ንግድ ባንክ አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላለፈ!!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀሰተኛ ድረ-ገፅ ለማጭበርበር ተግባር እየዋለ ስለሚገኝ ደንበኞች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል!!
አጭበርባሪዎች ሀሰተኛ የሆኑ ድረ-ገፆችን በመፍጠር (htttps://renewu.site/?xxx) እንደ ቴሌግራም፣ ዋትስኣፕ፣ የመሳሰሉ ገፆች ላይ እያሰራጩና ከታች በምስሉ እንደሚታየው የሲቢኢብር መተግበሪያን አስመሰለው ሀሰተኛ ድረ-ገፅ በመፈብረክ እንደ ስልክ ቁጥር፣ የይለፍ ቃል፣ ለማረጋገጫነት የሚላከውን የአንድ ጊዜ ይለፍ ቃል (OTP) የመሳሰሉ የደንበኞችን ሚስጥራዊ መረጃዎች በመመንተፍ ጥቃት በማድረስ ላይ መሆናቸውን ደርሰንበታል ብሏል።
👉 የማጭበርበር ተግባሩ እንዴት ይፈፀማል?
ደንበኞች በማህበራዊ ገፆች ሼር የተደረጉ ሊንኮችን ሲከፍቱ ወደ ሀሰተኛ የሲቢኢብር ድረ-ገፅ በማሻገር የስልክ ቁጥር እንዲያስገቡ ይጠይቃሉ። በመቀጠል ሚስጥራዊ የይለፍ ቃል(PIN) እና የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል (OTP) እንዲያስገቡ ይጠይቃሉ። ጥቃቱ የሚጀምረው የስልክ ቁጥርዎንና የይለፍ ቃልዎን ሲያስገቡ፣ ጥቃት አድራሾች በትክክለኛ ሲቢኢብር መተግበሪያ ላይ እርስዎ ያስገቡትን ወዲያውኑ በመመንተፍ ትክክለኛ የአንድ ጊዜ ይለፍ ቃል በስልክዎ በማስላክ ይጠባበቃሉ። እርስዎ በፍቃድም ይሁን አውቶማቲክ ሲያረጋግጡ የሲቢኢብር ሂሳብዎ ሙሉ በሙሉ ጥቃት አድራሾች (ጠላፊዎች) ይቆጣጠራሉ። ከዚህ በኋላ ጥቃት አድራሾች የሚፈልጉትን ያልተፈቀደ ግብይትን በአጭር ኮድ (*847#) መፈፀም ያስችላቸዋል።
በመሆኑም መሰል ዘዴዎችን በመጠቀም ጥቃት አድራሾች የማጭበርበር ተግባር እየፈፅሙ እንደሚገኙ እና ባንኩ የሲቢኢብር አገልግሎትን በድረ-ገፅ እንደማይሰጥ በመገንዘብ ጥንቃቄ እንድታደርጉ አሳስቧል።
@Addis_Magazine

❤1
በኩታበር ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በ23 ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ
በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ ልዩ ስሙ "አምቦ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የኩታበር ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
አደጋው የደረሰው ሚያዝያ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡20 ሰዓት ላይ ሲሆን፣ ከደሴ ወደ ማሻ 85 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮ-3-አማ 34510 የሆነ የ"ታታ" የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ኩታበር ወረዳ 06 ቀበሌ ላይ ተገልብጧል።
እስከ አሁን ባለው መረጃ መሠረት በ12 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን በሌሎች 11 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል። በአደጋው የጠፋ የሰው ህይወት የሌለ ሲሆን ተጎጂዎቹም በአሁኑ ወቅት አስፈላጊው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።
የተሽከርካሪው አሽከርካሪ ከአደጋው በኋላ ከአካባቢው ያመለጠ ሲሆን የፖሊስ ሃይል አደጋው የተከሰተበትን ትክክለኛ መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

❤2
ኢራን የጠመደቻቸውን ፈንጂዎች በሙሉ ማግኘት ባለመቻሏ የሆርሙዝ ስትሬትን (Strait of Hormuz) ሙሉ በሙሉ መክፈት እንዳልቻለች ኒውዮርክ ታይምስ (NYT) ዘግቧል።
@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
❤3😁3
የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ዘጠኝ ጊዜ መድፍ ይተኮሳል
የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት ዘጠኝ (9) ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር አሳውቋል።
ህብረተሰቡ ተገቢው መረጃ እንዲኖረው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክት አስተላልፏል።

❤7
ከሁለት ሳምንት በኋላ የተመለሰው የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ የሊጉ መሪ አርሰናል በሜዳው በበርንማውዝ 2 ለ 1 ተሸንፏል።
ውጤቱ የአርሰናል ደጋፊዎችን አስቆጥቷል።
@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
ውጤቱ የአርሰናል ደጋፊዎችን አስቆጥቷል።
@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
😁9
"የተኩስ አቁሙ ይቀጥላል አይቀጥልም የሚለው ውሳኔ በዚህ ድርድር ነው የሚወሰነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ሻሪፍ
በፓኪስታን አደራዳሪነት የሚካሄደው የኢራን እና የአሜሪካ ድርድር በኢስላማባድ መካሄድ ጀምሯል።
ኢራን እና አሜሪካ ግልጽ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ፓኪስታን ማሰሰቧ ተገልጿል።
የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸባዝ ሻሪፍ፣ "ስምምነት ላይ የመድረስ እድሉ የሚወሰነው አሜሪካ እና በኢራን ተደራዳሪዎች ፍላጎት ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ሻሪፍ የድርድሩ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ንግግር "የተኩስ አቁሙ ይቀጥላል አይቀጥልም የሚለው ውሳኔ በዚህ ድርድር ነው የሚወሰነው" ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የሰላም ድልድዩን ስሩት አልያ ስበሩት" በማለት ሁለቱ ሀገራት ለውይይቱ ውሳኔ እንዲሰጡት አሳስበዋል።

❤3
የ #ኢትዮጵያ ብር እና የ #ደቡብ_ሱዳን ፓውንድ በዓለም ላይ ደካማ አፈጻጸም ካሳዩ የመገበያያ ገንዘቦች ተርታ ተመደቡ‼️
የኢትዮጵያ ብር እና የደቡብ ሱዳን ፓውንድ እ.ኤ.አ በ2025 (ከታኅሣሥ 2017 እስከ ታኅሣሥ 2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ) እያንዳንዳቸው ከ10 በመቶ በላይ ዋጋቸውን በማጣት በዓለም ላይ ደካማ አፈጻጸም ካሳዩ የመገበያያ ገንዘቦች ተርታ ተመደቡ።
ኢትዮጵያ ውስብስብ በሆነ የዕዳ ሽግሽግ ሂደት ውስጥ ኢኮኖሚዋን ለማረጋጋት በምትታገልበት በዚህ ወቅት፤ ብር ከአርጀንቲና ፔሶ እና ከቱርክ ሊራ በመቀጠል በዓለም ሦስተኛው ደካማ የመገበያያ ገንዘብ ሆኖ ተመዝግቧል።
የኢትዮጵያ መገበያያ ብር ከአሜሪካ ዶላር አንጻር 18 በመቶ ዋጋውን ያጣው በዶላር እጥረት፣ በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እና በበውጭ ኢንቨስተሮች እምነት መቀነስ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።
የዓለም ባንክን የመጋቢት 2018 ዓ.ም (April 2026) ወቅታዊ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ሪፖርት ዋቢ በማድረግ “ዘ ኢስት አፍሪካን” ጋዜጣ እንደዘገበው፤ ከዶላር አንጻር ሲሰላ፣ የኢትዮጵያ ብር 18 በመቶ እንዲሁም የደቡብ ሱዳን ፓውንድ 15 በመቶ ዓመታዊ የምንዛሬ አቅማቸውን አጥተዋል።

😢4❤2
18 የሙዚቃ ክር የያዘው የድምፃዊ ቴዲ አፍሮ አዲሱ አልበም ሐሙስ እለት ይለቀቃል ተባለ
ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ለዘጠኝ አመታት የለፋበት "ኢትዮሪካ" የተሰኘ አልበሙ የፊታችን ሐሙስ ስምንት ሰዓት በራሱ የዩትዮብ ገፅ ላይ ይለቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ከተለያዩ ነጠላ ዜማዎች በተጨማሪ በ1993 ዓ.ም ለህዝብ በቀረበው ‹‹አቡጊዳ›› በተሰኘ አልበሙ የሙዚቃ አድማጭን ቀልብ ለመግዛት በቅቷል፡፡
ከአቦጊዳ አልበም ቀደም ብሎ የተሰራው "ቴዲ" ወይም "ሌቦ" አልበም በመቀጠል ‹‹ያስተሰርያል›› ፣ ‹‹ጥቁር ሰው›› እና ለመጨረሻ ጊዜ ‹‹ኢትዮጵያ›› አልበም የተሰኘ ወጥ የአልበም ስራዎችን እስካሁን አበርክቷል፡፡

👍5❤1👏1