አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17.1K photos
418 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ቴዲ አፍሮ ለ3ኛ ሳምንት የኢትዮጵያን የሙዚቃ ገበታ ተቆጣጠረ

በሳምንቱ በዩቲዩብ ከፍተኛ ተመልካች ያገኙ 10 የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች ዝርዝር ይፋ ሲሆን፣ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ከአንደኛ እስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ ሙሉ በሙሉ በመያዝ አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል።

​የሙዚቃ መረጃዎችን ተንትኖ ደረጃ የሚያወጣው “የኔ ቫይብ” (YeneVibe) ሚያዝያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው ሳምንታዊ መረጃ መሰረት፣ የቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም ስራዎች በሳምንቱ ውስጥ ብቻ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አዳዲስ ተመልካቾችን በማግኘት የገበታውን አናት ተቆጣጥረውታል። ይህ ደረጃ የወጣው ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ አውቶማቲክ አሰራር ሲሆን፣ መለኪያውም ሙዚቃዎቹ በሳምንቱ ውስጥ በዩቲዩብ ላይ የጨመሩት የተመልካች ብዛት (New Views) ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

​በደረጃው መሰረት “ዳስ ጣል (አንሳው)” የተሰኘው ስራ በሳምንት ውስጥ ከ2.8 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ተመልካቾችን በማግኘት በአንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በአጠቃላይ በሳምንቱ ምርጥ አስር ውስጥ የገቡት የቴዲ አፍሮ ስራዎች ብቻ መሆናቸው የአልበሙን ከፍተኛ ተቀባይነት የሚያሳይ ሲሆን፣ ይህም በኢትዮጵያ የዲጂታል ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ስኬት ሆኖ ተመዝግቧል።

​በሳምንቱ ከፍተኛ ተመልካች ያገኙ ምርጥ 10 ሙዚቃዎች ዝርዝር፦
1ኛ ​ዳስ ጣል (አንሳው) – ቴዲ አፍሮ (+2,846,156 አዲስ እይታ)
2ኛ ​ሺ ቢባል (ወደ 90ዎቹ) – ቴዲ አፍሮ (+2,269,028 አዲስ እይታ)
3ኛ ​ዝ ፀዳል – ቴዲ አፍሮ (+1,933,851 አዲስ እይታ)
4ኛ ​ስምምነን (ጉሬጌ) – ቴዲ አፍሮ (+1,790,725 አዲስ እይታ)
5ኛ ​መርከብ – ቴዲ አፍሮ (+1,282,541 አዲስ እይታ)
6ኛ ​ታየኝ – ቴዲ አፍሮ (+1,278,335 አዲስ እይታ)
7ኛ ​ጽዮን ሙሽራዬ – ቴዲ አፍሮ (+1,171,738 አዲስ እይታ)
8ኛ ​ብልጭታ – ቴዲ አፍሮ (+1,126,840 አዲስ እይታ)
9ኛ ​ተወዳጅ – ቴዲ አፍሮ (+851,045 አዲስ እይታ)
10ኛ ​ጀምበር – ቴዲ አፍሮ (+755,029 አዲስ እይታ)

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
60👍14👌5🥰1👏1
የሰው ልጅ አእምሮ መረጃን የማከማቸት አቅሙ በዲጂታል መለኪያ ሲሰላ እስከ 2.5 ፔታባይት (Petabytes) ይደርሳል። ይህ ማለት ምን ማለት መሰለህ? አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ ለ300 ዓመታት ያለማቋረጥ የሚያስተላልፈውን ከፍተኛ ጥራት ያለው (HD) ቪዲዮ በአንድ አእምሮ ውስጥ መያዝ ይቻላል ማለት ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
30😁15😱9🤔4👍3👀1
"ከኢራን ጋር ያለው ጦርነት አልተቋጨም" ኔታንያሁ
።።።።።።።።።።።።።።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ በኢራን ውስጥ የሚገኘው የበለጸገ ዩራኒየም ሙሉ በሙሉ እስካልተወገደ ድረስ አሁን እየተካሄደ ያለው ጦርነት እንደማያበቃ አስጠነቀቁ።

ኔታንያሁ ከኢራን ጋር ያለው ውጥረት ገና መቋጫ እንዳላገኘና የቴህራን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ዋነኛ ስጋት ሆኖ መቀጠሉንም ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ከኢራን የሚሰነዘረው ጥቃትና ቀጠናዊ አለመረጋጋት አሁንም ባለበት በመሆኑ፣ እስራኤል ዝግጁነቷን እንደማታቆም ገልጸዋል።

ኔታንሁ ለሲ.ቢ.ኤስ «60 Minutes» ፕሮግራም በሰጡት ቃለ-መጠይቅ፣ ምንም እንኳን በሀገራቱ መካከል የተኩስ አቁም ጥረት ቢኖርም፣ እስራኤል የኢራንን የኒውክሌር ስጋት እንደ ቀዳሚ አጀንዳ እንደምትይዝ  አስታውቀዋል።

ይህ መግለጫ የወጣው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ በከፍተኛ ደረጃ በጨመረበት ወቅት መሆኑ ጉዳዩን አሳሳቢ አድርጎታል።

እስራኤል የኢራንን የኒውክሌር ተቋማት እንደ ትልቅ ስጋት የምትመለከተው ሲሆን፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በቴህራን ላይ  ጫና እንዲያደርግ በተደጋጋሚ ስትጠይቅ ቆይታለች።

ዘ ናሽናል እና ኢኮኖሚክ ታይምስ ዘግበውታል

ቶማይ መኮንን

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍12😡76
"ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂየቫ ጋር ውይይት አድርገናል"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂየቫ ጋር ተገናኝተን በኢኮኖሚያዊ እድገት፣ በአጋርነት እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የጋራ   ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት አስታውቀዋል።


‎ለነበረን ጠቃሚ የሃሳብ ልውውጥና ቀጣይነት ላለው አጋርነት ምስጋናዬ የላቀ ነው ብለዋል።

‎ሁለተኛ አመቱን እየያዘ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሸያ አፈጻጸም   IMF እንዴት እንደሚያየው በዝርዝር እንደሚገመገም ይጠበቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁2312👍3🤔1💊1
ደቡብ ሱዳን የግብፅ ጦር ሰፈር እንዲዘጋ ማዘዟ ተዘግቧል።
በዚህም የካይሮ ጦር በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ያለውን የጦር ካምፕ ሊቀይር እንደሚችል ተነግሯል።
የደቡብ ሱዳን የፕሬስ ምንጮችን ጠቅሰው እንደዘገቡት፣ትዕዛዙ በቀጠናው የሚገኙ ሁሉም የግብፅ ወታደራዊ ካምፖች እንዲዘጉ የሚጠይቅ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24👍8
በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ስም በተፈጸመ ማጭበርበር የተጠረጠሩ ታዋቂ ግለሰቦች የዋስትና ውሳኔ አገኙ‼️

በ'ፊንቴክ ኢንቨስትመንት' የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ ታዋቂ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች በገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችሎት ዛሬ ሰኞ ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የዋስትና መጠኑ ዝርዝር፦

ፍርድ ቤቱ የተከሳሾቹን የዋስትና መብት መርምሮ የሚከተለውን የገንዘብ መጠን ወስኗል፡

* አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ፣ አርቲስት ሠለሞን ቦጋለ፣ አርቲስት ይገረም ደጀን እና አርቲስት ዳንኤል ተገኝ፦ እያንዳንዳቸው 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በማስያዝ ከእስር እንዲፈቱ።

* ካሊድ ናስር እና አብርሃም ግዛው፦ እያንዳንዳቸው 400,000 (አራት መቶ ሺህ) ብር ዋስትና በማስያዝ ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ተወስኗል።

ተጨማሪ ትዕዛዞች እና ገደቦች፦

ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብታቸው ቢከበርላቸውም፣ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ባለበት ወቅት ከሀገር እንዳይወጡ የሚከለክል የእግድ ትዕዛዝ ተላልፎባቸዋል።

ስለ መንሱር ጀማል፦

በተመሳሳይ መዝገብ 5ኛ ተከሳሽ የሆነው ቲክቶከሩ መንሱር ጀማል ላይ አቃቤ ህግ የዋስትና መብቱን በፅኑ በመቃወሙ ምክንያት፣ ችሎቱ ውሳኔ ለመስጠት ለሌላ ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። በመሆኑም መንሱር ጀማል ለጊዜው በእስር ላይ ይቆያል።

የጉዳዩ መነሻ፦

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት "ፊንቴክ ኢንቨስትመንት" በሚባል ድርጅት ስም ማህበረሰቡን ለከፍተኛ የገንዘብ ማጭበርበር ዳርገዋል በሚል ተጠርጥረው መሆኑ ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18👍8😡5🤷‍♂1🎉1
ኢትዮጵያ የ600 ሚሊዮን ዶላር የድንገተኛ ቀውስ ምላሽ ፈንድ ድርድር አጠናቀቀች!

የኢትዮጵያ መንግሥት በመካከለኛው ምስራቅ ካለው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ እየጨመረ የመጣውን የነዳጅ ዋጋና የኢኮኖሚ ጫና ለመቋቋም የሚያስችል የ 600 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ድርድር ማጠናቀቁን አስታወቀ።

ይህ ድጋፍ መንግሥት ከአለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት (አለም ባንክ እና አይ.ኤም.ኤፍ) እንዲሁም እንደ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን ካሉ አጋር ሀገራት ጋር ከሚያደርገው የቢሊዮን ዶላሮች የትብብር ስትራቴጂ አካል መሆኑ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍5😁4😡1
"የሚሳዔል ማምረቻ ግብዓቶችን እየሰጠች መሆኑን ደርሰንበታል" - ኔታንያሁ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያም ኔታንያሁ ቻይና ለኢራን ድጋፍ እያደረገች ነው ሲሉ ወነጀሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ቻይና የተወሰነ አይነት ድጋፍ እያደረገች ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

"ከCBS 69 Minutes" ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ቻይና ለኢራን "የሚሳዔል ማምረቻ ግብዓቶችን እየሰጠች መሆኑን ደርሰንበታል" ብለዋል።

ኔታንያሁ "የቻይናን ድርጊት አልወደድኩትም" ሲሉ ተደምጠዋል።

"በቅርቡ የአሜሪካን እርዳታ ወደ ዜሮ እንቀንሳለን" በማለትም ተናግረዋል።  

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍7😡7😁5
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
ከ500 ዳቦዎች የተሰራው ቀሚስ ….

ግንቦት 3 2018 ዓ.ም. ምሽት በናይጀሪያ ሌጎስ የተካሄደው 12ኛው የአፍሪካ ማጂክ የተመልካቾች ምርጫ ሽልማት የአፍሪካ ግዙፉ የፊልም እና የፋሽን ምሽት በመባል ይታወቃል።

የአፍሪካ ማጂክ ተመልካቾች ምርጫ ሽልማት (Africa Magic Viewers' Choice Award- AMVCA) የናይጀሪያ ዝነኞችን ጨምሮ ከደቡብ፣ ምዕራብና ምሥራቅ አፍሪካ አገራት የተወከሉ ስመ ጥር ተዋናዮች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችና ከፍተኛ ኃላፊዎች በተገኙበት በድምቀት ተከናውኗል።

ኤኤምቪሲኤ በአፍሪካ የፊቸር ፊልም፣ የቴሌቪዥን ድራማ እና ዶክመንተሪ ስራዎች የላቀ ጥራት ያላቸው ይዘቶችና የጎላ ስራ ከውነዋል ተብለው በተመልካቾችና በከፍተኛ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የተመረጡ ባለሙያዎች የሚሸለሙበት የሽልማት ስነ ስርዓት ነው።

እሁድ ግንቦት 2 2018 ዓ.ም. በናይጄሪያ በተካሄደው 12ኛው የአፍሪካ ፊልሞች አዋርድ ላይ ታዋቂ ሰዎች፣ የፊልም ባለሙያዎች እንዲሁም የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በተለያዩ አልባሳት ተውበው ተገኝተዋል።

ከግዙፉ የአፍሪካ የመዝናኛ ይዘቶች አቅራቢው መልቲቾይስ አፍሪካ አማካኝነት በናይጄሪያ ሌጎስ በተካሄደው በዚህ የፊልም አዋርድ ዝግጅት ላይ የተገኙ ታዋቂ ሰዎች የአህጉሪቱን ባሕል ከማሳየት በዘለለ በአልባሳቶቻቸው ተፎካክረዋል።

በሌጎስ በሚገኘው ኤኮ ሆቴል በተካሄደው ዓመታዊ የአፍሪካ ፊልም፣ ቴሌቪዝን እና ዲጂታል ሥነ ጥበባዊ ስራዎች ሽልማት ምሽቱን ልዩ ውበት ያጎናጸፉት በርካታ አልባሳት መነጋገሪያ ነበሩ።

በዕለቱ ከተገኙት ስመ ጥር ሰዎች ሁሉ ግን የአንዷ ታዋቂ የቴሌቪዥን ተዋናይ አልባሳት የበለጠ መነጋገሪያ ሆና አምሽታለች።

የእውናዊ ቴሌቪዥን ዝግጅት ላይ በመሳተፍ ታዋቂነትን ያገኘችው እና ራሷን ኩዊን ሜርሲ አታንግ በማለት የምትጠራው ታዋቂ ተዋናይት ከ500 ዳቦዎች የተሰራ ዘርፋፋ ቀሚስ ለብሳ ተገኝታለች።

ሁለት ሠራተኞች በግራ እና በቀኝ ያጀቧት ኩዊን ሜርሲ በርካታ ረዳቶች የለበሰችውን ቀሚስ በቀይ ምንጣፍ ላይ እንድታሳይ በማገዝ ረድተዋታል።

አታንግ በዳቦዎች የተሸመነው ቀሚሷን ለብሳ በነጻነት መንቀሳቀስ የተቸገረች ቢሆንም የዕለቱ መነጋገሪያ ሆና ግን አምሽታለች።

ከዳቦ የተሠራ ቀሚስ የለበሰችው የዳቦ መጋገሪያ ንግዷን ለማስተዋወቅ መሆኑን የገለጸችው አታገንግ፣ የፋሽን ስራው ገበያ ማፈላላግ እንጂ ድንጋጤን መፍጠር ዓላማው እንዳልሆነ አስታውቃለች፥

"ንግዴን ለማስተዋወቅ ከዚህ ከአዋርድ ምሽቱ የበለጠ አመቺ ጊዜ የለም" ስትልም ተናግራለች።

ቀሚሱን ዲዛይን ያደረገችው የቲያና ኢምፓየር ባለቤት ቶይን ላዋን ስትሆን በኢንሳታግራም ገጿ ላይ "ሁሉም የራሱን ንግድ ይልበስ" በሚል መሪ ቃል ንቅናቄ መጀመሯን ተናግራለች።

በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ ወዲያውኑ መነጋገሪያ የሆነው አልባሳቱ የተወሰኑት ሲያደንቁት አንዳንዶች ደግሞ ተችተውታል።

"የራስን ንግድ ከፊት ማስቀደምን ያሳየ" ሲሉ ያሞካሹት እንዳሉ ሁሉ ምግብን ማባከን ነው በማለት ያብጠለጠሉተም አልጠፉም።

Via ዘገባው የBBC አማረኛ ነው

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
26😡16👍5💔3🤪3🤔2😁1
የእንግሊዝ ስራ እና ጡረታ ቢሮ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ሚስቶች ላሏቸው ባሎች ጥቅማጥቅሞችን እንደሚጨምር አስታወቀ።
በብሪታንያ ሁለት ሚስት ማግባት በህግ የተከለከለ ቢሆንም  ጋብቻው በባህር ማዶ ከሆነ ከአንድ በላይ ማግባት ጥሩ ነው፣ለዚህም ጥቅማ ጥቅሞችን እንደሚሰጥ አሳውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😁2817👍5
🔥 ተመሳሳይ ያረጁ ዜናዎችን ማንበብ ይብቃዎ! አልጎሪዝምዎን ይቀይሩ።

🇪🇹 🌍 ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም አቀፍ ዙሪያ የተሰሙ አዳዲስ ክስተቶችን በተለየ ምልከታ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ይከታተሉ። እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን በየእለቱ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ብቻ ያገኛሉ።

ከሌሎች መገናኛ ብዙኃን የማያገኟቸውን ትኩስ ትኩስ መረጃዎችን ስፑትኒክ ኢትዮጵያ ለእርስኦ ያቀርብልዎታል።

📌አዳዲስ መረጃዎችን በየእለቱ ለመከታተል አሁኑኑ ቻናላችንን በመቀላቀል ያልተሰሙ መረጃዎችን ይከታተሉ::
👇🏾👇🏾👇🏾

https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy
👍51🤩1
ትራምፕ አስቸኳይ ስብሰባ ጠሩ‼️
ትራምፕ ኢራንን በተመለከተ አስቸኳይ የብሔራዊ የደህንነት ስብሰባ የጠሩ ሲሆን በኢራን ላይ ወታደራዊ እርምጃን እንደገና ለማስጀመር እንዳሰቡ' - አክሲዮስ ዘግቧል።
በኢራን ላይ በቀሩ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ጥቃት ለመፈፀም ትራምፕ እቅድ እንዳላቸው ተነግሯል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍14👏43😡3🫡2
መረጃ‼️

በኢትዮጵያ የአሜሪካ የርሃብ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት (ፈውስ ኔት)፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሴፍቲ ኔት መርሃ ግብር መቋረጥ የምግብ እጥረት ቀውሱን አባብሶታል አለ።

በምግብ ለሥራ የምግብ ዋስትና ችግር ላለባቸው ዜጎች በበርካታ የአገሪቱ ክፍሎች የሚሠጠው ድጋፍ ከጥር ጀምሮ ተቋርጧል።

በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሳቢያ የነዳጅና የምግብ ዋጋ መናር እንዲሁም የብር የመግዛት አቅም መቀነስና የግጭት ተጽዕኖዎች፣ በቤተሰቦች የምግብ ተደራሽነት ላይ ተጽዕኖ መፍጠራቸውን ተቋሙ ገልጧል።

ደረጃ 4 አስቸኳይ የምግብ እጥረት ቀውስ በግንቦት ወር በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ቆላማ አካባቢዎችና ባለፉት ወራት ጋምቤላ በገቡ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ላይ ይቀጥላል ተብሏል።

ደረጃ 3 ቀውስ በምሥራቅ ትግራይ፣ በሰሜን ምሥራቅ አማራ፣ በሰሜን አፋር፣ ኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች የሚቀጥል ሲሆን፣ የተወሠኑ ቤተሰቦች ሁኔታ ወደ ደረጃ 4 ቀውስ ሊወርድ እንደሚችል ሪፖርቱ አመልክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15😢12👍3😡3🙏1
“ለሁሉም ነገር ተዘጋጅቻለሁ”ኢራን

የኢራኑ ቁልፍ ተደራዳሪ መሐመድ ጋሊባፍ”አገሬ ለሁሉም ምርጫዎች ተዘጋጅታለች”አሉ።

የኢራኑ ከፍተኛ ተደራዳሪ እና የፓርላማ አፈ ጉባዔ “ጦራችን ዝግጁ  ነው፤የትኛውንም ምላሽ ይሰጣል ፤በየትኛውም መንገድ ተዘጋጅተናል “ማለታቸው የውጥረቱን አለመብረድ ጠቋሚ ያደርገዋል።

የተሳሳት ስሌት እና ውሳኔ  ሁል ጊዜም ውጤቱ የተሳሳተ ነው ያሉት ጋሊባፍ ዓለም የተረዳችውም ይህኑን ነው ብለዋል።

ኢራን ያቀረበችውን ባለ14 ነጥብ እቅድ ከመቀበል ውጭ ሌላ ምርጫ የላቸውም ሲሉም ተደራዳሪው ቀድመው ሀሳብ መስጠታቸው አይዘነጋም።

ሌሎች አማራጮችን ለመውሰድ መሞከር ሙሉ ለሙሉ አግላይነትን የሚያንፀባርቅ ይሆናል በሚልም አሜሪካን አሳስበዋል።

በዋሽንግተንና ቴህራን መካከል ያለው የሆርሙዝ ሰርጥ ውጥረት የዓለምን ኢኮኖሚ ከመጉዳቱም ባሻገር ለኢራን አዲስ የመደራደሪያ ነጥብ ሆኗታልም ተብሏል።

ጋሊባፍ ጠንካራውን አስተያየት የሰጡት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ያቀረበችው ውጥን “ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም “ማለታቸውን ተከትሎ ነው።

ዘገባው የሲ ኤን ኤን ነው።

በ-ቢኒያም ካሴ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23👍2🤔1😢1
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘገየ አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

አቶ ዘገየ የግብርና ሚኒስቴርን ከ1968–1970 ዓ.ም እና ከ1983 - 1984 ዓ.ም በሚኒስትርነት ማገልገላቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል፡፡

አቶ ዘገየ አስፋው መሬት ለአራሹ አዋጅ እንዲታወጅ ከፍተኛ ድርሻ ነበራቸው፡፡

አቶ ዘገየ አስፋው ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ አለም ተለይተዋል ሲል የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናግሯል፡፡

ከዚህ አለም በሞት እስከተለዩ ድረስም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው እየሰሩ ነበር፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢1312👏3👍2🏆1
በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በምርጫ ጉዳይ ላይ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ማስፈራሪያ እና ጫና እንደሚደርስባቸው ገለጹ!

ግንቦት 24 የሚካሄደውን 7ኛው አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ በአማራ ክልል እንቅስቃሴ የሚያደርጉ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የተለያዩ ማስፈራሪያዎች እንደሚደርስባቸው ለ “ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።

ለደኅንነታቸው ሲባል ሥማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ እነዚህ የድርጅቶቹ አመራሮች፣ ማስፈራሪያ እና ጫናው ከሁለት ወገን የሚመጣ ነው ብለዋል።

በባሕር ዳር የሴቶችን ፖለቲካዊ ተሳትፎ መሰረት አድርጎ የሚሠራ የአንድ ድርጅት አመራር የሆኑ ግለሰብ እንደሚሉት “ሴቶች በምርጫ ሂደት ውስጥ ሊኖራቸው የሚገባውን የተሳትፎ ዓይነትና መጠን የሚያስተምር ፕሮጀክት ላይ ሴቶችን ‘አሠለጠንን’ የሚል መረጃ በራሳችን የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ከአጋራን በኋላ ተደጋጋሚ ስልኮች ተደወሉብን” በማለት ገልጸዋል።

አመራሯ ሲያብራሩ “በየቀኑ ሕዝብ እየገደለ የራሱን ዕድሜ የሚገዛን መንግሥት የምርጫ ቅቡልነት እንዲያገኝ ለማድረግ የምታደርጉትን እንቅስቃሴ አቁሙ የሚል ማስፈራሪያ ነው የሰጡን” ካሉ በኋላ፣ ይህ ማስፈራሪያ የመጣው ፋኖ ተብለው ከሚጠሩት እና በክልሉ ከመንግሥት ጋር ግጭት ውስጥ ካሉ አካላት፣ በስልክ እንደሆነ አስረድተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍4👏2😁2
የዲግሪ ሰርተፊኬት ህትመት በአንድ ማዕከል ብቻ ሊከናወን ነው

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች የዲግሪ ሰርተፊኬት ህትመት በአንድ ማዕከል ብቻ ሊከናወን መሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር)እንዳሉት፤ አሰራሩ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ለመከላከል ያለመ ነው፡፡

ከዚህ በፊት ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጨረታ ባሸነፈ ድርጅት በኩል የተማሪዎችን የትምህርት ማስረጃ የሚያሳትሙበት አሰራር ለሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አጋላጭ ሆኖ ቆይቷል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎቻቸውን ዲግሪ በአንድ ማዕከል ብቻ እንዲያሳትሙ ይደረጋል ብለዋል፡፡

አዲሱ ዲግሪ ታትሞ እስኪደርስ ድረስ ትምህርት ሚኒስቴር ዲግሪ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የድጋፍ ደብዳቤ እንደሚጽፍ ገልጸው፤ ህትመቱ በዚህ ዓመት እንደሚጀምር ጠቁመዋል።

በ2017 ዓ.ም የተመረቁ ተማሪዎችን ጨምሮ ከዚህ በኋላ የሚመረቁትም ሙሉ በሙሉ በአዲሱ ስርዓት መሰረት በአንድ ማዕከል የሚታተመውን ዲግሪ ብቻ እንዲወስዱ ይደረጋሉ ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ከ2017 ዓ.ም በፊት ተመርቀው ነገር ግን ዲግሪያቸውን ያልወሰዱ ተማሪዎች በአዲሱ አሰራር ብቻ እንደሚስተናገዱ አመልክተዋል።

ፋና

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
25👍8
1 ሺህ 139 የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኞች በስነምግባር ጥሰት ተቀጡ‼️
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት 9 ወራት የብልሹ አሰራርና ስነ ምግባር ጥሰት በፈፀሙ 1 ሺህ 139 የአገልግሎቱ ሠራተኞች ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃ ወሰደ፡፡ 

እርምጃ ከተወሰደባቸው ኃላፊዎችና ሠራተኞች መካከል 16 ሲሰናበቱ፤ 721 የደሞዝ ቅጣት የተቀጡ እንዲሁም 402 የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ናቸው፡፡

አገልግሎቱ በ1 ሺህ 139 ሠራተኞች ላይ ከወሰዳቸው አስተዳደራዊ እርምጃዎች መካከል 103 ሠራተኞች ላይ በደንበኞች የቀረበን ጥቆማ በመመርመር የወሰደው ነው፡፡ ቀሪ 1 ሺህ 36ቱ ተቋሙ በራሱ ግኝት አጣርቶ የወሰዳቸው እርምጃዎች ናቸው፡፡

ባለፉት ዘጠኝ ወራት አገልግሎቱ በሙስና መጠቆሚያ ዘመናዊ መተግበሪያ (Corruption Reporting App) እና በሌሎች አማራጮች ከደንበኞቹ የደረሱትን 427 ጥቆማዎችን መርምሮ በ103 ኃላፊዎችና ሠራተኞች ላይ የተለያዩ እርምጃዎችን ወስዷል፡፡ 

በደንበኞቹ በቀረቡት ጥቆማዎች መሰረት 14 የፅሁፍ፣ 80 የደሞዝ ቅጣት፣ 2 ከቦታ የማንሳትና 7 ስንብት በድምሩ 103 እርምጃዎች ተወስዷል፡፡ 

ይህም የጥቆማ መቀበያ ስርዓቱ የፈጠረው ምቹ ሁኔታ፣ ደንበኞች የሚሰጡት ጥቆማ ዋጋ ያለው መሆኑንና የሚታዩ ብልሹ አሰራርን ለመታገል አገልግሎቱ እያደረገ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው፡፡

የብልሹ አሰራር ጥቆማ ከቀረበባቸው ጉዳዮች መካከል የአዲስ ቆጣሪ ጥያቄ፣ የኃይል መቆራረጥና አስቸኳይ ጥገና፣ የቆጣሪ ንባብና የቢል ስብሰባ እንዲሁም ንብረት አያያዝና አጠቃቀም ይገኙበታል፡፡
ደንበኞች አሁንም የዲጂታል የብልሹ አሰራር ጥቆማ መቀበያ (www.eeuethics.et) በመጠቀም በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚታዩ የሙስናና ብልሹ አሰራር ችግሮችን እንዲጠቁሙ አገልግሎቱ ያበረታታል፡፡

አገልግሎቱም ማንኛውም የህግና የሥነምግባር ጥሰት ድርጊቶችን ለሚያጋልጡ ጠቋሚዎች እውቅና የሚሰጥ ሲሆን፤ ተገቢውን ጥበቃ በማድረግ በነፃነትና በተነሳሽነት የሙስና ወንጀሎችን እንዲያጋልጡ የማበረታታና ምቹ ሁኔታዎችን የሚፍጠር መሆኑን ይገልፃል፡፡
ደንበኞች በወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699/2003 መሰረት ህጋዊ ከለላ የማግኘት መብታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በአገልግሎቱ አሰራርና መመሪያ መሰረት ጠቋሚዎች የሚያቀርቡት ህጋዊ ጥያቄ ያለተጽዕኖ እንዲስተናገዱ ተገቢውን ከለላና ጥበቃ ይሰጣል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17👍9💯2🥰1
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ልምምድ ላይ በገጠማት ድንገተኛ ህመም ሕይወቷ አለፈ

ባለትዳርና የሁለት ልጆች እናቷ አትሌት የብርጓል መለሰ፤ ዛሬ ማለዳ ልምምዷን እየሠራች ባለችበት ወቅት ህመም ተሰምቷት ለህክምና በሄደችበት ሆስፒታል በሞት እንደተለየች  ተሰምቷል፡፡

የ36 ዓመቷ የብርጓል የፓሪስ ግማሽ ማራቶንን ሁለት ጊዜ፣ ሊዝበን ግማሽ ማራቶንን አንድ ጊዜ እንዲሁም የሻንጋይ፣ ፕራግና ሂውስተን ማራቶንን በበላይነት አጠናቃለች፡፡

በ2015ቱ የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በግማሽ ማራቶን ለኢትዮጵያ የነሀስ ሜዳሊያ አስገኝታለች፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
💔41😢208😱4👍2
አፍሪካ ካልተሳካላት አውሮፓ ተስፋ የላትም! - ማክሮን

የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አፍሪካን በሚመለከት ባደረጉት ንግግር፣ የአውሮፓና የአፍሪካ ዕጣ ፈንታ የማይነጣጠል መሆኑን በግልጽ አስታወቁ።

ፕሬዝዳንቱ አፍሪካን "ምን ማድረግ እንዳለባት" ለመንገር አለመምጣታቸውን  ገልጸው፣ የአፍሪካ ስኬትም ሆነ ውድቀት የአውሮፓም ጭምር መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

"አፍሪካ ከወደቀች አውሮፓ ምንም ዕድል አይኖራትም፤ በመከራና በሁከት ትዋጣለች" በማለት፣ የአህጉሪቱ መረጋጋት ለአለም ሰላም ያለውን ወሳኝነት አመላክተዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ ስለ አውሮፓ የቅኝ ግዛት ታሪክ እውነቱን ከመናገር ወደኋላ አላሉም።

"የአውሮፓ ቅኝ ግዛት ወንጀሎች የማይካዱ ናቸው" በማለት፣ በታሪክ የተፈጸሙ ስህተቶችንና አስከፊ እውነታዎችን በይፋ አምነዋል።

እርሳቸው የሚወክሉት ትውልድ ቅኝ ግዛት በሌለበት ወቅት የተወለደ መሆኑን የጠቀሱት ማክሮን፣ ንግግራቸው ለትምህርት ሳይሆን ለወደፊት አብሮነትና አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ ንግግር አውሮፓ ከአፍሪካ ጋር ያላትን የቀድሞ የጌታና የሎሌ ግንኙነት ወደ እኩልነት ለመቀየር ያላትን ፍላጎት የሚያሳይ ሆኖ ተወስዷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪2417😡5👍2😁1