አዲስ MAGAZINE - መረጃ
31.5K subscribers
6.42K photos
221 videos
3 files
262 links
#አዲስ_Magazine_መረጃ

#መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ

#ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addis_Magazinebot

Addis Ababa , Ethiopia

የአዲስ ነገር መረጃ ቻናል አጋር ሚዲያ
Download Telegram
የጦርነት ስጋት‼️
በትግራይ ክልል የእርስ በርስ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ስጋት መኖሩን ነዋሪዎቹ ተናገሩ‼️

የትግራይ ወታደራዊ አመራር ሰሞኑን መፈንቅለ መንግስት የማድረግ ዕቅድ መኖሩን በመግለጫቸው ካሳወቁ በኋላ በትግራይ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።

ውጥረቱን ተከትሎ የሆነ ነገር ሊፈጠር ይችላል በሚል ከወትሮው በተለየ ገንዘብ ለማውጣት ባንኮች በሰልፍ ተጨናንቀዋል ሲሉ እማኞች ገልፀዋል።

በገበያ ማእከላት በተለይ የፍጅታ ሸቀጦች ላይ የፍላጎት መጠን በጣም ጨምሯል። ጦርነት ይቀሰቀስ ይሆናል ብሎ የሰጋው ህዝብ ሰማይን ደግፎ ኑሮውን እየመራ ነው። በዚህ ብቻ ግን አልተገደበም። የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄድ ጀምሯል።

«መንግስት የሚያፈርስ የትኛውም አካል አንታገስም» የመኾኒ ህዝብ በዛሬው ዕለት እያካሄደ በሚገኘው ሰልፍ ይዞት የወጣው መፈክር ነው።

https://t.me/zena_ethiopia24
12👍4👏1
አሜሪካ ስደተኞችን ማስወጣት ጀመረች‼️

የትራምፕ የስደተኞች ፖሊሲ ተግባራዊ እየተደረገ ሲሆን በአንድ ቀን ብቻ ከ500 በላይ ስደተኞችን ሲታሰሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ በወታደራዊ አውሮፕላኖች ተጭነው ወደሀገራቸው ተሸኝተዋል።

የፖለቲካ ጥገኝነት ለማግኘት በየአደባባዩ ባንድራ እየያዙ የተቃዎሞ ሰልፍ የሚያደርጉም ከህገ-ወጥ ስደተኞች ዝርዝር ውጭ ሊሆኑ እንደማይችሉ ታውቋል።

አሜሪካ ከሜክሲኮ የምትወሰንበት የደቡባዊ ድንበር ቅድሚያ ተሰጥቶት በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ጥብቅ እርምጃ እየተወሰደ ነው።

https://t.me/zena_ethiopia24
3👍3
“በጅማ 15 ሺህ ቤቶች አፍርሰን፣ ካሳ አልተጠየቅንም “ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ( ዶ/ር )

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ( ዶ/ር ) መንግስታቸው “ በጅማ ከተማ በትንሹ 15 ሺህ ቤቶች ማፍረሱን”  አረጋግጠው ነገር ግን “የፈረሰባቸው ሰዎች” ካሳ አለመጠየቃቸውን ተናግረዋል።

ዐብይ 11 ደቂቃ ገደማ ንግግራቸውን ያስተላለፉት ጅማ የነበራቸውን ቆይታ አስመልክተው በሰራጩት መልዕክት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ  “ለፈረሰው ቤት ካሳ አልጠየቀም፤ ለቦታው አልጠየቀም፤ እስቲ ሃሳባችሁን አፍሱት ነው ያለው” ቢሉም ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎች በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አላስረዱም።

ዐብይ መልዕክታቸውን ሲቀጥሉ “ከአንድ ሺህ በላይ የመቃብር ቦታዎች ተነስተዋል፤ መስጊድ” መነሳቱን ገልጸዋል።

“ ሌላ ቦታ ሊታሰቡ፣ ሊሞከሩ የማይችሉ በጣም በርካታ ጉዳዮች የጅማ ሕዝብ በቅንነት አምኖ በሃሳቡ ገንዘቡን፣ ጊዜውን፣ ጉልበቱን ሰውቶ ይሄ ህልም እንዲከወን ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል”  ሲሉ አድንቀዋል።

በተዘዋዋሪም መንግስታቸው በሚሰራቸው ሥራዎች ዙሪያ በሌሎች ነገር ግን ባልጠቀሷቸው አካባቢዎች እክል እንደሚገጥመው ፍንጭ ሰጥተዋል።

የጅማን ሕዝብ ደጋግመው ያመሰገኑት ዐብይ መልካም ነገር እንዲሁ አይመጣም በስቃይ እንጂ ሲሉ ተደምጠዋል።

የአሜሪካን ታሪክ በምሳሌነት የጠቀሱት ዐብይ  “መልካም ነገር እንዲሁ ስለማይመጣ መጨከን አለብን” ሲሉ ቀኝ እጃቸውን በቡጢ መልኩ ጨብተው፣ የግራ እጃቸውን መዳፍ እየመቱ አስገንዝበዋል።

“ሥራ ከጀመርን ጥቂት ዓመት ነው ፤ በጥቂት ዓመት ይህን ማድረግ ከቻልን፣ ሌላ ጥቂት ዓመት እንደ አሁኑ ሳንባላ፣ ሳንጓተት ብናክልበት ምንም ጥርጥር የለውም፤ የተሻለ ነገር መፍጠር ይቻላል” ሲሉም ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ እግረ መንገድ ጠቁመዋል።

@zena_ethiopia24
6👍2
በትምህርት ቤቶች አካባቢ አዋኪ ድርጊት ሲፈፅሙ በነበሩ ከ1ሺህ በላይ  የንግድ ድርጅቶች እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተገለጸ

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በጋራ ለመስራት ትስስር ከፈረሙ ባለድርሻ አካላት ጋር የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል፡፡

በከተማዋ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች አካባቢ አዋኪ ድርጊት በፈጸሙ 1ሺህ 984 የንግድ ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር ተናግረዋል።

በመዲናዋ  ሲከበሩ በነበሩ የአደባባይ ክብረ በዓላት ላይ የመዲናዋን ፀጥታ ሊያደፈርሱ ይችላሉ ተብለው የተጠረጠሩ 27 ሺህ 466 ተጠርጣሪዎች በ6 ወር ውስጥ መያዛቸውን ሃላፊው ገልፀዋል።

የሽብር ተግባር ለሚፈፅሙ አካላት መጠቀሚያ እንዳይውሉ ውሎና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ 17ሺህ 563 ዜጎችን ቢሮው ወደማቆያ ማስገባቱንም ተናግረዋል።

በመድረኩ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ አዲስ አበባን የደህንነት ስጋት የሌለባት ከተማ ለማድረግ እና ከተማዋን የሚመጥን ዘመናዊ የፀጥታ ተቋም ለመፍጠር በተሰሩ ስራዎች በርካታ ውጤቶች መገኘታቸውን ገልፀዋል።

በከተማዋ  ነዋሪ ላይ የሚፈፀሙትን ንጥቂያዎችን ለመከላከል ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመሆን እንደሚሰራና በተለይም በመዲናዋ የሚስተዋለውን የኑሮ ውድነት ለማሻሻል ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በቀጣይም በዲጂታል አሰራር የቁጥጥር ስራ ለማስጀመር ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ መሆኑንም የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ጠቁመዋል።
በመድረኩም በመዲናዋ በአፈጻጸማቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተቋማት የዋንጫና የምስክር ወረቀት ሽልማት ተበርክቷል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የእርምት እርምጃ ተወሰደ‼️

#ቲክቶከር ሮማን በመናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 በተባባሪ አዘጋጆች ከሚቀርቡ ዝግጅቶች መካከል አንዱ በሆነው  የብርሐን መንገድ በተሰኘ ፕሮግራም ላይ መቅረቧ ይታውቃል፡፡

የቀረበችው “ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ ማዋል” በሚል ከዚህ በፊት በማህበራዊ ሚዲያ ያስተላለፈችውን የተዛቡ አመለካከቶችን በተመለከተ ይቅርታ ለመጠየቅ እና ከስህተቷ ሌሎች ትምህርት እንዲወስዱ ነው፡፡

በመሆኑም በርካታ አድማጮቻችን በግለሰቧ መቅረብ መከፋታቸውን ነግረውናል፡፡

ለተፈጠረው ጉዳይ ጣቢያችን ይቅርታ እየጠየቀ ላልተወሰነ ጊዜ በተባበሪ አዘጋጆች የሚቀረበው የብርሐን መንገድ የተሰኘ ፕሮግራም የታገደ መሆኑን እናሳወቃለን፡፡ 

በተጨማሪም በቀጥታ ስርጭት ወቅት የፕሮግራሙ አዘጋጆች በቀጥታ ስልክ መስመር የገባ አድማጭን ያቋረጡበት መንገድ  ከሙያ ስነምግባር ያፈነገጠ በመሆኑ አጣርተን እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

Via መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሻሸመኔ 😭

አንዲት እድሜዋ በ12 ዓመት ክልል ውስጥ የምትመደብ ልጅ ለሊት ተ*ድላ ተገኝታለች

የሻሸመኔ ከተማ ፖሊስ የዚችን ህፃን ልጅ ገዳይ አጣርቶ ለህግ እንዲያቀብ እንማፀናለን::

Via:gursha

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
በትግራይ ጦርነት የተጎዱ 1026 ሰዎች ለእያንዳንዳቸው ክልሉ 140 ካሬ ሜትር ቦታ ሰጣቸው።

  በትግራይ ጦርነት የተጎዱ ሰዎች ሁሉ መኖሪያ ቤት ብቻ ሳይሆን ብዙ ይገባቸዋል ሲል የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ገለፀ።

ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ በጦርነት የተጎዱ የትግራይ ተወላጆች በሙሉ መኖሪያ ቤት ብቻ ሳይሆን ብዙ ይገባቸዋል ብለዋል።

በአጠቃላይ 1,026 የጦር ሰለባዎች ለእያንዳንዳቸው 140 ካሬ ሜትር ቦታ መመደቡን የከተማው የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ኦፊሰር ገ/ሚካኤል እንሁን ገልጸዋል።

የትግራይ ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጨርቆስ ወ/ማርያም መንግስት ላደረገው ድጋፍ አመስግኖ መንግስት በዚህ መልኩ መስራቱን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

#FastMereja

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
ማስጠንቀቂያ‼️

ቅዳሜ ጥር 17 ቀን - 2017 ዓ.ም በደብረ ታቦር የኃይል ማከፋፈያ ጣብያ ስራ ለማስጀመር ከላይ የተዘረዘረ ከተማዎች ኤሌክትሪክ ይቋረጣል።

ነዋሪዎች ቅድመ ዝግጅት አድርጉ!!!

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
2
#አስገራሚው_ዛፍ

👉| ይህ የዛፍ ዝርያ በአለማችን በርዝመቱም በውፍረቱም ወደር ያልተገኘለት ዛፍ ነው፡ ይህ ዛፍ Red Wood በመባል የሚጠራ ሲሆን
ቁመቱ 115.5 ሜትር ወይም 379 ጫማ ይረዝማል
ዲያሜትሩ ደግሞ 8.9 ሜትር ወይም 29.2 ጫማ ይረዝማል
የዚህ ዛፍ የእድሜ መጠኑ ከ 1200 - 2200 ድረስ መቆየት ይችላል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍1😱1
መረጃ‼️

የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር፣ የግል የጦር መሳሪያ ያላቸው ነዋሪዎች ከመደበኛ ጸጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት የአካባቢያቸውን ጸጥታ ተደራጅተው እንዲጠብቁ እንደፈቀደ ዋዜማ ሰምታለች።

ነዋሪዎቹ የሚይዙት የግል ጦር መሳሪያ፣ ሕጋዊ መኾኑን ለማሳወቅ ኩፖን ይዘው መንቀሳቀስ አለባቸው መባሉን ምንጮች ተናግረዋል።

ኾኖም በራሳቸው ጦር መሳሪያ ሰላም የሚያስብሩ ነዋሪዎች፣ ከራሳቸው ቀበሌ ወደ ሌላ ቀበሌ ወይም ወረዳ መንቀሳቀስ አይፈቀድላቸውም ተብሏል።

የክልሉ መንግሥትም፣ በኹሉም አካባቢዎች ጦር መሳሪያ ያላቸው ነዋሪዎች ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ተቀናጅተው የአካባቢያቸውን ሰላም እንዲያስጠብቁ የመፍቀድ ሃሳብ እንዳለው አንድ የዋዜማ ምንጭ ተናግረዋል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍1
ከ 730,000 የሚበልጡ የዩናይትድ ስቴትስ ተማሪዎች ከአገር ሊባረሩ እንደሚችሉ ዋሽንግተን ፖስት ዘገበ።

ስጋቱ የትራምፕ አስተዳደር የኢሚግሬሽን ባለስልጣናትና በሆስፒታሎች ያሉትን ጨምሮ - በአብያተ ክርስቲያናት እና በትምህርት ቤቶች ያሉ ሁሉ ትምህርታቸውን እንደማያቋርጡ ከተናገሩት መግለጫ ጋር በተያያዘ ነው - ሲል ጽሁፉ ገልጿል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
በኦንላይን ትኬት በመቁረጥ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት መሰጠት ሊጀመር ነው

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አ.ማ ከየካቲት 2017ዓ.ም  ጀምሮ በኦንላይን ትኬት በመቁረጥ የህዝብ መንገደኞች ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት  እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ(ኢ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ÷ አክሲዮን ማህበሩ ከየካቲት 2017 ጀምሮ በኦንላይን ቦታ በማስያዝ  የህዝብ መንገደኞች ትራንስፖርት አገልግሎት  እንደሚጀምር ገልፀዋል።

ጥራት ያለዉ እና ቀልጣፋ የጉዞ አገልግሎት  ለመስጠት ፣ ትክክለኛ የመንገደኛ መረጃን ለማረጋገጥ እንዲሁም ከችግር የጸዳ ጉዞን ለማመቻቸት አስፈላጊ በመሆኑ ለሁሉም የሀገር ውስጥ ተሳፋሪዎች ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) በመጠቀም ኦንላይን ቦታ ለመያዝም  ሆነ ለመጓዝ  መስፈርት መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24
👍1