Addis Insight -አዲስ እይታ
3.26K subscribers
9.68K photos
379 videos
33 files
3.14K links
እርሶ ቻናላችንን Subscribe ሲያደርጉ ወቅታዊና ሁሉን አቀፍ መረጃዎችን ያገኛሉ።
Link👇
https://t.me/AddisInsight23
Download Telegram
በማህበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ ያለ የኢትዮጵያዊያን አንድነት ፍቅር መተሳሰብ አሁንም እንዳለ የሚያሳይ ምስል።

ክስተቱ የተካሄደበት ቦታ ደቡብ ወሎ ደሴ ከተማ ውስጥ ሲሆን  ሁለት ሙስሊሞች ጸሎት በሚያደርጉበት ወቅት ዝናብ መዝነብ ይጀምራል ሌላኛው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ወጣት ዝናብ እንዳይመታቸው ጥላ ሲዘረጋላቸው ይታያል።
👎1
ሰበር❗

ኤርትራ ፀረ ድሮን መትከሏ ታወቀ

ኤርትራ በአክሱም እና አድዋ አካባቢ ፀረ ድሮን መትከሉ ታወቀ።ከዚህ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የመካናይዝድ ጦሩን በከፍተኛ ሁኔታ እያስጠጋ ይገኛል።

አሜሪካ ዛሬ ባወጣችው አስቸኳይ መግለጫ በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ የሚደረግ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲቆም እና ሁሉቱ ሀገራት በሰከነ መንገድ ጉዳዩን እንዲመለከቱ ጥሪ አቅርባለች።
❤1
ኢሳይያስ ለተጨማሪ ቀናት ካይሮ ይቆያሉ‼️
የግብፅ ፕሬዚዳንት አብድልፈታህ አልሲሲ ፣ የኤርትራዉ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ፣ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ እና የሱዳኑ የጦር ሀይል መሪ አል ቡርሃን በአንድ መድረክ የሚያደርጉት ስብሰባ በዛሬው እለት የሚጠናቀቅ ሲሆን ኢሳይያስ አፈወርቂ ለተጨማሪ ቀናት ካይሮ ይቆያሉ ተብሏል።
❤1
ኢራን አሜሪካ መስፈርቶቿን እስክትሟላ ድረስ የሆርሙዝ መስመር  ተዘግቶ እንደሚቆይ ገለጸች
 
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የባህር መስመሩን  መልሶ መክፈት ዋነኛ ግቡ እንደሆነ ሲናገር፣ አሜሪካ በበኩሏ ትኩረቷን በኒውክሌር ድርድሩ ላይ ማድረጓን ቀጥላለች።
 
የኢራን የፓርላማ አፈ-ጉባኤ ሞሐመድ ባገር ቃሊባፍ እንደተናገሩት፣ አሜሪካ የቴህራንን የሰባት ቀን ዕቅድ እስካልተቀበለች ድረስ የሆርሙዝ መስመር ተዘግቶ ይቆያል። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በበኩላቸው፣ ቴህራን ወታደራዊ ዝግጁነቷን እንደጠበቀች በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፍትሔ ለማግኘት እየሰራች መሆኑን አረጋግጠዋል፤ አሜሪካ ተጨማሪ እርምጃ የምትወስድ ከሆነ ግን ከቀድሞው በላይ "የበለጠ ዝግጁ" መሆኗን አስረድተዋል።
 
በየካቲት ወር አሜሪካና እስራኤል በኢራን ላይ ያካሄዱትን ጥቃት ተከተሎ፣ ከዓለም አቀፉ የነዳጅ አቅርቦት አንድ አምስተኛው የሚጓጓዝበት ይህ የባህር ወስጥ ከሰባት ወራት በላይ መደበኛ እንቅስቃሴው ተስተጉሏል። በአሁኑ ወቅት ሁለቱ ወገኖች የባህር መስመሩን መክፈት ቅድሚያ ይሰጥ ወይስ የኒውክሌር ድርድሩ በሚለው ነጥብ ላይ አለመግባባት ውስጥ ይገኛሉ ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።
 
የኢራን ዋና ተደራዳሪና የፓርላማ አፈ-ጉባኤ እንደተናገሩት፣ አሜሪካ የውሃ መንገዱን መልሶ ለመክፈት የቀረበውን የቴህራንን የሰባት ቀን ዕቅድ እስክትቀበል ድረስ የሆርሙዝ መስመር እንደተዘጋ ይቆያል።
 
ከኢራን መንግሥት ጋር ቁርኝት ያለው የኑርኒውስ (Nournews) የዜና ወኪል ሞሐመድ ባገር ቃሊባፍን ጠቅሶ እሁድ እንደዘገበው፣ አሜሪካ ለኢራን ዲፕሎማሲያዊ ጥያቄ ምላሽ ከሰጠች ከጥቂት ቀናት በኋላ በአደራዳሪዎች  በኩል "አንዳንድ የውሳኔ ሃሳቦችን" አቅርባለች።

 
❤3
የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ? ከራማ ወደ ኔቤሌት የተደረገው የጦር እንቅስቃሴ
አዲስ ኢንሳይት | መስከረም 24/2019
በትግራይ ክልል ከኤርትራ ጦር ጋር በተያያዘ አዲስ የጦር እንቅስቃሴ መኖሩን የሚገልጹ ሪፖርቶች ወጥተዋል።
ከአካባቢው የተገኙ ምንጮች እንደገለጹት፣ በሺህዎች የሚቆጠሩ የኤርትራ ወታደሮች ከራማ ወደ ኔቤሌት ታንኮቻቸውንና ከባድ መሳሪያዎቻቸውን ይዘው ገብተዋል ተብሏል።
በኔቤሌት ከተማ ውስጥ የሚገኙ ምንጮች እንደሚሉት፣ ሌሊቱን ሙሉ ከራማ፣ ዛላምበሳ፣ ሸራሮ እና ባድመ አቅጣጫዎች በርካታ የታጠቁ ተሽከርካሪዎችና ወታደሮች ወደ ከተማዋ ገብተዋል።
በተጨማሪም፣ በአዲግራት አቅጣጫ በፊያኮሺ አካባቢ በርካታ ወታደሮች ሰፍረው እንደነበር የሚገልጹ ሪፖርቶች መውጣታቸው ተገልጿል።
ምንጭ፦ ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎች
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሲከፋው እንኳን ሰው፣ ውሻም ያለቅሳል።
እንስሳት ምንም እንኳን እንደ ሰው በቃላት ስሜታቸውን መግለጽ ባይችሉም፣ ደስታን፣ ፍርሃትን፣ ብቸኝነትን እና ህመምን ይሰማሉ።
የሚያለቅስ ውሻ ስናይ፣ “እንስሳ ነው” ብለን ማለፍ ቀላል ነው።
ግን ከዚያ እንባ ጀርባ ህመም ሊኖር ይችላል፤ ከዝምታው ጀርባም ልመና።
ስሜት የሰው ልጅ ብቻ አይደለም።
እነሱ መናገር አይችሉም እንጂ፣ መሰማት ግን ይችላሉ።
የአራቱ መሪዎች ስምምነት‼️
ግብፅ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ሶማሊያ በአባይ ወንዝ፣ በቀይ ባህር ደህንነት እና በሀገራት ሉዓላዊነት ዙሪያ የጋራ አቋም የያዙበትን «የአላሜይን መግለጫ»(Alamein declaration) በጋራ ፈረሙ።

በግብፅ አስተናጋጅነት በተካሄደው የዚህ መሪዎች ጉባኤ ላይ የተላለፉ ዋና ዋና ውሳኔዎች፡-
🌊 የአባይ ወንዝ እና የውሃ መብት፦
የታችኞቹ የአባይ ተፋሰስ ሀገራት (ግብፅ እና ሱዳን) የውሃ ድርሻን የሚነካ ማንኛውንም «በአንድ ወገን ብቻ የሚወሰድ እርምጃ» በጽኑ እንደሚቃወሙ አስታውቀዋል።
ማንኛውም ውሳኔ በቅድመ ስምምነትና ምክክር መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።

🚢 የቀይ ባህር አስተዳደር፦
የቀይ ባህር እና የኤደን ባህረ ሰላጤ ደህንነት ጉዳይ ባህሩን በሚያዋስኑ ሀገራት (littoral states) ብቻ (ኢትዮጵያ አይመለከታትም) የሚወሰን ብቸኛ ኃላፊነት መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

🇸🇴 የሶማሊያ ሉዓላዊነት፦
የሶማሊያን አንድነት እና ግዛት ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፉ ገልጸው፤ ራሷን የገለለችውን «ሶማሊላንድን» እውቅና መስጠትንም ሆነ መደገፍን ፈጽሞ እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል።

🇸🇩 የሱዳን አንድነት፦
ለሱዳን ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ተቋማት ያላቸውን ድጋፍ ያረጋገጡ ሲሆን፤ ከሕጋዊው መንግሥት ውጭ የሚንቀሳቀሱ ማናቸውንም አካላት እንደሚቃወሙ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ምላሽ ሰጠች❗❗
ኢትዮጵያ በዓባይ እና በቀይ ባሕር ላይ ያላትን ቁርጠኛ አቋም አስታወቀች❗❗
ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም እና በቀይ ባሕር ቀጣና ያላትን ታሪካዊ፣ ጂኦግራፊያዊ እና ህጋዊ አቋሞች በተመለከተ ጠንካራ መልእክት አስተላልፏል።

1.ኢትዮጵያ የዓባይ (ብሉ ናይል) ወንዝ ዋነኛ ምንጭ እንደሆነችና ከጠቅላላው የናይል ወንዝ ውኃ 85 በመቶ የሚሆነውን እንደምታበረክት ሚኒስቴሩ ገልጿል። ስለ ወንዙ አጠቃቀምና አስተዳደር የሚደረጉ ማናቸውም ውይይቶች ይህንን መሠረታዊና ተፈጥሮአዊ እውነታ ያገናዘቡ መሆን እንዳለባቸው በጥብቅ አሳስቧል።

2. በታሪክም ሆነ በጂኦግራፊ አቀማመጥ ኢትዮጵያ ከቀይ ባሕር ጋር የጠበቀ ቁርኝት እንዳላት ያመላከተው መግለጫው፤ የፖለቲካ ድንበሮች በጊዜ ሂደት ቢቀያየሩም የአገሪቱ ወሰን ከባሕሩ ዳርቻ በ30 ማይልስ ያህል ርቀት ላይ ብቻ እንደሚገኝ አስታውሷል። በመሆኑም በማንኛውም ቀጣናዊ የባሕር affairs እና የደኅንነት መዋቅር ውይይት ውስጥ የኢትዮጵያ ህጋዊ ፍላጎቶችና ዘላቂ ቁርኝት ግምት ውስጥ መግባት አለባቸው ተብሏል።

3.እነዚህ ጂኦግራፊያዊ እና ታሪካዊ እውነታዎች በፖለቲካዊ ውዥንብሮች፣ በኃይል እርምጃዎች ወይም በወኪሎች (proxies) በኩል በሚደረጉ የትነኮሳ ድርጊቶች ሊቀየሩ አይችሉም ሲል ሚኒስቴሩ ገልጿል። በማንኛውም አካል የሚደረግ የጎንዮሽ ተጽዕኖ በመሬት ላይ ያለውን እውነታና የኢትዮጵያን አገራዊ ፍላጎቶች፣ ሚና እና ሃላፊነት ሊቀንስ እንደማይችል አረጋግጧል።

4. ኢትዮጵያ ሁልጊዜም ቢሆን ሰላማዊ ውይይትን፣ እርስ በእርስ መከባበርንና ቀጣናዊ ትብብርን እንደምትከተል የገለጸው መግለጫው፤ አገሪቱ ሉዓላዊነቷን፣ ግዛታዊ አንድነቷን እና መሠረታዊ አገራዊ ጥቅሞቿን ለመከላከል ሙሉ ዝግጁ መሆኗን አስታውቋል። በመጨረሻም ሁሉም ቀጣናዊ አካላት ተግዳሮቶችን በጋራ ውይይት፣ በባለቤትነት እና በበጎ ጎረቤትነት መርሆች ለመፍታት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርቧል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
የፍትህ ድምፅ!

የህዝብ ወገንተኝነትን በቃል ብቻ ሳይሆን በአቋምና በተግባር የሚያረጋግጡ፣ የተገፉትን ድምፅ በድፍረት የሚያሰሙ፣ የተበደሉትን ጉዳይ የሚያነሱ፣ በፍትህ ፊት ለማንም የማይንበረከኩ የሀገር ልጅ፤ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ!

እውነትን ለመናገር ድፍረት፣ ለተገፉት መቆም ልበ-ሙሉነት፣ ለፍትህ መታገል ጽናት—እነዚህ ሁሉ የዶ/ር ደሳለኝ መገለጫዎች ናቸው።

እስኪ እናንተ ምን ትላላችሁ ?
❤5
ሰበር መረጃ‼️
አቶ አህመድ ሺዴ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተመረጡ።
አቶ አህመድ ሺዴ የገንዘብ ሚኒስቴር በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
መሰረት ሚዲያ
❤1
ፌዴሬሽን ምክር ቤት‼️
ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ደስታ ሌዳሞ ምክትል አፈ-ጉባኤ ኾነዋል።
🚨 FACT CHECK | የህወሓት አመራሮችን በተመለከተ
በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስለ አንዳንድ የህወሓት አመራሮች ሞት፣ መጎዳትና እጅ መስጠት የሚገልጹ ወሬዎች ተሰራጭተዋል።
ከእነዚህም፦
1️⃣ ጆን ወልደጊዮርጊስ (ሜዲድ) — ጉዳት ደርሶበታል የሚለው መረጃ።

2️⃣ ገብረ ቲንሳኢ ብርሃኔ — በራያ ግንባር ሞቷል የሚለው ወሬ።

3️⃣ አለም ገብረዋህድ — እጅ ሰጥቷል የሚለው መረጃ።

4️⃣ አማኑኤል አሰፋ — እጅ ሰጥቷል የሚለው ወሬ።
🔎 አዲስ ኢንሳይት ባደረገው የመረጃ ፍተሻ፣ እነዚህን ዘገባዎች የሚያረጋግጥ በቂና ገለልተኛ የታመነ ምንጭ አልተገኘም። ስለዚህ ወሬዎቹን እንደ እውነት ማሰራጨት ተገቢ አይደለም።
በተለይ በጦርነትና በፖለቲካ ዙሪያ ያልተረጋገጡ መረጃዎች በፍጥነት ሊሰራጩ ይችላሉ። በቅርቡም አንድ የTPLF አዛዥ እጅ እንዲሰጡ ጥሪ ተደርጓል ተብሎ የተሰራጨ ቪዲዮ በAI የተመረተ ሐሰተኛ ቪዲዮ መሆኑ ተገልጿል።
📌 “ተባለ” ማለት “እውነት ነው” ማለት አይደለም።
ከታመነ ምንጭ እስኪረጋገጥ ድረስ ያልተረጋገጠ መረጃን ከማሰራጨት ይቆጠቡ።
አዲስ ኢንሳይት — ዓለምን በአዲስ እይታ