ትራምፐ እና ኤርዶዋን ምን መከሩ?
የቱርክ ፕሬዝዳንት ረጂብ ጠይብ ኤርዶዋን እና የአሜሪካው አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ በቀጠናዊ ጉዳዮችና በኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት ዙሪያ በስልክ ተወያዩ፡፡
ውይይቱ በዋናነት ትኩረቱን ያደረገው በኢራን እና አሜሪካ መካከል በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ነው።
ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ከ40 ቀናት ውጥረት በኋላ የተገኘው የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት ወደ ዘላቂ ሰላም ለመሸጋገር ወሳኝ ዕድል መሆኑን ገልጸዋል።
ቱርክ ከወዳጅ አገራት ጋር በመሆን ለቀጣይ የሰላም ስምምነቶች የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ያረጋገጡት ኤርዶዋን ይህንን ሂደት ሊያደናቅፉ ከሚችሉ ማናቸውም ድርጊቶች መቆጠብ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ቱርክ ለሰላም ጥረቱ የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ካረጋገጡ በኋላ ፤ እንደ ፓኪስታን ካሉ ወዳጅ እና ወንድም አገራት ጋር በመሆን ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን ለማጠናከር ቃል ገብተዋል።
ትራምፕ በበኩላቸው የኢራን መንግስት ለድርድር ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ባለ 10 ነጥብ የውሳኔ ሃሳብ አቅርቧል ቢሉም አሁንም ድረስ የተኩስ አቁሙ ጉዳይ ከስጋት አልወጣም ሲሉ ተንታኞች ይሞግታሉ፡፡
@Addis_Magazine

❤7
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለትንሳኤ በዓል አስተማማኝ የኃይል አቀርባለው አለ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በመጪው የትንሳኤ በዓል ወቅት ሊከሰት የሚችለውን የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ለመቀነስ ሰፊ የቅድመ-ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል።
ተቋሙ በበዓላት ሰሞን የሚኖረውን ከፍተኛ የኃይል ፍላጎትና በመሰረተ-ልማቱ ላይ የሚፈጠረውን ጫና ታሳቢ ያደረገ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገልጿል።
የተቋሙ የኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ አንዋር አብራር እንደገለጹት፣ ከበዓሉ አስቀድሞ የመካከለኛና ዝቅተኛ ማሰራጫ መስመሮችን የመፈተሽ፣ የረገቡ ገመዶችን የመወጠር እና የእንጨት ምሰሶዎችን በኮንክሪት የመተካት ስራዎች ተከናውነዋል።
በተጨማሪም የኃይል ጫና ያለባቸውን ትራንስፎርመሮች አቅም የማሳደግና አዳዲስ አጋዥ ትራንስፎርመሮችን የመትከል ስራ መከናወኑን አስረድተዋል።
በበዓሉ ዋዜማና በዕለቱ ለሚከሰቱ ድንገተኛ የኃይል መቆራረጦች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በሁሉም የአገልግሎት አደረጃጀቶች ውስጥ የአስቸኳይ ጥገና ግብረ-ኃይል ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱ ተገልጿል።
ይህም ደንበኞች አስተማማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል እንደሆነ ተቋሙ አመልክቷል።

😁6❤3👏1🕊1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ፣ ዛሬ ጠዋት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች እና ጽሕፈት ቤቱ ለሚያሳድጋቸው ሕጻናት ማዕድ አጋርተዋል።
@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
❤5
"ሦስት የጤና ባለሙያዎች በጥይት ተገድለዋል" - ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ሦስት ጤና ባለሙያዎች ተገድለዋል አሉ።
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ/ም ሦስት የጤና ባለሙያዎች በጥይት ተገድለዋል ሲሉ አሳውቀዋል።
አንድ ነርስና ሁለት ጤና ባለሙያዎች "አቢዮት ፋና" የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያ፣ ሦስተኛው ደግሞ በግል የጤና ተቋም ውስጥ ይሰሩ እንደነበር ገልጸው፣ " ግድያው የተፈጸመው በኢትዮጵያ መንግስት እና በአማራ ክልል ኃይሎች መካከል ግጭት እየተስፋፋ ባለበት ወቅት ነው " ብለዋል።
"የጤና ባለሙያዎች በማንኛውም ጊዜ ሊጠበቁ እና ለሚያስፈልጋቸው ሰው ሁሉ ህይወትን የሚያድኑ ስራዎቻቸውን ሊያከናውኑ ይገባል" ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የዓለም ጤና ድርጅት ግድያው በገለልተኛ አካል ምርመራ እንዲያደረግ ይጠይቃል የሚል መረጃ አጋርተዋል።

#ፋይዳ ተራዝሟል‼️
የፋይዳ መታወቂያን ከባንክ ሂሳብ ጋር ለማጣመር ተቅምጦ የነበረው የጊዜ ገደብ ተራዝሟል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንክ ሂሳብን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ለማጣመር ተቀምጦ የነበረው የመጋቢት 30/2018 ዓ.ም የጊዜ ገደብ ለአንድ ጊዜ እንዲራዘም መወሰኑ ተገልጿል።
እስካሁን የተመዘገበው ሰው ቁጥር አመርቂ ባለመሆኑ እና በአንዳንድ ባንኮች ላይ የታዩ የሲስተም ችግሮችን ለመፍታት ሲባል ለአንድ ጊዜ እንዲራዘም ተወስኗል።
የተራዘመበት ትክክለኛ ቀን እስካሁን ያልተወሰነ ሲሆን በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግ ብሔራዊ ባንክ አሳውቋል።
እንዲራዘም የተወሰነው ብሔራዊ ባንክ እና የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ተወያይተውበት ነው።
ህብረተሰቡ በሊንክ ወይም ደግሞ በአካል በመቅረብ ምዝገባውን እንዲያከናውን እና ባንኮች የቴክኒክ ችግሮችን እንዲያስተካክሉ መመሪያ ተሰጥቷል።

❤6
በአሶሳ ወታደራዊ ካምፕ ለሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የሚያሳይ አዲስ ሪፖርት ወጣ
በዬል ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ጤና ትምህርት ቤት የሰብአዊ ምርምር ላብራቶሪ (HRL) ያወጣው አዲስ ሪፖርት፤ ኢትዮጵያ ለሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) ወታደራዊ ድጋፍ እያደረገች መሆኑን የሚያሳዩ “ከፍተኛ እምነት የሚጣልባቸው” ማስረጃዎች ማግኘቱን ገልጿል።
ይህም ቀጣናዊ ደህንነትን አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል የሚል ስጋት ይፈጥራል ሲል ገልጿል።
በ የካቲት2018 ዓ.ም “ኢትዮጵያ ለሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ታጣቂዎች የሥልጠና ካምፕ ገንብታለች” ሲል ሮይተርስ የምርመራ ዘገባ ማውጣቱ ይታወሳል።
ዘገባውን ተከትሎም፤ የዩናይትድ ስቴትስ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሰብሳቢ ሴናተር ሪሽ ድርጊቱ የሚያስከትለው “መዘዝ” እንደሚኖር አስጠንቅው ነበር።
የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እስካሁን ለቀረበው ክስ ይፋዊ ምላሽ ባይሰጡም፤ መንግሥት በአዲስ አበባ የሚገኙ ሦስት የሮይተርስ ጋዜጠኞችን የሥራ ፈቃድ ለማደስ ፈቃደኛ ሳይሆን መቅረቱን የዜና ወኪሉ አስታውቋል።

❤9
#ኢትዮጵያዊው ዕጩ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚቴ አባል ሆነው ተመረጡ
አዲስ አበባ — ኢትዮጵያዊው ዕጩ ዓብዲ ጅብሪል ዓሊ (ዶ/ር)፤ በኒውዮርክ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በተሰጠ ድምፅ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ መብቶች ኮሚቴ አባልነት ተመረጡ።
ዓብዲ ጅብሪል ለሁለት የአፍሪካ መቀመጫዎች ከተወዳደሩ ስድስት ዕጩዎች መካከል 49 ድምፅ በማግኘት ማሸነፍ ችለዋል። ኮሚቴው በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ መብቶች ስምምነት አፈጻጸምን የሚከታተሉ 18 ገለልተኛ ባለሙያዎችን የያዘ ነው።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዓብዲ ጅብሪል የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ያስተላለፈ ሲሆን፤ በአራት ዓመት የሥራ ዘመናቸው ስኬትን ተመኝቶላቸዋል።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በበኩሉ ባወጣው መግለጫ፤ በአሁኑ ወቅት በኮሚሽኑ የሲቪል፣ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ኮሚሽነር ሆነው እያገለገሉ ያሉት ዓብዲ ጅብሪል የተመረጡት ትናንት መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም መሆኑን አስታውቋል። ኮሚሽኑ አክሎም፤ የባለሙያው መመረጥ ያላቸውን የሰብአዊ መብት ዕውቀትና ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት ጋር ያላትን ቀጣይነት ያለው ግንኙነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጿል።

❤4🔥1
ወደ ካናዳ‼️
ዜጎችን አሰልጥኖ ወደ ካናዳ መላክ የሚያስችል ስምምነት ተደረገ‼️
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ዜጎችን አብቅቶ ወደ ካናዳ ለመላክ ከፊውቸር ፊል ኢንተርናሽናል ጋር ስምምነት አደረገ።
የስራና ክህሎት ሚንስትር ሙፈሪያት ካሚል በወቅቱ እንደገለፁት
ስምምነቱ ብቁ የሆኑ ዜጎችን አሰልጥኖ ወደ ካናዳ ለመላክ የተደረገ ነው።
የካናዳ መንግስት እውቅና ባለው መልኩ ዜጎችን ለይቶ ወደ ውጪ በመላክ ሁለቱም ሃገራት የጋራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ በኩል ዜጎች በቅተው የስራ እድል የሚያገኙበት እንዲሁም በካናዳ በኩል ደግሞ በቂ የሰለጠነ የሰው ሃይል እንዲኖር የሚያደርግ ነው ብለዋል።
እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ ወደ ካናዳ እንልካለን የሚሉ ህገወጦች አሉ። ይህ ተገቢ አይደለም። በተለያየ ጊዜም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዜጎች ከነዚህ ህገወጦች እንዲጠነቀቁ አሳስቧል።
የዛሬው ስምምነት ግን ዜጎች ሰልጥነው ወደ ካናዳ የሚሄዱበት ነው ብለዋል።
የፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ አብይ ራይሞንድ በበኩላቸው፤ የተደረገው ስምምነት የዜጎችን ችሎታ እና አቅምን ለማውጣት የሚያስችል ነው ብለዋል።
ስልጠናው ለተማሩ ዜጎች ቅድሚያ የሚሰጥ ቢሆንም አቅም አለኝ የሚሉ ዜጎች ተመዝግበው ስልጠናውን ማግኘት ይችላሉ ነው ያሉት።
አክለውም ምዝገባ የሚጀምርበትን ቀን በዋና ዋና መገናኛ ብዙሃም የምናሳውቅ ይሆናል ብለዋል።
ስምምነቱ ኢትዮጵያን ብቻ የሚጠቅም ሳይሆን ለካናዳም የሰለጠነ በቂ የሰው ሃይል እንድታገኝ የሚያደርጋት መሆኑን ገልፀዋል።

👍11❤1
"አሰብ ወደብ ላይ ስቱዲዮ እንከፍታለን" ካሙዙ ካሳ
ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በዕጩነት የቀረቡት ታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ ካሙዙ ካሳ፤ ኢትዮጵያ በቅርቡ የባሕር በር እንደምታገኝና አሰብ ላይ የሙዚቃ ስቱዲዮ እንደሚከፍት ገለጸ።
ካሙዙ አክሎም አሁን ያለው መንግሥት ተቃዋሚዎቹን እንደማያስር ገልጾ፣ የብልፅግና ፓርቲን አለመደገፍ ለቁጭት ሊዳርግ እንደሚችል አስጠንቅቋል። "መደገፍ አገር ወዳድነት ነው" ያለው አቀናባሪው፣ ሁሉም ዜጋ በመንግሥት የልማት ሥራዎች ላይ እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል።

🤪25😁6🤣6❤5🔥1😢1
ቻይና አዳዲስ የኢንተርኔት ሳተላይቶችን ወደ ዝቅተኛዉ የምድር ምህዋር አመጠቀች
ቻይና ዛሬ ሃሙስ ማለዳ ላይ አዲስ ቡድን ነዉ የተባለ ዝቅተኛ የምድር ምህዋር የኢንተርኔት ሳተላይቶችን በተሳካ ሁኔታ አምጥቃለች ፣ይህም ማስፋፊያ የህዋ ፕሮግራሟ ላይ ሌላ እርምጃ መሆኑን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።
ሳተላይቶቹ በሰሜን ሻንዚ ግዛት ከሚገኘው ታይዩዋን የሳተላይት ማስጀመሪያ ማዕከል በጠዋት ወደ ህዋ የተላኩ መሆናቸውን ዢንዋ ዘግቧል።
ባለሥልጣናቱ እንዳረጋገጡት የሳተላይት ቡድኑ 21ኛው ባች ሲሆን ዝቅተኛ ምህዋር ሲሆን የኢንተርኔት ሳተላይቶቹ ወደተዘጋጀለት ምህዋር በተሳካ ሁኔታ መግባቱን አረጋግጠዋል።
ተልእኮው 637ኛው የሎንግ መጋቢት ሮኬት ተከታታዮች በረራ በመሆን ለቻይና የጠፈር ጥረቶች ምእራፍ አዲስ ምልክት ተደርጓል።

የአሜሪካ ፍርድ ቤት 5,000 ኢትዮጵያውያን ለማባረር የቀረበው ክስ ውድቅ አደረገ።
የአሜሪካ ፌደራል ዳኛ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በሺዎች በሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ተግባራዊ ለማድረግ አቅዶት የነበረውን የጊዜያዊ የህግ ከለላ (TPS) ስረዛ ውድቅ አደረጉ።
ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ፣ አስተዳደሩ ከለላውን ለመሰረዝ ያቀረበው ምክንያት በቂ ህጋዊ መሰረት የሌለውና በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ያላገናዘበ መሆኑን ገልጿል።
ይህም ውሳኔ በአሜሪካ የሚኖሩና ከለላው ተጠቃሚ የሆኑ 5,000 ያህል ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ በህጋዊ መንገድ መቆየታቸውንና ስራቸውን መቀጠል እንዲችሉ የሚያስችል ነው ተብሏል።
የፍትህ ሚኒስቴር ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የነበረው ግጭትና አስቸጋሪ ሁኔታ መሻሻል አሳይቷል በሚል ከለላውን ለማንሳት ቢሞክርም፣ ዳኛው ግን አስተዳደሩ ውሳኔውን ከማሳለፉ በፊት በሀገሪቱ ያለውን ተጨባጭ የጸጥታና የሰብዓዊ ሁኔታ በሚገባ አልመረመረም ሲሉ ተችተዋል።
ውሳኔው ለሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና ለኢሚግሬሽን ጠበቆች፣ ፍርዱ በስጋት ላይ ለነበሩ ቤተሰቦች ትልቅ እፎይታ የሰጠ ነው።

👍9❤2
በትራፊክ አደጋ ጉዳት ደርሶባት የነበረችው ህፃን ሔርማ ስንታየሁ ህይወቷ አለፈ
በተባበሩት አደባባይ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ምክንያት በፅኑ ቆስላ በህክምና ስትረዳ የቆየችው ህፃን ሔርማ ስንታየሁ (እኩቹ) በዛሬው እለት ህይወቷ ማለፉ ተረጋገጠ። የህፃኗ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም በሰዓሊተ ምህረት ማርያም ካቴድራል ተፈጽሟል።
መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም በደረሰው በዚሁ የትራፊክ አደጋ፣ የአንድ ሰው ህይወት ወዲያውኑ ማለፉንና ሶስት ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው እንደነበር ፖሊስ መግለጹ ይታወሳል። ህፃን ሔርማ በደረሰባት ከባድ ጉዳት ላለፉት ቀናት በህክምና ስትረዳ ብትቆይም፣ ጥረቱ ሳይሳካ ቀርቶ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

😢33💔8❤2😍1
ትክክለኛ የባህል መዳኒት ይፈልጋሉ??
👆መርጌታ የባህል ህክምና 0915398834
1🌿ለሀብት ማምጫ
2🌿ለእቁብ (እቁብ እንዲወጣላችሁ የሚያረግ)
3ለመስተፋቅር
4🌿 &መጠብቅ (ከጠላት ከሚላክ ሟርት የሚጠብቅ)
5🌿ለጋኔን
6🌿ለማንኛውም ዓይነት በሽታ መፍትሔ
7🌿ለራእይ (በህልም የሚያሳይ)7
8🌿 ለፀር (ለጠላት)
9🌿ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)
10🌿 ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)
11🌿ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)
12🌿ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)
13🌿 መስተፋቅር
14🌿ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
15🌿ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ
16🌿ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)
17🌿የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ
18🌿ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)
19🌿መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)
20🌿መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)
21🌿ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)
22🌿ለልሳነ_ሰብእ
23🌿ለበረከት
24🌿ለእግረ_መልስ (ጥሎ ለጠፋ ሰው መመለሻ ማምጫ)
25🌿ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)
26🌿ጸሎተ_ዕለታት
27🌿ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ
28🌿ንባብ ስናነብ ቀልጣፋ የሚያረግ
29🌿ለከበሮ
30🌿ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)
31🌿ለሙግት
32🌿ለሰላቢ
33🌿ለስንፈት ወሲብ
34🌿ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)
35🌿ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)
36🌿ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)
በ 0915398834 ይደውሉልን

❤1