አዲስ MAGAZINE - መረጃ
31.4K subscribers
6.46K photos
223 videos
3 files
262 links
#አዲስ_Magazine_መረጃ

#መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ

#ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addis_Magazinebot

Addis Ababa , Ethiopia

የአዲስ ነገር መረጃ ቻናል አጋር ሚዲያ
Download Telegram
ከቀናት በፊት አዳዲስ አመራሮችን የመረጠው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፤ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው ያለውን “የእርስ በእርስ ጦርነት” ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ መወሰኑን ገለጸ። ፓርቲው “የተበላሸ” ሲል የጠራውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስርዓት ለማረምም “ከምንጊዜውም በላይ እታገላለሁ” ብሏል።

መኢአድ ይህን ያለው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በአዲስ አበባ ያካሄደውን 10ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በተመለከተ በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ ነው። ፓርቲው በዚሁ ጉባኤው፤ የድርጅቱን ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት ጨምሮ የስራ አስፈጻሚ፣ የማዕከላዊ ምክር ቤት እንዲሁም የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚቴ አባላትን መርጧል።

ተመራጮቹ ፓርቲውን “ለቀጣዩ ሶስት ዓመታት ሊመሩ የሚችሉ” እና ድርጅቱን “ወደተሻለ ደረጃ ያደርሳሉ” በሚል በጠቅላላ ጉባኤው ተሳታፊዎች የታመነባቸው እንደሆኑም መኢአድ አስታውቋል። ጠቅላላ ጉባኤው “አዳዲስ እና ወጣት የሴት አመራሮችን ወደፊት እንዲመጡ አድርጓል” ሲልም ፓርቲው በመግለጫው አክሏል።

via:Ethiopia Insider

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍1
ጊዮን ሆቴል የሚገኘው ግሮቭ ጋርደን ለወንዝ ዳር ልማት መፈረሱን ባለቤቱ አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ገልጿል።

via:Fast Mereja

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍1😢1
በታገዱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ “ተጨማሪ ምርመራ” እየተከናወነ መሆኑን ተቆጣጣሪ ባለስልጣኑ አስታወቀ

የእግድ እርምጃ በተወሰደባቸው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ ተጨማሪ “የማጣራት” እና “የምርመራ” ስራ እያከናወነ መሆኑን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ በዚህ ምርምራ ግኝቱ ላይ ተመስርቶ፤ እግዱ “በመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንዲነሳ” ሊያደርግ አሊያም ድርጅቶቹ “እንዲፈርሱ” ወይም “እንዲሰረዙ” ለመስሪያ ቤቱ ቦርድ የውሳኔ ሃሳብ ሊያቀርብ እንደሚችልም ገልጿል።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተመዘገቡበት ዓላማ መሰረት ስራቸውን ማከናወናቸውን የመከታተል እና የመቆጣጠር ኃላፊነት በአዋጅ የተሰጠው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፤ ባለፈው መንፈቅ ዓመት ብቻ ሰባት ድርጅቶች ላይ የእግድ ውሳኔ አስተላልፏል። ባለስልጣኑ በዚሁ ጊዜ ውስጥ ለ10 ድርጅቶች ማስጠንቀቂያ መስጠቱም፤ ዛሬ ረቡዕ በፓርላማ በተካሄደ የቋሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ይፋ ተደርጓል።

በቋሚ ኮሚቴው ስብሰባ የጥያቄ እና ምላሽ ወቅት የመናገር ዕድል የተሰጣቸው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ፤ መስሪያ ቤታቸው በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ የሚያደርገው “ክትትል፣ ቁጥጥር እና ምርመራ” “ተጠናክሮ ቀጥሏል” ብለዋል።

“የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለተቋቋሙለት ዓላማ፣ በዚያ መስመር ላይ እንዲሰሩ፤ ህግን እና ህግን ብቻ አክብረው እንዲሰሩ ያላሰለሰ ጥረት እያደረግን ነው” ሲሉም አቶ ሳምሶን ለቋሚ ኮሚቴው አባላት ተናግረዋል። እርሳቸው የሚመሩት መስሪያ ቤት፤ “ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ ተንቀሳቅሰዋል” ያላቸውን 4 የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ባለፈው ታህሳስ ወር አጋማሽ ማገዱ ይታወሳል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍7
የትኛውም አይነት ሀሳብ አስተያየት እንዲሁም መረጃ ሲኖራችሁ በቀጥታ ከታች ባለው bot ልታሳውቁን ትችላላችሁ🙏

📨 @zena_ethiopia_bot
👍7
ለኤች አ ይቪ ሕክምና የሚሰጥ ርዳታ እንደማይቋረጥ አሜሪካ አስታወቀች

አሜሪካ ለ90 ቀናት የውጪ ርዳታ እንደሚቋረጥ ብታስታወቅም፣ ‘የፕሬዝደንቱ የኤድስ አስቸኳይ ጊዜ ርዳታ’ ወይም ‘ፔፕፋር’ በሚባል የሚታወቀው ፕሮግራም እንደማይቋረጥ ታውቋል። ፔፕፋር በዓለም መሪ የሆነ በኤድስ ላይ የሚሠራ ፕሮግራም ሲሆን፣ ሕይወት አድን ፕሮግራሞች እንዲቀጥሉ በመወሰኑ የ90 ቀናት እገዳው እንደማይመለከተው ታውቋል።

ፕሬዝደንት ትረምፕ ሥልጣኑን ደግመው በተረከቡ በሰዓታት ውስጥ ነበር “አሜሪካ ትቅደም” ከሚለው የውጪ ፖሊሲያቸው ጋራ የሚጣጣሙ መሆናቸው እስከሚጣራ ለውጪ ሃገራት የሚሰጡ ዕርዳታዎች ለ90 ቀናት እንዲቆሙ ያዘዙት፡፡

የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ምኒስትር ማርኮ ሩቢዮ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ እንደሚቀጥል ቀደም ብለው አስታውቀው የነበረ ሲሆን፣ ቆየት ብለው ደግሞ ደግሞ ሕይወት አድን መድሃኒቶችና የሕክምና አገልግሎቶች እንዲሁም የምግብና...

via:የአሜሪካ ድምፅ

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍5
ከተተመነው ግራም በታች ሲሸጡ የተገኙ ከ70 በላይ ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ ።

በንግድ ቢሮ ከተተመነው ግራም በታች ሲሸጡ የተገኙ ከ70 በላይ ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ያስታወቀ ሲሆን፤ በቀጣይም በሁሉም ዳቦ ቤቶች ላይ የሚያደርገውን ቁጥጥር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከ70 ከግራም በታች የሆነ የዳቦ ምርት ለሸማች እንዳያቀርቡ የቁጥጥር ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ፤ የቢሮ የንግድ ቁጥጥር ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር ቅድስት ስጦታው ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ምክትል ዳይሬክተሯ አክለውም ቢሮው በዳቦ ምርት ላይ የዋጋ ተመን እንደማያወጣ የገለጹ ሲሆን፤ "ሆኖም በከተማዋ በሚገኙ ዳቦ ቤቶች ላይ በቢሮው ከተተመነው ግራም በታች የሆነ ምርት ለገበያ እንዳይቀርብ እየተሰራ ይገኛል" ብለዋል፡፡

በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ በሚገኙ ዳቦ ቤቶች ላይ ከተቀመጠው ግራም መጠን በታች የሆነ ምርት እንዳይቀርብ ከዳቦ ቤቶች ናሙና በመውሰድ የተተመነውን መጠን የልኬት ሥራ የሚቆጣጠሩበት አሰራር ስለመኖሩ ምክትል ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡

በንግድ ቢሮው በስድስት ወራት ውስጥ በተከናወነ የቁጥጥር ሥራም፤ ከ70 በላይ ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል፡፡

ቢሮ በክትትል ወቅት በሚያገኛቸው ከግራም በታች የሆነ መጠን ያለው ምርት በሚሸጡ ዳቦ ቤቶች ላይ ከጽሁፍ እስከ ንግድ ፈቃድ የመሰረዝ እርምጃ የሚወስድበት አሰራር ስለመኖሩ ኃላፊዋ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

via:አሐዱ ራዲዮ

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍1🤔1
በአዲስ አበባ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ ነው

ምርጫችን ሠላም ነው" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች የድጋፍ ሠልፍ እያካሄዱ ነው።

በመዲናዋ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ለሠላም ያላቸውን ድጋፍ እና ቁርጠኝነት የሚገልፅ ሰልፍ ነው እያካሄዱ የሚገኙት።

ነዋሪዎቹ ለትግራይ ልማት እንጂ ዳግም ጦርነት አያሥፈልጋትም፣ በክልሉ ያለውን ሠላማዊ እንቅሥቃሴ እና መሠል እንቅሥቃሴዎች በማሥተጓጎል የሚገኝ ጥቅም የለም የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችን እያስተላለፉ ይገኛሉ።

ለትግራይ እና ነዋሪዎቿ ሠላም በምንም የማይተካ መሆኑንም ሠልፈኞቹ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ፖለቲከኞች ችግሮቻቸውን በመነጋገር እንዲፈቱ ለሠላም ጠንቅ ከመሆን እንዲታቀቡም አስገንዝ

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍2
በአማራ ክልል አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች ናቸዉ መባሉን ሰምናል።

በክልሉ 86.5 በመቶ ትምህርት ቤቶች ናቸው ከደረጃ በታች መሆናቸዉ የተገለፀው። የተካሄዱና እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶች ለትምህርት ተቋማት መጎዳት ምክንያት ናቸዉም ተብሏል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
1👍1
ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት ይሰጣል‼️

በወልዲያ-ቆቦ መንገድ የሚገኘው የአሚድ ወንዝ ብረት ድልድይ መሰበሩን ተከትሎ የትራንስፖርት አገልግሎት ችግር እንዳይፈጠር ጊዜያዊ ተለዋጭ መተላለፊያ መንገድ የተሰራ ሲሆን ከዛሬ ሀሙስ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት እንደሚችል ተሰምቷል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍2
አዲስ MAGAZINE - መረጃ
Photo
"የትግራይ ህዝብ ወደ መደበኛ ህገመንግስታዊ ስርዓት መመለስ የህወሓት ቀዳሚ መርህ ነው":-ህወሓት‼️

በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (#ህወሓት) ቡድን የትግራይ ህዝብ እና የትግራይ ልሂቃን ቀዳሚ ምርጫው ሰላም ነው ሲል ትላንት ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ጠ/ሚኒስት አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ህወሓት የጠ/ሚኒስትሩን ጥሪ ተከትሎ ትላንት ጥር 28 ቀን መግለጫ ያወጣ ሲሆን በመግለጫውም የትግራይ ህዝብ ቀዳሚ ምርጫ ሰላም ነው ብሏል፤ የትግራይ ህዝብን የሰላም ምኞት አውን ለማድረግ ሁሉመ ገንቢ ሚና ይጫወት ሲል ጠይቋል፤ ከማንኛውም አካል ጋር በሰላም ዙሪያ ለመስራት ዝግጁ ነኝ ሲል አስታውቋል።

ህወሓት በመግለጫው ባለፉት መቶ አመታት የትግራይ ህዝብ ያደረጋቸው ጦርነቶች “ህልውናውን ለማረጋገጥ እና ለጭቆና አጅ አልሰጥ በማለት ነው” ሲል በመግለጽ “የትግራይ ህዝብ ያደረጋቸው ተጋድሎዎች ያኮሩታል እንጂ አያስቆጩትም” ብሏል።

የህዝቡ የሰላም ምኞት ዕውን እንዲሆን የሚመለከታቸው ሁሉ ገንቢ ግንኙነት ላይ የተመሰረተ ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን ብሏል። አሁንም ቢሆን እንደተለመደው የትግራይ ህዝብ ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት በተለያዩ መንገዶች እያስመሰከረ ነው። ለሰላም ካለው ፍላጎት የተነሳ የዘር ማጥፋት ጦርነትን ለማስቆም የፕሪቶሪያን ስምምነት ተቀብሎ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን ጥሪ ያቀርባል ብሏል። ምንም እንኳን የፕሪቶሪያ ስምምነት የትግራይን ህዝብ ሙሉ ደህንነት የማያረጋግጥ ቢሆንም፣ እያንዳንዱ የትግራይ ህዝብ ስምምነቱን የማስፈጸም ተግባር ሰላምና መተማመንን እየፈጠረ ተጠቃሚ እንዲሆን አላስፈላጊ ዋጋ እየከፈሉ ቢሆንም ነገር ግን ታሪክ እራሱን ደግሟል እና የፕሪቶሪያ ስምምነት ተግባራዊ መሆን አልቻለም። የትግራይ ህዝብ ዋና ዋና ጥያቄዎች እና በፕሪቶሪያ ስምምነት ላይ የተቀመጡት ጉዳዮች አፈፃፀማቸው በመዘግየቱ ዋጋ እየከፈለ ነው። ህወሀት የትግራይን ህዝብ ጥቅም የሚያረጋግጥ የሰላም ጥሪ ሁሌም ይመኝ ነበር። ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የተሻለ ደረጃ ላይ መድረስ እና የትግራይን ህዝብ ተጠቃሚ ማድረግ የትግሉ ዋና ምሰሶ ነው። ሰላማችንን እና ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ እየሰራን ነው። እያንዳንዱ የሰላም ጥሪ እንዳይስተጓጎል በጥንቃቄ እንሰራለን።

የትግራይ ህዝብ በትግላቸው ያመጣው የፕሪቶሪያ ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን እንሰራለን። ስለሆነም ከወራሪ ሃይሎች ያልተላቀቁ ዜጎች ተፈተውና የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቤታቸው ይመለሱ። የትግራይ መሬት ሉዓላዊነት ይመለስ; ለትግራይ ሰላም ቀጣይነት በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙ አካላት ተጠያቂ መሆን አለባቸው።

ትግራይ ወደ መደበኛ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት መመለስ የትግራይ ሕዝብ ፍላጎትና የህወሓት ዋነኛ መርህ ነው። ትላንትም ዛሬም ነገም ከሁሉም የሰላም ሃይሎች ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናችንን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን"ሲል ገልጿል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍3