አዲስ MAGAZINE - መረጃ
31.4K subscribers
6.45K photos
222 videos
3 files
262 links
#አዲስ_Magazine_መረጃ

#መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ

#ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addis_Magazinebot

Addis Ababa , Ethiopia

የአዲስ ነገር መረጃ ቻናል አጋር ሚዲያ
Download Telegram
መረጃ‼️

የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር፣ የግል የጦር መሳሪያ ያላቸው ነዋሪዎች ከመደበኛ ጸጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት የአካባቢያቸውን ጸጥታ ተደራጅተው እንዲጠብቁ እንደፈቀደ ዋዜማ ሰምታለች።

ነዋሪዎቹ የሚይዙት የግል ጦር መሳሪያ፣ ሕጋዊ መኾኑን ለማሳወቅ ኩፖን ይዘው መንቀሳቀስ አለባቸው መባሉን ምንጮች ተናግረዋል።

ኾኖም በራሳቸው ጦር መሳሪያ ሰላም የሚያስብሩ ነዋሪዎች፣ ከራሳቸው ቀበሌ ወደ ሌላ ቀበሌ ወይም ወረዳ መንቀሳቀስ አይፈቀድላቸውም ተብሏል።

የክልሉ መንግሥትም፣ በኹሉም አካባቢዎች ጦር መሳሪያ ያላቸው ነዋሪዎች ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ተቀናጅተው የአካባቢያቸውን ሰላም እንዲያስጠብቁ የመፍቀድ ሃሳብ እንዳለው አንድ የዋዜማ ምንጭ ተናግረዋል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍1
ከ 730,000 የሚበልጡ የዩናይትድ ስቴትስ ተማሪዎች ከአገር ሊባረሩ እንደሚችሉ ዋሽንግተን ፖስት ዘገበ።

ስጋቱ የትራምፕ አስተዳደር የኢሚግሬሽን ባለስልጣናትና በሆስፒታሎች ያሉትን ጨምሮ - በአብያተ ክርስቲያናት እና በትምህርት ቤቶች ያሉ ሁሉ ትምህርታቸውን እንደማያቋርጡ ከተናገሩት መግለጫ ጋር በተያያዘ ነው - ሲል ጽሁፉ ገልጿል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
በኦንላይን ትኬት በመቁረጥ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት መሰጠት ሊጀመር ነው

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አ.ማ ከየካቲት 2017ዓ.ም  ጀምሮ በኦንላይን ትኬት በመቁረጥ የህዝብ መንገደኞች ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት  እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ(ኢ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ÷ አክሲዮን ማህበሩ ከየካቲት 2017 ጀምሮ በኦንላይን ቦታ በማስያዝ  የህዝብ መንገደኞች ትራንስፖርት አገልግሎት  እንደሚጀምር ገልፀዋል።

ጥራት ያለዉ እና ቀልጣፋ የጉዞ አገልግሎት  ለመስጠት ፣ ትክክለኛ የመንገደኛ መረጃን ለማረጋገጥ እንዲሁም ከችግር የጸዳ ጉዞን ለማመቻቸት አስፈላጊ በመሆኑ ለሁሉም የሀገር ውስጥ ተሳፋሪዎች ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) በመጠቀም ኦንላይን ቦታ ለመያዝም  ሆነ ለመጓዝ  መስፈርት መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍1
PLAGIARISM ‼️

ኢትዮጵያ የጥናት እና ምርምር ውጤቶችን በመኮረጅ በዓለም ቀዳሚዋ ሀገር ተብላለች።

መቀመጫውን ሕንድ ያደረገው ዓለም አቀፍ ሪሰርች ዋች እንዳለው ከሆነ ኢትዮጵያ በሌሎች ሀገራት የተሰሩ ጥናቶችን ቀጥታ ትቀዳለች። ሳውዲ አረቢያ፣ ፓኪስታን፣ ቻይና እና ግብጽ ከኢትዮጵያ በመቀጠል የጥናት ውጤቶችን የሚኮርጁ ሀገራት ናቸው።

እነዚህ ሀገራት የሌሎች ሰዎችን ጥናት ሲኮርጁ የሚቀጣ ህግ የላቸውም ብሏል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍1
አራት የፍጥነት መንገዶች‼️

የኢትዮጵያ መንገዶች አስዳደር ከአዲስ አበባ በተለያዩ   መስመሮች የሚወጡ 4   አዳዲስ  የፍጥነት  መንገዶችን  ለመገንባት  የሚያስችል  ጥናት እየተደረገ መሆኑን አሳውቋል።
መንገዶቹ:
🎯ከአዲስ  አበባ - ደሴ
🎯ከአዲስ  አበባ - ጅማ
🎯ከአዲስ  አበባ - ደብረማርቆስ  እና
🎯ከአዲስ አበባ - ነቀምት በሚዘልቁት  መንገዶችን ላይ ነው።

👉ከተጠቀሱት የፍጥነት  መንገዶች  መካከል  የአዲስ አበባ  ጅማ እና አዲስ አበባ ደብረ ማርቆስ ፕሮጀክቶች ለገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት የግል  አጋርነት  ቦርድ  የቀረቡ  ሲሆን  ቀሪዎቹም በቀጣይ  ይቀርባሉ ተብሏል።
👍2
ወይ ጉደ‼️😭😭

የ9 ዓመት ሴት ህፃን ልጅ አታልሎ የደፈረዉ አዛዉንት በጽኑ እስራት መቀጣቱን የቦረዳ ወረዳ  ፖሊስ ገለፀ።

ተከሳሽ አቶ እሳቱ ዳንጎረ የተባለው የ60 ዓመት አዛውንት ጥር 5/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ገደማ የግል ተበዳይ የ9 ዓመት ህጻን የሆነች  በጎቹን ለመጠበቅ በቦረዳ ወረዳ ዘፍነ ቀጠና 3 ሀንዝያ መሄጃ ልዩ ስፍራ ሾንከ ዛፍ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ባህር ዛፍ ውስጥ ሸንኮራ እንቺ በማለት አታሏዋት ወደራሱ አቅርቦ አስገድዶ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ወንጀል በመፈፀሙ የቦረዳ ወረዳ ፖሊስ በሰውና ሀኪም ማስረጃ ምርመራዉን አጣርቶ ለዐቃቤ ህግ ያቀረበዉ ክስ ተከፍቶ የቀረበለት የወረዳዉ ፍርድ ቤት አከራክሮ ጥር 27/2017 ዓ.ም በዋለው 1ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሽን በ16 ዓመት ጽኑ እስራት እንድቀጣ ወስነዋል።

መረጃዉ፦ የቦረዳ ወረዳ ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ነዉ።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
2
የአዲስ አበባ ፖሊስ የደኅንነት ስጋት ትፈጥራላችኹ በሚል

ጠርጥሬያቸዋለሁ ያላቸውን ነዋሪዎች በዘፈቀደ ካሠረ በኋላ በነፍስ ወከፍ 2 ሺሕ ብር እየተቀበለ እንደሚለቅ ዋዜማ ታስረው ከተፈቱ ሰዎች ሰምታለች።

ባለፈው ቅዳሜ ገርጂ አካባቢ ከታሠሩ 50 ወጣቶች መካከል፣ ስድስቱ በነፍስ ወከፍ 2 ሺሕ ብር ከፍለው መለቀቃቸውን ተናግረዋል።

ገንዘቡን መክፈል አንችልም ያሉ ወጣቶች፣ ለአራት ቀናት ከታሠሩ በኋላ ፖሊስ ጣቢያውን የሚጎበኙ ዓቃቢያነ ሕግ እንደሚመጡ ሲታወቅ እንደተለቀቁ ተናግረዋል። ገንዘቡ የሚከፈለው በደረሰኝ ሳይኾን፣ ለተረኛ ፖሊሶች በጉቦ መልክ የሚከፈል ነው ተብሏል።

ዋዜማ ሬዲዮ በጉዳዩ ዙሪያ የከተማውን ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሠን ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካ ገልጿል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍3
የምስራቅ ወለጋ አባገዳዎች የሰላም ጥሪ አቀረቡ

የምሥራቅ ወለጋ ዞን የአባዳዎች ሕብረት ሰብሳቢ አባገዳ ደሳለኝ ፈይሳ ውስብስብ እየሆነ የመጣውን የሰላም እጦት ችግር ለመፍታት ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ሸማቂዎችና መንግሥት የሕዝቡን የሰላም ጥያቄ በመቀበል ወደ እርቅ መምጣት እንደለባቸው አመልክተዋል።

ከዚህ ቀደም ተጀመሩ የተባሉ ድርድሮችም በተለያዩ ቦታዎች የተሟላ ሰላም ባለመኖሩ ለተፈጠሩ ለችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ያመጣል ተብሎ እምነት ተጥሎበት እንደነበር በማንሳት አሁንም ለሕዝቡ ሰላም ቅድሚያ በመስጠት ሁለቱም አካላት ድርድር በመቀመጥ ይሄን ችግር መፍታት አለባቸው ሲሉ መናገራቸውን ዶቼቬሌ ዘግቧል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍3
መረጃ‼️

የአራት ኪሎ ፕላዛ የምድር ውስጥ መተላለፊያ እና የመዝናኛ ስፍራ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

በአዲስ አበባ በኮሪደር ልማት የተገነቡ መሰረተ ልማቶችና የመዝናኛ ስፍራዎች መካከል አንዱ የሆነው የአራት ኪሎ ፕላዛ የምድር ውስጥ መተላለፊያ እና መዝናኛ ስፍራ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቆ ዛሬ ወደ አገልግሎት ገብቷል።

አካባቢው ከዚህ ቀደም ለተሽከርካሪ፣ ለእግረኞችና ለአካል ጉዳተኞች መተላለፊያነት አስቸጋሪ እንደነበር  የተነገረ ሲሆን አሁን አካል ጉዳተኞችም በቀላሉ መተላለፍ የሚችሉበት የአሳንስር መጓጓዣ መኖሩ ተነግሯል።

በውስጡ የሀገር ውስጥ አልባሳት፣ መዋቢያዎች፣ ወርቅና ብር መሸጫ ቤቶች፣ የስልክ መሸጫዎች፣ የፈጣን ምግብ አገልግሎት እና መሰል የንግድ አገልግሎቶች አሉ ተብሏል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍3
ይህ ከአዋሽ አርባ ስኳር ፋብሪካ መገንጠያ አለፍ ብሎ ቴሌ የሚባል ቦታ የደረሰ ዘግናኝ አደጋ ነው።

ኬሚካል የጫነ መኪና በመውደቁ እሳት ተፈጥሮ ሹፌሩ እና ረዳት በሚያሳዝን ሁኔታ ተቃጥለው ህይወታቸው ማለፉን የሾፌሮች አንደበት መረጃ ያመለክታል።ለቤተሰቦቻቸው መፅናናቱን ይስጥልን።

Via:wasu

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍2
አዲስ MAGAZINE - መረጃ
Photo
የምርመራዘገባ አለም ባንክ በዲጂታል ፋውንዴሽን በኩል ለኢትዮጵያ የሰጠው 200 ሚልዮን ዶላር ምን ላይ እየዋለ ነው?

- በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ስር በግል አማካሪነት በአመት 120 ሺህ ዶላር የሚከፈለው ግለሰብ አለ

በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ይፋ ተደርጎ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የተጀመረው በ2013 ዓ/ም ነበር። በዚህ ወቅት ነበር የኢትዮጵያ ዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት ብሄራዊ ኮሚቴ በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ስር ሆኖ መንቀሳቀስ የጀመረው።

ፋውንዴሽኑ ዋና አላማው የመንግስት የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎትን ማስፋፋት፣ የህዝብ ተቋማት ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ዝርጋታ፣ የብሄራዊ መታወቂያ ስራ፣ የግል የቴክኖሎጂ ተቋማትን አቅም መገንባት በስራው ውስጥ የተካተቱ ነበሩ።

እንቅስቃሴው ከተጀመረ ወዲህ በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ በመንግስት በይፋ ቢገለፅም አንዳንድ አነጋጋሪ ድርጊቶች ግን መታየት ጀምረዋል።

ለምሳሌ የአለም ባንክ የዛሬ አራት አመት 200 ሚልዮን ዶላር መድቦለት ስራ በጀመረው የዲጂታል ፋውንዴሽን ውስጥ በአማካሪነት ተቀጥረው እየሰሩ ከሚገኙት መሀል ዶ/ር ስሜነው ቀስስ ሲሆኑ የትምህርት መስካቸው የእንስሳት ህክምና ቢሆንም በዚህ የዲጂታል ዘርፍ በአማካሪነት ተቀጥረው በአመት 130,000 ብር በአማካሪነት እንደሚከፈላቸው ለመሠረት ሚድያ የደረሰው መረጃ ያሳያል።

በሌላ በኩል አቶ ሰለሞን ካሳ፣ ወይም ኢቢኤስ ቴሌቭዥን ላይ 'ቴክ ቶክ' በሚል ስያሜው የሚታወቀው ግለሰብ በተመሳሳይ በማማከር ቅጥር በአመት 120,000 የአሜሪካ ዶላር መቀጠሩ አነጋጋሪ እንደሆነባቸው ጉዳዩን የሚያውቁ ምንጮች ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል፣ ሰለሞን በአመት በርካታ ወራትን በአሜሪካ የሚያሳልፍ መሆኑ ጉዳዩን ይበልጥ አስገራሚ እንደሚያደርገው ይገልፃሉ።

ይህ ብቻ ሳይሆን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር "Internet Exchange Point" በተባለ ፕሮግራም የኢንተርኔት ፍሰት በሀገር ውስጥ የዳታ ማእከል እንዲያልፍ የሚያደርገው ፕሮጀክት በጀት ተይዞ የነበረ ቢሆንም ስራውን ይዞ የነበረው ተቋም ከቢሮው እንዲለቅ ተደርጎ በሌላ እንዲተካ እንደተደረገ እና ይህም ከገንዘብ ጥቅም ጋር የተያያዘ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ።

"አይቲ ፓርክ" ተብሎ በሚጠራው ማእከል ውስጥ በዶላር እየከፈሉ የተከራዩ በርካታ ተቋማት እንዳሉ የሚታወቅ ሲሆን ይህ ገቢ ግን ወደየት እየገባ እንደሆነም እንደማይታወቅ እነዚህ ምንጮች ያስረዳሉ።

"በሸገር ከተማ ቡራዩ ውስጥ ለሚገኝ አንድ የአዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች 'የቴክኖሎጂ ክህሎት ስልጠና ለመስጠት' በሚል ፋሪስ ለተባለ ድርጅት 21 ሚልዮን ብር በዲጂታል ፋውንዴሽን በኩል ተከፍሏል" የሚሉት እነዚሁ ምንጮች ይህም የተከናወነው በጨረታ ስም ሆኖ ሌሎች አቅም ያላቸው ተቋማት ገለል ተደርገው መሆኑን ጠቁመዋል።

የፋሪስ ድርጅት ባለቤት በቅርቡ የቴስላ 'ሳይበርትራክ' መኪና ካለቀረጥ ወደ ሀገር በማስገባቱ የሚታወቅ ሲሆን የዚህን መኪና ወደ ኢትዮጵያ መግባት ባለቤቱ አቶ ኤልያስ ይርዳው ማህበራዊ ሚድያ ላይ ለሀገሪቱ ትልቅ "የኢኖቬሽን" እምርታ ብሎ የገለፀበት መንገድ ብዙዎችን አነጋግሮ ነበር።

በዚህ ዙርያ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩን ዶ/ር በለጠ ሞላን እንዲሁም የዲጂታል ፋውንዴሽን ሀላፊውን አቶ ተሰማ ገዳን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

via:Meseret Media

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍3
የኢትዮጵያ አየር መንገድ መግለጫ

ዛሬ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃ ውስጥ ወደ በረራ ይዞ መግባት ከሚከለከሉ ቁሳቁሶች መካከል ከመንገደኞች የሚሰበሰብ የሲጋራ መለኮሻ (ላይተር) ጊዜያዊ የማስቀመጫ ስፍራ ውስጥ ጭስ በመከሰቱ ለመንገደኞች ደህንነት ሲባል ሕንፃው ለጊዜው አገልግሎት አቋርጧል።

በመሆኑም በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ውስጥ መዳረሻዎቻችን የምትጓዙ መንገደኞቻችን በዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል ወደ በረራችሁ እንድትሳፈሩ ከታላቅ አክብሮት ጋር እያሳሰብን ከነገ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለመደው የሀገር ውስጥ ተርሚናል አገልግሎት መስጠት የምንቀጥል መሆኑን እናስታውቃለን። ለተፈጠረው መጉላላት መንገደኞቻችንን ይቅርታ እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍1
አዲስ MAGAZINE - መረጃ
Photo
የ14 አመት ታዳጊ በማገት ከወላጆቿ 1.5 ሚሊየን ብር የተቀበሉ ግለሰቦች

በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ዲባዬ ክፍለ ከተማ ውስጥ የ14 ዓመቷን ልጅ አግተው በመውሰድ ከወላጆቹ 1.5 ሚሊየን ብር የተቀበሉ አራት ግለሰቦች በእስራት መቀጣታቸውን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ለብስራት የላከዉ መረጃ ያሳያል።

እንደ ቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት መግለጫ አንደኛ ተከሳሽ አቢ ሰለሞን ፣ሁለተኛ ተከሳሽ ታደለ ጉታ፣ ሶስተኛ ተከሳሽ ለታ ሶሪ እና አራተኛ ተከሳሽ ዳንኤል ተገኑ የተባሉ  ግለሰቦች ሚያዝያ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ሰአት ላይ የ14 ዓመቱን ልጅ አግተው በመውሰድ ወላጆቹን 1.5 ሚሊየን ብር እንደጠየቁ መግለጫው አመልክቷል።

እነዚህ አራት ግለሰቦች ያገቱትን ልጅ ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ሆኖ እንዲገባ ካደረጉት በኋላ ከቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ዲባዬ ክፍለከተማ ሆራ ወረዳ ልዮ ቦታው ሁለገብ የተባለው ስፍራ በተከራዩበት ቤት አፍነው እንዳስቀመጡት ተገልፆል። ልጁን አፍነው ካስቀመጡ በኋላ ለወላጆቹ ደውለው 1.5 ሚሊየን ብር እንዲላክላቸው ማድረጋቸው እና የጠየቁትን ብር ሚያዚያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም ከ አስራ አምስት ቀን በኋላ ከወላጆቹ እንደተቀበሉ እና ልጁም በሰላም እንዲለቀቅ ሆኗል።

ፖሊስ የድርጊቱን አፈፃፀም ከወላጆቹ መረጃ ካገኘ በኋላ ባደረገው ከፍተኛ ክትትል ከአስራ አምስት ቀን በኋላ አራቱም ተከሳሾች ከተቀበሉት 1.5 ሚሊየን ብር ላይ አንድ አዲስ ሞተር ብስክሌት እና 1 ማካሮቭ ሽጉጥ በመግዛት ለሌላ የተመሣሣይ የእገታ ተግባር ሲዘጋጁ በቁጥጥር ስር ዉለዋል። ፖሊስ አራቱን ግለሰቦች ከተያዘው የኤግዚቢት እቃ ጋር በቁጥጥር ስር ውለው የምርመራ መዝገባቸውን በማጣራት ለአቃቤ ህግ ልኳል፡፡

አቃቤ ህግም ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ  በማስገደድ በተንኮል እና በማታለል ሰውን የመጥለፍ እና የማገት ወንጀል በመጥቀስ ክስ መስርቷልል።

በአቃቤህግ የተመለከተውን ክስ ሲከታተል የነበረው የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት አንደኛ ተከሳሽ አቢ ሰለሞን ፣ሁለተኛ ተከሳሽ ታደለ ጉታ ፣ሶስተኛ ተከሳሽ ለታ ሶሪ እያንዳንዳቸው በ 9 አመት እስራት እንዲቀጡ ሲወስን አራተኛው ተከሳሽ ዳንኤል ተገኑ ደግሞ በ 10 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍1
አስመጪዎች መክፈል የሚችሉት ቅድመ ክፍያ መጠን ላይ ማሻሻያ ሊደረግ ነው‼️

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስመጪዎች ያለባንክ ዋስትና መላክ የሚችሉት ቅድመ ክፍያ/advance payment መጠን ላይ ማሻሻያ ሊያደርግ ነው።

ላለፉት 27 አመታት ሲተገበር በቆየው አሰራር መሰረት አስመጪዎች ያለባንክ ዋስትና ለሚያስገቡት እቃ በቅድሚያ መላክ/መክፈል የሚችሉት የውጭ ምንዛሬ መጠን ከ5 ሺ ዶላር መብለጥ እንደማይችል የማእከላዊ ባንኩ መመሪያ ይደነግጋል።

ሆኖም ከ5ሺ ዶላር በላይ ቅድመ ክፍያ መፈፀም ከፈለጉ ከአገር ውስጥ ባንክ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸው ነበር።
አሁን ማእከላዊ ባንኩ ያለዋስትና መላክ በሚቻለው ቅድመ ክፍያ መጠን ላይ ጭማሪ ለማድረግ መመሪያውን እየከለሰ ይገኛል።
ምንጮች የጭማሪ መጠኑ ምን ያህል እንደሆነ ከመግለጥ ቢቆጠቡም አዲሱ መመሪያው ግን በቀጣይ መጋቢት ወር ወደ ስራ ይገባል ብለዋል።

via:ቅዳሜገበያ

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በባህርዳር ዩኒቨርስቲና ሆስፒታሎች የሚሰሩ የህክምና ዶክተሮች የዶ/ር አንዷለምን ግድያና በህክምና ባለሙያዎች ላይ የሚደርሰውን ግድያ እንዲቆም የሚጠይቅ ሰልፍ ጠየቁ።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍2
ከቀናት በፊት አዳዲስ አመራሮችን የመረጠው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፤ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው ያለውን “የእርስ በእርስ ጦርነት” ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ መወሰኑን ገለጸ። ፓርቲው “የተበላሸ” ሲል የጠራውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስርዓት ለማረምም “ከምንጊዜውም በላይ እታገላለሁ” ብሏል።

መኢአድ ይህን ያለው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በአዲስ አበባ ያካሄደውን 10ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በተመለከተ በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ ነው። ፓርቲው በዚሁ ጉባኤው፤ የድርጅቱን ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት ጨምሮ የስራ አስፈጻሚ፣ የማዕከላዊ ምክር ቤት እንዲሁም የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚቴ አባላትን መርጧል።

ተመራጮቹ ፓርቲውን “ለቀጣዩ ሶስት ዓመታት ሊመሩ የሚችሉ” እና ድርጅቱን “ወደተሻለ ደረጃ ያደርሳሉ” በሚል በጠቅላላ ጉባኤው ተሳታፊዎች የታመነባቸው እንደሆኑም መኢአድ አስታውቋል። ጠቅላላ ጉባኤው “አዳዲስ እና ወጣት የሴት አመራሮችን ወደፊት እንዲመጡ አድርጓል” ሲልም ፓርቲው በመግለጫው አክሏል።

via:Ethiopia Insider

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍1
ጊዮን ሆቴል የሚገኘው ግሮቭ ጋርደን ለወንዝ ዳር ልማት መፈረሱን ባለቤቱ አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ገልጿል።

via:Fast Mereja

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍1😢1