልጣን ላይ የቆየውን የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሃት) ፓርቲን ክፉኛ ተችተዋል።
ህወሃት ባለፉት ዓመታት የተከተላቸው የተሳሳቱ የፖለቲካ መስመሮችና የወሰዳቸው ውሳኔዎች የትግራይን ህዝብ ለከፍተኛ መከራ፣ ስደትና ውድመት የዳረጉ መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ድርጅቱ በተግባር የትግራይ ህዝብ ዋነኛ አጥፊ ነው ሲሉ በደፍረት ተናግረዋል።

❤10👍2