አዲስ MAGAZINE - መረጃ
31.5K subscribers
6.42K photos
221 videos
3 files
262 links
#አዲስ_Magazine_መረጃ

#መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ

#ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addis_Magazinebot

Addis Ababa , Ethiopia

የአዲስ ነገር መረጃ ቻናል አጋር ሚዲያ
Download Telegram
ምንም ጥያቄ የለውም አሜሪካ አሸንፋለች ሲሉ ትራምፕ ተናገሩ

ዶናልድ ትራምፕ ዩናይትድ ስቴትስ ከኢራን ጋር ለሁለት ሳምንታት የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ “ጠቅላላ እና የተሟላ ድል” አሜሪካ ማግኘቷ ምንም ጥርጥር የለውም ሲሉ ተናገሩ። ይፋ ከተደረገው ስምምነት በኋላ ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በሰጡት ቃለ ምልልስ የኢራን የበለፀገው ዩራኒየም በስምምነቱ “ፍፁም እንክብካቤ ይደረግለታል” ሲሉ ተደምጠዋል።

ትራምፕ በዩራኒየም ላይ ስለሚሆነው ነገር ምንም አይነት ዝርዝር መረጃ ሳይሰጡ " እልባት አልነበረም" ብለዋል። ስምምነቱ ከተቋረጠ የኢራንን የሲቪል ኃይል ማመንጫዎች እና ድልድዮች ለማጥፋት ወደ መጀመሪያው ዛቻቸው ይመለስ እንደሆነ የተጠየቁት ትራምፕ የምናየው ይሆናል ብለዋል።

የዋይት ሀውስ የፕሬስ ሴክሬታሪ ካሮሊን ሌቪት የተኩስ አቁም ስምምነቱ ለአሜሪካ እንደ ድል ይወሰዳል በማለት አሞካሽተው በትራምፕ እና የአሜሪካ ጦር ተፈፀመ ብለዋል። ከመጀመሪያው አንስቶ፣ ትራምፕ ጦርነቱ ከአራት እስከ ስድስት ሳምንታት እንደሚቆይ ገምተው ነበር፣ እናም በ38 ቀናት ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስ የዋሽንግተንን ዋና ዋና ወታደራዊ አላማዎች አሳክታለች ሲሉ አክለዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
5👏5😁5
ብራዚል የሥጋ ውጤቶችን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ፍቃድ አገኘች‼️

​የላቲን አሜሪካዊቷ ሀገር ብራዚል፣ የበሬ፣ የዶሮ እና የአሳማ ሥጋን ጨምሮ 17 የግብርና ምርቶችን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ የሚያስችላትን ይፋዊ ፍቃድ ማግኘቷን የሀገሪቱ ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

​የብራዚል ግብርና ሚኒስቴር የንግድ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ፀሐፊ ልዊስ ሩዋ ለሮይተርስ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በ130 ሚሊዮን ህዝቧ ለብራዚል ምርቶች ትልቅና ወሳኝ ገበያ ናት።

ይህ ስምምነት ባለፈው ሳምንት ሹመት ለተቀበሉት አዲሱ የግብርና ሚኒስትር አንድሬ ዲ ፓውላ የመጀመሪያው የገበያ ስኬት ተደርጎ ተወስዷል።

​ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ እንደሚያሳድገው ይጠበቃል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
🤣137👍1
አዲስ MAGAZINE - መረጃ
Photo
ኢሕአፓ ከአንድ ወር በኋላ የሚካሄድ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ

ኢሕአፓ አስቻይ ሁኔታዎች ባልተሟሉበት የሚካሄድ ምርጫ “አምባገነንነትን እንደሚያጠናክር” በመግለጽ ለሚያዝያ 30 የተቃውሞ ሰልፍ ጠራ፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ በአገሪቱ በአሁኑ ወቅት ያለው ነባራዊ ሁኔታ “ነፃ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒነት ያለው ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል አይደለም” ሲል አስታውቋል።

ፓርቲው የሥልጣን ሽግግር በሕዝብ ፈቃድና በነፃ ምርጫ መከናወን እንዳለበት በጽኑ ቢያምንም፣ አሁን ያለው ሁኔታ ግን የገዥው ብልጽግና ፓርቲ “የሥልጣን ዕድሜውን ለማራዘም የሚጠቀምበት የመሸወጃ ትርዒት” እንጂ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሂደት አይደለም ሲል ወቅሷል።

ምርጫ “በአንድ ጀምበር ድምፅ በመስጠት ብቻ የሚጠናቀቅ ሳይሆን ዜጎች ሃሳባቸውን በነፃነት የሚገልጹበት፣ የፖለቲካ ኃይሎች አማራጭ ሃሳብ የሚያቀርቡበት ሰፊ ምኅዳርና ነፃ የምርጫ አስፈጻሚ አካል የሚጠይቅ ሂደት መሆኑን” ኢሕአፓ በመግለጫው አመልክቷል።

በአሁኑ ወቅት በመላ አገሪቱ ሰላምና መረጋጋት በጠፋበት፣ ንጹሐን ዜጎች በድሮንና በከባድ መሣሪያዎች ጥቃት ሰለባ እየሆኑ ባለበት እንዲሁም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በረሃብና በድህነት እየማቀቁ በሚገኙበት ሁኔታ ምርጫ ማካሄድ አደገኛ መሆኑን ፓርቲው አስገንዝቧል።

በተለይም በትግራይ፣ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ያለው የጦርነት ወላፈንና የዜጎች መፈናቀል ሳይቆም የሚደረግ ምርጫ “የአገር አንድነትን ከመሠረቱ የሚንድና አምባገነንነትን የሚያነግሥ እንደሆነም” አክሎ ገልጿል። በተጨማሪም ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በማንነታቸውና በፖለቲካ አመለካከታቸው ታስረው በሚገኙበት እንዲሁም የዴሞክራሲ ተቋማትና ሚዲያዎች በመንግሥት ጫና ሥር በወደቁበት ወቅት የምርጫው ተዓማኒነት ጥያቄ ውስጥ እንደሚወድቅ ፓርቲው አስታውቋል።
ኢሕአፓ ከዚህ ቀደም ትክክለኛ ምርጫ ሊካሄድ ይችል ዘንድ ያቀረባቸው ቅድመ ሁኔታዎች አለመሟላታቸውን የገለጸ ሲሆን፣ ያለ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎችና ያለ እውነተኛ ብሔራዊ ድርድር የሚካሄድ ሂደት “ለሕዝብ ስቃይ መቀጠል ምክንያት” እንደሚሆን ገልጿል።

በመሆኑም “የንጹሐን ጭፍጨፋና አፈና በአስቸኳይ እንዲቆም፣ የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱና የኑሮ ውድነትን የሚገቱ እርምጃዎች እንዲወሰዱ” ፓርቲው ጠይቋል።

እነዚህን ጥያቄዎች ለማስተጋባትና አምባገነንነትን ለመቃወም በሚልም፣ ኢሕአፓ ልክ ለዛሬ ወር ዓርብ ሚያዝያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ፣ በመቀሌ፣ በባሕር ዳር፣ በጎንደር፣ በሐዋሳ፣ በአሶሳ፣ በአዳማ፣ በአምቦ፣ በድሬዳዋና በሐረር ከተሞች ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱን በማሳወቅ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጎኑ እንዲቆም ጥሪውን አስተላልፏል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
11😁11🙏3
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለትንሳኤ በዓል ከ4 ሺህ በላይ የእርድ እንስሳትን አዘጋጅቷል

የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ንጽህናው የተጠበቀ ሥጋ ለማቅረብ ከከተማ ግብርና እና ከልኳንዳ ነጋዴዎች ማኅበር ጋር በመሆን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ድርጅቱ ገልጿል።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ ደሳለኝ እንደገለጹት፤ ለእርድ ከቀረቡት እንስሳት መካከል 2 ሺህ 600 በሬዎች እንዲሁም 1 ሺህ 400 የሚሆኑ በግና ፍየሎች ይገኙበታል።

ድርጅቱ ቀደም ሲል ያጋጥሙት የነበሩ የቦታ ጥበብ ችግሮችን በመቅረፍ፣ በአሁኑ ወቅት በአንድ ሰዓት ውስጥ ብቻ እስከ 800 የሚደርሱ ከብቶችን ማረድ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም አቶ ሙሉጌታ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ፀጋ ለማ፤ ለበዓሉ የሚቀርቡ እንስሳትን ጤንነት የሚመረምሩ ከ40 በላይ ባለሙያዎች መሰማራታቸውን ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ እንስሳቱ በቁመና ላይ እያሉ የጤና ሁኔታቸው መመርመር ስላለበት፤ የከሱ፣ የጤና ሁኔታቸው የሚያሰጋ እና የጸነሱ ሴት እንስሳትን የመለየት ሥራ እንደሚሠራ ገልጸዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
3😱1
ኢራን ጦርነቱን ሙሉ ለሙሉ ለማቆም ምሽት ላይ ለአሜሪካ የድርድር ነጥቦችን አስገብታለች።

1. ኢራን ላይ ጥቃት ላለመሰንዘር

2. የኢራን የሆርሙዝ ባህር ሰርጥ ቁጥጥር እንዲቀጥል ለማድረግ

3. የኢራንን ዩራኒየም ማበልጸግን ለመቀበል

4. ለኢራን ካሳ ለመክፈል

5. ሁሉንም የጸጥታው ምክር ቤት እና Guardian Council ውሳኔዎችን ለማቋረጥ

6. ሁሉንም ኢራን ላይ የተጣሉ ቀዳሚ እና የሁለተኛ ደረጃ ማዕቀቦችን ለማንሳት

7. የአሜሪካ ተዋጊ ኃይሎችን ከቀጠናው ለማስወጣት

8. እንዲሁም በሊባኖስ ውስጥ በሒዝቦላህ ላይ የሚደረገውን ጨምሮ በሁሉም ግንባሮች ላይ ጦርነት ለማቆም

ዶናልድ ትራምፕ እነዚህ የኢራን የድርድር ነጥቦች እንደ ደረሳቸው ይፋ አድርገዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
😁5💔4👍32
“ለኢራን ጦር መሳሪያ እንዳትሸጡ “ትራምፕ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኢራን የጦር መሳሪያ የሚሸጡ አገራት ላይ 50 በመቶ ታሪፍ እጥላለሁ ሲሉ ዛቱ።

አሜሪካ እና ኢራን ለረዥም ጊዜ የሰላም መንገድ ተጉዘዋል ያሉት ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ሚዲያቸው ላይ ታሪፍን ማንሳታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

ለቴህራን አጋሮች እና ወዳጆች ማሳሰቢያ ሰጥተዋል ሪፐብሊካኑ።

ወታደራዊ ጦር መሳሪያዎችን ለኢራን የሚያቀርቡ አገራት ወዲያውኑ ታሪፍ ይጣልባቸዋል በሚል መዛታቸው ዋሽንግተን የያዘችውን አቋም ጥያቄ ውስጥ አስገብቷል።

ለኢራን የጦር መሳሪያ የሚሸጡ አገራት
ወደ አሜሪካ በሚገቡ በሁሉም ምርቶቻቸው ላይ ቀረጥ እንደሚጣልባቸው እያወቁ ያድርጉት ብለዋል።

ከታሪፍ የሚያልፍ አንድም ምርት አይኖርም በሚል አሳስበዋል ዶናልድ ትራምፕ።

ማሳሰቢያው የሁለት ሳምንቱን የተኩስ አቁም ስምምነት ችግር ውስጥ እንዳይከተውም ተሰግቷል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
5
ሰበር ዜና፦ በኤምሬትስ እና ኩዌት ላይ ጥቃት ተሰነዘረ

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ቢኖርም፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና በኩዌት ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተሰማ። ጥቃቱ የተሰነዘረው በዓለም አቀፍ የንግድ መስመር በሆነው የሆርሙዝ ወሽመጥ አካባቢ ባለው የደህንነት ስጋት ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁኔታውን እየተከታተሉ ሲሆን፣ ክስተቱ በቀጣናው አዲስ የጂኦፖለቲካ ውጥረት እና በነዳጅ ገበያው ላይ ስጋት ደቅኗል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
1
"ተኩስ አቁሙ ይፈርሳል"ኢራን

ኢራን ይህን ያለችው እሰራኤል በሊባኖስ እያደረገች ያለችውን ጥቃት ካላቆመች የተኩስ አቁም ስምምነቱ ይፈርሳል ብላለች ።

ኢራን በሊባኖስ ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ዛሬ ፈጽማለች።

እሰራኤል በ10 ደቂቃ ውስጥ ከ100 በላይ ጥቃቶችን ፈጽማለች ።

ከዚህ በፊት ኢላማ ያልነበሩ ቦታዎችም በሊባኖስ ጥቃት ደርሶባችዋል ።

ከተኩስ አቁሙ በሗላ የአሜሪካው ምክትል ኘሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ "በቀላሉ ሊፈርስ የሚችል ስምምነት" ሲሉ መደመጣቸውም ሌላው የተኩስ አቁሙ መጽናት ስጋት ሆኗል።(አልጀዚራ)

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
1
ሰበር

በሆርሙዝ ሰርጥ ሲያልፉ የነበሩ ነዳጅ የጫኑ መርከቦች እንዲቆሙ ተደረገ ።

እስራኤል ሊባኖስ ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ በሆርሙዝ ሰርጥ ያልፉ የነበሩ መርከቦችን ኢራን ማስቆሟን ዋልተር ብሉምበርግ ገልፍ ኒውስን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል ።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
4😱3
ትራምፕ በሆርሙዝ ሰርጥ የመርከቦች ጉዞን ከኢራን ጋር መቆጣጠር ይፈልጋሉ

ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን የፍኖተ ሆርሙዝ ለመርከቦች ክፍት መሆን የተኩስ አቁሙ ስምምነት ቁልፍ ቅድመ ሁኔታ እንደነበር ገለጠች።

እንደ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ገለጻ፦ ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ደሕንነት በማስጠበቅ አብረው ሊሠሩ ይችላሉ።

ይህን በተመለከተም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሲናገሩ፤ በሆርሙዝ ሰርጥ የሚያልፉ መርከቦች ደሕንነት በኢራን እና በአሜሪካ ጥበቃ እንደሚደረግላቸው ተናግረዋል።

ፕሬዚደንቱ ለኤቢሲ ኒውስ እንደተናገሩት ከሆነ፤ የመርከቦች ደሕንነትን ለማስጠበቅ በዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን መካከል የጋራ ፕሮጄክትን ለመተግበር እያሰቡበት መሆኑንም ገልጠዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ኢራን አሁንም በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ የመርከብ ጭነቶችን መቆጣጠርዋን እንደቀጠለች መሆኑ ተዘግቧል።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በሰጡት መግለጫ መሠረት፣ የመርከቦች ትራፊክ ፍሰት እንደቀድሞው ሁሉ «በኢራን የጦር ኃይሎች ፈቃድ» ተገዢ ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
8👏3
ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን መልሳ ዘጋች

እስራኤል በሊባኖስ ላይ የሰነዘረችውን ተከታታይ ጥቃት ተከትሎ የኢራን መንግስት ለአለም የነዳጅ ንግድ ቁልፍ መተላለፊያ የሆነውን የሆርሙዝ ወሽመጥ የንግድ መርከቦች እንዳያልፉበት ሙሉ በሙሉ መዝጋቱን አስታውቋል።

የኢራን ይፋዊ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከሆነ ይህ እርምጃ የተወሰደው ቀጠናዊ ውጥረቱ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ሲሆን ይህም በቅርቡ ተደርሶ የነበረውን ደካማ የተኩስ አቁም ስምምነት ወደ መፍረስ ደረጃ አድርሶታል።

በአሁኑ ሰዓት በወሽመጡ ላይ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች እንቅስቃሴ ተቋርጦ የሚገኝ ሲሆን፥ ይህ ድንገተኛ ውሳኔ በአለም አቀፍ የኢነርጂ አቅርቦት እና በኢኮኖሚ መረጋጋት ላይ ከፍተኛ አደጋ ሊደቅን እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች በስጋት እየገለጹ ይገኛሉ።

የእስራኤል ጥቃት በሊባኖስ ውስጥ እያደረሰ ያለው ጉዳት መቀጠሉ ኢራን እንዲህ ያለውን ጠንከር ያለ እርምጃ እንድትወስድ ያስገደዳት ሲሆን፥ ሁኔታው ወደ ሰፋ ያለ ቀጠናዊ ጦርነት የማምራት እድሉ ሰፊ ሆኗል።

"የቀጠናው ደህንነት እስካልተረጋገጠ ድረስ የሆርሙዝ ወሽመጥ ዝግ ሆኖ ይቆያል።" ይላል ከቴህራን የተሰጠ መግለጫ


@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
6👍3😁1😢1
ትክክለኛ የባህል መዳኒት ይፈልጋሉ??
👆መርጌታ
የባህል ህክምና 0915398834


1🌿ለሀብት ማምጫ
2🌿ለእቁብ (እቁብ እንዲወጣላችሁ የሚያረግ)
3ለመስተፋቅር
4🌿 &መጠብቅ (ከጠላት ከሚላክ ሟርት የሚጠብቅ)
5🌿ለጋኔን
6🌿ለማንኛውም ዓይነት በሽታ መፍትሔ
7🌿ለራእይ (በህልም የሚያሳይ)7
8🌿  ለፀር (ለጠላት)
9🌿ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)
10🌿 ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)
11🌿ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)
12🌿ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)
13🌿 መስተፋቅር
14🌿ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
15🌿ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ
16🌿ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)
17🌿የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ
18🌿ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)
19🌿መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)
20🌿መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)
21🌿ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)
22🌿ለልሳነ_ሰብእ
23🌿ለበረከት
24🌿ለእግረ_መልስ (ጥሎ ለጠፋ ሰው መመለሻ ማምጫ)
25🌿ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)
26🌿ጸሎተ_ዕለታት
27🌿ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ
28🌿ንባብ ስናነብ ቀልጣፋ የሚያረግ
29🌿ለከበሮ
30🌿ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)
31🌿ለሙግት
32🌿ለሰላቢ
33🌿ለስንፈት ወሲብ
34🌿ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)
35🌿ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)
36🌿ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)

በ 0915398834  ይደውሉልን
1🙈1
በሊባኖስ በትላንትናው እለት ብቻ ቢያንስ 254 ሰዎች በእስራኤል ጥቃት ተገደሉ

የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋፍ ሳላም "የእስራኤልን የግድያ ማሽን ለማስቆም ሁሉንም የሊባኖስ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ሀብቶች" እያሰባሰቡ ባሉበት በዚህ ወቅት ረቡዕ ዕለት ብቻ ቢያንስ 254 ሰዎች ሲገደሉ ከ1,165 በላይ በእስራኤል የጥቃት ማዕበል ቆለስዋል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ሊባኖስ በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል የተኩስ አቁም ውስጥ አልተካተተችም ያሉ ሲሆን የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ እንዲሁ “ይህንን ቃል አልገባንም” ብለዋል ።

በዚህ ጥቃት እስራኤል አለም አቀፍ ህግን፣ አለም አቀፍ የሰብአዊ ህግጋትን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተርን መርሆችን ጥሳለች ሲል የሶሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴሩ የዜጎችን ጥበቃ እና የሊባኖስን ሉዓላዊነት ለማክበር አግባብነት ያለው የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎች በአስቸኳይ ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር ጠይቋል ሲል በኤክስ ላይ በተጋራው መግለጫ ተመላክቷል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
6
የ10 ዓመት ታዳጊ የሆነችውን የስጋ ዘመዱን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በምስራቅ ቦረና ዞን ጐሮ  ዶላ ወረዳ ውስጥ የወንጀለ ድርጊቱ ተፈጽሟል፡፡ተከሳሽ  የቅርብ ዝምድና ያላትን የአስር አመት ልጅ አታሎ በመውሰድ የግብረ ስጋ ድፍረት ፈጽሟል፡፡

የምስራቅ ቦረና ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር በቃሉ በለጠ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ተከሣሽ ደንቦባ ነፃነት የተባለው ሲሆን የቅርብ የስጋ ዝምድና ያላትን  የአስር አመት ታዳጊ አታሎ በመውሠድ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል  እንደፈፀመባት ተናግረዋል። ታዳጊዋ ከልጆች ጋር ስትጫወት አታሎ በመውሰድ የአገድዶ መድፈር ወንጀል ከፈፀመባት በኃላ እራሱን ሸሽጎ የተሠወረ ሲሆን ታዳጊዋ ሽንት መሽናት ሲያቅታት ቤተሠቦች ተጠራጥረው ሲጠይቋት የመደፈር ጥቃት እንደተፈፀመባት በመናገገሯ ቤተሰቦች ጉዳዩን ለፖሊስ በማሳወቅ የድርጊቱ ፈፃሚ ከተሸሸገበት ስፍራ  በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡

ፖሊስም ጥቃት የደረሠባት ታዳጊ በነገሌ ሆስፒታል በማስመርመር የምርመራ መዝገቡን ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር በማያያዝ ለአቃቢ ህግ ይልካል።ክሱን የተመለከተው የምስራቅ ቦረና ዞን መጋቢት28 ቀን 2018 ዓም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ደንቦባ ነፃነት ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ  በ14 ዓመት እስራት እንዲቀጣ የተወሠነበት መሆኑን ኮማደር በቃሉ በለጠ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
2😢2
ትራምፐ እና ኤርዶዋን ምን መከሩ?

የቱርክ ፕሬዝዳንት ረጂብ ጠይብ ኤርዶዋን እና የአሜሪካው አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ በቀጠናዊ ጉዳዮችና በኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት ዙሪያ በስልክ ተወያዩ፡፡

ውይይቱ በዋናነት ትኩረቱን ያደረገው በኢራን እና አሜሪካ መካከል በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ነው።

ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ከ40 ቀናት ውጥረት በኋላ የተገኘው የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት ወደ ዘላቂ ሰላም ለመሸጋገር ወሳኝ ዕድል መሆኑን ገልጸዋል።

ቱርክ ከወዳጅ አገራት ጋር በመሆን ለቀጣይ የሰላም ስምምነቶች የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ያረጋገጡት ኤርዶዋን ይህንን ሂደት ሊያደናቅፉ ከሚችሉ ማናቸውም ድርጊቶች መቆጠብ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ቱርክ ለሰላም ጥረቱ የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ካረጋገጡ በኋላ ፤ እንደ ፓኪስታን ካሉ ወዳጅ እና ወንድም አገራት ጋር በመሆን ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን ለማጠናከር ቃል ገብተዋል።

ትራምፕ በበኩላቸው የኢራን መንግስት ለድርድር ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ባለ 10 ነጥብ የውሳኔ ሃሳብ አቅርቧል ቢሉም አሁንም ድረስ የተኩስ አቁሙ ጉዳይ ከስጋት አልወጣም ሲሉ ተንታኞች ይሞግታሉ፡፡

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
7
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለትንሳኤ በዓል አስተማማኝ የኃይል አቀርባለው አለ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በመጪው የትንሳኤ በዓል ወቅት ሊከሰት የሚችለውን የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ለመቀነስ ሰፊ የቅድመ-ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል።

ተቋሙ በበዓላት ሰሞን የሚኖረውን ከፍተኛ የኃይል ፍላጎትና በመሰረተ-ልማቱ ላይ የሚፈጠረውን ጫና ታሳቢ ያደረገ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገልጿል።

የተቋሙ የኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ አንዋር አብራር እንደገለጹት፣ ከበዓሉ አስቀድሞ የመካከለኛና ዝቅተኛ ማሰራጫ መስመሮችን የመፈተሽ፣ የረገቡ ገመዶችን የመወጠር እና የእንጨት ምሰሶዎችን በኮንክሪት የመተካት ስራዎች ተከናውነዋል።

በተጨማሪም የኃይል ጫና ያለባቸውን ትራንስፎርመሮች አቅም የማሳደግና አዳዲስ አጋዥ ትራንስፎርመሮችን የመትከል ስራ መከናወኑን አስረድተዋል።

በበዓሉ ዋዜማና በዕለቱ ለሚከሰቱ ድንገተኛ የኃይል መቆራረጦች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በሁሉም የአገልግሎት አደረጃጀቶች ውስጥ የአስቸኳይ ጥገና ግብረ-ኃይል ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱ ተገልጿል።

ይህም ደንበኞች አስተማማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል እንደሆነ ተቋሙ አመልክቷል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
😁63👏1🕊1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ፣ ዛሬ ጠዋት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች እና ጽሕፈት ቤቱ ለሚያሳድጋቸው ሕጻናት ማዕድ አጋርተዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
5