አዲስ MAGAZINE - መረጃ
31.5K subscribers
6.44K photos
222 videos
3 files
262 links
#አዲስ_Magazine_መረጃ

#መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ

#ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addis_Magazinebot

Addis Ababa , Ethiopia

የአዲስ ነገር መረጃ ቻናል አጋር ሚዲያ
Download Telegram
ትክክለኛ የባህል መዳኒት ይፈልጋሉ??
👆መርጌታ
የባህል ህክምና 0915398834


1🌿ለሀብት ማምጫ
2🌿ለእቁብ (እቁብ እንዲወጣላችሁ የሚያረግ)
3ለመስተፋቅር
4🌿 &መጠብቅ (ከጠላት ከሚላክ ሟርት የሚጠብቅ)
5🌿ለጋኔን
6🌿ለማንኛውም ዓይነት በሽታ መፍትሔ
7🌿ለራእይ (በህልም የሚያሳይ)7
8🌿  ለፀር (ለጠላት)
9🌿ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)
10🌿 ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)
11🌿ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)
12🌿ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)
13🌿 መስተፋቅር
14🌿ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
15🌿ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ
16🌿ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)
17🌿የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ
18🌿ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)
19🌿መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)
20🌿መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)
21🌿ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)
22🌿ለልሳነ_ሰብእ
23🌿ለበረከት
24🌿ለእግረ_መልስ (ጥሎ ለጠፋ ሰው መመለሻ ማምጫ)
25🌿ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)
26🌿ጸሎተ_ዕለታት
27🌿ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ
28🌿ንባብ ስናነብ ቀልጣፋ የሚያረግ
29🌿ለከበሮ
30🌿ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)
31🌿ለሙግት
32🌿ለሰላቢ
33🌿ለስንፈት ወሲብ
34🌿ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)
35🌿ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)
36🌿ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)

በ 0915398834  ይደውሉልን
1
#ሾተላይ ( RH incompatibility )

ሾተላይ ( RH incompatibility )፡ - የእናት እና የፅንስ የደም አይነት አለመጣጣም ሲሆን RH negative በሆኑ ሴቶች ላይ የሚከሰት ችግር ነው ።

ስለሾተላይ ለማወቅና ጥንቃቄ ለማድረግ በመጀመሪያ ስለ ቀይ የደም አይነት እንዴት እንደሚከፈል ማወቅ ያስፈልጋል ። ቀይ የደም አይነት በተለያየ መንገድ ይከፈላል:-

1. ABO System፡- መሰረት በማድረግ Group A, B, AB, እና O ተብሎ ይከፈላል

2. Rh System:– ከላይ ABO ተብለው የተከፈሉት እያንዳንዳቸው በሁለት ማለትም Rh negative እና Rh positive ተብለው ይከፈላሉ, ይህም ማለት A (A+, A-), B (B+, B-), AB (AB+, AB-), እና O (O+ O-) ነው።

Rh negative እና Rh positive ምን ማለት ነው?

✓Rh በቀይ የደም አይነት ላይ የሚገኝ protein ነው ። ይህ Rh protein በላዩ ላይ ያለው ቀይ የደም አይነት Rh+ ሲባል, ይህ protein የሌለው ደግሞ Rh- የደም አይነት ይባላል ።

✓አንድ ሰው የደም አይነቱ የሚወሰነው በወላጆቹ የደም አይነት መሰረት ነው ።

1. ሁለቱም ወላጆች Rh+ ከሆኑ, እርሱም Rh+ የመሆን እድሉ የሰፋ ነው ።

2. ሁለቱም ወላጆች Rh- ከሆኑ እርሱም Rh- ይሆናል።

3. እናት Rh+ ከሆነችና አባት Rh- ከሆነ፣ ልጅ Rh+ወይም Rh- ሊሆን ይችላል ።

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ነገሮች ሁሉ ብዙ ጊዜ ምንም ችግር የላቸውም።

✓ሾተላይ የሚከሰተው ግን እናት ( Rh-) ከሆችና አባት ( Rh+) ሆኖ Rh+ የሆነ ፅንስ በምትፀንስበት ጊዜ ነው።

✓እናት Rh- ሁና፣ Rh+ ፅንስ በምትፀንስበት ጊዜ በተለያዩ አጋጣሚዎች ደም መፍሰስ ሲያጋጥም የፅንሱ ደም ወደ እናት የደም ስር ይገባል፣ በዚህም ጊዜ ከልጁ የቀይ ደም ላይ የሚገኙ ፕሮቲኖችን የእናት በሽታ ተከላካይ ህወሳት ያዩና እንደ ባእድ ነገር በመቁጠር መከላከያ ( antibody ) ያመርታሉ። እነዚህ የተመረቱ antibodies በእናት ደም ውስጥ ተመርተው ወደፅንስ ከሚሄደው የእናት ደም ጋር አብረው በመሄድ የፅንሱን ደም ማጥቃት ይጀምራሉ።

✓Antibody ለማምረት ጊዜ ስለሚፈጅና አብዛኛው ጊዜ የልጅ ደም ወደ እናት የሚሄደው በወሊድ ጊዜ በመሆኑ የመጀመሪያ ልጅ ላይ ችግር አይፈጥርም ።

✓በተከታታይ የሚረገዘው ፅንስ Rh- ከሆነም ምንም አይነት ችግር አይገጥማቸውም።

✓ነገር ግን Rh+ በተረገዘ ጊዜ፣ በእናት ደም ውስጥ ተመረተው የተቀመጡ antibodies የልጁን Rh+ የደም ዓይነት እንደ ባዕድ በመቁጠር እየሄዱ ያጠቁታል።

✓የሰውነታችን በሽታ ተከላካይ ህዋስ፣ በሽታ አምጭ ነገሮች ወደሰውነት ሲገባ የተለያዩ መንገዶች ተጠቅሞ እንደሚጠቃው ሁሉ ፅንሱንም Rh+ የሚል ምልክት በቀይ የደም ሴሉ ሲያይ እንደ ባዕድ ነገር ያየውና ጥቃት ያደርስበታል።

✓ይህ የተፈጠረው antibody የእንግዴ ልጁን በማለፍ የፅንሱን ቀይ የደም ህዋስ ያጠቃል።

በዚህም ምክንያት

-የፅንስ የደም ማነስ
-የፅንስ የልብ ድካም
-በሰውነት በተለያዩ ቦታወች ውሀ መቋጠር
-የፅንስ ውርጃ
-ከተወለደ በኋላ የህፃን ቆዳና አይን ቢጫ መሆን
-እንዲሁም ሞት ሊያስከትል ይችላል

የፅንሱ ደም ወደ እናት እንዲገባ በማድረግ ለሾተላይ የሚያጋልጡ ምክንያቶች

✓በእርግዝና ወቅት ደም መፍሰስ
✓በእርግዝና ወቅት ሆድን መምታት
✓የፅንስ አቀማመጥን ለማስተካከል መሞከር(ECV)
✓የፅንስ በማህፀን ውስጥ መሞት
✓በቅድመ ወሊድ የተለያዩ የምርመራ ሂደቶች (amniocentesis(ከሽርት ውሀ ናሙና  መውሰድ)፣  chorion villus sampling ፣ የፅንስ የደም ናሙና)
✓ከማህፀን ውጭ እርግዝና 

በእነዚህ ክስተቶች ወቅት የፅንስ ደም ወደ እናት ደም ውስጥ በመግባት በእናትየው ደም  ውስጥ ፀረ-እንግዳ(Antibodies) እንዲፈጠር ያደርጋል።

ሾተላይን መከላከል እንዴት ይቻላል?

✓የሾተላይ የመጀመሪያ ደረጃ መከላከል የሚጀምረው RH Negative ሴቶችን ለRH  Positive ደም ከመጋለጣቸው በፊት Anti-D መስጠት ነው፡፡ 

✓በመጀመርያው የእርግዝና ክትትል Indirect coombs test ኔጋቲቭ ሆኖ ከተገኘ:-

1. ከ28-32 ሳምንት ባለው ጊዜ፣

2. ከወሊድ በኋላ የልጁ ደም አይነት RH+ ከሆነ በ72 ሰዓት ውስጥ፣

3. በእርግዝና ወቅት ደም መፍሰስ (ውርጃ፣ ከማህፅን ውጭ እርግዝና እና ሌሎችም ሁኔታዎች እና

4. RH+ ደም ከወሰዱ (በድንገተኛ ጊዜ) Anti-D በመውሰድ ሾተላይን መከላከል ይቻላል።

ሕክምናው
1. የደም ዓይነቷ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) የሆነች እናት ክትትሏ ሆስፒታል ቢሆን ይመረጣል

2. በደሟ ውስጥ ያለውን የንጥረ-ነገር መጠን በመለካትና የጽንሱን የጉዳት መጠን በማየት  ብዙ ሳይጎዳ እንዲወለድ ማድረግ።

3. ጽንሱ በማህጸን ውስጥ እያለ ደም በመለገስ እንዲያድግና እንዲወለድ ማድረግ ይቻላል ።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
7
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዶርም ገብቶ ሁከት የፈጠረው ዝንጀሮ

ዝንጀሮው በዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማደሪያ ውስጥ ገብቶ ምግብ ሲሰርቅ እና ተማሪዎችን ሲያሽበር ታይቷል፡፡

እንዲህ ያለ ገጠመኝ ስንቶቻቹ አላችሁ?

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
😁15
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ጠዋት በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦላቸው በውጤቶቹ ላይ ግምገማ እና ውይይት ተደርጓል።

#PMOEthiopia

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
6🤣4
አንጋፋዋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

አምባሳደር ቆንጂት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን በ1950ዎቹ በለጋ እድሜያቸው ተቀላቅለው ከዴስክ ኦፊሰርነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት አገልግለዋል።

አምባሳደር ቆንጂት ከዮዲት እምሩ በመቀጠል በኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ሴት አምባሳደርም ናቸው።

አምባሳደሯ በኦቶዋ፣ ካይሮ፣ ቴል አቪቭና ቬይና በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን÷ በአፍሪካ ሕብረትና በተባባሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቋሚ መልዕክተኛ በመሆንም ሰርተዋል።

ከሰኔ 2009 እስከ መስከረም 2011 ዓ.ም ደግሞ ኢጋድ በመራው የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ላይ ልዩ አማካሪ ሆነው ማገልገላቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
😢41
ኢራን የተኩስ አቁም ጥያቄውን ውድቅ አደረገች፤ የፕሬዝዳንት ትራምፕ የማስጠንቀቂያ ቀነ-ገደብም ሰዓታት ቀርተውታል

በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ዙሪያ የቀረበውን የተኩስ አቁም የሰላም ጥያቄ ኢራን ውድቅ ማድረጓ ተሰምቷል።

ይህ የቴህራን ውሳኔ የተሰማው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጥቃቱ ከመቀጠሉ በፊት የሰጡት የ10 ቀናት ቀነ-ገደብ ሊጠናቀቅ ጥቂት ሰዓታት በቀሩበት ወቅት ነው።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን የቀረበላትን የሰላም አማራጭ ካልተቀበለች አሜሪካ ጥቃቷን በከፍተኛ ሁኔታ እንደምታጠናክር ገልፀዋል::

ፕሬዝዳንቱ ይህ ጥቃት ለኢራን "ከባዱ ቅዠት" ይሆንባታል ሲሉም ነው በድጋሚ ያስጠነቀቁት።

ምንም እንኳን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ድርድሩ በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑን ቢገልጹም ኢራን ግን የአሜሪካው የሰላም ዕቅድ "አድሏዊና የእስራኤልን ጥቅም ብቻ የሚያስቀድም ነው" በሚል ሳትቀበለው ቀርታለች።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል የንግድና የሰብዓዊ እርዳታ ፍሰቱ እንዳይቋረጥ አዲስ የሥራ ቡድን በማቋቋም ጥረት እያደረገ ይገኛል።

ይሁን እንጂ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ቀነ-ገደብ ዛሬ ማክሰኞ ከእኩለ ሌሊት በኃላ የሚያበቃ በመሆኑ፣ ቀጣዮቹ ሰዓታት ለቀጣናው ሰላም ወሳኝ ሆነው ይጠበቃል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
4
ጥሰት የፈፀመ ድጋሚ አይሾምም‼️
በመንግሥት ተሿሚዎች ላይ ጠንካራ ቁጥጥር የሚያደርግ አዲስ ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጀ‼️

የገንዘብ ሚኒስቴር በመንግሥት ተሿሚዎች ላይ ጠንካራ ቁጥጥር የሚያደርግ አዲስ ረቂቅ መመሪያ ማዘጋጀቱ ተሰማ። በዚህ መመሪያ መሠረት፣ ማንኛውም የመንግሥት ተሿሚ ከመንግሥት የግዥ አፈጻጸምና ከንብረት አስተዳደር ጋር በተያያዘ ጥሰት የፈጸመ መሆኑ ከተረጋገጠ፣ በየትኛውም የመንግሥት ተቋም ውስጥ ዳግም እንዳይመደብ ወይም እንዳይሾም የሚደነግግ መሆኑ ተገልጿል። ይህ እርምጃ በመንግሥት ሀብት ላይ የሚፈጸሙ ብክነቶችን ለመግታትና ተጠያቂነትን ለማስፈን ያለመ መሆኑን የሪፖርተር ዘገባ ያመለክታል።

በረቂቅ መመሪያው ላይ በዋናነት በጥፋተኝነት ከተጠቀሱት ነጥቦች መካከል፦ ዓመታዊ የመንግሥት የግዥ ዕቅድን በወቅቱና በጥራት በኤሌክትሮኒክ ዘዴ አለማቅረብ፣ የንብረት አስተዳደር ሪፖርቶችን በጊዜው አለመላክ፣ እንዲሁም አገልግሎት የጨረሱ ንብረቶችን በወቅቱ አለማስወገድ ይገኙበታል። በተጨማሪም፣ የግዥ መረጃዎችን ለሕዝብ ግልጽ አለማድረግ እንደ ትልቅ ጥሰት ተቆጥሮ ተሿሚዎችን ከቀጣይ የሥራ ድልድል የሚያግድ መሆኑ ተመላክቷል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
2👍1🔥1
የሪል ስቴት ዘርፉ ከሕዝብ አመኔታ በማጣት እየተቀዛቀዘ ነው ተባለ

በኢትዮጵያ የሪል ስቴት ኢንዱስትሪው የሕዝብ አመኔታ በማጣቱ ምክንያት እየተቀዛቀዘ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማኅበር አስታውቋል።

ማኅበሩ ይህን ያስታወቀው፤ ኢትዮጵያ ከሚያዝያ 15 እስከ 18 ቀን 2018 ዓ.ም የመጀመሪያውን የአፍሪካ ሪል ስቴት ማኅበር የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ጉባዔና ‹‹አዲስ - አፍሪካ›› የተሰኘውን የሪል ስቴት ኤግዚቢሽን የምታስተናግድ መሆኑን አስመልክቶ በተሰጠው መግለጫ ላይ ነው።

የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዓለማየሁ ከተማ እንደተናገሩት፤ የሪል ስቴት ኢንዱስትሪው የሕዝብ አመኔታን በማጣቱ እንዳያድግና ወደፊት እንዳይራመድ እየሆነ ይገኛል ብለዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
2
አንጋፋዋ ዲፕሎማት አምባሳደር  ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

አምባሳደር ቆንጂት በአገልግሎት ዘመናቸው፣ በኦታዋ፣ ካይሮ፣ ቴል አቪቭ እና ቪዬና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ኾነው ያገለገሉ ሲኾን፤ በአፍሪካ ኅብረትና በተባባሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቋሚ መልዕክተኛ በመሆን ሠርተዋል።

አምባሳደር ቆንጂት፣ በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክቶሬትንም ለበርካታ ዓመታት በዋና ዳይሬክተርነት መርተዋል። ከዮዲት እምሩ በመቀጠል በኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ሴት አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ቆንጂት፣ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴርን በወጣትነታቸው የተቀላቀሉት በ1950ዎቹ ነበር።

ጠቅላይ ሚሚንስትር ዐቢይ፣ አምባሳደር ቆንጂት ከእርሳቸው በኋላ በርካታ ሴት ዲፕሎማቶች በመስኩ እንዲሠማሩ መንገዱን አስፍተዋል በማለት በአምባሳደሯ ሕልፈት የተሠማቸውን ሐዘን በገለጹበት መልዕክት ላይ ጠቅሠዋል።

@Addis_Magazine
1
ሰበር መረጃ‼️
በኢራን ላይ ትልቁ የአሜሪካ ጥቃት ዛሬ ለሊት 9:47 ላይ እንደሚጀመር ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ።
ከሁሉም የተሻለ እቅድ አለኝ፣ ግን እቅዴ ምን እንደሆነ በግልጽ መናገር አልፈልግም" ያሉ ሲሆን የነገው ጥቃት ከዛሬው ይብሳል ብለዋል። ኢራን ከነገ ጀምሮ ድልድይ፣ የሀይል ማመንጫ... አይኖራቸውም። የድንጋይ ዘመን ሰዎች ይሆናሉ ብለዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
😁94👏1😡1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ ሕልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የኀዘን መልዕክት÷ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲው መስክ ያገለገሉት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ ብለዋል።

አምባሳደር ቆንጂት ከልጅነት እስከ ዕውቀት ኢትዮጵያን በዲፕሎማትነት በማገልገል ከአምባሳደር ዮዲት እምሩ ቀጥለው ሁለተኛዋ ሴት የኢትዮጵያ አምባሳደር መሆናቸውን ገልጸዋል።

ለሕግ፣ ለአሠራር፣ ለፕሮቶኮል እና ለኢትዮጵያ ጥቅሞች በነበራቸው የጸና አቋም እናስታውሳቸዋለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷ ከእርሳቸው በኋላ አያሌ ሴት ዲፕሎማቶች በመስኩ እንዲሠማሩ መንገዱን አስፍተዋል ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ስላሴ እና የአፍሪካ ህብረትም በአምባሳደር ቆንጂት ስነ ጊዮርጊስ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል፡፡

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
6
በአየርላንድ ደሴቶች ላይ ለመኖር ፈቃደኛ የሆነ 90 ሺህ ዶላር ክፍያ እሰጣለው አለች

አዲስ ህይወት በውብ የባህር ዳርቻ ላይ ለመጀመር ለሚያልሙ ሰዎች አየርላንድ አስገራሚ እድል ይዛ ቀርባለች።

"Our Living Islands" የተሰኘውና በመላው ዓለም ከፍተኛ ትኩረት የሳበው ይህ አዲስ መርሃ ግብር፣ በሀገሪቱ ገለልተኛ ደሴቶች ላይ ሄደው ለሚኖሩ ዜጎች እስከ 90 ሺህ የአሜሪካ ዶላር (84 ሺህ ዩሮ) የሚደርስ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ይህ ከፍተኛ የገንዘብ ማበረታቻ የቀረበው የህዝብ ቁጥራቸው በእጅጉ እየቀነሰ የመጡ 30 የሚጠጉ ራቅ ያሉ የደሴት ማህበረሰቦችን እንደገና ለማነቃቃትና ወደ ቀድሞ ህይወታቸው ለመመለስ ታስቦ የተዘጋጀ የ10 ዓመት ስትራቴጂ አካል ነው።

ነገር ግን ይህ ማራኪ አሃዝ በነጻ የሚታደል ገንዘብ አይደለም።

መንግስት ይህንን ድጋፍ የሚሰጠው አዲስ ሰፋሪዎች በነዚህ ደሴቶች ላይ ለዓመታት ተጥለው የቆዩና የፈራረሱ ቤቶችን ገዝተው ሙሉ በሙሉ እንዲያድሱ ለማገዝ ነው።

በአሁኑ ወቅት በነዚህ ደሴቶች ላይ የሚኖሩት ሰዎች ቁጥር ከ3 ሺህ በታች ሲሆን፤ አንዳንዶቹ ደሴቶች ደግሞ በከፍተኛ የባህር ሞገድ ወቅት ከዋናው የሀገሪቱ ክፍል ሙሉ በሙሉ የሚቆረጡ ናቸው።

በመሆኑም እድሉን የሚጠቀሙ ሰዎች የከተማውን ግርግር በባህር ዳርቻው ድምጽ ለመቀየር የሚወስኑት ቁርጠኝነትና የጥገና ስራውን የመወጣት አቅም ሊኖራቸው ይገባል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
12