አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ሩሲያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች‼️

የዩክሬን ድሮኖች በራይዛን የነዳጅ ማጣሪያ ላይ በፈጸሙት ጥቃት ከፍተኛ ውድመት መድረሱንና ስትራቴጂካዊ በሆኑ ቀጠናዎች ላይ የእሳት አደጋ መከሰቱን ተከትሎ፣ የሩሲያ ባለሥልጣናት በአንዱ ተጎጂ ከተማ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል።

በተመሳሳይ ወቅት ሞስኮ በዩክሬን ይዞታዎች ላይ አዳዲስ ጥቃቶችን የሰነዘረች ሲሆን፣ ሁለቱም ወገኖች ከጠላት የጦር ግንባር በስተጀርባ ባሉ ጥልቅ ይዞታዎች ላይ ረጅም ርቀት በሚጓዙ ድሮኖችና ትክክለኛ ኢላማቸውን በሚመቱ ጥቃቶች ላይ ይበልጥ መተማመናቸውን ተከትሎ በተለያዩ ግንባሮች ላይ ያለው ጫና በርትቷል።

እየተባባሰ የመጣው የጥቃት ማዕበል ግጭቱ መሠረተ ልማትን ወደ ማውደም ሰፊ ጦርነት እየተቀየረ መምጣቱን የሚያመለክት ሲሆን፣ ሁለቱም አገራት የሎጂስቲክስ፣ የነዳጅ ማጠራቀሚያዎች፣ የአየር መከላከያ ሥርዓቶች እና የወታደራዊ አቅርቦት መረቦችን መዳረሻ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍4🤔2
የሰራተኛ ችግር አለ-ጠቅላይ ሚኒስትሩ‼️
''ኢትዮጵያ ውስጥ የስራ ሳይሆን የሰራተኛ ችግር ነው ያለው ስራ በየቦታው አለ።  የውጭ ሀገር ዜጎችን እየተጠቀምን ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ''

በትናንትናው ዕለት በገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ ውስጥ ሰራተኛ ማግኘት ከባድ ነገር ሆኗል።  ወጣቱ ስራ እያለ መስራት አልቻለም ሲሉ ወቅሰዋል።  በየቦታው በምንሰራው ስራ ላይ እንቅፋት እየሆነ የመጣው የጉልበት ሰራተኛ ችግር ነው በማለት አብራርተዋል።

ኢትዮጲያ ውስጥ የስራ ሳይሆን የሰራተኛ ችግር ነው ያለው፤ሌላው ቀርቶ የቤት ሰራተኛ እንኳን ማግኘት ችግር ነው ያሉ ሲሆን ይህን ችግር ለመግረፍ የውጭ ዜጎችን ለመጠቀም ተገደናል በማለት'' ለምሳሌ ያክል የቻይና፣ ፊሊፒንስ፣ ኬኒያና ናይጀሪያ ዜጎችን በስፋት እያሳተፍን ነው ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣90🙉2811🤔8👍6👀3😡3🤪2🥰1😁1🙊1
በዶ/ር ደብረጽዮን የሚመራው የትግራይ ክልል አስተዳደር የግንቦትና ሰኔ ወራት ደመወዝ እንዳይከፈል አገደ"

በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት፣ የክልሉ የመንግስት ሰራተኞች የግንቦት እና የሰኔ ወር ደመወዝ ለጊዜው እንዳይከፈል ማገዱ ታወቀ።

አስተዳደሩ ለዚህ ውሳኔ እንደ ምክንያት የጠቀሰው፤ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች ያለው የደመወዝ አከፋፈል ወጥነት የሌለው፣ ኢ-ፍትሃዊ እና ግልጽነት የጎደለው ሆኖ በመገኘቱ ነው።

በመሆኑም ፍትሃዊነትን የሚያረጋግጥና "የተማከለ የአከፋፈል መመሪያ" ተዘጋጅቶ ስራ ላይ እስኪውል ድረስ፣ ማንኛውም መሥሪያ ቤት በራሱ ፍላጎት ደመወዝ እንዳይከፍል በደብዳቤ አሳስቧል።

በትግራይ ክልል ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ ከፌዴራል መንግስት የሚላከው የበጀት ድጎማ በገንዘብ ሚኒስቴር ትዕዛዝ ተቋርጦ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን አስተዳደሩ በዚህ ደብዳቤው ላይ የፌዴራል መንግስት በጀትን በመከልከሉና በፈጠረው ጫና ምክንያት ሰራተኞች ደመወዛቸውን በወቅቱ ለማግኘት መቸገራቸውን በድጋሚ ጠቁሟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍6🤔4🙊3😁2😢2🤯1
#MoE‼️
የዩኒቨርሲቲዎች የአመራር ምደባ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚወጣ ማስታወቂያ በውድድር እንደሚሆን መንግሥት ገለፀ።

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የአመራር ምደባ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚወጣ ማስታወቂያ እውቀት እና ችሎታ መሠረት ባደረገ ውድድር እንዲሆን እየተሠራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ አባላት ጋር ሰሞኑን ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

"ዩኒቨርሲቲዎች በዘር የሚሰባሰቡበት (ቦታ) ሳይሆን በእውቀት፣ በችሎታ እና በውድድር ሰዎች የሚገቡባቸው ከልብ የማሰቢያ፣ የመወያያ እና ጥናትና ምርምር የሚደረግባቸው ተቋማት እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል" ሲሉ ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች ከምንም ዓይነት ፖለቲካ ተፅዕኖ ነጻ መሆን አለባቸው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ዩኒቨርሲቲዎች በነፃነት ለማሰብ እና ለመናገር ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ ተቋማት መሆን አለባቸው ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17👍9👏2🤪2😡1
የዒድ አል-አድሃ (የአረፋ) በዓል የሚውልበትን ቀንq ዛሬ ማታ ይወሰናል።

የታላቁን የዒድ አል-አድሃ (የአረፋ) በዓል የሚውልበትን ትክክለኛ ቀን ለመወሰን፣ የዙል ሂጃህን ወር መግቢያ ጨረቃ ዛሬ ማታ ይከታተላሉ።

እንደ ዘገባዎች መግለጫ፡

* የጨረቃዋ መታየት ዛሬ ማታ ከተረጋገጠ፣ ታላቁ የዒድ በዓል ረቡዕ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም (May 27, 2026) ይጀምራል።

* ጨረቃዋ ዛሬ ማታ ካልታየች ደግሞ፣ በዓሉ ሐሙስ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም (May 28, 2026) ላይ የሚውል ይሆናል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
34😁4👍3
እነ ጌታቸው ረዳ ትግራይን ለመቆጣጠር ምክር ቤት መሠረቱ !!

በህወሓት ጫና ከትግራይ የሸሹ የፖለቲካ ኃይሎች፣ ክልሉን መልሶ ለመቆጣጠር ያስችለናል ያሉትን ምክር ቤት ዛሬ በአዲስ አበባ መሥርተዋል።

እንደ ጌታቸው ረዳ እና ጀነራል ጻድቃን ገብረተንሳይ ያሉ የህወሓት ተቃዋሚዎች የመሰረቱት፣ "የትግራይ ሰላምና ለውጥ ምክር ቤት" የተሰኘ ተቋም ነው።  ምክር ቤቱ የተመሰረተው በአፋር ክልል የሚንቀሳቀሰውን ሓራ መሬት ወይይ የትግራይ ለውጥ ኃይል ታጢቂ ቡድን አዛዥ ጀኔራሎች አቅፎ መሆኑ ታውቋል።

በአዲስ አበባ ከተማ መመስረቱ የተነገረለት የለውጥ ኃይሎች ምክር ቤት፣ ህወሓት አስወግዶ ትግራይን ለመቆጣጠር የሚሠራ ነው ተብሏል።

በህወሓት ግፊት ከትግራይ የወጡት የፖለቲካ ኃይሎች እና አፋር ክልል የመሸገው ታጣቂ ቡድን በቀጣይ ስለሚኖራቸው የጋራ ትግል ሲመክሩ መሰንበቻውን ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23🤣22👍14👏2😎1
1447ኛው የዒድ አልአድሃ በዓል ረቡዕ ይውላል።

​ዛሬ በሳዑዲ አረቢያ ጨረቃ በመታየቷ የዙል-ሂጃ ወር መግባቱ ተገልጿል።

​ይህን ተከትሎ 1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (የዓረፋ) በዓል ዕሮብ ረቡዕ ግንቦት 19 ተከብሮ ይውላል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍6🤔1
የማስታወቂያ ግብዣ

የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል
Youtube ቻናል …
የትምህርት ተቋማት…...
የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
የትራንስፖርት አገልግሎት…....
ኤጀንሲዎች……
ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot
👍53
ጠሚ አብይ አዋጭ አይደለም ያሉት የባቡር ፕሮጀክት ግንባታ ዳግም ተጀመረ።

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ግንባታው ተቋርጦ የቆየው የአዋሽ - ኮምቦልቻ - መቀሌ የባቡር ፕሮጀክት ዳግም ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ። ፕሮጀክቱ ከመቋረጡ በፊት መጠነኛ የግንባታ ስራዎች ብቻ ቀርተውት የነበረ ቢሆንም ባለፉት ጊዜያት የሀዲድ ቁሳቁሶች ለስርቆትና ለብክነት ተጋልጠው ቆይተዋል። ፕሮጀክቱ ከቆመበት እንዲቀጥልም የህዝብ ተደጋጋሚ ጥያቄ ሲቀርብበት ቆይቷል። ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ በሰጡት ማብራሪያ ፕሮጀክቱ በ2.6 ቢሊዮን ዶላር ብድር የሚከናወን መሆኑን ጠቅሰው ከመቀሌ ኮምቦልቻ የሚመላለስ በቂ ምርት ባለመኖሩ ፕሮጀክቱ በኢኮኖሚ ረገድ አዋጭ እንዳልሆነና የወጣበትን ወጪ በ50 ዓመታት ውስጥ እንኳ መመለስ እንደማይችል መግለጻቸው ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ባለፉት ጥቂት ቀናት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በባቡር መስመሩ ላይ የደረሱ ጉዳቶችን ጠግነው ወደ ስራ የሚያስገቡ ሰራተኞችን ለመቅጠር የቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል። ዛሬ እሁድ ደግሞ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በፕሮጀክቱ ሳይት ላይ በመገኘት ግንባታውን ከቆመበት ለማስቀጠልና አጠናቆ ወደ አገልግሎት ለማስገባት ስራ መጀመሩን ገልጸዋል።

የአዋሽ - ኮምቦልቻ - ሀራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት አማራ፣ ትግራይ እና አፋር ክልሎችን ከጅቡቲና ከዓሳብ ወደቦች ጋር በማገናኘት ረገድ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ፋይዳ እንዳለው ይነገራል። ፕሮጀክቱን ሲያከናውን የነበረው የቱርክ ኩባንያ ከግንባታው መቋረጥ ጋር ተያይዞ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በህግ እየተካሰሰ በመሆኑ ቀሪው ስራ በሀገር ውስጥ ባለሙያዎችና ኩባንያዎች ብቻ እንደሚከናወን ታውቋል። የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሀሰን ሙሐመድ ግንባታውን ለማጠናቀቅ ስራ መጀመሩን አረጋግጠዋል።

@Addis_Reporter
34👍7😁5🤪4👏1🎉1🙏1👌1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሁለት የአሜሪካ የጦር ጄቶች በአየር ላይ ተጋጭተው ተከሰከሱ

​በአሜሪካ አይዳሆ ግዛት በሚገኘው የነፋስ ተራራ የባህር ኃይል ጣቢያ በተካሄደው የ"Gunfighter Skies" የአየር ትዕይንት ላይ፣ ሁለት የአሜሪካ ባህር ኃይል EA-18G Growler የጦር ጄቶች በአየር ላይ ተጋጭተው መከስከሳቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት እና የዐይን እማኞች ገልጸዋል።

​ ሁለቱ የኤሌክትሮኒክስ ውጊያ አውሮፕላኖች የአየር ላይ ትዕይንት እያሳዩ ባሉበት ወቅት የተጋጩ ሲሆን፣ ከጣቢያው በስተሰሜን ምዕራብ 2 ማይል ርቀት ላይ መከስከሳቸው ተረጋግጧል።ከአደጋው በኋላ በቪዲዮ ምስሎች ላይ 4 አብራሪዎች በአየር ላይ በፓራሹት አማካኝነት ከአውሮፕላኖቹ እራሳቸውን አውጥተው ሲወርዱ ታይተዋል።

​አደጋውን ተከትሎ የጦር ሰፈሩ በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በቦታው ላይ የማዳን ስራ እያከናወኑ ይገኛል። ስለ አብራሪዎቹ ወቅታዊ የጤና ሁኔታ ዝርዝር መረጃ አልወጣም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍6😢6🙏3🤣3
ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን በደቡባዊ የአገራቸው ድንበር መከላከያው እንዲጠናከር ትዕዛዝ ሰጡ።

ከሰሜን ኮሪያ የተለያዩ ዕዞች ከተውጣጡ ወታደራዊ ሀላፊዎች ጋር ስለዝግጁነት መክረዋል ኪም ጆንግ ኡን።

ከዕዝና ብርጌድ አዛዦች ጋር የተወያዩት ኪም በደቡባዊ የሰሜን ኮሪያ ክፍል ያለው ድንበር ላይ ዝግጅት እንዲደረግ ማሳሰባቸው ለደቡብ ኮሪያ ፖለቲከኞች አዲስ ወታደራዊ ስጋት ጋርጦባቸዋል ።

ሊቀሰቀስ የሚችልን ማንኛውንም ጦርነት ለመቀልበስ የጦሩን ትጥቅ ማዘመን፣ቁልፍ ዕዞችን ማጠናከር እና መሰል ዝግጅቶች እንዲደረጉም ጥሪ ቀርቧል።

በደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ መካከል ያለው ወታደራዊ ትስስር ስጋት የሆነባቸው ኪሞቹ በተለያየ ጊዜ የሚፈፀምብንን ወታደራዊ ትንኮሳ መመከት አለብን የሚል ዕምነት አላቸውም ተብሏል።

በፒዮንግያንግ እና ሴዑል መካከል ያለው ወታደራዊ ውጥረት መልኩን እየለወጠ መምጣቱን የሚጠቁም ትዕዛዝ ሆኖም ተመዝግቧል።

ኪም ጆንግ ኡን አዳዲስ የጦር መሳሪያ ስርዓቶች ወደ ውጊያ አውድ እንዲገቡ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ መስጠታቸውም አይዘነጋም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍6
በኢትዮጵያ የዲጂታል ኦቲዝም በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገለፀ

ልጆች ረጅም ሰዓት በስልክና በቪዲዮ ጌሞች ላይ ማሳለፋቸው፣ መናገር የሚችሉ ሆነው ከተወለዱ በኋላ አንደበታቸው እንዲያዝ እያደረገ መምጣቱ ተገልጿል።

ይህም በተፈጥሮ ከሚመጣ ኦቲዝም ባልተናነሰ ለዲጂታል ኦቲዝም እያጋለጣቸው መሆኑን ፍቅር ኢትዮጵያ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበር ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ  ሸዋጌጥ ክብረት ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅት ወላጆች ልጆቻቸው ሲያለቅሱ ወይም ሲያስቸግሩ ስልካቸውን ሰጥተው ዝም ማሰኘትን እንደ ዋነኛ አማራጭ መውሰዳቸው በትውልዱ ላይ ትልቅ አደጋ እየጋረጠ ይገኛልም ብለዋል።

ዲጂታል ኦቲዝም የሚባለው ስያሜ ልጆች ከስክሪን ጋር ረጅም ጊዜ በማጥፋታቸው ሳቢያ የሚፈጠር የተግባቦትና የማህበራዊ ግንኙነት ክፍተት መሆኑን ያስረዱት ወ/ሮ ሸዋጌጥ፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቷ ላይ እየተስተዋለ የመጣው የህፃናት ስልክ አጠቃቀም ጤነኛ ሆነው የተወለዱ ህፃናትን ሳይቀር መናገር አቅቷቸው ወደ ማህበራቸው እንዲመጡ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ስራ አስኪያጇ ልጆች ዝም ብለው ስልክ ላይ ጊዜ ካጠፉ አያወሩም፤ ቃላት ማውጣት ያለበት ላንቃቸውም  ዝም እያለ ነው የሚሄደው ያሉ ሲሆን ፣ በሕክምና ሲረጋገጥም "ዲጂታል ኦቲዝም" ሆኖባቸው የተገኙ የብዙ ህፃናት ቁጥር በአዲስ አበባም ሆነ በክልል ከተሞች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍም ትልቁ ሥራ ወላጆች ላይ እንደሚጣልና በተለይም ህፃናት ትምህርት ቤት ከመግባታቸው በፊት ባለው ከ1 እስከ 4 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10😢4👍3💯3🙊1
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኢራን "ጊዜው እያለቀ ነው" ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ

በመካከለኛው ምስራቅ ባለው የጂኦፖለቲካ ውጥረት ተከትሎ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ለዋጋው መጨመር የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጦርነቱን ለማቆም የሚደረገው ድርድር በመቀዝቀዙ ለኢራን "ጊዜው እያለቀ ነው" ሲሉ ማስጠንቀቃቸው በምክንያትነት ተጠቅሷል።
የዓለምን 20 በመቶ የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ትራንስፖርት የሚያስተናግደው የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት፣ በአቡ ዳቢ የሚገኘው የባራካ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ አቅራቢያ በተሰነዘረ የድሮን ጥቃ እሳት መነሳ ምክንያት በነዳጅ አቅርቦት ላይ ስጋት መፍጠሩን ቢቢሲ ዘግቧል።

በዛሬው ዕለት ብሬንት የተሰኘው ድፍድፍ ነዳጅ በ1.7 በመቶ በመጨመር አንድ በርሜል በ111.13 ዶላር ደርሷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11😢6👍3
“ግብፅ በግብርና ምርት ራሷን መቻል እንደማትችል ልታውቁ ይገባል” - ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ

የግብጹ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ግብፅ በግብርና ምርት ሙሉ በሙሉ ራስን የመቻል ግብ ላይ መድረስ እንደማትችል በይፋ አስታወቁ።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን የተናገሩት፣ በአባይ ውሃ ከለማ በኋላ ተርፎ ወደ ሜዲቴራኒያን ባህር የሚቀላቀለውን የግብርና ፍሳሽ ውሃ በማጣራትና ወደ በረሃማ ቦታዎች በመግፋት ለድጋሚ ጥቅም ለማዋል የታለመ ግዙፍ ፕሮጀክት በምርቃት ወቅት ባደረጉት ንግግር ነው።

የ16 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ ፕሮጀክት ግብፅ በአሮጌው የአባይ ሸለቆ ግብርና ላይ ውሎ ተርፎ ወደ ሜዲቴራኒያን ባህር የሚፈሰውን ውሃ፣ ባህሩ ውስጥ ከመቀላቀሉ በፊት በመጥለፍና በማጣራት ለበረሃማው "ጊዛ" ግብርና እንዲውል የሚያደርግ የ800 ቢሊዮን የግብፅ ፓውንድ (16 ቢሊዮን ዶላር) ፕሮጀክት በይፋ አስጀምራለች።

ይህ ፕሮጀክት በዝቅተኛ ቦታ ላይ የሚገኘውን ያገለገለ የግብርና ፍሳሽ ውሃ፣ እጅግ ግዙፍ በሆኑ የፓምፕ ጣቢያዎች በመታገዝ ወደ ከፍታማው በረሃ እንዲወጣ የሚያደርግ ነው።

ፕሮጀክቱ የተበከለውንና ጨዋማ የሆነውን ውሃ በዘመናዊ መንገድ በማጣራት ለግብርና ምርት ዝግጁ ያደርጋል።

ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በዚሁ መድረክ ባደረጉት ንግግር፣ ግብፅ ምንም ያህል ብትጥር በምግብ ዋስትና ራሷን መቻል እንደማትችል ለህዝባቸው በግልጽ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ሲናገሩ “በግብርና ምርት ሙሉ በሙሉ ራስን መቻል ይቻላል ብላችሁ እንዳታስቡ ፤ ቢያንስ እንደ ግብፅ ባሉ አገራት... ምንም ያህል ብንጥር ራስን ሙሉ በሙሉ መቻል ፈጽሞ የማይቻል ነገር ነው። እኛ የፈለግነውን ሁሉ ለማምረት የሚያስችል በቂ መሬትና ውሃ ስለሌለን ራሳችንን ሙሉ በሙሉ መቻል አንችልም” ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24🤷‍♂3👍2😢1
ዶናልድ ትራምፕ ያጋሯቸው ምስሎች‼️
📌የመጀመሪያው ምስል ኦርቢት ላይ ሆነው ቀይ በተን ተጭነው የኑክሌያር ቦንብ ጥቃት ሲፈፅሙ የሚያሳይ ሲሆን ይህንን ተከትሎ በኢራን ላይ የኑክሌያር ቦንብ ሊጠቀሙ ይሆን? የሚል ጥያቄ አስነስቷል።
📌ሁለተኛው ምስል ደግሞ ኢራንን ከሁሉም አቅጣጫ ጥቃት ሲዘነዝሩ የሚያሳይ ሲሆን ይህም በኢራን ላይ ጥቃት ሊክፈቱ እንዳሰቡ የሚያሳይ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16😢8👍5🤣3🥰1
የ500 ሚሊዮን ዶላር ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ሊካሄድ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንኩ ነገ ማክሰኞ ግንቦት 11 ቀን 2016 ዓ.ም 500 ሚሊዮን ዶላር ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ እንደሚካሄድ  ይፋ አድርጓል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍9
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንክ ሂሳብን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ማስተሳሰርን በተመለከተ ይህን ብሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሠረት ሂሳባቸውን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ያላስተሳሰሩ ደንበኞች የባንክ አገልግሎት ማግኘት አይችሉም። በመሆኑም ባንካችን ያዘጋጀውን የበይነ መረብ (Online) ማስተሳሰሪያ አማራጭ (https://cbefayda.cbe.com.et) በመጠቀም ወይም ወደሚቀርባችሁ የባንካችን ቅርንጫፍ በመሄድ  ሂሳባችሁን እንድታስተሳስሩ እንገልፃለን ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍2😁2👏1
የቀብር ዋጋ ጭማሪ‼️
የቀብር አገልግሎት የዋጋ ማሻሻያ የማሕበረሰቡን ጫና ለመቀነስ መሆኑን አዲስ አበባ መጅሊስ አስታወቀ‼️

​የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት (መጅሊስ) በጀናዛ ማረፊያ ቦታዎች ላይ ያደረገው የዋጋ ማሻሻያ ተገልጋዮችን ከተጨማሪ ወጪ ለመታደግ የተደረገ መሆኑን አስታወቀ።

​የምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሪያድ ጀማል እንደገለጹት፤ ቀደም ሲል የነበረው አሰራር ለብልሹ አሰራር የተጋለጠና ወጥነት የጎደለው ነበር። ይህንን ለመቅረፍ መጅሊሱ ባለፉት 9 ወራት ውስጥ ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የመሠረተ ልማትና የሸሪዓዊ አቀባበር ሥርዓት ማሻሻያ ሥራዎችን አከናውኗል።

​በአዲሱ ማሻሻያ መሠረት የሕፃናት ቀብር 2,000 ብር፣ የአዋቂ ደግሞ 4,000 ብር ሆኗል።ይህም ቀደም ሲል ተገልጋዮች ለብሎኬት ግዢ ያወጡት የነበረውን ከ2,200 እስከ 2,800 ብር ተጨማሪ ወጪ የሚያስቀር ሲሆን፣ ከአሁን በኋላ እስከ 28 የሚደርሰው የብሎኬት አቅርቦት በራሱ በመጅሊሱ የሚሸፈን ይሆናል።

​በበጎ ፈቃደኝነት የጀናዛ እጥበትና ሽኝት በሚያደርጉ ተቋማት ላይ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ እንዳልተደረገባቸውና ምክር ቤቱ አሰራሩን ለማዘመን የተለያዩ መመሪያዎችን አጽድቆ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21😁17👍5🙊3
መረጃ‼️

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ፣ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ደኅንነት እንዲያስጠብቅ ጠየቁ።

ጌዲዮን ይህን ጥያቄ ያቀረቡት፣ ዛሬ ከሳዑዲ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋሊድ ኤልክረጂ ጋር በተወያዩበት ወቅት መሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባሠራጨው መረጃ ገልጧል።

ጌዲዮን፣ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ለኢትዮጵያዊያን ሠራተኞች ሕጋዊ የሥራ እድሎችን እንዲያመቻችም መጠየቃቸውን ሚንስቴሩ ጠቅሷል።

ሚንስትር ዋሊድ፣ ሕጋዊ የሠራተኞች ፍልሠት ኢትዮጵያዊያን ደኅንነቱ የተጠበቀ የሥራ ቅጥር እድል እንዲያገኙ ለማስቻል አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ተብሏል።

የሳዑዲ ዓረቢያ ፍርድ ቤት ከአደንዛዥ እጽ ዝውውር ጋር በተያያዘ የሞት ቅጣት የጣለባቸው በርካታ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ በውይይቱ ወቅት ይነሳ አይነሳ መረጃው አላመለከትም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍6😡1
“ጥቃቱን ለጊዜው ትቼዋለሁ”ትራምፕ

። ። ። ። ። : : : : : : : : : :
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ ሊፈፅሙት የነበረውን ጥቃት ማራዘማቸውን አሳውቀዋል።

የባህረ ሰላጤው አገራት ሳውዲ አረቢያ፣ኳታርና አረብ ኤሚሬቶች እንዲሁም ሌሎች አገራት ኢራን ላይ ጥቃት እንዳይሰነዝር ጠይቀውኛል ብለዋል ትራምፕ።

ለማክሰኞ ቀን ተቆርጦለት የነበረው ጥቃት ለዲፕሎማሲ ጊዜ መግዣ በሚል ለአሁኑ ቆሟል።

በዕርግጥ ጥቃቱ ለሁለት እና ሶስት ቀናት ያህል እንደተራዘመ መነገሩ ያን ያህል ዘላቂ ሰላም ላያመጣ ይችላል።

ፔንታጎን ቢያንስ ለአሁኑ እርምጃ እንዳይወስድ በትራምፕ ታዟል።

ትራምፕ ኢራን ጋር ያለው ውይይት በጎ ባለመሆኑ ነገ ወደ ጥቃቱ እንመለሳለን በሚልም ዝተዋል።

የትኛውም ስምምነት ቴህራን ኑክሌር ቦምብ እንዳትታጠቅ ማድረግ አለበት የሪፐብሊካኑ ዕምነት ነው።

ፕሬዚዳንቱ በትሩዝ ሶሻል ሚዲያቸው ላይ ተቀባይነት የሌለው ሀሳብ ኢራን የምተቀርብ ከሆነ የጦር ሚኒስቴሩ(ፔንታጎን) ወደ ጥቃት ለመመለስ በተጠንቀ ቅ ላይ እንዲቆይም አዘዋል።

ትራምፕ ማክሰኞ የያዙትን ጥቃት አራዘሙ እንጂ ኢራን ላይ መጠነ ሰፊ  ጥቃት ለማድረስ አሁንም ተዘጋጅተዋል ተብሏል።

ኢራን የመደራደሪያ ነጥቧን በፓኪስታን በኩል ለአሜሪካ መላኳም የሚዘነጋ አይደለም።

ዘገባው የአር ቲ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12🥱11🤣6👍2🥰2🤯2👏1😢1