Addis Insight -አዲስ እይታ
3.26K subscribers
9.68K photos
379 videos
33 files
3.14K links
እርሶ ቻናላችንን Subscribe ሲያደርጉ ወቅታዊና ሁሉን አቀፍ መረጃዎችን ያገኛሉ።
Link👇
https://t.me/AddisInsight23
Download Telegram
የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ? ከራማ ወደ ኔቤሌት የተደረገው የጦር እንቅስቃሴ
አዲስ ኢንሳይት | መስከረም 24/2019
በትግራይ ክልል ከኤርትራ ጦር ጋር በተያያዘ አዲስ የጦር እንቅስቃሴ መኖሩን የሚገልጹ ሪፖርቶች ወጥተዋል።
ከአካባቢው የተገኙ ምንጮች እንደገለጹት፣ በሺህዎች የሚቆጠሩ የኤርትራ ወታደሮች ከራማ ወደ ኔቤሌት ታንኮቻቸውንና ከባድ መሳሪያዎቻቸውን ይዘው ገብተዋል ተብሏል።
በኔቤሌት ከተማ ውስጥ የሚገኙ ምንጮች እንደሚሉት፣ ሌሊቱን ሙሉ ከራማ፣ ዛላምበሳ፣ ሸራሮ እና ባድመ አቅጣጫዎች በርካታ የታጠቁ ተሽከርካሪዎችና ወታደሮች ወደ ከተማዋ ገብተዋል።
በተጨማሪም፣ በአዲግራት አቅጣጫ በፊያኮሺ አካባቢ በርካታ ወታደሮች ሰፍረው እንደነበር የሚገልጹ ሪፖርቶች መውጣታቸው ተገልጿል።
ምንጭ፦ ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎች
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሲከፋው እንኳን ሰው፣ ውሻም ያለቅሳል።
እንስሳት ምንም እንኳን እንደ ሰው በቃላት ስሜታቸውን መግለጽ ባይችሉም፣ ደስታን፣ ፍርሃትን፣ ብቸኝነትን እና ህመምን ይሰማሉ።
የሚያለቅስ ውሻ ስናይ፣ “እንስሳ ነው” ብለን ማለፍ ቀላል ነው።
ግን ከዚያ እንባ ጀርባ ህመም ሊኖር ይችላል፤ ከዝምታው ጀርባም ልመና።
ስሜት የሰው ልጅ ብቻ አይደለም።
እነሱ መናገር አይችሉም እንጂ፣ መሰማት ግን ይችላሉ።
የአራቱ መሪዎች ስምምነት‼️
ግብፅ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ሶማሊያ በአባይ ወንዝ፣ በቀይ ባህር ደህንነት እና በሀገራት ሉዓላዊነት ዙሪያ የጋራ አቋም የያዙበትን «የአላሜይን መግለጫ»(Alamein declaration) በጋራ ፈረሙ።

በግብፅ አስተናጋጅነት በተካሄደው የዚህ መሪዎች ጉባኤ ላይ የተላለፉ ዋና ዋና ውሳኔዎች፡-
🌊 የአባይ ወንዝ እና የውሃ መብት፦
የታችኞቹ የአባይ ተፋሰስ ሀገራት (ግብፅ እና ሱዳን) የውሃ ድርሻን የሚነካ ማንኛውንም «በአንድ ወገን ብቻ የሚወሰድ እርምጃ» በጽኑ እንደሚቃወሙ አስታውቀዋል።
ማንኛውም ውሳኔ በቅድመ ስምምነትና ምክክር መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።

🚢 የቀይ ባህር አስተዳደር፦
የቀይ ባህር እና የኤደን ባህረ ሰላጤ ደህንነት ጉዳይ ባህሩን በሚያዋስኑ ሀገራት (littoral states) ብቻ (ኢትዮጵያ አይመለከታትም) የሚወሰን ብቸኛ ኃላፊነት መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

🇸🇴 የሶማሊያ ሉዓላዊነት፦
የሶማሊያን አንድነት እና ግዛት ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፉ ገልጸው፤ ራሷን የገለለችውን «ሶማሊላንድን» እውቅና መስጠትንም ሆነ መደገፍን ፈጽሞ እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል።

🇸🇩 የሱዳን አንድነት፦
ለሱዳን ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ተቋማት ያላቸውን ድጋፍ ያረጋገጡ ሲሆን፤ ከሕጋዊው መንግሥት ውጭ የሚንቀሳቀሱ ማናቸውንም አካላት እንደሚቃወሙ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ምላሽ ሰጠች❗❗
ኢትዮጵያ በዓባይ እና በቀይ ባሕር ላይ ያላትን ቁርጠኛ አቋም አስታወቀች❗❗
ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም እና በቀይ ባሕር ቀጣና ያላትን ታሪካዊ፣ ጂኦግራፊያዊ እና ህጋዊ አቋሞች በተመለከተ ጠንካራ መልእክት አስተላልፏል።

1.ኢትዮጵያ የዓባይ (ብሉ ናይል) ወንዝ ዋነኛ ምንጭ እንደሆነችና ከጠቅላላው የናይል ወንዝ ውኃ 85 በመቶ የሚሆነውን እንደምታበረክት ሚኒስቴሩ ገልጿል። ስለ ወንዙ አጠቃቀምና አስተዳደር የሚደረጉ ማናቸውም ውይይቶች ይህንን መሠረታዊና ተፈጥሮአዊ እውነታ ያገናዘቡ መሆን እንዳለባቸው በጥብቅ አሳስቧል።

2. በታሪክም ሆነ በጂኦግራፊ አቀማመጥ ኢትዮጵያ ከቀይ ባሕር ጋር የጠበቀ ቁርኝት እንዳላት ያመላከተው መግለጫው፤ የፖለቲካ ድንበሮች በጊዜ ሂደት ቢቀያየሩም የአገሪቱ ወሰን ከባሕሩ ዳርቻ በ30 ማይልስ ያህል ርቀት ላይ ብቻ እንደሚገኝ አስታውሷል። በመሆኑም በማንኛውም ቀጣናዊ የባሕር affairs እና የደኅንነት መዋቅር ውይይት ውስጥ የኢትዮጵያ ህጋዊ ፍላጎቶችና ዘላቂ ቁርኝት ግምት ውስጥ መግባት አለባቸው ተብሏል።

3.እነዚህ ጂኦግራፊያዊ እና ታሪካዊ እውነታዎች በፖለቲካዊ ውዥንብሮች፣ በኃይል እርምጃዎች ወይም በወኪሎች (proxies) በኩል በሚደረጉ የትነኮሳ ድርጊቶች ሊቀየሩ አይችሉም ሲል ሚኒስቴሩ ገልጿል። በማንኛውም አካል የሚደረግ የጎንዮሽ ተጽዕኖ በመሬት ላይ ያለውን እውነታና የኢትዮጵያን አገራዊ ፍላጎቶች፣ ሚና እና ሃላፊነት ሊቀንስ እንደማይችል አረጋግጧል።

4. ኢትዮጵያ ሁልጊዜም ቢሆን ሰላማዊ ውይይትን፣ እርስ በእርስ መከባበርንና ቀጣናዊ ትብብርን እንደምትከተል የገለጸው መግለጫው፤ አገሪቱ ሉዓላዊነቷን፣ ግዛታዊ አንድነቷን እና መሠረታዊ አገራዊ ጥቅሞቿን ለመከላከል ሙሉ ዝግጁ መሆኗን አስታውቋል። በመጨረሻም ሁሉም ቀጣናዊ አካላት ተግዳሮቶችን በጋራ ውይይት፣ በባለቤትነት እና በበጎ ጎረቤትነት መርሆች ለመፍታት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርቧል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
የፍትህ ድምፅ!

የህዝብ ወገንተኝነትን በቃል ብቻ ሳይሆን በአቋምና በተግባር የሚያረጋግጡ፣ የተገፉትን ድምፅ በድፍረት የሚያሰሙ፣ የተበደሉትን ጉዳይ የሚያነሱ፣ በፍትህ ፊት ለማንም የማይንበረከኩ የሀገር ልጅ፤ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ!

እውነትን ለመናገር ድፍረት፣ ለተገፉት መቆም ልበ-ሙሉነት፣ ለፍትህ መታገል ጽናት—እነዚህ ሁሉ የዶ/ር ደሳለኝ መገለጫዎች ናቸው።

እስኪ እናንተ ምን ትላላችሁ ?
❤5
ሰበር መረጃ‼️
አቶ አህመድ ሺዴ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተመረጡ።
አቶ አህመድ ሺዴ የገንዘብ ሚኒስቴር በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
መሰረት ሚዲያ
❤1
ፌዴሬሽን ምክር ቤት‼️
ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ደስታ ሌዳሞ ምክትል አፈ-ጉባኤ ኾነዋል።
🚨 FACT CHECK | የህወሓት አመራሮችን በተመለከተ
በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስለ አንዳንድ የህወሓት አመራሮች ሞት፣ መጎዳትና እጅ መስጠት የሚገልጹ ወሬዎች ተሰራጭተዋል።
ከእነዚህም፦
1️⃣ ጆን ወልደጊዮርጊስ (ሜዲድ) — ጉዳት ደርሶበታል የሚለው መረጃ።

2️⃣ ገብረ ቲንሳኢ ብርሃኔ — በራያ ግንባር ሞቷል የሚለው ወሬ።

3️⃣ አለም ገብረዋህድ — እጅ ሰጥቷል የሚለው መረጃ።

4️⃣ አማኑኤል አሰፋ — እጅ ሰጥቷል የሚለው ወሬ።
🔎 አዲስ ኢንሳይት ባደረገው የመረጃ ፍተሻ፣ እነዚህን ዘገባዎች የሚያረጋግጥ በቂና ገለልተኛ የታመነ ምንጭ አልተገኘም። ስለዚህ ወሬዎቹን እንደ እውነት ማሰራጨት ተገቢ አይደለም።
በተለይ በጦርነትና በፖለቲካ ዙሪያ ያልተረጋገጡ መረጃዎች በፍጥነት ሊሰራጩ ይችላሉ። በቅርቡም አንድ የTPLF አዛዥ እጅ እንዲሰጡ ጥሪ ተደርጓል ተብሎ የተሰራጨ ቪዲዮ በAI የተመረተ ሐሰተኛ ቪዲዮ መሆኑ ተገልጿል።
📌 “ተባለ” ማለት “እውነት ነው” ማለት አይደለም።
ከታመነ ምንጭ እስኪረጋገጥ ድረስ ያልተረጋገጠ መረጃን ከማሰራጨት ይቆጠቡ።
አዲስ ኢንሳይት — ዓለምን በአዲስ እይታ
"ሰላዮችና ተባባሪዎቻቸው የሞት ቅጣት ይጠብቃቸዋል"-ትራኦሬ

የቡርኪና ፋሶ መሪ ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ፣ በሀገሪቱ ላይ የስለላ ወይም ክህደት ተግባር የሚፈጽሙ ሰዎች ከተያዙ ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስጠንቅቀዋል።
ትራኦሬ ይህን የተናገሩት የአገሪቱን አራተኛ ዓመት የሥልጣን ዘመን በሚያስመለክቱ ዝግጅቶች ዋዜማ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ሰፊ ቃለ-መጠይቅ ነው።
የቡርኪና ፋሶው መሪ በተለይ የውጭ ሰላዮችንና ከእነሱ ጋር የሚተባበሩ የአገር ውስጥ ሰዎችን በተመለከተ ጠንካራ ቃል ተጠቅመዋል። እንደ ትራኦሬ ገለጻ፣ አንድ ሰላይ እንደገና ተይዞ ከተረጋገጠ የሞት ቅጣት እንደሚተገበርበት፣ ተባባሪዎቹም ከዚህ ቅጣት እንደማያመልጡ አስጠንቅቀዋል።
ትራኦሬ አክለውም አንዳንድ የውጭ አገራት የስለላ ተግባራቸውን በዲፕሎማሲያዊ ተወካይነት ሽፋን ሊያካሂዱ እንደሚችሉ ተናግረዋል። መሪው የውጭ ጣልቃ ገብነትን በተመለከተም ሀገሪቱ የራሷን “ጠላቶች” መለየትና ለማንኛውም ስጋት መዘጋጀት እንዳለባት ገልጸዋል።
ይህ አቋም የሚመጣው ቡርኪና ፋሶ ከፈረንሳይ ጋር የነበራትን የዲፕሎማሲ ግንኙነት ሰኔ 26፣ 2026 በይፋ ካቋረጠች በኋላ ነው። የቡርኪና ፋሶ መንግሥት ፈረንሳይን “በሀገሪቱ ጥቅም ላይ የሚቃረን ተግባር” እና “ኒዮ-ኮሎኒያሊስት ዓላማዎች” እንዳሏት በመክሰስ ግንኙነቱን አቋርጣለች።

የሞት ቅጣት ጉዳይስ?

ቡርኪና ፋሶ በ2018 የሞት ቅጣትን አስወግዳ ነበር። በታህሳስ 2025 ግን የትራኦሬ መንግሥት የሞት ቅጣትን ለከፍተኛ ክህደት፣ ሽብርተኝነትና ስለላ ወንጀሎች ለመመለስ የሚያስችል የወንጀል ሕግ ረቂቅ አጽድቆ ለሕግ አውጪው አካል ልኳል።
ነገር ግን ይህ ረቂቅ ሕግ እስከ መስከረም 2026 ድረስ አሁንም በሕግ አውጪው አካል እየተመረመረ ነው። የሕግ አውጪው ኮሚቴዎችም የሞት ቅጣትን አፈጻጸም ጨምሮ በረቂቁ ላይ ውይይት እያደረጉ መሆኑን የፓርላማው ይፋዊ መረጃ ያሳያል።
ስለዚህ የትራኦሬ የቅርብ ጊዜ ማስጠንቀቂያ እውነት ቢሆንም፣ የሞት ቅጣቱ በሕግ ተግባራዊ ሆኖ ተጀምሯል ማለት ግን በአሁኑ ደረጃ ትክክል አይደለም። ጉዳዩ አሁንም በሕግ አውጪ ሂደት ላይ ነው።
👍2❤1
«ጌታቸው ረዳ ወደ መቐለ ተመለሱ‼️
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የቀድሞ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ መቐለ ከተማ ከህወሓት ታጣቂዎች ነፃ መውጣቷን ተከትሎ ወደ ከተማዋ መመለሳቸውን ሮይተርስ ዘገበ።

🔹 ዋና ዋና ነጥቦች፦
ወደ መቐለ መመለስ፦ የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ወደ ክልሉ መዲና መቐለ መድረሳቸውን የአለም አቀፉ የዜና ተቋም ሮይተርስ አረጋግጧል።

አካባቢያዊ ሁኔታ፦ አቶ ጌታቸው ረዳ ወደ ከተማዋ የተመለሱት መቐለ ከህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ነፃ መውጣቷን ተከትሎ መሆኑ ተመላክቷል።

ወቅታዊ ሁኔታ፦ የአካባቢውን ሰላምና ወታደራዊ ሁኔታ በተመለከተ አዳዲስ መረጃዎች እየወጡ እንደሚገኙ ተገልጿል።
❤3
ውቅሮ ከባድ ውጊያ ሲደረግ አድሯል‼️
ከመቀሌ-ሐውዜን-አዲግራት መስመር በምትገኘው ውቅሮ መውጫ ልዩ ስሙ እንዳ አብርሀ ወ አጽብሀ ኣካባቢ ትናንት መስከረም 25 ለሊቱን የከባድ መሳርያ ድምጽ ሲሰማ ማደሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
መከላከያ ወደ ውቅሮ ከተማ ባይገባም በውቅሮ ከተማ የነበሩ የህወሓት ታጣቂዎች ከተማዋን ለቀው ወጥተዋል ብለዋል።
ትግራይ ክልል አሁናዊ መረጃ‼️
ከመቀሌ በሁለት አቅጣጫ ውጊያው ቀጥሏል።
📌ከመቀሌ-ሀገረ ሰላም-አብዪ አዲ-አድዋ መስመር ውጊያው የቀጠለ ሲሆን መከላከያ ሰራዊት ሀገረ ሰላምን በዛሬው ዕለት መስከረም 26 መቆጣጠሩ ታውቋል።
📌ከመቀሌ-ውቅሮ-ነጋሽ-ደጋ ሐሙስ-አዲግራት መስመር ውጊያው የቀጠለ ሲሆን ውቅሮ የነበሩ የህወሓት ታጣቂዎች ከተማዋን ለቀው ወጥተዋል።
📌በማይፀብሪ-እንዳባጉና-ሽሬ መስመር ያለው ውጊያ መከላከያ ሰራዊት እንዳ ባጉናን ተቆጣጥሮ ባለበት ቆሟል።
📌በአዲግራት ከለሊቱ 7:30 ልዩ ስሙ ዋላኹ በተባለ ቦታ የድሮን ጥቃት ተፈፅሟል፣ የደረሰውን ጉዳት ማወቅ አልተቻለም።