የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኛዋን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል የተሰወረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ!
የሰንዳፋ በኬ ከተማ ነዋሪ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሌልቱ ቅርንጫፍ ሠራተኛ የሆነችውን ወ/ሮ አዳነች ኩምሳ ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል የተሰወረው ፀጋዬ አሳልፈው ጎንጤ የተባለው ተጠርጣሪ በደብረ ብርሃን ከተማ በቁጥጥር ሥር ውሏል።
ሟች እና ተጠርጣሪ ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በምሽት በሆቴል ውስጥ ምግብ ሲመገቡ በመካከላቸው አለመግባት በመፈጠሩ ሟች ተጠርጣሪውን ጥላ በመሄዷ ተከትሏት ወደ መኪና ውስጥ ካስገባት በኋላ ''ጎማጣ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሽጉጥ ትኩሶ ገድሏት ጥሎ በመጥፋቱ የሟች አስክሬን በዱር አራዊት ተበልቶ ጭንቅላቷ ብቻ መገኘቱን የፖሊስ የምርመራ መዝገብ ያመላክታል።
ተጠርጣሪው ወንጀሉን የፈጸመበትን መኪና እና ሽጉጥ በአሌልቱ ከተማ ጥሎ መሰወሩን የደረሰበት ፖሊስ በመኪናው ውስጥ የደም ዱካ እና ሽጉጡን እንደ ማስረጃ በመጠቀም ግለሰቡን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና ከሌሎች የፀጥታና ደህንነት ኃይሎች እንዲሁም ከሰንዳፋ በኬ ከተማ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት ባደረገው ከፍተኛ ክትትል ተጠርጣሪው የተለያዩ ሐሰተኛ መታወቂያዎችን በማውጣት በደብረ ብርሃን፣ በከሚሴ፣ በሸዋ ሮቢትና በአጣዬ ከተሞች ውስጥ ሰላማዊ ሰው መስሎ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ሥር ሊያውል ችሏል።
ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ምርመራውን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ማንኛውንም ወንጀል ፈጽሞ ከፖሊስ ለመሰወር የሚሞክር ወንጀለኛ ከሕግ ማምለጥ እንደማይችል ገልጿል። ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ሥር ለማዋል በተደረገው ጠንካራ ክትትል ትብብር ላደረጉ ኣካላት በሙሉ ምስጋናውን አቅርቧል።
@Addis_Reporter

❤22😢6👍3🥰1
የድል ዜና፡ መድፈኞቹ በለንደን ስታዲየም ድል ቀንቷቸዋል!
ዌስትሃም ዩናይትድ 0 - 1 አርሰናል
አርሰናል ወደ ምስራቅ ለንደን ተጉዞ የዌስትሃም ዩናይትድን ፈታኝ ስብስብ 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት በማሸነፍ፣ በሊጉ የዋንጫ ፉክክር ውስጥ እጅግ ወሳኝ የሆኑ ሦስት ነጥቦችን በልበ ሙሉነት ተቀላቅሏል።
መድፈኞቹ በለንደን ስታዲየም ብርቱ ፉክክር ባደረጉበት በዚህ መርሃ ግብር፣ ቤልጄሚያዊው ኮከብ ሊያንድሮ ትሮሳርድ ከመረብ ያሳረፋት ብቸኛ ግብ የጨዋታው ልዩነት ሆና ተመዝግባለች።
ጨዋታው መጠናቀቁን የሚገልጸው ዳኛ ፊሽካ ሲነፋ፣ በስታዲየሙ የታደሙ የአርሰናል ደጋፊዎች በታላቅ የደስታ ስሜትና በእንባ ታጅበው ድላቸውን ሲያከብሩ ተስተውሏል።
ይህ ድል አርሰናል ወደ ዋንጫው የሚያደርገውን ግስጋሴ ይበልጥ ያፋጠነ ሲሆን፣ ለደጋፊዎቹም ትልቅ ተስፋን የሰነቀ ውጤት ሆኗል።

❤19👍3👏2😢1🎉1💊1
አንጋፋዉ ጋዜጠኛ ወደ ቴሌግራም መጣ፡፡ መረጃዎችን ጎልጉሎ በማዉጣት እራስ ምታት ሆኖል ፡፡
ተቀላቀሉት Join👇👇
"በዚህ ሊንክ ግቡ 👇👇
https://t.me/darashMedia
https://t.me/darashMedia
ተቀላቀሉት Join👇👇
"በዚህ ሊንክ ግቡ 👇👇
https://t.me/darashMedia
https://t.me/darashMedia
👍9❤8
ቴዲ አፍሮ ለ3ኛ ሳምንት የኢትዮጵያን የሙዚቃ ገበታ ተቆጣጠረ
በሳምንቱ በዩቲዩብ ከፍተኛ ተመልካች ያገኙ 10 የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች ዝርዝር ይፋ ሲሆን፣ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ከአንደኛ እስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ ሙሉ በሙሉ በመያዝ አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል።
የሙዚቃ መረጃዎችን ተንትኖ ደረጃ የሚያወጣው “የኔ ቫይብ” (YeneVibe) ሚያዝያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው ሳምንታዊ መረጃ መሰረት፣ የቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም ስራዎች በሳምንቱ ውስጥ ብቻ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አዳዲስ ተመልካቾችን በማግኘት የገበታውን አናት ተቆጣጥረውታል። ይህ ደረጃ የወጣው ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ አውቶማቲክ አሰራር ሲሆን፣ መለኪያውም ሙዚቃዎቹ በሳምንቱ ውስጥ በዩቲዩብ ላይ የጨመሩት የተመልካች ብዛት (New Views) ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።
በደረጃው መሰረት “ዳስ ጣል (አንሳው)” የተሰኘው ስራ በሳምንት ውስጥ ከ2.8 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ተመልካቾችን በማግኘት በአንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በአጠቃላይ በሳምንቱ ምርጥ አስር ውስጥ የገቡት የቴዲ አፍሮ ስራዎች ብቻ መሆናቸው የአልበሙን ከፍተኛ ተቀባይነት የሚያሳይ ሲሆን፣ ይህም በኢትዮጵያ የዲጂታል ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ስኬት ሆኖ ተመዝግቧል።
በሳምንቱ ከፍተኛ ተመልካች ያገኙ ምርጥ 10 ሙዚቃዎች ዝርዝር፦
1ኛ ዳስ ጣል (አንሳው) – ቴዲ አፍሮ (+2,846,156 አዲስ እይታ)
2ኛ ሺ ቢባል (ወደ 90ዎቹ) – ቴዲ አፍሮ (+2,269,028 አዲስ እይታ)
3ኛ ዝ ፀዳል – ቴዲ አፍሮ (+1,933,851 አዲስ እይታ)
4ኛ ስምምነን (ጉሬጌ) – ቴዲ አፍሮ (+1,790,725 አዲስ እይታ)
5ኛ መርከብ – ቴዲ አፍሮ (+1,282,541 አዲስ እይታ)
6ኛ ታየኝ – ቴዲ አፍሮ (+1,278,335 አዲስ እይታ)
7ኛ ጽዮን ሙሽራዬ – ቴዲ አፍሮ (+1,171,738 አዲስ እይታ)
8ኛ ብልጭታ – ቴዲ አፍሮ (+1,126,840 አዲስ እይታ)
9ኛ ተወዳጅ – ቴዲ አፍሮ (+851,045 አዲስ እይታ)
10ኛ ጀምበር – ቴዲ አፍሮ (+755,029 አዲስ እይታ)

❤60👍14👌5🥰1👏1
የሰው ልጅ አእምሮ መረጃን የማከማቸት አቅሙ በዲጂታል መለኪያ ሲሰላ እስከ 2.5 ፔታባይት (Petabytes) ይደርሳል። ይህ ማለት ምን ማለት መሰለህ? አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ ለ300 ዓመታት ያለማቋረጥ የሚያስተላልፈውን ከፍተኛ ጥራት ያለው (HD) ቪዲዮ በአንድ አእምሮ ውስጥ መያዝ ይቻላል ማለት ነው።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤30😁15😱9🤔4👍3👀1
"ከኢራን ጋር ያለው ጦርነት አልተቋጨም" ኔታንያሁ
።።።።።።።።።።።።።።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ በኢራን ውስጥ የሚገኘው የበለጸገ ዩራኒየም ሙሉ በሙሉ እስካልተወገደ ድረስ አሁን እየተካሄደ ያለው ጦርነት እንደማያበቃ አስጠነቀቁ።
ኔታንያሁ ከኢራን ጋር ያለው ውጥረት ገና መቋጫ እንዳላገኘና የቴህራን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ዋነኛ ስጋት ሆኖ መቀጠሉንም ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢራን የሚሰነዘረው ጥቃትና ቀጠናዊ አለመረጋጋት አሁንም ባለበት በመሆኑ፣ እስራኤል ዝግጁነቷን እንደማታቆም ገልጸዋል።
ኔታንሁ ለሲ.ቢ.ኤስ «60 Minutes» ፕሮግራም በሰጡት ቃለ-መጠይቅ፣ ምንም እንኳን በሀገራቱ መካከል የተኩስ አቁም ጥረት ቢኖርም፣ እስራኤል የኢራንን የኒውክሌር ስጋት እንደ ቀዳሚ አጀንዳ እንደምትይዝ አስታውቀዋል።
ይህ መግለጫ የወጣው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ በከፍተኛ ደረጃ በጨመረበት ወቅት መሆኑ ጉዳዩን አሳሳቢ አድርጎታል።
እስራኤል የኢራንን የኒውክሌር ተቋማት እንደ ትልቅ ስጋት የምትመለከተው ሲሆን፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በቴህራን ላይ ጫና እንዲያደርግ በተደጋጋሚ ስትጠይቅ ቆይታለች።
ዘ ናሽናል እና ኢኮኖሚክ ታይምስ ዘግበውታል
ቶማይ መኮንን

👍12😡7❤6
"ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂየቫ ጋር ውይይት አድርገናል"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂየቫ ጋር ተገናኝተን በኢኮኖሚያዊ እድገት፣ በአጋርነት እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት አስታውቀዋል።
ለነበረን ጠቃሚ የሃሳብ ልውውጥና ቀጣይነት ላለው አጋርነት ምስጋናዬ የላቀ ነው ብለዋል።
ሁለተኛ አመቱን እየያዘ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሸያ አፈጻጸም IMF እንዴት እንደሚያየው በዝርዝር እንደሚገመገም ይጠበቃል።

😁23❤12👍3🤔1💊1
ደቡብ ሱዳን የግብፅ ጦር ሰፈር እንዲዘጋ ማዘዟ ተዘግቧል።
በዚህም የካይሮ ጦር በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ያለውን የጦር ካምፕ ሊቀይር እንደሚችል ተነግሯል።
የደቡብ ሱዳን የፕሬስ ምንጮችን ጠቅሰው እንደዘገቡት፣ትዕዛዙ በቀጠናው የሚገኙ ሁሉም የግብፅ ወታደራዊ ካምፖች እንዲዘጉ የሚጠይቅ ነው።

❤24👍8
በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ስም በተፈጸመ ማጭበርበር የተጠረጠሩ ታዋቂ ግለሰቦች የዋስትና ውሳኔ አገኙ‼️
በ'ፊንቴክ ኢንቨስትመንት' የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ ታዋቂ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች በገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችሎት ዛሬ ሰኞ ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ትዕዛዝ ሰጥቷል።
የዋስትና መጠኑ ዝርዝር፦
ፍርድ ቤቱ የተከሳሾቹን የዋስትና መብት መርምሮ የሚከተለውን የገንዘብ መጠን ወስኗል፡
* አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ፣ አርቲስት ሠለሞን ቦጋለ፣ አርቲስት ይገረም ደጀን እና አርቲስት ዳንኤል ተገኝ፦ እያንዳንዳቸው 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በማስያዝ ከእስር እንዲፈቱ።
* ካሊድ ናስር እና አብርሃም ግዛው፦ እያንዳንዳቸው 400,000 (አራት መቶ ሺህ) ብር ዋስትና በማስያዝ ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ተወስኗል።
ተጨማሪ ትዕዛዞች እና ገደቦች፦
ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብታቸው ቢከበርላቸውም፣ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ባለበት ወቅት ከሀገር እንዳይወጡ የሚከለክል የእግድ ትዕዛዝ ተላልፎባቸዋል።
ስለ መንሱር ጀማል፦
በተመሳሳይ መዝገብ 5ኛ ተከሳሽ የሆነው ቲክቶከሩ መንሱር ጀማል ላይ አቃቤ ህግ የዋስትና መብቱን በፅኑ በመቃወሙ ምክንያት፣ ችሎቱ ውሳኔ ለመስጠት ለሌላ ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። በመሆኑም መንሱር ጀማል ለጊዜው በእስር ላይ ይቆያል።
የጉዳዩ መነሻ፦
ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት "ፊንቴክ ኢንቨስትመንት" በሚባል ድርጅት ስም ማህበረሰቡን ለከፍተኛ የገንዘብ ማጭበርበር ዳርገዋል በሚል ተጠርጥረው መሆኑ ይታወሳል።

❤18👍8😡5🤷♂1🎉1
ኢትዮጵያ የ600 ሚሊዮን ዶላር የድንገተኛ ቀውስ ምላሽ ፈንድ ድርድር አጠናቀቀች!
የኢትዮጵያ መንግሥት በመካከለኛው ምስራቅ ካለው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ እየጨመረ የመጣውን የነዳጅ ዋጋና የኢኮኖሚ ጫና ለመቋቋም የሚያስችል የ 600 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ድርድር ማጠናቀቁን አስታወቀ።
ይህ ድጋፍ መንግሥት ከአለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት (አለም ባንክ እና አይ.ኤም.ኤፍ) እንዲሁም እንደ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን ካሉ አጋር ሀገራት ጋር ከሚያደርገው የቢሊዮን ዶላሮች የትብብር ስትራቴጂ አካል መሆኑ ተገልጿል።

❤11👍5😁4😡1
"የሚሳዔል ማምረቻ ግብዓቶችን እየሰጠች መሆኑን ደርሰንበታል" - ኔታንያሁ
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያም ኔታንያሁ ቻይና ለኢራን ድጋፍ እያደረገች ነው ሲሉ ወነጀሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ቻይና የተወሰነ አይነት ድጋፍ እያደረገች ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
"ከCBS 69 Minutes" ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ቻይና ለኢራን "የሚሳዔል ማምረቻ ግብዓቶችን እየሰጠች መሆኑን ደርሰንበታል" ብለዋል።
ኔታንያሁ "የቻይናን ድርጊት አልወደድኩትም" ሲሉ ተደምጠዋል።
"በቅርቡ የአሜሪካን እርዳታ ወደ ዜሮ እንቀንሳለን" በማለትም ተናግረዋል።

❤12👍7😡7😁5
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
ከ500 ዳቦዎች የተሰራው ቀሚስ ….
ግንቦት 3 2018 ዓ.ም. ምሽት በናይጀሪያ ሌጎስ የተካሄደው 12ኛው የአፍሪካ ማጂክ የተመልካቾች ምርጫ ሽልማት የአፍሪካ ግዙፉ የፊልም እና የፋሽን ምሽት በመባል ይታወቃል።
የአፍሪካ ማጂክ ተመልካቾች ምርጫ ሽልማት (Africa Magic Viewers' Choice Award- AMVCA) የናይጀሪያ ዝነኞችን ጨምሮ ከደቡብ፣ ምዕራብና ምሥራቅ አፍሪካ አገራት የተወከሉ ስመ ጥር ተዋናዮች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችና ከፍተኛ ኃላፊዎች በተገኙበት በድምቀት ተከናውኗል።
ኤኤምቪሲኤ በአፍሪካ የፊቸር ፊልም፣ የቴሌቪዥን ድራማ እና ዶክመንተሪ ስራዎች የላቀ ጥራት ያላቸው ይዘቶችና የጎላ ስራ ከውነዋል ተብለው በተመልካቾችና በከፍተኛ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የተመረጡ ባለሙያዎች የሚሸለሙበት የሽልማት ስነ ስርዓት ነው።
እሁድ ግንቦት 2 2018 ዓ.ም. በናይጄሪያ በተካሄደው 12ኛው የአፍሪካ ፊልሞች አዋርድ ላይ ታዋቂ ሰዎች፣ የፊልም ባለሙያዎች እንዲሁም የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በተለያዩ አልባሳት ተውበው ተገኝተዋል።
ከግዙፉ የአፍሪካ የመዝናኛ ይዘቶች አቅራቢው መልቲቾይስ አፍሪካ አማካኝነት በናይጄሪያ ሌጎስ በተካሄደው በዚህ የፊልም አዋርድ ዝግጅት ላይ የተገኙ ታዋቂ ሰዎች የአህጉሪቱን ባሕል ከማሳየት በዘለለ በአልባሳቶቻቸው ተፎካክረዋል።
በሌጎስ በሚገኘው ኤኮ ሆቴል በተካሄደው ዓመታዊ የአፍሪካ ፊልም፣ ቴሌቪዝን እና ዲጂታል ሥነ ጥበባዊ ስራዎች ሽልማት ምሽቱን ልዩ ውበት ያጎናጸፉት በርካታ አልባሳት መነጋገሪያ ነበሩ።
በዕለቱ ከተገኙት ስመ ጥር ሰዎች ሁሉ ግን የአንዷ ታዋቂ የቴሌቪዥን ተዋናይ አልባሳት የበለጠ መነጋገሪያ ሆና አምሽታለች።
የእውናዊ ቴሌቪዥን ዝግጅት ላይ በመሳተፍ ታዋቂነትን ያገኘችው እና ራሷን ኩዊን ሜርሲ አታንግ በማለት የምትጠራው ታዋቂ ተዋናይት ከ500 ዳቦዎች የተሰራ ዘርፋፋ ቀሚስ ለብሳ ተገኝታለች።
ሁለት ሠራተኞች በግራ እና በቀኝ ያጀቧት ኩዊን ሜርሲ በርካታ ረዳቶች የለበሰችውን ቀሚስ በቀይ ምንጣፍ ላይ እንድታሳይ በማገዝ ረድተዋታል።
አታንግ በዳቦዎች የተሸመነው ቀሚሷን ለብሳ በነጻነት መንቀሳቀስ የተቸገረች ቢሆንም የዕለቱ መነጋገሪያ ሆና ግን አምሽታለች።
ከዳቦ የተሠራ ቀሚስ የለበሰችው የዳቦ መጋገሪያ ንግዷን ለማስተዋወቅ መሆኑን የገለጸችው አታገንግ፣ የፋሽን ስራው ገበያ ማፈላላግ እንጂ ድንጋጤን መፍጠር ዓላማው እንዳልሆነ አስታውቃለች፥
"ንግዴን ለማስተዋወቅ ከዚህ ከአዋርድ ምሽቱ የበለጠ አመቺ ጊዜ የለም" ስትልም ተናግራለች።
ቀሚሱን ዲዛይን ያደረገችው የቲያና ኢምፓየር ባለቤት ቶይን ላዋን ስትሆን በኢንሳታግራም ገጿ ላይ "ሁሉም የራሱን ንግድ ይልበስ" በሚል መሪ ቃል ንቅናቄ መጀመሯን ተናግራለች።
በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ ወዲያውኑ መነጋገሪያ የሆነው አልባሳቱ የተወሰኑት ሲያደንቁት አንዳንዶች ደግሞ ተችተውታል።
"የራስን ንግድ ከፊት ማስቀደምን ያሳየ" ሲሉ ያሞካሹት እንዳሉ ሁሉ ምግብን ማባከን ነው በማለት ያብጠለጠሉተም አልጠፉም።
Via ዘገባው የBBC አማረኛ ነው

❤26😡16👍5💔3🤪3🤔2😁1
የእንግሊዝ ስራ እና ጡረታ ቢሮ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ሚስቶች ላሏቸው ባሎች ጥቅማጥቅሞችን እንደሚጨምር አስታወቀ።
በብሪታንያ ሁለት ሚስት ማግባት በህግ የተከለከለ ቢሆንም ጋብቻው በባህር ማዶ ከሆነ ከአንድ በላይ ማግባት ጥሩ ነው፣ለዚህም ጥቅማ ጥቅሞችን እንደሚሰጥ አሳውቋል።

😁28❤17👍5
🔥 ተመሳሳይ ያረጁ ዜናዎችን ማንበብ ይብቃዎ! አልጎሪዝምዎን ይቀይሩ።
🇪🇹 🌍 ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም አቀፍ ዙሪያ የተሰሙ አዳዲስ ክስተቶችን በተለየ ምልከታ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ይከታተሉ። እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን በየእለቱ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ብቻ ያገኛሉ።
✅ከሌሎች መገናኛ ብዙኃን የማያገኟቸውን ትኩስ ትኩስ መረጃዎችን ስፑትኒክ ኢትዮጵያ ለእርስኦ ያቀርብልዎታል።
📌አዳዲስ መረጃዎችን በየእለቱ ለመከታተል አሁኑኑ ቻናላችንን በመቀላቀል ያልተሰሙ መረጃዎችን ይከታተሉ::
👇🏾👇🏾👇🏾
https://t.me/+r3LZG4PCAKI3NmMy

👍5❤1🤩1
ትራምፕ አስቸኳይ ስብሰባ ጠሩ‼️
ትራምፕ ኢራንን በተመለከተ አስቸኳይ የብሔራዊ የደህንነት ስብሰባ የጠሩ ሲሆን በኢራን ላይ ወታደራዊ እርምጃን እንደገና ለማስጀመር እንዳሰቡ' - አክሲዮስ ዘግቧል።
በኢራን ላይ በቀሩ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ጥቃት ለመፈፀም ትራምፕ እቅድ እንዳላቸው ተነግሯል።

👍14👏4❤3😡3🫡2
መረጃ‼️
በኢትዮጵያ የአሜሪካ የርሃብ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት (ፈውስ ኔት)፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሴፍቲ ኔት መርሃ ግብር መቋረጥ የምግብ እጥረት ቀውሱን አባብሶታል አለ።
በምግብ ለሥራ የምግብ ዋስትና ችግር ላለባቸው ዜጎች በበርካታ የአገሪቱ ክፍሎች የሚሠጠው ድጋፍ ከጥር ጀምሮ ተቋርጧል።
በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሳቢያ የነዳጅና የምግብ ዋጋ መናር እንዲሁም የብር የመግዛት አቅም መቀነስና የግጭት ተጽዕኖዎች፣ በቤተሰቦች የምግብ ተደራሽነት ላይ ተጽዕኖ መፍጠራቸውን ተቋሙ ገልጧል።
ደረጃ 4 አስቸኳይ የምግብ እጥረት ቀውስ በግንቦት ወር በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ቆላማ አካባቢዎችና ባለፉት ወራት ጋምቤላ በገቡ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ላይ ይቀጥላል ተብሏል።
ደረጃ 3 ቀውስ በምሥራቅ ትግራይ፣ በሰሜን ምሥራቅ አማራ፣ በሰሜን አፋር፣ ኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች የሚቀጥል ሲሆን፣ የተወሠኑ ቤተሰቦች ሁኔታ ወደ ደረጃ 4 ቀውስ ሊወርድ እንደሚችል ሪፖርቱ አመልክቷል።

❤15😢12👍3😡3🙏1
“ለሁሉም ነገር ተዘጋጅቻለሁ”ኢራን
የኢራኑ ቁልፍ ተደራዳሪ መሐመድ ጋሊባፍ”አገሬ ለሁሉም ምርጫዎች ተዘጋጅታለች”አሉ።
የኢራኑ ከፍተኛ ተደራዳሪ እና የፓርላማ አፈ ጉባዔ “ጦራችን ዝግጁ ነው፤የትኛውንም ምላሽ ይሰጣል ፤በየትኛውም መንገድ ተዘጋጅተናል “ማለታቸው የውጥረቱን አለመብረድ ጠቋሚ ያደርገዋል።
የተሳሳት ስሌት እና ውሳኔ ሁል ጊዜም ውጤቱ የተሳሳተ ነው ያሉት ጋሊባፍ ዓለም የተረዳችውም ይህኑን ነው ብለዋል።
ኢራን ያቀረበችውን ባለ14 ነጥብ እቅድ ከመቀበል ውጭ ሌላ ምርጫ የላቸውም ሲሉም ተደራዳሪው ቀድመው ሀሳብ መስጠታቸው አይዘነጋም።
ሌሎች አማራጮችን ለመውሰድ መሞከር ሙሉ ለሙሉ አግላይነትን የሚያንፀባርቅ ይሆናል በሚልም አሜሪካን አሳስበዋል።
በዋሽንግተንና ቴህራን መካከል ያለው የሆርሙዝ ሰርጥ ውጥረት የዓለምን ኢኮኖሚ ከመጉዳቱም ባሻገር ለኢራን አዲስ የመደራደሪያ ነጥብ ሆኗታልም ተብሏል።
ጋሊባፍ ጠንካራውን አስተያየት የሰጡት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ያቀረበችው ውጥን “ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም “ማለታቸውን ተከትሎ ነው።
ዘገባው የሲ ኤን ኤን ነው።
በ-ቢኒያም ካሴ

❤23👍2🤔1😢1
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘገየ አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
አቶ ዘገየ የግብርና ሚኒስቴርን ከ1968–1970 ዓ.ም እና ከ1983 - 1984 ዓ.ም በሚኒስትርነት ማገልገላቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል፡፡
አቶ ዘገየ አስፋው መሬት ለአራሹ አዋጅ እንዲታወጅ ከፍተኛ ድርሻ ነበራቸው፡፡
አቶ ዘገየ አስፋው ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ አለም ተለይተዋል ሲል የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናግሯል፡፡
ከዚህ አለም በሞት እስከተለዩ ድረስም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው እየሰሩ ነበር፡፡

😢13❤12👏3👍2🏆1