አዲስ MAGAZINE - መረጃ
31.3K subscribers
6.5K photos
224 videos
3 files
262 links
#አዲስ_Magazine_መረጃ

#መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ

#ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addis_Magazinebot

Addis Ababa , Ethiopia

የአዲስ ነገር መረጃ ቻናል አጋር ሚዲያ
Download Telegram
ንቦች በጭስ ጊዜ ለምን አይናደፉም? የንቦች አስገራሚው የተፈጥሮ ምስጢር!

ንብ አርቢዎች ወደ ንብ ቀፎ ከመጠጋታቸው በፊት ጭስ ሲጠቀሙ አስተውለው ያውቃሉ? ይህ የሚደረገው ንቦቹን ለማባረር ሳይሆን በውስጣቸው ያለውን የመከላከያ ስሜት በሁለት አስገራሚ መንገዶች ለማደንዘዝ ነው።

በመጀመሪያ፣ ጭሱ ንቦች እርስ በእርሳቸው የሚግባቡበትን የሽታ ምልክት (Pheromones) ያውከዋል። አንዲት ንብ አደጋ ሲሰማት ሌሎቹን ለማንቃት የምታመነጨውን የጥንቃቄ ሽታ ጭሱ ስለሚሸፍነው፣ ንቦቹ ተባብረው ጥቃት መሰንዘር አይችሉም።

በሁለተኛ ደረጃ፣ ጭሱ በንቦቹ ዘንድ "ሰደድ እሳት ተነስቷል" የሚል የድንጋጤ ስሜት ይፈጥራል። በዚህ ጊዜ ንቦቹ ቀፎውን ጥለው ለመውጣት በማሰብ ለጉዞ የሚሆናቸውን ማር በከፍተኛ ሁኔታ መብላት ይጀምራሉ። ሆዳቸው በማር ሲሞላና ሲወጠር ደግሞ እንደ ልብ መታጠፍና መውጊያቸውን ማውጣት በዝግጅት ረገድ ስለሚከብዳቸው በጣም የዋህና ታዛዥ ይሆናሉ።

በዚህም ምክንያት ነው ንቦች በጭስ ወቅት መናደፋቸውን የሚቀንሱት ሲል አንድ የቅርብ ጊዜ ጥናት አመላክቷል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
👍85
በነጻ የንግድ ቀጠና ውስጥ ተሰማርተው ምርቶችን ለገበያ የሚያቀርቡ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ መፈቀዱን የገንዘብ ሚኒስቴር አሳወቀ

የአገራችን የኢንዱስትሪ ልማት በሚፈለገው መጠን እንዳያድግ ምክንያት ከሆኑት መካከል የካፒታል እጥረት፤ የግብአት አቅርቦት ችግር እና የባለሙያ እጥረት በዋንኛነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው። በመሆኑም እነዚህን ችግሮች ደረጃ በደረጃ በማቃለል የአገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ልማትን ማሳደግ ይገባል ብሏል።

በዚህም መሰረት ግብአቶች እና ሌሎችም ምርቶች በበቂ መጠን ለገበያ እንዲቀርቡ ለማድረግ አስመጪዎች ምርቱን ለገበያ ከማቅረባቸው በፊት የሚከፍሉት ቀረጥ እና ታክስ ውስን የሆነውን ካፒታላቸውን በመያዝ ረገድ የሚያሳድረባቸውን ጫና ማቃለል እንደሚያስፈልግ አሳውቋል።

በእነዚህ ምክንያቶች አስመጪዎች ግብቶችን እና ምርቶችን ቀረጥ እና ታክስ ሳይከፍሉ ወደአገር አስገብተው ለግብአቱ ወይም ለምርቱ ገበያ ባገኙ ጊዜ ቀረጥ እና ታክሱን የሚከፍሉበትን አሰራር የሚፈቅድ የነጻ የንግድ ቀጠና አሰራር የተዘረጋ ሲሆን፤ ይህንን ስርአት የሚያስፈጸሙ ነጻ የንግድ ቀጠናዎች በየካባቢው የተቋቋሙ መሆኑ ይታወቃል::

እነዚህ ነጻ የንግድ ቀጠናዎች ባለሃብቶችን የበለጠ የሚሰቡ እንዲሆኑ ለማድረግ ከላይ ከተገለጸው በተጨማሪ በነጻ የንግድ ቀጠናዎች ውስጥ ተሰማርተው ግብአቶችን እና ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ ተፈቅዷል።

ሰለዚህ ባለሃብቶች ይህንን እድል በመጠቀም በነጻ የንግድ ቀጠናዎች ውስጥ እንዲሰማሩ እናሳሳባለን ሲል በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስነብቧል ።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተደራዳሪዎቹ ተመለሱ‼️
የኢራን ተደራዳሪ ቡድን በ9 የፓኪስታን ተዋጊ ጀቶች ታጅቦ ወደ ኢራን እየተመለሰ ነው።(አዩ)

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
2😁2😱1
የኢራን መርከቦች አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ በጣለችው እገዳ አቅራቢያ ከመጡ "ይደመሰሳሉ" - ትራምፕ

በዋሽንግተን እና በቴህራን መካከል የተደረገው ውይይት መክሸፉን ተከትሎ፣ የአሜሪካ ማዕከላዊ ኮማንድ የዶናልድ ትራምፕን መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ በሆርሙዝ ውሽመጥ ላይ እገዳ መጣል ጀምሯል።

​ትራምፕ ከቴህራን ጋር የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረጋቸውን ካወጁ በኋላ፣ ኢራን እና አሜሪካ ቅዳሜ ዕለት በኢስላማባድ ውይይት አድርገው ነበር። ነገር ግን እሁድ ዕለት የአሜሪካ ልዑካን ቡድን መሪ ጄዲ ቫንስ ምንም ዓይነት ስምምነት ላይ አለመደረሱን ገልጸዋል። በመቀጠልም ትራምፕ የአሜሪካ ባህር ኃይል በባህር ሰርጡ ላይ እገዳ እንዲጥል እና ወሽመጡ ለማለፍ ለኢራን የጉዞ ቀረጥ የሚከፍሉ ማናቸውንም መርከቦች እንዲያስቆም ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
2👏1
የጊዜያዊ አስተዳደሩ የትግራይ ሰራዊት እንቅስቃሴ ላይ ገደብ እንዲጣል ትእዛዝ አስተላልፏል በሚል የተሰራጨው መረጃ "ሐሰተኛ" ነው ሲል አስተባበለ!

​ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፤ ባለሥልጣናት የሰራዊት እንቅስቃሴ ላይ ገደብ እንዲጣል ትእዛዝ አስተላልፈዋል በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ የሚዘዋወረውን ሰነድ “መሠረተ ቢስ”፣ “የተቀነባበረ” እና “ሐሰተኛ” ሲል አጣጣለው። አስተዳደሩ ሰነዱ ሆን ተብሎ አለመረጋጋትን ለመፍጠር እና ሕዝብን ለማሳሳት የተዘጋጀ መሆኑንም አስጠንቅቋል።

​ጊዜያዊ አስተዳደሩ ትናንት ባወጣው መግለጫ፤ ለአስተዳደሩ ተሰጥቶ የተሰራጨው ደብዳቤ “መሠረተ ቢስ ፈጠራ እና የተለመደ የማጭበርበር ድርጊት ነው” ብሏል።

​ይህ ማስተባበያ የወጣው፤ በትግራይ ክልል ውስጥ የአመራር መከፋፈል፣ የመፈንቅለ መንግሥት ዝግጅት፣ እንዲሁም በወታደራዊ መዋቅሮች እና በመገናኛ ብዙኃን ላይ ያነጣጠሩ መመሪያዎችን የያዘ ሰነድ በስፋት መሰራጨቱን ተከትሎ ነው።

Via AS

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
4
ትራምፕ ምስሉን አጥፍተውታል‼️
ትራምፕ "በጦር አውሮፕላኖች ፈውስ የምሰጥ እየሱስ ነኝ" በሚል አጋርተውት የነበረውን አነጋጋሪ ምስል አጥፍተውታል። ይህ ምስል ትራምፕ ለክርስቲያን እምነት ተከታዮች ያላቸውን ንቀት ያሳል በሚል ኢራንን ጨምሮ በርካታ ተቃዎሞ ሲያሰሙ ነበር።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
🤪4
ብዙዎች እየተማሩ ነው 💥

እንግሊዝኛ ቋንቋን ቤትዎ ቁጭ ብለው ይማሩ

Mark Language Academy

የእንግሊዝኛ ቋንቋ የመናገር ክህሎትዎን ወይም ችሎታዎን የትም ሳይሄዱ ቤትዎ ቁጭ ብለው Face to Face በ Zoom, በቴሌግራም Video Call ወይም Google meet ላይ መማር ይችላሉ
እንዲሁም   አስገራሚ ለውጥ ያመጣሉ

Speaking  ( ንግግር)

Listening ( ማዳመጥ)

Grammar ( ሰዋሰው )

How to read and Write ( መፃፍ ና ማንበብ )

ሁሉንም በ5 ወር ውስጥ ብቻ ይቻሉና ራስዎን ይለውጡ

ከ ሰርተፍኬት ጋር ......
ለመመዝገብ ያናግሩን 👇

@MarkEngAcademy

☎️ 0908880599
3
''ትራምፕን አልፈራም'' ጳጳሱ

በታሪክ የመጀመሪያው አሜሪካዊ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሆኑት ሊዮ 14ኛ፣ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለተሰነዘረባቸው ትችት በሰጡት ምላሽ ለትራምፕ አስተዳደር "ምንም ዓይነት ፍርሃት የለኝም" በማለት የጸና አቋማቸውን ገልጠዋል።

ትራምፕ ጳጳሱን "በወንጀል ረገድ ደካማ እና በውጭ ፖሊሲ አስከፊ" በማለት የነቀፏቸው፣ ቅዱስነታቸው አሜሪካ በኢራን ላይ የከፈተችውን ጦርነት እና የስደተኞች አያያዝ ፖሊሲን በግልጽ በመቃወማቸው ነበር።

ጳጳሱ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ እያደረጉት ባለው ጉብኝት ወቅት እንደተናገሩት፣ ትችታቸው ከፖለቲካዊ ፍላጎት የመነጨ ሳይሆን ከሃይማኖታዊ እና ከሰብዓዊነት ግዴታ የመነጨ መሆኑን በማብራራት ለሰላም ጥሪያቸው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
14👍2
የጠጡበትን ሂሳብ  ላለመክፈል የቡድን ፀብ በማንሳት የሆቴል ቤትን ንብረት ላይ ጉዳት ያደረሱ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

በምስራቅ ባሌ ዞን ጊኒር ከተማ ውስጥ የጠጡበትን ሂሳብ ላለመክፈል የቡድን ፀብ በማንሳት የሆቴል ቤቱን ንብረት ላይ ጉዳት ያደረሱ ግለሰቦች በእስራት ተቀጥተዋል ።የዞኑ ፖሊስ ዋና መምርያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አሻግሬ ጥላሁን ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ተከሳሾቹ 1ኛ ሃምዛ አቡሽ፣ 2ኛ አልሙዲ መሃመድ፣ 3ኛ መኮንን ብርሃኑ የተባሉ ወጣቶች ሲሆኑ መጋቢት 23 ቀን 2018  ከምሽቱ አራት ሰዓት ተኩል ድርጊቱን ፈጽመዋል።

በሃያዎቹ አጋማሽ የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙት ወጣቶች በጊኒር ከተማ ሸራተን ሆቴል ተብሎ በሚጠራዉ ስፍራ መጠጥ ጠጥተው የጠጡበትን ሂሳብ ላለመክፈል የቡድን ፀብ በማስነሳት የሆቴሉን ንብረት አዉድመዋል። ከሆቴል ቤቱ ባለቤት ጋር ባስነሱት ግጭት የሆቴል ቤቱን አራት የላሜራ በሮች ፣ መስኮት መስታዎቶችን እና 50 የቢራ ጠርሙሶችን በመሰባበር ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል።

ተከሳሾች በአጠቃላይ ግምት ከ37 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት ማውደማቸው በማስረጃ ተረጋግጧል። ፖሊስም የምርመራ መዝገቡ በወደሙት ንብረቶች የዋጋ ተመን በማያያዝ መዝገቡን ለአቃቢ ህግ የላከ ሲሆን አቃቢ ህግም በሰው ንብረት ላይ ሁከት በመፍጠር ጉዳት በማድረስ ወንጀል ክስ መስርቷል።

ክሱን ሲከታተል የቆየውን የጊኒር ወረዳ ፍርድ ቤት መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ሶስቱም ተከሳሾች እያንዳዳቸው በ2 ዓመት እስራት እንዲቀጡ የወሰባቸው መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር አሻግሬ ጥላሁን ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
8
ትክክለኛ የባህል መዳኒት ይፈልጋሉ??
👆መርጌታ
የባህል ህክምና 0915398834


1🌿ለሀብት ማምጫ
2🌿ለእቁብ (እቁብ እንዲወጣላችሁ የሚያረግ)
3ለመስተፋቅር
4🌿 &መጠብቅ (ከጠላት ከሚላክ ሟርት የሚጠብቅ)
5🌿ለጋኔን
6🌿ለማንኛውም ዓይነት በሽታ መፍትሔ
7🌿ለራእይ (በህልም የሚያሳይ)7
8🌿  ለፀር (ለጠላት)
9🌿ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)
10🌿 ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)
11🌿ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)
12🌿ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)
13🌿 መስተፋቅር
14🌿ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
15🌿ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ
16🌿ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)
17🌿የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ
18🌿ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)
19🌿መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)
20🌿መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)
21🌿ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)
22🌿ለልሳነ_ሰብእ
23🌿ለበረከት
24🌿ለእግረ_መልስ (ጥሎ ለጠፋ ሰው መመለሻ ማምጫ)
25🌿ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)
26🌿ጸሎተ_ዕለታት
27🌿ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ
28🌿ንባብ ስናነብ ቀልጣፋ የሚያረግ
29🌿ለከበሮ
30🌿ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)
31🌿ለሙግት
32🌿ለሰላቢ
33🌿ለስንፈት ወሲብ
34🌿ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)
35🌿ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)
36🌿ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)

በ 0915398834  ይደውሉልን
1
የጉበት መስባት ምን ማለት ነው?

ከፍተኛ የሆነ የስብ ክምችት በጉበት ላይ ሲኖር የጉበት መስባት(Fatty Liver) ይባላል። ትንሽ መጠን ያለው የስብ ክምችት እንደ ችግር አይቆጠርም።

✔️እንደሚታወቀው ጉበት ከሰውነታችን አካል ክፍሎች በትልቅነቱ 2ኛ ደረጃ ሲሆን በምግብና መጠጥ አማካኝነት ወደ ሰውነታችን የገቡ ነገሮችን በማጣራትና በመፈተሽ ሰውነትን ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮችን በማስወገድና የጉዳት መጠናቸውን በመቀነስ ሰውነት ላይ ሊደርስ የሚችልን ከባድ ችግር ያስቀራል።

✔️መጠኑ የጨመረ የስብ መጠን ለጉበት መጠቃትና መመረዝ ያጋልጣል። ይህም ጉበት ላይ ጠባሳ እንድፈጠር ያደርጋል። ይህ ደግሞ ጉበት ስራውን በአግባቡ እንዳያከናውን ያደርገዋል።
በጉበት ውስጥ ስብ ሲከማች ሊታዩ የሚችሉ ምልክቶች
👉 የጉበት ጠባሳ መፈጠር 
#የጉበት ጠባሳ ካለ የሚታዩ ምልክቶች

1. የክብደት መቀነስና ድካም ስሜት
2. በአፍንጫ ደም መፍሰስ
3. የቆዳ ማሳከክ
4. ቆዳና አይን ቢጫ መሆን
5. የሆድ ህመም
6. የሆድ ማበጥ
7. የእግር ማበጥ
8. ግራ መጋባት
#በጉበት ላይ ለምን ስብ ይጠራቀማል?
👉ብዙ ጣፋጭ ተጠቃሚ መሆን
👉መጠኑ ከፍ ያለ አልኮል መጠጣት
ችግሩን የሚያባብሱ ነገሮች
👉 ውፍረት
👉 ከፍተኛ ደም ግፊት
👉ስኳር በሽታ
👉ብዙ ስብ በሰውነት ውስጥ መከማቸት
👉የጉበት ቫይረስ ሲ
👉መድሀኒቶች(methotrexate, tamoxifen, amiodorone and valproic)
👉ለመርዛማ ነገሮች መጋለጥ
👉እርግዝናና ሌሎችም ናቸው።

መመርመሪያ መንገዶች

👉የተለያዩ ጥያቄዎች በመጠየቅ
👉የተለያዩ ምልክቶችን በማየት
👉የደም ናሙና በመውሰድ
👉ከጉበት ናሙና በመውሰድ
ህክምናው
👉የሚታዘዝ መድሀኒት ባይኖርም አልኮልን ባለመጠጣት፡ ክብደትን በመቀነስና የባለሙያ ምክርንና ክትትልን በማክበር መቀነስና ከችግሩ መላቀቅ ይቻላል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
4
ቻይና አሜሪካን አወገዘች

ቤጂንግ በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ የሚደረግ ማንኛውንም እገዳ እንደምትቃወም አስታወቀች

የቻይና መንግስት በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ የሚደረግ ማንኛውም የባህር ላይ እገዳ የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ጥቅም የሚጎዳ መሆኑን በመግለጽ፣ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ራሳቸውን እንዲገቱ አሳሰበች።

​አሜሪካ በኢራን ወደቦች ላይ የባህር ላይ ትራፊክ እገዳ እንደምትጀምር ማስታወቋን ተከትሎ ቤጂንግ በሰጠችው ምላሽ፣ ከኢራን ጋር ያላትን ጠንካራ የንግድና የኢነርጂ ትብብር እንደምታስቀጥል ገልጻለች።

የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ የሀገሪቱ መርከቦች በሰርጡ በኩል የሚያደርጉትን ጉዞ እንደማያቋርጡና የኢራን መንግስት መንገዱን ክፍት ማድረጉን ጠቁሟል።

​ይህ ውጥረት የነገሰው በኢራን ጦርነት ዙሪያ ቅዳሜና እሁድ በኢስላማባድ የተደረገው ድርድር ያለ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ሲሆን፣ ቻይና የኢራን የነዳጅ ምርት ዋነኛ ገዢ እንደመሆኗ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለችው ትገኛለች።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
8👍1
ሊቨርፑል ከፒኤስጂ፤ አትሌቲኮ ማድሪድ ከባርሰሎና

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት መደረግ ይጀምራሉ፡፡

ምሽት 4 ሰዓት ላይ ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ሮድ የፈረንሳዩን ክለብ ፒኤስጂን ያስተናግዳል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በፓርክ ደ ፕሪንስ ያደረጉትን የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ፒኤስጂ 2 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

ሊቨርፑል ዛሬ ምሽት በሜዳው በሚያደርገው ጨዋታ ውጤቱን ቀልብሶ ግማሽ ፍጻሜውን ለመቀላቀል ብርቱ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአምና የመድረኩ አሸናፊ ፒኤስጂ በበኩሉ ውጤቱን አስጠብቆ ቀጣዩን ዙር ለመቀላቀል የሚያደርገው ፍልሚያ ተጠባቂ ነው፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት አትሌቲኮ ማድሪድ በሜዳው ዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ከባርሴሎና ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

የመጀመሪያውን ዙር የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ አትሌቲኮ ማድሪድ 2 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ባርሴሎና ሦስቱን ሲያሸንፍ አትሌቲኮ ማድሪድ በሁለቱ ድል አድርጓል፡፡

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
5👍1
ፓኪስታን የአሜሪካ እና የኢራን ሁለተኛ ዙር ድርድርን ለማስተናገድ ጥያቄ አቀረበች

አሶሼትድ ፕሬስ የዜና ወኪል እንደዘገበው፤ ፓኪስታን የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከማብቃቱ በፊት በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ የአሜሪካ እና የኢራን ሁለተኛ ዙር ድርድር በኢስላማባድ እንዲካሄድ ሀሳብ አቅርባለች።

የዜና ወኪሉ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ሁለት የፓኪስታን ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የቀረበው ሀሳብ ተግባራዊ የሚሆነው ተደራዳሪ ወገኖቹ ሌላ የተለየ ቦታ እንዲሆን ካልጠየቁ ብቻ ነው።

አንደኛው ባለሥልጣን እንደገለጹት፤ የመጀመሪያዎቹ ድርድሮች ያለ ስምምነት ቢጠናቀቁም፣ በአንድ ጊዜ ብቻ የሚያበቁ ጥረቶች ሳይሆኑ ቀጣይነት ያለው ዲፕሎማሲያዊ ሂደት አካል ናቸው።

አሶሼትድ ፕሬስ የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ አዲሱ የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር በመጪው ሐሙስ ሊካሄድ ይችላል።

  @Addis_Magazine
@Addis_Magazine
4👏1
ከ10 ሰዎች ሰባቱ ሱዳናውያን ለድህነት መዳረጋቸውን ተገለፀ

በሱዳን ጦርነት ምክንያት ከ10 ሰዎች መካከል ሰባቱ ሱዳናውያን በድህነት ውስጥ እንደሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት አስታወቀ።

አንድ ከፍተኛ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሥራ ኃላፊ ለኤኤፍፒ (AFP) እንደተናገሩት፤ ይህ ስጋት ከሦስት ዓመት በፊት በጦር ሠራዊቱ እና በከፊል ወታደራዊ ኃይሎች መካከል ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የሁለት እጥፍ ጭማሪ አሳይቷል።

የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) የሱዳን ተወካይ ሉካ ሬንዳ፤ ጦርነቱ የተጀመረበትን ሦስተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ተቋሙ ያወጣውን አዲስ ሪፖርት መሠረት በማድረግ እንደገለጹት፤ “ከጦርነቱ በፊት በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር 38 በመቶ ገደማ ነበር፤ አሁን ግን ወደ 70 በመቶ ከፍ ብሏል ብለን እንገምታለን።”

ሬንዳ የጠቀሱት አሃዝ በቀን 4 ዶላር የድህነት ወለል ላይ የተመሰረተ ሲሆን፤ ቢያንስ ሩብ የሚሆነው የሀገሪቱ ሕዝብ ደግሞ ከዚህ ግማሽ በሚያንስ ገቢ እንደሚተዳደር ተገልጿል።

ሁኔታው በተለይም የጦርነቱ ዋነኛ የውጊያ ቀጠና በሆነው ደቡብ ኮርዶፋን እና በሰሜን ዳርፉር እጅግ የከፋ መሆኑን የጠቀሱት ሬንዳ፤ በእነዚህ አካባቢዎች ከ70 እስከ 75 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ በችግር ውስጥ እንደሚገኝ አክለዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
2
የድምፃዊ ቴዲ አፍሮን አዲስ አልበም "ኢትዮሪካ"ን አስመልክቶ ዛሬ ሊሰጥ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ በይፋ መታገዱ መነጋገሪያ ሆናኗል።

በሚሊዮኖች ዘንድ በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን የድምፃዊ ቴዲ አፍሮን አዲስ አልበም "ኢትዮሪካ"ን አስመልክቶ ዛሬ ሊሰጥ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ በይፋ መታገዱ በሀገሪቱ የፖለቲካ እና የጥበብ ምህዳር ላይ ትልቅ መነጋገሪያ ፈጥሯል።

ቴዲ አፍሮ ይህንን ወሳኝ መግለጫ ከአርትስ ቲቪ (Arts TV) ጋር በመተባበር በቀጥታ ስርጭት ለህዝብ ለማድረስ አስቀድሞ ስምምነት ፈፅሞ የነበረ ቢሆንም፤ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በጣቢያው ላይ ባስተላለፉት ጥብቅ ትዕዛዝ እና እገዳ ስርጭቱ ሙሉ ለሙሉ ሊቋረጥ ችሏል።

ይህ ያልተጠበቀ የእገዳ እርምጃ የመነጨው አዲሱ የቴዲ አልበም ከፍተኛ ፖለቲካዊ እና ወቅታዊ ሀገራዊ ትችቶችን ያዘለ ይዘት ይኖረዋል ከሚል የመንግስት ከፍተኛ ስጋት እና ድንጋጤ እንደሆነ የፖለቲካ ታዛቢዎች በስፋት እየገለፁ ይገኛሉ።

​ይሁን እንጂ መንግስት የቴዲን ድምፅ ለማፈን እና መልዕክቱ እንዳይተላለፍ የወሰደው ይህ እርምጃ፤ ያልታሰበ ተቃራኒ ውጤት በማምጣት ለአልበሙ ትልቅ የማወቅ ጉጉት ከመፍጠሩም በላይ በቢሊዮን የሚገመት ታሪካዊ "ነፃ ማስታወቂያ" ሰርቶለታል እየተባለ ይገኛል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
🤣13🙉21
መፍትሄው እግረኛ ጦር ነው-UAE‼️
ከኢራን ጋር በእግረኛ ጦርነት ካልተደረገ በስተቀር ምንም መፍትሄ የለም' ሲሉ 'የሳውዲ ንጉሣዊ ቤተሰብ' ለ N12 ገልፀዋል።
እ.ኤ.አ 'በ 2003 በሳዳም አገዛዝ ላይ የተካሄደው የመሬት ላይ ጦርነት በኢራን ላይ መደገም አለበት፣'የኢራን መንግስት የኒውክሌር አላማ ስላለው በጣም አደገኛ ነው ብለዋል።
ለዚህ ብቸኛው መፍትሔ ወደ ኢራን እግረኛ ጦር ማስገባት ነው፣ ሌላ መፍትሔ የለውም ብለዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
8😁4
የሃንጋሪ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፑቲን ስልክ ከደወሉ የዩክሬንን ጦርነት እንዲያቆም እነግራቸዋለሁ ሲሉ አስታወቁ

ፒተር ማጃር በምርጫ ማሸነፋቸዉ በታወጀ በመጀመሪያዉ ቀን ከ10 የአውሮፓ ሀገራት መሪዎች ጋር መነጋገራቸዉን ያስታወቁ ሲሆን ሃንጋሪን ለ16 ዓመታት የመሩት ቪክተር ኦርባን የስልጣን ዘመን እንዲያበቃ ማድረግ ችለዋል፡፡ለቀድሞ መሪ ኦርባን የቅርብ አጋር ወደሆኑት ቭላድሚር ፑቲን ስልክ እንደማይደዉሉ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፒተር ማጃር ተናግረዋል፡፡

እሁድ እለት የቲሳ ፓርቲያቸው ምርጫዉን ማሸነፉን ተከትሎ ለሶስት ሰአት በዘለቀዉ እና ማራቶን በተሰኘዉ ጋዜጣዊ መግለጫቸዉ ላይ ሲናገሩ "ቭላድሚር ፑቲን ከደወለ ስልኩን አነሳለሁ" ሲሉ አክለዋል፡፡ ግን"ይህ የሚሆን አይመስለኝም" ብለዋል፣ "ነገር ግን ነገሮች ተለዉጠዉ ስልክ ደዉለዉልኝ ከተነጋገርን እባክህ ከአራት አመታት በላይ የቀጠለዉን የዩክሬን ግድያን እንዲያቆሙ እና ይህንን ጦርነት እንዲያቆም እነግራቸዉ ነበር።" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ሞስኮ የማጊርን የምርጫ ድል እንደምታከብር በመግለጽ ከቡዳፔስት ጋር ያላትን "ተግባራዊ" ግንኙነቶች እንደምትጠብቅ ተናግራለች።ኦርባን የእሁዱን ምርጫ እንዲያሸንፉ የደገፉት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቁልፍ አጋር ሲሆኑ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ባለፈው ሳምንት የሁለት ቀን ጉብኝት በማድረግም ግንኙነታቸዉን አጠናክረዉ ነበር፡፡

ማጂያ ወደ ትራምፕም ስልክ እንደማይደውሉ ለጋዜጠኞች የተናገሩ ሲሆን ነገር ግን ትራምፕ ስልክ ቢደውሉላቸው "የኔቶ ጠንካራ አጋሮች በመሆናቸው ደስተኛ ነኝ" እንደሚሉ እና ሀንጋሪ በመጪው ጥቅምት ወር በሶቪየት ወረራ ላይ የተቃጣበትን 70ኛ ዓመትን ስታከብር በእንግድነት እንዲገኙ እንደሚጋብዙ መናገራቸዉ ተሰምቷል፡፡

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
8😁3
ኮማንደር አልማዝ ዮሐንስ በተፈፀመባቸው ጥቃት ህይወታቸው አለፈ

በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ በፖሊስ ከፍተኛ አመራርነት ህዝባቸውን ሲያገለግሉ የቆዩት ኮማንደር አልማዝ ዮሐንስ፣ ሚያዝያ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11:35 ላይ በታጠቁ ኃይሎች በደረሰባቸው ጥቃት ህይወታቸው አልፏል።

ኮማንደር አልማዝ ለትንሳኤ በዓል ወደ ቤተሰቦቻቸው መጥተው፣ በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ (ዋር ኮሌጅ) የሚከታተሉትን የስትራቴጂክ አመራር ስልጠና ለመቀጠል ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ ሳሉ ነው ይህ አሰቃቂ ጥቃት የደረሰባቸው።

በፖሊስ ሰራዊት ውስጥ ለ21 ዓመታት በታማኝነት ያገለገሉት ኮማንደሯ፣ በስራቸው ጠንካራና ለብዙዎች አርአያ ከመሆናቸውም ባለፈ፣ ለድሆችና ለተበደሉ ሰዎች ድምፅ በመሆን የሚታወቁ እናት ነበሩ።

ከሙያዊ ግዴታቸው ጎን ለጎን የተቸገሩ ወገኖችን በማስተባበርና በመርዳት የሚታወቁት ኮማንደሯ፣ የባለ ትዳርና የሦስት ልጆች እናት ነበሩ ሲል የከምባት ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
💔87