1 ሺህ 139 የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኞች በስነምግባር ጥሰት ተቀጡ‼️
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት 9 ወራት የብልሹ አሰራርና ስነ ምግባር ጥሰት በፈፀሙ 1 ሺህ 139 የአገልግሎቱ ሠራተኞች ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃ ወሰደ፡፡
እርምጃ ከተወሰደባቸው ኃላፊዎችና ሠራተኞች መካከል 16 ሲሰናበቱ፤ 721 የደሞዝ ቅጣት የተቀጡ እንዲሁም 402 የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ናቸው፡፡
አገልግሎቱ በ1 ሺህ 139 ሠራተኞች ላይ ከወሰዳቸው አስተዳደራዊ እርምጃዎች መካከል 103 ሠራተኞች ላይ በደንበኞች የቀረበን ጥቆማ በመመርመር የወሰደው ነው፡፡ ቀሪ 1 ሺህ 36ቱ ተቋሙ በራሱ ግኝት አጣርቶ የወሰዳቸው እርምጃዎች ናቸው፡፡
ባለፉት ዘጠኝ ወራት አገልግሎቱ በሙስና መጠቆሚያ ዘመናዊ መተግበሪያ (Corruption Reporting App) እና በሌሎች አማራጮች ከደንበኞቹ የደረሱትን 427 ጥቆማዎችን መርምሮ በ103 ኃላፊዎችና ሠራተኞች ላይ የተለያዩ እርምጃዎችን ወስዷል፡፡
በደንበኞቹ በቀረቡት ጥቆማዎች መሰረት 14 የፅሁፍ፣ 80 የደሞዝ ቅጣት፣ 2 ከቦታ የማንሳትና 7 ስንብት በድምሩ 103 እርምጃዎች ተወስዷል፡፡
ይህም የጥቆማ መቀበያ ስርዓቱ የፈጠረው ምቹ ሁኔታ፣ ደንበኞች የሚሰጡት ጥቆማ ዋጋ ያለው መሆኑንና የሚታዩ ብልሹ አሰራርን ለመታገል አገልግሎቱ እያደረገ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው፡፡
የብልሹ አሰራር ጥቆማ ከቀረበባቸው ጉዳዮች መካከል የአዲስ ቆጣሪ ጥያቄ፣ የኃይል መቆራረጥና አስቸኳይ ጥገና፣ የቆጣሪ ንባብና የቢል ስብሰባ እንዲሁም ንብረት አያያዝና አጠቃቀም ይገኙበታል፡፡
ደንበኞች አሁንም የዲጂታል የብልሹ አሰራር ጥቆማ መቀበያ (www.eeuethics.et) በመጠቀም በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚታዩ የሙስናና ብልሹ አሰራር ችግሮችን እንዲጠቁሙ አገልግሎቱ ያበረታታል፡፡
አገልግሎቱም ማንኛውም የህግና የሥነምግባር ጥሰት ድርጊቶችን ለሚያጋልጡ ጠቋሚዎች እውቅና የሚሰጥ ሲሆን፤ ተገቢውን ጥበቃ በማድረግ በነፃነትና በተነሳሽነት የሙስና ወንጀሎችን እንዲያጋልጡ የማበረታታና ምቹ ሁኔታዎችን የሚፍጠር መሆኑን ይገልፃል፡፡
ደንበኞች በወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699/2003 መሰረት ህጋዊ ከለላ የማግኘት መብታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በአገልግሎቱ አሰራርና መመሪያ መሰረት ጠቋሚዎች የሚያቀርቡት ህጋዊ ጥያቄ ያለተጽዕኖ እንዲስተናገዱ ተገቢውን ከለላና ጥበቃ ይሰጣል፡፡
@Addis_Reporter

❤17👍9💯2🥰1
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ልምምድ ላይ በገጠማት ድንገተኛ ህመም ሕይወቷ አለፈ
ባለትዳርና የሁለት ልጆች እናቷ አትሌት የብርጓል መለሰ፤ ዛሬ ማለዳ ልምምዷን እየሠራች ባለችበት ወቅት ህመም ተሰምቷት ለህክምና በሄደችበት ሆስፒታል በሞት እንደተለየች ተሰምቷል፡፡
የ36 ዓመቷ የብርጓል የፓሪስ ግማሽ ማራቶንን ሁለት ጊዜ፣ ሊዝበን ግማሽ ማራቶንን አንድ ጊዜ እንዲሁም የሻንጋይ፣ ፕራግና ሂውስተን ማራቶንን በበላይነት አጠናቃለች፡፡
በ2015ቱ የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በግማሽ ማራቶን ለኢትዮጵያ የነሀስ ሜዳሊያ አስገኝታለች፡፡

💔41😢20❤8😱4👍2
አፍሪካ ካልተሳካላት አውሮፓ ተስፋ የላትም! - ማክሮን
የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አፍሪካን በሚመለከት ባደረጉት ንግግር፣ የአውሮፓና የአፍሪካ ዕጣ ፈንታ የማይነጣጠል መሆኑን በግልጽ አስታወቁ።
ፕሬዝዳንቱ አፍሪካን "ምን ማድረግ እንዳለባት" ለመንገር አለመምጣታቸውን ገልጸው፣ የአፍሪካ ስኬትም ሆነ ውድቀት የአውሮፓም ጭምር መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
"አፍሪካ ከወደቀች አውሮፓ ምንም ዕድል አይኖራትም፤ በመከራና በሁከት ትዋጣለች" በማለት፣ የአህጉሪቱ መረጋጋት ለአለም ሰላም ያለውን ወሳኝነት አመላክተዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ ስለ አውሮፓ የቅኝ ግዛት ታሪክ እውነቱን ከመናገር ወደኋላ አላሉም።
"የአውሮፓ ቅኝ ግዛት ወንጀሎች የማይካዱ ናቸው" በማለት፣ በታሪክ የተፈጸሙ ስህተቶችንና አስከፊ እውነታዎችን በይፋ አምነዋል።
እርሳቸው የሚወክሉት ትውልድ ቅኝ ግዛት በሌለበት ወቅት የተወለደ መሆኑን የጠቀሱት ማክሮን፣ ንግግራቸው ለትምህርት ሳይሆን ለወደፊት አብሮነትና አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ ንግግር አውሮፓ ከአፍሪካ ጋር ያላትን የቀድሞ የጌታና የሎሌ ግንኙነት ወደ እኩልነት ለመቀየር ያላትን ፍላጎት የሚያሳይ ሆኖ ተወስዷል።

🤪24❤17😡5👍2😁1
የ6 ዓመት ታዳጊን በማገት ገንዘብ ሲቀበሉ የተያዙ ሁለት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ
በሁለት ግለሰቦች ታግቶ የነበረውን የ6 ዓመት ታዳጊ ልጅ ከነ አጋቾቹ በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን የዲላ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።ተከሳሾቹ ሲሆኑ ጌቱ ገረመው እና እንዳሻው በቀለ የተባሉ ናቸው።
የ6 ዓመት ታዳጊ የሆነውን ብሩክ ወ/ኪዳነ የተባለ ሲሆን ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ/ም ከዲላ ከተማ ሴሳ ክ/ከተማ ቡኖ ቀበሌ ካለው መኖርያ ቤት ወጥቶ ሳይመለስ በመቅረቱ ቤተሰቦቹ ፈለጋ ላይ እያሉ ተከሳሽ የሆነው ጌቱ ገረመው ስልክ በመደወል ልጃችሁ ለማግኘት 80 ሺህ ብር በባንክ ይግባልን ይላል።የታጋች ወላጆች የተጠየቁትን ገንዘብ ለፖሊስ በማሳወቅ ገቢ ይደረጋል። ከሰዓታት በኋላ ተከሳሽ ጌቱ ገረመው ባንክ በመሄድ 50 ሺህ ብር ወጪ አድርጎ ሲወጣ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል።
ፖሊስም 48 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ህፃኑ የተደበቀበትን ስፍራ በማወቅ ሁለተኛ ተከሳሽን በቁጥጥር ስር በማዋል የታገተውን የ6 ዓመት ታዳጊውን ለቤተሰብ ማስረከቡን ተገልጿል:: በዚህም ተከሳሾቹ ላይ የወንጀል ምርመራ አጠናክሮ የቀጠለው የዲላ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከዐ/ህግ ጋር ባደረገው የጋራ ጥምረት ክስ መስርቷል፡፡
ክሱን የተመለከተዉ የዲላ ከተማ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ በ12 ዓመት እና ሁለተኛ ተከሳሽን ደግሞ በ9 ዓመት ጽኑ እስራት እንድቀጡ ወሳኔ መተላለፉን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ሀይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በሳምራዊት ስዩም

❤18👏5👍4
"በሳዑዲ በሞት ጥላ ሥር ላሉ ኢትዮጵያውያን ምሕረት እንዲደረግ እንጠይቃለን" - አቡነ ማትያስ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሊክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በሳዑዲ ዓረቢያ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ወገኖችን በማስመልከት ጥሪ አስተላለፉ።
የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳዑዲ ባለሥልጣናት ጋር በከፍተኛ ደረጃ ተነጋግሮ የሞት ፍርዱ እንዲነሳና ወገኖቻችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥም አሳስበዋል።

❤64👍9🤪9😢1😍1
UAE በኢራን ላይ በድብቅ ጥቃት ፈጸመች።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) በወሰደችው የአፀፋ እርምጃ በኢራን የነዳጅ ማጣሪያ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈጸሟ ተገልጿል።
በላቫን አይስላንድ የሚገኘው የነዳጅ ማጣሪያ በአቡዳቢ ጥቃት ከባድ ጉዳት አስተናግዷል ተብሏል።
አሜሪካ ዩኤኢ የአፀፋ እርምጃ መውሰዷን ማድነቋም ተመላክቷል።
ኢራን በጦርነቱ ከየትኛውም የገልፍ ሀገር በበለጠ ብዙ ጥቃት ያደረሰችው በአቡዳቢ ላይ መሆኑ ተገልጿል። #trtworld

❤19👍8🤪3😢2👏1😁1🎉1👌1
አንጋፋዉ ጋዜጠኛ ወደ ቴሌግራም መጣ፡፡ መረጃዎችን ጎልጉሎ በማዉጣት እራስ ምታት ሆኖል ፡፡
ተቀላቀሉት Join👇👇
"በዚህ ሊንክ ግቡ 👇👇
https://t.me/darashMedia
https://t.me/darashMedia
ተቀላቀሉት Join👇👇
"በዚህ ሊንክ ግቡ 👇👇
https://t.me/darashMedia
https://t.me/darashMedia
❤3👍3
ትራምፕ ወደ ቻይና እየበረሩ ነው‼️
ዶናልድ ትራምፕ ወደ ቻይና አቀኑ።
ፕሬዝዳንቱ ወደ ቻይና ያቀኑት በዋናነት በኢራን፣በንግድ እንዲሁም በታይዋን ጉዳይ ለመምከር ሲሆን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከ10 አመታት በኋላ ወደ ቻይና የተጓዙ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነዋል።
ትራምፕ ከቻይና ጋር ከተወያዩ በኋላ በኢራን ላይ አዲስ ውሳኔ እንደሚወስኑ CNN ዘግቧል።
ቻይና የኢራን ዋነኛ አጋር መሆኗ ይታወቃል።

❤12😁11👍2😱1🙉1😡1
በፖሊስ አባል ህይወቱ ለጠፋው ግለሰብ ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤትና የመሥሪያ ቦታ ተሰጠ
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በፖሊስ አባል ህይወቱ ያለፈው የአቶ ተገኝ ባልቻ ቤተሰቦች፣ ከአዲስ አበባ አስተዳደር የመኖሪያ ቤትና የመሥሪያ ቦታ ርክክብ ተደረገ።

🌚40🤣28❤14🙉9👍7🤪5🤔3👏2😢2🥰1👌1
የአሜሪካ የፀሐይ ብርሃን ኃይል አምራቾች በኢትዮጵያ ላይ የንግድ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቁ
በአሜሪካ የሚገኙ የፀሐይ ብርሃን ኃይል አምራቾች፣ የቻይና ኩባንያዎች የአሜሪካን የታሪፍ ቀረጥ ለማምለጥ ምርቶቻቸውን በኢትዮጵያ በኩል እያሳለፉ ነው በሚል የንግድ ምርመራ እንዲደረግ ለፌዴራል ባለስልጣናት ጥያቄ ማቅረባቸው ታዉቋል።
ኩባንያዎቹ ለአሜሪካ የንግድ ሚኒስቴር ባስገቡት አቤቱታ፣ "ቶዮ" እና "ኦሪጅን ሶላር ማንፋክቸሪንግ" የተባሉ የጃፓን ኩባንያዎች በቻይና የተሰሩ ግብዓቶችን በመጠቀም በኢትዮጵያ ውስጥ የሶላር ሴሎችን እንደሚያመርቱ ገልጸዋል። እነዚህም ምርቶች በኢትዮጵያ ወይም በቬትናም ተገጣጥመው ወደ አሜሪካ እንደሚላኩ ተጠቁሟል።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2025 አጋማሽ ላይ የጀመረው የኢትዮጵያ የሶላር ምርቶች ወደ አሜሪካ የመላክ ሂደት፣ እስከ ዓመቱ መጨረሻ 300 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል። ይህም ኢትዮጵያን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰባተኛዋ ከፍተኛ የሶላር ምርት ወደ አሜሪካ ላኪ ሀገር አድርጓታል።
አቤቱታውን ካቀረቡት መካከል "ፈርስት ሶላር" እና የደቡብ ኮሪያው "ኪውሴልስ" የሚገኙበት ሲሆን፣ ኩባንያዎቹ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር በአሜሪካ ፋብሪካዎች ላይ ኢንቨስት ማድረጋቸውንና ይህ "ህገ-ወጥ የታሪፍ ማምለጫ መንገድ" እድገታችንን ያደናቅፋል ሲሉ ተከራክረዋል።
አሜሪካ ከዚህ ቀደም መሰል እርምጃዎችን በቻይና፣ ማሌዢያ፣ ታይላንድ፣ ካምቦዲያ እና ቬትናም ምርቶች ላይ መውሰዷ ይታወሳል። የንግድ ሚኒስቴሩ የቀረበለትን አቤቱታ መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
በኢያሱ ዘካሪያስ

❤21👍6
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪዲዮ‼️
በትናንትናው ዕለት ግንቦት 4/2018 ዓ.ም ከአሶሳ ወደ ግልገል በለስ ሲጓዙ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ በተፈፀመ ጥቃት ከ34 በላይ ሰዎች የሞቱበት፣ከ50 በላይ የቆሰሉ(15 ከባድ ቁስለኛ) የሆኑበት ጥቃት ቪዲዮ ከላይ ተያይዟል።
Via : አዩዘሀበሻ

😢47💔8❤6👍5🕊2🤔1🤯1😱1👀1🙉1
የማስታወቂያ ግብዣ
የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ36,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል‼
✔Youtube ቻናል …
✔የትምህርት ተቋማት…...
✔የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
✔የትራንስፖርት አገልግሎት…....
✔ኤጀንሲዎች……
✔ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
✔ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot

❤6🤣3👍2👌1🤝1
Update‼️
ወደ ቤታቸው በሰላም ተመልሰዋል!
ከትናንት በስቲያ ግንቦት 03/2018 ዓ.ም ምሽት ላይ በመቀሌ ከተማ 'ዲያስፖራ' ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ታፍነው ተወስደው የነበሩት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ዶ/ር ገብሩ ካህሳይ፣ አሁን ላይ በሰላም ተለቀው ወደ ቤታቸው መመለሳቸው ተረጋግጧል።
ዶ/ር ገብሩ ካህሳይ በማህበራዊ ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት "ተፈቲሐ እዚ ዓደይ እትየ!" (ተፈትቼ ወደ ቤቴ ገብቻለሁ) በማለት መለቀቃቸውን አብስረዋል።

❤9👍6😁3👏1🤔1
የባንክ ሂሳብን ከፋይዳ ቁጥር ጋር ለማስተሳሰር የተሰጠው የጊዜ ገደብ ነገ ይጠናቀቃል
አዲስ አበባን ጨምሮ በ27 ዋና ዋና ከተሞች ለሚገኙ የባንክ ደንበኞች የባንክ ሂሳባቸው ከፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ቁጥራቸው ጋር የሚያስተሳስሩበት የጊዜ ቀነ ገደብ ነገ ግንቦት 6 ቀን 2018 እንደሚጠናቀቅ መገለፁ ይታወሳል።
ደንበኞች ካሉበት ሆነው id.et/connect ማስፈንጠሪያን በመጠቀም ፋይዳ መታወቂያን ከባንክ ጋር ማስተሳሰር እንደሚችሉም ተመላክቷል።
እስከ ነገ ድረስ አካውንታቸውን ያላስተሳሰሩ ደንበኞች የባንክ ሂሳባቸው እንዲዘጋ ወይም እንዳይንቀሳቀስ የሚደረግ ቢሆንም ሂሳባቸው የተዘጋባቸው ደንበኞች ወደ ባንክ በመቅረብ የማስተሳሰር ሂደቱን በማከናወን ሂሳባቸውን መልሰው ማንቀሳቀስ እንደሚችሉም ነው የተጠቆመው።

❤10👍7
የኢራን የሚሳኤል መሠረት ልማቶች 10% ብቻ በአሜሪካ ጥቃቶች እንደወደሙ ተዘገበ።
የቀሩት 90% የሚሆኑት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሚሰሩ ሲሆኑ ምናልባትም በአየር ድብደባ ብቻ ከጥቅም ውጪ ለማድረግ አስቸጋሪ እንደሆኑ NYT ዘግቧል።
የኢራን የሚሳኤል መሠረተ ልማት በትራምፕ ውጊያ ጉዳት አላስተናገደም ማለት ይቻላል።
አሜሪካ የእግረኛ ጦር ካላሰማራች ወይም ሌላ መሳሪያ ካልተጠቀመች በስተቀር የኢራንን የሚሳኤል ተቋማት ለማውደም አስቸጋሪ እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል።

❤21👍12😢4👏2😁1
መረጃ‼️
የአሜሪካ የመከላከያና የንግድ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት በኢትዮጵያ ላይ የተጣለውን ጥብቅ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማዕቀብ አነሳ።
ዳይሬክቶሬቱ፣ ከትናንት ጀምሮ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት፣ ፖሊስ እና የጸጥታ ኃይሎች ጦር መሳሪያ የተናጥል የግዥ ጥያቄዎች እየተገመገሙ እንደሚሆን ገልጧል።
ተቋሙ፣ በቅርቡ በሚያወጣው ኢትዮጵያን የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማዕቀብ ከተጣለባቸው አገራት ዝርዝር በቅርቡ እንደሚሠርዝም አስታውቋል።
የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በኢትዮጵያ ላይ የጦር መሣሪያ ሽያጭ ማዕቀብ መጣሉ አይዘነጋም።

❤17👍2😢2🍾1
ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ የ54.6 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ድጋፍ አገኘች
ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ መንግሥት ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ማካሄዷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ በዚሁ ወቅት በሁለቱ ሀገራት መካከል ቁልፍ ስምምነቶች ተፈራርመዋል።
ከስምምነቶቹ መካከል በዋናነት የሚጠቀሰው የታዳሽ፣ የተቀናጀ እና ዘላቂ ኃይል እንዲሁም የዲጂታላይዜሽን ፕሮግራሞችን ለመተግበር የሚውል የ54.6 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት ነው።
ይህ የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ የኢነርጂ ዘርፍ ልማት እና በዲጂታል ሽግግር ላይ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል።
በተጨማሪም፣ በሁለቱ መሪዎች የጋራ መሪነት የ150 ሜጋ ዋት የጂኦተርማል ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን የሚመለከት የመንግሥትና የግል አጋርነት (PPP) አዲስ የማዕቀፍ እና የፍኖተ ካርታ ልውውጥ መካሄዱ ተጠቁሟል።

❤16😡14😁4😱4👍2👀2👏1🤪1🙊1