አዲስ MAGAZINE - መረጃ
31.5K subscribers
6.44K photos
222 videos
3 files
262 links
#አዲስ_Magazine_መረጃ

#መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ

#ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addis_Magazinebot

Addis Ababa , Ethiopia

የአዲስ ነገር መረጃ ቻናል አጋር ሚዲያ
Download Telegram
የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ዘጠኝ ጊዜ መድፍ ይተኮሳል

የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት ዘጠኝ (9) ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ህብረተሰቡ ተገቢው መረጃ እንዲኖረው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክት አስተላልፏል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
7
ከሁለት ሳምንት በኋላ የተመለሰው የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ የሊጉ መሪ አርሰናል በሜዳው በበርንማውዝ 2 ለ 1 ተሸንፏል።

ውጤቱ የአርሰናል ደጋፊዎችን አስቆጥቷል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
😁10
"የተኩስ አቁሙ ይቀጥላል አይቀጥልም የሚለው ውሳኔ በዚህ ድርድር ነው የሚወሰነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ሻሪፍ

በፓኪስታን አደራዳሪነት የሚካሄደው የኢራን እና የአሜሪካ ድርድር በኢስላማባድ መካሄድ ጀምሯል።

ኢራን እና አሜሪካ ግልጽ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ፓኪስታን ማሰሰቧ ተገልጿል።

የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸባዝ ሻሪፍ፣ "ስምምነት ላይ የመድረስ እድሉ የሚወሰነው አሜሪካ እና በኢራን ተደራዳሪዎች ፍላጎት ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

ሻሪፍ የድርድሩ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ንግግር "የተኩስ አቁሙ ይቀጥላል አይቀጥልም የሚለው ውሳኔ በዚህ ድርድር ነው የሚወሰነው" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የሰላም ድልድዩን ስሩት አልያ ስበሩት" በማለት ሁለቱ ሀገራት ለውይይቱ ውሳኔ እንዲሰጡት አሳስበዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
4👍1
#ኢትዮጵያ ብር እና የ #ደቡብ_ሱዳን ፓውንድ በዓለም ላይ ደካማ አፈጻጸም ካሳዩ የመገበያያ ገንዘቦች ተርታ ተመደቡ‼️

የኢትዮጵያ ብር እና የደቡብ ሱዳን ፓውንድ እ.ኤ.አ በ2025 (ከታኅሣሥ 2017 እስከ ታኅሣሥ 2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ) እያንዳንዳቸው ከ10 በመቶ በላይ ዋጋቸውን በማጣት በዓለም ላይ ደካማ አፈጻጸም ካሳዩ የመገበያያ ገንዘቦች ተርታ ተመደቡ።

ኢትዮጵያ ውስብስብ በሆነ የዕዳ ሽግሽግ ሂደት ውስጥ ኢኮኖሚዋን ለማረጋጋት በምትታገልበት በዚህ ወቅት፤ ብር ከአርጀንቲና ፔሶ እና ከቱርክ ሊራ በመቀጠል በዓለም ሦስተኛው ደካማ የመገበያያ ገንዘብ ሆኖ ተመዝግቧል።

የኢትዮጵያ መገበያያ  ብር ከአሜሪካ ዶላር አንጻር 18 በመቶ ዋጋውን ያጣው በዶላር እጥረት፣ በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እና በበውጭ ኢንቨስተሮች እምነት መቀነስ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

የዓለም ባንክን የመጋቢት 2018 ዓ.ም (April 2026) ወቅታዊ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ሪፖርት ዋቢ በማድረግ “ዘ ኢስት አፍሪካን” ጋዜጣ እንደዘገበው፤ ከዶላር አንጻር ሲሰላ፣ የኢትዮጵያ ብር 18 በመቶ እንዲሁም የደቡብ ሱዳን ፓውንድ 15 በመቶ ዓመታዊ የምንዛሬ አቅማቸውን አጥተዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
😢52
18 የሙዚቃ ክር የያዘው የድምፃዊ ቴዲ አፍሮ አዲሱ አልበም ሐሙስ እለት ይለቀቃል ተባለ

ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ለዘጠኝ አመታት የለፋበት "ኢትዮሪካ" የተሰኘ አልበሙ የፊታችን ሐሙስ ስምንት ሰዓት በራሱ የዩትዮብ ገፅ ላይ ይለቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ከተለያዩ ነጠላ ዜማዎች በተጨማሪ በ1993 ዓ.ም ለህዝብ በቀረበው ‹‹አቡጊዳ›› በተሰኘ አልበሙ የሙዚቃ አድማጭን ቀልብ ለመግዛት በቅቷል፡፡

ከአቦጊዳ አልበም ቀደም ብሎ የተሰራው "ቴዲ" ወይም "ሌቦ" አልበም በመቀጠል ‹‹ያስተሰርያል›› ፣ ‹‹ጥቁር ሰው›› እና ለመጨረሻ ጊዜ  ‹‹ኢትዮጵያ›› አልበም የተሰኘ ወጥ የአልበም ስራዎችን እስካሁን አበርክቷል፡፡

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
👍73👏3🔥1
ትክክለኛ የባህል መዳኒት ይፈልጋሉ??
👆መርጌታ
የባህል ህክምና 0915398834


1🌿ለሀብት ማምጫ
2🌿ለእቁብ (እቁብ እንዲወጣላችሁ የሚያረግ)
3ለመስተፋቅር
4🌿 &መጠብቅ (ከጠላት ከሚላክ ሟርት የሚጠብቅ)
5🌿ለጋኔን
6🌿ለማንኛውም ዓይነት በሽታ መፍትሔ
7🌿ለራእይ (በህልም የሚያሳይ)7
8🌿  ለፀር (ለጠላት)
9🌿ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)
10🌿 ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)
11🌿ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)
12🌿ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)
13🌿 መስተፋቅር
14🌿ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
15🌿ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ
16🌿ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)
17🌿የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ
18🌿ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)
19🌿መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)
20🌿መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)
21🌿ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)
22🌿ለልሳነ_ሰብእ
23🌿ለበረከት
24🌿ለእግረ_መልስ (ጥሎ ለጠፋ ሰው መመለሻ ማምጫ)
25🌿ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)
26🌿ጸሎተ_ዕለታት
27🌿ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ
28🌿ንባብ ስናነብ ቀልጣፋ የሚያረግ
29🌿ለከበሮ
30🌿ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)
31🌿ለሙግት
32🌿ለሰላቢ
33🌿ለስንፈት ወሲብ
34🌿ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)
35🌿ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)
36🌿ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)

በ 0915398834  ይደውሉልን
ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች፤ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!

በአሉ የጤና ፣ የፍቅር ፣ የብልፅግና  የአንድነት ፣ የመተሳሰብ ፣ ይሁልንላቹ።

🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
ለሀገራችን ጤና እና ሰላም ፣ ለህዝቦቿ ፣ ፍቅርና አንድነት ፣ የተራቡ የሚጠግቡበት፣ የተቸገሩ የሚትረፈረፉበት ፣ ያዘኑ የሚፅናኑበት ፣ የታመሙ የሚድኑበት ፣ የተጨነቁ ከጭንቀታቸው የሚላቀቁበት የትንሳኤ በአል ይሁንላችሁ።

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

መልካም የፋሲካ በአል ይሁንልን!
            
@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
🙏6
ሰበር ዜና

ድርድሩ ከሸፈ!

በፓኪስታን መዲና ኢስላማባድ ሲደረግ የነበረው የአሜሪካ እና ኢራን ከፍተኛ ባለስልጣናት ድርድር መክሸፉ እየተሰማ ነው።

አልጀዚራ የጄዲ ቫንስን ንግግር ዋቢ አድርጎ አሁን ባወጣው መረጃ፣ የአሜሪካ ተደራዳሪዎች ያለምንም ስምምነት ፓኪስታንን ለቀው እንደሚሄዱ ዘግቧል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
4
ሩሲያ እና ዩክሬን 350 እስረኞችን ተለዋወጡ

የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓልን ተከትሎ በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል የተስፋ ጭላንጭል የታየበት ተግባር ተከናውኗል።

በዛሬው ዕለት በሁለቱ አገራት መካከል በተደረገ የእስረኞች ልውውጥ እያንዳንዳቸው 175 የጦር ምርኮኞችን እና 7 ሲቪሎችን በድምሩ 350 ሰዎችን በሰላም ለየአገራቸው አስረክበዋል።

በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አመቻችነት የተከናወነው ይህ ልውውጥ፤ በጦርነቱ ሳቢያ ተለይተው ለነበሩ ቤተሰቦች ትልቅ የትንሣኤ በዓል ስጦታ ሆኗል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በሰጡት መግለጫ፤ ወደ አገራቸው የተመለሱት ወታደሮች ከ2022 ጀምሮ በምርኮ ላይ የነበሩ መሆናቸውን ገልጸው ይህ አጋጣሚ ለዘላቂ ሰላም መጀመሪያ እንዲሆን ያላቸውን ምኞት ገልጸዋል።

በሌላ በኩል የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴርም ከኩርስክ አካባቢ የተማረኩ ዜጎቹን ጨምሮ ወታደሮቹ በሰላም ወደ አገራቸው መመለሳቸውን አረጋግጧል።

ከእስረኞች ልውውጡ በተጨማሪ፣ ሁለቱ አገራት ለበዓሉ ክብር ሲሉ ለ32 ሰዓታት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ቅዳሜ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ እስከ እሁድ እኩለ ሌሊት ድረስ የሚቆየው ይህ ስምምነት፣ በምድርም ሆነ በባሕር ምንም ዓይነት ጥቃት እንዳይፈጸም የሚያግድ ነው።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
11🕊4👍1
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የትንሣኤ በዓልን በማክበር ላይ!


@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
🔥11🥰1
የቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም ቀጠሮ ተቀየረ‼️

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የተወዳጁ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አዲስ አልበም "ኢትዮሪካ" ከተያዘለት የዳግማዊ ትንሳኤ ዋዜማ ቀደም ብሎ ለህዝብ ሊደርስ መሆኑ ታውቋል።

ከዘጠኝ ዓመታት ረጅም ጥበቃ በኋላ የሚለቀቀው ይህ ተናፋቂ ስራ ፣ በመጪው ሐሙስ ሚያዝያ 8 ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በቴዲ አፍሮ ይፋዊ የዩቲዩብ ገጽ እና በዋና ዋና የሙዚቃ አማራጮች ይለቀቃል።

👉 ሐሙስ ሚያዝያ 8 | 8:00 ሰዓት

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
👍9🎉21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሆርሙዝ ፀጥ ብሏል‼️
በቀን ከ100 በላይ መርከቦችን የሚያስተናግደው ሆርሙዝ ዛሬ ላይ ይህንን ይመስላል‼️
በአሜሪካና እና በኢራን መካከል በፓኪስታን ኢስላማባድ የተደረገው ድርድር መክሸፉን ተከትሎ የሆርሙዝ ሰርጥ ይህን ይመስላል፣ምንም እንቅስቃሴ የለም። ከአሜሪካ ጋር በድጋሚ ለመደራደር ቀጠሮ እንዳልተያዘ ነገር ግን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች እንደሚቀጥሉ ኢራን አስታውቃለች። አሜሪካ አትታመንም ብለዋል።
በ ሆርሙዝ ማለፍ የሚፈልግ መርከብ ለኢራን መክፈል አለበት ብላለች።
(አዩ)

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
👍43
በሮቤ ከተማ በጤና ባለሙያ ላይ ጥቃት የፈጸሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በሮቤ ከተማ በጤና ባለሙያው አቶ ከዲር ዋቆ ላይ አሰቃቂ የድብደባ ወንጀል ፈጽመው የተሰወሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ በይፋ አስታወቀ።

ፖሊስ እንደገለጸው፣ ዋናው ተጠርጣሪ የእጅ ስልኬን ወስዶብኛል"የሚል የሐሰት ምክንያት በመፍጠር ግብረ-አበሮቹን በማስተባበር በጤና ባለሙያው ላይ ጥቃት እንዲሰነዘር አድርጓል። ድርጊቱን ይበልጥ አሳዛኝ የሚያደርገው ተጎጂው እየተደበደበ ባለበት ወቅት ምስሉን በካሜራ የመቅረጽ ተግባር መከናወኑ ነው።

የሮቤ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ገመዳ ቱሊቻ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ፣ የጸጥታ አካላት ባደረጉት ጥብቅ ክትትል ዋናው ተጠርጣሪና አብረውት የነበሩ ግብረ-አበሮቹ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋል መቻላቸውን አረጋግጠዋል።

ኮማንደር ገመዳ ህብረተሰቡ ከእንዲህ መሰል ህገ-ወጥ ድርጊቶች እንዲታቀብ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፈዋል።ማንኛውንም የወንጀል ድርጊት የማጣራትም ሆነ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን ያለው የፍትህ አካላት ብቻ ነው።

በቡድን ተደራጅቶ በግለሰብ ላይ ጥቃት መፈጸም በህግ የሚያስቀጣ ወንጀል መሆኑን ህዝቡ ሊገነዘብ ይገባል ብለዋል።በአሁኑ ወቅት በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እየተጣራ ሲሆን፣ የክስ ሂደት እንደሚመሰረትባቸው ይጠበቃል።

Via ኦሮሚያ ፖሊስ

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
4👍1
🚨 መዓት ነው የማዘንበው፤ ማንኛውም መርከብ በሆርሙዝ ሰርጥ እንዳያልፍ ስትል ኢራን አስጠነቀቀች!

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው የጦርነት ደመና ከምንጊዜውም በላይ አጥልቶባታል።

ኢራን ባወጣችው እጅግ አስደንጋጭ መግለጫ ማንኛውም የአሜሪካም ሆነ የሌላ አገር የጦር መርከብ ወደ ሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ለመግባት ቢሞክር በደቂቃዎች ውስጥ የሚወርድበትን "የእሳት መዓት" እንዲጠባበቅ ስትል በይፋ አስጠንቅቃለች።

ይህ የኢራን ቁጣ የተቀሰቀሰው የአሜሪካ የጦር መርከቦች ከቴህራን ጋር ምንም ዓይነት ቅንጅት ሳይኖራቸው በወሳኙ የውሃ መስመር ላይ መታየታቸውን ተከትሎ ሲሆን፣ ጉዳዩ የቀጠናውን ሰላም በጥሬው ገደል አፋፍ ላይ አቁሞታል።

በሌላ በኩል ውጥረቱን ለማርገብ በፓኪስታን በኩል ሲደረግ የነበረው ወሳኝ የዲፕሎማሲ ድርድር ያለ ምንም ውጤት መጠናቀቁ ስጋቱን ይበልጥ አክብዶታል።

የዓለም ነዳጅ ዋጋ መቆጣጠሪያ ተደርጎ የሚወሰደው የሆርሙዝ ሰርጥ አሁን የኃያላን አገራት የኃይል ማሳያ ሆኗል።

ተስፋ ተጥሎበት የነበረው የፓኪስታን ድርድር መክሸፍ ደግሞ የጦርነት ድምፅን ከዲፕሎማሲው ድምፅ በላይ ከፍ እንዲል አድርጎታል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሁኔታውን በከፍተኛ ድንጋጤ እየተከታተለ ሲሆን፣ አንዲት ስህተት የዓለምን ኢኮኖሚ ሊያፈራርስ የሚችል ሰፊ ጦርነት ሊቀሰቅስ ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
15
አንዳንድ አስገራሚ መረጃዎች በአርሰናል እና ቦርንመዝ ጨዋታ...

- አርሰናል በትናንትናው የቦርንመዝ ጨዋታ ከክፍት ጨዋታ ግብ ለማስቆጠር ያስመዘገበው ዉጤት 0.19 ብቻ ነበር። አርሰናል የቆመ ኳስ ላይ ጥገኛ መሆኑ ግልጽ እየሆነ እና ክለቡንም እጅጉን ዋጋ ሊያስከፍለዉ እንደሆነ ተፈርቷል። አርሰናሎች ካላቸዉ ጥሩ ስብስብ አንጻር በክፍት ጨዋታ ግብ ለማስቆጠር በዚህ ደረጃ መቸገራቸዉ ምናልባትም ሚኬል አርቴታ ለቦታዉ የሚመጥኑ አሰልጣኝ ናቸዉን የሚል ጥያቄን ያስነሳል።

- ዴቪድ ራያ በትናንትናው ጨዋታ ከአርሰናል ተጨዋቾች 2ኛዉ ብዙ ኳስ የነካው ተጨዋች ሲሆን 38 የኋልዮሽ ኳሶችን ከቡድን አጋሮቹ ተቀብሏል።

- አርሰናል በትናንትናው ጨዋታ 3 ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎች ብቻ ነበር ያደረገው።

- አርሰናል ካለፉት 4 ጨዋታዎች በሶስቱ ሽንፈት ገጥሞታል። ባለፉት 4 ጨዋታዎችም 1 ግብ ብቻ ነዉ ያስቆጠረዉ።

- አርሰናል ለመጨረሻ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ሲሆን ቡካዮ ሳካ 2 አመቱ ነበር።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
😁103