አዲስ ነገር መረጃ
104K subscribers
24.3K photos
907 videos
53 files
3.36K links
#አዲስ_ነገር_መረጃ

#መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ

Addis Ababa , Ethiopia

Buy Ads :

https://telega.io/?r=UbutLo2z

#ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addisnegermereja_bot
Download Telegram
አዲስ ነገር መረጃ
Photo
“ሞት በጥር… በነሐሴ መቃብር”

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ሦስት ዓመት ከቤተሰቧ ጋር፤ አሥራ-ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ፤ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀናት ጌታን ጸንሳ፤ ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ከጌታችን ጋራ፤ አሥራ አምስት ዓመት በወንጌላዊው ዮሐንስ ቤት ከኖረች በኋላ በስድሳ አራት ዓመቷ ጥር ሃያ አንድ ቀን አርፋለች። ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 131÷8 “አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦትም” በማለት ስለእመቤታችን እረፍት በምሥጢር ይገልጻል። ይህን ቃለ ትንቢት የተናገረው ፈጣሪዬ ሆይ ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህን ታቦት ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ ሲል ነው። ይህም እመቤታችን እንደ ልጇ ትንሣኤ መነሣቷን የሚያመለክት ነው። ታቦት ያላትም ማደሪያው ስለሆነች ነው። እመቤታችን ስታርፍ ቅዱሳን ሐዋርያት ሊቀብሯት ቅዱስ ስጋዋን ይዘው ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲሄዱ አይሁድ በምቀኝነት ተነሱ፡፡

“ቀድሞ ልጇን ተነሣ፣ አረገ፤ እንደገናም ይህን ዓለም ለማሳለፍ ተመልሶ ይመጣል” እያሉ በማስተማር ሕዝቡን ፈጽመው ወስደውታል። አሁን ደግሞ እርሷንም እንደ ልጇ ተነሣች፤ ዐረገች እያሉ በማስተማር ሲያውኩን አይደለምን? “ኑ! በእሳት እናቃጥላት” ብለው መጡ፡፡ ከመካከላቸው ታውፍንያ የተባለ አይሁዳዊ ስጋዋን ያለበትን አልጋ ሸንኮር ተራምዶ ሲይዝ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሠይፍ ሁለት እጆቹን ቆረጠውና ተንጠልጥለው ቀሩ። በፈጸመው ድርጊት ተጸጽቶ ወደ እመቤታችን ስለተማጸነ በተአምር የተቆረጡ እጆቹን ፈውሳዋለች። በዚያ ጊዜም መልአክ እግዚአብሔር እመቤታችንና ቅዱስ ዮሐንስን ወስዶ በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጣቸው ቅዱስ ዮሐንስም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደ ሐዋርያት ሲመጣ የእመቤታችን አስከሬን በገነት መኖሩን ነገራቸው።

ሐዋርያትም ዮሐንስ ይህን ክብር አይቶ፣ እኛ ሳናይ ብለው በነሐሴ 1 ቀን ሱባኤ ጀምረው በ14ኛው ቀን ጌታችን ስጋዋን ሰጥቷቸው በታላቅ ዝማሬና ውዳሴ በጌቴሴማኒ ቀበሯት። በሶስተኛው ቀን ተነስታ ስታርግ ቅዱስ ቶማስ አልነበረምና ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ ያገኛታል። ያን ጊዜም ትንሣኤዋን ሌሎች ሐዋርያት አይተው እርሱ የቀረበት መስሎት በፊት የልጅሽን ትንሣኤ አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ ብሎ በሀዘን ከደመናው ተወርውሮ ሊወድቅ ቃጣው። እመቤታችንም ከእርሱ በቀር ሌሎቹ ሓዋርያት ትንሣኤዋን እንዳላዩ፣ ለሐዋርያት የሆነውን ሁሉ እንዲነግራችው አዝዛው ለምልክት ይሆነው ዘንድ የተገነዘችበትን ሰበኗን ሰጥታው ወደ ሰማይ ዐርጋለች። ሐዋርያትም ቅዱስ ቶማስ ስለእመቤታችን ሲጠይቃቸው አጊኝተን ቀበርናት አሉት። እርሱም የያዘውን ያውቃልና “አይደረግም! ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንደምን ይሆናል?” አላቸው።

ቅዱስ ጴጥሮስም ተቆጥቶ “አንተ እንጂ፤ ቀድሞ የጌታን ትንሣኤ ተጠራጠርክ። አሁንም አታምንምን?” ብሎ ወደ እመቤታችን መካነ መቃብር ቢሔድ አጣት፤ ደነገጡ፡፡ ቅዱስ ቶማስ “አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችንስ ተነሥታ ዐርጋለች” ብሎ ሰበኗን ሰጣቸው። ለበረከት ቆራርጠው ከተከፋፈሉ በኋላ ወደየአህጉረ ስብከታቸው ሄደዋል። በዓመቱ ቶማስ ትንሣኤሽን አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ነሐሴ 1 ቀን ሱባኤ ገቡ፡፡ በነሐሴ 16 ቀን ጌታችን እመቤታችንን መንበር፤ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቅ ቄስ፤ ቅዱስ እስጢፋኖስን፤ ገባሬ-ሠናይ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ አቁርቧቸው የእመቤታችንን ዕርገቷን ለማየት አብቅቷቸዋል። ሐዋርያዊቷ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንም ይህን ታላቅ ጾም ከሰባቱ አጽዋማት ተርታ አስገብታ ትጾማለች። ከብርሃነ ትንሣኤዋ ረድኤት በረከት ያሳትፈን፡፡ ገዳማውያንም በጾምና በጸሎት ይህን በረከት ያገኛሉ፡፡ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን ከበረከታቸው እንሳተፍ፡፡
ካለን ላይ ለተቸገሩ በማካፈል ለነፍሳችን ስንቅን እንያዝ

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
48🤣6👏3🔥1🤔1
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ተከትሎ፤ ዜጎች መልካም ምኞታቸውን የሚገልጹበት "የትውልድ አሻራ" የተሰኘ አጭር የጽሁፍ መልዕክት መላኪያ ቁጥር መዘጋጀቱን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት  አስታውቋል።

ፕሮጀክቱ "የትውልድ አሻራ" የተሰኘ መጠሪያ የተሰጠው የዲጂታል የብስራት መልክትና የገቢ ማስገኛ መሆኑን፤ የጽ/ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን ዳንኤል ተናግረዋል።

ከአሁን ቀደም በ8100 አጭር ቁጥር ላይ የእንግሊዘኛውን A ፊደል በመላክ ማንኛውም ሰው ለግድቡ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል።

በአሁኑ ወቅት ተዘጋጅቶ በቅርቡ ይፋ የሚደረገው ደግሞ ተጨማሪ የመልክት መላኪያ አጭር ቁጥር ሲሆን፤ አገልግሎቱም እስከ ሁለት ወር ድረስ ብቻ የሚቆይ መሆኑን ሥራ አስፈፃሚው ገልጸዋል።

"ዋና ዓላማው ዜጎች ከአሁን ቀደም ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድጋፋቸውን ሲገልጹ እንደቆዩት ሁሉ፤ ግድቡ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ደስታቸውን መግለፅ ለሚፈልጉ ሰዎች አገልግሎት እንዲሰጥ ነው" ብለዋል።

ስለሆነም ዜጎች ማንኛውም መልዕክታቸውን በ8120 ላይ አጭር የፅሑፍ መልክት እንዲያደርሱ ጽ/ቤቱ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ተናግረዋል።

ይህም አገልግሎት በቅርቡ በሚካሄድ የማስጀመሪያ ደማቅ መርሃ-ግብር በይፋ እንደሚጀመር የጽ/ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን ዳንኤል ለአሐዱ አስታውቀዋል።
via_አሐዱ

@Addis_News
@Addis_News
32🤪10
አንድ ኮሎምቢያዊ ገበሬ በእርሻው ላይ ሲሰራ 600 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተቀብሮ አገኘ

ገንዘቡ የሟቹ አደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪ የነበረው ፓብሎ ኤስኮባር ሊሆን ይችላል ተብሏል።

የኮሎምቢያ ሚዲያን ዋቢ በማድረግ ማርካ የተባለ የየቀን ጋዜጣ ድረ-ገፅ ከቀናቶች በፊት እንደዘገበው አንቲዮኪያ በተባለ ቦታ  የተገኘው ገንዘብ ማንነቱ እንዳይገለጽ የፈለገው ገበሬ፣ የእርሻ ቦታውን ሲያሰፋ ከመሬት አንድ ሜትር በላይ ጥልቀት ላይ የተቀበሩ በርካታ የዛገ የብረት በርሜሎች አገኝቷል።

በርሜሎቹ በመቶዎች የሚቆጠሩ በጥቅል የታሰሩ በዋነኝነት የአሜሪካ ዶላር የባንክ ኖቶች የያዙ ሲሆን፣ እነዚህም በጥሩ ሁኔታ ተጠብቀው ተገኝተዋል።

የኮሎምቢያ ባለስልጣናት ግኝቱ እንደተነገረ ወዲያውኑ ገብተው የገንዘቡን ትክክለኛ ምንጭ ለመወሰን ምርመራ ጀመሩ። የመጀመሪያው ግምት እንደሚያሳየው፣ ገንዘቡ የ1980ዎቹ እና 1990ዎቹ የሜደሊን ካርቴል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በቀላሉ ህጋዊ ማድረግ ወይም ማንቀሳቀስ ስላልተቻለ ለማከማቸት ይጠቀሙባቸው ከነበሩት መደበቂያዎች አንዱ ሊሆን ይችላል ተብሏል።

ይህ የፓብሎ ኤስኮባር ገንዘብ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘበት አይደለም። ዝናው በከፍተኛ ደረጃ በነበረበት ጊዜ፣ የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪው ራሱ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በእርሻ ቦታዎችና በጫካ ውስጥ ደብቆ ነበር። ከእነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ በ1993 ከሞተ በኋላ ተረስተው ነበር።

ይህ ግኝት ስለ አፈ ታሪካዊው "ፓብሎ ኤስኮባር ሀብቶች" ፍላጎትን እንደገና አነሳስቷል፣ ነገር ግን የገበሬውን እና የቤተሰቡን ደህንነት በተመለከተም ስጋትን ፈጥሯል።

የጉስታቮ ፔድሮ መንግስት አሁን ገንዘቡን መውረስ ወይም ለገበሬው ሽልማት መስጠት እንዳለበት እያጤነ ነው።

@Addis_News
@Addis_News
42🤔2🔥1
የአሜሪካ አጠቃላይ እዳ ከ37 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ተሻገረ

ይህ እዳ ለአጠቃላይ የህዝብ ብዛቷ ቢካፈል 108,938 ዶላር በነፍስ ወከፍ ይደርስባቸዋል።አሜሪካን በዋናነት ለዚህ እዳ የዳረጋት  የምታወጣዉ ወጪ ከምታገኘው ገቢ ጋር ባለመመጣጠኑ ነው።

ይህ እዳ  ከአጠቃላይ የ GDP ገቢዋ ጋር ሲነፃፀር  123% ይይዛል።
አሜሪካ በብድር ብዛት ከአለም አንደኛ
ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

@Addis_News
@Addis_News
🤪2912👏2
🏆 አዲሱ ጌማችን "ቺከን ሮድ" 🐔 ተለቋል።

አንዲት ዶሮ መንገድ መሻገር ትፈልጋለች...🐓

አሁኑኑ ሁሉጌምስ ላይ ገብታችሁ ሞክሩት እና በጨዋታው ፈታ በሉ።

👇👇👇
🔗https://t.me/HulugameBot/startapp
4🤣1
ግብፅ በናይል ተፋሰስ ላይ "ዓለም አቀፍ ሕግን የጣሰ የተናጠል እርምጃን" እንደማትቀበል ለበርካታ የአፍሪካ አገራት አስታወቀች!

የሕዳሴ ግድብ በመጪው መስከረም ይመረቃል መባሉን ተከትሎ ግብፅ "የዓለም አቀፍ ሕግን በጣሰ መልኩ በምሥራቃዊ ናይል ተፋሰስ የሚደረግ የተናጠል እርምጃን" እንደማትቀበል ለበርካታ አፍሪካ አገራት አሳወቀች።

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ የናይል ተፋሰስ አገራት ከሆኑት ከሱዳን፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከኡጋንዳ፣ ከኬንያ እንዲሁም ከተፋሰሱ ውጭ ካሉት ከጂቡቲ እና ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በተናጠል ባደረጉት የስልክ ውይይት ነው ይህንን ያስታወቁት።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት 14 ዓመታትን የፈጀው እንዲሁም አምስት ቢሊዮን ዶላር ገደማ ወጪን የጠየቀው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ አምስተኛ ዙር ሙሌት ተጠናቆ ምረቃው በመጪው መስከረም እንደሚካሄድ ኢትዮጵያ በቅርቡ ማሳወቋን ተከትሎ ነው።

በግድቡ የውሃ ሙሌት እና ከግድቡ በሚለቀቀው የውሃ መጠን ላይ ከታችኛው ተፋሰስ አገራት ጋር ሕጋዊ እና አስገዳጅ ሦስትዮሽ ስምምነት ካልተፈረመ ኢትዮጵያ የውሃ ሙሌቱን ማከናወን እንደሌለባትም ስትወተውት የቆየችው ግብፅ ይህንኑ በመድገም ስታስጠነቅቅ ቆይታለች።

ይህንን አቋሟን በተለይም ኢትዮጵያ የሕዳሴን ግድብ አስመርቃለሁ ባለች ማግስት ያጠናከረች ሲሆን፤ ሚኒስትሩ "በናይል ወንዝ ላይ ዓለም አቀፍ ሕግን የሚቃረኑ የተናጠል እርምጃን ውድቅ ማድረጋቸውን" የግብፅ ሚዲያዎች አጽንኦት ሰጥተውታል።

@Addis_News
@Addis_News
16👍4🤔2
በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ያልተመለሱበት አማራ ክልል በቀጣይ ሳምንት የ2018 የትምህርት ዘመን ምዝገባ እንደሚጀምር አስታወቀ

ባለፉት አመታት በጸጥታ ችግር በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ተማሪዎቹ ወደ ትምህርት ገበታ ያልተመለሱበት የአማራ ክልል በ2018 የትምህርት ዘመን ሙሉ በሙሉ ለማስጀመር ዝግጅት ማድረጉን እያስተዋወቀ ይገኛል።

ክልሉ የተማሪዎች ምዝገባ በይፋ ነሃሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጀምር እና እስከ ነሃሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚቆይም አስታውቋል።

በአማራ ክልል ባለፉት ሁለት አመታት በጸጥታ ችግር ምክንያት በሚሊየኖች የሚቆጠሩ የክልሉ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው አመመለሳቸውን የክልሉ የትምህርት ቢሮ መረጃ ያሳያል። የመማር ማስተማሩ ሂደት የተቋረጠባቸው የክልሉ ቦታዎችም በርካታ ናቸው፡፡

ክልሉ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን 7 ሚሊየን ተማሪዎችን መዝግቦ ለማስተማር ቢያቅድም፤ የተመዘገቡት ተማሪዎች ቁጥር 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ብቻ ናቸው።

@Addis_News
@Addis_News
11😢2
Are u looking for unique gifts?

       🎁 ሀበሻ Gifts 🎁
ለልደት፣ለምርቃት፣ለሰርግ፣ለፍቅረኛሞች ስጦታ በሚፈልጉት ሰው ፎቶ ወይም በድርጅት ሎጎ እንሰራለን
@Habeshagifts1
Or Call us 0935199954

    ሰዓት በፎቶ , ኩባያ ህትመት ,እንጨት ላይ ህትመት , Puzzle ላይ ህትመት, ቁልፍ ላይ ህትመት ,  መስታወት ላይ ህትመት , የግድግዳ ሰዓት በፎቶ ወይም በድርጅት ሎጎ , Cube ላይ ህትመት , Stone ላይ ህትመት , ትራስ በፎቶ እና ሌሎች የGift Pakge እናዘጋጃለን ይዘዙን በፍጥነት እናደርሳለን ለበለጠ መረጃ linkun በመንካን Page ይመልከቱ @Habesha_Gift
               @Habesha_Gift
               @Habesha_Gift
5
የሶማሊላንዱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ለኖቤል የሰላም ሽልማት አጩ

የሶማሊላንዱ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ሞሀመድ አብዱላሂ (ኢሮ) የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ለኖቤል የሰላም ሽልማት በይፋ እጩ አድርገው አቀረቡ።

ኢሮ ትራምፕን ለሽልማቱ እጩ አርገው ያቀረቡትም በዓለማችን ላይ በጣም አሳሳቢ የሆኑ ግጭቶችን ለመፍታት ላደረጉት ጥረት ምስጋናቸውን በመግለጽ ነው።

የሶማሊላንድ ሁለተኛ ዋና ከተማ በሆነችው ቡሮአ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ኢሮ፤ በሩሲያና ዩክሬን መካከል ያለውን ጦርነት እንዲሁም በእስራኤልና በኢራን መካከል የነበረውን ውጥረት ጨምሮ አሜሪካ የተለያዩ ግጭቶችን ለማስቆም ላደረገችው ጥረት ምስጋናቸውን ገልጸው፤ ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኖቤል የሰላም ሽልማት እንዲሰጥ ድምፃቸውን እንደሚያሰሙ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ሞሀመድ አብዱላሂ (ኢሮ) በንግግራቸውም "የሶማሊላንድ ሪፐብሊክን እውቅና ለመስጠት ላሰቡት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ምስጋናዬን ማቅረብ እፈልጋለሁ" ያሉ ሲሆን፤ "ዛሬ እኔ እንደ ሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ግጭቶችን ለመፍታት እና በመላው ዓለም ሰላምን ለማምጣት ላደረጉት ጥረት ዕውቅና በመስጠት ለፕሬዝዳንት ትራምፕ የኖቤል የሰላም ሽልማት እንዲሰጣቸው ለመደገፍ ከዓለም አቀፍ መሪዎች ጎን መሰለፌን በይፋ አውጃለሁ" ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ኢሮ ይህን የገለጹት በትራምፕ አስተዳደር በቀጣናው በተለይም በሶማሊላንድ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ላይ ለውጥ ይመጣል ተብሎ በሚጠበቅበት ወቅት ሲሆን፤ ሶማሊላንድም ከሶስት አስርት ዓመታት በኋላ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ለማግኘት እየጣረች በምትገኝበት ወቅት መሆኑን ሆርን ዲፕሎማት ዘግቧል።

@Addis_News
@Addis_News
19😁13🤪3
የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ  አገልግሎት ለማግኘት የሚያመለክቱ ተገልጋዮች የሚከተሉትን ቅድመ-ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1. በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊና ሬጅስትራር ፊርማና ማህተም ያለበት ኦሪጅናል/temporary / ዲግሪ፤
2. በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊና ሬጅስትራር ፊርማና ማህተም ያለበት ኦሪጅናል ትራንስክሪፕት/Student Copy/፤
3. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘ ኦሪጅናል ዲፕሎማ ወይም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት፤
4. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘው የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ከሆነ በሀገር አቀፍ የት/ት ምዘናና ፈተናዎች አገልገሎት ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ ፤
5. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘው ዲፕሎማ ከሆነ ዲፕሎማው በተገኘበት ክልል የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ወይም የዞን/የከተማ መስተዳደር የሥራና ስልጠና ቢሮ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የደረጃ 4 ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት (COC) ፤
6. የዲግሪ መግቢያው ከውጭ በተገኘ የትምህርት ማስረጃ ከሆነ ከባለስልጣኑ የተገኘ የአቻ ግመታ ደብዳቤ፤
7. የሁለተኛ/የማስተርስ/ ዲግሪን ለማረጋገጥ ከሆነ ደግሞ በቅድሚያ የመጀመሪያው ዲግሪ ከላይ በተገለፀው መንገድ መረጋገጥ ይኖርበታል፤
8. የስም ለውጥ ካለ የፍርድ ቤት ውሳኔ የተላፈበት ማስረጃ፤
9. የማመልከቻ ክፍያ በኤሌክትሮኒክ ክፍያ በቴሌ ብር እና በሲኢቢ ብር ፤
10. ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የፋይዳ ልዩ ቁጥር FIN፤
11. ስካን (Scan) የተደረገ ሶስት በአራት (3x4) ጉርድ ፎቶግራፍ እና
12. ከላይ የተጠቀሱትን ሁሉም ማስረጃዎች አንድ አንድ ስካን (Scan) በማድረግ ባሉበት ሆነው በበይነ መረብ https://neta.gov.et ማስፈንጠሪያን በመጠቀም ማመልከት ይችላሉ፤
በተጨማሪም ቀጠሮ አስይዘው በአካል ሲመጡ በባለጉዳዩ ወይም ሕጋዊ የውክልና ሰነድ ባላቸው ተወካዮች አማካኝት  ሁሉንም የትምህርት ማስረጃ ዋናውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን

@Addis_News
@Addis_News
20👍5🤪2🔥1
Forwarded from LinkedIn Ethiopia
⚠️ ''ደሞዝተኛ እናድርግዎ''

🚨 በሳምንት ከ1,000 - 4,000 ብር ተከፋይ ይሁኑ

🌐 ከተከፈቱ ከአንድ ዓመት በላይ የሆኑ የLinkedin አካውንቶችን በማከራዬት በሳምንት ጠቀም ያለ ክፍያ ያግኙ !

⚠️መስፈርቶች

💠ከተከፈተ ከ1 ዓመት እና ከዛ በላይ የሆነ
💠ምንም Friend (Connection) ባይኖረውም እንከራያለን

📮 የክፍያው መጠን በተከፈተበት ዓመት ቆይታ ይወሰናል።

☎️+251934848429 ይደውሉልን

⬛️ በውስጥ መስመር ➡️
@linkedin_ethiop ያግኙን

🌐 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ➡️ @linkedin_ethiopiaa
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
3👍1
❗️ ትራምፕ ለዩክሬን እልባት ያቀረቧቸውን ሁሉንም ምክረ ሐሳቦች ዜለንስኪ “አይሆንም” ማለታቸውን ላቭሮቭ ተናገሩ

ምክረ ሐሳቦቹ አሜሪካ በዋሽንግተኑ ስብሰባ አስፈላጊ አድርጋ ያጤነቻቸውን እንደነበሩ ነው የገለፁት፡፡

ሞስኮ ከአላስካው ስብሰባ በኋላ ትራምፕ ላቀረቧቸው በርካታ ነጥቦች ግትር አለመሆኗን ለማሳየት  መስማማቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለምዕራባውያን ሚዲያ ተናግረዋል፡፡ 

👇 አሁን ላይ በፑቲን እና በዜለንስኪ መካከል ስብሰባ የማካሄድ እቅድ የለም፡፡ ነገር ግን የሩሲያው ፕሬዝዳንት የጉባኤው አጀንዳዎች እንደተዘጋጁ ለመሳተፍ ፈቃደኞች ናቸው፡፡ እንዲያም ሆኖ አስካሁን አለመዘጋጀታቸውንም የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናግረዋል፡፡

@Addis_News
@Addis_News
17🤔3
የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ በክልሉ የሚገኙ ከተማ እና ወረዳ አስተዳደሮች ለጤና ባለሞያዎች የዲዩቲ ክፍያ በጀት እንዲይዙ መመሪያ ሰጠ።

በአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ አታላይ ጥላሁን ተፈርሞ በሁሉም በክልሉ ለሚገኙ ከተማ እና ወረዳ አስተዳደሮች የተላከው ሰርኩላር፣ በየደረጃው የሚገኙ አስተዳደሮች ለጤና ባለሞያዎች የትርፍ ሰአት ስራ (ዲዩቲ) ክፍያ በጀት እንዲይዙ መመሪያ መሰጠቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከደብዳቤው ተመልክቷል።

ደብዳቤው " የጤና ስራ በየትኛውም ሁኔታ የማይቋረጥ ስራ በመሆኑ ባለሙያዎች የዲዩቲ እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን በተመለከተ በመንግስት ጤና ተቋማት ለሚያገለግሉ የጤና ሙያተኞች የዲዩቲ እና የኃላፊነት አበል ክፍያ መወሰኛ የአማራ ብሔራዊ ክልል መስተዳድር ም/ቤት መመሪያ ቁጥር 20/2006 ዓ.ም በማጽደቅ ላለፉት 12 ዓመታት ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል " ሲል ያብራራል።

ነገር ግን አንዳንድ ወረዳዎች እና ከተሞች በጀት ሲይዙ እንደ ግዴታ ወጭ አለመያዛቸው እና አቆራርጠው መክፈላቸው ቅሬታ እና የመልካም አስተዳደር ችግር ፈጥሯል ብሏል።

ይህንን ችግር በመግለጽም መፍትሄ እንዲሰጥበት በክልሉ ጤና ቢሮ በደብዳቤ መጠየቁን ሰርኩላሩ ጠቅሷል።

ጥያቄውን የተቀበለው የገንዘብ ቢሮም ሁሉም ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር በበጀት ምደባ ወቅት የዲዩቲ በጀት የግዴታ ወጪ መሆኑን በመገንዘብ አስፈላጊውን የበጀት ምደባ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

via_tikvah

@Addis_News
@Addis_News
6🤔1
አዲስ ነገር መረጃ
Video
“ሞት በጥር… በነሐሴ መቃብር”

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ሦስት ዓመት ከቤተሰቧ ጋር፤ አሥራ-ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ፤ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀናት ጌታን ጸንሳ፤ ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ከጌታችን ጋራ፤ አሥራ አምስት ዓመት በወንጌላዊው ዮሐንስ ቤት ከኖረች በኋላ በስድሳ አራት ዓመቷ ጥር ሃያ አንድ ቀን አርፋለች። ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 131÷8 “አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦትም” በማለት ስለእመቤታችን እረፍት በምሥጢር ይገልጻል። ይህን ቃለ ትንቢት የተናገረው ፈጣሪዬ ሆይ ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህን ታቦት ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ ሲል ነው። ይህም እመቤታችን እንደ ልጇ ትንሣኤ መነሣቷን የሚያመለክት ነው። ታቦት ያላትም ማደሪያው ስለሆነች ነው። እመቤታችን ስታርፍ ቅዱሳን ሐዋርያት ሊቀብሯት ቅዱስ ስጋዋን ይዘው ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲሄዱ አይሁድ በምቀኝነት ተነሱ፡፡

“ቀድሞ ልጇን ተነሣ፣ አረገ፤ እንደገናም ይህን ዓለም ለማሳለፍ ተመልሶ ይመጣል” እያሉ በማስተማር ሕዝቡን ፈጽመው ወስደውታል። አሁን ደግሞ እርሷንም እንደ ልጇ ተነሣች፤ ዐረገች እያሉ በማስተማር ሲያውኩን አይደለምን? “ኑ! በእሳት እናቃጥላት” ብለው መጡ፡፡ ከመካከላቸው ታውፍንያ የተባለ አይሁዳዊ ስጋዋን ያለበትን አልጋ ሸንኮር ተራምዶ ሲይዝ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሠይፍ ሁለት እጆቹን ቆረጠውና ተንጠልጥለው ቀሩ። በፈጸመው ድርጊት ተጸጽቶ ወደ እመቤታችን ስለተማጸነ በተአምር የተቆረጡ እጆቹን ፈውሳዋለች። በዚያ ጊዜም መልአክ እግዚአብሔር እመቤታችንና ቅዱስ ዮሐንስን ወስዶ በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጣቸው ቅዱስ ዮሐንስም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደ ሐዋርያት ሲመጣ የእመቤታችን አስከሬን በገነት መኖሩን ነገራቸው።

ሐዋርያትም ዮሐንስ ይህን ክብር አይቶ፣ እኛ ሳናይ ብለው በነሐሴ 1 ቀን ሱባኤ ጀምረው በ14ኛው ቀን ጌታችን ስጋዋን ሰጥቷቸው በታላቅ ዝማሬና ውዳሴ በጌቴሴማኒ ቀበሯት። በሶስተኛው ቀን ተነስታ ስታርግ ቅዱስ ቶማስ አልነበረምና ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ ያገኛታል። ያን ጊዜም ትንሣኤዋን ሌሎች ሐዋርያት አይተው እርሱ የቀረበት መስሎት በፊት የልጅሽን ትንሣኤ አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ ብሎ በሀዘን ከደመናው ተወርውሮ ሊወድቅ ቃጣው። እመቤታችንም ከእርሱ በቀር ሌሎቹ ሓዋርያት ትንሣኤዋን እንዳላዩ፣ ለሐዋርያት የሆነውን ሁሉ እንዲነግራችው አዝዛው ለምልክት ይሆነው ዘንድ የተገነዘችበትን ሰበኗን ሰጥታው ወደ ሰማይ ዐርጋለች። ሐዋርያትም ቅዱስ ቶማስ ስለእመቤታችን ሲጠይቃቸው አጊኝተን ቀበርናት አሉት። እርሱም የያዘውን ያውቃልና “አይደረግም! ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንደምን ይሆናል?” አላቸው።

ቅዱስ ጴጥሮስም ተቆጥቶ “አንተ እንጂ፤ ቀድሞ የጌታን ትንሣኤ ተጠራጠርክ። አሁንም አታምንምን?” ብሎ ወደ እመቤታችን መካነ መቃብር ቢሔድ አጣት፤ ደነገጡ፡፡ ቅዱስ ቶማስ “አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችንስ ተነሥታ ዐርጋለች” ብሎ ሰበኗን ሰጣቸው። ለበረከት ቆራርጠው ከተከፋፈሉ በኋላ ወደየአህጉረ ስብከታቸው ሄደዋል። በዓመቱ ቶማስ ትንሣኤሽን አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ነሐሴ 1 ቀን ሱባኤ ገቡ፡፡ በነሐሴ 16 ቀን ጌታችን እመቤታችንን መንበር፤ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቅ ቄስ፤ ቅዱስ እስጢፋኖስን፤ ገባሬ-ሠናይ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ አቁርቧቸው የእመቤታችንን ዕርገቷን ለማየት አብቅቷቸዋል። ሐዋርያዊቷ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንም ይህን ታላቅ ጾም ከሰባቱ አጽዋማት ተርታ አስገብታ ትጾማለች። ከብርሃነ ትንሣኤዋ ረድኤት በረከት ያሳትፈን፡፡ ገዳማውያንም በጾምና በጸሎት ይህን በረከት ያገኛሉ፡፡ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን ከበረከታቸው እንሳተፍ፡፡
ካለን ላይ ለተቸገሩ በማካፈል ለነፍሳችን ስንቅን እንያዝ

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
49👍2
መንግስት 541 የሕግ ታራሚዎች በይቅርታ ወደ መጡበት ማህበረሰብ እንዲቀላቀሉ ማድረጉን ገለፀ

መንግሥት በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በከፍተኛ ጥበቃ፣ በዝዋይ፣ በድሬዳዋ፣ በሸዋ ሮቢት፣ በቀጠሮ እና በሴቶች ማረሚያ እና ማረፊያ ማዕከላት ውስጥ በእርምት ሂደት ላይ ለነበሩ እና የባህሪ መሻሻል ላሳዩ፤ 541 የሕግ ታራሚዎች በይቅርታ ወደ መጡበት ማህበረሰብ እንዲቀላቀሉ መደረጉ ተገልጿል፡፡

በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሸን የታራሚዎች ፍትህ አስተዳደር ዳይሬክተር ረ/ኮሚሽነር ሲሳይ ሃይለ እየሱስ፤ ለሕግ ታራሚዎች ይቅርታ የሰጠው ይቅርታ ቦርድ ጉዳዩን ሲከታተል መቆየቱን ገልጸው፤ የባህሪ መሻሻል ላሳዩ 32 ሴት እና 509 ወንድ በድምሩ ለ 541 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ መሰጠቱን አረጋግጠዋል፡፡

@Addis_News
@Addis_News
11👍4

7
የባንክ ሰራተኞች በግዴታ ደንበኛ እንዲያመጡ የሚያስገድዱበትን አሰራር እንደሚመረምር ብሔራዊ ባንክ ለሚድያችን አስታወቀ

"እውነት ለመናገር ጉዳዩን አናውቀውም ወይም አልሰማንም ማለት አችልም፣ ነገር ግን በተባለው መጠን ሰራተኞች እየተንገላቱ እና ከስራቸው እስከመባረር ጭምር እየደረሱ ከሆነ እናየዋለን።"

ምንጭ : meseret media

@Addis_News
@Addis_News
30👍15🤔2
ዩክሬን 15 ሺሕ የሮቦት ተዋጊዎችን ልታሰማራ እንደምትችል አስታወቀች

ሁለት ሚልዮን ወታደሮቿን በሞትና በተለያዩ ምክንያቶች አጥታለች የተባለችው ዩክሬን፤ በጦር ግንባር ከሩሲያ ጦር ጋር ሊዋጉ የሚችሉ 15 ሺሕ ሮቦቶችን ልታሰማራ እንደምትችል የኬይቭ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን ተናግረዋል።

በቅርቡ ሾልከው የወጡ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ኪየቭ እ.ኤ.አ ከ2022 ጀምሮ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ወታደሮችን በጦርነቱ አጥታለች።

ወደ 400 ሺሕ የሚጠጉ ወታደሮች የጦር ክፍሎቻቸውን ጥለው መሄዳቸውን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት የገለጹ ሲሆን፤፤ የተዋጊዎች መመናመን መቀጠሉን እና ብዙዎቹ የመመለስ ፍላጎት እንደሌላቸው መታወቁን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የሩሲያ ጦር ከሦስት ዓመት በላይ የተቆጣጠራቸውን የዩክሬን ግዛቶች ሳይለቅ፤ ተጨማሪ ጥቃት በመክፈት ወደ ፊት እየገሰገሰ መሆኑ ሮይተርስ ዘግቧል።

@Addis_News
@Addis_News
19🤣8🤔3🤪3
ናይጄሪያ በክሪፕቶና በፍቅር ማጭበርበር የተከሰሱ ከ100 በላይ የውጭ ሀገር ዜጎችን ከሀገሯ አስወጣች

ናይጄሪያ 60 ቻይናውያን እና 39 የፊሊፒንስ ዜጎችን ጨምሮ 102 የውጭ ሀገራት ነዋሪዎችን በኢንተርኔት ማጭበርበር እና የሳይበር ወንጀሎችን ተሳትፎ ከሀገሯ ማስወጣቷን የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እና የፋይናንስ ወንጀሎች ኮሚሽን አስታወቀ። እርምጃው ተጎጂዎችን ወደ ሀሰተኛ የክሪፕቶ ኢንቨስትመንቶች እና የማጭበርበር የኦንላይን የፍቅር ግንኙነቶች ላይ ያነጣጠረ ነው ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

ኮምሽኑ ከኦገስት 15 ጀምሮ ተጨማሪ ምርመራዎቾንና እርምጃዎችን አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል። የናይጄርያ መንግስት በዘመቻው 192 የውጭ ዜጎችን ጨምሮ 792 ተጠርጣሪ የሳይበር ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰራ ሲሆን ይህ ዘመቻ የተጀመረውም በታህሳስ ወር ሌጎስ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ ነው።

ባለሙያዎች እነዚህ ወንጀለኞች በአብዛኛው አሜሪካውያንን፣ ካናዳውያንን፣ ሜክሲካውያንን እና አውሮፓውያንን ላይ በማነጣጠር ጥቃት የሚፈፅሙ ሲሆን በተለይም ደካማ የሳይበር ደህንነት ስርዓቶችን የሚጠቀሙትን ላይ በማነጣጠር ለከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ እንደሚዳርጉ ይነገራል።

@Addis_News
@Addis_News
14👍2