በሮቤ ከተማ በጤና ባለሙያ ላይ ጥቃት የፈጸሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በሮቤ ከተማ በጤና ባለሙያው አቶ ከዲር ዋቆ ላይ አሰቃቂ የድብደባ ወንጀል ፈጽመው የተሰወሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ በይፋ አስታወቀ።
ፖሊስ እንደገለጸው፣ ዋናው ተጠርጣሪ የእጅ ስልኬን ወስዶብኛል"የሚል የሐሰት ምክንያት በመፍጠር ግብረ-አበሮቹን በማስተባበር በጤና ባለሙያው ላይ ጥቃት እንዲሰነዘር አድርጓል። ድርጊቱን ይበልጥ አሳዛኝ የሚያደርገው ተጎጂው እየተደበደበ ባለበት ወቅት ምስሉን በካሜራ የመቅረጽ ተግባር መከናወኑ ነው።
የሮቤ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ገመዳ ቱሊቻ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ፣ የጸጥታ አካላት ባደረጉት ጥብቅ ክትትል ዋናው ተጠርጣሪና አብረውት የነበሩ ግብረ-አበሮቹ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋል መቻላቸውን አረጋግጠዋል።
ኮማንደር ገመዳ ህብረተሰቡ ከእንዲህ መሰል ህገ-ወጥ ድርጊቶች እንዲታቀብ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፈዋል።ማንኛውንም የወንጀል ድርጊት የማጣራትም ሆነ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን ያለው የፍትህ አካላት ብቻ ነው።
በቡድን ተደራጅቶ በግለሰብ ላይ ጥቃት መፈጸም በህግ የሚያስቀጣ ወንጀል መሆኑን ህዝቡ ሊገነዘብ ይገባል ብለዋል።በአሁኑ ወቅት በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እየተጣራ ሲሆን፣ የክስ ሂደት እንደሚመሰረትባቸው ይጠበቃል።
@Addis_Magazine

❤1
ንግድ ባንክ አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላለፈ!!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀሰተኛ ድረ-ገፅ ለማጭበርበር ተግባር እየዋለ ስለሚገኝ ደንበኞች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል!!
አጭበርባሪዎች ሀሰተኛ የሆኑ ድረ-ገፆችን በመፍጠር (htttps://renewu.site/?xxx) እንደ ቴሌግራም፣ ዋትስኣፕ፣ የመሳሰሉ ገፆች ላይ እያሰራጩና ከታች በምስሉ እንደሚታየው የሲቢኢብር መተግበሪያን አስመሰለው ሀሰተኛ ድረ-ገፅ በመፈብረክ እንደ ስልክ ቁጥር፣ የይለፍ ቃል፣ ለማረጋገጫነት የሚላከውን የአንድ ጊዜ ይለፍ ቃል (OTP) የመሳሰሉ የደንበኞችን ሚስጥራዊ መረጃዎች በመመንተፍ ጥቃት በማድረስ ላይ መሆናቸውን ደርሰንበታል ብሏል።
👉 የማጭበርበር ተግባሩ እንዴት ይፈፀማል?
ደንበኞች በማህበራዊ ገፆች ሼር የተደረጉ ሊንኮችን ሲከፍቱ ወደ ሀሰተኛ የሲቢኢብር ድረ-ገፅ በማሻገር የስልክ ቁጥር እንዲያስገቡ ይጠይቃሉ። በመቀጠል ሚስጥራዊ የይለፍ ቃል(PIN) እና የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል (OTP) እንዲያስገቡ ይጠይቃሉ። ጥቃቱ የሚጀምረው የስልክ ቁጥርዎንና የይለፍ ቃልዎን ሲያስገቡ፣ ጥቃት አድራሾች በትክክለኛ ሲቢኢብር መተግበሪያ ላይ እርስዎ ያስገቡትን ወዲያውኑ በመመንተፍ ትክክለኛ የአንድ ጊዜ ይለፍ ቃል በስልክዎ በማስላክ ይጠባበቃሉ። እርስዎ በፍቃድም ይሁን አውቶማቲክ ሲያረጋግጡ የሲቢኢብር ሂሳብዎ ሙሉ በሙሉ ጥቃት አድራሾች (ጠላፊዎች) ይቆጣጠራሉ። ከዚህ በኋላ ጥቃት አድራሾች የሚፈልጉትን ያልተፈቀደ ግብይትን በአጭር ኮድ (*847#) መፈፀም ያስችላቸዋል።
በመሆኑም መሰል ዘዴዎችን በመጠቀም ጥቃት አድራሾች የማጭበርበር ተግባር እየፈፅሙ እንደሚገኙ እና ባንኩ የሲቢኢብር አገልግሎትን በድረ-ገፅ እንደማይሰጥ በመገንዘብ ጥንቃቄ እንድታደርጉ አሳስቧል።

በኩታበር ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በ23 ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ
በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ ልዩ ስሙ "አምቦ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የኩታበር ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
አደጋው የደረሰው ሚያዝያ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡20 ሰዓት ላይ ሲሆን፣ ከደሴ ወደ ማሻ 85 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮ-3-አማ 34510 የሆነ የ"ታታ" የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ኩታበር ወረዳ 06 ቀበሌ ላይ ተገልብጧል።
እስከ አሁን ባለው መረጃ መሠረት በ12 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን በሌሎች 11 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል። በአደጋው የጠፋ የሰው ህይወት የሌለ ሲሆን ተጎጂዎቹም በአሁኑ ወቅት አስፈላጊው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።
የተሽከርካሪው አሽከርካሪ ከአደጋው በኋላ ከአካባቢው ያመለጠ ሲሆን የፖሊስ ሃይል አደጋው የተከሰተበትን ትክክለኛ መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ኢራን የጠመደቻቸውን ፈንጂዎች በሙሉ ማግኘት ባለመቻሏ የሆርሙዝ ስትሬትን (Strait of Hormuz) ሙሉ በሙሉ መክፈት እንዳልቻለች ኒውዮርክ ታይምስ (NYT) ዘግቧል።
@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
❤3😁3
የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ዘጠኝ ጊዜ መድፍ ይተኮሳል
የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት ዘጠኝ (9) ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር አሳውቋል።
ህብረተሰቡ ተገቢው መረጃ እንዲኖረው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክት አስተላልፏል።

❤6
ከሁለት ሳምንት በኋላ የተመለሰው የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ የሊጉ መሪ አርሰናል በሜዳው በበርንማውዝ 2 ለ 1 ተሸንፏል።
ውጤቱ የአርሰናል ደጋፊዎችን አስቆጥቷል።
@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
ውጤቱ የአርሰናል ደጋፊዎችን አስቆጥቷል።
@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
😁9
"የተኩስ አቁሙ ይቀጥላል አይቀጥልም የሚለው ውሳኔ በዚህ ድርድር ነው የሚወሰነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ሻሪፍ
በፓኪስታን አደራዳሪነት የሚካሄደው የኢራን እና የአሜሪካ ድርድር በኢስላማባድ መካሄድ ጀምሯል።
ኢራን እና አሜሪካ ግልጽ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ፓኪስታን ማሰሰቧ ተገልጿል።
የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸባዝ ሻሪፍ፣ "ስምምነት ላይ የመድረስ እድሉ የሚወሰነው አሜሪካ እና በኢራን ተደራዳሪዎች ፍላጎት ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ሻሪፍ የድርድሩ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ንግግር "የተኩስ አቁሙ ይቀጥላል አይቀጥልም የሚለው ውሳኔ በዚህ ድርድር ነው የሚወሰነው" ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የሰላም ድልድዩን ስሩት አልያ ስበሩት" በማለት ሁለቱ ሀገራት ለውይይቱ ውሳኔ እንዲሰጡት አሳስበዋል።

❤2