Addis Insight -አዲስ እይታ
3.25K subscribers
9.7K photos
381 videos
33 files
3.15K links
እርሶ ቻናላችንን Subscribe ሲያደርጉ ወቅታዊና ሁሉን አቀፍ መረጃዎችን ያገኛሉ።
Link👇
https://t.me/AddisInsight23
Download Telegram
ሹመት‼️
የደሴ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ፤  ጃንጥራር አባይን በመተካት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ።
የአዲስ አበባ ካቢኔ አባላት

👉 አቶ ግርማ ሰይፉ የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ቤት በከንቲባ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት የከተማውን የካቢኔ አባላት ሹመት አፅድቋል።

በዚህም መሰረት፦

1. አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ - የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ
2. አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
3. አቶ ጥላሁን ከበደ - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
4. አቶ ሃፍታይ ገ/እግዚአብሔር - በም/ ከንቲባ ማዕረግ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
5. ዶ/ር አህመዲን መሃመድ - የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ
6. ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ - የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ
7. ኢንጂነር አያልነሽ ኃብተማሪያም - የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ
8. ወ/ሪት ፂዮን ደረጀ (የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል) - የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ
9. ኢንጂነር ህይወት ፀጋዬ - የግንባታ ቁጥጥርና ፈቃድ ቢሮ ኃላፊ
10. ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ - የቴክኒክና ሙያ ቢሮ ኃላፊ
11. ወ/ሮ ዚያዳ ካሚል - የአረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ
12. አቶ ግርማ ሰይፉ - የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ
13. አቶ ቢኒያም ምክሩ - ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
14. አቶ ሙሉቀን ታሪኩ - የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ
15. ወይዘሮ ሃቢባ ሲራጅ - የንግድ ቢሮ ኃላፊ
16. ዶ/ር ዮሃንስ ጫላ - የጤና ቢሮ ኃላፊ
17. ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ - የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
18. አቶ አወሌ መሃመድ ኡመር - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ
19. ዶ/ር ተፈራ ሞላ - የትራንስፖርት ቢሮ
20 ኢንጂነር አይሻ መሃመድ - የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር
21. ኢንጂነር ሔለን ገመዳ - የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ
22. ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ - የህፃናት ማህበራዊ ጉዳይና ሴቶች ቢሮ
23. አቶ ተስፋዬ ደጀኔ - የፍትህ ቢሮ ኃላፊ
24. አቶ አሰግደው ወልደጊዮርጊስ - የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
25. አቶ መላኩ ታምሩ - የመሬት ልማት ቢሮ ኃላፊ
ማራኪ የተፈጥሮ ስዕል! 🌄🌿
​ከተራሮች ግርማ ሞገስ ጋር የተዋሃደው ይህ የከተማችን ውበት፣ የሰላም እና የesthetic ስሜት የሚሰጥ እጅግ ድንቅ ዕይታ ነው። አረንጓዴ ለምለም የሆኑት ኮረብቶች፣ በረጋ መንፈስ የታቀፉት ሰፋፊ ሕንፃዎች እና ከበስተጀርባ የሚታየው የተፈጥሮ ገጽታ አዕምሮን የሚያሳርፍ ልዩ ማራኪነት አለው።
​ኢትዮጵያችን በበርካታ ውብ ስፍራዎች እና ተፈጥሮን ባከበሩ ውብ ከተሞች የተሞላች ታላቅ ሀገር ናት።
ለመሆኑ ይህ ከተማ ማነው?
❤1
🇧🇫 ቡርኪና ፋሶ የመጀመሪያዋን ብሔራዊ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ አስመረቀች

“ወርቃችንን እዚሁ እናጣራለን፤ እሴቱንም እዚሁ እንፈጥራለን።”

ቡርኪና ፋሶ የማዕድን ሀብቷን ከመሬት በማውጣት ብቻ ሳትቆም፣ በሀገር ውስጥ የመጨረሻ የእሴት ሰንሰለት ለመፍጠር አዲስ እርምጃ ወስዳለች።

በመስከረም 28፣ 2026 የሀገሪቱ መሪ ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ በዋና ከተማዋ ኦዋጋዱጉ የተገነባውን RAFFINOR-BF የተባለውን የቡርኪና ፋሶ የመጀመሪያ ብሔራዊ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ በይፋ አስመርቀዋል።

ፋብሪካው የወርቅ ዶሬን ወደ ከፍተኛ ንጽሕና ያለው የወርቅ ብሎን ለመቀየር የተዘጋጀ ሲሆን፣ በመጀመሪያው የሥራ ደረጃ በዓመት 164 ቶን ወርቅ ማጣራት የሚችል አቅም አለው። በቀጣይ የማስፋፊያ ደረጃ ይህ አቅም 515 ቶን በዓመት እንዲደርስ ታቅዷል።

ፕሮጀክቱ ከ11 ቢሊዮን CFA ፍራንክ በላይ የተወጣበት ሲሆን፣ በቡርኪና ፋሶ መንግሥት በSONASP እና በግል አጋሮች ተሳትፎ ተከናውኗል። ፋብሪካው በ5 ሄክታር መሬት ላይ የማቅለጫ ክፍል፣ የላቦራቶሪ ምርመራ ክፍል፣ የወርቅ ማከማቻ እና የጌጣጌጥ ክፍልን ያካትታል።

በምረቃው ላይ ትራኦሬ እንዳሉት፣ የሀገሪቱ ዓላማ ወርቅን በመሬቷ ላይ ማውጣት ብቻ ሳይሆን፣ ማጣራት፣ መቆጣጠር፣ ዋጋ መጨመር እና ማረጋገጥ በሀገር ውስጥ ማከናወን ነው። “ሁሉንም ብረቶቻችንን በሀገር ውስጥ ማጣራት እንፈልጋለን፤ ሙሉውን የእሴት ሰንሰለትም እዚሁ እንዲኖር እንፈልጋለን” ብለዋል።

ይህም ቡርኪና ፋሶ ከጥሬ ወርቅ ላኪ ሀገር በመሆን ወደ ወርቅን በሀገር ውስጥ የምታጣራና ተጨማሪ እሴት የምትፈጥር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር የምትከተለው ፖሊሲ አካል ነው።

አዲስ ኢንሳይት | ዓለምን በአዲስ እይታ 🌍
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኤርትራ ሰራዊት ውጊያ ከፍቶብናል-አወል አርባ‼️
በአፋር ክልል ኪልበቲ ረሱ የኤርትራ ሰራዊት ከህወሃት ሀይል ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ጥሶ ገብቶ በከባድ መሳሪያ ጭምር ጦርነት ከፍቶ ይገኛል ሲሉ የአፋር ክልል ርዕስ መስተዳደር ሀጂ አወል አርባ ከክልሉ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል። በዚህ የተነሳ በርካታ ሰዎች ተፈናቅለዋል ብለዋል።
በአዲስ አበባና አካባቢው ድሮን ማብረር ተከለከለ

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባወጣው ማሳሰቢያ ላልተወሰነ ጊዜ በአዲስ አበባ እና አካባቢው ማንኛውንም አይነት ድሮን የማብረር ፍቃድ እንደማይሰጥ አስታውቋል። ተቋሙ የመሪዎችን እና የቁልፍ መሠረተ-ልማቶችን ደኅንነት ለመጠበቅ ሲል በዘመናዊ የጸረ-ድሮን ቴክኖሎጂዎች ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጿል።

ይህን ትዕዛዝ ጥሶ በሚደረግ ማንኛውም የበረራ ሙከራ ላይ ድሮኖቹን በመጥለፍ፣ በማሳረፍ እና አብራሪዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተመላክቷል። ብሔራዊ ደኅንነትን ለመጠበቅ የተዘረጋውን ይህንን ሕግ ለማስፈጸም ተቋሙ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሙሉ ዝግጅት አድርጓል።
👎1
ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ! በልጅሽ በወዳጅሽ ፊት ዘወትር ስለ እኛ ለምኝልን፤ እናታዊ ምልጃሽ አይለየን! አሜን!🤲
👏10❤3
🐝🍯 ንብ ማርን ከአበባ እንደምትሰበስብ እናውቃለን… ግን የምትሰበስበው ማር ሳይሆን ሌላ ነገር ነው!
ንብ ከአበባ የምትሰበስበው “nectar” የሚባል ጣፋጭ ፈሳሽ ነው። ነገር ግን ይህን ፈሳሽ በተለመደው የምግብ ሆዷ ውስጥ አታከማችም።
🐝 ለዚህ የተለየ “Honey Stomach” ወይም “Crop” የሚባል የማከማቻ ክፍል አላት።
እዚያም ንብ የራሷን ኢንዛይሞች በመጠቀም nectar-ውን መለወጥ ትጀምራለች።
ከዚያስ? 🤔
ወደ ቀፎ ስትመለስ፣ nectar-ውን ከዚህ ልዩ የማከማቻ ሆድ ወደ አፏ በማምጣት ለሌሎች ንቦች ታስተላልፋለች። እነሱም የበለጠ ኢንዛይም ይጨምሩበታል።
💨 ከዚያ ንቦች በክንፎቻቸው አየር በማንቀሳቀስ ከnectar-ው ውስጥ ያለውን ብዙ ውሃ እንዲተን ያደርጋሉ።
🍯 በመጨረሻም የተለወጠውንና ውሃው የቀነሰውን ፈሳሽ በማር ማሰሮዎች ውስጥ ያከማቹታል፤ ማሩ ሲደርስም በሰም ይዘጉታል።
😮 እና እዚህ ላይ አስገራሚው ነገር ይመጣል!
“የማር ሆድ” ተብሎ የሚጠራው የንብ ክፍል እንደ መደበኛ ሆድ ምግብን ለመፍጨት የሚያገለግል አይደለም። ዋና ሥራው ንብ የሰበሰበችውን nectar ወደ ቀፎ በማጓጓዝ ላይ ነው።
እንግዲህ በአንድ ሐረግ፦
🌸 አበባ → 🐝 Nectar → 🐝 Honey stomach → 🏠 ቀፎ → 💨 ውሃ መትነን → 🍯 ማር
የምንበላው ማር በቀጥታ ከአበባ የተሰበሰበ ማር ሳይሆን፣ ንቦች የሚሰበስቡትን nectar በኢንዛይሞች እና በውሃ መትነን ሂደት የሚያዘጋጁት ምርት ነው።
አንዲት ትንሽ ንብ… እንዴት ያለ የተወሳሰበ ሥራ ትሠራለች! 🐝🍯
— አዲስ ኢንሳይት | ዓለምን በአዲስ እይታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፍጥረት ሁሉ የሚያመሰግንሽ እና የሚሰግድልሽ ቅድስት ሆይ አማልጂን ከልጂሽ ክርስቶስ ፤አይደለም የሰው ልጆች አዕዋፋትም የሚወዷት እናት ስላለችን ፈጣሪ ይመስገን።
❤9
🇺🇬🇪🇹 የኡጋንዳ ጦር አዛዥ፦ “ግጭቱ በአስቸኳይ ይቁም”
የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች (UPDF) ዋና አዛዥ ጄኔራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም በተቀሰቀሰው ግጭት ላይ መልዕክት አስተላለፉ።
ጄኔራሉ በX ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሠራዊት ድጋፋቸውን ገልጸው፣ እየተባባሰ ያለው የጦርነት እና የጠላትነት እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
በተጨማሪም ጄኔራል ሙሁዚ በ2022 በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተፈረመው የሰላም ስምምነት እንዲከበርና በተግባር እንዲተገበር ጥሪ አቅርበዋል።
ጄኔራሉ በመልዕክታቸው የኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት በሁሉም ወገኖች ሊከበርና ሊጠበቅ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ይህ መልዕክት የመጣው በሰሜን ኢትዮጵያ የጸጥታ ሁኔታ እንደገና በተናወጠበት ወቅት ሲሆን፣ የኡጋንዳ ወታደራዊ አዛዥ ለግጭቱ አስቸኳይ ማቆሚያ እና ለፕሪቶሪያ ስምምነት መከበር መጠየቃቸው ትኩረት ስቧል።
📌 ምንጭ፦ RadioTV10 — 30 September 2026
“Uganda’s Army Chief Gen. Muhoozi Supports the Ethiopian Army and Calls for an Immediate End to the War.”

ምንጭ-Radio TV 10
አዲስ ኢንሳይት
ዓለምን በአዲስ እይታ
❤1
#ችሎት

​በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የኢሕአፓ አባላት የዋስትና ጉዳይ ዛሬም ውሳኔ ሳያገኝ ለአርብ ተቀጠረ።

​የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት የሰጠው የዋስትና ውሳኔ ሊጸና ይገባል ወይስ አይገባም? እንዲሁም ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም? የሚሉትን ነጥቦች ለመመልከት የፌደራል ፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንዲቀርብለት ማዘዙ ይታወሳል።

​ይሁን እንጂ ሰኞ ዕለት በዋለው ችሎት "መዝገቡን እየተመለከትን ነው፣ አላጠቃለልንም" ያለው ፍርድ ቤቱ፤ በዛሬው ዕለት ደግሞ የስር ፍርድ ቤት ዋስትና የፈቀደበት ሰነድ (Hard Copy) እንዲቀርብለት በማዘዙ ምክንያት ብያኔ ሳይሰጥ ቀርቷል።

​በዚህም መሰረት ችሎቱ የሚቀርቡለትን ሰነዶች መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለመጪው አርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

​ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተጠርጣሪዎች አቶ ይስሓቅ ወልዳይ፣ አቶ አበበ አካሉ እና ጠበቃ አቶ አበራ ንጉሥ ሲሆኑ፤ የዋስትና አቤቱታቸው ቀደም ሲል በዳኞች ፈረቃ መቀያየር ምክንያት በተደጋጋሚ ሲራዘም መቆየቱ አይዘነጋም።

ተጠርጣሪዎች ፖሊስ ይግባኝ በማለቱ ምክንያት የዋስትና መብታቸው ሳይከበር 25 ቀናት በላይ በእስር ላይ ይገኛሉ።
አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ በድጋሚ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ።

የሶማሊ ክልል ምክር ቤት 7ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት የመጀመሪያ ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል።

በዚህም አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ኡመርን በድጋሚ የክልሉ ፕሬዝዳንት በማድረግ ሾሟል።

መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ/ም
ዶክተር መሳይ ኃይሉ የሲዳማ ክልል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ።
‎
‎የፌዴራል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ዶክተር መሳይ ኃይሉ የሲዳማ ክልል ፕሬዜዳንት ሆነው ተሹመዋል።
‎
‎የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዛሬ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ/ም የመንግስት ምስረታ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

በዚህም ዶ/ር መሳይ ኃይሉን የክልሉ ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾሟቸዋል።
‎
‎ዶክተር መሳይ ኃይሉ ሲዳማ ክልል በሪፈረንደም ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት የሆነው የተሾሙትን አቶ ደስታ ሌዳሞን ይተካሉ።

መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ/ም
‎
‎