አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
416 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
UAE በኢራን ላይ በድብቅ ጥቃት ፈጸመች።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) በወሰደችው የአፀፋ እርምጃ በኢራን የነዳጅ ማጣሪያ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈጸሟ ተገልጿል።

በላቫን አይስላንድ የሚገኘው የነዳጅ ማጣሪያ በአቡዳቢ ጥቃት ከባድ ጉዳት አስተናግዷል ተብሏል።

አሜሪካ ዩኤኢ የአፀፋ እርምጃ መውሰዷን ማድነቋም ተመላክቷል።

ኢራን በጦርነቱ ከየትኛውም የገልፍ ሀገር በበለጠ ብዙ ጥቃት ያደረሰችው በአቡዳቢ ላይ መሆኑ ተገልጿል። #trtworld

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19👍8🤪3😢2👏1😁1🎉1👌1
አንጋፋዉ ጋዜጠኛ ወደ ቴሌግራም መጣ፡፡ መረጃዎችን ጎልጉሎ በማዉጣት እራስ ምታት ሆኖል ፡፡
ተቀላቀሉት Join👇👇
"በዚህ ሊንክ ግቡ 👇👇
https://t.me/darashMedia
https://t.me/darashMedia
3👍3
ትራምፕ ወደ ቻይና እየበረሩ ነው‼️
ዶናልድ ትራምፕ ወደ ቻይና አቀኑ።
ፕሬዝዳንቱ ወደ ቻይና ያቀኑት በዋናነት በኢራን፣በንግድ እንዲሁም በታይዋን ጉዳይ ለመምከር ሲሆን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከ10 አመታት በኋላ ወደ ቻይና የተጓዙ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነዋል።
ትራምፕ ከቻይና ጋር ከተወያዩ በኋላ በኢራን ላይ አዲስ ውሳኔ እንደሚወስኑ CNN ዘግቧል።
ቻይና የኢራን ዋነኛ አጋር መሆኗ ይታወቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12😁11👍2😱1🙉1😡1
በፖሊስ አባል ህይወቱ ለጠፋው ግለሰብ ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤትና የመሥሪያ ቦታ ተሰጠ

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በፖሊስ አባል ህይወቱ ያለፈው የአቶ ተገኝ ባልቻ ቤተሰቦች፣ ከአዲስ አበባ አስተዳደር የመኖሪያ ቤትና የመሥሪያ ቦታ ርክክብ ተደረገ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🌚40🤣2814🙉9👍7🤪5🤔3👏2😢2🥰1👌1
የአሜሪካ የፀሐይ ብርሃን ኃይል አምራቾች በኢትዮጵያ ላይ የንግድ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቁ

በአሜሪካ የሚገኙ የፀሐይ ብርሃን ኃይል አምራቾች፣ የቻይና ኩባንያዎች የአሜሪካን የታሪፍ ቀረጥ ለማምለጥ ምርቶቻቸውን በኢትዮጵያ በኩል እያሳለፉ ነው በሚል የንግድ ምርመራ እንዲደረግ ለፌዴራል ባለስልጣናት ጥያቄ ማቅረባቸው ታዉቋል።

ኩባንያዎቹ ለአሜሪካ የንግድ ሚኒስቴር ባስገቡት አቤቱታ፣ "ቶዮ"  እና "ኦሪጅን ሶላር ማንፋክቸሪንግ" የተባሉ የጃፓን ኩባንያዎች በቻይና የተሰሩ ግብዓቶችን በመጠቀም በኢትዮጵያ ውስጥ የሶላር ሴሎችን እንደሚያመርቱ ገልጸዋል። እነዚህም ምርቶች በኢትዮጵያ ወይም በቬትናም ተገጣጥመው ወደ አሜሪካ እንደሚላኩ ተጠቁሟል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2025 አጋማሽ ላይ የጀመረው የኢትዮጵያ የሶላር ምርቶች ወደ አሜሪካ የመላክ ሂደት፣ እስከ ዓመቱ መጨረሻ 300 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል። ይህም ኢትዮጵያን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰባተኛዋ ከፍተኛ የሶላር ምርት ወደ አሜሪካ ላኪ ሀገር አድርጓታል።

አቤቱታውን ካቀረቡት መካከል "ፈርስት ሶላር" እና የደቡብ ኮሪያው "ኪውሴልስ"  የሚገኙበት ሲሆን፣ ኩባንያዎቹ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር በአሜሪካ ፋብሪካዎች ላይ ኢንቨስት ማድረጋቸውንና ይህ "ህገ-ወጥ የታሪፍ ማምለጫ መንገድ" እድገታችንን ያደናቅፋል ሲሉ ተከራክረዋል።

አሜሪካ ከዚህ ቀደም መሰል እርምጃዎችን በቻይና፣ ማሌዢያ፣ ታይላንድ፣ ካምቦዲያ እና ቬትናም ምርቶች ላይ መውሰዷ ይታወሳል። የንግድ ሚኒስቴሩ የቀረበለትን አቤቱታ መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በኢያሱ ዘካሪያስ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21👍6
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪዲዮ‼️
በትናንትናው ዕለት ግንቦት 4/2018 ዓ.ም ከአሶሳ ወደ ግልገል በለስ ሲጓዙ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ በተፈፀመ ጥቃት ከ34 በላይ ሰዎች የሞቱበት፣ከ50 በላይ የቆሰሉ(15 ከባድ ቁስለኛ) የሆኑበት ጥቃት ቪዲዮ ከላይ ተያይዟል።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢47💔86👍5🕊2🤔1🤯1😱1👀1🙉1
የማስታወቂያ ግብዣ

የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል
Youtube ቻናል …
የትምህርት ተቋማት…...
የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
የትራንስፖርት አገልግሎት…....
ኤጀንሲዎች……
ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot
6🤣3👍2👌1🤝1
Update‼️
ወደ ቤታቸው በሰላም ተመልሰዋል!
ከትናንት በስቲያ ግንቦት 03/2018 ዓ.ም ምሽት ላይ በመቀሌ ከተማ 'ዲያስፖራ' ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ታፍነው ተወስደው የነበሩት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ዶ/ር ገብሩ ካህሳይ፣ አሁን ላይ በሰላም ተለቀው ወደ ቤታቸው መመለሳቸው ተረጋግጧል።
ዶ/ር ገብሩ ካህሳይ በማህበራዊ ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት "ተፈቲሐ እዚ ዓደይ እትየ!" (ተፈትቼ ወደ ቤቴ ገብቻለሁ) በማለት መለቀቃቸውን አብስረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍6😁3👏1🤔1
የባንክ ሂሳብን ከፋይዳ ቁጥር ጋር ለማስተሳሰር የተሰጠው የጊዜ ገደብ ነገ ይጠናቀቃል

አዲስ አበባን ጨምሮ በ27 ዋና ዋና ከተሞች ለሚገኙ የባንክ ደንበኞች የባንክ ሂሳባቸው ከፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ቁጥራቸው ጋር የሚያስተሳስሩበት የጊዜ ቀነ ገደብ ነገ ግንቦት 6 ቀን 2018 እንደሚጠናቀቅ መገለፁ ይታወሳል።

ደንበኞች ካሉበት ሆነው id.et/connect ማስፈንጠሪያን በመጠቀም ፋይዳ መታወቂያን ከባንክ ጋር ማስተሳሰር እንደሚችሉም ተመላክቷል።

እስከ ነገ ድረስ አካውንታቸውን ያላስተሳሰሩ ደንበኞች የባንክ ሂሳባቸው እንዲዘጋ ወይም እንዳይንቀሳቀስ የሚደረግ ቢሆንም ሂሳባቸው የተዘጋባቸው ደንበኞች ወደ ባንክ በመቅረብ የማስተሳሰር ሂደቱን በማከናወን ሂሳባቸውን መልሰው ማንቀሳቀስ እንደሚችሉም ነው የተጠቆመው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍7
የኢራን የሚሳኤል መሠረት ልማቶች 10% ብቻ በአሜሪካ ጥቃቶች እንደወደሙ ተዘገበ።
የቀሩት 90% የሚሆኑት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሚሰሩ ሲሆኑ ምናልባትም በአየር ድብደባ ብቻ ከጥቅም ውጪ ለማድረግ አስቸጋሪ እንደሆኑ NYT ዘግቧል።
የኢራን የሚሳኤል መሠረተ ልማት በትራምፕ ውጊያ ጉዳት አላስተናገደም ማለት ይቻላል።
አሜሪካ የእግረኛ ጦር ካላሰማራች ወይም ሌላ መሳሪያ ካልተጠቀመች በስተቀር የኢራንን የሚሳኤል ተቋማት ለማውደም አስቸጋሪ እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21👍12😢4👏2😁1
መረጃ‼️

የአሜሪካ የመከላከያና የንግድ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት በኢትዮጵያ ላይ የተጣለውን ጥብቅ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማዕቀብ አነሳ።

ዳይሬክቶሬቱ፣ ከትናንት ጀምሮ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት፣ ፖሊስ እና የጸጥታ ኃይሎች ጦር መሳሪያ የተናጥል የግዥ ጥያቄዎች እየተገመገሙ እንደሚሆን ገልጧል።

ተቋሙ፣ በቅርቡ በሚያወጣው ኢትዮጵያን የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማዕቀብ ከተጣለባቸው አገራት ዝርዝር በቅርቡ እንደሚሠርዝም አስታውቋል።

የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በኢትዮጵያ ላይ የጦር መሣሪያ ሽያጭ ማዕቀብ መጣሉ አይዘነጋም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17👍2😢2🍾1
ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ የ54.6 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ድጋፍ አገኘች

ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ መንግሥት ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ማካሄዷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ በዚሁ ወቅት በሁለቱ ሀገራት መካከል ቁልፍ ስምምነቶች ተፈራርመዋል።

ከስምምነቶቹ መካከል በዋናነት የሚጠቀሰው የታዳሽ፣ የተቀናጀ እና ዘላቂ ኃይል እንዲሁም የዲጂታላይዜሽን ፕሮግራሞችን ለመተግበር የሚውል የ54.6 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት ነው።

ይህ የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ የኢነርጂ ዘርፍ ልማት እና በዲጂታል ሽግግር ላይ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል።

በተጨማሪም፣ በሁለቱ መሪዎች የጋራ መሪነት የ150 ሜጋ ዋት የጂኦተርማል ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን የሚመለከት የመንግሥትና የግል አጋርነት (PPP) አዲስ የማዕቀፍ እና የፍኖተ ካርታ ልውውጥ መካሄዱ ተጠቁሟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16😡14😁4😱4👍2👀2👏1🤪1🙊1
ኩዬት በኢራን ላይ ጥቃት‼️
ኩዌት የኢራንን ጀልባ በማጥቃት 4 ኢራናውያንን በፋርስ ባህረ ሰላጤ አስራለች ስትል ከሰሰች።
ለዚህ ጥቃት 'መልስ የመስጠት መብታችን የተጠበቀ ነው' - ሲሉ የኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍5👏2😡2🎉1🤣1🤪1
አንጋፋዉ ጋዜጠኛ ወደ ቴሌግራም መጣ፡፡ መረጃዎችን ጎልጉሎ በማዉጣት እራስ ምታት ሆኖል ፡፡
ተቀላቀሉት Join👇👇
"በዚህ ሊንክ ግቡ 👇👇
https://t.me/darashMedia
https://t.me/darashMedia
👍6😡21🌚1
#Grade12
#NationalExam

ከመጪው ሰኔ 24/2018 ዓ/ም ጀምሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ ተፈታኞች የተዘጋጀ የመፈተኛ ክፍል መግቢያ ካርድ (Admission Card) በፈተና አስተዳደር ሲስተም (https://exam.eaes.et/) ከ03/09/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለክልል ትምህርት ቢሮ፣ ለዞን ትምህርት መምሪያዎች እና ለትምህርት ቤት ተወካዮች መለቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

አገልግሎት መ/ቤቱ ፦

1. እያንዳንዱ ተፈታኝ ተማሪ በአድሚሽን ካርዱ ጀርባ ላይ የትምህርት  ቤቱን ወይም የወረዳው አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ማህተም የተደረገበትን አድሚሽን ካርድ ከትምህርት ቤቱ ወስዶ በእጁ መያዝ መያዝ እንዳለበት አሳስቧል።

2. በምዝገባ ወቅት በተፈታኙ ወይም በመዝጋቢው የተከሰተ የትምህርት መስክ ፣ የጾታ ፣ የፎቶ እና መሰል ማስተካከያዎች ካሉ ከግንቦት 30/2018 ዓ.ም በፊት ለትምህርት ቤቱ ማሳወቅና ሂደቱን ጠብቆ መስተካከሉንም ከትምህርት ቤቱ ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጿል።

3. እያንዳንዱ ተፈታኝ አድሚሽን ካርዱን ወደ መፈተኛ ማዕከል ሆነ መፈተኛ ክፍል ለመግባት የሚጠቀምበት በመሆኑ በአግባቡና በጥንቃቄ እንዲይዝ አሳስቧል።

4. ተፈታኞች ፈተና ላይ ከአድሚሽን ካርድ በተጨማሪ የፋይዳ መታወቂያ መያዝ እንደሚጠበቅባቸው ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍3🤪2👏1🤔1
የጤና መረጃ፡ የሃንታ ቫይረስ ስርጭት እና የዓለም ጤና ድርጅት ስጋት

በአሁኑ ሰዓት "ኤምቪ ሆንድየስ" (MV Hondius) በተሰኘች የቱሪስት መርከብ ላይ የተከሰተው የሃንታ ቫይረስ ስርጭት ዓለም አቀፍ ትኩረትን ስቧል።

ቫይረሱ በፈረንሳይ፣ ስፔን እና አሜሪካ በሚገኙ ተጓዦች ላይ እየታየ ሲሆን፣ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተለ ይገኛል።

ዋናው ስርጭት የተከሰተው በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ በነበረችው MV Hondius በተባለች የደች (Dutch) መርከብ ላይ ነው።

ከመግለጫው ጀምሮ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ጀርመን፣ ስዊዘርላንድ እና አሜሪካ ውስጥ በሚገኙ ሆስፒታሎች ክትትል እየተደረገላቸው ነው።

እስከ አሁን ድረስ በመርከቧ ላይ በነበሩ 3 ሰዎች ላይ የሞት አደጋ ደርሷል።

እስካሁን በኢትዮጵያም ሆነ በጎረቤት አገራት የተመዘገበ ስርጭት የለም። ነገር ግን ቫይረሱ ከአይጥ ወደ ሰው የሚተላለፍ በመሆኑ ጥንቃቄ አስፈላጊ ነው።

ቫይረሱ እንዴት ይተላለፋል?

ይህ ቫይረስ በዋነኝነት የሚተላለፈው በአይጥ ዝርያዎች ሲሆን፦

1. በአይጥ ንክሻ ወይም አይጦች በነኩት ምግብ።

2. የአይጥ ሽንት ወይም ቆሻሻ ያለበትን አቧራ በመተንፈስ።

3. አሁን የተከሰተው "የአንዴስ" (Andes virus) ዝርያ በጣም አልፎ አልፎ ከሰው ወደ ሰው ሊተላለፍ እንደሚችል ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ።

ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

* ከፍተኛ ትኩሳት እና ብርድ ብርድ ማለት

* ከባድ የጡንቻ እና የራስ ምታት

* የመተንፈስ ችግር (ሳንባ ላይ ውሃ በመቋጠር)

* ማቅለሽለሽ እና ተቅማጥ

ራስዎን እንዴት ይጠብቁ?

* መኖሪያ ቤትዎን እና የስራ አካባቢዎን ከአይጥ ንክኪ ነጻ ያድርጉ።

* ቆሻሻዎችን በአግባቡ ያስወግዱ።

* ምግብዎን በደንብ ሸፍነው ያስቀምጡ።

* አይጥ ያለባቸውን ቦታዎች ሲያጸዱ የአፍና አፍንጫ ማስገጃ (Mask) እና ጓንት ይጠቀሙ።

ቫይረሱ በአሁኑ ሰዓት እንደ ኮቪድ-19 አይነት የጎላ ስርጭት ባይኖረውም፣ የታየባቸው ሰዎች ላይ ግን እስከ 50% የሞት አደጋ ሊያደርስ ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።

ይህንን መረጃ ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የበኩዎን ይወጡ!

Via WHO

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
34👍6🥰1👏1🎉1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ትራምፕ ወደ ቻይና ባቀኑበት ወቅት የተሳፈሩበት AIR FORCE 1አውሮፕላን ቤጂንግ ሲደርስ በተደረገ የአቀባበል ላይ አንድ ቻይናዊ ወታደር Air force 1 የሚያወጣው ከፍተኛ የሚረብሽ ድምፅ ሳይበግራቸው አንድም እንቅስቃሴ ሳያደርጉ ብቻቸውን ፀንተው የቆሙበት መንገድ የአለም አቀፍ ሚዲያዎችን ትኩረት ከሳቡ የሳምንቱ አንድ ክስተት ሆኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🫡2719👍9👏2🥰1
ወደ ፌደራል ፖሊስ መሄደ ቀረ‼️
ከዛሬ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ለሥራ ለመሰማራት የወንጀል ነጻ ሠርቲፊኬት የሚፈልጉ ተገልጋዮች በአካል አዲስ አበባ በሚገኘው ፎሬንሲክ ወንጃል ምርመራ አሻራ ምርመራ ዋና ክፈል መምጣት እንደማያስፈልጋቸው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አሳወቀ።

ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ለሥራ ለመሰማራት የወንጀል ነጻ ሠርቲፊኬት የሚፈልጉ በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በተዘጋጁ ማዕከላት አማካኝነት በየአካባቢያቸው በሚገኙና በሚልኳሸው ኤጀንሲዎች በኩል አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍246👏2🥰1👌1
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በህ-ወጥ መንገድ ለገበያ ሊቀርብ የተዘጋጀ ስጋ ተያዘ

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በወረዳ 11 ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት በተካሄደው ድንገተኛ ኦፕሬሽን በድብቅ የታረደና ለገበያ ሊቀርብ የነበረ ከፍተኛ መጠን ያለው የእንስሳት ስጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተገለፀ።
 
​ኦፕሬሽኑ የተካሄደው በወረዳ 11 ልዩ ቦታው ቀጠና 01 "ሰው ለሰው እድር ቤት" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን፣ ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በተደረገ ጥብቅ ፍተሻ ጤንነታቸው ያልተረጋገጡ 13 የታረዱ በጎች፣ 14 ፍየሎች እንዲሁም ፅዳቱ ያልተጠበቀ 312 ኪሎ ግራም ስጋ ተይዟል።
 
​የወረዳው የደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተክሉ ምንዳ እንደገለጹት የተያዘው ስጋ እንዲወገድ ለአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተረከበ ሲሆን ድርጊቱን የፈጸሙ ግለሰቦችም በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል።
 
ኃላፊው አክለውም ህብረተሰቡ መሰል ህገ-ወጥ እርዶችንም ሆነ ማንኛውንም የደንብ መተላለፍ ሲመለከት በነፃ ስልክ መስመር 9995 ጥቆማ በመስጠት ከተቋሙ ጎን እንዲቆም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23👍9😢6🙉3👏1😁1🎉1