Addis Insight -አዲስ እይታ
3.26K subscribers
9.68K photos
379 videos
33 files
3.14K links
እርሶ ቻናላችንን Subscribe ሲያደርጉ ወቅታዊና ሁሉን አቀፍ መረጃዎችን ያገኛሉ።
Link👇
https://t.me/AddisInsight23
Download Telegram
❗️የአማራ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እጅ የሠጡ የቀድሞ የፋኖ ታጣቂዎችን አደራጅቶ እያሠማራ መሆኑን ዋዜማ ከምንጮች ሠምታለች።

"የአማራ የሰላም ኃይል" በሚል ስያሜ በተደራጀው ኃይል ውስጥ በፋኖ አደረጃጀት ውስጥ ያልነበሩ ፈቃደኛ ግለሰቦችም ተካተዋል። ታጣቂዎቹ ራሳቸው በመረጡትና አካባቢያቸውን መሠረት ባደረገ መልኩ እንደሚደራጁ የገለጡት ምንጮች፣ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ጎን ለጎን በጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ለመንቀሳቀስ መስማማታቸውን ምንጮች ተናግረዋል።

የጎንደር አካባቢ የቀድሞ የፋኖ ታጣቂዎች ሥልጠና አጠናቅቀው ለግዳጅ የተሠማሩ ሲኾን፤ በተመሳሳይ በወሎ የፋኖ አባል የነበሩ ግለሰቦች የሚመሯቸው አደረጃጀቶች እየተፈጠሩ መኾኑን ምንጮች ገልጸዋል።

ከክልሉ መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት የተፈታረሙት የቀድሞው የፋኖ ከፍተኛ አመራር ማስረሻ ሠጤ፣ አዲሱን አደረጃጀት በመፍጠር ሂደት ውስጥ እንዳሉበት ተረድተናል።
👎3
🔴 ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) የሚኒስትርነት ሹመት እንዳልተሰጣቸው ገለጹ
በማኅበራዊ ሚዲያ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሾማቸውን በሚገልጽ መልኩ የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑ ተገለጸ።
የቀድሞው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) መረጃው እውነት እንዳልሆነ በጽሑፍ ለTikvah Ethiopia ማሳወቃቸው ተገልጿል።
📅 መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም.

አዲስ ኢንሳይት — ዓለምን በአዲስ እይታ
🔴 የጥሬ ወተት አያያዝ የጤና ስጋት አለው-ጥናት
በአዲስ አበባ የጥሬ ወተት ጥራትና ደህንነትን ከእርባታ ሼድ እስከ ሽያጭ ድረስ የተመለከተ ጥናት፣ ለጤና ስጋት ሊዳርጉ የሚችሉ የአያያዝና የግብይት ክፍተቶች መኖራቸውን ማሳየቱን የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ገለጸ።
ጥናቱ በከተማዋ 11 ክፍለ ከተሞች የተካሄደ ሲሆን፣ ከተስተዋሉት ችግሮች መካከል ወተት ላይ ከፍተኛ ውሃ መጨመር፣ ከእንስሳት ህክምና በኋላ የመድኃኒት ቅሪት ሳይጠፋ ወተት መለብ፣ የመኖ አያያዝ ችግሮች እና ለምግብ ተስማሚ ባልሆኑ መሳሪያዎች ወተት መለብና ማጓጓዝ ተጠቅሰዋል።
ኮሚሽኑ እንደገለጸው፣ ህብረተሰቡ ወተት እንዳይረጋ ኬሚካል እንደሚጨመርበት የሚያቀርባቸው ጥቆማዎች ቢኖሩም፣ ጥናቱ በተጨባጭ ያረጋገጠው ይህንን አይደለም። በቀጣይ ጥናት ሊጣራ የሚገባ ጉዳይ መሆኑ ተገልጿል።
በተመሳሳይ፣ ጥናቱ ወተት ላይ ካንሰር አምጪ ንጥረ ነገር መገኘቱን አላረጋገጠም። ይልቁንም አሁን ያለው የወተት አያያዝ ከሚፈለገው ደረጃ በታች በመሆኑ ጥንቃቄና ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ አመልክቷል።
ለምግብ ተስማሚ ያልሆኑ የወተት ማለቢያና ማጓጓዣ መሳሪያዎች፣ የመድኃኒት ቅሪት እና የመኖ አያያዝ ክፍተቶች በተለይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውን ጥናቱ አሳይቷል።

📅 መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም.
ሰበር መረጃ❗
የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ ክልል ይበልጥ ጠልቆ በመግባት ከመቀሌ ቀጥላ ክልሉ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ የሆነችውን አዲግራትን መቆጣጠሩን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራን ድርጊት "ወረራ" ሲል በይፋ ኮነነ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ለብሉምበርግ የዜና አውታር እንደተናገሩት፣ "በትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱት የኤርትራ ኃይሎች ያለምንም የጊዜ ገደብ ከኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ለቀው መውጣት አለባቸው" በማለት የመንግስትን ጥብቅ አቋም አንጸባርቀዋል። ምንም እንኳን የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ መኖሩ ከዚህ ቀደም በከፍተኛ የፖለቲካ እና የወታደራዊ መኮንኖች ሲነገር ቢቆይም፣ የሚኒስትሯ የዛሬው መግለጫ ግን ኤርትራ ጦሯን በቀጥታ በማስገባት ሉዓላዊ አገር መውረሯን የሚያረጋግጥ "ይፋዊ የመንግስት ማረጋገጫ" ሆኖ ተመዝግቧል።
❤1
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር‼️
የኢትዮጵያ መንግስት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እስከ ከፍተኛ ወታደራዊ እና የፖለቲካ ባለስልጣናት ድረስ - "የባህር በር ሉዓላዊ መዳረሻ" የሚለውን ለማግኘት በኤርትራ ላይ ግልጽ ጦርነት እንደሚጀምር በግልጽ ሲናገር ቆይቷል ብለዋል።
በሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍል በተነሳው ጦርነት ምክንያት በማድረግ ከፍተኛ ጄኔራሎች "... ጥቃቱን ስንጀምር በትግራይ አናቆምም፣ሌላኛው ጄኔራል ደግሞ "መቀሌ የሚቆም አይደለም የመጨረሻው መድረሻችን አሰብ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል ብለዋል።
ይህ ሂደት አለምአቀፍ ህግን በግልጽ ይጥሳል ያሉ ሲሆን የኤርትራ ሰራዊት በዛሬው ዕለት ወደ ትግራይ መግባቱን በተመለከተ ግን ያሉት ነገር የለም።
ተሽከርካሪዎቹ ከ40 በላይ ይሆናሉ-ነዋሪዎቹ‼️
በዛሬው ዕለት ፋፂ ከሚባል ቦታ ወደ አዲግራት የገቡ የኤርትራ ወታደሮችን በተመለከተ የከተማወ ነዋሪዎች 'ወታደሮቹን ጭነው የገቡት የጭነት መኪኖች "በግምት ከ40 በላይ" እንደሚሆኑ እና በእግርም ሲጓዙ የነበሩት "ብዙ" መሆናቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል።
Update‼️
የፌዴራል መንግሥቱ ኤርትራ በአዲግራት በኩል ያስገባውን ሰራዊት በአስቸኳይ እንዲያስወጣ ማስጠንቀቁን ተከትሎ ኤርትራ ሰራዊቷን ወደ ዛላምበሳ እየመለሰች መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል። የድሮን ጥቃቱ ከባድ ጉዳት አድርሷል ብለዋል።
በኤርትራ ወታደሮች ላይ  የድሮን ጥቃት መፈጸሙ ተነገረ

የኤርትራ ወታደሮች ከዛላምበሳ አቅጣጫ አዲግራትን ጥሰው በመግባት ወደ ዕዳጋ ሐሙስ እና አፅቢ ማምራታቸው ተሰማ። የትግራይ የሰላም ኃይል አንድ ወታደራዊ አዛዥ ለዶይቼ ቬለ እንደገለጹት፣ እነዚህ ወታደሮች በሁለት የጭነት መኪኖች ተጭነው ወደ አፅቢ ወንበርታ ሲጓዙ ዕዳጋ ዓርቢ በሚባል አካባቢ የድሮን ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።

በተጨማሪም በምዕራብ ትግራይ በሸራሮና ሽረ መካከል በሚገኙ አካባቢዎች የኤርትራ ወታደሮች መግባታቸው ተነግሯል። ይሁን እንጂ ዶይቼ ቬለ የድሮን ጥቃቱን በገለልተኝነት ማረጋገጥ እንዳልቻለ የገለጸ ሲሆን፣ በጉዳዩ ላይ የመንግሥት እና የኤርትራ ባለሥልጣናት ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፖለቲካን በሚገባ የተረዳ፣ ዛሬን ተንትኖ ነገን ቀድሞ ለማንበብ የሚሞክር፣ አንደበተ ርቱዕና ጥልቅ ሐሳብ ያለው ወጣት—ሰለሞን መንግስት።

ቃላቱ ከአፉ ብቻ አይወጡም፤ ከሐሳብና ከትንታኔ ይመነጫሉ። የዛሬን ክስተት ከትናንት ጋር አገናኝቶ፣ የነገን አቅጣጫ ለማሳየት የሚጥር አስተዋይ ወጣት።

ሰለሞን መንግስት—ሐሳብን በቃል፣ እውነታን በትንታኔ የሚያቀርብ ድንቅ ወጣት።
❤1
አሜሪካ በኢትዮጵያ ሊኖሩ ስለሚችሉ የረጅም ርቀት ጥቃቶች ማስጠንቀቂያ ሰጠች
የአሜሪካ ኤምባሲ በአዲስ አበባ በጥቅምት ወር በኢትዮጵያ ወታደራዊ ተቋማት ላይ ሊፈጸሙ ስለሚችሉ የረጅም ርቀት ጥቃቶች ሪፖርቶች እንደደረሱት ገልጿል።
ኤምባሲው በጥቅምት 7 ባወጣው የደህንነት ማስጠንቀቂያ፣ የአሜሪካ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ፣ የአካባቢ ባለሥልጣናትን መመሪያ እንዲከተሉ እና የሁኔታውን ለውጥ በቅርበት እንዲከታተሉ አሳስቧል።
በተጨማሪም ኤምባሲው የአሜሪካ ዜጎች ወደ አማራ ክልል፣ ላሊበላን ጨምሮ፣ ወደ ትግራይ እና ወደ ዓፋር ክልል ለማንኛውም ጉዳይ እንዳይጓዙ መክሯል። በእነዚህ አካባቢዎች ያሉ ዜጎችም ደህንነታቸው ከፈቀደ አካባቢዎቹን እንዲለቁ፣ ካልሆነ ደግሞ ሁኔታው እስኪሻሻል ድረስ ባሉበት እንዲጠለሉ አሳስቧል።
አስፈላጊው ነጥብ ግን፣ የአሜሪካ ኤምባሲ ጥቃቱ በተወሰነ ቦታ፣ በተወሰነ ጊዜ ወይም በየትኛው አካል እንደሚፈጸም ዝርዝር አልሰጠም። ስለዚህ ማስጠንቀቂያው ቀጣይ ጥቃት እንደሚፈጸም የተረጋገጠ መረጃ ሳይሆን፣ ኤምባሲው የደረሱትን የደህንነት ሪፖርቶች በመመርኮዝ የሰጠው ጥንቃቄ ማሳሰቢያ ነው።
አዲስ ኢንሳይት — መረጃን ከወሬ ለይተን፣ እውነታውን እንከታተላለን።
አሜሪካ–ኢራን አዲስ ውጥረት‼️
ፔንታጎን ለኢራን ሊደረግ ለሚችል አዲስ ወታደራዊ ዘመቻ እንዲዘጋጅ ታዘዘ
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ አዲስ ሰፊ ወታደራዊ ጥቃት ለመጀመር የመጨረሻ ውሳኔ እንዳላሳለፉ ቢነገርም፣ የአሜሪካ ፔንታጎን ለሚደረግ ሊሆን የሚችል አዲስ የወታደራዊ ዘመቻ ዝግጅቱን እንዲያጠናቅቅ ለዩኤስ ሴንትራል ኮማንድ (CENTCOM) መመሪያ መሰጠቱን አክሲዮስ ዘግቧል።
የአሜሪካና የእስራኤል ባለሥልጣናት ለአክሲዮስ እንደገለጹት፣ የእርምጃው ትክክለኛ ቀን አልተወሰነም። ሆኖም አዲስ የወታደራዊ እርምጃ ከተወሰደ በኢራን የኃይል ማመንጫዎች፣ የመሠረተ ልማት ተቋማት እና ከኑክሌር ፕሮግራሟ ጋር ተያያዥ ዒላማዎች ላይ ሰፊ የአየር ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል ምንጮቹ ጠቁመዋል።
ይህ የሚመጣው በዋሽንግተንና በቴህራን መካከል ያለው የዲፕሎማሲ ውይይት መቆሙ በተጠቀሰበት ወቅት ነው። የኳታር አማላጆችም ኢራን ለአሜሪካ የቀረበውን የኑክሌር ቅናሽ የሚጠይቀውን የተሻሻለ ሀሳብ እንድትመልስ እየጠበቁ መሆናቸው ተዘግቧል።
በተጨማሪም፣ የትራምፕ ከፍተኛ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪዎች በካምፕ ዴቪድ ለሰዓታት ተሰብስበው ስለ ኢራን ጦርነትና ስለ ቀጣይ የአሜሪካ ስትራቴጂ መወያየታቸው ተገልጿል። በስብሰባው ላይ ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት እና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተሳትፈዋል።
አክሲዮስ የጠቀሰው የአሜሪካና የእስራኤል ምንጮች እንደሚሉት፣ አዲሱ የወታደራዊ እርምጃ ከኖቬምበር 3 የአሜሪካ አጋማሽ ዘመን ምርጫ በፊት ሊከሰት ይችላል፤ ነገር ግን ይህ እርግጠኛ የሆነ የጥቃት ቀን አይደለም። አንድ የእስራኤል ባለሥልጣን የጥቃቱ ዕድል ከምርጫው በፊት ከፍተኛ እንዳልሆነ ገልጾ፣ ከምርጫው በኋላ ግን ዕድሉ በእጅጉ ሊጨምር እንደሚችል ተናግሯል።
በሌላ በኩል፣ ከፍተኛ የእስራኤል ባለሥልጣናት ከአሜሪካ ጋር በጋራ ወታደራዊ እርምጃ ከተጀመረ ኢራን በአጸፋው በርካታ የባሊስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል ልትተኩስ እንደምትችል ስጋታቸውን ገልጸዋል። ይህም ግጭቱ ከኢራንና እስራኤል ባለፈ ወደ ሰፊ የክልሉ ግጭት እንዳይስፋፋ የሚያሰጋ ሁኔታ ነው።
እስካሁን የተረጋገጠው፦ አሜሪካ ለሊሆን ለሚችል አዲስ የኢራን ጥቃት የወታደራዊ ዝግጅት እያጠናከረች ነው፤ ትራምፕ ግን ጥቃቱን ለመጀመር የመጨረሻ ውሳኔ እንዳላሳለፉ ሪፖርቶቹ ያመለክታሉ።
❤2
#ችሎት

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በማጽናት በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የኢህአፓ አባላት የዋስትና መብት እንዲከበር ብያኔ ሰጠ።

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የኢህአፓ አባላት የዋስትና ጉዳይ በዳኞች ፈረቃ መቀያየርና መዝገብ ባለመቅረቡ ምክንያት በተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሲሰጥበት መቆየቱ ይታወሳል።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት የዋስትና ውሳኔ ሊጸና ይገባል ወይስ አይገባም፤ እንዲሁም ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም የሚለውን ለመመርመር የፌደራል ፖሊስ ያደራጀውን የምርመራ መዝገብ አስቀርቦ ሲመለከት ቆይቷል።

ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት፣ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ አጽንቷል።

በዚህም መሠረት በሽብር ተግባር ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ይስሓቅ ወልዳይ፣ አቶ አበበ አካሉ እና ጠበቃ አቶ አበራ ንጉሥ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእስር እንዲፈቱ ብያኔ መሰጠቱን ጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት፣ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት፣ ፖሊስ የፎረንሲክ ውጤቶችን ለመጠበቅና ተጨማሪ ምስክሮችን ለመስማት በሚል የጠየቀውን የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ውድቅ በማድረግ ተጠርጣሪዎቹ እያንዳንዳቸው በ50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ውሳኔ መስጠቱ ይታወሳል።

የፌዴራል ፖሊስ የተሰጠውን የፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ማለቱን ተከትሎ ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸውን እስከዛሬ መስከረም 27/2019 ዓም ድረስ በእስር ላይ ሆነው ሲከታተሉ ቆይተዋል።

መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም