አዲስ MAGAZINE - መረጃ
31.4K subscribers
6.46K photos
223 videos
3 files
262 links
#አዲስ_Magazine_መረጃ

#መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ

#ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addis_Magazinebot

Addis Ababa , Ethiopia

የአዲስ ነገር መረጃ ቻናል አጋር ሚዲያ
Download Telegram
ከተተመነው ግራም በታች ሲሸጡ የተገኙ ከ70 በላይ ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ ።

በንግድ ቢሮ ከተተመነው ግራም በታች ሲሸጡ የተገኙ ከ70 በላይ ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ያስታወቀ ሲሆን፤ በቀጣይም በሁሉም ዳቦ ቤቶች ላይ የሚያደርገውን ቁጥጥር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከ70 ከግራም በታች የሆነ የዳቦ ምርት ለሸማች እንዳያቀርቡ የቁጥጥር ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ፤ የቢሮ የንግድ ቁጥጥር ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር ቅድስት ስጦታው ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ምክትል ዳይሬክተሯ አክለውም ቢሮው በዳቦ ምርት ላይ የዋጋ ተመን እንደማያወጣ የገለጹ ሲሆን፤ "ሆኖም በከተማዋ በሚገኙ ዳቦ ቤቶች ላይ በቢሮው ከተተመነው ግራም በታች የሆነ ምርት ለገበያ እንዳይቀርብ እየተሰራ ይገኛል" ብለዋል፡፡

በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ በሚገኙ ዳቦ ቤቶች ላይ ከተቀመጠው ግራም መጠን በታች የሆነ ምርት እንዳይቀርብ ከዳቦ ቤቶች ናሙና በመውሰድ የተተመነውን መጠን የልኬት ሥራ የሚቆጣጠሩበት አሰራር ስለመኖሩ ምክትል ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡

በንግድ ቢሮው በስድስት ወራት ውስጥ በተከናወነ የቁጥጥር ሥራም፤ ከ70 በላይ ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል፡፡

ቢሮ በክትትል ወቅት በሚያገኛቸው ከግራም በታች የሆነ መጠን ያለው ምርት በሚሸጡ ዳቦ ቤቶች ላይ ከጽሁፍ እስከ ንግድ ፈቃድ የመሰረዝ እርምጃ የሚወስድበት አሰራር ስለመኖሩ ኃላፊዋ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

via:አሐዱ ራዲዮ

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍1🤔1
በአዲስ አበባ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ ነው

ምርጫችን ሠላም ነው" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች የድጋፍ ሠልፍ እያካሄዱ ነው።

በመዲናዋ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ለሠላም ያላቸውን ድጋፍ እና ቁርጠኝነት የሚገልፅ ሰልፍ ነው እያካሄዱ የሚገኙት።

ነዋሪዎቹ ለትግራይ ልማት እንጂ ዳግም ጦርነት አያሥፈልጋትም፣ በክልሉ ያለውን ሠላማዊ እንቅሥቃሴ እና መሠል እንቅሥቃሴዎች በማሥተጓጎል የሚገኝ ጥቅም የለም የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችን እያስተላለፉ ይገኛሉ።

ለትግራይ እና ነዋሪዎቿ ሠላም በምንም የማይተካ መሆኑንም ሠልፈኞቹ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ፖለቲከኞች ችግሮቻቸውን በመነጋገር እንዲፈቱ ለሠላም ጠንቅ ከመሆን እንዲታቀቡም አስገንዝ

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍2
በአማራ ክልል አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች ናቸዉ መባሉን ሰምናል።

በክልሉ 86.5 በመቶ ትምህርት ቤቶች ናቸው ከደረጃ በታች መሆናቸዉ የተገለፀው። የተካሄዱና እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶች ለትምህርት ተቋማት መጎዳት ምክንያት ናቸዉም ተብሏል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
1👍1
ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት ይሰጣል‼️

በወልዲያ-ቆቦ መንገድ የሚገኘው የአሚድ ወንዝ ብረት ድልድይ መሰበሩን ተከትሎ የትራንስፖርት አገልግሎት ችግር እንዳይፈጠር ጊዜያዊ ተለዋጭ መተላለፊያ መንገድ የተሰራ ሲሆን ከዛሬ ሀሙስ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት እንደሚችል ተሰምቷል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍2
አዲስ MAGAZINE - መረጃ
Photo
"የትግራይ ህዝብ ወደ መደበኛ ህገመንግስታዊ ስርዓት መመለስ የህወሓት ቀዳሚ መርህ ነው":-ህወሓት‼️

በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (#ህወሓት) ቡድን የትግራይ ህዝብ እና የትግራይ ልሂቃን ቀዳሚ ምርጫው ሰላም ነው ሲል ትላንት ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ጠ/ሚኒስት አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ህወሓት የጠ/ሚኒስትሩን ጥሪ ተከትሎ ትላንት ጥር 28 ቀን መግለጫ ያወጣ ሲሆን በመግለጫውም የትግራይ ህዝብ ቀዳሚ ምርጫ ሰላም ነው ብሏል፤ የትግራይ ህዝብን የሰላም ምኞት አውን ለማድረግ ሁሉመ ገንቢ ሚና ይጫወት ሲል ጠይቋል፤ ከማንኛውም አካል ጋር በሰላም ዙሪያ ለመስራት ዝግጁ ነኝ ሲል አስታውቋል።

ህወሓት በመግለጫው ባለፉት መቶ አመታት የትግራይ ህዝብ ያደረጋቸው ጦርነቶች “ህልውናውን ለማረጋገጥ እና ለጭቆና አጅ አልሰጥ በማለት ነው” ሲል በመግለጽ “የትግራይ ህዝብ ያደረጋቸው ተጋድሎዎች ያኮሩታል እንጂ አያስቆጩትም” ብሏል።

የህዝቡ የሰላም ምኞት ዕውን እንዲሆን የሚመለከታቸው ሁሉ ገንቢ ግንኙነት ላይ የተመሰረተ ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን ብሏል። አሁንም ቢሆን እንደተለመደው የትግራይ ህዝብ ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት በተለያዩ መንገዶች እያስመሰከረ ነው። ለሰላም ካለው ፍላጎት የተነሳ የዘር ማጥፋት ጦርነትን ለማስቆም የፕሪቶሪያን ስምምነት ተቀብሎ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን ጥሪ ያቀርባል ብሏል። ምንም እንኳን የፕሪቶሪያ ስምምነት የትግራይን ህዝብ ሙሉ ደህንነት የማያረጋግጥ ቢሆንም፣ እያንዳንዱ የትግራይ ህዝብ ስምምነቱን የማስፈጸም ተግባር ሰላምና መተማመንን እየፈጠረ ተጠቃሚ እንዲሆን አላስፈላጊ ዋጋ እየከፈሉ ቢሆንም ነገር ግን ታሪክ እራሱን ደግሟል እና የፕሪቶሪያ ስምምነት ተግባራዊ መሆን አልቻለም። የትግራይ ህዝብ ዋና ዋና ጥያቄዎች እና በፕሪቶሪያ ስምምነት ላይ የተቀመጡት ጉዳዮች አፈፃፀማቸው በመዘግየቱ ዋጋ እየከፈለ ነው። ህወሀት የትግራይን ህዝብ ጥቅም የሚያረጋግጥ የሰላም ጥሪ ሁሌም ይመኝ ነበር። ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የተሻለ ደረጃ ላይ መድረስ እና የትግራይን ህዝብ ተጠቃሚ ማድረግ የትግሉ ዋና ምሰሶ ነው። ሰላማችንን እና ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ እየሰራን ነው። እያንዳንዱ የሰላም ጥሪ እንዳይስተጓጎል በጥንቃቄ እንሰራለን።

የትግራይ ህዝብ በትግላቸው ያመጣው የፕሪቶሪያ ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን እንሰራለን። ስለሆነም ከወራሪ ሃይሎች ያልተላቀቁ ዜጎች ተፈተውና የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቤታቸው ይመለሱ። የትግራይ መሬት ሉዓላዊነት ይመለስ; ለትግራይ ሰላም ቀጣይነት በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙ አካላት ተጠያቂ መሆን አለባቸው።

ትግራይ ወደ መደበኛ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት መመለስ የትግራይ ሕዝብ ፍላጎትና የህወሓት ዋነኛ መርህ ነው። ትላንትም ዛሬም ነገም ከሁሉም የሰላም ሃይሎች ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናችንን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን"ሲል ገልጿል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍3
ሜክሲኮ 10 ሺህ ወታደሮቿን በአሜሪካ አዋሳኝ ድንበር ላይ አሰማራች

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የታሪፍ ዛቻን ተከትሎ ሜክሲኮ 10 ሺህ ወታደሮችን በዩናይትድ ስቴትስ አዋሳኝ ድንበር ላይ ማሰማራቷን አስታወቀች፡፡

የሜክሲኮ ፕሬዚዳንት ክላውዲያ ሼንቦም ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተክትሎ የሀገሪቱ ብሄራዊ ጦር አባላት ከአሜሪካዋ ቴክሳስ ግዛት ጋር በሚዋሰኑት ሱዳድ ጁዋሬዝና ኢል ፓሶ በተሰኙ አካባቢዎች መስፈራቸው ተገልጿል፡፡

ዛሬ ጠዋት ላይም ጭንበል የለበሱና የታጠቁ ከ1 ሺህ 650 በላይ የሜክሲኮ ብሄራዊ ጦር አባላት በድንብር አካባቢ በመስፈር በአካባቢው ቅኝት ሲያደርጉ መታየታቸው ነው የተገለጸው፡፡

ሜክሲኮ ወታደሮቿን ለማስፈር የወሰነችው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሜክሲኮ ምርቶች ላይ ከበደ ያለ ታሪፍ እንደሚጥሉ መናገራቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

ወታደሮቹ በዋናነት በሜክሲኮ እና አሜሪካ ድንበር የሚደረጉ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን የሚቆጣጠሩ ሲሆን÷ በተጓዳኝ ከአሜሪካ መንግስት የሚሰነዘርባቸውን ማንኛውም ጫና ለመመከት እንደሚሰሩ መጠቀሱን ቲ አር ቲ ዘግቧል፡፡
@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወ/ሮ መድህን የተባሉ የመቀሌ ከተማ ነዋሪ  በ75 ዓመታቸው መውለዳቸውን የመቀሌ ምንጮቻችን ገልፀዋል።

በአብዝሃኛው ሴቶች ከ45 ዓመት እድሜያቸው በኋላ ልጅ የመውለድ እድላቸው ያነሰ ነው።

ከዚህ ቀደም በ73 ዓመቷ ሕንዳዊ ተይዞ የነበረው ክብረ ወሰንም በእጃቸው ማስገባት ችለዋል::

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይህ ሁሉ ሠልፍ ጥቁር አምበሳ ሆስፒታል ነው።

ወደ ውጭ የሚሄዱ ዜጎች የወባ ክትባት ለማግኘት የሚደረግ ትንቅንቅ ነው ከሌሊት እስከ ምሽት የሚቀጥል እንደሆነ ባለጉዳዮቹ ጠቁመዋል።

ወደ ውስጥ ለመግባት ከ1000-1500 በተናጠል በር ላይ እናስተባብራለን ለሚሉና ለጥበቃዎች እንደሚያስከፍሏቸው ተናግረዋል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍2
በአዲስ አበባ ከተማ እየተገነባ ካለ ህንጻ ላይ አንድ የግንባታ ባለሙያ ወድቆ ህይወቱ አለፈ

ሀሙስ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ረፋድ ላይ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፊጋ መብራት ኃይል እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ዕድሜዉ 27 ዓመት የተገመተ የኮንስትራክሽን ባለሙያ በግለሰብ እየተገነባ ካለ ህንጻ ላይ ወድቆ ህይወቱ ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ህይወቱ ያለፈዉ ወጣት በስራ ላይ እያለ በነበረበት ጊዜ ለአሳንሰር  መገጣጠሚያ በተተዉ ክፍት ቦታ ላይ ወደታች ወድቆ ህይወቱ ማለፉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በማናቸዉም የህንጻና መሰል ግንባታዎች አደጋዎችን ለመከላከል አስፈላጊዉን የደህንነት መርሆዎችን መከተል የሚገባ ሲሆን ለዚሁም ከባለሙያዎች ባሻገር አሰሪዎች ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው ኮሚሽኑ አሳስቧል።

በትግስት ላቀው
@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
😱3
ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ትናንት ምሽት በትዝታው ንጉሥ ማህሙድ አህመድ መኖሪያ ቤት ከባለቤቱና ከወዳጆቹ ጋር በመገኘት፣ በወርቅ የተጻፈ የማህሙድ የስሙ የመጀምሪያ ፌደል (M) ያለበትና መተጣጠፊያዎቹ ላይ በወርቅ ቀለበቶች የተጌጠ ከዘራ እንዳበረከተለት ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።

ማህሙድ አህመድ ቤት የራት ግብዣ እንደተደረገ የገለጹት ምንጮቻችን በዚህ ምሽት ላይ  ለረዥም ሰዓታት ያለፉ ታሪኮችና ገጠመኞች እየተነሱ ተጨዋውተዋል ብለዋል።

"ቴዲ አፍሮ ለታላላቆቹ የሚገባቸውን ክብር የሚሰጥ ትልቅ አርቲስት ነው፣ በዚህም ታላላቆቹም በጣም ይወዱታል፣ ያከብሩታል"  ያሉት ምንጩ፣ ማህሙድ አህመድም በመኖሪያ ቤቱ ይህን ገልጾለታል ብለዋል። ቴዲም ለትዝታው ንጉሥ ረዥም ዕድሜና ጤናውን ተመኝቶ ጥሩ ምሽት አሳልፈዋል በማለት ገልጸውልናል።

በዚህ ምሽት ላይ ቴዲ አፍሮ፣ ባለቤቱ አምለሰት ሙጬ፣ ዝነኛዋ ድምጻዊት ኩኩ ሰብስቤን ጨምሮ የቴዲ ሥራ አስኪያጅና ሌሎችም ተገኝተዋል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍4