አዲስ MAGAZINE - መረጃ
31.4K subscribers
6.46K photos
223 videos
3 files
262 links
#አዲስ_Magazine_መረጃ

#መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ

#ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addis_Magazinebot

Addis Ababa , Ethiopia

የአዲስ ነገር መረጃ ቻናል አጋር ሚዲያ
Download Telegram
የትራንም አነጋጋሪ መልክት በ Truthsocial

“ማክሰኞ በኢራን "የኃይል ማመንጫ ቀን’ እና ‘የድልድይ ቀን" ይሆናል፣ ሁሉንም ነገር በአንድ ቀን ይከናወናል እናወድመዋለን። ታይቶ የማይታወቅ ጥቃት እናደርሳለን። ያንን የባህር መንገድ ክፈቱ፣ እናንተ እብዶች፤ ካልከፈታችሁ ግን በገሃነም ውስጥ ትኖራላችሁ
ተመልከቱ!!! JUST WATCH!!
አላህ ይመስገን።”

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
🤣7👏32
በሜዲትራንያን ባሕር ከ70 በላይ ስደተኞች ህይወት አለፈ

ከሊብያ ስደተኞችን አሳፍራ ወደ አውሮፓ ለማሻገር ትቀዝፍ የነበረች ጀልባ በሜዲትራንያን ባሕር በመስጠሟ ከ70 በላይ ስደተኞች እስከ አሁን ደብዛቸው አልተገኘም።

አንድ በባሕር ላይ የሚጓዙ ስደተኞች የአደጋ አድን መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንዳለው ጀልባዋ ከሊብያ የባሕር ጠረፍ ጉዞ የጀመረችው ትላንት ከሰዓት በኋላ ነው።

ጀልባዋ ከ100 በላይ ስደተኞችን አሳፍራ የነበረች ሲሆን እስከአሁን ባለው መረጃ 2ቱ ሲሞቱ 32 ደግሞ በሕይወት ተርፈዋል።

በአለፈው ሳምንትም በሜድትራንያን ባህር ላይ በአነስተኛ የፕላስቲክ ጀልባ ሲጓዙ ከነበሩ ስደተኞች መካከል 22ቱ በግሪክ የባሕር ጠረፍ መሞታቸው ይታወሳል።

ስደተኞቹ የሞቱት በረሃብና በውሃ ጥም ምክንያት ነው ተብሏል።

መነሻቸውን ከሊብያ አድርገው የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ወደተለያዩ የአውሮጳ ሃገራት ሲጓዙ የነበሩ ስደተኞቹ በግሪክ የባሕር ጠረፍ አካባቢ ሲደርሱ ጀልባዋ እክል ገጥሟት ለ 6 ቀናት ያህል በባሕር ላይ ሲንሳፈፉ እንደነበረ ታውቋል።

ከስደተኞቹ በሕይወት የተረፉት 2 ብቻ ናቸው ተብሏል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
4😢2
አዲስ MAGAZINE - መረጃ
Photo
በጎንደር ከተማ ቤተክርስቲያን ተሳልመን እንመለስ በማለት ፍቅረኛውን በፌሮ ብረት   ደብድቦ በመግደል የዝርፊያ ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ


በጎንደር ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኘው ማራኪ ክፍለ ከተማ አንዲት ወጣት ላይ አሰቃቂ የግድያና የዝርፊያ ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በ25 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታውቋል ።

ተከሳሽ ብሩክ ወይም ሰለሞን ደጀን የሚባል ሲሆን  ሟች ጥጋብ ሙላትን "የፍቅር ጓደኛዬ ትሆኛለሽ" በሚል አግባብቶ በፍቅር በአብሯት  ከቆየ በኋላ በባንክ ያላትን ገንዘብና የያዘችውን ስልክ ለመውሰድ እቅድ ያወጣ መሆኑን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

ግለሰቡ ወንጀሉን ለመፈጸም እንዲመቸው "ባህር ዳር የታመመ ቤተሰብ ስላለ እንጠይቅ" በሚል  ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከቤቷ ይዟት ይወጣል።ለሁለት ቀናት ያህል ሁኔታዎች እስኪ መቻቹለት ድረስ በተለያዩ ሆቴሎች ሲያዟዙራት ቆይቶ፣ በሀምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 11 ሰዓት ላይ 'ቤተክርስቲያን ተሳልመን እንመለስ' በማለት ሟችን ቀስቅሶ ወደ አቡነ ሃራ ቤተክርስቲያን አቅራቢያ ካለ ጫካ አስገብቶ በፌሮ ብረት ጭንቅላቷን በተደጋጋሚ በመምታት በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቷ እንዲያልፍ አድርጓል።

ተከሳሹ ግድያውን ከፈጸመ በኋላ የሟችን የኢንፊኒክስ  ሞባይል ስልክ እና በባንክ አካውንቷ የነበረን 465,214 ብር ወደ ተለያዩ ሰዎች በማስተላለፍ ወስዷል። በተጨማሪም ገንዘብ ለማግኘትም በሟች ስልክ ለወንድሟ 'ፀበል ቦታ ነኝ፣ ብር ስለቸገረኝ ላኩልኝ' በሚል አጭር መልዕክት በመላክ 86,000 ብር መቀበሉ ፖሊስ አረጋግጧል።የሟች ቤተሰቦች በሁኔታው ተጠራጥረው መስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መሰረት ምርመራ ተጀምሮ ተከሳሹ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የጎንደር ከተማ ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በሰውና በሰነድ ማስረጃ አጠናክሮ ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፍትህ መምሪያ አቅርቧል።በዓቃቤ ህግ የተመሰረተውን ክስ የተመለከተው  የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ25 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።


@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
7😱6😢4
በምዕራብ አርሲ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ

👉አደጋው የደረሰበት ቦታ በተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋ የሚደርስበት ነው


በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ መስቀሉ ሃርጮ ቀበሌ በተለምዶ ሰብስቤ ዋሻ የተባለው ስፍራ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ሕይወት ማለፋን ፖሊስ አስታውቋል።

የምዕራብ አርሲ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የትራፊክ ደህንነት ቁጥጥርና አስተባባሪ ምክትል  ኮማንደር ከማል አማን ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት አደጋው የደረሰው መጋቢት 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት አንድ ሰዓት አካባቢ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2-C56496 አዲስ አበባ የሆነው ላንድ ክሮዘር ተሽከርካሪ አምስት ሰዎችን አሳፍሮ ከባሌ ሮቤ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ፤ ምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ መስቀሉ ሀርቾ ልዩ ስሙ ሰብስቤ ዋሻ ሲደርስ ፍጥነቱን መቆጣጠር ባለመቻሉ ተገልብጧል።

በአደጋውም ወዲያው የሶስት ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ በሁለቱ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርስዋል ሲሉ ገልፀዋል።

የአደጋው መንስኤ ከርብ በሆነ ጠመዝማዛ መንገድ በፍጥነት በመጓዝ ባላንስ በመሳቱ የተፈጠረ መሆኑን የገለፁት አስተባባሪው በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው በአዳባ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

አሽከርካሪዎች መጭውን የትንሳኤ በአል ምክንያት በማድረግ በሚደረግ የትራንስፖርት ጉዞ በተለይ የሕዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪዎች እንደ ሰብስቤ ዋሻ ዓይነቶች ጠመዝማዛ ና ከርቭ የሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ምክትል ኮማንደር ከማል አማን አሳስበዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
1😢1
የገንዘብ ሚኒስቴር በግዥና ንብረት አስተዳደር ላይ ያወጣው ጠንከር ያለ መመሪያ

በሚኒስቴሩ የተዘጋጀው ይህ አዲስ መመሪያ ሁሉንም የመንግስት ሰራተኞች የሚመለከት ሲሆን፤ የመንግሥት ግዥና ንብረትን ያለአግባብ በሚያባክኑ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ተገልጿል።

መመሪያው ጥፋት ብሎ ከለያቸው ተግባራት መካከል፦

▫️ ዓመታዊ የግዥ ዕቅድን በወቅቱና በዲጂታል ዘዴ (በኢንተርኔት) አለማቅረብ ወይም ቀድሞ አለማሳወቅ
▫️ የግዥ ሪፖርቶችን በወቅቱና በጥራት አለማቅረብ
▫️ አገልግሎት የማይሰጡና ያረጁ ንብረቶችን (እንደ ተሽከርካሪና ኤሌክትሮኒክስ ያሉ) በወቅቱ ከግቢ አለማስወገድ
▫️ የግዥ መረጃዎችን ለሕዝብ ግልጽ አለማድረግ
▫️ በኦዲት የተገኙ ግድፈቶችን በወቅቱ አለማስተካከል።

እነዚህን ጥፋቶች በሚፈጽሙ ሰራተኞችና ኃላፊዎች ላይ ባለ አራት ደረጃ ቅጣቶች የሚተላለፉ ሲሆን፤ እነሱም፦ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ ከደመወዝ የሚቀነስ የገንዘብ ቅጣት፣ መስሪያ ቤቱ ክፍያ እንዲያቆም ማድረግ እና በመጨረሻም ከኃላፊነት ማንሳት ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪም፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ጥፋት ምክንያት ከሥራ የተባረረ ወይም የተነሳ ኃላፊ፤ በማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ዳግመኛ እንዳይቀጠር ወይም እንዳይመደብ የሚከለክል ረቂቅ ተዘጋጅቷል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
ኢራን በኩዌት የሚገኙ የአሜሪካ ኃይሎችን መምታቷን ገለጸች።

ሀገሪቱ የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ በ“ጊዜያዊ ተኩስ አቁም” ስምምነት ምክንያት እንዲከፈት ለቀረበላትን ጥያቄ ውድቅ ማድረጓ የቀጠናውን ውጥረት ይበልጥ አክሮታል።

የኢራን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ባሰራጩት የቪዲዮ መግለጫ፣ የኻታም አል-አንቢያ ማዕከላዊ ቃል አቀባይ ኢብራሂም ዞልፋቃሪ፤ የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) በቡቢያን ደሴት የሚገኙ የአሜሪካ ኃይሎችን የሳተላይት መሣሪያዎችና የጦር ትጥቆችን መምታታቸውን ገልጸዋል።

ቃል አቀባዩ አክለውም፣ የአሜሪካ ወታደሮች ቀደም ሲል ይገኝበት የነበረው ‘ካምፕ አሪፍጃን’ በተደጋጋሚ ጥቃት ስለደረሰበት ወደ ደሴቱ ተዛውረው እንደነበር ተናግረዋል።

በሰሜን ምዕራብ ባሕረ ሰላጤ ላይ የምትገኘው ቡቢያን ደሴት በኩዌት የባሕር ዳርቻ ግዛት ውስጥ ትልቁ ደሴት ናት።

ከጥቃቱ በኋላ የኩዌት ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ፣ በሰሜን ኩዌት በሚገኝ የመኖሪያ መንደር ውስጥ “የፍርስራሽ መውደቅ” አደጋ በማጋጠሙ ስድስት ሰዎች መቁሰላቸውን አስታውቋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
5👍2
39 የአፍሪካ ሀገራት የሚሳተፉበት ታላቅ ጉባዔ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

ከፊታችን ረቡዕ መጋቢት 30 ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ 39 የአፍሪካ አባል ሀገራትና ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት የ"አፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም" (ARC-COP 16) ጉባዔ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማሪያም እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በሰብዓዊ ድጋፍ ራሷን ለመቻል የምታደርገው ጥረት፣ በአረንጓዴ ዐሻራና በምግብ ዋስትና ረገድ ያስመዘገበችው ውጤት ለጉባዔው አስተናጋጅነት ተመራጭ አድርጓታል።

ይህ መድረክ "የአፍሪካን ችግር በአፍሪካውያን የመፍታት" ስትራቴጂ አካል ሲሆን፣ ሀገራዊ ተሞክሮዎች ለሌሎች አባል ሀገራት የሚቀርቡበት ወሳኝ መድረክ ይሆናል ብለዋል።

ከውይይቱ ጎን ለጎንም ኢትዮጵያ ያሏትን የቱሪስት መዳረሻዎች የማስተዋወቅ ሥራ በስፋት እንደሚሰራ ተገልጿል።

የጉባዔው ተሳታፊዎች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ የተለያዩ የከተማዋን መስህቦች እንዲጎበኙ ዝግጅት መጠናቀቁ ተናግረዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
10
«ከህሊናዬ እና ከሙያ ስነ-ምግባሬ ጋር መጋጨት አልፈልግም» — አርቲስት ሙሉዓለም ጌታቸው

ታዋቂው የጥበብ ሰው አርቲስት ሙሉዓለም ጌታቸው፣ ከ«ጤግሮስ ትሬዲንግ» ጋር የነበረውን የብራንድ አምባሳደርነት ውል በይፋ ማቋረጡን ገለጸ።

አርቲስቱ ውሉን ለማቋረጥ የተገደደባቸውን ዋና ዋና ምክንያቶች እና ቀጣይ ህጋዊ እርምጃዎቹን በሚመለከት መግለጫ አውጥቷል፡፡

አርቲስቱ ላለፉት 11 ወራት የድርጅቱን ምርቶች እና አገልግሎቶች ሲያስተዋውቅ የቆየ ቢሆንም፤ ድርጅቱ በውሉ ላይ የገባውን ቃል እና ለተጠቃሚው ማህበረሰብ የገባውን ተስፋ በተግባር አለመፈጸሙን በተደጋጋሚ ማረጋገጡን ገልጿል።

"ይህ የድርጅቱ መርሕ አልባ አካሄድ ከእኔ የግል ህሊና፣ ከሙያ ስነ-ምግባር እና ከህዝብ ጥቅም አንፃር በቀጥታ የሚጋጭ ሆኖ አግኝቼዋለሁ" ብሏል፡፡

የአርቲስቱ ውሳኔዎች እና ጥያቄዎች ፡-

1. ድርጅቱ የገባውን ቃል ባለመፈጸሙና የውል ጥሰት በመፈጸሙ፣ ከዛሬ መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የብራንድ አምባሳደርነት ውሉ በይፋ ተቋርጧል።

2 አርቲስቱ ላለፉት ወራት ለሰራቸው የማስታወቂያ ስራዎች እስካሁን ምንም አይነት ክፍያ እንዳልተፈጸመለት በመጥቀስ፣ የድካም ዋጋው በአስቸኳይ እንዲከፈለው ጠይቋል።

3. በድርጅቱ የአሰራር ጉድለት ምክንያት በስሙ እና በዝናው ላይ ለደረሰው ማህበራዊ ኪሳራ ተመጣጣኝ ካሳ የመጠየቅ መብቱ በህግ የተጠበቀ መሆኑን አሳስቧል።

ከመጋቢት 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ፣ ድርጅቱ የአርቲስት ሙሉዓለም ጌታቸውን ምስል፣ ድምፅ ወይም ስም ለማንኛውም አይነት የማስታወቂያ ስራ መጠቀም በጥብቅ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
10🤣6
ድንበርን በእባብ እና አዞ‼️
ህንድ ድንበሯን ለመጠበቅ እባቦችን እና አዞዎችን ልትጠቀም መሆኑ ተሰማ‼️
ሂንዱ የሀገሪቱን የድንበር ደህንነት ሃይል መመሪያን በመጥቀስ እንደዘገበው
በህንድ-ባንግላዴሽ ድንበር በሚገኙ ወንዞች፣ረግረጋማ ቦታዎች እና አስቸጋሪ የሆኑ ቦታዎች ላይ አዞ እና እባብን ለድንበር ጥበቃ ለማሰማራት እቅድ መነደፉን ዘገባው ጠቅሷል።
ምስል-በ AI የበለፀገ

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
🤣13🙉21
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስቸኳይ ማሳሰቢያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ 23 የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ህጋዊ የሥራ ፈቃድ የሌላቸው ወይም በህገ-ወጥ ተግባር የተሰማሩ መሆኑን አሳውቋል።

ህብረተሰቡ ከእነዚህ ድርጅቶች ጋር ከማንኛውም የገንዘብ ዝውውር እንዲቆጠብ ባንኩ በጥብቅ አሳስቧል።

ዝርዝራቸው የተጠቀሱት ተቋማት፦

o አዱሊስ መኒ ትራንስፈር
o አማል ዩኤስኤ
o አማና ኤክስፕረስ
o አማል ኤክስፕረስ
o አቫንቲ
o አዋሽ ዳይሬክት
o ባካኣል መኒ ትራንስፈር
o ባናናፔይ
o ሆልደን ግሎባል
o ጁባ ኤክስፕረስ
o መኒቶስ
o ኦሊምፒክ ፋይናንሻል ግሩፕ (OFG)
o ኩዊክ ፔይ
o ራማድ ፔይ (ካአህ)
o ራስሚ ፔይ
o ሬድሲ (ዩኤስኤ)
o ሽጌይ
o ታአጅ መኒ ትራንስፈር
o ታሳ ፔይ
o ታዋካል መኒ ሰርቪስስ
o ዩኤስዋይር / ዴሮ
o ዋይዝ ትሬዲንግ መኒ ትራንስፈር
o ወርልድ ዳይሬክት ሊንክ ናቸው።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
2