አዲስ MAGAZINE - መረጃ
31.4K subscribers
6.45K photos
222 videos
3 files
262 links
#አዲስ_Magazine_መረጃ

#መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ

#ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addis_Magazinebot

Addis Ababa , Ethiopia

የአዲስ ነገር መረጃ ቻናል አጋር ሚዲያ
Download Telegram
ኢራን በኩዌት የሚገኙ የአሜሪካ ኃይሎችን መምታቷን ገለጸች።

ሀገሪቱ የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ በ“ጊዜያዊ ተኩስ አቁም” ስምምነት ምክንያት እንዲከፈት ለቀረበላትን ጥያቄ ውድቅ ማድረጓ የቀጠናውን ውጥረት ይበልጥ አክሮታል።

የኢራን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ባሰራጩት የቪዲዮ መግለጫ፣ የኻታም አል-አንቢያ ማዕከላዊ ቃል አቀባይ ኢብራሂም ዞልፋቃሪ፤ የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) በቡቢያን ደሴት የሚገኙ የአሜሪካ ኃይሎችን የሳተላይት መሣሪያዎችና የጦር ትጥቆችን መምታታቸውን ገልጸዋል።

ቃል አቀባዩ አክለውም፣ የአሜሪካ ወታደሮች ቀደም ሲል ይገኝበት የነበረው ‘ካምፕ አሪፍጃን’ በተደጋጋሚ ጥቃት ስለደረሰበት ወደ ደሴቱ ተዛውረው እንደነበር ተናግረዋል።

በሰሜን ምዕራብ ባሕረ ሰላጤ ላይ የምትገኘው ቡቢያን ደሴት በኩዌት የባሕር ዳርቻ ግዛት ውስጥ ትልቁ ደሴት ናት።

ከጥቃቱ በኋላ የኩዌት ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ፣ በሰሜን ኩዌት በሚገኝ የመኖሪያ መንደር ውስጥ “የፍርስራሽ መውደቅ” አደጋ በማጋጠሙ ስድስት ሰዎች መቁሰላቸውን አስታውቋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
5👍2
39 የአፍሪካ ሀገራት የሚሳተፉበት ታላቅ ጉባዔ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

ከፊታችን ረቡዕ መጋቢት 30 ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ 39 የአፍሪካ አባል ሀገራትና ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት የ"አፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም" (ARC-COP 16) ጉባዔ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማሪያም እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በሰብዓዊ ድጋፍ ራሷን ለመቻል የምታደርገው ጥረት፣ በአረንጓዴ ዐሻራና በምግብ ዋስትና ረገድ ያስመዘገበችው ውጤት ለጉባዔው አስተናጋጅነት ተመራጭ አድርጓታል።

ይህ መድረክ "የአፍሪካን ችግር በአፍሪካውያን የመፍታት" ስትራቴጂ አካል ሲሆን፣ ሀገራዊ ተሞክሮዎች ለሌሎች አባል ሀገራት የሚቀርቡበት ወሳኝ መድረክ ይሆናል ብለዋል።

ከውይይቱ ጎን ለጎንም ኢትዮጵያ ያሏትን የቱሪስት መዳረሻዎች የማስተዋወቅ ሥራ በስፋት እንደሚሰራ ተገልጿል።

የጉባዔው ተሳታፊዎች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ የተለያዩ የከተማዋን መስህቦች እንዲጎበኙ ዝግጅት መጠናቀቁ ተናግረዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
10
«ከህሊናዬ እና ከሙያ ስነ-ምግባሬ ጋር መጋጨት አልፈልግም» — አርቲስት ሙሉዓለም ጌታቸው

ታዋቂው የጥበብ ሰው አርቲስት ሙሉዓለም ጌታቸው፣ ከ«ጤግሮስ ትሬዲንግ» ጋር የነበረውን የብራንድ አምባሳደርነት ውል በይፋ ማቋረጡን ገለጸ።

አርቲስቱ ውሉን ለማቋረጥ የተገደደባቸውን ዋና ዋና ምክንያቶች እና ቀጣይ ህጋዊ እርምጃዎቹን በሚመለከት መግለጫ አውጥቷል፡፡

አርቲስቱ ላለፉት 11 ወራት የድርጅቱን ምርቶች እና አገልግሎቶች ሲያስተዋውቅ የቆየ ቢሆንም፤ ድርጅቱ በውሉ ላይ የገባውን ቃል እና ለተጠቃሚው ማህበረሰብ የገባውን ተስፋ በተግባር አለመፈጸሙን በተደጋጋሚ ማረጋገጡን ገልጿል።

"ይህ የድርጅቱ መርሕ አልባ አካሄድ ከእኔ የግል ህሊና፣ ከሙያ ስነ-ምግባር እና ከህዝብ ጥቅም አንፃር በቀጥታ የሚጋጭ ሆኖ አግኝቼዋለሁ" ብሏል፡፡

የአርቲስቱ ውሳኔዎች እና ጥያቄዎች ፡-

1. ድርጅቱ የገባውን ቃል ባለመፈጸሙና የውል ጥሰት በመፈጸሙ፣ ከዛሬ መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የብራንድ አምባሳደርነት ውሉ በይፋ ተቋርጧል።

2 አርቲስቱ ላለፉት ወራት ለሰራቸው የማስታወቂያ ስራዎች እስካሁን ምንም አይነት ክፍያ እንዳልተፈጸመለት በመጥቀስ፣ የድካም ዋጋው በአስቸኳይ እንዲከፈለው ጠይቋል።

3. በድርጅቱ የአሰራር ጉድለት ምክንያት በስሙ እና በዝናው ላይ ለደረሰው ማህበራዊ ኪሳራ ተመጣጣኝ ካሳ የመጠየቅ መብቱ በህግ የተጠበቀ መሆኑን አሳስቧል።

ከመጋቢት 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ፣ ድርጅቱ የአርቲስት ሙሉዓለም ጌታቸውን ምስል፣ ድምፅ ወይም ስም ለማንኛውም አይነት የማስታወቂያ ስራ መጠቀም በጥብቅ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
10🤣6
ድንበርን በእባብ እና አዞ‼️
ህንድ ድንበሯን ለመጠበቅ እባቦችን እና አዞዎችን ልትጠቀም መሆኑ ተሰማ‼️
ሂንዱ የሀገሪቱን የድንበር ደህንነት ሃይል መመሪያን በመጥቀስ እንደዘገበው
በህንድ-ባንግላዴሽ ድንበር በሚገኙ ወንዞች፣ረግረጋማ ቦታዎች እና አስቸጋሪ የሆኑ ቦታዎች ላይ አዞ እና እባብን ለድንበር ጥበቃ ለማሰማራት እቅድ መነደፉን ዘገባው ጠቅሷል።
ምስል-በ AI የበለፀገ

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
🤣13🙉21
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስቸኳይ ማሳሰቢያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ 23 የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ህጋዊ የሥራ ፈቃድ የሌላቸው ወይም በህገ-ወጥ ተግባር የተሰማሩ መሆኑን አሳውቋል።

ህብረተሰቡ ከእነዚህ ድርጅቶች ጋር ከማንኛውም የገንዘብ ዝውውር እንዲቆጠብ ባንኩ በጥብቅ አሳስቧል።

ዝርዝራቸው የተጠቀሱት ተቋማት፦

o አዱሊስ መኒ ትራንስፈር
o አማል ዩኤስኤ
o አማና ኤክስፕረስ
o አማል ኤክስፕረስ
o አቫንቲ
o አዋሽ ዳይሬክት
o ባካኣል መኒ ትራንስፈር
o ባናናፔይ
o ሆልደን ግሎባል
o ጁባ ኤክስፕረስ
o መኒቶስ
o ኦሊምፒክ ፋይናንሻል ግሩፕ (OFG)
o ኩዊክ ፔይ
o ራማድ ፔይ (ካአህ)
o ራስሚ ፔይ
o ሬድሲ (ዩኤስኤ)
o ሽጌይ
o ታአጅ መኒ ትራንስፈር
o ታሳ ፔይ
o ታዋካል መኒ ሰርቪስስ
o ዩኤስዋይር / ዴሮ
o ዋይዝ ትሬዲንግ መኒ ትራንስፈር
o ወርልድ ዳይሬክት ሊንክ ናቸው።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
2
በዓለም አቀፍ ደረጃ ይፈለግ የነበረ አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ ይትባረክ ዳዊት (ክብሮም) ከነግብረ-አበሮቹ በቁጥጥር ስር ዋለ


ከ3 ሺህ በላይ ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ በማዘዋወር፣ ከ100 በላይ ሰዎችን ለሞት የዳረገ እና ከ50 በላይ ሴቶች እንዲደፈሩ ያደረገው ይትባረክ ዳዊት (ክብሮም)ን ከ9 ግብረ-አበሮቹ ጋር በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ አጠናቆ ለዓቃቢ ሕግ መላኩን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

ይህንን ውስብስብ እና ድንበር ተሻጋሪ የወንጀል ምርመራ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል ከሚሠራ “The Regional Operational Centre in support of the Khartoum process (ROCK) ከተባለ ድርጅት ጋር ባደረገው የመረጃ ልውውጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ይፈለግ የነበረው አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ ይትባረክ ዳዊት አለሙን በትግራይ ክልል ሽሬ ከተማ ላይ ፖሊስ በቅንጅት በቁጥጥር ሥር አውሏል።

ተጠርጣሪው በፓስፖርት ስሙ ይትባረክ ዳዊት አለሙ፣ ቤተሰቦቹ በልጅነቱ ያወጡለት ስም ጳውሎስ ዳዊት ወልዳይ፤ ወንጀል መሥራት ሲጀምር የሚታወቅባቸው ስሞች አድሀኖም፣ ሱዳን ሀገር የሚታወቅበት ስም አሕመድ፤ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ እና ኬንያ የሚጠቀምበት ስም ሙኒር ሲሆን ክብሮም ደግሞ በስዊድን እና በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የሚጠቀምባቸው ሀሰተኛ ስሞች መሆናቸውን ፖሊስ በምርመራው አረጋግጧል።

ፖሊስ እነዚህን ስሞች ለምርመራው አጋዥ አድርጎ ያደገ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተጠናከረ ምርመራና ክትትል በማድረግ ከ70 በላይ በሀገር ውስጥና በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ዋና ዋና የሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎችን ከለየ በኋላ ዋናውን ተጠርጣሪ ጨምሮ በአጠቃላይ 10 ህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን ተከታትሎ በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራውን ሲያከናውን ቆይቷል።

ፖሊስ የተያዙትንም ሆነ ያልተያዙትን ተጠርጣሪዎች በወንጀሉ ያፈሩትን ሀብት በጥናት በመለየት ሌሎች ሀብቶቻቸውንና በባንክ የሚገኝ ገንዘብ እንዳይንቀሳቀስ በፍርድ ቤት እንዲታገድ ማድረጉን ገልጿል።

ሕገ-ወጥ አዘዋዋሪ ቡድኑ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ወጣቶችን ከኢትዮጵያ፣ ከሱዳን፣ ከኤርትራ፣ ከጅቡቲ፣ ከኬንያ እና ከሶማሊያ በመመልመል ወደ ሊቢያ በመውሰድ ሊቢያ ውስጥ ባዘጋጁት መጋዝን እንዲታገቱ በማድረግ የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ ከቤተሰቦቻቸው በማስላክ፤ ገንዘብ ያልከፈሉትን በቀን አንድ ጊዜ ብቻ በትንሹ ምግብ እንዲመገቡ በማድረግ፣ በጎማ፣ በዱላ እና በኤሌክትሪክ ገመድ በሰንሰለት እጅ እና እግራቸውን አስረው በመግረፍና በማስገረፍ፣ የውሃ ማሸጊያ ፕላስቲክ አቃጥለው ሰውነታቸው ላይ በማንጠባጠብ ከፍተኛ ስቃይ በማድረስ፣ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በመፈፀም በርካታ ሰዎች ሕይወታቸው እንዲያልፍ፣ የአካል ጉዳት እንዲደርስባቸው፣ ሴቶች እንዲደፈሩ እና ከፍተኛ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት እንዲደርስባቸው ማድረጋቸውን ፖሊስ በምርመራ ማረጋገጥ ችሏል።

ሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎቹ ሊቢያ ውስጥ ተጎጅዎችን አግተው የሚያሰቃዩባቸው አምስት ማከማቻ መጋዘን እንዳላቸው እና በዚህ አደገኛ ወንጀል ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ በህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎቹ ሲንቀሳቀስ እንደነበረ ፖሊስ በሰበሰበው ማስረጃ ማረጋገጥ የቻለ ሲሆን ከ100 በላይ ተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸውን በሀገር ወስጥና በውጭ ሀገር የምስክርነት ቃል የመቀበል ሥራ መሰራቱንም ጨምሮ ገልጿል።

ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሊቢያ፤ ሱዳን፤ ቤልጂየም፤ እንግሊዝ፤ ካናዳ፤ ኖርዌይ፤ ኔዘርላንድ፤ ሉግዘንበርግ እና ስዊዘርላንድ ከሚገኙ አሥራ ስድስት ተጎጅዎች ላይ ቃል መቀበሉንም ፖሊስ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሀገርና በህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለውን ይህንን ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ለመከላከል ዘመኑ ያፈራቸውን የምርመራ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም በተሟላ ፖሊሳዊ ስብዕናና ስነ-ምግባር እየተመራ በላቀ ቁርጠኝነት ተልዕኮውን እየተወጣ ይገኛል።

ተቋሙ ከሀገራት ጋር በፈጠረው የፖሊስ ለፖሊስ ግንኙነትም ዓለም አቀፍ የወንጀል ተፈላጊዎችን ጭምር በቁጥጥር ሥር አውሎ በተለያየ ጊዜ ምርመራ በማጣራት በሀገር ውስጥ በሕግ እንዲጠየቁና የተወሰኑት ደግሞ ከሀገራት ጋር ባለው የወንጀለኛ ልውውጥ ስምምነት መሰረት ተላልፈው እንዲሰጡ እያደረገ ይገኛል።

ይህ ውስብስብ ድንበር ተሸጋሪ የወንጀል ጉዳይ በተሳካ ሁኔታ እንዲጣራ ከፖሊስ ጋር በትብብር ለሰሩት ለፍትህ ሚኒስቴር፣ ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ለROCK እና በጉዳዩ ላይ መረጃ ሲሰጡ ለነበሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ላቅ ያለ ምስጋና እያቀረበ ኅብረተሰቡ ማንኛውንም የወንጀል ድርጊት ሲመለከት በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp)፤ በ991 ነፃ የስልክ መስመር እና ሰው አልባ ፖሊስ ጣቢያ (SPS) በመጠቀም ወይም በአቅራቢያው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት ቀርቦ ጥቆማ በመስጠት የዘወትር ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
10
ስጋ 650 ብር እንዲሸጥ ተወስኗል

ለትንሳዔ በዓል የሸቀጦች አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል፡- የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በከተማዋ የሸቀጦች አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰትና ገበያው እንዲረጋጋ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አስታውቋል።

የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ሀቢባ ሲራጅ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ ከተማ አስተዳደሩ በዓሉን ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን የፍላጎት መጨመር ታሳቢ በማድረግ ካለፈው ወር ጀምሮ ከተለያዩ ክልሎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ምርት የማሰባሰብ ሥራ ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል።

ወቅታዊው ዓለም አቀፍ የነዳጅ ችግር በምርት ስርጭት ላይ ተፅዕኖ እንዳያሳድር የተቀናጀ ዝግጅት መደረጉን  ኃላፊዋ አመላክተዋል፡፡

በዚህም ለኅብረተሰቡ አማራጭ የገበያ ቦታዎችን ለማቅረብ በተሰራው ሥራ በመንግሥት በተዘጋጁ 6 ዋና ዋና የግብርና ምርት መሸጫ ማዕከላት፣ በ246 የሰንበት ገበያዎችና በ2 ሺህ 56 የኅብረት ሥራ ማህበራት ሱቆች በቂ ምርት እንዲገባ መደረጉን ተናግረዋል።

በተለይም መሰረታዊ ሸቀጦችንና እንደ ዘይት ያሉ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለተጠቃሚው ለማድረስ ሰፊ የገበያ ትስስር መፈጠሩ የተገለጸ ሲሆን፤ የሥጋ ምርትን በተመለከተም ኅብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ በህብረት ሥራ ማህበራት በኩል አንድ ኪሎ ሥጋ በ650 ብር እንዲቀርብ መወሰኑ ተመላክቷል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በበዓሉ ወቅት የዋጋ ንረትና የንግድ ማጭበርበር እንዳይኖር ቢሮው በሁሉም የገበያ ማዕከላት፣ ባዛሮችና መደበኛ ሱቆች ላይ ቁጥጥር የሚያደርግ ግብረ ኃይል አሰማርቷል።

በዚህም መሰረት ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ፣ በምርት ላይ ባዕድ ነገር በሚቀላቅሉና በሚዛን በሚያጭበረብሩ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቋል።

ኅብረተሰቡ የምርት እጥረት ሳያጋጥመው በዓሉን እንዲያከብር የሚያስችሉ እነዚህ የገበያ ማረጋጋት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ቢሮው አስታውቋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
5
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የጥላቻ ንግግሮችንና ሀሰተኛ መረጃዎችን ሲያጋራ የነበረው  ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በጅማ ዞን ጮራ ቦተሪ ወረዳ ኮራ ዲማ ቀበሌ ውስጥ የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን በመክፈት የጥላቻ እና ሃሰተኛ የሆኑ ማስረጃዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡ ውስጥ አለመግባባት እንዲፈጠር ያደረገው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱ ተገለፀ። እንደ ወረዳዉ አቃቢ ህግ ገለፃ ተከሳሽ ሸለማ አበራ የተባለ የ22 ዓመት ወጣት ፣ሮብ ገብያ የተባለ ስፍራ ማህበራዊ ሚዲያውን እንደ ሽፋን በመጠቀም የጥላቻ ንግግሮች ሲያሰራጭ መቆየቱን ገልጿል ።

ከታህሳስ 2018 ዓም ጀምሮ አባ ሴና የሚል ሀሰተኛ ገጽ በመክፈት  ድርጊቱን ሲፈጽም ቆይቷል።በዚህም  በሮብ ገብያ  አካባቢ  ዙርያው ማህበረሰብ መካከል ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ ድርጊቶች መከሰታቸው አጋርቷል።ለዘመናት ባህሉን፣ እምነቱን፣ እሴቱንና ልማዱን ጠብቆ ተከባብሮ የሚኖርን ማህበረሰብ  እርስ በእርስ እንዲጠራጠር እና ግጭት ውስጥ እንዲገባ ማድረጉን ፖሊስ በበቂ ማስረጃ አረጋግጧል። ፖሊስ በተከሳሹ ላይ ክትትል በማድረግ በቁጥጥር ስር ካዋለው በኋላ አስፈላጊ ነው ያለውን ማስረጃ በማጠናከር የምርመራ መዝገቡን ለአቃቢ ህግ ልኳል።

አቃቢ ህግ የሀሰተኛ መረጃዎች እና የጥላቻ ንግግሮችን ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ፣የማህበረሰብን መብት በመጣስ  የሀሰት ስም ማጥፋት ድርጊት ክስ መስርቷል።  ክሱን ሲከታተል የቆየው የወረዳዉ ፍርድ ቤት መጋቢት 22 ቀን 2018 በዋለው ቸሎት ተከሳሹን ጥፋተኛ ሆኖ በማለት በሶስት አመት ከስድስት ወር እስራት እና በአንድ ሺህ ብር ገንዘብ እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
6👏1
ትክክለኛ የባህል መዳኒት ይፈልጋሉ??
👆መርጌታ
የባህል ህክምና 0915398834


1🌿ለሀብት ማምጫ
2🌿ለእቁብ (እቁብ እንዲወጣላችሁ የሚያረግ)
3ለመስተፋቅር
4🌿 &መጠብቅ (ከጠላት ከሚላክ ሟርት የሚጠብቅ)
5🌿ለጋኔን
6🌿ለማንኛውም ዓይነት በሽታ መፍትሔ
7🌿ለራእይ (በህልም የሚያሳይ)7
8🌿  ለፀር (ለጠላት)
9🌿ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)
10🌿 ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)
11🌿ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)
12🌿ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)
13🌿 መስተፋቅር
14🌿ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
15🌿ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ
16🌿ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)
17🌿የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ
18🌿ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)
19🌿መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)
20🌿መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)
21🌿ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)
22🌿ለልሳነ_ሰብእ
23🌿ለበረከት
24🌿ለእግረ_መልስ (ጥሎ ለጠፋ ሰው መመለሻ ማምጫ)
25🌿ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)
26🌿ጸሎተ_ዕለታት
27🌿ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ
28🌿ንባብ ስናነብ ቀልጣፋ የሚያረግ
29🌿ለከበሮ
30🌿ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)
31🌿ለሙግት
32🌿ለሰላቢ
33🌿ለስንፈት ወሲብ
34🌿ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)
35🌿ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)
36🌿ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)

በ 0915398834  ይደውሉልን
1