ወደ ቆሻሻ መጣያ የገቡት ስጦታዎች‼️
ከቀናት በፊት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ወደ ቤጂንግ ያቀኑት ልዑኮች ቤጂንግን ለቀው ወደ ፕሬዝዳንቱ AIR FORCE 1 ከመሳፈራቸው በፊት ሁሉም ልዑካን ቡድኖች ከቻይና አስተናጋጆቻቸው የተሰጡን ስጦታዎችን፣ ባጆችን፣ ፒን፣ስልኮችን እና ቅርሶችን በአየር ማረፊያው ውስጥ በሚገኝ የቆሻሻ መጣያ ውስጥ ሁሉንም ስጦታዎች ሲጥሉ ታይተዋል።
ይህ የሆነው ማንኛውም የቻይና ስሪት የሆነ ዕቃ ወደ ፕሬዝዳንቱ AIR FORCE 1 አውሮፕላን ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ስለሆነ ነው ።
ከትራምፕ ጋር የተጓዙት ልዑካን ቡድን ለደህንነት ሲባል ሲጠቀሙባቸው የነበሩ የግል ስልኮቻቸውን በቤታቸው ትተው በበረራ ጊዜ እስከዛሬ ጥቅም ላይ ያልዋሉ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን እንዲጠቀሙ ተገደዋል።
@Addis_Reporter

😁26❤15👍4🤔4
ውድ የአዲስ ሪፖርተር ተከታታዮቻችን ማስታወቂያ ማሰራት የምትፈልጉ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል👇
@Addis_reporter_bot
@Addis_reporter_bot
❤3👍2👏1
የኤርትራና ኢትዮጵያ ማዕቀቦች ተነሱ‼️
የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ በባይደን አስተዳደር ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ በኢትዮጵያና በኤርትራ ላይ ተጥሎ የነበረው የጦር መሳሪያ እግድ እንዲሁም ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ በአመራሮች እና በወታደራዊ መሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረውን ማዕቀብ አንስታለች።
ይህ የሆነው ከሰሞኑ የሁለቱም ሀገራት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴሮች ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር በአሜሪካ ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተው ከተፈራረሙ በኋላ ነው።
አሜሪካ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ለቀይ ባህር ደህንነት አስፈላጊ እነደሆኑ በማመን ከሁለቱ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ወስናለች።
ይህ የአሜሪካ እርምጃ ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብ ይገባኛል ጥያቄ ማንሳቷን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ወደ ጦርነት እንደማትገባ ሊያረጋግጥ እንደሚችል ተነግሯል።

❤27👍5👏4
በታክስ አስተዳደር አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ አስተያየት ለማሰባሰብ እና ውይይት ለማድረግ ጥሪ ቀረበ
በታክስ አስተዳደር አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ከባለድርሻ አካላት አስተያየት ለማሰባሰብ እና ውይይት ለማድረግ ጥሪ ያስተላለፈው የገንዘብ ሚኒስቴር ነው።
የታክስ አስተዳደር ሥርዓቱን ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊ እና ከወቅቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጋር የተጣጣመ ለማድረግ ይቻል ዘንድ፤ ነባሩን የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 ለማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ያለው ሚኒስቴሩ የሕጉ ረቂቅ ጸድቆ ወደ ሥራ ከመግባቱ በፊት፣ በሕጉ ቀጥተኛ ተገዢ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችንና ባለሙያዎችን ማሳተፍ፣ ግብዓት መሰብሰብና ግልጽ ውይይት ማድረግ አፈላጊ እንደሆነ አስታውቋል።
የታክስ አስተዳደር አዋጅ ማሻሻያ የሚመለከታችሁ ግብር ከፋዮች፣ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት፣ የሕግና የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እንዲሁም ፍላጎት ያላችሁ የኅብረተሰብ ክፍሎች ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የሚኒስቴሩ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ፤በአካል በመገኘት አስተያየት መስጠት እንደሚችሉ ጥሪ አስተላልፏል።
እንዲሁም በረቂቅ አዋጁ ላይ የጽሑፍ አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ አካላት፣ የአዋጁን ዝርዝር የድንጋጌዎች ረቂቅ (በአማርኛ ቅጂ) በገንዘብ ሚኒስቴር ድኅረ-ገጽ ላይ መመልከት እንደሚችሉና ያዘጋጁትን ዝርዝር አስተያየት እስከ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በኢሜይል አድራሻ መላክ እንደሚችሉ አስታውቋል

❤7👍3👏1
በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያውያን ሱቆች እየፈረሱ መሆኑ ተገለጸ‼
በደቡብ አፍሪካ መጤ አፍሪቃውያን ላይ ይደርስ የነበረው ጥቃት ጋብ ያለ ቢመስልም፣ “ህገ-ወጥ ግንባታ” በሚል ምክንያት የበርካታ ስደተኞች ሱቆች በፀጥታ ኃይሎች እየፈረሱባቸው መሆኑን በጆሃንስበርግ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለDW ገልፀዋል።
ድርጊቱን የገለጹ አንድ ነዋሪ “ነገሩ ሂድ አትበለው ግን እንዲሄድ አድርገው ነው” ሲሉ እርምጃው በስደተኞች ላይ ተጨማሪ እንግልት እየፈጠረ መሆኑን አስረድተዋል።
በደቡብ አፍሪካ ካሉ አነስተኛና መካከለኛ የሸቀጥ መደብሮች መካከል አብዛኞቹ የኢትዮጵያውያን መሆናቸው ይታወቃል።
እዚያው ትዳርና ልጆች መስርተው ከ10 እስከ 20 ዓመታት የኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለስ ቢፈልጉም፤ በአገር ቤት የመኖሪያ ቤት እና ለልጆቻቸው የትምህርት ቤት አቅርቦት ችግር ስጋት በመሆኑ አሁንም በደቡብ አፍሪካ ባለው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለመቆየት መገደዳቸውን ተናግረዋል።

❤16😢14👍2👀1
የአሜሪካ የነዳጅ ማደያዎች በኢራን ሃከሮች የሳይበር ጥቃት ተሰነዘረባቸው
በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች የነዳጅ መጠን መቆጣጠሪያ ስርዓቶች ላይ ለተሰነዘሩት ተከታታይ የሳይበር ጥቃቶች ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸው ሃከሮች ሳይሆኑ አይቀሩም ሲል CNN የሀገሪቱን ባለስልጣናት ጠቅሶ ዘግቧል።
ሃከሮቹ ጥቃቱን የፈጸሙት ያለ ምንም የይለፍ ቃል በቀጥታ ከኢንተርኔት ጋር የተገናኙ አውቶማቲክ የነዳጅ ታንከር መቆጣጠሪያዎችን በመጠቀም ነው። በዚህም ጥቃት በማደያዎቹ ስክሪን ላይ የሚታየውን የነዳጅ መጠን ንባብ ማዛባት የቻሉ ሲሆን፣ በትክክለኛው ታንከሮቹ ውስጥ ባለው የነዳጅ መጠን ላይም የተወሰነ ጉዳት አድርሰዋል።

👍13😁10❤9👏2🎉1
እስራኤል በጋዛ ከፍተኛውን የሃማስ የጦር አዛዥ ለመግደል በሃማስ ላይ ድብደባ ፈጸመች
የእስራኤል መከላከያ ኃይል (በጋዛ የሚገኘውን የሃማስ ወታደራዊ ክንፍ ዋና አዛዥ እና የድርጅቱ ቁልፍ መሪ የሆነውን ኢዝ አል-ዲን አል-ሃዳድን መግደል የታለመ የአየር ጥቃት መፈጸሙን በይፋ አስታወቆዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው በጋዛ ከተማ ሪማል በተባለ አካባቢ በሚገኝ የመኖሪያ ህንፃ ላይ መሆኑን የፍልስጤም ሚዲያዎች ዘግበዋል።
አል-ሃዳድ የኦክቶበር 7 ጥቃት ግንባር ቀደም አቀነባባሪ ከሆኑት መካከል አንዱ ሲሆን፣ የቀድሞ መሪዎች መገደላቸውን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት በጋዛ ውስጥ የሃማስ ወታደራዊ ክንፍ ቁጥር 1 መሪ ነው። እስከ አሁን 6 ጊዜ ከተሰነዘሩ የግድያ ሙከራዎች በማምለጡ "The Ghost" (መንፈሱ) በሚል ቅጽል ስም ይታወቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የመከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ በሰጡት የጋራ መግለጫ ጥቃቱን ትዕዛዝ መስጠታቸውን አረጋግጠዋል። መሪው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ የመሩትን የጦር መሳሪያ የመፍታት ስምምነት ውድቅ ማድረጉን ጠቅሰዋል።

❤16👍4😢2😡1
የተወለዱት አራት ልጆች የእኔ አይደሉም በማለት የገዛ ሚስቱን ልጆቹ ፊት የገደለዉ አባት በእስራት ተቀጣ
በባሌ ዞን ሐረና ቡልቅ አንጋቱ ከተማ ነዋሪ የሆነው ሁሴን መሐመድ ከሩቅያ ሐሠን ጋር ትዳር መስርቶ መኖር ከጀመረ 19 ዓመታትን አስቆጥሯል። ሑሴን ከሩቅያ ጋር በነበረዉ የትዳር ሕይወት አራት ልጆች ያፈራና ሠላማዊ ትዳር ሲመራ መቆየቱን የዞኑ አቃቢ ሕግ ፅህፈት ቤት የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራ አቃቢ ሕግ ደጀኔ ይገረሙ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ከቅርብ ግዜ ወዲሕ ግን ሑሴን በትዳሩ ደስተኛ አለመሆንና የተለያዩ መጠራጠሮች ያንፀባርቅ እንደነበረ የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ለዚሕም ምንም ማስረጃ ሆኖ የተገኘ ነገር ሣይኖር፣ በ19 ዓመታት የትዳር ጉዞ የተፈጠሩት አራት ልጆች የኔ ፍሬ አይደሉም የሚል እምነት አሣድሮ የተለያዩ ግጭቶችን ከተለያዩ ሠዎች ጋር ፈጥሮ ቆይቷል፡፡ ከዚያ ውስጥም፣ ከዚያው አካባቢ ሠው ጋር ግጭት ፈጥሮ የአካል ጉዳት በማድረስ በፍርድ ቤት የስድስት ወር ቀላል እስራት እንደተፈረደበትም አቃቢ ሕግ ደጀኔ ይጠቅሳሉ ።ይሕ በሑሴን በኩል የተፈጠረ በማስረጃ ያልተረጋገጠ ጥርጣሬ እየገፋ መጥቶ የካቲት 10 ቀን 2018 ከጠዋቱ ሶስት ሠዓት ላይ ከባድ ጸብ ያስነሳል፡፡
በወቅቱ ባለቤቱ ቁርስ ለቤተሠቦች እያዘጋጀች እያለች ʻእነዚሕን ልጆች ወደ የአባታቸው ስጭ ስልሽ እንቢ አልሽʼ ሲል ʻ ልጆቼ ብለህ ተቀብለህ ያሣደካቸውን እኔ አሁን የማናቸው ብዬ ለማን ልስጣቸው? እነዚሕም ልጆች፣ አሁንም በሆዴ ያለው ፅንስ ያንተው ነውʼ ስትል እንደመለሰችለት በንዴት ስለታም ባንጋ በማንሣት ʻየማቅልሽ ነገር የለም እዚያው ካመጣሽባቸውʼ ሲላት ነገሩ ያላማራት ሚስት ከባሏ ፊት ለማምለጥ ስትሮጥ አደናቅፏት ትወድቃለች።በዚሕ ግዜ ባል ሚስቱ በወደቀችበት አንገቷና የተለያየ የሠውነት ክፍሎቿን በመምታት ጭካኔ በተሞላበት ሑኔታ ልጆቹ ፊት እናታቸውንና የባለቤቱን ሕይወት ያጠፋል።
ይሕን የእናታቸውን ሞት የተመለከቱ አራቱ ልጆች ስለታም መሳሪያዉን በመያዝ ወደነሱ ሲመጣ ተደናግጠው ወደ ውጭ በመውጣት ባሰሙት የድረሱልኝ ጩሕት የአካባቢ ሠዎች ደርሠው የድርጊቱ ፈፃሚ ሌላ የወንጀል ድርጊት ሣይፈፅም በቁጥጥር ስር እንዲውል አድርገዋል፡፡ፖሊስ የድርጊቱን ፈፃሚ በቁጥጥር ስር ካዋለ በኃላ የአራት ልጆች እናትና የሶስት ወር ነፍሰጡሯን ሟች አስክሬን በማስነሣት ለምርመራ ወደ ሆስፒታል ይልካል፡፡የምርመራ መዝገቡን በአስክሬን ምርመራ ውጤት፣ በተለያዩ ማስረጃዎችና በተከሳሽ የእምነት ቃል የምርመራ መዝገቡ በማጣራት አጠናቆ ለአቃቢ ሕግ ይልካል።
አቃቢ ሕግም ከፖሊስ የቀረበውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶና የከዚሕ ቀደም የነበረን የጥፋተኝነት ውሣኔ ሪከርድ በማያያዝ በከባድ የሠው መግደል ወንጀል ክስ ይመሠርታል።ክሱን የተመለከተው የባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓም በዋለው ችሎት ተከሣሽ ፣ምንም የተረጋገጠ ማስረጃ ሣይኖር ልጆች የእኔ አይደሉም ብሎ በመጠራጠር በባለቤቱ ላይ የፈፀመው የወንጀል ድርጊት እጅግ ነውረባ ፣ጨካኝና ከባድ እንዲሁም ከነረዉ የወንጀል ሪከርድ ጋር ተደምሮ በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ የተወሠነበት መሆኑን አቃቢ ሕግ ደጀኔ ይገረሙ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
Via : dagu

❤16😢14👍3👏3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
😁21❤6👍4🤔2
የደብረ ማርቆስ አየር ማረፊያ የመጀመሪያ የሙከራ በረራውን አደረገ!
የአካባቢውን ሁለንተናዊ ገጽታ ይቀይራል የተባለለት የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ የመጀመሪያውን የሙከራ በረራ በዛሬው ዕለት በደመቀ ሁኔታ አስተናግዷል።
ይህ ክስተት ለከተማዋና ለአከባቢው የኢኮኖሚ፣ የንግድና የቱሪዝም እንቅስቃሴ አዲስ የብሩህ ተስፋ ምዕራፍ የከፈተ ታላቅ ስኬት መሆኑ ተነግሯል።
የመጀመሪያው የመንገደኞች አውሮፕላን ማረፊያውን ሲረግጥ በስፍራው የነበረው ድባብ እጅግ አስደሳች ነበር።
በታሪካዊው የበረራ መርሃ-ግብር ላይ የከተማው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች እና ቁጥራቸው የበዛ የከተማዋና የአካባቢው ነዋሪዎች በመገኘት ደስታቸውን በዕልልታና በጭብጨባ ገልጸዋል።

❤20👍9
ሆርሙዝን ለማለፍ ክፍያ ግዴታ‼️
ኢራን በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ላይ አዲስ የትራፊክ ስርዓት እየዘረጋች መሆኑን አስታወቀች።
👉'የአገልግሎት ክፍያ ይፈፀማል ብላለች።
'ከኢራን ጋር የሚተባበሩ የንግድ መርከቦች እና ወገኖች ብቻ ተጠቃሚ ይሆናሉ ሲሉ - የኢራን የደህንነት ኃላፊ አዚዚ ገልፀዋል።
የነፃነት ፕሮጀክት (Freedom project) እያሉ ለሚጃጃሉ (ለአሜሪካ) ሆርሙዝ ዝግ ሆኖ ይቆያል ብላለች።
ጦርነቱ ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ እስከአሁን በርካታ መርከቦች በሆርሙዝ እንደቆሙ ነው።

❤20👍7😁5👏1
የዝንጆሮዎች አመታዊ ቡፌ‼️
በታይላንድ በየአመቱ ለዝንጆዎች የምግብ ቡፌ ተዘጋጅቶላቸው አመታዊ ክብረ በአላቸው ይከበርላቸዋል።
ይህ ፈስቲቫል ዝንጀሮዎች በሀገሪቱ ቱርዝም ለሚያበረክቱት አስተዋጽኦ የሚደረግ የምስጋና ስረዓት ነው።

👍21😁17❤9🤣3👏1
የመውጫ ፈተና‼️
የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና በድጋሚ በግል መፈትን ለምትፈልጉ ምዝገባው ከዛሬ ግንቦት 8 እስከ 12/2018 ዓ.ም በዚህ https://exam.ethernet.edu.et
ድረገፅ መመዝገብ ትችላላችሁ።
ለመመዝገብ የፋይዳ መታወቂያ እንዲሁም በቴሌብር የሚከል 750 ብር ግዴታ ነው።
የፈተና መስጪያ ጊዜው ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል።

👍4❤3👏2
በቤት ሰራተኛዋ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ
በቆላድባ ከተማ ቀበሌ 03 ነዋሪ የሆነው አቶ አደራጀው ማንደፍሮ ክብረት፣ ከሰሜን ጎንደር ዞን አድርቃይ ወረዳ ዛሪማ ከተማ በቤት ሰራተኝነት አመጥቶ በቤቱ ያስቀመጣትን ታዳጊ ወጣት አስገድዶ በመድፈር ወንጀል ተከሶ የ12 አመት ፅኑ እስራት እንደፈረደበት ተገልጿል።
እንደ መዝገቡ መረጃ ወንጀሉ የተፈጸመው መጋቢት 21 ቀን ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ላይ በግለሰቡ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው። ተከሳሹ ረዳት የሌላትን እና ከሩቅ አካባቢ ለስራ የመጣችን ታዳጊ ወጣት ጥበቃ ሊያደርግላት እና እንደ ልጁ ሊያያት ሲገባ እምነቷን በመክዳት እና ጉልበት በመጠቀም አስነዋሪውን የደፈራ ወንጀል ፈጽሟል።
የቆላድባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ምርመራውን በአጭር ጊዜ አጣርቶ ለምስራቅ ደንቢያ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት አቅርቧል። ፍትህ ጽህፈት ቤቱም ክሱን ለወረዳው ፍርድ ቤት በመመሥረት ሲከራከር ቆይቷል።
የምስራቅ ደንቢያ ወረዳ ፍርድ ቤት ግንቦት 05 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት የቀረቡትን ማስረጃዎች እና የምርመራ ውጤቶች መርምሮ የድርጊቱን አስነዋሪነት እና በታዳጊዋ ላይ የደረሰውን የስነ-ልቦናዊና አካላዊ ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት ተከሳሹ በ12 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የቆላድባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።

❤17👍10😢3👏1😁1
መረጃ‼️
ኤርትራ እና ግብጽ የባሕር ትራንስፖርት ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ።
ስምምነቱ የተፈረመው፣ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ባደር አብደላቲ እና የትራንስፖርት ሚንስትር ካሜል አል ዋዚር ትናንት በአሥመራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት መሆኑን የግብጽ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
ስምምነቱ፣ የሁለቱን አገራት ወደቦች በባሕር ትራንስፖርት በማስተሳሰር የንግድ ግንኙነቱን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ዘገባዎቹ ጠቅሠዋል።
ግብጽ፣ በባሕርና ባቡር ሐዲድ ትራንስፖርት እንዲሁም በወደብ አስተዳደር ዙሪያ ለኤርትራ ልምዷን ለማጋራት መስማማቷንም ዘገባዎቹ አመልክተዋል።
በግብጹ ልዑካን ቡድን የተካተቱ ባለሀብቶች፣ ኤርትራ ውስጥ በማዕድን፣ ትራንስፖርት፣ መድሃኒት እና አሳ ልማት ዘርፍ መሠማራት በሚችሉበት ሁኔታ ዙሪያ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ጋር መወያየታቸውም ተገልጧል።

❤26😁8👍3🤪3🤷♂1🤡1🤣1
ከዓመት ከመንፈቅ በላይ ምርት አቋርጦ የነበረው የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ምርት ማምረት ጀመረ ‼️
በአማራ ክልል አዊ ዞን ጃዊ ወረዳ የሚገኘው ፋብሪካው በኃይል ማከፋፋይ ጣቢያ ብልሽት ሳቢያ ምርት አቁሞ የነበረ ሲኾን፣ ሠራተኞቹም በወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ እና ኦሞ ኩራዝ ቀጥር 1 እና ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካዎች በጊዜያዊነት ተመድበው ነበር።
ኾኖም ፋብሪካው ባሁኑ ወቅት በትንሹ 5 ሺሕ ሠራተኞች እንደሚያስፈልጉት የፋብሪካው ሃላፊዎች መናገራቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙኀን ዘግቧል።
በፋብሪካው ሥራ ለመቀጠር የሚፈልጉ ወገኖች የሥራ ዕድሉ ተጠቃሚ እንዲኾኑ ጥሪ ያደረጉት ሃላፊዎቹ፣ ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር ከ23 ሺሕ በላይ ለሚኾኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ሊፈጥር ይችላል ማለታቸውን የዜና ምንጩ ጠቅሷል።

❤14👍6🥰2👏1🤣1
ቆሻሻ ማስወገጃ እንዲቆፍር ተወሰነ‼️
የብልፅግና ፓርቲን ምርጫ ማስታወቂያን የቀደደ ተከሳሽ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ እንዲቆፍር ተወሰነበት
በሀድያ ዞን በጊምቢቹ ከተማ የሚኖረው ተከሳሽ ግንቦት 02 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ10 ሰዓት ተኩል ገደማ በጊምቢቹ ከተማ ልዩ ስሙ ቀጠና 03 መንደር 19 ተብሎ በሚጠራ አከባቢ በአንድ የሕክምና ተቋም ግድግዳ ላይ የተለጠፈውን የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት ማስታወቂያ መገንጠሉ ተገልጿል።
ድርጊቱን ሲፈፅም በዕለቱ ስምሪት ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት በሕግ ቁጥጥር ስር ሊውል እንደቻለ የከተማዋ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እስታውቋል
የግለሰቡ ድርጊት የፈፀመው ሆን ብሎ የምርጫ ሂደቱን ለማደናቀፍ በማሰብ በመሆኑም የጥፋተኝነት ፍርድ መሰጠቱ ተገልጿል።
በመሆኑም በቅጣት አወሳሰን መምሪያ መሠረት እርከን ሁለት ከ10 ቀን እስከ 6 ወር ቀላል እስር ወይም ከ10 ቀን እስከ 6 ወር የግዴታ ሥራ የሚያስቀጣ ሲሆን ፍ/ቤቱ የተከሳሽን ያለፈ የሕይወት ታሪክ የድርጊቱን አፈፃፀም ከግምት ውስጥ በማስገባት የግዴታ ሥራ አማራጭን ወስኖበታል።
በውሳኔው መሠረት ተከሳሽን ያርማል ያስተምራል ሌሎችን ያስጠነቅቃል በሚል ለሁለት ወራት፣ በሳምንት 3 ቀን በየዕለቱ 2:00 ሰዓት በጊምቢቹ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽህፈት ቤት አማካኝነት የሚሰራ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ጉድጓድ እንዲቆፍር በማለት ውሳኔ አስተላልፏል።
የጊምቢቹ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ዳኛ አቤነዘር ላምቦሬ በስተላለፉት መልዕክት፤ ወቅቱ የምርጫ ወቅት ስለሆነ ሕብረተሰቡ ማንኛውንም አይነት ከምርጫ ጋር ተያይዞ እንቅስቃሴዎችን በሚያደርጉበት ጊዜ ሕጉን በጠበቀ መልኩ ልሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

🤪36❤13🙉10👍2😁2🤔2🥰1👏1
ሩሲያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች‼️
የዩክሬን ድሮኖች በራይዛን የነዳጅ ማጣሪያ ላይ በፈጸሙት ጥቃት ከፍተኛ ውድመት መድረሱንና ስትራቴጂካዊ በሆኑ ቀጠናዎች ላይ የእሳት አደጋ መከሰቱን ተከትሎ፣ የሩሲያ ባለሥልጣናት በአንዱ ተጎጂ ከተማ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል።
በተመሳሳይ ወቅት ሞስኮ በዩክሬን ይዞታዎች ላይ አዳዲስ ጥቃቶችን የሰነዘረች ሲሆን፣ ሁለቱም ወገኖች ከጠላት የጦር ግንባር በስተጀርባ ባሉ ጥልቅ ይዞታዎች ላይ ረጅም ርቀት በሚጓዙ ድሮኖችና ትክክለኛ ኢላማቸውን በሚመቱ ጥቃቶች ላይ ይበልጥ መተማመናቸውን ተከትሎ በተለያዩ ግንባሮች ላይ ያለው ጫና በርትቷል።
እየተባባሰ የመጣው የጥቃት ማዕበል ግጭቱ መሠረተ ልማትን ወደ ማውደም ሰፊ ጦርነት እየተቀየረ መምጣቱን የሚያመለክት ሲሆን፣ ሁለቱም አገራት የሎጂስቲክስ፣ የነዳጅ ማጠራቀሚያዎች፣ የአየር መከላከያ ሥርዓቶች እና የወታደራዊ አቅርቦት መረቦችን መዳረሻ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

❤10👍4🤔2