የቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም ቀጠሮ ተቀየረ‼️
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የተወዳጁ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አዲስ አልበም "ኢትዮሪካ" ከተያዘለት የዳግማዊ ትንሳኤ ዋዜማ ቀደም ብሎ ለህዝብ ሊደርስ መሆኑ ታውቋል።
ከዘጠኝ ዓመታት ረጅም ጥበቃ በኋላ የሚለቀቀው ይህ ተናፋቂ ስራ ፣ በመጪው ሐሙስ ሚያዝያ 8 ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በቴዲ አፍሮ ይፋዊ የዩቲዩብ ገጽ እና በዋና ዋና የሙዚቃ አማራጮች ይለቀቃል።
👉 ሐሙስ ሚያዝያ 8 | 8:00 ሰዓት
@Addis_Magazine

👍9🎉2❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሆርሙዝ ፀጥ ብሏል‼️
በቀን ከ100 በላይ መርከቦችን የሚያስተናግደው ሆርሙዝ ዛሬ ላይ ይህንን ይመስላል‼️
በአሜሪካና እና በኢራን መካከል በፓኪስታን ኢስላማባድ የተደረገው ድርድር መክሸፉን ተከትሎ የሆርሙዝ ሰርጥ ይህን ይመስላል፣ምንም እንቅስቃሴ የለም። ከአሜሪካ ጋር በድጋሚ ለመደራደር ቀጠሮ እንዳልተያዘ ነገር ግን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች እንደሚቀጥሉ ኢራን አስታውቃለች። አሜሪካ አትታመንም ብለዋል።
በ ሆርሙዝ ማለፍ የሚፈልግ መርከብ ለኢራን መክፈል አለበት ብላለች።
(አዩ)

👍4❤3
በሮቤ ከተማ በጤና ባለሙያ ላይ ጥቃት የፈጸሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በሮቤ ከተማ በጤና ባለሙያው አቶ ከዲር ዋቆ ላይ አሰቃቂ የድብደባ ወንጀል ፈጽመው የተሰወሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ በይፋ አስታወቀ።
ፖሊስ እንደገለጸው፣ ዋናው ተጠርጣሪ የእጅ ስልኬን ወስዶብኛል"የሚል የሐሰት ምክንያት በመፍጠር ግብረ-አበሮቹን በማስተባበር በጤና ባለሙያው ላይ ጥቃት እንዲሰነዘር አድርጓል። ድርጊቱን ይበልጥ አሳዛኝ የሚያደርገው ተጎጂው እየተደበደበ ባለበት ወቅት ምስሉን በካሜራ የመቅረጽ ተግባር መከናወኑ ነው።
የሮቤ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ገመዳ ቱሊቻ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ፣ የጸጥታ አካላት ባደረጉት ጥብቅ ክትትል ዋናው ተጠርጣሪና አብረውት የነበሩ ግብረ-አበሮቹ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋል መቻላቸውን አረጋግጠዋል።
ኮማንደር ገመዳ ህብረተሰቡ ከእንዲህ መሰል ህገ-ወጥ ድርጊቶች እንዲታቀብ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፈዋል።ማንኛውንም የወንጀል ድርጊት የማጣራትም ሆነ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን ያለው የፍትህ አካላት ብቻ ነው።
በቡድን ተደራጅቶ በግለሰብ ላይ ጥቃት መፈጸም በህግ የሚያስቀጣ ወንጀል መሆኑን ህዝቡ ሊገነዘብ ይገባል ብለዋል።በአሁኑ ወቅት በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እየተጣራ ሲሆን፣ የክስ ሂደት እንደሚመሰረትባቸው ይጠበቃል።
Via ኦሮሚያ ፖሊስ

❤4👍1
🚨 መዓት ነው የማዘንበው፤ ማንኛውም መርከብ በሆርሙዝ ሰርጥ እንዳያልፍ ስትል ኢራን አስጠነቀቀች!
በመካከለኛው ምስራቅ ያለው የጦርነት ደመና ከምንጊዜውም በላይ አጥልቶባታል።
ኢራን ባወጣችው እጅግ አስደንጋጭ መግለጫ ማንኛውም የአሜሪካም ሆነ የሌላ አገር የጦር መርከብ ወደ ሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ለመግባት ቢሞክር በደቂቃዎች ውስጥ የሚወርድበትን "የእሳት መዓት" እንዲጠባበቅ ስትል በይፋ አስጠንቅቃለች።
ይህ የኢራን ቁጣ የተቀሰቀሰው የአሜሪካ የጦር መርከቦች ከቴህራን ጋር ምንም ዓይነት ቅንጅት ሳይኖራቸው በወሳኙ የውሃ መስመር ላይ መታየታቸውን ተከትሎ ሲሆን፣ ጉዳዩ የቀጠናውን ሰላም በጥሬው ገደል አፋፍ ላይ አቁሞታል።
በሌላ በኩል ውጥረቱን ለማርገብ በፓኪስታን በኩል ሲደረግ የነበረው ወሳኝ የዲፕሎማሲ ድርድር ያለ ምንም ውጤት መጠናቀቁ ስጋቱን ይበልጥ አክብዶታል።
የዓለም ነዳጅ ዋጋ መቆጣጠሪያ ተደርጎ የሚወሰደው የሆርሙዝ ሰርጥ አሁን የኃያላን አገራት የኃይል ማሳያ ሆኗል።
ተስፋ ተጥሎበት የነበረው የፓኪስታን ድርድር መክሸፍ ደግሞ የጦርነት ድምፅን ከዲፕሎማሲው ድምፅ በላይ ከፍ እንዲል አድርጎታል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሁኔታውን በከፍተኛ ድንጋጤ እየተከታተለ ሲሆን፣ አንዲት ስህተት የዓለምን ኢኮኖሚ ሊያፈራርስ የሚችል ሰፊ ጦርነት ሊቀሰቅስ ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።

❤14
አንዳንድ አስገራሚ መረጃዎች በአርሰናል እና ቦርንመዝ ጨዋታ...
- አርሰናል በትናንትናው የቦርንመዝ ጨዋታ ከክፍት ጨዋታ ግብ ለማስቆጠር ያስመዘገበው ዉጤት 0.19 ብቻ ነበር። አርሰናል የቆመ ኳስ ላይ ጥገኛ መሆኑ ግልጽ እየሆነ እና ክለቡንም እጅጉን ዋጋ ሊያስከፍለዉ እንደሆነ ተፈርቷል። አርሰናሎች ካላቸዉ ጥሩ ስብስብ አንጻር በክፍት ጨዋታ ግብ ለማስቆጠር በዚህ ደረጃ መቸገራቸዉ ምናልባትም ሚኬል አርቴታ ለቦታዉ የሚመጥኑ አሰልጣኝ ናቸዉን የሚል ጥያቄን ያስነሳል።
- ዴቪድ ራያ በትናንትናው ጨዋታ ከአርሰናል ተጨዋቾች 2ኛዉ ብዙ ኳስ የነካው ተጨዋች ሲሆን 38 የኋልዮሽ ኳሶችን ከቡድን አጋሮቹ ተቀብሏል።
- አርሰናል በትናንትናው ጨዋታ 3 ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎች ብቻ ነበር ያደረገው።
- አርሰናል ካለፉት 4 ጨዋታዎች በሶስቱ ሽንፈት ገጥሞታል። ባለፉት 4 ጨዋታዎችም 1 ግብ ብቻ ነዉ ያስቆጠረዉ።
- አርሰናል ለመጨረሻ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ሲሆን ቡካዮ ሳካ 2 አመቱ ነበር።

😁11❤4
የ 650 ብሩ ስጋ‼️
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከቀናት በፊት እንዳስታወቀው በከተማዋ የሚገኙ 276 የሸማቾች መሰረታዊ የህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች ለፋሲካ በዓል አንድ ኪሎ ስጋ በ650 ብር እንዲሸጡ ወስኖ ነበር።
ይሁንና ነዋሪዎች ወደተባሉት መሸጫ ቦታዋች በጠዋት ቢሄዱም ብዙዎቹ መሸጫዎች ላይ " ስጋ አልቋል እነደተባሉ፣በዚህ ዋጋ ስጋ መሸጥ አንችልም" የሚሉ ማስታወቂያዎችን በሸማች ሱቆች ላይ እንደተመለከቱ ለአዩዘሀሻ ገልፀዋል ።
እነዚህ ሱቆች ስጋ መሸጥ የሚጀምሩት ከጠዋቱ ከ12 ሰአት አንስቶ እንደሆነ ማስታወቂያ ለጥፈዋል ሆኖም 12 ሰአት ከአሰር የደረሱ ሰዎች ስጋ አልቋል ተብለው እንደተመለሱ ለሚዲያችን ገልፀዋል። አንዳንድ የሱቅ ባለቤቶች በዚህ ብር ስጋ ሸጠን አያዋጣንም በማለት ሱቅ የለቀቁ እንዳሉም ሰምተናል።
ለሚኩራን ጨምሮ በተወሰኑ አካባቢዎች ጠዋት ላይ ከማህበራት በ650 ብር ስጋ የገዙ እንዳሉ የደረሱን መረጃዎች ቢጠቁሙም በአብዛኛው የሸማች ሱቁች በጠዋቱ ስጋ አልቋል ተብለው እንደተመለሱ ገልፀውልናል።

❤7😁3
ቶተንሀም 14ተኛ ተከታታይ ድል አልባ ጉዞ ቀጥሏል
የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ከሰንደርላንድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።
የሰንደርላንድን የማሸነፊያ ግብ ሙኬሌ አስቆጥሯል።
ቶተንሀም መሸነፉን ተከትሎ ከ18 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በወራጅ ቀጠና ገብተዋል።

❤4💔2
ሰበር❗
የጦር መርከቦች ወደ ሆርሙዝ
በርካታ የጦር መርከቦች ወደ ሆርሙዝ እየተቃረቡ ነው፣የተኩስ አቁሙ አደጋ ላይ ወድቋል ሲሉ የኢራን ጦር ቃል አቀባይ ገለፁ።
እነዚህ የጦር መርከቦች 'በከባድ እና ቆራጥ ጥቃት ይስተናገዳሉ" ሲሉ ዝተዋል። አሜሪካ የሆርሙዝን ትራፊክ ሙሉ ለመሉ ለመቆጣጠር የአሜሪካ ባህር ሀይል ወደ ቦታው እንደሚያቀና ትራምፕ ገልፀው ነበር።

❤7🤣2
የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከጂንካ ማረሚያ ተቋም 81 ታራሚዎች ተፈቱ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የጂንካ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም የ2018 ዓ.ም የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ 81 ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጎላቸው መፈታታቸውን አስታውቋል።
ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች ዉስጥ 78ቱ ወንዶች ሲሆኑ ሶስቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸዉን የጂንካ ማረሚያ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር አስቻለዉ ኔሬሬ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል ።
ታራሚዎቹ በስርቆት ወንጀል ወደ ተቋሙ የገቡ ሲሆን በማረሚያ ቤት በነበራቸው ቆይታ መልካም ስነምግባር የነበራቸዉና እና የእስራቸዉን አንድ ሶስተኛ ያጠናቀቁ መሆናቸዉ ተገልጿል። የይቅርታዉ ተጠቃሚዎች የተሰጠዉን ይህን ትልቅ ዕድል በመጠቀም ወደ ሌላ ምዕራፍ የሚሸጋገሩበት መሆኑን የገለፁት ኮማንደር አስቻለዉ ከዚህ ወጥተዉ በተመሳሳይ ወንጀል ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦች የሚከፍሉትን ዋጋ ታሳቢ በማድረግ ከድርጊታቸው መቆጠብ እንዳለባቸው ገልፀዋል ።
በማረሚያ ተቋሙ ሲሰሩ የነበሩትን የሙያ ስራ አጠናክረው መቀጠል እንዲሁም ከፖሊስና ሚሊሻ ጋር በመተባበር የፀጥታ ስራ መስራት አለባቸዉ ሲሉ ምክትል ኮማንደር አስቻለዉ ኔሬሬ ጨምረዉ ለጣቢያችን ተናግረዋል ።

❤3
ትክክለኛ የባህል መዳኒት ይፈልጋሉ??
👆መርጌታ የባህል ህክምና 0915398834
1🌿ለሀብት ማምጫ
2🌿ለእቁብ (እቁብ እንዲወጣላችሁ የሚያረግ)
3ለመስተፋቅር
4🌿 &መጠብቅ (ከጠላት ከሚላክ ሟርት የሚጠብቅ)
5🌿ለጋኔን
6🌿ለማንኛውም ዓይነት በሽታ መፍትሔ
7🌿ለራእይ (በህልም የሚያሳይ)7
8🌿 ለፀር (ለጠላት)
9🌿ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)
10🌿 ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)
11🌿ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)
12🌿ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)
13🌿 መስተፋቅር
14🌿ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
15🌿ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ
16🌿ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)
17🌿የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ
18🌿ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)
19🌿መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)
20🌿መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)
21🌿ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)
22🌿ለልሳነ_ሰብእ
23🌿ለበረከት
24🌿ለእግረ_መልስ (ጥሎ ለጠፋ ሰው መመለሻ ማምጫ)
25🌿ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)
26🌿ጸሎተ_ዕለታት
27🌿ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ
28🌿ንባብ ስናነብ ቀልጣፋ የሚያረግ
29🌿ለከበሮ
30🌿ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)
31🌿ለሙግት
32🌿ለሰላቢ
33🌿ለስንፈት ወሲብ
34🌿ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)
35🌿ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)
36🌿ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)
በ 0915398834 ይደውሉልን

በጎረቤት ሀገር ጅቡቲ በተካሄደ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ፕሬዝዳንት ኢስማኢል ኡመር ጌሌህ በ97.8% ድምፅ ማሸነፋቸው ተሰምቷል።
መሐመድ ፋራህ ሳማታር የተባሉ ብቸኛ ተፎካካሪያቸው 2.19% ድምፅ ብቻ አግኝተዋል።
ውጤቱ ለፕሬዝዳንቱ 6ኛ የሥልጣን ዘመን ለተጨማሪ 5 ዓመታት የሚያቆያቸው ነው።
በሀገሪቱ ያሉ ዋና ዋና የሚባሉ ተቃዋሚዎች " ምርጫው ፍትሃዊ አይደለም " በሚል ምክንያት በውድድሩ ላይ አልተሳተፉም። ደጋፊዎቻቸውም ድምፅ እንዳይሰጡ ጥሪ አቅርበው ነበር።
ምንም እንኳን ተቃዋሚዎች " በምርጫው አንሳተፍም " ቢሉም መንግስት ግን ድምፅ ለመስጠት ብቁ ከሆኑት ሰዎች ውስጥ 80.4% የሚሆኑት ወጥተው ድምፅ ሰጥተዋል እያለ ነው።
ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኡመር ጌሌህ በአሁኑ ወቅት የ78 ዓመት አዛውንት ናቸው። እ.ኤ.አ. ከ1999 ጀምሮ ለ27 ዓመታት አገሪቱን እየመሩ ይገኛሉ።
ጌሌህ ቀደም ሲል ከሥልጣን ለመልቀቅ ቃል ገብተው ነበር። በሀገሪቱ ህገመንግስት አንድ ፕሬዜዳንት እጩ ከ75 ዓመት መብለጥ የለበትም ለዚሁ ምርጫ ሲባል ግን የ75 ዓመት እድሜ ገደቡ እንዲነሳ ተደርጓል።

የገላ መጥፎ ጠረን
✅ ላብ በራሱ የሰውነት ሽታን አያመጣም ፣ የሰው ላብ ሽታ የለውም ማለት ይቻላል።በአንድ ሰው ቆዳ ላይ በባክቴሪያ ምክንያት የሰውነት ሽታ የሚከሰተው በላብ ውስጥ የፕሮቲን ሞለኪውሎችን በማፍረስ እና በዚህም ምክንያት ሽታ በማምረት ነው።
✅ የሰውነት ሽታ የተለመደ ችግር ነው ። ምንም እንኳን የእሱ መንስኤዎች ብዙውን ጊዜ በአንድ ሰው ንፅህና አጠባበቅ ልምዶች ላይ ቢሆኑም ፣ የሰውነት ሽታ በአንዳንድ አጋጣሚዎች የበለጠ ከባድ የጤና ሁኔታን ሊያመለክት ይችላል።
✅ ይኸ ችግር ሊከሰት የሚችለው በላብ ውስጥ የበሽታ አምጭ ረቂቅ ህዋሳት ሽታ በሚፈጠሩበት ጊዜ ነው፡፡ ይህ መጥፎ ሽታ በምግብ ፣ በንህጽና ፣በጤና ፣ በጾታ እና በአንዳንድ የመድሃኒት ዓይነቶች አወሳሰድ ላይ ይወሰናል፡፡ ችግሩ የሚነሳው ከእጅ ፣ከእጅ ንፍፊት ፣ ከብልት ፣ ከብብት እና ከፊንጢጣ አካባቢዎች ነው፡፡
✅አጋላጭ ሁኔታዎች (risk factors)
👉የሆድ ድርቀት፣ በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ
👉ሁል ጊዜ ፕሮቲን ያላቸውን ምግቦች ማዘውተር
👉አልኮል ፣ሲጋራና ጫት መጠቀም
👉የቫይታሚን እጥረት መኖር
👉ጥሩ ጠረን የሌለው ዶድራንት መጠቀም
👉ስኳር የሚበዛባቸውን ምግቦች እና መጠጦች አዘውትሮ መጠቀም
👉 ከመጠን በላይ ውፍረት
👉ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ
👉የተወሰኑ የሕክምና ሁኔታዎች - የስኳር በሽታ ፣ የኩላሊት ወይም የጉበት ችግሮች ፣ ከመጠን በላይ እንቅስቃሴ በተለመደው የሰውነትዎ ሽታ ላይ ለውጥ ሊያስከትሉ ይችላሉ።
👉በአንዳንድ አጋጣሚዎች ግን አንድ ያልተለመደ የሰውነት ሽታ የከፋ ነገር ምልክት ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ሽንት መሰል ሽታ የኩላሊት ወይም የጉበት ችግሮች ማለት ሊሆን ይችላል።
👉ውጥረት ወይም መጨናነቅ/stress- ውጥረት የአፖክሪን ዕጢዎችዎ (apocrine glands) የትርፍ ሰዓት ሥራ እንዲሠሩ ያደርጋቸዋል። ያስታውሱ ፣ እነዚህ ሽታ ያለው ላብ የሚያመጡ እጢዎች ናቸው።
👉በዘር/genetics- አንዳንድ ሰዎች ከሌሎች ይልቅ የሰውነት ሽታ ለማዳበር በጣም የተጋለጡ ናቸው።
✔️ጾታ ይህ ችግር ሴቶች ላይ ቢከሰትም ወንዶች ላይ ግን በይበልጥ ይከሰታል፡፡
✔️ የሰውነት ጠረንን ለመቀነስ የሚረዱ ምክሮች
👉 አዘውትሮ ሞቅ ባለ ውሃ መታጠብ ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ (በተለይ በሞቃታማ ፣ እርጥበት አዘል በሆኑ አካባቢዎች ፣ በቀን ሁለት ጊዜ ገላ መታጠብ።)
✍ ፀረ-ባክቴሪያ ሳሙና ይጠቀሙ
✍ የብብትን ንህጽህና መጠበቅ
✍ሽቶ ትክክለኛ የሽቶና የዲዎደረንት ምርቶችን ይምረጡ።
✍ አየር የሚያዘዋውሩ ልብሶችን እና ሰውነት ላይ የማይጣበቁ ልብሶችን ይልበሱ።
✍ ላብ በቆዳ ላይ የሚይዙ ጨርቆችን ያስወግዱ። እነዚህ የሰውነት ሽታ እንዲዳብር የተሻለ የመራቢያ ቦታን ይፈቅዳሉ።
✍ ቅመማ ቅመሞችን ወይም ሚያቃጥሉ ምግቦችን ከአመጋገብዎ ያስወግዱ ወይም ይቀንሱ። እንደ ቃሪያ ፣ ነጭ ሽንኩርት ፣ ቁንዶ በርበሬ ፣ ብሮኮሊ እና ሽንኩርት ያሉ ጠንካራ የሚሸቱ ምግቦች የበለጠ የበዛ ላብ ሊያስከትሉ ይችላሉ።
✍ የአልኮል መጠጥ በላብዎ ሽታ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።
✍ በቀን 8-10 ብርጭቆ ንፁህ ውሃ መጠጣት
✍ በብብት እና በሌሎች የሰውነት ክፍሎች ያለ ፀጉርን መላጨት ። ፀጉሩ ላብ ይይዛል እና ባክቴሪያዎች ሊበቅሉ የሚችሉበት ጥሩ አከባቢን ይፈጥራል።
- ፀጉርን ማስወገድ የሰውነት ሽታ ለመቆጣጠር ይረዳል።

❤5
የአሜሪካ ተግባር የዓለምን የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር አገረገ
አሜሪካ ወደ ኢራን ወደቦች የሚገቡና የሚወጡ መርከቦችን ለማገድ የባሕር ላይ ከበባ እንደምታደርግ ማስታወቋን ተከትሎ፤ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።
አልጀዚራ እንደዘገበው፤ የአሜሪካ ድፍድፍ ነዳጅ (US crude oil) ዋጋ 8 በመቶ በመጨመር በአንድ በርሜል 104.24 ዶላር ደርሷል።
የዓለም አቀፍ መለኪያ የሆነው የብሬንት (Brent) ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋም በ7 በመቶ ጭማሪ በማሳየት በበርሜል 102.29 ዶላር ሆኖ ተመዝግቧል።
ዓለማቀፉ ግዙፍ የኢነርጂ ገበያ ተንታኝ ኦኒክስን (Onyx) ዋቢ በማድረግ ብሉምበርግ እንደዘገበው ደግሞ፤ አሜሪካ የባሕር ላይ ከበባውን የምትቀጥል ከሆነ ዓለማቀፍ የነዳጅ ዋጋ እስከ 150 ዶላር ሊያሻቅብ ይችላል።

❤7
የቫቲካን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፀረ-ጦርነት መልዕክት በማስተላለፋቸው ትራምፕ ብስጭታቸውን ገለፁ
ትራምፕ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ሊዮ አሥራ አራተኛን በመተቸት ረዥም የማህበራዊ ሚዲያ ጽሁፍ አጋርተዋል። ሊዮ አስራ ሶስተኛን “በወንጀል ላይ ደካማ” እና “ለውጭ ፖሊሲ አስፈሪ” በማለት ጠርተዋል።
በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሪ ላይ የተሰነዘረው ያልተለመደ ትችት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በኢራን ላይ የሚደረገው ጦርነት እንዲያበቃ ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው። “ሁሉን ቻይነት የሚመስል ማታለል” ግጭቱን እየመራው ነው ሲሉ ሊዮ ያሰሙት ንግግር ትራምፕን ክፉኛ አባሳጭቷል።
ትራምፕን በስም ባይጠቅሱም ይህው ንግግር በቀጥታ በአሜሪካ ወታደራዊ ጥንካሬ በሚፎክሩት እና ጦርነቱን ከሃይማኖታዊ አንፃር ካያያዙት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት እና ሌሎች ባለስልጣናትን የሚተች ይመስላል። "ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ቢኖራት ምንም ችግር የለውም ብለው የሚያስቡ ጳጳስ አልፈልግም" ሲሉ ትራምፕ የግል ንብረታቸው በሆነው ማህበራዊ መድረክ ትሩዝ ሶሻል ላይ ጽፈዋል።
"ሊዮ እንደ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አንድ ላይ ሁሉን መሰብሰብ፣ በማስተዋል መምራት፣ የግራ አክራሪዎችን ሃሳብ ማስተናገድ ማቆም እንዲሁም ፖለቲከኛ ሳይሆን ታላቅ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት መሆን ላይ ማተኮር አለባቸው" ሲሉ ትራምፕ አክለዋል። ትራምፕ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ምርጫ ምስጋናቸውን አቅርበው እንደነበር በማስታወስ ቤተክርስቲያኗ በኋይት ሀውስ ዘንድ ሞገስ በማግኘት የመጀመሪያውን የአሜሪካ ተወላጅ ባለፈው ዓመት የተመረጡትን ሊቀ ጳጳስ በይፋ ደግፌ ነበር ብለዋል። ትራምፕ "በኋይት ሀውስ ውስጥ ባልሆን ኖሮ ሊዮ አስራ ሶስተኛ በቫቲካን አይመረጡም ነበር" ሲሉ አክለዋል።

❤8
የኡጋንዳው ጄኔራል በቱርክ ላይ የ1 ቢሊዮን ዶላር እና "የቆንጆ ሚስት" ጥያቄ በማቅረብ ዓለምን አስገረሙ!
የኡጋንዳ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ አዛዥ እና የፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ የሆኑት ጄኔራል ሙሁዚ ኬይነሩጋባ በቱርክ ላይ ባቀረቡት ያልተለመደ ጥያቄ እና ማስጠንቀቂያ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ አስነስተዋል።
ጄኔራሉ በኤክስ (X) ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ቱርክ ለኡጋንዳ 1 ቢሊዮን ዶላር ካሳ እንድትከፍል የጠየቁ ሲሆን ለዚህም እንደ ምክንያት ያቀረቡት የኡጋንዳ ጦር በሶማሊያ ሰላም ለማስከበር በከፈለው መስዋዕትነት ቱርክ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ሆናለች የሚል መከራከሪያን ነው።
ከገንዘቡ በተጨማሪ "ከሀገሪቱ እጅግ ቆንጆ የሆነችውን ሴት ሚስት ማድረግ እፈልጋለሁ" የሚል አነጋጋሪ የግል ጥያቄ ማቅረባቸው ለጉዳዩ የበለጠ ትኩረት ሰጥቶታል።
ቱርክ እነዚህን ጥያቄዎች በ30 ቀናት ውስጥ ካልፈጸመች በካምፓላ የሚገኘው የቱርክ ኤምባሲ እንዲዘጋ፣ የቱርክ አየር መንገድ ወደ ኡጋንዳ እንዳይበር እንዲታገድ እና ሁሉም ዓይነት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች እንዲቋረጡ እንደሚያደርጉ ጄኔራሉ ዝተዋል።
ይህ ድርጊት በሁለቱ ሀገራት መካከል የቆየውን መሻከር የሚያሳይ ሲሆን በተለይም ቱርክ በሀገሯ የሚገኘውን የመንግስት ተቺ ፍሬድ ሉምቡዬን አሳልፋ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኗ እና ኡጋንዳ ከቱርክ ኩባንያ ጋር የነበራትን የቢሊዮን ዶላር የባቡር መስመር ስምምነት ሰርዛ ወደ ቻይና ማዞሯ ለውዝግቡ ዋነኛ መንስኤዎች እንደሆኑ ይታመናል።
ጄኔራል ሙሁዚ ከዚህ ቀደምም በጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ መሰል የጋብቻ ጥያቄ አቅርበው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን የኡጋንዳ መንግስት ግን እስካሁን በጉዳዩ ላይ የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም።

🤪9❤4😁4