አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
በኢትዮጵያ የዲጂታል ኦቲዝም በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገለፀ

ልጆች ረጅም ሰዓት በስልክና በቪዲዮ ጌሞች ላይ ማሳለፋቸው፣ መናገር የሚችሉ ሆነው ከተወለዱ በኋላ አንደበታቸው እንዲያዝ እያደረገ መምጣቱ ተገልጿል።

ይህም በተፈጥሮ ከሚመጣ ኦቲዝም ባልተናነሰ ለዲጂታል ኦቲዝም እያጋለጣቸው መሆኑን ፍቅር ኢትዮጵያ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበር ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ  ሸዋጌጥ ክብረት ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅት ወላጆች ልጆቻቸው ሲያለቅሱ ወይም ሲያስቸግሩ ስልካቸውን ሰጥተው ዝም ማሰኘትን እንደ ዋነኛ አማራጭ መውሰዳቸው በትውልዱ ላይ ትልቅ አደጋ እየጋረጠ ይገኛልም ብለዋል።

ዲጂታል ኦቲዝም የሚባለው ስያሜ ልጆች ከስክሪን ጋር ረጅም ጊዜ በማጥፋታቸው ሳቢያ የሚፈጠር የተግባቦትና የማህበራዊ ግንኙነት ክፍተት መሆኑን ያስረዱት ወ/ሮ ሸዋጌጥ፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቷ ላይ እየተስተዋለ የመጣው የህፃናት ስልክ አጠቃቀም ጤነኛ ሆነው የተወለዱ ህፃናትን ሳይቀር መናገር አቅቷቸው ወደ ማህበራቸው እንዲመጡ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ስራ አስኪያጇ ልጆች ዝም ብለው ስልክ ላይ ጊዜ ካጠፉ አያወሩም፤ ቃላት ማውጣት ያለበት ላንቃቸውም  ዝም እያለ ነው የሚሄደው ያሉ ሲሆን ፣ በሕክምና ሲረጋገጥም "ዲጂታል ኦቲዝም" ሆኖባቸው የተገኙ የብዙ ህፃናት ቁጥር በአዲስ አበባም ሆነ በክልል ከተሞች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍም ትልቁ ሥራ ወላጆች ላይ እንደሚጣልና በተለይም ህፃናት ትምህርት ቤት ከመግባታቸው በፊት ባለው ከ1 እስከ 4 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10😢4👍3💯3🙊1
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኢራን "ጊዜው እያለቀ ነው" ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ

በመካከለኛው ምስራቅ ባለው የጂኦፖለቲካ ውጥረት ተከትሎ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ለዋጋው መጨመር የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጦርነቱን ለማቆም የሚደረገው ድርድር በመቀዝቀዙ ለኢራን "ጊዜው እያለቀ ነው" ሲሉ ማስጠንቀቃቸው በምክንያትነት ተጠቅሷል።
የዓለምን 20 በመቶ የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ትራንስፖርት የሚያስተናግደው የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት፣ በአቡ ዳቢ የሚገኘው የባራካ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ አቅራቢያ በተሰነዘረ የድሮን ጥቃ እሳት መነሳ ምክንያት በነዳጅ አቅርቦት ላይ ስጋት መፍጠሩን ቢቢሲ ዘግቧል።

በዛሬው ዕለት ብሬንት የተሰኘው ድፍድፍ ነዳጅ በ1.7 በመቶ በመጨመር አንድ በርሜል በ111.13 ዶላር ደርሷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11😢6👍3
“ግብፅ በግብርና ምርት ራሷን መቻል እንደማትችል ልታውቁ ይገባል” - ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ

የግብጹ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ግብፅ በግብርና ምርት ሙሉ በሙሉ ራስን የመቻል ግብ ላይ መድረስ እንደማትችል በይፋ አስታወቁ።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን የተናገሩት፣ በአባይ ውሃ ከለማ በኋላ ተርፎ ወደ ሜዲቴራኒያን ባህር የሚቀላቀለውን የግብርና ፍሳሽ ውሃ በማጣራትና ወደ በረሃማ ቦታዎች በመግፋት ለድጋሚ ጥቅም ለማዋል የታለመ ግዙፍ ፕሮጀክት በምርቃት ወቅት ባደረጉት ንግግር ነው።

የ16 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ ፕሮጀክት ግብፅ በአሮጌው የአባይ ሸለቆ ግብርና ላይ ውሎ ተርፎ ወደ ሜዲቴራኒያን ባህር የሚፈሰውን ውሃ፣ ባህሩ ውስጥ ከመቀላቀሉ በፊት በመጥለፍና በማጣራት ለበረሃማው "ጊዛ" ግብርና እንዲውል የሚያደርግ የ800 ቢሊዮን የግብፅ ፓውንድ (16 ቢሊዮን ዶላር) ፕሮጀክት በይፋ አስጀምራለች።

ይህ ፕሮጀክት በዝቅተኛ ቦታ ላይ የሚገኘውን ያገለገለ የግብርና ፍሳሽ ውሃ፣ እጅግ ግዙፍ በሆኑ የፓምፕ ጣቢያዎች በመታገዝ ወደ ከፍታማው በረሃ እንዲወጣ የሚያደርግ ነው።

ፕሮጀክቱ የተበከለውንና ጨዋማ የሆነውን ውሃ በዘመናዊ መንገድ በማጣራት ለግብርና ምርት ዝግጁ ያደርጋል።

ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በዚሁ መድረክ ባደረጉት ንግግር፣ ግብፅ ምንም ያህል ብትጥር በምግብ ዋስትና ራሷን መቻል እንደማትችል ለህዝባቸው በግልጽ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ሲናገሩ “በግብርና ምርት ሙሉ በሙሉ ራስን መቻል ይቻላል ብላችሁ እንዳታስቡ ፤ ቢያንስ እንደ ግብፅ ባሉ አገራት... ምንም ያህል ብንጥር ራስን ሙሉ በሙሉ መቻል ፈጽሞ የማይቻል ነገር ነው። እኛ የፈለግነውን ሁሉ ለማምረት የሚያስችል በቂ መሬትና ውሃ ስለሌለን ራሳችንን ሙሉ በሙሉ መቻል አንችልም” ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24🤷‍♂3👍2😢1
ዶናልድ ትራምፕ ያጋሯቸው ምስሎች‼️
📌የመጀመሪያው ምስል ኦርቢት ላይ ሆነው ቀይ በተን ተጭነው የኑክሌያር ቦንብ ጥቃት ሲፈፅሙ የሚያሳይ ሲሆን ይህንን ተከትሎ በኢራን ላይ የኑክሌያር ቦንብ ሊጠቀሙ ይሆን? የሚል ጥያቄ አስነስቷል።
📌ሁለተኛው ምስል ደግሞ ኢራንን ከሁሉም አቅጣጫ ጥቃት ሲዘነዝሩ የሚያሳይ ሲሆን ይህም በኢራን ላይ ጥቃት ሊክፈቱ እንዳሰቡ የሚያሳይ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16😢8👍5🤣3🥰1
የ500 ሚሊዮን ዶላር ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ሊካሄድ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንኩ ነገ ማክሰኞ ግንቦት 11 ቀን 2016 ዓ.ም 500 ሚሊዮን ዶላር ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ እንደሚካሄድ  ይፋ አድርጓል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍9
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንክ ሂሳብን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ማስተሳሰርን በተመለከተ ይህን ብሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሠረት ሂሳባቸውን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ያላስተሳሰሩ ደንበኞች የባንክ አገልግሎት ማግኘት አይችሉም። በመሆኑም ባንካችን ያዘጋጀውን የበይነ መረብ (Online) ማስተሳሰሪያ አማራጭ (https://cbefayda.cbe.com.et) በመጠቀም ወይም ወደሚቀርባችሁ የባንካችን ቅርንጫፍ በመሄድ  ሂሳባችሁን እንድታስተሳስሩ እንገልፃለን ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍2😁2👏1
የቀብር ዋጋ ጭማሪ‼️
የቀብር አገልግሎት የዋጋ ማሻሻያ የማሕበረሰቡን ጫና ለመቀነስ መሆኑን አዲስ አበባ መጅሊስ አስታወቀ‼️

​የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት (መጅሊስ) በጀናዛ ማረፊያ ቦታዎች ላይ ያደረገው የዋጋ ማሻሻያ ተገልጋዮችን ከተጨማሪ ወጪ ለመታደግ የተደረገ መሆኑን አስታወቀ።

​የምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሪያድ ጀማል እንደገለጹት፤ ቀደም ሲል የነበረው አሰራር ለብልሹ አሰራር የተጋለጠና ወጥነት የጎደለው ነበር። ይህንን ለመቅረፍ መጅሊሱ ባለፉት 9 ወራት ውስጥ ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የመሠረተ ልማትና የሸሪዓዊ አቀባበር ሥርዓት ማሻሻያ ሥራዎችን አከናውኗል።

​በአዲሱ ማሻሻያ መሠረት የሕፃናት ቀብር 2,000 ብር፣ የአዋቂ ደግሞ 4,000 ብር ሆኗል።ይህም ቀደም ሲል ተገልጋዮች ለብሎኬት ግዢ ያወጡት የነበረውን ከ2,200 እስከ 2,800 ብር ተጨማሪ ወጪ የሚያስቀር ሲሆን፣ ከአሁን በኋላ እስከ 28 የሚደርሰው የብሎኬት አቅርቦት በራሱ በመጅሊሱ የሚሸፈን ይሆናል።

​በበጎ ፈቃደኝነት የጀናዛ እጥበትና ሽኝት በሚያደርጉ ተቋማት ላይ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ እንዳልተደረገባቸውና ምክር ቤቱ አሰራሩን ለማዘመን የተለያዩ መመሪያዎችን አጽድቆ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21😁17👍5🙊3
መረጃ‼️

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ፣ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ደኅንነት እንዲያስጠብቅ ጠየቁ።

ጌዲዮን ይህን ጥያቄ ያቀረቡት፣ ዛሬ ከሳዑዲ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋሊድ ኤልክረጂ ጋር በተወያዩበት ወቅት መሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባሠራጨው መረጃ ገልጧል።

ጌዲዮን፣ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ለኢትዮጵያዊያን ሠራተኞች ሕጋዊ የሥራ እድሎችን እንዲያመቻችም መጠየቃቸውን ሚንስቴሩ ጠቅሷል።

ሚንስትር ዋሊድ፣ ሕጋዊ የሠራተኞች ፍልሠት ኢትዮጵያዊያን ደኅንነቱ የተጠበቀ የሥራ ቅጥር እድል እንዲያገኙ ለማስቻል አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ተብሏል።

የሳዑዲ ዓረቢያ ፍርድ ቤት ከአደንዛዥ እጽ ዝውውር ጋር በተያያዘ የሞት ቅጣት የጣለባቸው በርካታ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ በውይይቱ ወቅት ይነሳ አይነሳ መረጃው አላመለከትም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍6😡1
“ጥቃቱን ለጊዜው ትቼዋለሁ”ትራምፕ

። ። ። ። ። : : : : : : : : : :
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ ሊፈፅሙት የነበረውን ጥቃት ማራዘማቸውን አሳውቀዋል።

የባህረ ሰላጤው አገራት ሳውዲ አረቢያ፣ኳታርና አረብ ኤሚሬቶች እንዲሁም ሌሎች አገራት ኢራን ላይ ጥቃት እንዳይሰነዝር ጠይቀውኛል ብለዋል ትራምፕ።

ለማክሰኞ ቀን ተቆርጦለት የነበረው ጥቃት ለዲፕሎማሲ ጊዜ መግዣ በሚል ለአሁኑ ቆሟል።

በዕርግጥ ጥቃቱ ለሁለት እና ሶስት ቀናት ያህል እንደተራዘመ መነገሩ ያን ያህል ዘላቂ ሰላም ላያመጣ ይችላል።

ፔንታጎን ቢያንስ ለአሁኑ እርምጃ እንዳይወስድ በትራምፕ ታዟል።

ትራምፕ ኢራን ጋር ያለው ውይይት በጎ ባለመሆኑ ነገ ወደ ጥቃቱ እንመለሳለን በሚልም ዝተዋል።

የትኛውም ስምምነት ቴህራን ኑክሌር ቦምብ እንዳትታጠቅ ማድረግ አለበት የሪፐብሊካኑ ዕምነት ነው።

ፕሬዚዳንቱ በትሩዝ ሶሻል ሚዲያቸው ላይ ተቀባይነት የሌለው ሀሳብ ኢራን የምተቀርብ ከሆነ የጦር ሚኒስቴሩ(ፔንታጎን) ወደ ጥቃት ለመመለስ በተጠንቀ ቅ ላይ እንዲቆይም አዘዋል።

ትራምፕ ማክሰኞ የያዙትን ጥቃት አራዘሙ እንጂ ኢራን ላይ መጠነ ሰፊ  ጥቃት ለማድረስ አሁንም ተዘጋጅተዋል ተብሏል።

ኢራን የመደራደሪያ ነጥቧን በፓኪስታን በኩል ለአሜሪካ መላኳም የሚዘነጋ አይደለም።

ዘገባው የአር ቲ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12🥱11🤣6👍2🥰2🤯2👏1😢1
የኢራን ፓርላማ የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ለሚገድል ማንኛውም ሰው 50 ሚሊዮን ዩሮ (ወደ 58 ሚሊዮን ዶላር ገደማ) የመንግስት የገንዘብ ሽልማት የሚሰጥ አዲስ የህግ ረቂቅ እያዘጋጀ መሆኑ ታወቀ

ይህ በኢራን ከፍተኛ ህግ አውጪዎች ደረጃ እየተመከረበት ያለው አዲስ የህግ ረቂቅ “የእስላማዊቷ ሪፐብሊክ ወታደራዊ እና የደህንነት ሃይሎች የአረባዊ እርምጃ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፥ መንግስት ለግድያው የተመደበውን ከፍተኛ የገንዘብ መጠን በይፋ እንዲከፍል የሚያስገድድ ነው።

የኢራን ፓርላማ የብሔራዊ ደህንነት እና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኢብራሂም አዚዚ በሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው እንደተናገሩት፥ ይህ እርምጃ አሜሪካ እና እስራኤል የኢራን ወታደራዊ መሪዎችን እና አዛዦችን ለገደሉበት አጸፋዊ ምላሽ የተዘጋጀ ነው።

አዚዚ አክለውም ዶናልድ ትራምፕ፣ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የአሜሪካ መካከለኛው ዕዝ (CENTCOM) ዋና አዛዥ በዋናነት መገደል እንዳለባቸው ገልጸው፥ ይህንን የግድያ እርምጃ “ሃይማኖታዊ እና ርዕዮተ-ዓለማዊ ተልዕኮ” ሲሉ ጠርተውታል።

ከዚህ መግለጫ አስቀድሞ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በርካታ የኢራን የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች የትራምፕን ግድያ ዘመቻ የሚደግፉ እና ለዚሁ ተግባር የሚውል የገንዘብ ማሰባሰቢያ ጥሪዎችን የያዙ የጽሑፍ መልዕክቶች ደርሷቸው እንደነበር ተገልጿል።

በተያያዘም በቅርቡ ይፋ የሆኑ የአሜሪካ የስለላ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከኢራን ጋር ግንኙነት አለው የተባለ አንድ ተላላኪ ግለሰብ ትራምፕን ለመግደል በቅድሚያ 5 ሺህ ዶላር ተከፍሎት ሲንቀሳቀስ እንደነበር ተደርሶበታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣2014👍4👏2😢1😎1
በሱሉልታ የእገታ ወንጀል ሲፈጽሙ የነበሩ አራት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ
 
አዲሱ ነጋሽ ፣ደሮ ተሾመ፣ ደጀኔ  ተስፋና ቶላ አለሙ የተባሉ አራት ወጣቶች ነዋሪነታቸው በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ ኑኑ ሳዩ ቀበሌ ነው።ወጣቶቹ በአካባቢያቸው የሚታወቁት የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ሲሆን በመዝናኛ ስፍራም ሆነ በተለያዩ ቦታውች የማይነጣጠሉ ጓደኛማቾች መሆናቸዉን የወረዳዉ ፖሊስ ፅህፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ሙሉ ጉደታ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ከቅርብ ግዜያት ወዲህ ግን የተለየና የተለወጠ እንቅስቃሴ በአካባቢው ያሣዩ እንደነበረም ይገልፃሉ።
 
ወጣቶቹ በአካባቢው ማሕበረሠብ ውስጥ ትዝብት ውስጥ ወድቀው ባሉበት ወቅት ጥር 5 ቀን 2017 ዓም ምሽት አልጌ ሠዮ በተባለ ስፍራ ያልተፈቀደ የጦር መሠርያ በመታጠቅ በአካባቢው ነዋሪ የሆኑት አራት ግለሠቦች አግተው በመውሰድ ከአንድ መቶ እስከ ሑለት መቶ ሺሕ ብር ድረስ ቤተሠቦቻቸው እንዲያመጡ በማስገደድ ቆይተዋል። ከጥቅምት 21 እስከ ጥር 5 ቀን 2017 ዓም ድረስ በዚሑ አካባቢ ለአራት ወራት የእገታ ወንጀል ሲፈፅሙ በመቆየት ገንዘብ ቤተሠቦቻቸውን ጠይቀው የሰጡትን ሲለቁ መክፍል አንችልም ያሉት ደግሞ ልጆቻቸውን ጭምር በማገት ተደራራቢ ወንጀል ሲፈፅሙ እንደነበረ በማስረጃ ተረጋግጧል፡፡
 
ወጣቶቹ አንድ ግለሠብን አግተው በመውሠድ ለወራት ባዘጋጁት ስፍራ በማስቀመጥ ካቆዩት በኃላ 200 ሺ ብር እንዲያመጣ ጠይቀውት የለኝም በማለቱ ፣ እሱን በመልቀቅ በእርሱ ፋንታ ልጁን አግተው በመውሰድ 300 ሺሕ ብር ተቀብለዋል፡፡የተቋቋመው የፀጥታ ግብረ ኃይል ሙሉ መረጃ ከደረሰዉ በኃላ ባደረገዉ ክትትል አራቱንም በቁጥጥር ስር አዉሏል፡፡ፖሊስም አስፈላጊ ማጣራት ካደረገ በኃላ የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ ለአቃቢ ሕግ ይልካል። አቃቢ ሕግም ስድስት ክሶችን መስርቷል፡፡
 
ክሱን የተመለከተው የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራቱ ተከሳሾች በሰላማዊ ሠው መሐል ገብተው ሕገወጥ የጦር መሣርያ ታጥቀው ጨለማን ተገን በማድረግ ከፍተኛ የውብድና ተግባር በመፈፀማቸው ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓም በዋለው ችሎት እያንዳዳቸው በአስራ ስምንት አመት እስራት እንዲቀጡ የወሠነባቸው መሆኑን ረዳት ኢንስፔክተር ሙሉ ጉደታ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
 
Via : dagu

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍3🤯2😢2
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመስጠት 667 የፈተና ማዕከላት ተዘጋጁ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በ667 የፈተና ማዕከላት ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ገለፀ።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለፋና እንደገለጹት÷ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን በ97 ዩኒቨርሲቲዎች እና በ570 የክልል ማዕከላት ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚሰጠው ፈተና መደበኛ ተማሪዎችን ጨምሮ በሁሉም ፕሮግራሞች በተፈጥሮ ሳይንስ 306 ሺህ 964 እንዲሁም በማህበራዊ ሳይንስ 257 ሺህ 255 በድምሩ 564 ሺህ 219 ተማሪዎች መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡

ፈተናውን በሙሉ አቅም በበይነ መረብ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ÷ በተለያዩ ምክንያቶች ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ በወረቀት የሚፈተኑ ተማሪዎች እንደሚኖሩም ጠቁመዋል።

ከባለፈው አርብ ጀምሮ ለተፈታኞች የበይነ መረብ የሙከራ ፈተና መሰጠት መጀመሩንም አንስተዋል።

ፈተናው በ6 ዙር እንደሚሰጥና በማህበራዊ ሳይንስ በሶስት ዙር በተመሳሳይ በተፈጥሮ ሳይንስ ደግሞ በሶስት ዙር በመሆኑ አንድ ኮምፒዩተር ስድስት ተማሪን ያስተናግዳል ነው ሉት።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7😁6👍2
ቡና ለገበያ አውጡ‼️
በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ምክንያት የቡና ዋጋ ስለማይጨምር፣ አምራችና ነጋዴዎች ምርታቸውን ለገበያ ማቅረብ እንዳለባቸው ተገለጸ‼️

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበለ የመካከለኛው ምስራቅን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ሀገራት በሚቀሰቀሱ ግጭቶች ምክንያት የቡና ዋጋ ሊጨምር ይችላል በሚል የተሳሳተ መረጃ ነጋዴዎች ኪሳራ ውስጥ እንዳይገቡ አሳስበዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና ምርቷ በስፋት የምትታወቀው ብራዚል ከሰኔ ወር ጀምሮ 78 ሚሊዮን ኩንታል የሚጠጋ ምርት ለገበያ ስለምታቀርብ፣ የሀገራችን አምራችና ነጋዴዎች ከዛ አስቀድመው ገበያ ላይ ቢያወጡት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ የቡና ዋጋ በቶን 30 በመቶ ያህል መቀነሱን የገለጹት ዶክተር አዱኛ፤ ምንም እንኳን ለሀገራችን ጉዳት ሆኖ የሚታይ ባይሆንም የቬትናምና የብራዚል ቡና ወደ ገበያ ከገባ ከዚህ በታች ሊወርድ ስለሚችል ምርቱን ባለው ገበያ ማቅረብ ይገባል ብለዋል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ ቬትናምና ብራዚል በዚህ ዓመት ከፍተኛ የቡና ምርት ማምረታቸው፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊከማች ይችላል ተብሎ ከተገመተው 8 ሚሊዮን ቶን በላይ የቡና ምርት እንዲኖር እንደሚያደርግና ይህም ለዋጋው መቀነስ አንዱ ምክንያት እንደሆነ ገልፀዋል።

የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ በማጓጓዣው ዘርፍ ላይ ተፅዕኖ ስለሚያሳድር በገበያው ላይ ተግዳሮት ቢፈጥርም፣ በቡና ዋጋ ላይ ግን ለውጥ እንደማይኖር ነው የተናገሩት።

የኢትዮጵያ የቡና ምርት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በዋጋም በገበያም የተሻለ እንደሆነና እስካሁንም ከደረጃ 4 በላይ የሆኑ የቡና ዓይነቶችን ብቻ ለዓለም አቀፉ ገበያ በማቅረብ ታዋቂነትንና የገበያ ትስስርን የመፍጠር ሂደቱ ውጤታማ እንዳደረገው ተናግረዋል።

በዘንድሮው የቡና ሽያጭም ኢትዮጵያ 320 ሺህ ሜትሪክ ቶን ቡና ወደ ውጭ ገበያ የላከች ሲሆን፣ ከዚህም 2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደተገኘ አመልክተዋል።

የቡና አምራችና ነጋዴዎች በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ምክንያት የቡና ዋጋ ይጨምራል በሚል ቡና ማከማቸት እንደሌለባቸውና ምርታቸውን ባለው ገበያ መሸጥ እንዳለባቸው ተመላክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍4
⚡️ እስራኤል በጋዛ፣ ሊባኖስ እና ሶሪያ 1,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ገደማ መሬት መቆጣጠሯ ተገለጠ!

​የፋይናንሻል ታይምስ ባደረገው አዲስ ትንተና መሠረት፣ ከጥቅምት 7 ጥቃት በኋላ እስራኤል በጋዛ፣ በሊባኖስ እና በሶሪያ በድምሩ የሀገሪቱን የ1949 ድንበር 5% የሚያክል (1,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር) መሬት በቁጥጥሯ ሥር አውላለች።

በደቡብ ሊባኖስ፦ ከተያዘው መሬት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው እዚህ የሚገኝ ሲሆን፣ እስራኤል ሄዝቦላህን ወደ ኋላ ለመግፋት በሚል እስከ 12 ኪሎ ሜትር ዘልቃ በመግባት “የደህንነት ቀጠና” ፈጥራለች። ሙሉ መንደሮች የወደሙ ሲሆን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ሁኔታውን “ከጋዛው ሞዴል” ጋር አነጻጽረውታል።

በጋዛ ሰርጥ፦ የእስራኤል ጦር በአሁኑ ወቅት ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የጋዛ ግዛት የተቆጣጠረ ሲሆን፣ ተጨማሪ የደህንነት ቀጠናዎችን በመፍጠሩ ምክንያት የጋዛ ህዝብ ከጦርነቱ በፊት ከነበረው ይዞታው 40% በሚሆነው ጠባብ መሬት ላይ ተጨናንቆ እንዲኖር ተገዷል።

በሶሪያ፦ እስራኤል ከኮረብታማው የሄርሞን ተራራ  በስተደቡብ ያለውን የድንበር አካባቢ ወደ 233 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚጠጋ መሬት ተቆጣጥራለች።

ኔታንያሁ ጦራቸው ከሊባኖስ “አይወጣም” ማለታቸውን ተከትሎ፣ እንዲሁም የእስራኤል ቀኝ አክራሪ ሚኒስትሮች በቦታው ላይ አዳዲስ ሰፈራዎች እንዲመሰረቱና “ሊታኒ ወንዝ” አዲሱ ድንበር እንዲሆን መጠየቃቸው፣ ይዞታው ቋሚ ሊሆን ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት በጎረቤት ሀገራት ላይ ፈጥሯል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😡107👍6
የአዋሽ-ኮምቦልቻ-ሐራ ገበያ የባቡር መስመር ግንባታ ከዓመታት መቋረጥ በኋላ ዳግም ተጀመረ!

በአዋሽ-ኮምቦልቻ-ሐራ ገበያ መስመር ላይ ተቋርጦ የነበረው የ1.7 ቢሊዮን ዶላር የባቡር መስመር ግንባታ፣ ከዓመታት መዘግየት በኋላ በይፋ ዳግም መጀመሩ ተገለጸ።

ይህ 392 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የኤሌክትሪክ ባቡር መስመር፣ የአማራ ክልል ዋና ዋና የንግድና የኢንዱስትሪ ማዕከላትን ከአዲስ አበባ-ጂቡቲ የባቡር ኮሪደር ጋር የሚያገናኝ በመሆኑ ለሀገሪቱ የጭነትና የሰው ትራንስፖርት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።

ግንባታው በ2015 እ.ኤ.አ. በቱርኩ "ያፒ መርከዚ" ኩባንያ የተጀመረ ቢሆንም፣ በኖቬምበር 2020 በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ምክንያት መሠረተ ልማቶቹ ላይ ጉዳት ደርሶና ውሎች ተስተጓጉለው ሥራው ቆሞ ቆይቷል።

በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ያለው የጸጥታ ሁኔታ በመሻሻሉ ሠራተኞችና መሣሪያዎች ወደ ሳይት የተመለሱ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ባቡር ኮርፖሬሽን የጥገና እና መልሶ ግንባታ ሥራው በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍4🤣4
ደረሰኝ ሳይሰጡ ሽያጭ የፈፀሙ ግብር ከፋዩች ቅጣትን ከ50 ሺህ ብር ወደ 100 ሺህ ብር ከፍ እንዲል የሚያደርግ የታክስ አስተዳደር የማሻሻያ አዋጅ ተዘጋጀ 

በዛሬዉ እለት ለ10 አመት ሲሰራበት የቆየዉን የታክስ አስተዳደር አዋጅ ማሻሻያ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት እና ባለሙያዎች ጋር የግብአት መሰባሰብ ዉይይት አድርጓል።

በዚህ የማሻሻያ ረቂቅ ዉስጥ ተሻሽለው ከቀረቡ ነጥቦች መካከል ደረሰኝ ሳይሰጡ ሽያጭ የሚፈፅሙ ግብር ከፋዩች ላይ ከዚህ ቀደም ቅጣት ተብሎ ተቀምጦ የነበረዉን የገንዘብ ቅጣት ከፍ ያደረገ ህግ ተቀምጦበታል።

በዚህም 50 ሺህ ብር ቅጣትን ያስቀምጥ የነበረዉን በማሻሻል የ100 ሺህ ብር ቅጣት የሚጥል አዲስ ህግ በረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ላይ ተቀምጧል።

ይህም በእያንዳንዱ  ደረሰኝ የደረሰኙ ዋጋ ከግምት ዉስጥም የማይገባ ነዉ ተብሏል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ የህግ አማካሪዉ አቶ ዋሲሁን አባተ እንደገለፁት "የተቀመጠዉ ገንዘቡ መጠን  በግብር ከፋዩ ዘንድ እንደ አንድ ወጪ ታሳቢ እየተደረገ  መጥቷል፤  ይህ ደግሞ ህገወጥነቱን እየጨመረ እንዲመጣ እያደረገ መጥቷል ብለዋል"።

ለዚህም ማሻሻያ እንዲደረግበት ሆኖ መቀመጡን ለዉይይቱ ተሳታፊዎች አስረድተዋል ።

በዚህ ሽያጭ ደረሰኝ ሳይሰጡ ሽያጭ በሚፈፅሙ ግብር ከፋይ በዚህ ድርጊት ከሁለት ጊዜ በላይ ከተገኙ ግን ወደ እስር የሚወስድ  አስተዳደራዊ ቅጣት  እንደሚኖር አያይዘዉ ገልፀዋል።

ቁምነገር አየለ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10😡7👍3
የዶላር ዋጋ ወደ 159.98 ብር ከፍ አለ፤ ብሔራዊ ባንክ ካቀረበው የውጭ ምንዛሬ ከእጥፍ በላይ ፍላጎት ቀረበበት
አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ፣ የዶላር አማካይ የማሸነፊያ ዋጋ 159.98 ብር መድረሱን ይፋ አደረገ።

ባንኩ ይፋ ባደረገው መግለጫ መሠረት፣ በገበያው ውስጥ አሁንም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት መኖሩን የሚያሳዩ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

ብሔራዊ ባንኩ ለዚህ ልዩ ጨረታ 500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያቀረበ ቢሆንም፣ ከንግድ ባንኮች በኩል የቀረበው አጠቃላይ የፍላጎት መጠን ግን ከቀረበው አቅርቦት በእጥፍ በመጨመር 1.06 ቢሊዮን (አንድ ቢሊዮን ከስድሳ ሚሊዮን) ዶላር ሆኖ ተመዝግቧል።

በጨረታው ላይ በአጠቃላይ 30 የንግድ ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 14ቱ ባንኮች ብቻ ጨረታውን አሸንፈው የውጭ ምንዛሬውን ማግኘት ችለዋል።

የዕለቱ የምንዛሬ ተመን ዝርዝር፦

1. የማሸነፊያ አማካይ ክብደት ዋጋ (Weighted Average Rate): 159.9865 ብር

2. የመቁረጫ ዋጋ (Marginal/Cut-off Rate): 159.6299 ብር

3. ከፍተኛው የቀረበ የማሸነፊያ ዋጋ:160.9064 ብር

4. ዝቅተኛው የቀረበ የማሸነፊያ ዋጋ:157.3005 ብር

ብሔራዊ ባንክ ከሁለት ወራት በፊት ባካሄደው ተመሳሳይ ጨረታ 70 ሚሊዮን ዶላር አቅርቦ የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱ የአንድ ዶላር አማካይ ዋጋ 157 ብር ከ46 ሳንቲም ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20😢5😱4👍3
ትራምፕ ሌላ ጦርነት ሊጀምሩ ነው‼️
ትራምፕ በኩባ ላይ ጦርነት ለመጀመር እያሰቡ መሆኑን ፖለቲኮ ዘግቧል።
"ትራምፕ እና አማካሪዎቹ በኩባ ላይ እየተደረገ ያለው ጫና ባለመስራቱ እንደተበሳጩ እና ወታደራዊ አማራጭን ለመጠቀም እያጤኑ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል። አሜሪካ ጦርነት ከጀመረች ኩባ እፋለማለሁ ብላለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17😢5🙉3👍2🤷‍♂1😈1👀1
በኦሮሚያ ክልል ታጣቂዎች በሕዝብ አውቶብስ ላይ ተኩስ በመክፈት ተሳፋሪዎችን አገቱ

በኦሮሚያ ክልል ከገብረ ጉራቻ ወደ ፍቼ በሚወስደው መንገድ አሊደሮ በተባለ አካባቢ ታጣቂዎች ሕዝብ ጭኖ እየተጓዘ በነበረ ልዩ የሕዝብ አውቶብስ ላይ ተኩስ በመክፈትና ተሽከርካሪውን አስገድደው በማስቆም ከሦስት ሰዎች በቀር ሁሉንም ተሳፋሪዎች አፍነው መውሰዳቸውን የካቢኔ ሹፌሮች ገለጹ።

የአውቶብሱን መስታወትና ጎማዎች በመምታት የተፈጸመውን ይህንን ጥቃት ተከትሎ፣ አካባቢው ለዓመታት የታጠቁ ወንበዴዎች እገታ፣ ዘረፋና ግድያ የሚፈጽሙበት ቢሆንም በጉዳቱ ግዝፈት ልክ ትኩረት እንዳልተሰጠው የተጠቆመ ሲሆን፤ የሕግ አስከባሪዎች ተሳፋሪዎችን ለማዳን ሕይወታቸውን ጭምር እየከፈሉ መሆኑ ቢመሰገንም፣ የአፈና ወንጀሉን ከስር መሰረት ለመንቀልና ሾፌሮችን፣ ረዳቶችንና ተሳፋሪዎችን ከአደጋ ለመጠበቅ የአሠራር ግምገማ በማድረግ አዳዲስ ስልቶችን መከተልና በቂ ጥበቃ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢1614💔12👍4
መረጃ‼️

የኦሮሚያ ክልል የጸጥታና አሥተዳድር ቢሮ፣ የመንግሥትን የሠላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ማኅበረሰቡ የተቀላቀሉ የቀድሞ የ"ሸኔ" ታጣቂዎችንና ቤተሰቦቻቸውን ቡድኑ እየገደለ፣ አፍኖ እየወሠደና ቤታቸውን እያቃጠለ ይገኛል ሲል ከሠሠ።

በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች አርሶ አደሮችን የመዝረፍ፣ ሰዎችን አግቶ የማስለቀቂያ ገንዘብ የመጠየቅና ባለሀብቶችን በማስፈራራት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ የመቀበል ወንጀሎችን የሚፈጽሙት የ"ሸኔ" ታጣቂዎች ናቸው ሲል የከሠሠው ቢሮው፣ ታጣቂዎቹ ከሻዕቢያ፣ ከሕወሃትና ሌሎች ጠላቶች ተልእኮ የሚቀበሉ ናቸው በማለት ጭምር ወንጅሏል።

ጥቂቶቹ ታጣቂዎች "ከተራ ዝርፊያ" ያለፈ ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ዓላማ እንደሌላቸው የቢሮው ኃላፊ ኮሚሽነር ጄነራል አራርሳ መርዳሳ መናገራቸውን ቢሮው በይፋዊ ማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሠራጨው መረጃ ገልጿል።

ኮሚሽነር ጄነራል አራርሳ፣ የመንግሥትን የሠላም ጥሪ በማይቀበሉ ታጣቂዎች ላይ የጸጥታ ኃይሎች አስፈላጊውን ርምጃ ይወስዳሉ ማለታቸውንም ከቢሮው መረጃ ላይ ተመልክተናል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪107👍42🙉2👏1😁1😢1