ኢትዮጵያ እና ጣሊያን ለቀበና ወንዝ ልማት ፕሮጀክት የሚውል የ5 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ስምምነት ተፈራረሙ
የኢትዮጵያ እና የጣሊያን መንግሥታት በየካ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን የቀበና ወንዝ ተፋሰስ ለማልማት የሚያስችል የ5 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ዛሬ ተፈራርመዋል።
ይህ በ24 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ይበቃል ተብሎ የሚጠበቀው "የከበና ወንዝ ገባር ወንዞች ልማት ፕሮጀክት" በአዲስ አበባ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ አማካኝነት ተግባራዊ እንደሚደረግ ተጠቁሟል።
ፕሮጀክቱ በዋናነት የአካባቢ ጥበቃን፣ የከተማን የአየር ንብረት የመቋቋም አቅምን ማሳደግ እና የከተማዋን ውበት መጠበቅ ላይ ትኩረት ያደርጋል።
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቱ የወንዝ ዳርቻዎችን በጂኦ-ኢንጂነሪንግ ዘዴ ከመጠበቅ ባለፈ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን በመገንባት የወንዙን መበከል ለመከላከልና ለአካባቢው ማህበረሰብ ምቹ የመዝናኛ ስፍራዎችን ለመፍጠር ያለመ ነው።
ይህ ፕሮጀክት በወንዝ ዳርቻው የሚኖሩ 9 ሺህ ገደማ ነዋሪዎችን በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን፣ በተለይም ሴቶች በጽዳት እና በመዝናኛ አገልግሎት አስተዳደር ዘርፍ ወደ ስራ እንዲሰማሩ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።
@Addis_Reporter

🤪11❤9👍8👏1🤯1
መረጃ‼️
የተመድ ዓለማቀፍ ፍርድ ቤት፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂውማን ራይትስ ዎችን ጨምሮ 31 መንግሥታዊ ያልኾኑ ዓለማቀፍ ድርጅቶች፣ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በቀጣዩ ወር በሚጀምረው ዓመታዊ ስብሰባው የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ተቆጣጣሪ ልዩ ራፖርተርን የጊዜ ቆይታ እንዲያራዝም ጠየቁ።
ልዩ ራፖርተሩና የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር፣ በቀጣዩ ዓመት ለሚደረገው የምክር ቤቱ ስብሰባ በአገሪቱ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ዙሪያ ሪፖርት እንዲያቀርቡም ድርጅቶቹ ለምክር ቤቱ በጻፉት ደብዳቤ ጥያቄ አቅርበዋል።
ድርጅቶቹ፣ ድንበር ዘለል ጥቃቶች ጨምሮ የኤርትራ መንግሥት ይፈጽማቸዋል ያሏቸውን የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሠቶች አውግዘዋል።
የኤርትራ መንግሥት ከተመድ ልዩ ራፖርተር ጋር እንዲተባበርና ልዩ ራፖርተሩ ወደ አገሪቱ ገብተው ምርመራ እንዲያደርጉ እንዲፈቅድም ድርጅቶቹ ጠይቀዋል።

❤7👍3
በኢትዮጵያ ኩርሙክ ከተማ ሱዳን ፈፀመችው በተባለ የድሮን ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች ሲገደሉ በእርዳታ ሰጪዎች ላይ ጉዳት ደረሰ!
ከሱዳን ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ኩርሙክ ወረዳ ኩርሙክ ከተማ ውስጥ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት፣ አንድ የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) የሥራ ባልደረባን ጨምሮ ቢያንስ ስምንት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውንና ሌሎች በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች እና የአካባቢው የጤና ባለሥልጣናት ገለጹ።
ነዋሪዎች ጥቃቱ የተፈጸመው ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 5:00 ገደማ መሆኑንና ከአሶሳ ከተማ 94 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የኩርሙክ ከተማ የሰዎች እንቅስቃሴ በሚበዛበት አካባቢ ላይ ማረፉን ተናግረዋል።የዓይን እማኞች ድሮኑ የመጣው ከሱዳን ብሉ ናይል ግዛት አቅጣጫ መሆኑን ጠቅሰው፣ የሱዳን ጦር ከፈጣን ድጋፍ ኃይሎች (RSF) ጋር እያካሄደ በነበረው ግጭት ወቅት ጥቃቱን እንደፈጸመ አስረድተዋል።

❤13👍6🤔4😢2💔1
በተከለከለ ቦታ ትምባሆ ሲሸጥ የተገኘ ሰው በእስራትና በገንዘብ እንደሚቀጣ ተነገረ
የአዲስ አበባ ከተማ ምግብ መድኃኒት ባለስልጣን አዲስ አበባን ከትምባሆ ጭስ ነፃ ለማድረግ በማዕከል እና በ11ዱ ቅርንጫፍ የተለያየ ስራዎች አከናውኗል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የምግብና ጤና ነክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸዉ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት ትምባሆ መሸጥ በተከለከለ ቦታ ሲሸጥ የተገኘ ሰው ከ6 ወር በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም በ5ሺህ ብር መቀጮ እንደሚቀጣ ተናግረዋል፡፡
ሙሉ በሙሉ ከተከለከለባቸው ቦታዎች ውስጥ የጤና ፣የመንግስት ፣የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ወጣት ማዕከላት እና የትምህርት ቤቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡የትምባሆ ኢንዱስትሪ የሚጠቀሙው አሳሳች ስልቶች እና የጤና ጉዳቶች በተለይ ትምባሆ ሱሰኝነትን የሚያበረታቱ የገበያ እና ማስታወቂያ ስልቶች ወጣቶችን ለመሳብ የሚደረጉ አሳሳች የምርት ማቅረቢያ መንገዶች፣ትምባሆ ጉዳትን ለመደበቅ የሚቀርቡ ሐሰተኛ መልዕክቶች በማጋለጥ ወጣቶችን ወደ ኒኮቲን ሱሰኝነት እንዳይገቡና ጤናማ ከትምባሆ ነፃ ህይወት ለማስፋፋት ሰፊ ስራዎች እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡
በህጉ የተመለከቱ ክልክላዎችን መተላለፍ ለአስተዳደራዊ እና የወንጀል ቅጣት የሚስከትል በመሆኑ በቀጣይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እርምጃ መውሰዱ ይቀጥላል ሲሉ አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡በተጨማሪም ፕሮሞሽንና ስፖንሰር ማደረግ ከ3 ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት እና 50 ሺ ብር ያስቀጣል፡፡
Via : dagu

❤13👍5
#ጭርት የሚባለው የቆዳ በሽታ (#tineacorporis) ሕክምናው ምንድን ነው❓️
✏️ጭርት ማለት ደርማቶፋይትስ በሚባሉ የፈንገስ ዝርያዎች አማካኝነት የሚመጣ የላይኛውን የቆዳ ክፍል የሚያጠቃ የቆዳ በሽታ ሲሆን ህፃናትን ጨምሮ በሁሉም የእድሜ ክልል ሊከሰት የሚቺል ተላላፊ በሽታ ነው።
መተላለፍያ መንገዱ ምንድነው?
✏️ህፃናት ይህንን የቆዳ በሺታ በበሽታው ከተያዙ ልጆች አዋቂ ሰዎች ወይም ከእንስሳት ሊተላለፍባቸው ይችላል።
በተለይ ደሞ ህፃናት ላይ የሚተላለፈው በፎጣ አልጋ ልብስ ካልሲ የፀጉር ማበጠሪያ በጋራ መጠቀም እና ንክኪ መፍጠር ዋነኛ መተላለፊያ መንገዶች ናቸው።
ምልክቶቹስ ምንድናቸው ❓️
✏️በሰውነት ላይ ክብ ክብ የሆነ ፣ ጠርዝ ጠርዙ ቀላ እና ከፍ ያለ ይሆናል
✏️ የማሳከክ ስሜት ሊኖረውም ላይኖረውም ይቺላል እየሰፋ ከሄደ ነጭ እንደ ቅርፊት ያለ ነገር ሊወጣ ይችላል።
ጭርት በሽታ መሆኑን እና አለመሆኑ በምን ይታወቃል❓️
✏️ አንድ የቆዳ በሽታ ጭርት መሆኑን እና አለመሆኑን በህክምና ባለሙያው በቆዳ ላይ የወጣውን ነገር አይቶ እንደ አስፈላጊነቱ ከቆዳ ላይ ናሙና በመውሰድ በላቦራቶሪ በመመርመር ፈንገስ መኖር እና አለመኖሩን ማወቅ ይችላል።
ካልታከመ የሚያመጣውስ ችግር አለ ይሆን?
✏️የሚያሳክክ፣ የተቆጣ እና የቆዳ መሰንጠቅ ሲኖር ለሌላ ባክቴሪያ ኢንፌክሽን (secondary bacterial infection) ሊጋለጡ ይችላሉ።
✏️ኅይለኛ የቆዳ መቆጣት/ብግነት
መከላከል ይቻላል❓️
የሚከተሉን ጥንቃቄዎችን በማድረግ የህፃናትን የጭርት በሺታ መከላከል ይቻላል
✔️ የህፃናት ግል እና የአካባቢ ንፅህናን መጠበቅ
✔️ ህፃናትን ሰውነታቸውን ካጠብን በዋላ በንፁህ ፎጣ ወይም ጨርቅ በደንብ ማድረቅ
✔️ ህፃናት በግል መጠቀም ያለባቸውን ነገሮች በጋራ አለመጠቀም ለምሳሌ ፎጣ የዉስጥ ልብሶች ካልሲ እና የመሳሰሉት
✔️ በተቻለ መጠን በዚህ በሽታ ካለባቸው ሌሎች ህፃናት ጋር ንክኪ አለመፍጠር
✔️ በአካባቢያችን የታመሙም እንስሳት ካሉ የእንስሳት ሀኪም ጋር በመውሰድ እና ማሳከም ተገቢ ነው።
ህክምናውስ ምንድነው❓️
መድሃኒቱ እንደ በሺታው ስፋት እና ጥልቀት የሚወሰን ሲሆን በቦታው ላይ የሚቀባ ቅባት ወይም የሚዋጥ መድሃኒት ሊድን ይችላል ።

❤21👍4👀3🥰1👏1
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 3,600 የውጪ ሃገር ዜጎች በሀሰት የኢትዮጵያ ፓስፖርት ለመያዝ ሲንቀሳቀሱ ደርሼባቸዋለሁ ብሏል።
አገልግሎቱ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች ሀሰተኛ የልደት ሰርተፍኬት፣ መታወቂያ እና ፋይዳ በመያዝ ህጋዊ አገልግሎት ለማግኘት ሲሉ እንደተደረሰባቸው ተናግሯል።
በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የፓስፖርት አገልግሎት ዳሬክተር የሆኑት አቶ ሙሉጌታ ብርሃኑ ከድንበር አከባቢ የሚመጡ ኢትዮጵያውያን ከውጪ ሃገር ከሚመጡ ዜጎች ጋር የሚመሳሰል ማንነት ስላላቸው የውጪ ዜጎች ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ሃሰተኛ ሰነድ ለመያዝ ሙከራ እንደሚያደርጉ አስረድተዋል።
አቶ ሙሉጌታ ረጅም ዓመታትን በኢትዮጵያ የኖሩ ኤርትራዊያን የኢትዮጵያ ዜግነት ሊያገኙ የሚችሉበትን ሁኔታም አስረድተዋል።
በሪፈረንደሙ ወቅት ያልመረጡ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ የዜግነት መብት ይሰጣቸዋል፣ ሪፈረንደም የመረጡ ግን ህጉን ተከትለው የዜግነት ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ ብለዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የሚነሱበትን ቅሬታዎች ለመፍታት እየሰራ መሆኑን ያነሱት ኃላፊው ፣ ሰዎችም ለአግልግሎት ሲመጡ የሚያጋጥማቸውን እንግልት ለመቀነስ የሚጠበቅባቸውን ሰነድ ሁሉ አሟልተው እንዲመጡ አሳስበዋል።

❤10👍4
ለ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና የኦንላይን ልምምድ ያድርጉ!
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ተፈታኞች ፈተና የሚለማመዱበት አድራሻ ይፋ አድርጓል።
ተፈታኞች በተደለደሉበት ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ትይዩ ያለውን ሊንክ በመጠቀም፣ User Name በሚለው ላይ የፈተና አዳራሽ መግቢያ ካርድ ላይ ያለውን አድሚሽን ቁጥር በማስገባት እና Password በሚለው ላይ 1234 በማስገባት በዴስክቶፕ ኮምፒውተር፣ በላፕቶፕ፣ በታብሌት፣ በስልክ እና በመሰል የኤልክትሮኒክስ መሳሪያዎች ማንኛውንም አይነት የኢንተርኔት አማራጭ በመጠቀም ከዛሬ ግንቦት 07/2018 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከፈተናው ድረስ መለማመመድ እንደሚችሉ ተገልጿል።

❤7👍5🥰2🎉2👏1
ከወጪ ንግድ 8.71 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ
በ2018 በጀት ዓመት የ10 ወራት የወጪ ንግድ አፈጻጸም ከታቀደው በላይ ውጤት መመዝገቡ ነው የተገለጸው።
በበጀት ዓመቱ 10 ወራት ውስጥ 7.25 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ቢታቀድም 8.71 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ማስመዝገብ እንደተቻለ የንግድና ቀጣናዊ ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡
አፈጻጸሙም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተመዘገበው ጋር ሲነጻጸር የ43.32 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

😁17❤6👍3👏2🤔2
#UAE
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) የሆርሙዝ ሰርጥን ሳትጠቀም ነዳጅ ወደ ውጭ መላክ የሚያስችላትን አዲስ የነዳጅ መስመር ዝርጋታ እያፋጠነች መሆኑን ተነግሯል።
እንደ ብሉምበርግ ዘገባ፥ አዲሱ የምዕራብ-ምስራቅ የነዳጅ መስመር የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በፉጃይራ ወደብ በኩል ወደ ውጭ የምትልከውን የነዳጅ መጠን በእጥፍ ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
ፕሮጀክቱ ቀደም ብሎ የተጀመረ ቢሆንም አሁን ባለው የቀጠናው ውጥረት ምክንያት ግንባታው እንዲፋጠን ተደርጎ በ2027 (እ.አ.አ) ሙሉ በሙሉ ስራ እንደሚጀምር ይጠበቃል።
የሆርሙዝ ሰርጥ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ጂኦፖለቲካዊ ምክንያቶች ስጋት ውስጥ በመውደቁ ይህ መስመር አረብ ኤምሬትስ ያለ ምንም እንቅፋት ነዳጇን ለዓለም ገበያ እንድታቀርብ ይረዳታል።
አዲሱ መስመር ሲጠናቀቅ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ በፉጃይራ በኩል የምትልከው የነዳጅ መጠን በቀን ወደ 4 ሚሊዮን በርሜል እንደሚያደርሰው ይገመታል።

❤20👍6🥰1👏1😢1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዕለቱ አነጋጋሪ ምስል‼️
ትራምፕ በቤጂንግ የእራት ግብዣ ላይ የቻይናው ፕሬዚዳንት ከመቀመጫቸው ተነስተው ሲሄዱ ትራምፕ የፕሬዝዳንቱን የግል ማስታወሻ ደብተር ሲያገላብጡ መታየታቸው መነጋገሪያ ሆኗል።

🤣54😁44❤8🙊5👍3🤔3🤪3👏1💯1😎1😡1
በቦይንግ 737 ማክስ አደጋ ህይወቷ ለጠፋው ሳምያ ስቱሞ ቤተሰቦች የ49.5 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ተፈረደ!
በቺካጎ የሚገኝ የፍርድ ቤት ዳኝነት፣ እ.ኤ.አ በ2019 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ህይወቷ ለጠፋው አሜሪካዊቷ ሳምያ ስቱሞ ቤተሰቦች የ49.5 ሚሊዮን ዶላር የካሳ ክፍያ እንዲፈጸም ወሰነ።ይህ የፍርድ ቤት ውሳኔ በዓለም ዙሪያ የ346 ሰዎችን ህይወት በቀጠፉት በሁለቱ የቦይንግ 737 ማክስ አሰቃቂ አደጋዎች ምክንያት በቦይንግ ኩባንያ ላይ የተሰጠ ሁለተኛው ትልቅ የዳኝነት ውሳኔ ነው።
የ24 ዓመቷ ሳምያ ስቱሞ በአውሮፕላን ደህንነት ላይ የምትሰራ ወጣት የነበረች ሲሆን፣ እ.ኤ.አ መጋቢት 10 ቀን 2019 የአውሮፕላን በረራ ቁጥር ET 302 ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ናይሮቢ በመጓዝ ላይ ሳለ ቢሾፍቱ አቅራቢያ በደረሰው አደጋ ህይወታቸው ካለፈው 157 ሰዎች መካከል አንዷ ነበረች። ይህ አደጋ ከመድረሱ ከአምስት ወራት በፊት በኢንዶኔዢያ የሊዮን ኤር አውሮፕላን በተመሳሳይ ችግር ተከስክሶ የነበረ ሲሆን፣ የቺካጎ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቦይንግ ኩባንያ በአውሮፕላኑ የቴክኖሎጂ አሰራር ላይ ለነበረበት ከፍተኛ የቸልተኝነት ጉድለት ተጠያቂ መሆኑን በድጋሚ ያረጋገጠ ሆኗል።

❤24👍9👀2
🔥 ተመሳሳይ ያረጁ ዜናዎችን ማንበብ ይብቃዎ! አልጎሪዝምዎን ይቀይሩ።
🇪🇹 🌍 ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም አቀፍ ዙሪያ የተሰሙ አዳዲስ ክስተቶችን በተለየ ምልከታ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ይከታተሉ። እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን በየእለቱ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ብቻ ያገኛሉ።
✅ከሌሎች መገናኛ ብዙኃን የማያገኟቸውን ትኩስ ትኩስ መረጃዎችን ስፑትኒክ ኢትዮጵያ ለእርስኦ ያቀርብልዎታል።
📌አዳዲስ መረጃዎችን በየእለቱ ለመከታተል አሁኑኑ ቻናላችንን በመቀላቀል ያልተሰሙ መረጃዎችን ይከታተሉ::
👇🏾👇🏾👇🏾
https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy

❤5👍3🥰1
ወደ ቆሻሻ መጣያ የገቡት ስጦታዎች‼️
ከቀናት በፊት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ወደ ቤጂንግ ያቀኑት ልዑኮች ቤጂንግን ለቀው ወደ ፕሬዝዳንቱ AIR FORCE 1 ከመሳፈራቸው በፊት ሁሉም ልዑካን ቡድኖች ከቻይና አስተናጋጆቻቸው የተሰጡን ስጦታዎችን፣ ባጆችን፣ ፒን፣ስልኮችን እና ቅርሶችን በአየር ማረፊያው ውስጥ በሚገኝ የቆሻሻ መጣያ ውስጥ ሁሉንም ስጦታዎች ሲጥሉ ታይተዋል።
ይህ የሆነው ማንኛውም የቻይና ስሪት የሆነ ዕቃ ወደ ፕሬዝዳንቱ AIR FORCE 1 አውሮፕላን ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ስለሆነ ነው ።
ከትራምፕ ጋር የተጓዙት ልዑካን ቡድን ለደህንነት ሲባል ሲጠቀሙባቸው የነበሩ የግል ስልኮቻቸውን በቤታቸው ትተው በበረራ ጊዜ እስከዛሬ ጥቅም ላይ ያልዋሉ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን እንዲጠቀሙ ተገደዋል።

😁26❤15👍4🤔4
ውድ የአዲስ ሪፖርተር ተከታታዮቻችን ማስታወቂያ ማሰራት የምትፈልጉ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል👇
@Addis_reporter_bot
@Addis_reporter_bot
❤3👍2👏1
የኤርትራና ኢትዮጵያ ማዕቀቦች ተነሱ‼️
የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ በባይደን አስተዳደር ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ በኢትዮጵያና በኤርትራ ላይ ተጥሎ የነበረው የጦር መሳሪያ እግድ እንዲሁም ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ በአመራሮች እና በወታደራዊ መሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረውን ማዕቀብ አንስታለች።
ይህ የሆነው ከሰሞኑ የሁለቱም ሀገራት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴሮች ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር በአሜሪካ ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተው ከተፈራረሙ በኋላ ነው።
አሜሪካ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ለቀይ ባህር ደህንነት አስፈላጊ እነደሆኑ በማመን ከሁለቱ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ወስናለች።
ይህ የአሜሪካ እርምጃ ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብ ይገባኛል ጥያቄ ማንሳቷን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ወደ ጦርነት እንደማትገባ ሊያረጋግጥ እንደሚችል ተነግሯል።

❤27👍5👏4
በታክስ አስተዳደር አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ አስተያየት ለማሰባሰብ እና ውይይት ለማድረግ ጥሪ ቀረበ
በታክስ አስተዳደር አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ከባለድርሻ አካላት አስተያየት ለማሰባሰብ እና ውይይት ለማድረግ ጥሪ ያስተላለፈው የገንዘብ ሚኒስቴር ነው።
የታክስ አስተዳደር ሥርዓቱን ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊ እና ከወቅቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጋር የተጣጣመ ለማድረግ ይቻል ዘንድ፤ ነባሩን የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 ለማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ያለው ሚኒስቴሩ የሕጉ ረቂቅ ጸድቆ ወደ ሥራ ከመግባቱ በፊት፣ በሕጉ ቀጥተኛ ተገዢ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችንና ባለሙያዎችን ማሳተፍ፣ ግብዓት መሰብሰብና ግልጽ ውይይት ማድረግ አፈላጊ እንደሆነ አስታውቋል።
የታክስ አስተዳደር አዋጅ ማሻሻያ የሚመለከታችሁ ግብር ከፋዮች፣ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት፣ የሕግና የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እንዲሁም ፍላጎት ያላችሁ የኅብረተሰብ ክፍሎች ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የሚኒስቴሩ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ፤በአካል በመገኘት አስተያየት መስጠት እንደሚችሉ ጥሪ አስተላልፏል።
እንዲሁም በረቂቅ አዋጁ ላይ የጽሑፍ አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ አካላት፣ የአዋጁን ዝርዝር የድንጋጌዎች ረቂቅ (በአማርኛ ቅጂ) በገንዘብ ሚኒስቴር ድኅረ-ገጽ ላይ መመልከት እንደሚችሉና ያዘጋጁትን ዝርዝር አስተያየት እስከ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በኢሜይል አድራሻ መላክ እንደሚችሉ አስታውቋል

❤7👍3👏1
በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያውያን ሱቆች እየፈረሱ መሆኑ ተገለጸ‼
በደቡብ አፍሪካ መጤ አፍሪቃውያን ላይ ይደርስ የነበረው ጥቃት ጋብ ያለ ቢመስልም፣ “ህገ-ወጥ ግንባታ” በሚል ምክንያት የበርካታ ስደተኞች ሱቆች በፀጥታ ኃይሎች እየፈረሱባቸው መሆኑን በጆሃንስበርግ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለDW ገልፀዋል።
ድርጊቱን የገለጹ አንድ ነዋሪ “ነገሩ ሂድ አትበለው ግን እንዲሄድ አድርገው ነው” ሲሉ እርምጃው በስደተኞች ላይ ተጨማሪ እንግልት እየፈጠረ መሆኑን አስረድተዋል።
በደቡብ አፍሪካ ካሉ አነስተኛና መካከለኛ የሸቀጥ መደብሮች መካከል አብዛኞቹ የኢትዮጵያውያን መሆናቸው ይታወቃል።
እዚያው ትዳርና ልጆች መስርተው ከ10 እስከ 20 ዓመታት የኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለስ ቢፈልጉም፤ በአገር ቤት የመኖሪያ ቤት እና ለልጆቻቸው የትምህርት ቤት አቅርቦት ችግር ስጋት በመሆኑ አሁንም በደቡብ አፍሪካ ባለው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለመቆየት መገደዳቸውን ተናግረዋል።

❤16😢14👍2👀1
የአሜሪካ የነዳጅ ማደያዎች በኢራን ሃከሮች የሳይበር ጥቃት ተሰነዘረባቸው
በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች የነዳጅ መጠን መቆጣጠሪያ ስርዓቶች ላይ ለተሰነዘሩት ተከታታይ የሳይበር ጥቃቶች ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸው ሃከሮች ሳይሆኑ አይቀሩም ሲል CNN የሀገሪቱን ባለስልጣናት ጠቅሶ ዘግቧል።
ሃከሮቹ ጥቃቱን የፈጸሙት ያለ ምንም የይለፍ ቃል በቀጥታ ከኢንተርኔት ጋር የተገናኙ አውቶማቲክ የነዳጅ ታንከር መቆጣጠሪያዎችን በመጠቀም ነው። በዚህም ጥቃት በማደያዎቹ ስክሪን ላይ የሚታየውን የነዳጅ መጠን ንባብ ማዛባት የቻሉ ሲሆን፣ በትክክለኛው ታንከሮቹ ውስጥ ባለው የነዳጅ መጠን ላይም የተወሰነ ጉዳት አድርሰዋል።

👍13😁10❤9👏2🎉1
እስራኤል በጋዛ ከፍተኛውን የሃማስ የጦር አዛዥ ለመግደል በሃማስ ላይ ድብደባ ፈጸመች
የእስራኤል መከላከያ ኃይል (በጋዛ የሚገኘውን የሃማስ ወታደራዊ ክንፍ ዋና አዛዥ እና የድርጅቱ ቁልፍ መሪ የሆነውን ኢዝ አል-ዲን አል-ሃዳድን መግደል የታለመ የአየር ጥቃት መፈጸሙን በይፋ አስታወቆዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው በጋዛ ከተማ ሪማል በተባለ አካባቢ በሚገኝ የመኖሪያ ህንፃ ላይ መሆኑን የፍልስጤም ሚዲያዎች ዘግበዋል።
አል-ሃዳድ የኦክቶበር 7 ጥቃት ግንባር ቀደም አቀነባባሪ ከሆኑት መካከል አንዱ ሲሆን፣ የቀድሞ መሪዎች መገደላቸውን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት በጋዛ ውስጥ የሃማስ ወታደራዊ ክንፍ ቁጥር 1 መሪ ነው። እስከ አሁን 6 ጊዜ ከተሰነዘሩ የግድያ ሙከራዎች በማምለጡ "The Ghost" (መንፈሱ) በሚል ቅጽል ስም ይታወቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የመከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ በሰጡት የጋራ መግለጫ ጥቃቱን ትዕዛዝ መስጠታቸውን አረጋግጠዋል። መሪው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ የመሩትን የጦር መሳሪያ የመፍታት ስምምነት ውድቅ ማድረጉን ጠቅሰዋል።

❤16👍4😢2😡1