አዲስ MAGAZINE - መረጃ
31.4K subscribers
6.47K photos
223 videos
3 files
262 links
#አዲስ_Magazine_መረጃ

#መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ

#ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addis_Magazinebot

Addis Ababa , Ethiopia

የአዲስ ነገር መረጃ ቻናል አጋር ሚዲያ
Download Telegram
የ 650 ብሩ ስጋ‼️
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከቀናት በፊት እንዳስታወቀው በከተማዋ የሚገኙ 276 የሸማቾች መሰረታዊ የህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች ለፋሲካ በዓል አንድ ኪሎ ስጋ በ650 ብር እንዲሸጡ ወስኖ ነበር።
ይሁንና ነዋሪዎች ወደተባሉት መሸጫ ቦታዋች በጠዋት ቢሄዱም ብዙዎቹ  መሸጫዎች ላይ " ስጋ አልቋል እነደተባሉ፣በዚህ ዋጋ ስጋ መሸጥ አንችልም" የሚሉ ማስታወቂያዎችን በሸማች ሱቆች ላይ እንደተመለከቱ ለአዩዘሀሻ ገልፀዋል ።
እነዚህ ሱቆች ስጋ መሸጥ የሚጀምሩት ከጠዋቱ ከ12 ሰአት አንስቶ እንደሆነ ማስታወቂያ ለጥፈዋል ሆኖም 12 ሰአት ከአሰር የደረሱ ሰዎች ስጋ አልቋል ተብለው እንደተመለሱ ለሚዲያችን ገልፀዋል። አንዳንድ የሱቅ ባለቤቶች በዚህ ብር ስጋ ሸጠን አያዋጣንም በማለት ሱቅ የለቀቁ እንዳሉም ሰምተናል።
ለሚኩራን ጨምሮ በተወሰኑ አካባቢዎች ጠዋት ላይ ከማህበራት በ650 ብር ስጋ የገዙ እንዳሉ የደረሱን መረጃዎች ቢጠቁሙም በአብዛኛው የሸማች ሱቁች በጠዋቱ ስጋ አልቋል ተብለው እንደተመለሱ ገልፀውልናል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
7😁3
ቶተንሀም 14ተኛ ተከታታይ ድል አልባ ጉዞ ቀጥሏል

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ከሰንደርላንድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

የሰንደርላንድን የማሸነፊያ ግብ ሙኬሌ አስቆጥሯል።

ቶተንሀም መሸነፉን ተከትሎ ከ18 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በወራጅ ቀጠና ገብተዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
4💔2
ሰበር

የጦር መርከቦች ወደ ሆርሙዝ
በርካታ የጦር መርከቦች ወደ ሆርሙዝ እየተቃረቡ ነው፣የተኩስ አቁሙ አደጋ ላይ ወድቋል ሲሉ የኢራን ጦር ቃል አቀባይ ገለፁ።

እነዚህ የጦር መርከቦች 'በከባድ እና ቆራጥ ጥቃት ይስተናገዳሉ" ሲሉ ዝተዋል። አሜሪካ የሆርሙዝን ትራፊክ ሙሉ ለመሉ ለመቆጣጠር የአሜሪካ ባህር ሀይል ወደ ቦታው እንደሚያቀና ትራምፕ ገልፀው ነበር።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
7🤣2
የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከጂንካ ማረሚያ ተቋም 81 ታራሚዎች ተፈቱ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የጂንካ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም የ2018 ዓ.ም የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ 81 ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጎላቸው መፈታታቸውን አስታውቋል።

ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች ዉስጥ 78ቱ ወንዶች ሲሆኑ ሶስቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸዉን የጂንካ ማረሚያ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር አስቻለዉ ኔሬሬ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል ።

ታራሚዎቹ በስርቆት ወንጀል ወደ ተቋሙ የገቡ ሲሆን በማረሚያ ቤት በነበራቸው ቆይታ መልካም ስነምግባር የነበራቸዉና እና የእስራቸዉን አንድ ሶስተኛ ያጠናቀቁ መሆናቸዉ ተገልጿል። የይቅርታዉ ተጠቃሚዎች የተሰጠዉን ይህን ትልቅ ዕድል በመጠቀም ወደ ሌላ ምዕራፍ የሚሸጋገሩበት መሆኑን የገለፁት ኮማንደር አስቻለዉ ከዚህ ወጥተዉ በተመሳሳይ ወንጀል ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦች የሚከፍሉትን ዋጋ ታሳቢ በማድረግ ከድርጊታቸው መቆጠብ እንዳለባቸው ገልፀዋል ።

በማረሚያ ተቋሙ ሲሰሩ የነበሩትን የሙያ ስራ አጠናክረው መቀጠል እንዲሁም ከፖሊስና ሚሊሻ ጋር በመተባበር የፀጥታ ስራ መስራት አለባቸዉ ሲሉ ምክትል ኮማንደር አስቻለዉ ኔሬሬ ጨምረዉ ለጣቢያችን ተናግረዋል ።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
4👏1
ትክክለኛ የባህል መዳኒት ይፈልጋሉ??
👆መርጌታ
የባህል ህክምና 0915398834


1🌿ለሀብት ማምጫ
2🌿ለእቁብ (እቁብ እንዲወጣላችሁ የሚያረግ)
3ለመስተፋቅር
4🌿 &መጠብቅ (ከጠላት ከሚላክ ሟርት የሚጠብቅ)
5🌿ለጋኔን
6🌿ለማንኛውም ዓይነት በሽታ መፍትሔ
7🌿ለራእይ (በህልም የሚያሳይ)7
8🌿  ለፀር (ለጠላት)
9🌿ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)
10🌿 ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)
11🌿ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)
12🌿ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)
13🌿 መስተፋቅር
14🌿ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
15🌿ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ
16🌿ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)
17🌿የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ
18🌿ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)
19🌿መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)
20🌿መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)
21🌿ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)
22🌿ለልሳነ_ሰብእ
23🌿ለበረከት
24🌿ለእግረ_መልስ (ጥሎ ለጠፋ ሰው መመለሻ ማምጫ)
25🌿ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)
26🌿ጸሎተ_ዕለታት
27🌿ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ
28🌿ንባብ ስናነብ ቀልጣፋ የሚያረግ
29🌿ለከበሮ
30🌿ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)
31🌿ለሙግት
32🌿ለሰላቢ
33🌿ለስንፈት ወሲብ
34🌿ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)
35🌿ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)
36🌿ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)

በ 0915398834  ይደውሉልን
በጎረቤት ሀገር ጅቡቲ በተካሄደ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ፕሬዝዳንት ኢስማኢል ኡመር ጌሌህ በ97.8% ድምፅ ማሸነፋቸው ተሰምቷል።

መሐመድ ፋራህ ሳማታር የተባሉ ብቸኛ ተፎካካሪያቸው 2.19% ድምፅ ብቻ አግኝተዋል።

ውጤቱ ለፕሬዝዳንቱ 6ኛ የሥልጣን ዘመን ለተጨማሪ 5 ዓመታት የሚያቆያቸው ነው።

በሀገሪቱ ያሉ ዋና ዋና የሚባሉ ተቃዋሚዎች " ምርጫው ፍትሃዊ አይደለም " በሚል ምክንያት በውድድሩ ላይ አልተሳተፉም። ደጋፊዎቻቸውም ድምፅ እንዳይሰጡ ጥሪ አቅርበው ነበር።

ምንም እንኳን ተቃዋሚዎች " በምርጫው አንሳተፍም " ቢሉም መንግስት ግን ድምፅ ለመስጠት ብቁ ከሆኑት ሰዎች ውስጥ 80.4% የሚሆኑት ወጥተው ድምፅ ሰጥተዋል እያለ ነው።

ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኡመር ጌሌህ በአሁኑ ወቅት የ78 ዓመት አዛውንት ናቸው። እ.ኤ.አ. ከ1999 ጀምሮ ለ27 ዓመታት አገሪቱን እየመሩ ይገኛሉ።

ጌሌህ ቀደም ሲል ከሥልጣን ለመልቀቅ ቃል ገብተው ነበር። በሀገሪቱ ህገመንግስት አንድ ፕሬዜዳንት እጩ ከ75 ዓመት መብለጥ የለበትም ለዚሁ ምርጫ ሲባል ግን የ75 ዓመት እድሜ ገደቡ እንዲነሳ ተደርጓል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
3😁1
የገላ መጥፎ ጠረን

ላብ በራሱ የሰውነት ሽታን አያመጣም ፣ የሰው ላብ ሽታ የለውም ማለት ይቻላል።በአንድ ሰው ቆዳ ላይ በባክቴሪያ ምክንያት የሰውነት ሽታ የሚከሰተው በላብ ውስጥ የፕሮቲን ሞለኪውሎችን በማፍረስ እና በዚህም ምክንያት ሽታ በማምረት ነው።

የሰውነት ሽታ የተለመደ ችግር ነው ። ምንም እንኳን የእሱ መንስኤዎች ብዙውን ጊዜ በአንድ ሰው ንፅህና አጠባበቅ ልምዶች ላይ ቢሆኑም ፣ የሰውነት ሽታ በአንዳንድ አጋጣሚዎች የበለጠ ከባድ የጤና ሁኔታን ሊያመለክት ይችላል።

ይኸ ችግር ሊከሰት የሚችለው በላብ ውስጥ የበሽታ አምጭ ረቂቅ ህዋሳት ሽታ በሚፈጠሩበት ጊዜ ነው፡፡ ይህ መጥፎ ሽታ በምግብ ፣ በንህጽና ፣በጤና ፣ በጾታ እና በአንዳንድ የመድሃኒት ዓይነቶች አወሳሰድ ላይ ይወሰናል፡፡ ችግሩ የሚነሳው ከእጅ ፣ከእጅ ንፍፊት ፣ ከብልት ፣ ከብብት እና ከፊንጢጣ አካባቢዎች ነው፡፡

አጋላጭ ሁኔታዎች (risk factors)

👉የሆድ ድርቀት፣ በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ
👉ሁል ጊዜ ፕሮቲን ያላቸውን ምግቦች ማዘውተር
👉አልኮል ፣ሲጋራና ጫት መጠቀም
👉የቫይታሚን እጥረት መኖር
👉ጥሩ ጠረን የሌለው ዶድራንት መጠቀም
👉ስኳር የሚበዛባቸውን ምግቦች እና መጠጦች አዘውትሮ መጠቀም

👉 ከመጠን በላይ ውፍረት
👉ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ
👉የተወሰኑ የሕክምና ሁኔታዎች - የስኳር በሽታ ፣ የኩላሊት ወይም የጉበት ችግሮች ፣ ከመጠን በላይ እንቅስቃሴ  በተለመደው የሰውነትዎ ሽታ ላይ ለውጥ ሊያስከትሉ ይችላሉ።
👉በአንዳንድ አጋጣሚዎች ግን አንድ ያልተለመደ የሰውነት ሽታ የከፋ ነገር ምልክት ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ሽንት መሰል ሽታ የኩላሊት ወይም የጉበት ችግሮች ማለት ሊሆን ይችላል።

👉ውጥረት ወይም መጨናነቅ/stress- ውጥረት የአፖክሪን ዕጢዎችዎ (apocrine glands) የትርፍ ሰዓት ሥራ እንዲሠሩ ያደርጋቸዋል። ያስታውሱ ፣ እነዚህ ሽታ ያለው ላብ የሚያመጡ እጢዎች ናቸው።

👉በዘር/genetics- አንዳንድ ሰዎች ከሌሎች ይልቅ የሰውነት ሽታ ለማዳበር በጣም የተጋለጡ ናቸው።

✔️ጾታ ይህ ችግር ሴቶች ላይ ቢከሰትም ወንዶች ላይ ግን በይበልጥ ይከሰታል፡፡ 

✔️ የሰውነት ጠረንን ለመቀነስ የሚረዱ ምክሮች

👉 አዘውትሮ ሞቅ ባለ ውሃ መታጠብ ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ (በተለይ በሞቃታማ ፣ እርጥበት አዘል በሆኑ አካባቢዎች ፣ በቀን ሁለት ጊዜ ገላ መታጠብ።)

ፀረ-ባክቴሪያ ሳሙና ይጠቀሙ

የብብትን ንህጽህና መጠበቅ

ሽቶ ትክክለኛ የሽቶና የዲዎደረንት ምርቶችን ይምረጡ።

አየር የሚያዘዋውሩ ልብሶችን እና ሰውነት ላይ የማይጣበቁ ልብሶችን ይልበሱ።

ላብ በቆዳ ላይ የሚይዙ ጨርቆችን ያስወግዱ። እነዚህ የሰውነት ሽታ እንዲዳብር የተሻለ የመራቢያ ቦታን ይፈቅዳሉ።

ቅመማ ቅመሞችን ወይም ሚያቃጥሉ ምግቦችን ከአመጋገብዎ ያስወግዱ ወይም ይቀንሱ። እንደ ቃሪያ ፣ ነጭ ሽንኩርት ፣ ቁንዶ በርበሬ ፣ ብሮኮሊ እና ሽንኩርት ያሉ ጠንካራ የሚሸቱ ምግቦች የበለጠ የበዛ ላብ ሊያስከትሉ ይችላሉ።

የአልኮል መጠጥ በላብዎ ሽታ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።
በቀን 8-10 ብርጭቆ ንፁህ ውሃ መጠጣት

በብብት እና በሌሎች የሰውነት ክፍሎች ያለ ፀጉርን መላጨት ። ፀጉሩ ላብ ይይዛል እና ባክቴሪያዎች ሊበቅሉ የሚችሉበት ጥሩ አከባቢን ይፈጥራል።

- ፀጉርን ማስወገድ የሰውነት ሽታ ለመቆጣጠር  ይረዳል።


@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
5
የአሜሪካ ተግባር የዓለምን የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር አገረገ

አሜሪካ ወደ ኢራን ወደቦች የሚገቡና የሚወጡ መርከቦችን ለማገድ የባሕር ላይ ከበባ እንደምታደርግ ማስታወቋን ተከትሎ፤ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።

አልጀዚራ እንደዘገበው፤ የአሜሪካ ድፍድፍ ነዳጅ (US crude oil) ዋጋ 8 በመቶ በመጨመር በአንድ በርሜል 104.24 ዶላር ደርሷል።

የዓለም አቀፍ መለኪያ የሆነው የብሬንት (Brent) ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋም በ7 በመቶ ጭማሪ በማሳየት በበርሜል 102.29 ዶላር ሆኖ ተመዝግቧል።

ዓለማቀፉ ግዙፍ የኢነርጂ ገበያ ተንታኝ ኦኒክስን (Onyx) ዋቢ በማድረግ ብሉምበርግ እንደዘገበው ደግሞ፤ አሜሪካ የባሕር ላይ ከበባውን የምትቀጥል ከሆነ ዓለማቀፍ የነዳጅ ዋጋ እስከ 150 ዶላር ሊያሻቅብ ይችላል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
7
የቫቲካን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፀረ-ጦርነት መልዕክት በማስተላለፋቸው ትራምፕ ብስጭታቸውን ገለፁ

ትራምፕ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ሊዮ አሥራ አራተኛን በመተቸት ረዥም የማህበራዊ ሚዲያ ጽሁፍ አጋርተዋል። ሊዮ አስራ ሶስተኛን “በወንጀል ላይ ደካማ” እና “ለውጭ ፖሊሲ አስፈሪ” በማለት ጠርተዋል።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሪ ላይ የተሰነዘረው ያልተለመደ ትችት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በኢራን ላይ የሚደረገው ጦርነት እንዲያበቃ ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው። “ሁሉን ቻይነት የሚመስል ማታለል” ግጭቱን እየመራው ነው ሲሉ ሊዮ ያሰሙት ንግግር ትራምፕን ክፉኛ አባሳጭቷል።

ትራምፕን በስም ባይጠቅሱም ይህው ንግግር በቀጥታ በአሜሪካ ወታደራዊ ጥንካሬ በሚፎክሩት እና ጦርነቱን ከሃይማኖታዊ አንፃር ካያያዙት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት እና ሌሎች ባለስልጣናትን የሚተች ይመስላል። "ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ቢኖራት ምንም ችግር የለውም ብለው የሚያስቡ ጳጳስ አልፈልግም" ሲሉ ትራምፕ የግል ንብረታቸው በሆነው ማህበራዊ መድረክ ትሩዝ ሶሻል ላይ ጽፈዋል።

"ሊዮ እንደ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አንድ ላይ ሁሉን መሰብሰብ፣ በማስተዋል መምራት፣ የግራ አክራሪዎችን ሃሳብ ማስተናገድ ማቆም እንዲሁም ፖለቲከኛ ሳይሆን ታላቅ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት መሆን ላይ ማተኮር አለባቸው" ሲሉ ትራምፕ አክለዋል። ትራምፕ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ምርጫ ምስጋናቸውን አቅርበው እንደነበር በማስታወስ ቤተክርስቲያኗ በኋይት ሀውስ ዘንድ ሞገስ በማግኘት የመጀመሪያውን የአሜሪካ ተወላጅ ባለፈው ዓመት የተመረጡትን ሊቀ ጳጳስ በይፋ ደግፌ ነበር ብለዋል። ትራምፕ "በኋይት ሀውስ ውስጥ ባልሆን ኖሮ ሊዮ አስራ ሶስተኛ በቫቲካን አይመረጡም ነበር" ሲሉ አክለዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
8
የኡጋንዳው ጄኔራል በቱርክ ላይ የ1 ቢሊዮን ዶላር እና "የቆንጆ ሚስት" ጥያቄ በማቅረብ ዓለምን አስገረሙ!

የኡጋንዳ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ አዛዥ እና የፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ የሆኑት ጄኔራል ሙሁዚ ኬይነሩጋባ በቱርክ ላይ ባቀረቡት ያልተለመደ ጥያቄ እና ማስጠንቀቂያ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ አስነስተዋል።

ጄኔራሉ በኤክስ (X) ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ቱርክ ለኡጋንዳ 1 ቢሊዮን ዶላር ካሳ እንድትከፍል የጠየቁ ሲሆን ለዚህም እንደ ምክንያት ያቀረቡት የኡጋንዳ ጦር በሶማሊያ ሰላም ለማስከበር በከፈለው መስዋዕትነት ቱርክ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ሆናለች የሚል መከራከሪያን ነው።

ከገንዘቡ በተጨማሪ "ከሀገሪቱ እጅግ ቆንጆ የሆነችውን ሴት ሚስት ማድረግ እፈልጋለሁ" የሚል አነጋጋሪ የግል ጥያቄ ማቅረባቸው ለጉዳዩ የበለጠ ትኩረት ሰጥቶታል።

ቱርክ እነዚህን ጥያቄዎች በ30 ቀናት ውስጥ ካልፈጸመች በካምፓላ የሚገኘው የቱርክ ኤምባሲ እንዲዘጋ፣ የቱርክ አየር መንገድ ወደ ኡጋንዳ እንዳይበር እንዲታገድ እና ሁሉም ዓይነት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች እንዲቋረጡ እንደሚያደርጉ ጄኔራሉ ዝተዋል።

ይህ ድርጊት በሁለቱ ሀገራት መካከል የቆየውን መሻከር የሚያሳይ ሲሆን በተለይም ቱርክ በሀገሯ የሚገኘውን የመንግስት ተቺ ፍሬድ ሉምቡዬን አሳልፋ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኗ እና ኡጋንዳ ከቱርክ ኩባንያ ጋር የነበራትን የቢሊዮን ዶላር የባቡር መስመር ስምምነት ሰርዛ ወደ ቻይና ማዞሯ ለውዝግቡ ዋነኛ መንስኤዎች እንደሆኑ ይታመናል።

ጄኔራል ሙሁዚ ከዚህ ቀደምም በጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ መሰል የጋብቻ ጥያቄ አቅርበው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን የኡጋንዳ መንግስት ግን እስካሁን በጉዳዩ ላይ የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
🤪114😁4
ቻይና ዘመናዊ የጸረ-አውሮፕላን መከላከያ ለኢራን ልትልክ መሆኑ ተሰማ!

በቅርቡ የወጡ የአሜሪካ የደህንነት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ቻይና እጅግ የረቀቁ የጸረ-አውሮፕላን መከላከያ ስርዓቶችን በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ለኢራን ለማቅረብ እየተዘጋጀች ነው።

ይህ እርምጃ በዋሽንግተን ዘንድ ከፍተኛ ስጋትን የፈጠረ ሲሆን በቀጣናው ያለውን ውጥረት ይበልጥ ሊያባብሰው እንደሚችል ተነግሯል።

እነዚህ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች የኢራንን የአየር ላይ መከላከያ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያጠናክሩት ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ይህ የጦር መሳሪያ ዝውውር የታቀደው ቀጣናው ደካማ በሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ባለበት እና ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች በሚቀጥሉበት ስሱ ወቅት ላይ መሆኑ ሁኔታውን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል።

የቻይና እና የኢራን ወታደራዊ ትብብር ማደግ በአሜሪካ እና በተባባሪዎቿ ላይ ወታደራዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ይገመታል።

"ይህ እርምጃ የኢራንን ወታደራዊ አቅም ከመገንባቱም በላይ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን የሃይል ሚዛን ሊቀይር ይችላል።"— የደህንነት ተንታኞች

አሜሪካ ይህንን እንቅስቃሴ በቅርብ እየተከታተለች ሲሆን ጉዳዩ በቀጣናው ሰላም እና ደህንነት ላይ የሚኖረውን ተጽዕኖ በተመለከተ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶች እንደሚጠበቁ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
4😡3👍2🔥1
ኢራን በየትኛውም ማስፈራሪያና ዛቻ አትንበረከክም - የሀገሪቱ ፓርላማ

አሜሪካና ኢራን የመካከኛው ምስራቅ ጦርነትን ለማስቆም ከ47 ዓመታት በኋላ በፓኪስታን ያካሄዱት የፊት ለፊት የሰላም ውይይት ያለስምምነት መጠናቀቁ ይታወቃል፡፡

ይህን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ የሚወሰደው ሁለንተናዊ ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

ከዛሬ ጀምሮም በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚከናወንን የመርከብ እንቅስቃሴ እንደሚያግዱ ገልጸው÷ ለዚህም የሜሪካ ጦር ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡

የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባዔ ሞሃመድ ባጋር ጋሊቢፍ በበኩላቸው÷ ቴህራን አሜሪካ በየጊዜው በምታስተላልፈው የትኛውም ዘቻ እና ማስፈራሪያ እጅ አትሰጥም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የኢራን አብዮታዊ ዘብ ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ የሚጠጉ የጦር መርከቦች ላይ አስፈላጊውን ርምጃ ለመውሰድ በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝም አስገንዝበዋል፡፡

የፕሬዚዳንቱን ማስጠናቀቂያ እና የኢራን ምላሽ ተከትሎም የዓለም የነዳጅ ዋጋ በድጋሚ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ ማሻቀቡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
6
ትራምፕ ራሳቸውን እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ አድርጎ የሚያሳይ ምስል ማጋራታቸው ቁጣ ቀሰቀሰ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ላይ የሰላ ጥቃት ከሰነዘሩ በኋላ በተለምዶ ክርስቶስን የሚመስል ምስል አጋርተዋል። ትራምፕ ሊዮ 14ኛን በዓለም አቀፍ ግጭቶች ላይ ያላቸውን አቋም “ደካማ” እና “በጣም ሊበራል” ሲሉ ጠርተውታል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እሁድ ምሽት ከጳጳስ ሊዮ አሥራ አራተኛ ጋር በአደባባይ ከተጋጩ በኋላ በሊቀ ጳጳሱ አመራር እና በፖለቲካዊ ዳኝነት ላይ የሰላ ጥቃት ከሰነዘሩ በኋላ በማህበራዊ ድረ-ገጾች እራሳቸውን ኢየሱስ ክርስቶስን የመሰለ ሰው አድርገው የሚያሳይ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ምስል አካፍለዋል።

በምስሉ ላይ ትራምፕ በመለኮታዊ ብርሃን የተከበበ እና የታመመን ሰው "የሚፈውሱ" በሚመስል መልኩ ይታያሉ። መላእክትን በሚመስሉ እና በወታደሮች ምስሎች ታጅበው ታይተዋል።

በጥር ወር ከፕሬዚዳንቱ እና ከፓርቲያቸው ጋር ከተጋጨች በኋላ ከኮንግረሱ የተገለለችው ታይለር ግሪኒ በምስሉ ላይ የሰማትን አስተያየት በኤክስ ገጿ ላይ ጽፋለች ። ይህ ከስድብ በላይ ነው፤ "የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ነው" ስትል አጋርታለች።

የፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች እና የትሩዝ ሶሻል ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በምስሉ ላይ ትችታቸውን ሰንዝረዋል። "ራስህን ከኢየሱስ ጋር ማመሳሰል ነው? በእርግጥ ሲኦል ውስጥ ትቃጠያለህ" ሲል ሼሪፍ ዊዲ የተባለ ተጠቃሚ ለትራምፕ ልጥፍ ምላሽ ሰጥቷል። "ራስህን ክርስቲያን ብለህ ከጠራህ እና በዚህ ካልተናደድክ እምነትህን እንደገና መገምገም አለብህ" ሲል ምሳሚራጋብ የተባለ ሌላ ተጠቃሚ ጽፏል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
😡105😁3🙈1
ንቦች በጭስ ጊዜ ለምን አይናደፉም? የንቦች አስገራሚው የተፈጥሮ ምስጢር!

ንብ አርቢዎች ወደ ንብ ቀፎ ከመጠጋታቸው በፊት ጭስ ሲጠቀሙ አስተውለው ያውቃሉ? ይህ የሚደረገው ንቦቹን ለማባረር ሳይሆን በውስጣቸው ያለውን የመከላከያ ስሜት በሁለት አስገራሚ መንገዶች ለማደንዘዝ ነው።

በመጀመሪያ፣ ጭሱ ንቦች እርስ በእርሳቸው የሚግባቡበትን የሽታ ምልክት (Pheromones) ያውከዋል። አንዲት ንብ አደጋ ሲሰማት ሌሎቹን ለማንቃት የምታመነጨውን የጥንቃቄ ሽታ ጭሱ ስለሚሸፍነው፣ ንቦቹ ተባብረው ጥቃት መሰንዘር አይችሉም።

በሁለተኛ ደረጃ፣ ጭሱ በንቦቹ ዘንድ "ሰደድ እሳት ተነስቷል" የሚል የድንጋጤ ስሜት ይፈጥራል። በዚህ ጊዜ ንቦቹ ቀፎውን ጥለው ለመውጣት በማሰብ ለጉዞ የሚሆናቸውን ማር በከፍተኛ ሁኔታ መብላት ይጀምራሉ። ሆዳቸው በማር ሲሞላና ሲወጠር ደግሞ እንደ ልብ መታጠፍና መውጊያቸውን ማውጣት በዝግጅት ረገድ ስለሚከብዳቸው በጣም የዋህና ታዛዥ ይሆናሉ።

በዚህም ምክንያት ነው ንቦች በጭስ ወቅት መናደፋቸውን የሚቀንሱት ሲል አንድ የቅርብ ጊዜ ጥናት አመላክቷል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
👍75
በነጻ የንግድ ቀጠና ውስጥ ተሰማርተው ምርቶችን ለገበያ የሚያቀርቡ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ መፈቀዱን የገንዘብ ሚኒስቴር አሳወቀ

የአገራችን የኢንዱስትሪ ልማት በሚፈለገው መጠን እንዳያድግ ምክንያት ከሆኑት መካከል የካፒታል እጥረት፤ የግብአት አቅርቦት ችግር እና የባለሙያ እጥረት በዋንኛነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው። በመሆኑም እነዚህን ችግሮች ደረጃ በደረጃ በማቃለል የአገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ልማትን ማሳደግ ይገባል ብሏል።

በዚህም መሰረት ግብአቶች እና ሌሎችም ምርቶች በበቂ መጠን ለገበያ እንዲቀርቡ ለማድረግ አስመጪዎች ምርቱን ለገበያ ከማቅረባቸው በፊት የሚከፍሉት ቀረጥ እና ታክስ ውስን የሆነውን ካፒታላቸውን በመያዝ ረገድ የሚያሳድረባቸውን ጫና ማቃለል እንደሚያስፈልግ አሳውቋል።

በእነዚህ ምክንያቶች አስመጪዎች ግብቶችን እና ምርቶችን ቀረጥ እና ታክስ ሳይከፍሉ ወደአገር አስገብተው ለግብአቱ ወይም ለምርቱ ገበያ ባገኙ ጊዜ ቀረጥ እና ታክሱን የሚከፍሉበትን አሰራር የሚፈቅድ የነጻ የንግድ ቀጠና አሰራር የተዘረጋ ሲሆን፤ ይህንን ስርአት የሚያስፈጸሙ ነጻ የንግድ ቀጠናዎች በየካባቢው የተቋቋሙ መሆኑ ይታወቃል::

እነዚህ ነጻ የንግድ ቀጠናዎች ባለሃብቶችን የበለጠ የሚሰቡ እንዲሆኑ ለማድረግ ከላይ ከተገለጸው በተጨማሪ በነጻ የንግድ ቀጠናዎች ውስጥ ተሰማርተው ግብአቶችን እና ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ ተፈቅዷል።

ሰለዚህ ባለሃብቶች ይህንን እድል በመጠቀም በነጻ የንግድ ቀጠናዎች ውስጥ እንዲሰማሩ እናሳሳባለን ሲል በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስነብቧል ።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተደራዳሪዎቹ ተመለሱ‼️
የኢራን ተደራዳሪ ቡድን በ9 የፓኪስታን ተዋጊ ጀቶች ታጅቦ ወደ ኢራን እየተመለሰ ነው።(አዩ)

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
2😁2😱1
የኢራን መርከቦች አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ በጣለችው እገዳ አቅራቢያ ከመጡ "ይደመሰሳሉ" - ትራምፕ

በዋሽንግተን እና በቴህራን መካከል የተደረገው ውይይት መክሸፉን ተከትሎ፣ የአሜሪካ ማዕከላዊ ኮማንድ የዶናልድ ትራምፕን መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ በሆርሙዝ ውሽመጥ ላይ እገዳ መጣል ጀምሯል።

​ትራምፕ ከቴህራን ጋር የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረጋቸውን ካወጁ በኋላ፣ ኢራን እና አሜሪካ ቅዳሜ ዕለት በኢስላማባድ ውይይት አድርገው ነበር። ነገር ግን እሁድ ዕለት የአሜሪካ ልዑካን ቡድን መሪ ጄዲ ቫንስ ምንም ዓይነት ስምምነት ላይ አለመደረሱን ገልጸዋል። በመቀጠልም ትራምፕ የአሜሪካ ባህር ኃይል በባህር ሰርጡ ላይ እገዳ እንዲጥል እና ወሽመጡ ለማለፍ ለኢራን የጉዞ ቀረጥ የሚከፍሉ ማናቸውንም መርከቦች እንዲያስቆም ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
2👏1
የጊዜያዊ አስተዳደሩ የትግራይ ሰራዊት እንቅስቃሴ ላይ ገደብ እንዲጣል ትእዛዝ አስተላልፏል በሚል የተሰራጨው መረጃ "ሐሰተኛ" ነው ሲል አስተባበለ!

​ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፤ ባለሥልጣናት የሰራዊት እንቅስቃሴ ላይ ገደብ እንዲጣል ትእዛዝ አስተላልፈዋል በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ የሚዘዋወረውን ሰነድ “መሠረተ ቢስ”፣ “የተቀነባበረ” እና “ሐሰተኛ” ሲል አጣጣለው። አስተዳደሩ ሰነዱ ሆን ተብሎ አለመረጋጋትን ለመፍጠር እና ሕዝብን ለማሳሳት የተዘጋጀ መሆኑንም አስጠንቅቋል።

​ጊዜያዊ አስተዳደሩ ትናንት ባወጣው መግለጫ፤ ለአስተዳደሩ ተሰጥቶ የተሰራጨው ደብዳቤ “መሠረተ ቢስ ፈጠራ እና የተለመደ የማጭበርበር ድርጊት ነው” ብሏል።

​ይህ ማስተባበያ የወጣው፤ በትግራይ ክልል ውስጥ የአመራር መከፋፈል፣ የመፈንቅለ መንግሥት ዝግጅት፣ እንዲሁም በወታደራዊ መዋቅሮች እና በመገናኛ ብዙኃን ላይ ያነጣጠሩ መመሪያዎችን የያዘ ሰነድ በስፋት መሰራጨቱን ተከትሎ ነው።

Via AS

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
4
ትራምፕ ምስሉን አጥፍተውታል‼️
ትራምፕ "በጦር አውሮፕላኖች ፈውስ የምሰጥ እየሱስ ነኝ" በሚል አጋርተውት የነበረውን አነጋጋሪ ምስል አጥፍተውታል። ይህ ምስል ትራምፕ ለክርስቲያን እምነት ተከታዮች ያላቸውን ንቀት ያሳል በሚል ኢራንን ጨምሮ በርካታ ተቃዎሞ ሲያሰሙ ነበር።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
🤪4