አዲስ MAGAZINE - መረጃ
31.4K subscribers
6.46K photos
223 videos
3 files
262 links
#አዲስ_Magazine_መረጃ

#መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ

#ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addis_Magazinebot

Addis Ababa , Ethiopia

የአዲስ ነገር መረጃ ቻናል አጋር ሚዲያ
Download Telegram
ቱርክ በሶማሊያ የባህር ክልል ታሪካዊውን የነዳጅ ቁፋሮ ልትጀምር ነው

​በቱርክ እና በሶማሊያ መካከል የተደረሰውን ስትራቴጂካዊ ስምምነት ተከትሎ፣ ግዙፍ የነዳጅ ቁፋሮ መርከብ “ቻግሪ ቤይ” በመጪው አርብ መቃዲሾ እንደምትደርስ ተነገረ። ይህ መርከብ በሶማሊያ የባህር ክልል ውስጥ የሚገኘውን የተፈጥሮ ሀብት ለመፈለግ የሚደረገውን የመጀመሪያውን ጥልቅ የባህር ውስጥ ቁፋሮ በይፋ ያስጀምራል።

​የቱርክ የኢነርጂ እና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር አልፓርስላን ባይራክታር እንደገለጹት፣ መርከቧ ከቱርክ መርሲን ወደብ ተነስታ የ45 ቀናት የባህር ጉዞ ካደረገች በኋላ “ኩራድ-1” በተሰኘው የባህር ውስጥ የነዳጅ ጉድጓድ ላይ ስራዋን ትጀምራለች።

​ይህ መጠነ ሰፊ የነዳጅ ፍለጋ ስራ እ.ኤ.አ. በ2024 በሁለቱ ሀገራት መካከል በተፈረመው የሃይድሮካርቦን ስምምነት መሰረት የሚከናወን ሲሆን፣ በሶማሊያ የባህር ክልል ውስጥ በግምት 16,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ ሶስት ዋና ዋና ብሎኮችን ያካትታል ተብሏል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
8👍2
ኢራን በኬዌትና በባህሬን የሀይል መሰረተ ልማቶች ላይ ብርቱ ጥቃት ፈፀመች

ኢራን በኩዌት ላይ በፈጸመችው ጥቃት በአንድ የነዳጅ ማጣያ መሰረተ ልማት ላይ ብርቱ ጉዳት ማድረሷን የኩዌት የፔትሮልየም ኮርፖሬሽን ገልጿል።

መንግስታዊው የነዳጅ ኮርፖሬሽን እንዳለው «ኢራን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም በኩዌት የሃይል መሰረተ ልማት ላይ አሰቃቂ ጥቃት ፈጽማለች።»

ኮርፖሬሽኑ አክሎም «ጥቃቱ በእነዚህ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ቃጠሎ አድርሷል፤ ከፍተኛ ቁሳዊ ጉዳትም አድርሷል» ነው ያለው።

በተመሳሳይ ዜና ኢራን በባሕሬይን 2 የሃይል መሰረተ ልማቶች ላይም ጥቃት ሰንዝራለች።

በጥቃቱ በሁለቱም የነዳጅ ማጣሪያ መሰረተ ልማቶች ከፍተኛ ቃጠሎ ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን በእሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ለማወቅ ተችሏል።

በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ግን ባሕሬን አስታውቃለች።

የዜናዎቹ ምንጭ አዣንስ ፍራንስ ፕረስና የጀርመን ዜና አገልግሎት ናቸው።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
2👍1
ኢትዮጵያ ለትራንዚት መንገደኞች የ7 ቀን ነፃ የቪዛ አገልግሎት ልትፈቅድ ነው

የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስቴር ቱሪዝምን ለማሳደግና የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሻሻል ለትራንዚት መንገደኞች እስከ ሰባት ቀናት የሚቆይ ነፃ የቪዛ አገልግሎት በቅርቡ ተግባራዊ ሊያደርግ ነው ተብሏል።

የቱሪዝም ዘርፍን ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀው የቪዛ ማሻሻያ በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መጽደቁን የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ ገልጸዋል።

ይህ ማሻሻያ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አልፈው የሚሄዱ መንገደኞች ከ24 ሰዓት እስከ ሰባት ቀናት ያለምንም የቪዛ ክፍያ ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ዕድል የሚሰጥ ነው ተብሏል።

ይህም ለመንገደኞች በአውሮፕላን ማረፊያ ረጅም ሰዓታት ከማሳለፍ ይልቅ አዲስ አበባንና ሌሎች የበረራ አማራጭ ያለባቸውን የቱሪስት መዳረሻዎች እንዲጎበኙ የሚያስችል መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል።

የ’ስቶፕ ኦቨር’ ቱሪዝምን ውጤታማ ለማድረግ የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅንጅት ለመሥራት ስምምነት ማድረጋቸውን አቶ ስለሺ ገልጸዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
4👍1
አሜሪካዊውን አብራሪ ለመታደግ
የእስራኤል ኮማንዶዎች ተሳትፈዋል


አሜሪካዊውን የጦር አውሮፕላን አብራሪ ከኢራን ምድር ለማስመለስ በተደረገው እጅግ አደገኛ ኦፕሬሽን ላይ የእስራኤል ልዩ የኮማንዶ ኃይሎች መሳተፋቸው ተሰማ። ለ"ኢራን ኢንተርናሽናል" መረጃ የሰጡ የእስራኤል ምንጮች እንደገለጹት፣ የታወቁት የ"ሻልዳግ" እና "ሳየረት ማትካል" የኮማንዶ ክፍሎች በዘመቻው ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርገዋል። ይህ 36 ሰዓታት የፈጀው ኦፕሬሽን እጅግ አስቸጋሪ የነበረ ሲሆን፣ በሂደቱ አንድ የአሜሪካ ሄሊኮፕተር ጥቃት ቢሰነዘርባትም በሰላም ወደ ጣቢያዋ መመለስ መቻሏ ታውቋል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁም በዘመቻው ስኬት የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኦፕሬሽኑን "አስደናቂ ስኬት" ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ "ነፃ ማህበረሰቦች በልበ ሙሉነትና በቁርጠኝነት ሲንቀሳቀሱ የጨለማንና የሽብርን ኃይሎች ድል ማድረግ እንደሚችሉ ማሳያ ነው" ብለዋል።

ኔታንያሁ አክለውም፣ ይህ ኦፕሬሽን "ማንንም ወደ ኋላ አለመተው" የሚለውን የተቀደሰ ወታደራዊ መርህ በተግባር ያረጋገጠ መሆኑን ገልጸዋል። እስራኤልና አሜሪካ ያላቸውን የጠበቀ ወታደራዊና የደህንነት ትብብር በኢራን እምብርት ላይ ያሳዩበት ይህ ክስተት፣ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ወታደራዊ ሚዛን ዳግም ያመላከተ ሆኗል። አብራሪው በሰላም መመለሱ በአሜሪካ ህዝብ ዘንድ ትልቅ እፎይታን የፈጠረ ሲሆን፣ የሁለቱ ሀገራት ወታደራዊ ጥምረትም ከመቼውም ጊዜ በላይ መጠናከሩ ተነግሯል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
👍64😁3👏1
በመንግስት መስሪያ ቤቶች እየባከነ ያለውን ንብረትና ሀብት ለመታደግ፤ የገንዘብ ሚኒስቴር በግዥና ንብረት አስተዳደር ዘርፍ ላይ በተሰማሩ ሰራተኞችና ኃላፊዎች ላይ ጠንከር ያለ መመሪያ ማውጣቱ ተነገረ።

በሚኒስቴሩ የተዘጋጀው ይህ አዲስ መመሪያ ሁሉንም የመንግስት ሰራተኞች የሚመለከት ሲሆን፤ የመንግሥት ግዥና ንብረትን ያለአግባብ በሚያባክኑ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ተገልጿል። መመሪያው ጥፋት ብሎ ከለያቸው ተግባራት መካከል፦

▫️ ዓመታዊ የግዥ ዕቅድን በወቅቱና በዲጂታል ዘዴ (በኢንተርኔት) አለማቅረብ ወይም ቀድሞ አለማሳወቅ
▫️ የግዥ ሪፖርቶችን በወቅቱና በጥራት አለማቅረብ
▫️ አገልግሎት የማይሰጡና ያረጁ ንብረቶችን (እንደ ተሽከርካሪና ኤሌክትሮኒክስ ያሉ) በወቅቱ ከግቢ አለማስወገድ
▫️ የግዥ መረጃዎችን ለሕዝብ ግልጽ አለማድረግ
▫️ በኦዲት የተገኙ ግድፈቶችን በወቅቱ አለማስተካከል።

እነዚህን ጥፋቶች በሚፈጽሙ ሰራተኞችና ኃላፊዎች ላይ ባለ አራት ደረጃ ቅጣቶች የሚተላለፉ ሲሆን፤ እነሱም፦ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ ከደመወዝ የሚቀነስ የገንዘብ ቅጣት፣ መስሪያ ቤቱ ክፍያ እንዲያቆም ማድረግ እና በመጨረሻም ከኃላፊነት ማንሳት ናቸው።
ከዚህ በተጨማሪም፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ጥፋት ምክንያት ከሥራ የተባረረ ወይም የተነሳ ኃላፊ፤ በማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ዳግመኛ እንዳይቀጠር ወይም እንዳይመደብ የሚከለክል ረቂቅ ተዘጋጅቷል። ረቂቁ በአሁኑ ወቅት በሚመለከታቸው ተቋማት ውይይት እየተደረገበት እንደሚገኝ ታውቋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
11👍6
ትክክለኛ የባህል መዳኒት ይፈልጋሉ??
👆መርጌታ
የባህል ህክምና 0915398834


1🌿ለሀብት ማምጫ
2🌿ለእቁብ (እቁብ እንዲወጣላችሁ የሚያረግ)
3ለመስተፋቅር
4🌿 &መጠብቅ (ከጠላት ከሚላክ ሟርት የሚጠብቅ)
5🌿ለጋኔን
6🌿ለማንኛውም ዓይነት በሽታ መፍትሔ
7🌿ለራእይ (በህልም የሚያሳይ)7
8🌿  ለፀር (ለጠላት)
9🌿ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)
10🌿 ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)
11🌿ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)
12🌿ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)
13🌿 መስተፋቅር
14🌿ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
15🌿ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ
16🌿ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)
17🌿የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ
18🌿ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)
19🌿መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)
20🌿መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)
21🌿ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)
22🌿ለልሳነ_ሰብእ
23🌿ለበረከት
24🌿ለእግረ_መልስ (ጥሎ ለጠፋ ሰው መመለሻ ማምጫ)
25🌿ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)
26🌿ጸሎተ_ዕለታት
27🌿ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ
28🌿ንባብ ስናነብ ቀልጣፋ የሚያረግ
29🌿ለከበሮ
30🌿ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)
31🌿ለሙግት
32🌿ለሰላቢ
33🌿ለስንፈት ወሲብ
34🌿ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)
35🌿ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)
36🌿ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)

በ 0915398834  ይደውሉልን
3
የኢራኑ አፈ ጉባኤ ለዶናልድ
ትራምፕ ብርቱ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባኤ መሐመድ ባገር ጋሊባፍ፣ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መዛታቸውን "ግድ የለሽነት" ሲሉ አጣጥለውታል። ጋሊባፍ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ "የእናንተ ግድ የለሽ እርምጃ የአሜሪካን እያንዳንዱን ቤተሰብ ወደ ከባድ 'ሲኦል' እየጎተተ ነው፤ መላው ቀጠናችንም በእሳት ሊቃጠል ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

አፈ ጉባኤው አክለውም፣ አሜሪካ በጦርነት ወንጀል የምታተርፈው ምንም ነገር እንደሌለ ገልጸው፣ "ስህተት እንዳትሰሩ፤ በጦርነት ወንጀል ምንም አታገኙም" ብለዋል። ትራምፕ በኢራን ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች እንዲጠናከሩ መግለጻቸውን ተከትሎ የተሰጠው ይህ ምላሽ፣ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት ከመቼውም ጊዜ በላይ መስመሩን ስቶ ወደለየለት ጦርነት ሊያመራ እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
💔52🙉2👍1😁1😱1
የትራንም አነጋጋሪ መልክት በ Truthsocial

“ማክሰኞ በኢራን "የኃይል ማመንጫ ቀን’ እና ‘የድልድይ ቀን" ይሆናል፣ ሁሉንም ነገር በአንድ ቀን ይከናወናል እናወድመዋለን። ታይቶ የማይታወቅ ጥቃት እናደርሳለን። ያንን የባህር መንገድ ክፈቱ፣ እናንተ እብዶች፤ ካልከፈታችሁ ግን በገሃነም ውስጥ ትኖራላችሁ
ተመልከቱ!!! JUST WATCH!!
አላህ ይመስገን።”

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
🤣7👏32
በሜዲትራንያን ባሕር ከ70 በላይ ስደተኞች ህይወት አለፈ

ከሊብያ ስደተኞችን አሳፍራ ወደ አውሮፓ ለማሻገር ትቀዝፍ የነበረች ጀልባ በሜዲትራንያን ባሕር በመስጠሟ ከ70 በላይ ስደተኞች እስከ አሁን ደብዛቸው አልተገኘም።

አንድ በባሕር ላይ የሚጓዙ ስደተኞች የአደጋ አድን መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንዳለው ጀልባዋ ከሊብያ የባሕር ጠረፍ ጉዞ የጀመረችው ትላንት ከሰዓት በኋላ ነው።

ጀልባዋ ከ100 በላይ ስደተኞችን አሳፍራ የነበረች ሲሆን እስከአሁን ባለው መረጃ 2ቱ ሲሞቱ 32 ደግሞ በሕይወት ተርፈዋል።

በአለፈው ሳምንትም በሜድትራንያን ባህር ላይ በአነስተኛ የፕላስቲክ ጀልባ ሲጓዙ ከነበሩ ስደተኞች መካከል 22ቱ በግሪክ የባሕር ጠረፍ መሞታቸው ይታወሳል።

ስደተኞቹ የሞቱት በረሃብና በውሃ ጥም ምክንያት ነው ተብሏል።

መነሻቸውን ከሊብያ አድርገው የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ወደተለያዩ የአውሮጳ ሃገራት ሲጓዙ የነበሩ ስደተኞቹ በግሪክ የባሕር ጠረፍ አካባቢ ሲደርሱ ጀልባዋ እክል ገጥሟት ለ 6 ቀናት ያህል በባሕር ላይ ሲንሳፈፉ እንደነበረ ታውቋል።

ከስደተኞቹ በሕይወት የተረፉት 2 ብቻ ናቸው ተብሏል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
4😢2
አዲስ MAGAZINE - መረጃ
Photo
በጎንደር ከተማ ቤተክርስቲያን ተሳልመን እንመለስ በማለት ፍቅረኛውን በፌሮ ብረት   ደብድቦ በመግደል የዝርፊያ ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ


በጎንደር ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኘው ማራኪ ክፍለ ከተማ አንዲት ወጣት ላይ አሰቃቂ የግድያና የዝርፊያ ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በ25 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታውቋል ።

ተከሳሽ ብሩክ ወይም ሰለሞን ደጀን የሚባል ሲሆን  ሟች ጥጋብ ሙላትን "የፍቅር ጓደኛዬ ትሆኛለሽ" በሚል አግባብቶ በፍቅር በአብሯት  ከቆየ በኋላ በባንክ ያላትን ገንዘብና የያዘችውን ስልክ ለመውሰድ እቅድ ያወጣ መሆኑን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

ግለሰቡ ወንጀሉን ለመፈጸም እንዲመቸው "ባህር ዳር የታመመ ቤተሰብ ስላለ እንጠይቅ" በሚል  ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከቤቷ ይዟት ይወጣል።ለሁለት ቀናት ያህል ሁኔታዎች እስኪ መቻቹለት ድረስ በተለያዩ ሆቴሎች ሲያዟዙራት ቆይቶ፣ በሀምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 11 ሰዓት ላይ 'ቤተክርስቲያን ተሳልመን እንመለስ' በማለት ሟችን ቀስቅሶ ወደ አቡነ ሃራ ቤተክርስቲያን አቅራቢያ ካለ ጫካ አስገብቶ በፌሮ ብረት ጭንቅላቷን በተደጋጋሚ በመምታት በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቷ እንዲያልፍ አድርጓል።

ተከሳሹ ግድያውን ከፈጸመ በኋላ የሟችን የኢንፊኒክስ  ሞባይል ስልክ እና በባንክ አካውንቷ የነበረን 465,214 ብር ወደ ተለያዩ ሰዎች በማስተላለፍ ወስዷል። በተጨማሪም ገንዘብ ለማግኘትም በሟች ስልክ ለወንድሟ 'ፀበል ቦታ ነኝ፣ ብር ስለቸገረኝ ላኩልኝ' በሚል አጭር መልዕክት በመላክ 86,000 ብር መቀበሉ ፖሊስ አረጋግጧል።የሟች ቤተሰቦች በሁኔታው ተጠራጥረው መስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መሰረት ምርመራ ተጀምሮ ተከሳሹ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የጎንደር ከተማ ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በሰውና በሰነድ ማስረጃ አጠናክሮ ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፍትህ መምሪያ አቅርቧል።በዓቃቤ ህግ የተመሰረተውን ክስ የተመለከተው  የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ25 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።


@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
7😱6😢4
በምዕራብ አርሲ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ

👉አደጋው የደረሰበት ቦታ በተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋ የሚደርስበት ነው


በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ መስቀሉ ሃርጮ ቀበሌ በተለምዶ ሰብስቤ ዋሻ የተባለው ስፍራ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ሕይወት ማለፋን ፖሊስ አስታውቋል።

የምዕራብ አርሲ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የትራፊክ ደህንነት ቁጥጥርና አስተባባሪ ምክትል  ኮማንደር ከማል አማን ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት አደጋው የደረሰው መጋቢት 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት አንድ ሰዓት አካባቢ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2-C56496 አዲስ አበባ የሆነው ላንድ ክሮዘር ተሽከርካሪ አምስት ሰዎችን አሳፍሮ ከባሌ ሮቤ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ፤ ምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ መስቀሉ ሀርቾ ልዩ ስሙ ሰብስቤ ዋሻ ሲደርስ ፍጥነቱን መቆጣጠር ባለመቻሉ ተገልብጧል።

በአደጋውም ወዲያው የሶስት ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ በሁለቱ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርስዋል ሲሉ ገልፀዋል።

የአደጋው መንስኤ ከርብ በሆነ ጠመዝማዛ መንገድ በፍጥነት በመጓዝ ባላንስ በመሳቱ የተፈጠረ መሆኑን የገለፁት አስተባባሪው በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው በአዳባ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

አሽከርካሪዎች መጭውን የትንሳኤ በአል ምክንያት በማድረግ በሚደረግ የትራንስፖርት ጉዞ በተለይ የሕዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪዎች እንደ ሰብስቤ ዋሻ ዓይነቶች ጠመዝማዛ ና ከርቭ የሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ምክትል ኮማንደር ከማል አማን አሳስበዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
1😢1
የገንዘብ ሚኒስቴር በግዥና ንብረት አስተዳደር ላይ ያወጣው ጠንከር ያለ መመሪያ

በሚኒስቴሩ የተዘጋጀው ይህ አዲስ መመሪያ ሁሉንም የመንግስት ሰራተኞች የሚመለከት ሲሆን፤ የመንግሥት ግዥና ንብረትን ያለአግባብ በሚያባክኑ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ተገልጿል።

መመሪያው ጥፋት ብሎ ከለያቸው ተግባራት መካከል፦

▫️ ዓመታዊ የግዥ ዕቅድን በወቅቱና በዲጂታል ዘዴ (በኢንተርኔት) አለማቅረብ ወይም ቀድሞ አለማሳወቅ
▫️ የግዥ ሪፖርቶችን በወቅቱና በጥራት አለማቅረብ
▫️ አገልግሎት የማይሰጡና ያረጁ ንብረቶችን (እንደ ተሽከርካሪና ኤሌክትሮኒክስ ያሉ) በወቅቱ ከግቢ አለማስወገድ
▫️ የግዥ መረጃዎችን ለሕዝብ ግልጽ አለማድረግ
▫️ በኦዲት የተገኙ ግድፈቶችን በወቅቱ አለማስተካከል።

እነዚህን ጥፋቶች በሚፈጽሙ ሰራተኞችና ኃላፊዎች ላይ ባለ አራት ደረጃ ቅጣቶች የሚተላለፉ ሲሆን፤ እነሱም፦ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ ከደመወዝ የሚቀነስ የገንዘብ ቅጣት፣ መስሪያ ቤቱ ክፍያ እንዲያቆም ማድረግ እና በመጨረሻም ከኃላፊነት ማንሳት ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪም፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ጥፋት ምክንያት ከሥራ የተባረረ ወይም የተነሳ ኃላፊ፤ በማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ዳግመኛ እንዳይቀጠር ወይም እንዳይመደብ የሚከለክል ረቂቅ ተዘጋጅቷል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
ኢራን በኩዌት የሚገኙ የአሜሪካ ኃይሎችን መምታቷን ገለጸች።

ሀገሪቱ የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ በ“ጊዜያዊ ተኩስ አቁም” ስምምነት ምክንያት እንዲከፈት ለቀረበላትን ጥያቄ ውድቅ ማድረጓ የቀጠናውን ውጥረት ይበልጥ አክሮታል።

የኢራን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ባሰራጩት የቪዲዮ መግለጫ፣ የኻታም አል-አንቢያ ማዕከላዊ ቃል አቀባይ ኢብራሂም ዞልፋቃሪ፤ የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) በቡቢያን ደሴት የሚገኙ የአሜሪካ ኃይሎችን የሳተላይት መሣሪያዎችና የጦር ትጥቆችን መምታታቸውን ገልጸዋል።

ቃል አቀባዩ አክለውም፣ የአሜሪካ ወታደሮች ቀደም ሲል ይገኝበት የነበረው ‘ካምፕ አሪፍጃን’ በተደጋጋሚ ጥቃት ስለደረሰበት ወደ ደሴቱ ተዛውረው እንደነበር ተናግረዋል።

በሰሜን ምዕራብ ባሕረ ሰላጤ ላይ የምትገኘው ቡቢያን ደሴት በኩዌት የባሕር ዳርቻ ግዛት ውስጥ ትልቁ ደሴት ናት።

ከጥቃቱ በኋላ የኩዌት ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ፣ በሰሜን ኩዌት በሚገኝ የመኖሪያ መንደር ውስጥ “የፍርስራሽ መውደቅ” አደጋ በማጋጠሙ ስድስት ሰዎች መቁሰላቸውን አስታውቋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
5👍2
39 የአፍሪካ ሀገራት የሚሳተፉበት ታላቅ ጉባዔ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

ከፊታችን ረቡዕ መጋቢት 30 ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ 39 የአፍሪካ አባል ሀገራትና ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት የ"አፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም" (ARC-COP 16) ጉባዔ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማሪያም እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በሰብዓዊ ድጋፍ ራሷን ለመቻል የምታደርገው ጥረት፣ በአረንጓዴ ዐሻራና በምግብ ዋስትና ረገድ ያስመዘገበችው ውጤት ለጉባዔው አስተናጋጅነት ተመራጭ አድርጓታል።

ይህ መድረክ "የአፍሪካን ችግር በአፍሪካውያን የመፍታት" ስትራቴጂ አካል ሲሆን፣ ሀገራዊ ተሞክሮዎች ለሌሎች አባል ሀገራት የሚቀርቡበት ወሳኝ መድረክ ይሆናል ብለዋል።

ከውይይቱ ጎን ለጎንም ኢትዮጵያ ያሏትን የቱሪስት መዳረሻዎች የማስተዋወቅ ሥራ በስፋት እንደሚሰራ ተገልጿል።

የጉባዔው ተሳታፊዎች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ የተለያዩ የከተማዋን መስህቦች እንዲጎበኙ ዝግጅት መጠናቀቁ ተናግረዋል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
10
«ከህሊናዬ እና ከሙያ ስነ-ምግባሬ ጋር መጋጨት አልፈልግም» — አርቲስት ሙሉዓለም ጌታቸው

ታዋቂው የጥበብ ሰው አርቲስት ሙሉዓለም ጌታቸው፣ ከ«ጤግሮስ ትሬዲንግ» ጋር የነበረውን የብራንድ አምባሳደርነት ውል በይፋ ማቋረጡን ገለጸ።

አርቲስቱ ውሉን ለማቋረጥ የተገደደባቸውን ዋና ዋና ምክንያቶች እና ቀጣይ ህጋዊ እርምጃዎቹን በሚመለከት መግለጫ አውጥቷል፡፡

አርቲስቱ ላለፉት 11 ወራት የድርጅቱን ምርቶች እና አገልግሎቶች ሲያስተዋውቅ የቆየ ቢሆንም፤ ድርጅቱ በውሉ ላይ የገባውን ቃል እና ለተጠቃሚው ማህበረሰብ የገባውን ተስፋ በተግባር አለመፈጸሙን በተደጋጋሚ ማረጋገጡን ገልጿል።

"ይህ የድርጅቱ መርሕ አልባ አካሄድ ከእኔ የግል ህሊና፣ ከሙያ ስነ-ምግባር እና ከህዝብ ጥቅም አንፃር በቀጥታ የሚጋጭ ሆኖ አግኝቼዋለሁ" ብሏል፡፡

የአርቲስቱ ውሳኔዎች እና ጥያቄዎች ፡-

1. ድርጅቱ የገባውን ቃል ባለመፈጸሙና የውል ጥሰት በመፈጸሙ፣ ከዛሬ መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የብራንድ አምባሳደርነት ውሉ በይፋ ተቋርጧል።

2 አርቲስቱ ላለፉት ወራት ለሰራቸው የማስታወቂያ ስራዎች እስካሁን ምንም አይነት ክፍያ እንዳልተፈጸመለት በመጥቀስ፣ የድካም ዋጋው በአስቸኳይ እንዲከፈለው ጠይቋል።

3. በድርጅቱ የአሰራር ጉድለት ምክንያት በስሙ እና በዝናው ላይ ለደረሰው ማህበራዊ ኪሳራ ተመጣጣኝ ካሳ የመጠየቅ መብቱ በህግ የተጠበቀ መሆኑን አሳስቧል።

ከመጋቢት 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ፣ ድርጅቱ የአርቲስት ሙሉዓለም ጌታቸውን ምስል፣ ድምፅ ወይም ስም ለማንኛውም አይነት የማስታወቂያ ስራ መጠቀም በጥብቅ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
10🤣6
ድንበርን በእባብ እና አዞ‼️
ህንድ ድንበሯን ለመጠበቅ እባቦችን እና አዞዎችን ልትጠቀም መሆኑ ተሰማ‼️
ሂንዱ የሀገሪቱን የድንበር ደህንነት ሃይል መመሪያን በመጥቀስ እንደዘገበው
በህንድ-ባንግላዴሽ ድንበር በሚገኙ ወንዞች፣ረግረጋማ ቦታዎች እና አስቸጋሪ የሆኑ ቦታዎች ላይ አዞ እና እባብን ለድንበር ጥበቃ ለማሰማራት እቅድ መነደፉን ዘገባው ጠቅሷል።
ምስል-በ AI የበለፀገ

@Addis_Magazine
@Addis_Magazine
🤣13🙉21