አዲስ MAGAZINE - መረጃ
31.3K subscribers
6.5K photos
224 videos
3 files
262 links
#አዲስ_Magazine_መረጃ

#መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ

#ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addis_Magazinebot

Addis Ababa , Ethiopia

የአዲስ ነገር መረጃ ቻናል አጋር ሚዲያ
Download Telegram
የድምፃዊ ቴዲ አፍሮን አዲስ አልበም "ኢትዮሪካ"ን አስመልክቶ ዛሬ ሊሰጥ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ በይፋ መታገዱ መነጋገሪያ ሆናኗል።

በሚሊዮኖች ዘንድ በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን የድምፃዊ ቴዲ አፍሮን አዲስ አልበም "ኢትዮሪካ"ን አስመልክቶ ዛሬ ሊሰጥ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ በይፋ መታገዱ በሀገሪቱ የፖለቲካ እና የጥበብ ምህዳር ላይ ትልቅ መነጋገሪያ ፈጥሯል።

ቴዲ አፍሮ ይህንን ወሳኝ መግለጫ ከአርትስ ቲቪ (Arts TV) ጋር በመተባበር በቀጥታ ስርጭት ለህዝብ ለማድረስ አስቀድሞ ስምምነት ፈፅሞ የነበረ ቢሆንም፤ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በጣቢያው ላይ ባስተላለፉት ጥብቅ ትዕዛዝ እና እገዳ ስርጭቱ ሙሉ ለሙሉ ሊቋረጥ ችሏል።

ይህ ያልተጠበቀ የእገዳ እርምጃ የመነጨው አዲሱ የቴዲ አልበም ከፍተኛ ፖለቲካዊ እና ወቅታዊ ሀገራዊ ትችቶችን ያዘለ ይዘት ይኖረዋል ከሚል የመንግስት ከፍተኛ ስጋት እና ድንጋጤ እንደሆነ የፖለቲካ ታዛቢዎች በስፋት እየገለፁ ይገኛሉ።

​ይሁን እንጂ መንግስት የቴዲን ድምፅ ለማፈን እና መልዕክቱ እንዳይተላለፍ የወሰደው ይህ እርምጃ፤ ያልታሰበ ተቃራኒ ውጤት በማምጣት ለአልበሙ ትልቅ የማወቅ ጉጉት ከመፍጠሩም በላይ በቢሊዮን የሚገመት ታሪካዊ "ነፃ ማስታወቂያ" ሰርቶለታል እየተባለ ይገኛል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
🤣13🙉21
መፍትሄው እግረኛ ጦር ነው-UAE‼️
ከኢራን ጋር በእግረኛ ጦርነት ካልተደረገ በስተቀር ምንም መፍትሄ የለም' ሲሉ 'የሳውዲ ንጉሣዊ ቤተሰብ' ለ N12 ገልፀዋል።
እ.ኤ.አ 'በ 2003 በሳዳም አገዛዝ ላይ የተካሄደው የመሬት ላይ ጦርነት በኢራን ላይ መደገም አለበት፣'የኢራን መንግስት የኒውክሌር አላማ ስላለው በጣም አደገኛ ነው ብለዋል።
ለዚህ ብቸኛው መፍትሔ ወደ ኢራን እግረኛ ጦር ማስገባት ነው፣ ሌላ መፍትሔ የለውም ብለዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
8😁4
የሃንጋሪ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፑቲን ስልክ ከደወሉ የዩክሬንን ጦርነት እንዲያቆም እነግራቸዋለሁ ሲሉ አስታወቁ

ፒተር ማጃር በምርጫ ማሸነፋቸዉ በታወጀ በመጀመሪያዉ ቀን ከ10 የአውሮፓ ሀገራት መሪዎች ጋር መነጋገራቸዉን ያስታወቁ ሲሆን ሃንጋሪን ለ16 ዓመታት የመሩት ቪክተር ኦርባን የስልጣን ዘመን እንዲያበቃ ማድረግ ችለዋል፡፡ለቀድሞ መሪ ኦርባን የቅርብ አጋር ወደሆኑት ቭላድሚር ፑቲን ስልክ እንደማይደዉሉ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፒተር ማጃር ተናግረዋል፡፡

እሁድ እለት የቲሳ ፓርቲያቸው ምርጫዉን ማሸነፉን ተከትሎ ለሶስት ሰአት በዘለቀዉ እና ማራቶን በተሰኘዉ ጋዜጣዊ መግለጫቸዉ ላይ ሲናገሩ "ቭላድሚር ፑቲን ከደወለ ስልኩን አነሳለሁ" ሲሉ አክለዋል፡፡ ግን"ይህ የሚሆን አይመስለኝም" ብለዋል፣ "ነገር ግን ነገሮች ተለዉጠዉ ስልክ ደዉለዉልኝ ከተነጋገርን እባክህ ከአራት አመታት በላይ የቀጠለዉን የዩክሬን ግድያን እንዲያቆሙ እና ይህንን ጦርነት እንዲያቆም እነግራቸዉ ነበር።" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ሞስኮ የማጊርን የምርጫ ድል እንደምታከብር በመግለጽ ከቡዳፔስት ጋር ያላትን "ተግባራዊ" ግንኙነቶች እንደምትጠብቅ ተናግራለች።ኦርባን የእሁዱን ምርጫ እንዲያሸንፉ የደገፉት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቁልፍ አጋር ሲሆኑ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ባለፈው ሳምንት የሁለት ቀን ጉብኝት በማድረግም ግንኙነታቸዉን አጠናክረዉ ነበር፡፡

ማጂያ ወደ ትራምፕም ስልክ እንደማይደውሉ ለጋዜጠኞች የተናገሩ ሲሆን ነገር ግን ትራምፕ ስልክ ቢደውሉላቸው "የኔቶ ጠንካራ አጋሮች በመሆናቸው ደስተኛ ነኝ" እንደሚሉ እና ሀንጋሪ በመጪው ጥቅምት ወር በሶቪየት ወረራ ላይ የተቃጣበትን 70ኛ ዓመትን ስታከብር በእንግድነት እንዲገኙ እንደሚጋብዙ መናገራቸዉ ተሰምቷል፡፡

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
8😁3
ኮማንደር አልማዝ ዮሐንስ በተፈፀመባቸው ጥቃት ህይወታቸው አለፈ

በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ በፖሊስ ከፍተኛ አመራርነት ህዝባቸውን ሲያገለግሉ የቆዩት ኮማንደር አልማዝ ዮሐንስ፣ ሚያዝያ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11:35 ላይ በታጠቁ ኃይሎች በደረሰባቸው ጥቃት ህይወታቸው አልፏል።

ኮማንደር አልማዝ ለትንሳኤ በዓል ወደ ቤተሰቦቻቸው መጥተው፣ በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ (ዋር ኮሌጅ) የሚከታተሉትን የስትራቴጂክ አመራር ስልጠና ለመቀጠል ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ ሳሉ ነው ይህ አሰቃቂ ጥቃት የደረሰባቸው።

በፖሊስ ሰራዊት ውስጥ ለ21 ዓመታት በታማኝነት ያገለገሉት ኮማንደሯ፣ በስራቸው ጠንካራና ለብዙዎች አርአያ ከመሆናቸውም ባለፈ፣ ለድሆችና ለተበደሉ ሰዎች ድምፅ በመሆን የሚታወቁ እናት ነበሩ።

ከሙያዊ ግዴታቸው ጎን ለጎን የተቸገሩ ወገኖችን በማስተባበርና በመርዳት የሚታወቁት ኮማንደሯ፣ የባለ ትዳርና የሦስት ልጆች እናት ነበሩ ሲል የከምባት ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
💔87
የኢራን አምባሳደር አሜሪካ የኢራን ወደቦችን መዝጋቷ "ከባድ" የሉዓዊነት “ጥሰት” ነው አሉ!

በመንግሥታቱ ድርጅት የኢራን አምባሳደር አሜሪካ የኢራን ወደቦችን መዝጋቷን የቴህራን ሉዓላዊነት ላይ የተፈፀመ “ከባድ ጥሰት” ሲሉ አወገዙ።

አምባሳደር አሚር ሳይድ ኦራቫኒ ለተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በፃፉት ደብዳቤ “ሕገ ወጥ” የሆነው እግድ “የዓለም አቀፍ የባሕር ሕግ መሠረታዊ መርህዎች ላይ ከባድ ጥሰት የሚፈፅም” ነው ብለዋል።

ጉቴሬዝ “ሁሉም ወገኖች” ለዓለም የነዳጅ ዝውውር ቁልፍ በሆነው የሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የመርከቦችን ነፃ እንቅስቃሴ እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በአሜሪካ እና ኢራን መካከል በፓኪስታን የተደረገው የሰላም ንግግር ያለ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ የአሜሪካ ጦር ከትናንት ሠኞ ጀምሮ የኢራን ወደቦችን ዘግቷል።

የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) እግዱ “ያለ ልዩነት” ወደ ኢራን ወደቦች ወይም የባሕር ዳርቻ አካባቢዎች በሚገቡ እና በሚወጡ የሁሉም አገራት መርከቦች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆን አስታውቋል።

ሆኖም ጦሩ በሆርሙዝ ወሽመጥ ከኢራን ወደቦች ውጭ የሚንቀሳቀሱ መርከቦችን እንደማይከለክል ገልጿል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
😁63
ለድርድሩ ዝግጁ ነኝ-ኢራን‼️
ሁለተኛው ዙር የአሜሪካ-ኢራን ድርድር በግብፅ ወይም በቱርክ ሊካሄድ ይችላል ተባለ። ብሉምበርግ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው እንደተናገሩት የአሜሪካ እና ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነቱ በሚቀጥለው ሳምንት ከመጠናቀቁ በፊት ለሁለተኛ ጊዜ እንደሚደራደሩ ዘገባው ገልጿል። ኢራን ለድርድሩ ዝግጁ መሆኗን ለፓኪስታን አረጋግጣለች።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
👍82😁2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይህ ቪዲዮ በሀገራችን በአምቦ የተከናወነ አሳዛኝ ድርጊት እንደሆነ እየተነገረ ነው። የሰው ልጅ በዚህ መልኩ መደብደቡ ቁጣን ቀስቅሷል። ድርጊቱ በአምቦ የተከናወነ እንደሆነ እየተገለጸ ይገኛል።


@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
😢16😡52
የሶማሊያ ነዳጅ ሊወጣ ነው

ሶማሊያ ከቱርክ ጋር በመተባበር የጀመረችው የነዳጅ ፍለጋና የወታደራዊ ግንባታ የቀጠናውን ጂኦ-ፖለቲካዊ ሚዛን እየቀየረ ነው።

ግዙፏ የቱርክ መርከብ "ቻግሪ ቤይ" ሥራ የጀመረች ሲሆን፣ ከሁለት ዓመት በኋላ ሶማሊያ በቀን 500 ሺህ በርሜል ነዳጅ በማምረት በዓመት 18 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ታገኛለች ተብሎ ይጠበቃል።

በቱርክ ድጋፍ የF-16ተዋጊ ጄቶች፣ ዘመናዊ ሄሊኮፕተሮችና የሳተላይት ማዕከል የታጠቀችው ሶማሊያ፤ አልሸባብንና የውስጥ አማጺያንን የመመከት አቅሟን እያጠናከረች ነው።

ሶማሊያ እነዚህን ዕድሎች ከተጠቀመችባቸው፣ የቀጠናው አዲስ ጉልበት ሆና እንደምትወጣ አዝማሚያዎች ያሳያሉ።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
7👍7👏2🤣2😢1
ትክክለኛ የባህል መዳኒት ይፈልጋሉ??
👆መርጌታ
የባህል ህክምና 0915398834


1🌿ለሀብት ማምጫ
2🌿ለእቁብ (እቁብ እንዲወጣላችሁ የሚያረግ)
3ለመስተፋቅር
4🌿 &መጠብቅ (ከጠላት ከሚላክ ሟርት የሚጠብቅ)
5🌿ለጋኔን
6🌿ለማንኛውም ዓይነት በሽታ መፍትሔ
7🌿ለራእይ (በህልም የሚያሳይ)7
8🌿  ለፀር (ለጠላት)
9🌿ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)
10🌿 ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)
11🌿ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)
12🌿ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)
13🌿 መስተፋቅር
14🌿ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
15🌿ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ
16🌿ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)
17🌿የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ
18🌿ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)
19🌿መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)
20🌿መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)
21🌿ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)
22🌿ለልሳነ_ሰብእ
23🌿ለበረከት
24🌿ለእግረ_መልስ (ጥሎ ለጠፋ ሰው መመለሻ ማምጫ)
25🌿ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)
26🌿ጸሎተ_ዕለታት
27🌿ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ
28🌿ንባብ ስናነብ ቀልጣፋ የሚያረግ
29🌿ለከበሮ
30🌿ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)
31🌿ለሙግት
32🌿ለሰላቢ
33🌿ለስንፈት ወሲብ
34🌿ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)
35🌿ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)
36🌿ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)

በ 0915398834  ይደውሉልን
1
ቀጣይ የአሜሪካ እና ኢራን ድርድር

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው የሰላም ንግግር በሁለት ቀናት ውስጥ ሊቀጥል እንደሚችል ፕሬዝዳንት ትራምፕ ገለጹ።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተቋረጠው የሰላም ድርድር በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ በፓኪስታን ዋና ከተማ ኢስላማባድ ሊቀጥል እንደሚችል አስታወቀዋል።

ፕሬዝዳንቱ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ድርድሩ በድጋሚ እንዲጀመር የፓኪስታን ጦር አዛዥ ጄነራል አሲም ሙኒር እያደረጉት ያለውን ጥረት አድንቀዋል። ትራምፕ ጄነራሉን ድንቅ ሰው ሲሉ የገለጿቸው ሲሆን የእሳቸው ሚና ለውይይቱ መሳካት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው አመልክተዋል።

ድርድሩ  በፓኪስታን አስተናጋጅነት በኢስላማባድ እንደሚካሄድ ይጠበቃል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ "ወደዚያው የመመለስ ዕድላችን ሰፊ ነው" በማለት ፍንጭም ሰጥተዋል።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል የተጀመረው ድርድር ያለ ስምምነት ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል።

ዘገባው የ ዘ ጋርዲያን ነው

በ-ሰላማዊት ወልደገሪማ

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
1
አነጋጋሪው የትራምፕ እና የሜሎኒ ፍጥጫ

በአንድ ወቅት የቅርብ የፖለቲካ አጋርና ጓደኛ የነበሩት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ባልተጠበቀ የቃላት ምልልስ ውስጥ መግባታቸው በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

ትራምፕ ከጣሊያኑ ኮሪየሬ ዴላ ሴራ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ በሜሎኒ አቋም እጅግ መገረማቸውንና "ደንግጫለሁ" ሲሉ በግልጽ ተናግረዋል።

ለዚህ ውጥረት እንደ ዋነኛ መንስኤ የተጠቀሰው ሜሎኒ አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ በምትከተለው ወታደራዊ አቋም ላይ ያሳየችው ተቃውሞ ነው።

በተለይም ጣሊያን በኢራን ላይ በሚወሰድ እርምጃ እንደማትሳተፍ መግለጿ ትራምፕን ክፉኛ ያስቆጣ ሲሆን፣ ፕሬዝዳንቱ ይህንን ውሳኔ "ድፍረት ማጣት" ሲሉ ነቅፈውታል።

በተጨማሪም ትራምፕ በሊቀ ጳጳሱ ላይ ለሰነዘሩት ትችት ሜሎኒ የሰጠችው "ተቀባይነት የሌለው ንግግር ነው" የሚል ምላሽ በእሳቸውና በጣሊያኗ መሪ መካከል ያለውን ልዩነት ይበልጥ አጉልቶታል።

ትራምፕ በቃለ መጠይቁ ወቅት "በእሷ በጣም ደንግጫለሁ፤ ድፍረት ያላት ይመስለኝ ነበር፣ ነገር ግን ተሳስቻለሁ" በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት ከሁለቱም መሪዎች ቢሮዎች በይፋ የተሰጠ ተጨማሪ መግለጫ ባይኖርም፣ ጉዳዩ በማህበራዊ ሚዲያና በዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች ላይ አሁንም ከፍተኛ ትኩረት አግኝቶ ቀጥሏል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
👍4👏2
ቀጣይ የአሜሪካ እና ኢራን ድርድር

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው የሰላም ንግግር በሁለት ቀናት ውስጥ ሊቀጥል እንደሚችል ፕሬዝዳንት ትራምፕ ገለጹ።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተቋረጠው የሰላም ድርድር በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ በፓኪስታን ዋና ከተማ ኢስላማባድ ሊቀጥል እንደሚችል አስታወቀዋል።

ፕሬዝዳንቱ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ድርድሩ በድጋሚ እንዲጀመር የፓኪስታን ጦር አዛዥ ጄነራል አሲም ሙኒር እያደረጉት ያለውን ጥረት አድንቀዋል። ትራምፕ ጄነራሉን ድንቅ ሰው ሲሉ የገለጿቸው ሲሆን የእሳቸው ሚና ለውይይቱ መሳካት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው አመልክተዋል።

ድርድሩ  በፓኪስታን አስተናጋጅነት በኢስላማባድ እንደሚካሄድ ይጠበቃል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ "ወደዚያው የመመለስ ዕድላችን ሰፊ ነው" በማለት ፍንጭም ሰጥተዋል።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል የተጀመረው ድርድር ያለ ስምምነት ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል።

@Addis_Magazine
3
“ወደ አዲስ አበባ የተጓዝኩት ከዶ/ር ደብረፅዮን ጋር ተመካክሬ ነው” ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ወደ አዲስ አበባ ያደረጉት ጉዞ ከህወሓት ሊቀ-መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ጋር በመመካከርና በመስማማት እንደነበር አስታወቁ።

ፕሬዝዳንቱ በሰጡት መግለጫ በአዲስ አበባ በነበራቸው ቆይታ ተፈናቃዮችን መመለስ፣ የክልሉን በጀትና የመድኃኒት እጥረት እንዲሁም በጅቡቲ ወደብ የቀሩ ትራክተሮችን በተመለከተ ለፌዴራል መንግሥት ሪፖርት ማቅረባቸውን ገልጸዋል።

የስልጣን ዘመናቸው ለአንድ ዓመት መራዘሙን በተመለከተም፣ ውሳኔው በክልሉ የመንግሥት አልባነት ክፍተት እንዳይፈጠር ከፌዴራል መንግሥት ጋር ቀደም ብሎ ሲመከርበት የቆየ መሆኑን አስገንዝበዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
3
ለአስም ህመምተኛ አስምን ሊያስነሱ/ሊቀሰቅሱ የሚችሉ ነገሮች

አቧራ (በተለይ የቤት ውስጥ እና በውስጡ ያሉ ጥቃቅን ተህዋሲያን)

የአበባ ዱቄት (ከእጽዋት የሚገኝ)

ሻጋታ

የእንስሳት ጸጉር ወይም ፎሮፎር (ለምሳሌ የድመት፣ የውሻ)

በረሮ እና ተረፈ ምርቱ

የትምባሆ ጢስ (ሲጋራ ማጨስ ወይም የሚጨስበት ቦታ መገኘት)

የአየር ብክለት (ከፋብሪካ፣ ከመኪና የሚወጣ ጭስ)

ሌሎች ጭሶች (ለምሳሌ የእንጨት ወይም የቆሻሻ ማቃጠል ጭስ)

ጠንካራ ሽታዎች (ሽቶ፣ የጽዳት ኬሚካሎች፣ የቀለም ሽታ፣ ወዘተ)

ጉንፋን፣ ፍሉ እና ሌሎች የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽኖች

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ (በተለይ በብርድ እና ደረቅ አየር ውስጥ ሲሰራ)

ቀዝቃዛ አየር

ድንገተኛ የአየር ንብረት ለውጥ

ከፍተኛ ስሜት (ውጥረት፣ ጭንቀት፣ በጣም መሳቅ ወይም ማልቀስ)

አንዳንድ ምግቦች ወይም መጠጦች (ለምሳሌ ሰልፋይት ያለባቸው የታሸጉ ምግቦች፣ ወይን)

አንዳንድ መድሃኒቶች (ለምሳሌ አስፕሪን፣ ሌሎች የህመም ማስታገሻዎች - ሀኪምን ሳያማክሩ አይውሰዱ)

የጨጓራ አሲድ ወደ ጉሮሮ መመለስ (GERD)

ማሳሰቢያ: ለእያንዳንዱ ሰው አስም ቀስቃሽ የሆኑ ነገሮች ሊለያዩ ይችላሉ። የእርሶን የአስም ቀስቃሾች በትክክል ለይቶ ለማወቅ እና ለመቆጣጠር ከሀኪምዎ ጋር መማከር አስፈላጊ ነው።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
👍2
ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ እያነሳች ባለችበትና ከኤርትራ ጋር ያለው ውጥረት በጨመረበት በአሁኑ ወቅት የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኤርትራ የግዛት አንድነት ሙሉ ድጋፍ እንዳላቸው አስታወቁ።

በከፍተኛ የኤርትራ ባለስልጣናት የሚመራ ልዑክ ካይሮ በመሄድ ከግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደልአጢ ጋር የተወያየ ሲሆን፤ ሚኒስትሩ ግብፅ ከኤርትራ ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነት እንዳላት ገልጸዋል።

ሚኒስትር ባድር አብደልአጢ አክለውም፤ ግብፅ ለኤርትራ ሉዓላዊነት፣ አንድነት እና የግዛት ደህንነት ሙሉ ድጋፍ እንዳላት ተናግረዋል።

ይህ መግለጫ የተሰጠው በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት በበረታበት በዚህ ወቅት ነው።

በግብፅ ጉብኝት እያደረገ የሚገኘውና በሕግደፍ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ኃላፊ በአቶ ሐጎስ ገብረሂወት የሚመራው የኤርትራ ልዑካን ቡድን፣ ከተለያዩ የሀገሪቱ ከፍተኛ መሪዎች ጋር በመገናኘት ላይ ይገኛል።

ከቀናት በፊት የቻይና የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ በአስመራ ተገኝተው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
10😁2