አዲስ MAGAZINE - መረጃ
31.5K subscribers
6.44K photos
222 videos
3 files
262 links
#አዲስ_Magazine_መረጃ

#መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ

#ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addis_Magazinebot

Addis Ababa , Ethiopia

የአዲስ ነገር መረጃ ቻናል አጋር ሚዲያ
Download Telegram
አንጋፋዋ ዲፕሎማት አምባሳደር  ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

አምባሳደር ቆንጂት በአገልግሎት ዘመናቸው፣ በኦታዋ፣ ካይሮ፣ ቴል አቪቭ እና ቪዬና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ኾነው ያገለገሉ ሲኾን፤ በአፍሪካ ኅብረትና በተባባሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቋሚ መልዕክተኛ በመሆን ሠርተዋል።

አምባሳደር ቆንጂት፣ በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክቶሬትንም ለበርካታ ዓመታት በዋና ዳይሬክተርነት መርተዋል። ከዮዲት እምሩ በመቀጠል በኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ሴት አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ቆንጂት፣ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴርን በወጣትነታቸው የተቀላቀሉት በ1950ዎቹ ነበር።

ጠቅላይ ሚሚንስትር ዐቢይ፣ አምባሳደር ቆንጂት ከእርሳቸው በኋላ በርካታ ሴት ዲፕሎማቶች በመስኩ እንዲሠማሩ መንገዱን አስፍተዋል በማለት በአምባሳደሯ ሕልፈት የተሠማቸውን ሐዘን በገለጹበት መልዕክት ላይ ጠቅሠዋል።

@Addis_Magazine
1
ሰበር መረጃ‼️
በኢራን ላይ ትልቁ የአሜሪካ ጥቃት ዛሬ ለሊት 9:47 ላይ እንደሚጀመር ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ።
ከሁሉም የተሻለ እቅድ አለኝ፣ ግን እቅዴ ምን እንደሆነ በግልጽ መናገር አልፈልግም" ያሉ ሲሆን የነገው ጥቃት ከዛሬው ይብሳል ብለዋል። ኢራን ከነገ ጀምሮ ድልድይ፣ የሀይል ማመንጫ... አይኖራቸውም። የድንጋይ ዘመን ሰዎች ይሆናሉ ብለዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
😁94👏1😡1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ ሕልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የኀዘን መልዕክት÷ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲው መስክ ያገለገሉት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ ብለዋል።

አምባሳደር ቆንጂት ከልጅነት እስከ ዕውቀት ኢትዮጵያን በዲፕሎማትነት በማገልገል ከአምባሳደር ዮዲት እምሩ ቀጥለው ሁለተኛዋ ሴት የኢትዮጵያ አምባሳደር መሆናቸውን ገልጸዋል።

ለሕግ፣ ለአሠራር፣ ለፕሮቶኮል እና ለኢትዮጵያ ጥቅሞች በነበራቸው የጸና አቋም እናስታውሳቸዋለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷ ከእርሳቸው በኋላ አያሌ ሴት ዲፕሎማቶች በመስኩ እንዲሠማሩ መንገዱን አስፍተዋል ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ስላሴ እና የአፍሪካ ህብረትም በአምባሳደር ቆንጂት ስነ ጊዮርጊስ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል፡፡

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
6
በአየርላንድ ደሴቶች ላይ ለመኖር ፈቃደኛ የሆነ 90 ሺህ ዶላር ክፍያ እሰጣለው አለች

አዲስ ህይወት በውብ የባህር ዳርቻ ላይ ለመጀመር ለሚያልሙ ሰዎች አየርላንድ አስገራሚ እድል ይዛ ቀርባለች።

"Our Living Islands" የተሰኘውና በመላው ዓለም ከፍተኛ ትኩረት የሳበው ይህ አዲስ መርሃ ግብር፣ በሀገሪቱ ገለልተኛ ደሴቶች ላይ ሄደው ለሚኖሩ ዜጎች እስከ 90 ሺህ የአሜሪካ ዶላር (84 ሺህ ዩሮ) የሚደርስ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ይህ ከፍተኛ የገንዘብ ማበረታቻ የቀረበው የህዝብ ቁጥራቸው በእጅጉ እየቀነሰ የመጡ 30 የሚጠጉ ራቅ ያሉ የደሴት ማህበረሰቦችን እንደገና ለማነቃቃትና ወደ ቀድሞ ህይወታቸው ለመመለስ ታስቦ የተዘጋጀ የ10 ዓመት ስትራቴጂ አካል ነው።

ነገር ግን ይህ ማራኪ አሃዝ በነጻ የሚታደል ገንዘብ አይደለም።

መንግስት ይህንን ድጋፍ የሚሰጠው አዲስ ሰፋሪዎች በነዚህ ደሴቶች ላይ ለዓመታት ተጥለው የቆዩና የፈራረሱ ቤቶችን ገዝተው ሙሉ በሙሉ እንዲያድሱ ለማገዝ ነው።

በአሁኑ ወቅት በነዚህ ደሴቶች ላይ የሚኖሩት ሰዎች ቁጥር ከ3 ሺህ በታች ሲሆን፤ አንዳንዶቹ ደሴቶች ደግሞ በከፍተኛ የባህር ሞገድ ወቅት ከዋናው የሀገሪቱ ክፍል ሙሉ በሙሉ የሚቆረጡ ናቸው።

በመሆኑም እድሉን የሚጠቀሙ ሰዎች የከተማውን ግርግር በባህር ዳርቻው ድምጽ ለመቀየር የሚወስኑት ቁርጠኝነትና የጥገና ስራውን የመወጣት አቅም ሊኖራቸው ይገባል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
12
የእስራኤል ጦር ኢራናውያን ዛሬ ባቡር እንዳይጠቀሙ አስጠነቀቀ፡፡

ትራምፕ በበኩላው የኢራን ስልጣኔ ዛሬ ምሽት መጥፊያው ነው ብለዋል፡፡

የእስራኤል ጦር በይፋዊ የማኅበራዊ የትስስር ገጹ ላይ በፋርስ ቋንቋ ባሰፈረው መልዕክት በኢራን የሚኖሩ ሰዎች “ለደህንነታችሁ” በማለት ”በባቡር ከመጓዝ ተቆጠቡ” ብሏል።

ማስጠንቀቂያው በመላው አገሪቱ ለሚኖሩ ኢራናውያን መሆኑን የገለጸው ጦሩ በኢራን ሰዓት አቆጣጠር “እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት” ድረስ ማስጠንቀቂያው እንደሚቆይ ገልጿል።

አክሎም “በባቡር ውስጥ መሆን አና በባር ሃዲዶች አቅራቢያ መገኘት ሕይወታችሁን አደጋ ላይ ይጥለዋል” ብሏል።

የእስራኤል ጦር ማስጠንቀቂያ የተሰማው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመላው ኢራን የሚገኘው የሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መዛታቸውን ተከትሎ ነው።

በተመሳሳይ ዜና የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ስልጣኔ ዛሬ ምሽት መጥፊያው ነው ሲሉ ዝተዋል፡፡

ይህ እንዳይሆን ሀገሪቱ ስምምነት መድረስ እንዳለባት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት በማኅበራዊ ገጻቸው ባሰራጩት የዛቻ መልዕክት ጠቁመዋል፡፡

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
5🕊2👍1😱1
ከ40,000 በላይ ፊሊፒናውያን በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት የተነሳ ስራ ማቆማቸዉ ተነገረ

በእስራኤል፣ በሊባኖስ እና በገልፍ ሀገራት ለስራ ሊያቀኑ የነበሩ ከ40,000 በላይ ፊሊፒናውያን ከፊሊፒንስ መውጣት አልቻሉም ሲል የፊሊፒንስ ዴይሊ ስታር ዘግቧል።ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚደረጉ የበረራዎች እጥረት ሰራተኞች ወደ ባህር ማዶ ለመጓዝ አዳጋች ሆነዋል። በ2026 በሁለተኛውና በሶስተኛው ሩብ አመት የሰራተኞች ምደባ እየቀነሰ እንደሚሄድ ዘገባው የፍልሰት ባለሙያን ጠቅሷል።

ወደ ቀጠናዉ መሄድ የነበረባቸው ሰራተኞች አሁን በማኒላ በሚገኙ የቅጥር ኤጀንሲዎች በተሰጡ የመጠለያ ማዕከላት ውስጥ ለጊዜው እየቆዩ ሲሆን አንዳንዶቹም ወደ ትውልድ ግዛታቸው ተልከዋል።የፊሊፒንስ መንግስት እስካሁን ከ4,000 የሚበልጡ የፊሊፒንስ ሰራተኞችን እና ጥገኞቻቸውን ከመካከለኛው ምስራቅ ወደ ሀገራቸው መልሷል።በመካከለኛው ምስራቅ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ፊሊፒናውያን በአብዛኛው በባህረ ሰላጤው ክልል ውስጥ ይሰራሉ።

በሌላ መረጃ በመካከለኛው ምስራቅ ለሚካሄደው የአሜሪካ ወታደራዊ ዘመቻ ኃላፊነት ያለው እና በኢራን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እየመራ ያለው የዩናይትድ ስቴትስ ሴንትራል ኮማንድ ኃይሉ ከ13,000 በላይ የኢራን ኢላማዎችን ማጥቃት ችሏል።በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰራጨው ጽሁፍ ከ155 በላይ የኢራን መርከቦች ተጎድተዋል ወይም ወድመዋል በማለት የአሜሪካ ኒውክሌር ኃይል አውሮፕላኖች አጓጓዦች እና ሰርጓጅ መርከቦች በኦፕሬሽን ኤፒክ ፉሪ እንዲሁም ከኤፍ-35 ስውር ተዋጊ አውሮፕላኖች እስከ ቢ-52 ቦምቦች የሚደርሱ አውሮፕላኖች እየተሳተፉ መሆኑን ገልጿል። ( ዳጉ_ጆርናል )

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
😢32
ትራምፕ የኢራን ስልጣኔ ዛሬ ምሽት መጥፊያው ነው ሲሉ አስፈራሩ

ይህ እንዳይሆን ሀገሪቱ ስምምነት መድረስ እንዳለባት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት በማኅበራዊ ገጻቸው ባሰራጩት የዛቻ መልዕክት ጠቁመዋል፡፡ ስፑትኒክ

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
👏63😡1
ትራምፕ ኑክሌር ሊጠቀሙ ይችላሉ‼️

ትራምፕ የኒውክሌር ጦር መሳሪያን በኢራን ላይ ሊያሰማራ ይችላል የሚል ስጋት መኖሩን ዘጋርዲያን ዘግቧል።
በአሜሪካ መንግስታዊ ስርዓት ፕሬዚዳንቱ የኒውክሌር ቦንብን የማዘዝ ብቸኛ ስልጣን አላቸው። በዚህ የኑክሌር ትዕዛዝ ሰንሰለት ውስጥ የፕሬዝዳንቱን የኑክሌር ትዕዛዝ ማንም ሰው ጣልቃ ገብቶ ማስቆም አይችልም።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
😱104👍2
አሜሪካ ጥቃት ጀምራለች‼️
የአሜሪካ ጦር በኢራን ወሳኝ የነዳጅ ገበያ ማሳለጫ በሆነችው በካርግ ደሴት ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ጥቃት ፈጽሟል።
ካርግ ደሴት 90% የኢራን ነዳጅ ለውጭ ገበያ የሚቀርብበት የኢራን ወሳኝ የኢነርጂ ማዕከል ነው።
ኢራን በበኩሏ ከዚህ በኋላ ያለምንም ገደብ በአሜሪካ እና አጋሮቿ ላይ ጥቃት እፈፅማለሁ ስትል ማስጠንቀቂያ የሰጠች ሲሆን የቀጠናው ሀገራት እና አሜሪካ ነዳጅ ለአመታት እንዳያገኙ አደርጋለሁ ብላለች።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
👏62😱1
ሩሲያ እና ቻይና የሆርሙዝ ሰርጥ መከፈትን ተቃወሙ

ሩሲያ እና ቻይና የሆርሙዝ ሰርጥ እንዲከፈት የሚጠይቀውን የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት የውሳኔ ሃሳብ ድምፅን በድምፅ በመሻር ውድቅ አደረጉ።

በመሆኑም የውሳኔ ሃሳቡ በአብዛኛው የምክር ቤቱ አባል ሀገራት ድጋፍ ቢኖረውም፣ በሁለቱ ሀገራት ተቃውሞ ሳይጸድቅ ቀርቷል።

ለውሳኔ ሃሳቡ ባሕሬን፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ፣ ግሪክ፣ ላቲቪያ፣ ላይቤሪያ፣ ፓናማ፣ ሶማሊያ፣ እንግሊዝ እና አሜሪካን ጨምሮ 11 ሀገራት የድጋፍ ድምፅ ሰጥተዋል።

በአንጻሩ ቻይና እና ሩሲያ የተቃውሞ ድምፅ ሲሰጡ፣ ኮሎምቢያ እና ፓኪስታን ድምፅ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

የድምፅ አሰጣጡ የተከናወነው፣ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ባለው የባሕር ትራንስፖርት መስመር ላይ በተፈጠረው መስተጓጎል ምክንያት ዓለም አቀፍ የኃይል አቅርቦት ስጋት በናረበት ወቅት ነው።

አልጀዚራ እንደዘገበው፣ የአቅርቦት እጥረት በመፈጠሩ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን፤ አንዳንድ የድፍድፍ ነዳጅ አይነቶች በአንድ በርሜል 150 ዶላር እስከመቸብቸብ ደርሰዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
14😡9
ትክክለኛ የባህል መዳኒት ይፈልጋሉ??
👆መርጌታ
የባህል ህክምና 0915398834


1🌿ለሀብት ማምጫ
2🌿ለእቁብ (እቁብ እንዲወጣላችሁ የሚያረግ)
3ለመስተፋቅር
4🌿 &መጠብቅ (ከጠላት ከሚላክ ሟርት የሚጠብቅ)
5🌿ለጋኔን
6🌿ለማንኛውም ዓይነት በሽታ መፍትሔ
7🌿ለራእይ (በህልም የሚያሳይ)7
8🌿  ለፀር (ለጠላት)
9🌿ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)
10🌿 ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)
11🌿ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)
12🌿ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)
13🌿 መስተፋቅር
14🌿ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
15🌿ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ
16🌿ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)
17🌿የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ
18🌿ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)
19🌿መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)
20🌿መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)
21🌿ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)
22🌿ለልሳነ_ሰብእ
23🌿ለበረከት
24🌿ለእግረ_መልስ (ጥሎ ለጠፋ ሰው መመለሻ ማምጫ)
25🌿ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)
26🌿ጸሎተ_ዕለታት
27🌿ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ
28🌿ንባብ ስናነብ ቀልጣፋ የሚያረግ
29🌿ለከበሮ
30🌿ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)
31🌿ለሙግት
32🌿ለሰላቢ
33🌿ለስንፈት ወሲብ
34🌿ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)
35🌿ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)
36🌿ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)

በ 0915398834  ይደውሉልን
3😱1
ሰበር 🔥

አሜሪካ እና ኢራን የ2 ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት አድርገዋል ። የሆርሙዝ ሰርጥም ሙሉ ለሙሉ ይከፈታል ።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
8👏3😁2😎1
"ስምምነቱ ሊባኖስን አያካትትም" እስራኤል

እስራኤል ሌሊቱን የተፈፀመውን የተኩስ አቁም ስምምነት እንደምትደግፍ በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ ይፋ አድርጋለች።

የጠቅላይ ሚኒስቴር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ፅህፈት ቤት በመግለጫው እስራኤል በኢራን ላይ የምታደርሰውን ጥቃት ለማቆም ፣ ኢራን የሆርሙዝን የባህር ወሽመጥ እንድትከፍት እና በአሜሪካ ፣ በእስራኤል እንዲሁም በቀጠናው ሀገራት ላይ የምታደርሰውን ጥቃት ለሁለት ሳምንታት ሙሉ በሙሉ እንድታቆም የተደረሰውን ስምምነት እንደምትደግፍ ይፋ አድርጓል።

የኔታንያሁ ቢሮ በተጨማሪም እስራኤል ኢራን “ከአሁን በኋላ የኑክሌር ፣ የሚሳኤል እና የሽብር ስጋት እንዳትሆን” ለማረጋገጥ የአሜሪካን ጥረት እንደምትደግፍ እና አሜሪካም በሚቀጥሉት ውይይቶች እነዚህን ግቦች ለማሳካት ቁርጠኛ መሆኗን ለእስራኤል መናገሯን ይፋ አድርጓል።

ይሁን እንጂ ይሄ የተኩስ አቁም ስምምነት ሊባኖስን እንደማያካትት ፅህፈት ቤቱ ያወጣው መግለጫ ያሳያል።

ሌሊቱን የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሼህባዝ ሻሪፍ የሁለት ሳምንቱ የተኩስ አቁም ስምምነት ሌባኖስንም ያካተተ ስለመሆኑ ተናግረው እንደነበር ይታወሳል።

ዘገባው የአልጀዚራ ነው።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
6👍3
ለየኔቢጤ ምጽዋት የሰጡ ተቀጡ

በመስቀለኛ መንገዶች ላይ ምጽዋት የሰጡ፤  ግብይት የፈጸሙ እና ሌሎች የትራፊክ ደንብ የተላለፉ አካላት ተቀጡ

ለአደጋ ተጋላጭነት አላቸው ተብለው በተለያዩ 40 የከተማዋ መንገዶች ላይ በተደረገ ቁጥጥር ከ100 ሽህ በላይ አሽከርካሪዎች መቀጣታቸው ተገልጿል።

በተለይም ለአደጋ መንሰኤ በሆኑት ከፍጥነት ወሰን በላይ ሲያሽከርከሩ የተገኙ 80ሺህ892 አሽከርካሪዎች፣ ከተፈቀደው የአልኮል መጠን በላይ ጠጥተው የተገኙ 1ሺህ 653 አሽከርካሪዎች ላይ የእርምት እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡ 

የደህንነት ቀበቶ ያላደረጉ 3ሺህ 066 ደንብ ተላላፊዎች እና የጭንቅላት መከላከያ ቆብ ያላስሩ 587 የሞተር ብስክሌተኞች እንደጥፋታቸው ደረጃ እንዲታረሙ መደረጉን ወይዘሮ ገነት ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይ 7ሺህ 026 አሽከርካሪዎች ስልክ በማነጋገር፤ 36 በተመረጡ የትራፊክ መብራቶች ፣ አደባባዮች ላይ እና በመስቀለኛ መንገዶች ላይ ምጽዋት የሰጡ እና ግብይት የፈጸሙ 4ሺህ 500 ግለሰቦች: በ110 ለህዝብ ትራንስፖርት ብቻ መቆሚያ ስፍራ (Bus stop) ላይ እንዳይቆሙ በተደረገ ቁጥጥር  25,238 ደንብ ተላላፊዎች በመገኘታቸው መቀጣታቸውን ገልፀዋል፡፡

በተያያዘም በ9 ወራት በእግረኛ መንገድ አጠቃቀም ዙሪያ በተደረገ ቁጥጥር 21 ሺህ 202 እግረኞች በገንዘብ ሲቀጡ: 16 ሺህ 651 እግረኞች  ደግሞ ማህበራዊ አገልግሎት እንዲሰጡና በድምሩ በ37 ሺህ 850 እግረኞች ተጠያቂ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
7👍1🥰1
ይፋ ሆነ

የሌ/ጄ ታደሰ ወረደን ሹመት ለአንድ ዓመት ተራዘመ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደን ሹመት ለአንድ ዓመት አራዝመዋል፡፡

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 62(9)እና በዐዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀፅ 2(ለ) መሠረት የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደርን በርዕሰ መስተዳደርነት እንዲመሩ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ በጸደቀው ደንብ ቁጥር 479/2013 አንቀጽ 4(2) እና የዓመቱን የሥራ አፈጻጸም ባቀረቡት መሠረት ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከሚያዚያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሌ/ጄ ታደሰ ወረደን ሹመት ለአንድ ዓመት ያራዘሙት፡፡

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
6