አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
416 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ከወጪ ንግድ 8.71 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ

በ2018 በጀት ዓመት የ10 ወራት የወጪ ንግድ አፈጻጸም ከታቀደው በላይ ውጤት መመዝገቡ ነው የተገለጸው።

በበጀት ዓመቱ 10 ወራት ውስጥ 7.25 ቢሊዮን  የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ቢታቀድም 8.71 ቢሊዮን  የአሜሪካን ዶላር በላይ ማስመዝገብ እንደተቻለ  የንግድና ቀጣናዊ ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)  አስታውቀዋል፡፡

አፈጻጸሙም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተመዘገበው  ጋር ሲነጻጸር የ43.32 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁176👍3👏2🤔2
#UAE

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) የሆርሙዝ ሰርጥን ሳትጠቀም ነዳጅ ወደ ውጭ መላክ የሚያስችላትን አዲስ የነዳጅ መስመር ዝርጋታ እያፋጠነች መሆኑን ተነግሯል።

እንደ ብሉምበርግ ዘገባ፥ አዲሱ የምዕራብ-ምስራቅ የነዳጅ መስመር የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በፉጃይራ ወደብ በኩል ወደ ውጭ የምትልከውን የነዳጅ መጠን በእጥፍ ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

ፕሮጀክቱ ቀደም ብሎ የተጀመረ ቢሆንም አሁን ባለው የቀጠናው ውጥረት ምክንያት ግንባታው እንዲፋጠን ተደርጎ በ2027 (እ.አ.አ) ሙሉ በሙሉ ስራ እንደሚጀምር ይጠበቃል።

የሆርሙዝ ሰርጥ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ጂኦፖለቲካዊ ምክንያቶች ስጋት ውስጥ በመውደቁ ይህ መስመር አረብ ኤምሬትስ ያለ ምንም እንቅፋት ነዳጇን ለዓለም ገበያ እንድታቀርብ ይረዳታል።

አዲሱ መስመር ሲጠናቀቅ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ በፉጃይራ በኩል የምትልከው የነዳጅ መጠን በቀን ወደ 4 ሚሊዮን በርሜል እንደሚያደርሰው ይገመታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍6🥰1👏1😢1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዕለቱ አነጋጋሪ ምስል‼️
ትራምፕ በቤጂንግ የእራት ግብዣ ላይ የቻይናው ፕሬዚዳንት ከመቀመጫቸው ተነስተው ሲሄዱ ትራምፕ የፕሬዝዳንቱን የግል ማስታወሻ ደብተር ሲያገላብጡ መታየታቸው መነጋገሪያ ሆኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣54😁448🙊5👍3🤔3🤪3👏1💯1😎1😡1
በቦይንግ 737 ማክስ አደጋ ህይወቷ ለጠፋው ሳምያ ስቱሞ ቤተሰቦች የ49.5 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ተፈረደ!

በቺካጎ የሚገኝ የፍርድ ቤት ዳኝነት፣ እ.ኤ.አ በ2019 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 737 ማክስ  አውሮፕላን አደጋ ህይወቷ ለጠፋው አሜሪካዊቷ ሳምያ ስቱሞ ቤተሰቦች የ49.5 ሚሊዮን ዶላር  የካሳ ክፍያ እንዲፈጸም ወሰነ።ይህ የፍርድ ቤት ውሳኔ በዓለም ዙሪያ የ346 ሰዎችን ህይወት በቀጠፉት በሁለቱ የቦይንግ 737 ማክስ አሰቃቂ አደጋዎች ምክንያት በቦይንግ ኩባንያ ላይ የተሰጠ ሁለተኛው ትልቅ የዳኝነት ውሳኔ ነው።

የ24 ዓመቷ ሳምያ ስቱሞ በአውሮፕላን ደህንነት ላይ የምትሰራ ወጣት የነበረች ሲሆን፣ እ.ኤ.አ መጋቢት 10 ቀን 2019 የአውሮፕላን በረራ ቁጥር ET 302 ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ናይሮቢ በመጓዝ ላይ ሳለ ቢሾፍቱ አቅራቢያ በደረሰው አደጋ ህይወታቸው ካለፈው 157 ሰዎች መካከል አንዷ ነበረች። ይህ አደጋ ከመድረሱ ከአምስት ወራት በፊት በኢንዶኔዢያ የሊዮን ኤር  አውሮፕላን በተመሳሳይ ችግር ተከስክሶ የነበረ ሲሆን፣ የቺካጎ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቦይንግ ኩባንያ በአውሮፕላኑ የቴክኖሎጂ አሰራር  ላይ ለነበረበት ከፍተኛ የቸልተኝነት ጉድለት ተጠያቂ መሆኑን በድጋሚ ያረጋገጠ ሆኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24👍9👀2
🔥 ተመሳሳይ ያረጁ ዜናዎችን ማንበብ ይብቃዎ! አልጎሪዝምዎን ይቀይሩ።

🇪🇹 🌍 ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም አቀፍ ዙሪያ የተሰሙ አዳዲስ ክስተቶችን በተለየ ምልከታ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ይከታተሉ። እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን በየእለቱ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ብቻ ያገኛሉ።

ከሌሎች መገናኛ ብዙኃን የማያገኟቸውን ትኩስ ትኩስ መረጃዎችን ስፑትኒክ ኢትዮጵያ ለእርስኦ ያቀርብልዎታል።

📌አዳዲስ መረጃዎችን በየእለቱ ለመከታተል አሁኑኑ ቻናላችንን በመቀላቀል ያልተሰሙ መረጃዎችን ይከታተሉ::
👇🏾👇🏾👇🏾

https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy
5👍3🥰1
ወደ ቆሻሻ መጣያ የገቡት ስጦታዎች‼️
ከቀናት በፊት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ወደ ቤጂንግ ያቀኑት ልዑኮች ቤጂንግን ለቀው ወደ ፕሬዝዳንቱ AIR FORCE 1 ከመሳፈራቸው በፊት ሁሉም ልዑካን ቡድኖች ከቻይና አስተናጋጆቻቸው የተሰጡን ስጦታዎችን፣ ባጆችን፣ ፒን፣ስልኮችን እና ቅርሶችን በአየር ማረፊያው ውስጥ በሚገኝ የቆሻሻ መጣያ ውስጥ ሁሉንም ስጦታዎች ሲጥሉ ታይተዋል።

ይህ የሆነው ማንኛውም የቻይና ስሪት የሆነ ዕቃ ወደ ፕሬዝዳንቱ AIR FORCE 1 አውሮፕላን ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ስለሆነ ነው ።

ከትራምፕ ጋር የተጓዙት ልዑካን ቡድን ለደህንነት ሲባል ሲጠቀሙባቸው የነበሩ የግል ስልኮቻቸውን በቤታቸው ትተው በበረራ ጊዜ እስከዛሬ ጥቅም ላይ ያልዋሉ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን እንዲጠቀሙ ተገደዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁2615👍4🤔4
ውድ የአዲስ ሪፖርተር ተከታታዮቻችን ማስታወቂያ ማሰራት የምትፈልጉ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል👇
@Addis_reporter_bot
3👍2👏1
የኤርትራና ኢትዮጵያ ማዕቀቦች ተነሱ‼️
የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ በባይደን አስተዳደር ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ በኢትዮጵያና በኤርትራ ላይ ተጥሎ የነበረው የጦር መሳሪያ እግድ እንዲሁም ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ በአመራሮች እና በወታደራዊ መሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረውን ማዕቀብ አንስታለች።

ይህ የሆነው ከሰሞኑ የሁለቱም ሀገራት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴሮች ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር በአሜሪካ ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተው ከተፈራረሙ በኋላ ነው።

አሜሪካ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ለቀይ ባህር ደህንነት አስፈላጊ እነደሆኑ በማመን ከሁለቱ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ወስናለች።

ይህ የአሜሪካ እርምጃ ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብ ይገባኛል ጥያቄ ማንሳቷን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ወደ ጦርነት እንደማትገባ ሊያረጋግጥ እንደሚችል ተነግሯል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
27👍5👏4
በታክስ አስተዳደር አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ አስተያየት ለማሰባሰብ እና ውይይት ለማድረግ ጥሪ ቀረበ

በታክስ አስተዳደር አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ከባለድርሻ አካላት አስተያየት ለማሰባሰብ እና ውይይት ለማድረግ ጥሪ ያስተላለፈው የገንዘብ ሚኒስቴር ነው።

የታክስ አስተዳደር ሥርዓቱን ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊ እና ከወቅቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጋር የተጣጣመ ለማድረግ ይቻል ዘንድ፤ ነባሩን የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 ለማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ያለው ሚኒስቴሩ የሕጉ ረቂቅ ጸድቆ ወደ ሥራ ከመግባቱ በፊት፣ በሕጉ ቀጥተኛ ተገዢ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችንና ባለሙያዎችን ማሳተፍ፣ ግብዓት መሰብሰብና ግልጽ ውይይት ማድረግ አፈላጊ እንደሆነ አስታውቋል።

የታክስ አስተዳደር አዋጅ ማሻሻያ የሚመለከታችሁ ግብር ከፋዮች፣ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት፣ የሕግና የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እንዲሁም ፍላጎት ያላችሁ የኅብረተሰብ ክፍሎች ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የሚኒስቴሩ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ፤በአካል በመገኘት አስተያየት መስጠት እንደሚችሉ ጥሪ አስተላልፏል።

እንዲሁም በረቂቅ አዋጁ ላይ የጽሑፍ አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ አካላት፣ የአዋጁን ዝርዝር የድንጋጌዎች ረቂቅ (በአማርኛ ቅጂ) በገንዘብ ሚኒስቴር ድኅረ-ገጽ ላይ መመልከት እንደሚችሉና ያዘጋጁትን ዝርዝር አስተያየት እስከ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በኢሜይል አድራሻ መላክ እንደሚችሉ አስታውቋል

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍3👏1
በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያውያን ሱቆች እየፈረሱ መሆኑ ተገለጸ

በደቡብ አፍሪካ መጤ አፍሪቃውያን ላይ ይደርስ የነበረው ጥቃት ጋብ ያለ ቢመስልም፣ “ህገ-ወጥ ግንባታ” በሚል ምክንያት የበርካታ ስደተኞች ሱቆች በፀጥታ ኃይሎች እየፈረሱባቸው መሆኑን በጆሃንስበርግ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለDW ገልፀዋል።

ድርጊቱን የገለጹ አንድ ነዋሪ “ነገሩ ሂድ አትበለው ግን እንዲሄድ አድርገው ነው” ሲሉ እርምጃው በስደተኞች ላይ ተጨማሪ እንግልት እየፈጠረ መሆኑን አስረድተዋል።

በደቡብ አፍሪካ ካሉ አነስተኛና መካከለኛ የሸቀጥ መደብሮች መካከል አብዛኞቹ የኢትዮጵያውያን መሆናቸው ይታወቃል።

እዚያው ትዳርና ልጆች መስርተው ከ10 እስከ 20 ዓመታት የኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለስ ቢፈልጉም፤ በአገር ቤት የመኖሪያ ቤት እና ለልጆቻቸው የትምህርት ቤት አቅርቦት ችግር ስጋት በመሆኑ አሁንም በደቡብ አፍሪካ ባለው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለመቆየት መገደዳቸውን ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16😢14👍2👀1
የአሜሪካ የነዳጅ ማደያዎች በኢራን ሃከሮች የሳይበር ጥቃት ተሰነዘረባቸው

​በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች የነዳጅ መጠን መቆጣጠሪያ ስርዓቶች  ላይ ለተሰነዘሩት ተከታታይ የሳይበር ጥቃቶች ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸው ሃከሮች ሳይሆኑ አይቀሩም ሲል CNN የሀገሪቱን ባለስልጣናት ጠቅሶ ዘግቧል።

​ሃከሮቹ ጥቃቱን የፈጸሙት ያለ ምንም የይለፍ ቃል  በቀጥታ ከኢንተርኔት ጋር የተገናኙ አውቶማቲክ የነዳጅ ታንከር መቆጣጠሪያዎችን በመጠቀም ነው። በዚህም ጥቃት በማደያዎቹ ስክሪን ላይ የሚታየውን የነዳጅ መጠን ንባብ ማዛባት የቻሉ ሲሆን፣ በትክክለኛው ታንከሮቹ ውስጥ ባለው የነዳጅ መጠን ላይም የተወሰነ ጉዳት አድርሰዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍13😁109👏2🎉1
  እስራኤል በጋዛ ከፍተኛውን የሃማስ የጦር አዛዥ ለመግደል በሃማስ ላይ ድብደባ ፈጸመች

​የእስራኤል መከላከያ ኃይል (በጋዛ የሚገኘውን የሃማስ ወታደራዊ ክንፍ  ዋና አዛዥ እና የድርጅቱ ቁልፍ መሪ የሆነውን ኢዝ አል-ዲን አል-ሃዳድን መግደል የታለመ የአየር ጥቃት መፈጸሙን በይፋ አስታወቆዋል። ​ጥቃቱ የተፈጸመው በጋዛ ከተማ ሪማል በተባለ አካባቢ በሚገኝ የመኖሪያ ህንፃ ላይ መሆኑን የፍልስጤም ሚዲያዎች ዘግበዋል።

​አል-ሃዳድ የኦክቶበር 7 ጥቃት ግንባር ቀደም አቀነባባሪ ከሆኑት መካከል አንዱ ሲሆን፣ የቀድሞ መሪዎች መገደላቸውን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት በጋዛ ውስጥ የሃማስ ወታደራዊ ክንፍ ቁጥር 1 መሪ ነው። እስከ አሁን 6 ጊዜ ከተሰነዘሩ የግድያ ሙከራዎች በማምለጡ "The Ghost" (መንፈሱ) በሚል ቅጽል ስም ይታወቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የመከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ በሰጡት የጋራ መግለጫ ጥቃቱን ትዕዛዝ መስጠታቸውን አረጋግጠዋል። መሪው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ የመሩትን የጦር መሳሪያ የመፍታት ስምምነት ውድቅ ማድረጉን ጠቅሰዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍4😢2😡1
የተወለዱት አራት ልጆች የእኔ አይደሉም በማለት የገዛ ሚስቱን ልጆቹ ፊት የገደለዉ አባት በእስራት ተቀጣ
 
በባሌ ዞን ሐረና ቡልቅ አንጋቱ ከተማ ነዋሪ የሆነው ሁሴን መሐመድ ከሩቅያ ሐሠን ጋር ትዳር መስርቶ መኖር ከጀመረ 19  ዓመታትን  አስቆጥሯል። ሑሴን ከሩቅያ ጋር  በነበረዉ የትዳር ሕይወት አራት ልጆች ያፈራና ሠላማዊ ትዳር ሲመራ መቆየቱን የዞኑ አቃቢ ሕግ ፅህፈት ቤት የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራ አቃቢ ሕግ ደጀኔ ይገረሙ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ከቅርብ ግዜ ወዲሕ ግን ሑሴን በትዳሩ ደስተኛ አለመሆንና የተለያዩ መጠራጠሮች ያንፀባርቅ እንደነበረ የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
 
ለዚሕም ምንም ማስረጃ ሆኖ የተገኘ ነገር ሣይኖር፣ በ19 ዓመታት የትዳር ጉዞ የተፈጠሩት አራት ልጆች የኔ ፍሬ አይደሉም የሚል እምነት አሣድሮ የተለያዩ ግጭቶችን ከተለያዩ ሠዎች ጋር ፈጥሮ ቆይቷል፡፡ ከዚያ ውስጥም፣ ከዚያው አካባቢ ሠው ጋር ግጭት ፈጥሮ የአካል ጉዳት በማድረስ በፍርድ ቤት የስድስት ወር ቀላል እስራት እንደተፈረደበትም አቃቢ ሕግ ደጀኔ  ይጠቅሳሉ ።ይሕ በሑሴን በኩል የተፈጠረ በማስረጃ ያልተረጋገጠ ጥርጣሬ እየገፋ መጥቶ የካቲት 10 ቀን 2018 ከጠዋቱ ሶስት ሠዓት ላይ ከባድ ጸብ ያስነሳል፡፡
 
በወቅቱ ባለቤቱ ቁርስ ለቤተሠቦች እያዘጋጀች እያለች ʻእነዚሕን ልጆች ወደ የአባታቸው ስጭ ስልሽ እንቢ አልሽʼ ሲል ʻ ልጆቼ ብለህ ተቀብለህ ያሣደካቸውን እኔ አሁን የማናቸው ብዬ ለማን ልስጣቸው? እነዚሕም ልጆች፣ አሁንም በሆዴ ያለው ፅንስ ያንተው ነውʼ ስትል እንደመለሰችለት በንዴት ስለታም ባንጋ በማንሣት  ʻየማቅልሽ ነገር የለም እዚያው ካመጣሽባቸውʼ  ሲላት ነገሩ ያላማራት ሚስት ከባሏ ፊት ለማምለጥ ስትሮጥ አደናቅፏት ትወድቃለች።በዚሕ ግዜ ባል ሚስቱ በወደቀችበት አንገቷና የተለያየ የሠውነት ክፍሎቿን በመምታት ጭካኔ በተሞላበት ሑኔታ ልጆቹ ፊት እናታቸውንና የባለቤቱን ሕይወት ያጠፋል።
 
ይሕን የእናታቸውን ሞት የተመለከቱ አራቱ ልጆች ስለታም መሳሪያዉን በመያዝ ወደነሱ ሲመጣ ተደናግጠው ወደ ውጭ በመውጣት ባሰሙት የድረሱልኝ ጩሕት የአካባቢ ሠዎች ደርሠው የድርጊቱ ፈፃሚ ሌላ የወንጀል ድርጊት ሣይፈፅም በቁጥጥር ስር እንዲውል አድርገዋል፡፡ፖሊስ የድርጊቱን ፈፃሚ በቁጥጥር ስር ካዋለ በኃላ የአራት ልጆች እናትና የሶስት ወር ነፍሰጡሯን ሟች አስክሬን በማስነሣት ለምርመራ ወደ ሆስፒታል ይልካል፡፡የምርመራ መዝገቡን በአስክሬን ምርመራ ውጤት፣ በተለያዩ ማስረጃዎችና በተከሳሽ የእምነት ቃል የምርመራ መዝገቡ በማጣራት አጠናቆ ለአቃቢ ሕግ ይልካል።
 
አቃቢ ሕግም ከፖሊስ የቀረበውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶና የከዚሕ ቀደም የነበረን የጥፋተኝነት ውሣኔ ሪከርድ በማያያዝ በከባድ የሠው መግደል ወንጀል ክስ ይመሠርታል።ክሱን የተመለከተው የባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓም በዋለው ችሎት ተከሣሽ ፣ምንም የተረጋገጠ ማስረጃ ሣይኖር ልጆች የእኔ አይደሉም ብሎ በመጠራጠር በባለቤቱ ላይ የፈፀመው የወንጀል ድርጊት እጅግ ነውረባ ፣ጨካኝና ከባድ እንዲሁም ከነረዉ የወንጀል ሪከርድ ጋር ተደምሮ በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ የተወሠነበት መሆኑን አቃቢ ሕግ ደጀኔ ይገረሙ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
 
Via : dagu

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16😢14👍3👏3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አናስገባም ሠርገኛ ወይስ የለየለት የሰፈር ፀብ? 🤔

ከማኀበራዊ የትስስር ገፅ የተገኘ ቪዲዮ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁216👍4🤔2
የደብረ ማርቆስ አየር ማረፊያ የመጀመሪያ የሙከራ በረራውን አደረገ!

የአካባቢውን ሁለንተናዊ ገጽታ ይቀይራል የተባለለት የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ የመጀመሪያውን የሙከራ በረራ በዛሬው ዕለት በደመቀ ሁኔታ አስተናግዷል።

ይህ ክስተት ለከተማዋና ለአከባቢው የኢኮኖሚ፣ የንግድና የቱሪዝም እንቅስቃሴ አዲስ የብሩህ ተስፋ ምዕራፍ የከፈተ ታላቅ ስኬት መሆኑ ተነግሯል።

የመጀመሪያው የመንገደኞች አውሮፕላን ማረፊያውን ሲረግጥ በስፍራው የነበረው ድባብ እጅግ አስደሳች ነበር።

በታሪካዊው የበረራ መርሃ-ግብር ላይ የከተማው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች እና ቁጥራቸው የበዛ የከተማዋና የአካባቢው ነዋሪዎች በመገኘት ደስታቸውን በዕልልታና በጭብጨባ ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍9
ሆርሙዝን ለማለፍ ክፍያ ግዴታ‼️
ኢራን በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ላይ አዲስ የትራፊክ ስርዓት እየዘረጋች መሆኑን አስታወቀች።

👉'የአገልግሎት ክፍያ ይፈፀማል ብላለች።
'ከኢራን ጋር የሚተባበሩ የንግድ መርከቦች እና ወገኖች ብቻ ተጠቃሚ ይሆናሉ ሲሉ  - የኢራን የደህንነት ኃላፊ አዚዚ ገልፀዋል።
የነፃነት ፕሮጀክት (Freedom project) እያሉ ለሚጃጃሉ (ለአሜሪካ) ሆርሙዝ ዝግ ሆኖ ይቆያል ብላለች።
ጦርነቱ ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ እስከአሁን በርካታ መርከቦች በሆርሙዝ እንደቆሙ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍7😁5👏1
የዝንጆሮዎች አመታዊ ቡፌ‼️
በታይላንድ በየአመቱ ለዝንጆዎች የምግብ ቡፌ ተዘጋጅቶላቸው አመታዊ  ክብረ በአላቸው ይከበርላቸዋል።
ይህ ፈስቲቫል ዝንጀሮዎች በሀገሪቱ ቱርዝም ለሚያበረክቱት አስተዋጽኦ የሚደረግ የምስጋና ስረዓት ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍21😁179🤣3👏1