አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ቡና ለገበያ አውጡ‼️
በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ምክንያት የቡና ዋጋ ስለማይጨምር፣ አምራችና ነጋዴዎች ምርታቸውን ለገበያ ማቅረብ እንዳለባቸው ተገለጸ‼️

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበለ የመካከለኛው ምስራቅን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ሀገራት በሚቀሰቀሱ ግጭቶች ምክንያት የቡና ዋጋ ሊጨምር ይችላል በሚል የተሳሳተ መረጃ ነጋዴዎች ኪሳራ ውስጥ እንዳይገቡ አሳስበዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና ምርቷ በስፋት የምትታወቀው ብራዚል ከሰኔ ወር ጀምሮ 78 ሚሊዮን ኩንታል የሚጠጋ ምርት ለገበያ ስለምታቀርብ፣ የሀገራችን አምራችና ነጋዴዎች ከዛ አስቀድመው ገበያ ላይ ቢያወጡት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ የቡና ዋጋ በቶን 30 በመቶ ያህል መቀነሱን የገለጹት ዶክተር አዱኛ፤ ምንም እንኳን ለሀገራችን ጉዳት ሆኖ የሚታይ ባይሆንም የቬትናምና የብራዚል ቡና ወደ ገበያ ከገባ ከዚህ በታች ሊወርድ ስለሚችል ምርቱን ባለው ገበያ ማቅረብ ይገባል ብለዋል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ ቬትናምና ብራዚል በዚህ ዓመት ከፍተኛ የቡና ምርት ማምረታቸው፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊከማች ይችላል ተብሎ ከተገመተው 8 ሚሊዮን ቶን በላይ የቡና ምርት እንዲኖር እንደሚያደርግና ይህም ለዋጋው መቀነስ አንዱ ምክንያት እንደሆነ ገልፀዋል።

የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ በማጓጓዣው ዘርፍ ላይ ተፅዕኖ ስለሚያሳድር በገበያው ላይ ተግዳሮት ቢፈጥርም፣ በቡና ዋጋ ላይ ግን ለውጥ እንደማይኖር ነው የተናገሩት።

የኢትዮጵያ የቡና ምርት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በዋጋም በገበያም የተሻለ እንደሆነና እስካሁንም ከደረጃ 4 በላይ የሆኑ የቡና ዓይነቶችን ብቻ ለዓለም አቀፉ ገበያ በማቅረብ ታዋቂነትንና የገበያ ትስስርን የመፍጠር ሂደቱ ውጤታማ እንዳደረገው ተናግረዋል።

በዘንድሮው የቡና ሽያጭም ኢትዮጵያ 320 ሺህ ሜትሪክ ቶን ቡና ወደ ውጭ ገበያ የላከች ሲሆን፣ ከዚህም 2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደተገኘ አመልክተዋል።

የቡና አምራችና ነጋዴዎች በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ምክንያት የቡና ዋጋ ይጨምራል በሚል ቡና ማከማቸት እንደሌለባቸውና ምርታቸውን ባለው ገበያ መሸጥ እንዳለባቸው ተመላክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍4
⚡️ እስራኤል በጋዛ፣ ሊባኖስ እና ሶሪያ 1,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ገደማ መሬት መቆጣጠሯ ተገለጠ!

​የፋይናንሻል ታይምስ ባደረገው አዲስ ትንተና መሠረት፣ ከጥቅምት 7 ጥቃት በኋላ እስራኤል በጋዛ፣ በሊባኖስ እና በሶሪያ በድምሩ የሀገሪቱን የ1949 ድንበር 5% የሚያክል (1,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር) መሬት በቁጥጥሯ ሥር አውላለች።

በደቡብ ሊባኖስ፦ ከተያዘው መሬት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው እዚህ የሚገኝ ሲሆን፣ እስራኤል ሄዝቦላህን ወደ ኋላ ለመግፋት በሚል እስከ 12 ኪሎ ሜትር ዘልቃ በመግባት “የደህንነት ቀጠና” ፈጥራለች። ሙሉ መንደሮች የወደሙ ሲሆን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ሁኔታውን “ከጋዛው ሞዴል” ጋር አነጻጽረውታል።

በጋዛ ሰርጥ፦ የእስራኤል ጦር በአሁኑ ወቅት ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የጋዛ ግዛት የተቆጣጠረ ሲሆን፣ ተጨማሪ የደህንነት ቀጠናዎችን በመፍጠሩ ምክንያት የጋዛ ህዝብ ከጦርነቱ በፊት ከነበረው ይዞታው 40% በሚሆነው ጠባብ መሬት ላይ ተጨናንቆ እንዲኖር ተገዷል።

በሶሪያ፦ እስራኤል ከኮረብታማው የሄርሞን ተራራ  በስተደቡብ ያለውን የድንበር አካባቢ ወደ 233 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚጠጋ መሬት ተቆጣጥራለች።

ኔታንያሁ ጦራቸው ከሊባኖስ “አይወጣም” ማለታቸውን ተከትሎ፣ እንዲሁም የእስራኤል ቀኝ አክራሪ ሚኒስትሮች በቦታው ላይ አዳዲስ ሰፈራዎች እንዲመሰረቱና “ሊታኒ ወንዝ” አዲሱ ድንበር እንዲሆን መጠየቃቸው፣ ይዞታው ቋሚ ሊሆን ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት በጎረቤት ሀገራት ላይ ፈጥሯል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😡107👍6
የአዋሽ-ኮምቦልቻ-ሐራ ገበያ የባቡር መስመር ግንባታ ከዓመታት መቋረጥ በኋላ ዳግም ተጀመረ!

በአዋሽ-ኮምቦልቻ-ሐራ ገበያ መስመር ላይ ተቋርጦ የነበረው የ1.7 ቢሊዮን ዶላር የባቡር መስመር ግንባታ፣ ከዓመታት መዘግየት በኋላ በይፋ ዳግም መጀመሩ ተገለጸ።

ይህ 392 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የኤሌክትሪክ ባቡር መስመር፣ የአማራ ክልል ዋና ዋና የንግድና የኢንዱስትሪ ማዕከላትን ከአዲስ አበባ-ጂቡቲ የባቡር ኮሪደር ጋር የሚያገናኝ በመሆኑ ለሀገሪቱ የጭነትና የሰው ትራንስፖርት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።

ግንባታው በ2015 እ.ኤ.አ. በቱርኩ "ያፒ መርከዚ" ኩባንያ የተጀመረ ቢሆንም፣ በኖቬምበር 2020 በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ምክንያት መሠረተ ልማቶቹ ላይ ጉዳት ደርሶና ውሎች ተስተጓጉለው ሥራው ቆሞ ቆይቷል።

በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ያለው የጸጥታ ሁኔታ በመሻሻሉ ሠራተኞችና መሣሪያዎች ወደ ሳይት የተመለሱ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ባቡር ኮርፖሬሽን የጥገና እና መልሶ ግንባታ ሥራው በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍4🤣4
ደረሰኝ ሳይሰጡ ሽያጭ የፈፀሙ ግብር ከፋዩች ቅጣትን ከ50 ሺህ ብር ወደ 100 ሺህ ብር ከፍ እንዲል የሚያደርግ የታክስ አስተዳደር የማሻሻያ አዋጅ ተዘጋጀ 

በዛሬዉ እለት ለ10 አመት ሲሰራበት የቆየዉን የታክስ አስተዳደር አዋጅ ማሻሻያ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት እና ባለሙያዎች ጋር የግብአት መሰባሰብ ዉይይት አድርጓል።

በዚህ የማሻሻያ ረቂቅ ዉስጥ ተሻሽለው ከቀረቡ ነጥቦች መካከል ደረሰኝ ሳይሰጡ ሽያጭ የሚፈፅሙ ግብር ከፋዩች ላይ ከዚህ ቀደም ቅጣት ተብሎ ተቀምጦ የነበረዉን የገንዘብ ቅጣት ከፍ ያደረገ ህግ ተቀምጦበታል።

በዚህም 50 ሺህ ብር ቅጣትን ያስቀምጥ የነበረዉን በማሻሻል የ100 ሺህ ብር ቅጣት የሚጥል አዲስ ህግ በረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ላይ ተቀምጧል።

ይህም በእያንዳንዱ  ደረሰኝ የደረሰኙ ዋጋ ከግምት ዉስጥም የማይገባ ነዉ ተብሏል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ የህግ አማካሪዉ አቶ ዋሲሁን አባተ እንደገለፁት "የተቀመጠዉ ገንዘቡ መጠን  በግብር ከፋዩ ዘንድ እንደ አንድ ወጪ ታሳቢ እየተደረገ  መጥቷል፤  ይህ ደግሞ ህገወጥነቱን እየጨመረ እንዲመጣ እያደረገ መጥቷል ብለዋል"።

ለዚህም ማሻሻያ እንዲደረግበት ሆኖ መቀመጡን ለዉይይቱ ተሳታፊዎች አስረድተዋል ።

በዚህ ሽያጭ ደረሰኝ ሳይሰጡ ሽያጭ በሚፈፅሙ ግብር ከፋይ በዚህ ድርጊት ከሁለት ጊዜ በላይ ከተገኙ ግን ወደ እስር የሚወስድ  አስተዳደራዊ ቅጣት  እንደሚኖር አያይዘዉ ገልፀዋል።

ቁምነገር አየለ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10😡7👍3
የዶላር ዋጋ ወደ 159.98 ብር ከፍ አለ፤ ብሔራዊ ባንክ ካቀረበው የውጭ ምንዛሬ ከእጥፍ በላይ ፍላጎት ቀረበበት
አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ፣ የዶላር አማካይ የማሸነፊያ ዋጋ 159.98 ብር መድረሱን ይፋ አደረገ።

ባንኩ ይፋ ባደረገው መግለጫ መሠረት፣ በገበያው ውስጥ አሁንም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት መኖሩን የሚያሳዩ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

ብሔራዊ ባንኩ ለዚህ ልዩ ጨረታ 500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያቀረበ ቢሆንም፣ ከንግድ ባንኮች በኩል የቀረበው አጠቃላይ የፍላጎት መጠን ግን ከቀረበው አቅርቦት በእጥፍ በመጨመር 1.06 ቢሊዮን (አንድ ቢሊዮን ከስድሳ ሚሊዮን) ዶላር ሆኖ ተመዝግቧል።

በጨረታው ላይ በአጠቃላይ 30 የንግድ ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 14ቱ ባንኮች ብቻ ጨረታውን አሸንፈው የውጭ ምንዛሬውን ማግኘት ችለዋል።

የዕለቱ የምንዛሬ ተመን ዝርዝር፦

1. የማሸነፊያ አማካይ ክብደት ዋጋ (Weighted Average Rate): 159.9865 ብር

2. የመቁረጫ ዋጋ (Marginal/Cut-off Rate): 159.6299 ብር

3. ከፍተኛው የቀረበ የማሸነፊያ ዋጋ:160.9064 ብር

4. ዝቅተኛው የቀረበ የማሸነፊያ ዋጋ:157.3005 ብር

ብሔራዊ ባንክ ከሁለት ወራት በፊት ባካሄደው ተመሳሳይ ጨረታ 70 ሚሊዮን ዶላር አቅርቦ የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱ የአንድ ዶላር አማካይ ዋጋ 157 ብር ከ46 ሳንቲም ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20😢5😱4👍3
ትራምፕ ሌላ ጦርነት ሊጀምሩ ነው‼️
ትራምፕ በኩባ ላይ ጦርነት ለመጀመር እያሰቡ መሆኑን ፖለቲኮ ዘግቧል።
"ትራምፕ እና አማካሪዎቹ በኩባ ላይ እየተደረገ ያለው ጫና ባለመስራቱ እንደተበሳጩ እና ወታደራዊ አማራጭን ለመጠቀም እያጤኑ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል። አሜሪካ ጦርነት ከጀመረች ኩባ እፋለማለሁ ብላለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17😢5🙉3👍2🤷‍♂1😈1👀1
በኦሮሚያ ክልል ታጣቂዎች በሕዝብ አውቶብስ ላይ ተኩስ በመክፈት ተሳፋሪዎችን አገቱ

በኦሮሚያ ክልል ከገብረ ጉራቻ ወደ ፍቼ በሚወስደው መንገድ አሊደሮ በተባለ አካባቢ ታጣቂዎች ሕዝብ ጭኖ እየተጓዘ በነበረ ልዩ የሕዝብ አውቶብስ ላይ ተኩስ በመክፈትና ተሽከርካሪውን አስገድደው በማስቆም ከሦስት ሰዎች በቀር ሁሉንም ተሳፋሪዎች አፍነው መውሰዳቸውን የካቢኔ ሹፌሮች ገለጹ።

የአውቶብሱን መስታወትና ጎማዎች በመምታት የተፈጸመውን ይህንን ጥቃት ተከትሎ፣ አካባቢው ለዓመታት የታጠቁ ወንበዴዎች እገታ፣ ዘረፋና ግድያ የሚፈጽሙበት ቢሆንም በጉዳቱ ግዝፈት ልክ ትኩረት እንዳልተሰጠው የተጠቆመ ሲሆን፤ የሕግ አስከባሪዎች ተሳፋሪዎችን ለማዳን ሕይወታቸውን ጭምር እየከፈሉ መሆኑ ቢመሰገንም፣ የአፈና ወንጀሉን ከስር መሰረት ለመንቀልና ሾፌሮችን፣ ረዳቶችንና ተሳፋሪዎችን ከአደጋ ለመጠበቅ የአሠራር ግምገማ በማድረግ አዳዲስ ስልቶችን መከተልና በቂ ጥበቃ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢1614💔12👍4
መረጃ‼️

የኦሮሚያ ክልል የጸጥታና አሥተዳድር ቢሮ፣ የመንግሥትን የሠላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ማኅበረሰቡ የተቀላቀሉ የቀድሞ የ"ሸኔ" ታጣቂዎችንና ቤተሰቦቻቸውን ቡድኑ እየገደለ፣ አፍኖ እየወሠደና ቤታቸውን እያቃጠለ ይገኛል ሲል ከሠሠ።

በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች አርሶ አደሮችን የመዝረፍ፣ ሰዎችን አግቶ የማስለቀቂያ ገንዘብ የመጠየቅና ባለሀብቶችን በማስፈራራት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ የመቀበል ወንጀሎችን የሚፈጽሙት የ"ሸኔ" ታጣቂዎች ናቸው ሲል የከሠሠው ቢሮው፣ ታጣቂዎቹ ከሻዕቢያ፣ ከሕወሃትና ሌሎች ጠላቶች ተልእኮ የሚቀበሉ ናቸው በማለት ጭምር ወንጅሏል።

ጥቂቶቹ ታጣቂዎች "ከተራ ዝርፊያ" ያለፈ ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ዓላማ እንደሌላቸው የቢሮው ኃላፊ ኮሚሽነር ጄነራል አራርሳ መርዳሳ መናገራቸውን ቢሮው በይፋዊ ማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሠራጨው መረጃ ገልጿል።

ኮሚሽነር ጄነራል አራርሳ፣ የመንግሥትን የሠላም ጥሪ በማይቀበሉ ታጣቂዎች ላይ የጸጥታ ኃይሎች አስፈላጊውን ርምጃ ይወስዳሉ ማለታቸውንም ከቢሮው መረጃ ላይ ተመልክተናል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪107👍42🙉2👏1😁1😢1
አርሰናል የዋንጫ ባለቤት መሆኑን ተከትሎ ከአቶ ጌታቸው ረዳ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ተላለፈ

​የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዋንጫ ባለቤት መሆኑን ተከትሎ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ "Bravo Arsenal" በማለት ለክለቡና ለደጋፊዎቹ ያላቸውን አድናቆትና ደስታ ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
43😁41👍16🤪6👏3🥱2🥰1🎉1👌1😎1
ጥንቃቄ‼️
በፋይዳ ማጣመር ስም እንዳይጭበረበሩ‼️
ደንበኞች የባንክ ሂሳባቸውን ከፋይዳ መታወቂያቸው ጋር እንዲያጣምሩ የተጀመረውን ሥራ አንዳንድ አጭበርባሪዎች እንደአጋጣሚ ለመጠቀም እየሞከሩ መሆኑ ተደርሶበታል።

በመሆኑም ደንበኞች የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች በማድረግ ራሳቸውን ከአጭበርባሪዎች እንዲከላከሉ ባንኩ አሳውቋል፡

• በባንኩ ቅርንጫፎች በመገኘት ወይም ባንካችን ያዘጋጀውን የበይነ መረብ (Online) ማስተሳሰሪያ አማራጭ (https://cbefayda.cbe.com.et) በመጠቀም ብቻ የሂሳብ ቁጥርዎን ከፋይዳ መታወቂያዎ ጋር ያስተሳስሩ፤

• የማስተሳሰሩ ሥራ በስልክ ተደውሎ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ በሚላኩ መልእክቶች የማይሠራ መሆኑን ተገንዝበው መሰል ጥያቄዎችን አያስተናግዱ፤

• ባሉበት በበይነ መረብ ለማስተሳሰር ሲሞክሩ እርዳታ ከፈለጉ ከማያውቁት ወይም በሚገባ ከማያምኑት ሰው እገዛ አይጠይቁ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍5
#EU : የአውሮፓ ኅብረት ከሁለት ዓመት በፊት በኢትዮጵያውያን ላይ የጣለውን የቪዛ ገደብ ማንሳቱን አስታውቋል።

" የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ ወጥ መንገድ በአውሮፓ የሚኖሩ ዜጎቹን ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ ነው " በሚል በኢትዮጵያውያን ላይ የቪዛ ገደብ ተጥሎ ቆይቷል።

የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት አሁን ባወጣው መግለጫ፤ በኅብረቱ አባል አገራት ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በመለየት እና ወደ አገራቸው በመመለስ ረገድ መሻሻሎች ስለታዩ ገደቡ እንዲነሳ ተወስኗል።

ተጠሎ የነበረው እግዳ ምን ነበር ?

- አባል ሀገራት ኢትዮጵያውያን በሚያቀርቧቸው ማስረጃዎች መሠረት ቪዛ ሲጠይቁ የሚያስፈልጓቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማንሳት (waiving requirements) እንዳይችሉ፤

- የኅብረቱ አባል ሀገራት ከሁለት ጊዜ በላይ ወደ ህብረቱ አባል ሀገራት ለመግባት የሚያስችለውን ቪዛ ለኢትዮጵያውያን መስጠት እንደማይችሉ ፤

- የዲፕሎማቲክ ወይም የሰርቪስ ፓስፖርት የያዙ ኢትዮጵያውያን ቪዛ ሲፈልጉ መደበኛ የቪዛ ክፍያ ለመክፈል እንደሚገደዱ፤

- መደበኛ ቪዛ ለማግኘት የሚጠበቀው የ15 ቀን ጊዜ ወደ 45 ቀን ከፍ እንዲል ... ተወስኖ ነበር።

አሁን ግን ይህ የቪዛ እገዳ ተነስቷል።

በሌላ በኩል፣ ከዚህ ቀደም በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ መስጠት አቋርጦት የነበረውን የበጀት ድጋፍ መልሶ አስጀምሯል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍2
የሁለት ወራት ደመወዝ የለም-ህወሓት‼️

በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የህወሃት ቡድን፣ በትግራይ ክልል ለሚገኝ ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ የግንቦት እና የሰኔ ወራት ደመወዝ እንዳይከፈል የሚል ጥብቅ መመሪያ አስተላለፈ።

ዶ/ር ደብረጽዮን ለክልሉ ዞኖች፣ ወረዳዎች እና ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ጭምር ባስተላለፉት የጽሁፍ ትዕዛዝ «ለሁለት ወራት ደሞዝ የለም፤ ይህንን ከወዲሁ እወቁት» ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ለውሳኔው እንደ ምክንያት የቀረበው የሀብት ውስንነት መኖሩ እና ፍትሃዊ የደመወዝ ማስተካከያ ለማድረግ መታሰቡ ቢሆንም፣ ቡድኑ «ፌደራሉ በጀት ከልክሎናል» በማለት አስቸኳይ የሀብት ማሰባሰብ ስራ እንዲጀምርም አዟል።

ይህ ይፋዊ መግለጫ «የበጀት እጥረት» ቢለውም፣ ታዛቢዎችና የፖለቲካ ተንታኞች ግን ውሳኔው ህወሃት ለሌላ አዲስ ጦርነትና ወታደራዊ ግጭት እያደረገው ያለውን ስውር ዝግጅት የሚያሳይ ግልጽ ማሳያ ነው ይላሉ።

ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ ክልል ትምህርት ግንቦት 30 እንዲያበቃ ወስኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁7👍65🤔1🤪1
የ26 ኪሎ ግራም እጢ በተሳካ ኦፕሬሽን ተወገደ

​በመቀሌ ዓይደር ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ14 ዓመታት በማህፀን እጢ ሲሰቃዩ የነበሩ የ56 ዓመት እናት፣ ከሦስት ሰዓታት በላይ በፈጀ አስቸጋሪ ቀዶ ጥገና የ26 ኪሎ ግራም እጢ ተወግዶላቸው እፎይታ አግኝተዋል።

📌​እነዚህ እናት ቀደም ሲል በርካታ የሕክምና ሙከራዎችን ቢያደርጉም ሳይሳካላቸው የቀረ ሲሆን፣ አልፎ ተርፎም የተሳሳተ ምርመራ ተደርጎላቸው የቲቢ መድኃኒት እስከመውሰድ ደርሰው ነበር። በአሁኑ ወቅት ከቀዶ ጥገናው በኋላ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።

📌​የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ዶ/ር ተወልደብርሃን አብርሃ የተመራውና ዶ/ር ገብረኪሮስ ፀጋዛአብ፣ ዶ/ር ተኽላይ ዘርአይ፣ ዶ/ር ማርየ አለሜ እንዲሁም ማደንዘዣ ባለሙያዎችና ነርሶችን ያካተተው የሕክምና ቡድን ከፍተኛ ምስጋና ተችቶታል።

Via : Wasu Mohammed

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
32🙏8👍7😱2👏1
ግጭት ተቀስቅሷል‼️
ከትናንት በስተያ ግንቦት 10/2018 ዓ.ም በኦሮሚያ እና በሲዳማ ድንበር በምስራቅ ሲዳማ ዞን በጭሬ ወረዳ ጉበ ሔማ ቀበሌ በገበያ ቦታ ላይ በተነሳ አለመግባባት ምክንያት በሲዳማ እና በኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት መካከል ግጭት ተቀስቅሷል።

በዚህም ምክንያት የሰው ሕይወት የጠፋ ሲሆን፣ በርካታ ወገኖቻች ጉዳት እንደደረሰባቸው የአካባቢው ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።

እስካሁን ባለው መረጃ የአንድ ሰው አስከሬን እና 7 የቆሰሉ ሰዎች ወደ ጤና ጣቢያ የገቡ ሲሆን፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሌሎች ሰዎችም መጎዳታቸው ታውቋል።

ግጭቱ አድማሱን አስፍቶ በሰብሎች ላይ ጭፍጨፋ ተፈፅሟል፣ ቤቶች ተቃጥለዋል።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢204🌚3👍2🕊2